tgindex
ዝክረ ቅዱሳን ማህበረ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጉባኤ ⁽ዘድሬዳዋ⁾

ዝክረ ቅዱሳን ማህበረ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጉባኤ ⁽ዘድሬዳዋ⁾

Статистика

⁽ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል⁾      ማ/ወ ፲:፵ 👉የሳምንቱን የዝክረ ቅዱሳን ታሪካቸውን የሚያዘክር ጉባኤ ➷የሚተላለፉ ትምህርቶች...➷ 📌 የየለቱን ዝክረ ቅዱሳን (ስንክሳር) 📌 ቃለ ወንጌል 📌 የበዓላት ትርጎሜ

Последний пост
31 окт. 2024 г.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
260
+2 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
295
22 постов
Вовлечённость
113,5%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 31 окт. 2024 г.64451из Finoteabewze

    ድንግል ማርያምን ማሰብ እመቤታችን መልአኩ እንደ ነገራት ጸነሰች።  በኦሪቱ ሕግ ሳታገባ ብትጸንስ በድንጋይ ያስወግራል። ይኽም ሌላ በልቧ የገባ ኀዘን ነው። በዚኽ ነገር ኹሉ ደግሞ ዝም ነው የምትለው። ነገሩን ለማንም አትናገረውም።  ለመልአኩ የመለሰችው “ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች።” የሚል ቃል ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ፍቃድ ተቀበለች።  ጌታን በቤተልሔም ወለደችው። የእግዚአብሔር ልጅ ልጇ ኾነ። የሰማይ ስጦታ ተሰጣት። ወንድ ልጅ ወልጃለሁ በልጄ ደስ ይለኛል ሳትል ገና ኹለት ዓመት ሲሞላው በሔሮድስ አማካኝነት ሌላ የመከራ ዜና ሰማች። ልጇን ሊገድለው እንደሚፈልግ። በግብጽ የበረሃ ልብ ውስጥ ልታልፍ ተነሳች። “እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።” ማቴ.2:13 ሔሮድስ ወታደሮቹን ላከባቸው። ጌታ፣ እመቤታችን፣ ቅዱስ ዮሴፍ፣ ሰሎሜ ከሔሮድስ ያመልጡ ዘንድ ስደት ጀመሩ። ወታደሮቹ ይከተሏቸው ስለ ነበር ምንም እረፍት አልነበራቸውም። ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ከበረሃ ወደ በረሃ ይሸሹ ነበር። ሦስት ዓመት ከስድስት ወር በመከራ አሳለፈች። ንጉሥ ከነሠራዊቱ ያሳድሳታል ልጇንና እርሷን ሊገድል። ዓለም ሊገድላት የሚፈልጋት ብቸኛ ሴት ናት ። ሊያድናት ሊታደጋት የመጣ ማንም የለም። ኹሉም በር ይዘጋባታል።  በዝምታ ምን ያክል ግዜ አለቀሰች፣? ምን ያኽል እንባ በጉንጯ በዝምታ ወረደ?፣ ምን ያኽል መገፋትን ምን ያኽል መነቀፍን በዝምታ ታገሰች። ይኽ ኹሉ ለዓለም ድኅነት በእርሷ በኩል ያልፍ ስለ ነበር ነው።  ሰይጣን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚወዱትን ይጠላል ይዋጋል። የሚወዱትን ይኽንን ያክል ከጠላ እናቱን ምን ያኽል እንደሚጠላት መረዳት ያስፈልጋል። ሰይጣን እንደ እመቤታችን የሚጠላው ሰው የለም። የሰይጣንን ራሱን የሚቀጠቅጠውን ወልዳለችና። የእግዚአብሔርን እቅድ ያቆም ዘንድ የሚችለውን ያኽል ተዋግቷታል። ነገር ግን ጸንታ ቆመች።  ያለፈችበት መንገድ ኹሉ ከአንዱ ጨለማ ወደ ሌላው ጨለማ ዋሻ ተንከራተተች። ማለቂያ  የሌለውን ጨለማ ለእኛ መዳን አለፈችበት። ሔሮድስ ሲሞት ተመለሰች። “ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦  የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።” ሉቃ.1:19 ናዝሬት ገብተው ተቀመጡ “በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።” ማቴ.2:23 ንዋይ ካሳሁን

  • без подписи

  • 31 окт. 2024 г.481из Finoteabewze

    без подписи

  • 31 окт. 2024 г.4704из Finoteabewze

    ድንግል ማርያምን ባሰብኩ ጊዜ እመቤታችንን ማን ምን እንደኾነች የሚያውቃት እርሱ ልጇ ብቻ ነው። ከእግዚአብሔር ጸጋና ከመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ነው ቅዱሳን እመቤታችንን ክብሯን የተናገሩት። ማወቅም የምንሞክረው በዚኽ መንገድ ብቻ እንጂ ፍጥረት እመቤታችንን በሙሉ ለማወቅ ይቸገራል። ድንግልናዋ፣ ኀዘኗ፣ ትኅትናዋ፣ ተጽእኖ መፍጠሯ፣ ቅድስናዋ ይደንቃል።   “በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።  በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በልጆች መካከል ነው።” መኃ.2:2 በመጽሐፍ ቅዱስ በምልክት symbolic ወይም በምሳሌ የተጻፉ መጽሐፍት ኹለት ናቸው አንዱ መኃይልየ ሰሎሞን ሲኾን ኹለተኛው ዮሐንስ ራዕይ ነው።  ኹለቱ መጽሐፍት በምልክት የተጻፉበት ምክንያት እግዚአብሔርን ወይም አምላክን መግለጥ የሚችል አቅም ያለው ቃል ስለሌለ ነው። እውነተኛ የእግዚአብሔር ፍቅር ምን እንዴት እንደኾነ መግለጽ የሚችል ቃል የለም። ብቸኛ መግለጫ መንገዱ ምሳሌያዊ ነው። የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጽ ቃል የለም ራዕይም የሚያሳየን ይኽንን ነው።  እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ልዩ ሰው በመኾኗ መግለጽ የሚቻለው በምሳሌ ነው።  የእመቤታችን ኀዘን እመቤታችን ከልደቷ ጀምሮ በመንግሥተ ሰማያት እስከ ገባችበት ጊዜ ያለው ሕይወቷ በኀዘን የተሞላ ጉዞ ነበር። ከቅዱሳን ቤተሰቦች ነው የተወለደችው። ልጅ እንዲሰጣቸው በሽምግልናቸው ሐናና ኢያቄም ተስለው ነው ያገኟት። በተአምር ልጃቸው ማርያምን ሰጣቸው ወለዱ። ስሟ ማርያም ተባለ። ትክክለኛ ቋንቋው አረማይኩ።“መርየም” የሚል ነው። ሕይወቷ ሁሉ እርሷም በኹለንተናዋ ለእግዚአብሔር የተሰጠች ናት።  ስሟ መሠረቱ በአረማይክ ወይም በእብራይስጥ “ሙራ” ከሚለው ቃል ነው። ሙራ ማለት ዕጽ (ተክል) ሲሆን ሲቀምሱት መራራ ነው። በእሳት ላይ ሲያቃጥሉት ግን መግለጽ የማይቻል እጅግ መልካም መዓዛ ያለው እእንጨት ነው። የእመቤታችንንም ነገር ሲሰሙት በአራት መዓዝነ ዓለም ሽታው ይደርሳል።  ሕይወቷን ሙሉ በእሳት ውስጥ በመቃጠል አልፋለች። የሦስት ዓመት ሕጻን  እያለች ወላጆቿ በተሳሉት መሠረት ቤተመቅደስ ወስደው ሰጧት። ሴት ልጅ ከሰጠህን ለቤተ መቅደስ አገልግሎት እንሰጣለን ብለው ነበር። መስዋዕት ትኾን ዘንድ ሰጧት።  ዘፍ.3:15 በቤተ መቅደስ ካሉት ኹሉ ትንሿ ሕጻን እርሷ ናት። “በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።” መኃ.2:2 እሾኽ ይዋጋል ይኽ በእመቤታችን ከሚደርሰው ኀዘን መካከል ነው። ለእመቤታችን የመጀመሪያው ኀዘን በሕጻንነት ከወላጅ መለየቷ ነው። እናትና አባት ምን ማለት እንደኾነ ጣዕሙን ሳታውቅ ተለያት።  ቤተ መቅደስ አሥራ ኹለት  ዓመት ኖረች። ይኽ እድሜ ደግሞ ለአቅመ ሔዋን የምትደርስበት ስለኾነ ከቤተመቅሰ መውጣት አለባት። ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ነበር አልወጣችም።  እመቤታችን በቤተመቅደስ ሰዎችን ትትታዘዛለች፣ ታገለግላለች፣ ታጸዳ ነበር። እመቤታችን ቤተመቅደስ ባሳለፈችበት ጊዜ ኹሉ አገልጋይ ነበረች።  ቤተ መቅደስ ዘወትር ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው የእንስሳት መስዋዕት የሚያቀርቡበት ደም የሚያፈሱበት ነው። እመቤታችን ያን የደም መስዋዕትን የሚያስቀረውን ልጇን ልትወልድ ምድሩን ከደም ልታነጻ እያጠበች ነበር።  እመቤታችን ከቤተመቅደስ በአሥራ አምስት ዓመቷ ስትወጣ ወላጆቿ በሞት ተለይተዋታል። ሌላው ኀዘን ይኽ ነው። በመካከለኛው ምስራቅ ባሕል አንዲት ልጃገረድ ሳታገባ ብቻዋን መኖር እንደ ነውር ይቆጥረዋል። ካላገባች ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀል አትችልም።  ቅዱስ ዮሴፍ በጣም ሽማግሌ ነው። ጠባቂዋ ይኾን ዘንድ ተሰጠችው። መልአኩም እርሷን ነገራት “ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።  መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤  ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።  ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።” አላት። ሉቃ.1:34 ንዋይ ካሳሁን

  • ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #መስከረም_28_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ዕብራውያን 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸ አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ⁹ ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ ¹⁰ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና። ¹¹ ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። ¹² ስለዚህ ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ እንደማይቈጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው ከአንዱ ተወለዱ። ¹³ እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ። ¹⁴ እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና። ¹⁵ ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤ ¹⁶ አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። ¹⁷-¹⁸ አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፥ የተስፋን ቃል የተቀበለው፦ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም አንድ ልጁን አቀረበ፤ ¹⁹ እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአልና፥ ከዚያም ደግሞ በምሳሌ አገኘው። ²⁰ ይስሐቅ ሊመጣ ስላለው ነገር ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው። ²¹ ያዕቆብ ሲሞት በእምነት የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸው ባረካቸው፥ በዘንጉም ጫፍ ተጠግቶ ሰገደ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ያዕቆብ 4 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም። ¹² ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? ¹³ አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። ¹⁴ ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። ¹⁵ በዚህ ፈንታ። ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል። ¹⁶ አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው። ¹⁷ እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሐዋርያት 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹² ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ። ¹³ ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤ ¹⁴ የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች። ¹⁵ እነርሱም፦ አብደሻል አሉአት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እነርሱም፦ መልአኩ ነው አሉ። ¹⁶ ጴጥሮስ ግን ማንኳኳቱን አዘወተረ፤ ከፍተውም አዩትና ተገረሙ። ¹⁷ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣው ተረከላቸውና፦ ይህን ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሩ አላቸው። ወጥቶም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ። ¹⁸ በነጋም ጊዜ፦ ጴጥሮስን ምን አግኝቶት ይሆን? ብለው በጭፍሮች ዘንድ ብዙ ሁከት ሆነ። ¹⁹ ሄሮድስም አስፈልጎ ባጣው ጊዜ ጠባቂዎችን መረመረ ይገድሉአቸውም ዘንድ አዘዘ፤ ከይሁዳም ወደ ቂሣርያ ወርዶ በዚያ ተቀመጠ። ²⁰ ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎችም ጋር ተጣልቶ ነበር፤ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ መጡ፥ የንጉሥንም ቢትወደድ ብላስጦስን እሺ አሰኝተው ዕርቅ ለመኑ፥ አገራቸው ከንጉሥ አገር ምግብ ያገኝ ነበረና። ²¹ በተቀጠረ ቀንም ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋን ተቀመጠ እነርሱንም ተናገራቸው፤ ²² ሕዝቡም፦ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው የሰውም አይደለም ብለው ጮኹ። ²³ ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ። ²⁴ የእግዚአብሔር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #መስከረም_28_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአዕይንትየኒ እምአንብዕ። ወለእገርየኒ እምዳኅዕ"። መዝ. 55፥13 “ነፍሴን ከሞት፥ እግሮቼን ከመውደቅ አድነሃልና፥ በሕያዋን ብርሃን እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ።” መዝ. 55፥13 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #መስከረም_28_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ዮሐንስ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፦ ⁴ መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ⁵ ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። ⁶ የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ ⁷ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፦ ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። ⁸ ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። ⁹ እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ¹⁰ ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። ¹¹ እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱሳን አባዲርና ኢራኢ፣ የቅድስት ሶስና የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

  • 🌹🥀🌹 እንኳን #ለዘመነ_ጽጌ_ለማኅሌተ_ጽጌ #የመጀመሪያ_ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።🌹🥀🌹 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #መስከረም_26_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ “በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።”— ሮሜ 5፥20-21 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ራእይ 21 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም። ² ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ። ³ ታላቅም ድምፅ ከሰማይ፦ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ ⁴ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ። ⁵ በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ። ⁶ አለኝም፦ ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። ⁷ ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል። ⁸ ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሐዋርያት 21 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³¹ ሊገድሉትም ሲፈልጉ፦ ኢየሩሳሌም ፈጽማ ታወከች የሚል ወሬ ወደ ጭፍራው ሻለቃ ወጣ፤ ³² እርሱም ያን ጊዜ ወታደሮችን ከመቶ አለቆች ጋር ይዞ እየሮጠ ወረደባቸው፤ እነርሱም የሻለቃውንና ወታደሮችን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መምታት ተዉ። ³³ በዚያን ጊዜም የሻለቃው ቀርቦ ያዘውና በሁለት ሰንሰለት ይታሰር ዘንድ አዞ ማን እንደ ሆነና ምን እንዳደረገ ጠየቀ። ³⁴ ሕዝቡም እኵሌቶቹ እንዲህ እኵሌቶቹም እንዲያ እያሉ ይጮኹ ነበር፤ ስለ ጫጫታውም እርግጡን ማወቅ ባልተቻለ ጊዜ፥ ወደ ወታደሮች ሰፈር ይወስዱት ዘንድ አዘዘ። ³⁵ ወደ ደረጃውም በደረሰ ጊዜ ስለ ሕዝቡ ግፊያ ወታደሮች እንዲሸከሙት ሆነ፤ ³⁶ ብዙ ሕዝብ፦ አስወግደው እያሉና እየጮኹ ይከተሉ ነበርና። ³⁷ ወደ ሰፈርም ሊያገቡት በቀረቡ ጊዜ፥ ጳውሎስ የሻለቃውን፦ አንድ ነገር ብነግርህ ትፈቅዳለህን? አለው። እርሱም፦ የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህን? ³⁸ አንተ ከዚህ ዘመን አስቀድሞ ከነፍሰ ገዳዮቹ አራቱን ሺህ ሰዎች አሸፍተህ ወደ ምድረ በዳ ያወጣህ የግብፅ ሰው አይደለህምን? አለ። ³⁹ ጳውሎስ ግን፦ እኔስ አይሁዳዊ በኪልቅያ ያለው የጠርሴስ ሰው ሆኜ ስመ ጥር በሆነ ከተማ የምኖር ነኝ፤ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ አለ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #መስከረም_26_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "ፍሬ ፃማከ ተሴሰየ። ብፁዕ አንተ ወሠናይ ለከ። ብእሲትከ ከመ ወይን ሥሙረ ውስተ ጽርሐ ቤትከ"። መዝ 127፥2-3። "የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል። ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው። መዝ 127፥2-3። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #መስከረም_26_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ዮሐንስ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁵ ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ። ²⁶ ወደ ዮሐንስም መጥተው፦ መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርህለት፥ እነሆ፥ እርሱ ያጠምቃል ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ አሉት። ²⁷ ዮሐንስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው እንዳች ሊቀበል አይችልም። ²⁸ እናንተ፦ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፥ ነገር ግን፦ ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ። ²⁹ ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ። ³⁰ እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል። ³¹ ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው። ³² ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም። ³³ ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ። ³⁴ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና። ³⁵ አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል። ³⁶ በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🌹የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታችን_ማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የመጀማሪያው ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ሰንበት በዓልና ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።🌹 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

  • #መስከረም_25 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሃያ አምስት በዚች ቀን የከበረች #ቅድስት_በርባራ መታሰቢያዋ ነው፣ #ታላቁ_ነቢይ_ዮናስ እረፍቱ ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ባርባራ (በርባራ) ሰማዕት አንድ አምላክ በሚሆን በ #አብ በ #ወልድ በ #መንፈስ_ቅዱስ ስም አሜን። [ታኅሣሥ 8 የዕረፍት በዓሏ እና መስከረም 25 ተዓምር ያደረገችበት በዓሏ የሚከበረው ቃል ኪዳኗ ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው የ #ቅድስት_በርባራ ድንቅ ታሪኳ፤ በቀደምት ኢትዮጵያውያን የቀረበላት ውዳሴና ዓለም ዐቀፍ ክብሯ] የተቀበለችው ቃል ኪዳን ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው በመላው ዓለም ከጥንት ጀምሮ የምትታወቀው ከ273-306 ዓ.ም የነበረችው ሰማዕቷ ቅድስት በርባራ Αγία Βαρβάρα, Great Martyr Barbara ከ305-311 በነገሠው በከሓዲው መክስምያኖስ (emperor Maximian) ዘመነ መንግሥት መስፍን የነበረው የዲዮስቆሮስ ልጅ ናት። እጅግ ውብ ስለነበረች ሰው እንዳያያት ጣዖት አምላኪ የነበረ አባቷ ለርሷም ለብቻዋ ሰገነት ያለው ማረፊያ ታላቅ ሕንፃ አሠርቶላት አንድ አረማዊ መምህር ብቻ ወደርሷ እንዲገባ አደረገ። ያሠራላት ሰገነት ከፍ ያለ ስለነበር አበባዎችን ይልቁኑ በምሽት የሚያበሩትን ከዋክብት የምሽቱ አስደናቂ ግርማ እየተመለከተች መደነቅ ጀመረች። በዚህ ጊዜ እነዚህ የአባቷ ጣዖታት አስደናቂ ዓለማትን እንደማይፈጥሩ ተረዳች። በሕይወቷ የዓለማት ፈጣሪን ለማወቅና በድንግልና ሕይወት ለመኖር ወሰነች። ብዙ የጋብቻ ጥያቄን ውድቅ አደረገች። በዚህ ምክንያት አባቷ ውጪውን እንድትለምደው ከግቢ እንድትወጣ ፈቀደላት። በዚህ ጊዜ ከክርስቲያን ሴቶች ጋር በመገናኘቷ ስለ ምስጢረ #ሥላሴ፣ የአምላክ ሰው የመሆን ምስጢርን አስረዷት። እውነተኛውን የድኅነት መንገድ በመረዳቷ ከእስክንድር ወደ ሄሊዎፓሊስ መጥቶ በነበረ ካህን በድብቅ ተጠመቀች። በዚያ ወቅት አባቷ በመታጠቢያ ክፍሏ ላይ ደግሞ ኹለት መስኮቶችና ቅንጡ የሆነ መታጠቢያ እንዲሠሩላት ዐናጺዎችን አዘዘ፤ ርሷ ግን የ #ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመኗና በመጠመቋ ምስጢረ #ሥላሴን አስባ ሦስተኛ መስኮትን እንዲጨምሩ ዳግመኛም አዳኝ የኾውን የ #መስቀሉን ምልክት በውሃ መታጠቢያው ላይ እንዲሠሩ ሐናጺዎችን አዘዘቻቸው፡፡ አባቷም ወደዚኽ ሕንጻ በገባ ጊዜ ልጁ ያሠራችውን አይቶ ዐናጺዎችን ሲጠይቃቸው፤ ይኽነን እንዲሠሩ ያዘዘቻቸው ልጁ መኾኗን ነገሩትን ርሱም “ለምን እንደዚኽ አደረግሽ” ብሎ ጠየቃት፡፡ “ወትቤሎ አእምር ወለቡ ኦ አቡየ እስመ በ #ሥሉስ ቅዱስ ይትፌጸም ኲሉ ግብር በእንተዝ አግበርኩ ሣልሲተ መስኮተ፤ ወዘንተኒ መስቀለ በአምሳለ ስቅለቱ ለ #መድኀኒነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ” ይላል ርሷም “አባቴ ሆይ አስተውል፤ ልዩ ሦስት በኾነ በ #ሥላሴ ስም ሥራ ኹሉ ይፈጸማልና ስለዚኽ ሦስተኛ መስኮት አሠራኊ፤ ይኽም #መስቀል ዓለሙ ኹሉ በርሱ በዳነበት በ #መድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_መስቀል አምሳል ነው አንተም አባቴ ሆይ ከስሕተትኽ ተመልሰኽ የፈጠረኽን አምላክ አምልከው” በማለት ተናገረችው፡፡ አባቷም ከርሷ ይኽነን በሰማ ጊዜ በንዴት ሰይፉን መዝዞ በኋላዋ ሮጠ፤ ያን ጊዜ ሸሽታ በዐለት ውስጥ ገብታ ለጊዜው ብትሸሸግም በኋላ ግን ወደ አባቷ ተመለሰች፤ ርሱም እንድትሠቃይ ለሌላ መኰንን አሳልፎ ሰጣት፤ ርሱም እየገረፈ በጊዜው አሉ በተባሉ በታላላቅ ሥቃይን ቢያሠቃያትም የባሕርይ አምላክ #ክርስቶስን ግን አልካደችም፤ ከዚያም ብቻዋን ወደ ወህኒ ተጣለች፤ በዚያም ኾና “ #ጌታዬ አምላኬ ሆይ አትተወኝ” ብላ ጸለየች፤ በእኩለ ሌሊትም የእስር ቤቱን ደማቅ ብርሃን መላው፤ “ከአንቺ ጋር ነኝና አትፍሪ” የሚለውን የአምላክን ድምፅ ሰማች፤ ከዚያም #ጌታችን ቊስሎቿን ኹሉ ፈወሰላት፡፡ በነጋታው ቅድስት በርባራን በማርቲያኑስ ፊት አቆሟት፤ ኹሉም ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንደዳነችና ፊቷም እንደ ፀሓይ ጨረር ሲያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ መኰንኑም “አማልክቶቻችን ስለፈወሱሽ የምስጋና መሥዋዕትን ሠዊ” አላት፤ ቅድስት በርባራም ለአገረ ገዢው “በ #ጌታዬ_በኢየሱስ_ክርስቶስ ነው የዳንኩት” አለችው፡፡ ማርቲያኑስም በቊጣ ኾኖ በአስከፊ ኹኔታ ቅድስት በርባራ እንድትሠቃይ አዘዘ፤ በዙሩያዋ ቆመው ይመለከቱ የነበሩ ሕዝቦች ርሷን ለመከላከል ምንም ቃል አልወጣቸውም፡፡ በዚያም የሂሊኦፓሊስ ነዋሪ ዮልያና የምትባል ሴት ነበረችና ቅድስት በርባራን ሲያሰቃይዋት አይታ ከርሷ ጋር በ #ክርስቶስ ስም መከራን ለመቀበል በመወሰን አብራት መከራ መቀበል ጀመረች። ሁለቱም ሰማዕታትን በምስማር ሰውነታቸውን እየወጉ ያሰቃይዋቸው ነበር። ለመዘባበት ዕርቃናቸውን በአደባባይ ሊወስዷቸው ቢሞክሩም በቅድስት በርባራ ጸሎት #ጌታ መልአኩን ልኮ በአስደናቂ መጎናጸፊያ ሰውነታቸውን ጋርዶታል። በመጨረሻም ጨካኙ መኰንን ብዙ ዐይነት ሥቃይ ቢደርስባቸው እነዚኽ ቅዱሳት አንስት በ #ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንደማይለውጡ ባየ ጊዜ አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘ። ከወታደሮቹ መኻከል አንዱ አንገታቸው ለመቊረጥ ሰይፉን መዘዘ፤ በአባቷ ወደ ተዘጋጀው ወደ መግደያው ስፍራ ይዟቸው ኼደ፤ ያን ጊዜ ቅድስት በርባራ እንዲኽ ብላ ጸለየች “ዘላለማዊ #እግዚአብሔር ሆይ ከእኔ ሞት በኋላ እኔንና መከራዬን ለሚያስቡ ኹሉ ሥጦታኽን ስጣቸው፤ ድንገተኛ ሕመምና ብርቱ (አስጨናቂ) ሞትን በእነርሱ ላይ ፈጽሞ አታምጣባቸው” አለች፡፡ ከዚያም የክብር ባለቤት #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ መሻቷን ኹሉ እንደሚፈጽምላት ቃል ኪዳን ሲገባላት በሰጣት ቃል ኪዳን የሚታመኑ ኹሉ ድንገተኛ ሞት እንደማያገኛቸው ቃል ኪዳን ገባላት። በመጨረሻም አባቷ የርሷንና የባልንጀራዋ የዮልያና አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘና ታኅሣሥ 8, በ306 ዓ.ም. አንገታቸው ተቈርጦ የሰማዕትነት አክሊል ሲቀዳጁ፤ ቅድስት ዮልያናንም በኹለት ጡቶቿ በኩላብ ሰቅለው ሰይፈዋታል፡፡ በዚያን ጊዜ ከሰማይ መብረቅ ወርዶ አባቷንና ጓደኛው የኾነ መኰንን መርትያኖስን አቃጠላቸው፤ ከዚኽ የተነሣ በዓለም ባለው ሥዕሏ ላይ የመብረቅ ብልጭታ ይሣላል፡፡ ቅድስት በርባራም በዚህ ምክንያት በአማላጅነቷ ከጥንት ጀምሮ ባሉት ክርስቲያኖች ከመብረቅ አደጋና ከእሳት የምትጠብቅ እንደሆነች ይነገራል። ያም በመታጠቢያ ቤት ውስጥ በ #መስቀል ምልክት ያሠራቸው መታጠቢያ ለታመመ ኹሉ ከርሱ በታጠበ ጊዜ የሚያድን ኾነ፤ ከዚኽም በኋላ የሰማዕታቱን ሥጋቸውን ወስደው ከከተማ ውጪ ባለች ቤተ ክርስቲያን ስሟ ገላልያ በሚባል ቦታ አኖሯቸው፤ ይኽ ሥጋቸውም በቅዱሳን ሰማዕታት በአቡቂርና በዮሐንስ በምስር አገር ባለ ቤተ ክርስቲያን ተቀመጠ፡፡ ይኽነን ተጋድሎዋን ለማዘከር በመላው ዓለም በሚሣለው ሥዕሏ ላይ ሦስት መስኮት ያለው ሰገነት፣ ዘንባባ፣ ጽዋ፣ መብረቅ፣ የሰማዕትነት አክሊል ይዛ ይታያል፡፡ በዐዲስ አበባ በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ባሉት የግድግዳ ላይ ሥዕላት ላይ ቅድስት በርባራና ቅድስት ዮልያና ተሥለዋል። በዓለም ላይ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ የታነጹላት ሲኾን በሩሲያ ብዙዎች ቤተ ክርስቲያናት በስሟ ሲሠየሙላት አንደኛው በሞስኮ ከቅዱስ ባስልዮስ ካቴድራል አጠገብ ይገኛል:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 8 በሚነበበው መዝገበ ቅዱሳን በሆነው ስንክሳር ላይ ቅድስት በርባራና ዮልያናን ታስባለች።

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • #መስከረም_24 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሃያ አራት ኢትዮጵያዊቷ #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ ወደ ደብረ ሊባኖስ የገባችበት፣ ከላይኛው ግብጽ የሆነ ቅዱስ አባት #መነኰስ_ጎርጎርዮስ ያረፈበት እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመረጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ #ሐዋርያ_አድሊጦስ የምስክርነቱ መታሰቢያ ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ መስከረም ሃያ አራት ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ወደ ደብረ ሊባኖስ የገባችበት ነው። ቅድስት እናት ክርስቶስ ሠምራ ቅንነቷ፣ ደግነቷና ቅድስናዋ እጅግ የበዛ ነው። አንድ ቀን ግን ገና በትዳር ውስጥ እያለች ከአገልጋዮቿ አንዷን ትጠራትና ታዛታለች። ያቺ አገልጋይ ግን የታዘዘችውን ጀሮ ዳባ ልበስ ብላ ሳትታዘዛት ትቀራለች። ደጋግማ ብትነግራትም ልትሰማት አልቻለችም። ያን ጊዜ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልትገስጻት ብላ ጠጠር ብትወረውርባት ያች አገልጋይ ወድቃ ሞተችባት። ቅድስቲቱ እጅግ ደንግጣ አለቀሰች። የምታደርገውንም አጣች። ወዲያው ግን ፈጠን ብላ: ወገቧን ታጥቃ ትጸልይ ጀመረች። " #ጌታየ ሆይ! ከሞት አስነሳልኝና ዓለምን ትቼ በቀሪ ዘመኔ አንተን አገልለግልሃለሁ" ብላ ፈጣሪን በብዙ እንባ ተማጸነችው:: ያን ጊዜም አገልጋዩዋ ከሞት ተነሳችላት። ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ጊዜን አላጠፋችም። ልጆቿን በቤት ትታ ሃብትን ንብረቷን ንቃ አንድ ልጇን አዝላ ቤቷን እንደ ተከፈተ ትታው ወደ ገዳም ወጣች። በዚህ ዕለትም (መስከረም 24 ቀን) ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገባች። #ለእግዚአብሔም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስቷ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ጎርጎርዮስ_ዘላዕላይ_ግብጽ ዳግመኛም በዚህች ቀን ከላይኛው ግብጽ የሆነ ቅዱስ አባት መነኰስ ጎርጎርዮስ አረፈ ። የዚህም የቅዱስና የተመሰገነ ጎርጎርዮስ ወላጆቹ ደጎች ናቸው በዚህ ዓለም ገንዘብም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህን ልጃቸውን ጎርጎርዮስንም በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት ። መንፈሳዊ የሆነ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን ሁሉ ሥጋዊም የሆነ ጥበብንና ቋንቋን አስተማሩት ። ከዚህም በኋላ የሀገራቸው ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነ ወደ አባ ይስሐቅ ወሰዱት እርሱም እጁን በላዩ ጭኖ አናጒንስጢስነት ሾመው ። ከዚህም በኋላ ወላጆቹ ሊአጋቡት አሰቡ እርሱ ግን ይህን ሥራ አልወደደም ሁለተኛም ወደ ጳጳስ ወስደውት ፍጹም ዲቁናን ተሾመ ወደ አባ ጳኲሚስም አዘውትሮ በመሔድ ከእርሱ የ #እግዚአብሔርን ሕግ የሚማር ሆነ ከወላጆቹም ብዙ ገንዘብን ወስዶ ወደ አባ ጳኲሚስ አቅርቦ በገዳማቱ ለሚሠሩ ሕንፃዎች ሥራ ያደርግለት ዘንድ ብዙ ልመናን ለመነው እርሱም ተሳትፎ እንዲሆንለት ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ለመነኰሳት ቤት መሥሪያ አደረገለት ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዓለምን ትቶ ጥሪቱንና ገንዘቡን ሁሉ ንቆ በመተው ወደ ቅዱስ አባ ጳኲሚስም ሒዶ የምንኲስና ልብስን ለብሶ በጾም በጸሎት በመትጋት በመስገድ ከትሕትና፣ ከቅንነት፣ ከፍቅር ጋር ይጋደል ጀመረ አርአያነቱንና ምሳሌነቱን በአዩ ጊዜ ከእርሱ ፈሪሀ #እግዚአብሔርን ተምረው አመንዝራዎች የከፋ ሥራቸውን እስከ ተውና ንስሐም ገብተው ንጹሐንም እስከ ሆኑ ድረስ ተጋደሉ ። ከአባ ጳኲሚስም ዘንድ ዐሥራ ሦስት ዓመት ኖረ ። አባ መቃርስም ወደ አባ ጳኲሚስ በመጣ ጊዜ ሰውነቱን በማድከም ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ጥቂት ቀኖች ኖረ ከዚያም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊመለስ ወደደ አባ ጳኲሚስም ከአባ መቃርስ ጋር እንዲሔድ አባ ጎርጎርዮስን አዘዘው እርሱም አብሮ ሔደ በእርሱም ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖረ ። ከዚህም በኋላ በዋሻ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንዲአሰናብተው የከበረ አባ መቃርስን ለመነው እርሱም እንደ ወደድክ አድርግ አለው ። ያን ጊዜ ወደ ተራራ ሒዶ ታናሽ ዋሻ ቆርቁሮ በውስጧ ሰባት ዓመት ኖረ አባ መቃርስም በየዓመቱ ሁለት ጊዜ መጥቶ ይጎበኘዋል አንደኛ ለከበረ የልደት በዓል ሁለተኛ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በተነሣባት በትንሣኤ በዓል ቀን ከርሱ ጋርም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብሎ ወደ ቦታው ይመለሳል ። አባ መቃርስም ስለ ሥራው ሁሉ ይጠይቀዋል እርሱም የሚያየውንና በእርሱ የሆነውን ሁሉ ይገልጽለታል አባ መቃርስም ሊሠራው የሚገባውን የምንኲስና ሥራን ይሠራ ዘንድ ያዘዋል ። በተጋድሎም ውስጥ ሃያ ሁለት ዓመታት ሲፈጽሙለት ከዚህ የድካም ዓለም ያሳርፈው ዘንድ #እግዚአብሔር ፈቅዶ መልአኩን ላከለት እርሱም ከሦስት ቀን በኋላ ከዚህ ከኀላፊው ዓለም ወጥተህ ወደ ዘላለም ሕይወት ትገባለህ አለው ። አባ ጎርጎርዮስም በአስቄጥስ ገዳም ያሉ አረጋውያንን አስጠራቸውና ተሳለማቸው በጸሎታቸውም እንዲአስቡት ለመናቸው እነርሱም ደግሞ በ #እግዚአብሔር ዘንድ እንዲአስባቸው ለመኑት ከሦስት ቀንም በኋላ አርፎ ወደ ዘላለም ሕይወት ገባ ። #ለእግዚአብሔም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አበው ጸሎት ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ሐዋርያ_አድሊጦስ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት) በዚህችም ቀን ክብር ይግባውና #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከመረጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ሐዋርያ ቅዱስ አድሊጦስ የምስክርነቱ መታሰቢያ ነው ። ይህም ሐዋርያ ትውልዱ ከአቴና አገር ከታላላቆቿና ከምሁራኖቿ ነው እርሱም ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አመነ አገለገለውም ። አጽናኝ የሆነ የ #መንፈስ_ቅዱስን ጸጋ በሃምሳኛው ቀን ከተቀበለ በኋላ ወደ ብዙዎች አገሮች ሒዶ ሕይወት የሆነ ወንጌልን ሰበከ መግኒን ወደሚባልም አገር ደርሶ በውስጧ የከበረ ወንጌልን ሰበከ የብዙዎችንም ልቦና ብሩህ አድርጎላቸው ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_በመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አመኑ ። የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ሕይወት የሆኑ የወንጌልንም ትእዛዞች አስተምሮ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው ። ከዚህም በኋላ ከእሳቸው ዘንድ ወጥቶ ወደ አቴና አገር ተመለሰ በውስጧም የከበረ ወንጌልን አስተማረ በዚያን ጊዜም በደንጊያ ወገሩት ጽኑዕ የሆነ ሥቃይንም አሠቃዩት ። ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ወረወሩትና በዚያ ተጋድሎውንና ምስክርነቱን ፈጽሞ የሕይወት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ። #መስከረም_24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ገዳማዊ 2.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ (ደብረ ሊባኖስ የገባችበት) 3.ቅዱስ አድሊጦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 4.አቡነ ሰላማ #ወርኀዊ_በዓላት 1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት) 2.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ 3.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን 4.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ) 5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ 6."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል) 7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ) "ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል"።(1ኛቆሮ.13÷4-7) (#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም_24 ና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

  • без подписи

  • без подписи

  • #መስከረም_23 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሃያ ሦስት በዚህች ዕለት የክርስቶስ ሙሽራው የሆነች #ቅድስት_ቴክላ መታሰቢያ በዓሏ ነው፤ ዳግመኛም #ቅዱሳን_አውናብዮስ_እና_እንድርያስ በሰማዕትነት አረፉ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ቴክላ_የክርስቶስ_ሙሽራው መስከረም ሃያ ሦስት በዚህች ዕለት የ #ክርስቶስ ሙሽራው የሆነች ቅድስት ቴክላ የመታሰቢያ በዓሏ ነው፡፡ ይህችውም ቅድስት ለሐዋርያው ለቅዱስ ጳውሎስ ረድእ ሆና ያገለገለች ታላቅ ሐዋርያዊት እናት ናት፡፡ የመቄዶንያ ሀገር ባለጸጎች የነበሩት ወላጆቿ ጣዖት አምላኪ ነበሩና በሕጋቸውና በሥርዓታቸው አሳደጓት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደዚህች ሀገር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን ሰበከ፡፡ ቅድስት ቴክላም ትምህርቱን በሰማች ጊዜ በቤቷ ሆና ሳትበላና ሳትጠጣ 3 ቀን ቆየች፡፡ ከዚህም በኋላ ለሚጠብቃት ዘበኛዋ እንዳይናገርባት በማለት የወርቅ ወለባዋን ሰጠችውና ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሄደች፡፡ እርሱም በደስታ ተቀብሎ የ #ክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራት፡፡ በማግሥቱም ቅድስት ቴክላን እናቷ ስትፈልጋት ከቅዱስ ጳውሎስ እግር ሥር አገኘቻት፡፡ ከዚያም ወደ መኰንኑ ዘንድ ሄዳ ልጇ ክርስቲያን መሆኗን በመናገር ከሰሰቻትና ለመኰንኑ አሳልፋ ሰጠቻት፡፡ መኰንኑም ሁለቱን ቅዱስ ጳውሎስንና ቅድስት ቴክላን እንዲያመጧቸው ወታደሮቹን ላከ፡፡ ካመጧቸውም በኋላ መጀመሪያ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ እሳት ወረወሩት፡፡ ነገር ግን #እግዚአብሔር በተአምራት አዳነው፡፡ ቅድስት ቴክላን ግን ለሀገሩ ልጆች መቀጣጫ ትሆን ዘንድ መኰንኑ ሰውን ሁሉ ከሰበሰበ በኋላ ወደ እሳቱ እንዲወረውሯት አዘዘ፡፡ እርሷ ግን በ #መስቀል ሦስት ምልክት ካማተበች በኋላ በራሷ ፈቃድ ማንም ሳይነካት ዘላ ከእሳቱ ውስጥ ገባች፡፡ ነገር ግን በ #እግዚአብሔር ጥበቃ ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ እርሷም ማንም ሳያያት ከእሳቱ ውስጥ ወጥታ ቅዱስ ጳውሎስ ካለበት ደረሰች፡፡ የራሷንም ጸጉር ቆርጣ በእርሱም ወገቧን ታጥቃ ቅዱስ ጳውሎስን ተከተለችው፡፡ መኰንኑም በሕይወት መኖሯን ሰምቶ ድጋሚ አስፈልጎ አስያዛትና ሃይማኖቷን እንድትለውጥ አስገደዳት፡፡ እሺ እንዳላለችው ባወቀ ጊዜ በተራቡ አንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ጨመራት ነገር ግን አንበሶቹ ሰግደው የእግሯን ትቢያ ሲልሱላት ተመለከተ፡፡ መኰንኑም ይህንን በተመለከተ ጊዜ እርሱና ወገኖቹም ሁሉ አምነው ተጠመቁና የ #ክርስቶስ መንጋዎች ሆኑ፡፡ ቅድስት ቴክላም የ #ጌታችንን ወንጌል በማስተማርና ቅዱስ ጳውሎስንም በማገልገል ብዙ ከተጋደለች በኋላ መስከረም 27 ቀን ዐርፋለች፡፡ #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ቴክላ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱሳን_አውናብዮስ_እና_እንድርያስ ዳግመኛም በዚች ቀን ቅዱሳን ጻድቃን መነኰሳት አውናብዮስና እንድርያስ በሰማዕትነት አረፉ። እሊህ ቅዱሳንም ከልዳ ሀገር ከታላላቆቹ ተወላጆች ናቸው ከታናሽነታቸውም በአምላካዊ ምክር ተስማምተው በሶርያ ውስጥ ከሚገኙ ገዳማት ወዳንዱ ገዳም ሒደው መነኰሳት ሆኑ። ከዚህም በኋላ ወደ ከበረ ወደ ተመሰገነ አባ መቃርስ ሔዱ ደቀ መዛሙርቱም ሁነው ታዘዙለት ምክሩንም በመቀበል በጾም በጸሎት በገድል ሁሉ ተጠምደው የሚኖሩ ሆኑ በእንዲህ ያለ ሥራም በዚያ ሦስት ዓመት ኖሩ በጎ የሆነ ተጋድሎአቸውና የአገልግሎታቸው ዜና በተሰማ ጊዜ አውናብዮስን መርጠው ኤጲስቆጶስነት፣ እንድርያስን ቅስና ሾሙአቸው በበጎ አጠባበቅም የ #ክርስቶስን መንጋዎች ጠበቋቸው። ከዚህም በኋላ ሥጋቸውን ፈጽሞ እስከ አደከሙ ድረስ ተጋድሎአቸውንና አገልግሎታቸውን እጅግ አበዙ። ከሀ*ዲ ንጉሥ ዮልዮስም ስለእርሳቸው በሰማ ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስቀርቦ የክብር ባለቤት #ክርስቶስን ክደው ወደ ረከሰች አምልኮቱ እንዲገቡ አዘዛቸው ያን ጊዜ እርሱንና የረከሱ ጣዖ*ታቱን ረገሙ እርሱም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ወደ ብዙ ክፍልም ቆራርጦ ከፋፈላቸውና ነፍሳቸውን በ #እግዚአብሔር እጅ ሰጡ። እያንዳንዳቸውም ሦስት ሦስት አክሊላትን ተቀበሉ አንዱ በገድል ስለ መጸመድና ስለ ምንኲስና ዋጋ፣ ሁለተኛው ስለ ክህነት አገልግሎት፣ ሦስተኛው ደማቸውን ስለ ማፍሰሳቸው ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም_23)

  • Location 📍

  • https://maps.app.goo.gl/sXJZYC7u8nb1Me5e8

  • без подписи

  • ነሐሴ 29 ዘሠርክ ምስባክ