የቅዱሳን ታሪክ
Статистикаበዚህ ቻናል ውስጥ፦ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ @kidanemiherat_bot
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 28
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 373
- 1/48двое суток
- 427
- 1/72трое суток
- 461
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
❝የምሥጢረ ሥላሴ አጭር መግለጫ ❞ °በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ° °°አብ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰገናል፡፡ ወልድም በአብና በመንፈስ ቅዱስ ይመሰገናል፡፡ መንፈስ ቅዱስም በአብና በወልድ ይመሰገናል፡፡ °°ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ አስቀድመው ለአብ ምስጋና በመስጠታቸውም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ይልቅ ለአብ ክብርን እንደስጡ አታስብ፡፡ እንዲህ አይደለምና፡፡ °°በአብ ያለ በወልድ ግን የሌለ ክብር የለም፡፡ በወልድ ያለ በአብና በመንፈስ ቅዱስ የሌለ ገናናነት የለም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ያለ በአብና በወልድ ግን የሌለ ክብር የለም፡፡ °°አብ ወልድ ባልነበረበት ወቅት አልነበረም፡፡ ወልድም መንፈስ ቅዱስ ባልነበረበት ወቅት አልነበረም፡፡ መንፈስቅዱስም አብና ወልድ ባልነበ ሩበት ዘመን አልነበረም፡፡ °°አብ ከወልድ አይበልጥም። ወልድም ከአባቱ አይበልጥም፡፡ መንፈስ ቅዱስም እንደ እነርሱ ነው፡፡ °°አብ ልጁን ይህ የእኔ ነው፣ ያ የአንተ ነው፤ ይህ የመንፈስ ቅዱስ ነው የሚለው አይደለም፡፡ ወልድም አባቱን ይህ የእኔ ነው ይህ የአንተ ነው ይህም የመንፈስ ቅዱስ ነው የሚለው አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስም አብን ይህ የአንተ ነው ይህ የወልድ ነው አይለውም፡፡ °°መጀመሪያችን ርስታችን የሆነ ወልድ ከአብ የሚለይ አይደለም፡፡ ወልድም በሀብትና በርስት ከአብ አይለ ይም፡፡ መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ፡፡ በሥላሴ የተለያየ መንግሥት የለም፡፡ በአንዲት አምልኮት ያመልኳቸዋል፡፡ አንዲት ስግደትም ይሰግዱላቸዋል። °°ሰውን በአርያችንና በምሳሌ ያችን እንፍጠር በማለት ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ የተናገረው የአብ ምክር ምን ይደንቅ፡፡ በዚህ ምክር የተሰማማ የወልድ ምክርም ዕፁብ ነው፡፡ በእጆቹ ሥራ የተደሰተ የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድም ምን ይደንቅ!
ሥላሴ በዕለተ ቀናቸው ሦስት የነገረ ድኅነት ማግኛ የመሠረት ድንጋዮችን ጣሉ። በዛሬዋ ዕለት የተጣሉ 3 የመሠረት ድንጋዮችም ❖ ፅንሰተ ማርያም ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ" እንዳለ ደራሲው በዛራዋ ዕለት የድኅነት መሠረት የሆነችዋ እናታችን ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ዕለት ነውና የነገረ ድኅነት ሕንፃው የመሠረት ድንጋዩ ተቀመጠ። ❖ ፅንሰተ ቤተ ክርስቲያን (በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ) ቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያትን ወክሎ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ በመመለሱ ይህንን ነገረ ሃይማኖት የምትመሰከር ቤተ ክርስቲያን በዚህ አስተምህሮት የጸናች ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይዋ በቂሳርያ ተመሠረተ። ❖ፅንሰተ ክህነት(የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻ ቁልፍ እሰጥሃለሁ በማለት ጌታችን መድኃኒታችን ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ ለመለሰው መልስ የክህነት ሽልማት በሐዋርያት በኩል ለቤተ ክርስቲያን ተሰጠ። እንኳን አደረሳችሁ
ይህቺን : ዕለት : ያልናፈቀ : ትውልድ : የለም #ነሐሴ_ሰባት_ቀን የባሕርያችን መመኪያ የምትሆን ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ዕለት ነው ፡፡ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ለሆነባቸው ቅዱሳን አበውና ቅዱሳን አንስት ተስፋቸው የሚፈጸመው በዛሬው ዕለት በተጸነሰችው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ነውና ፡፡ ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችንም ከእግዚአብሔር ቀጥሎ እንደ እመቤታችን ከፍ ከፍ የምታደርገው ፍጥረት የሌለው ስለዚሁ ነው ፡፡ ሊቃውንቱ፡- « ሐና አንቺን የጸነሰችበት የደስታ ቀን ምን ያህል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያህል የተባረከች የተቀደሰች ቀን ናት፤ » ብለው የሚዘምሩላትም ይህን ምሥጢር በልቡናቸው ቋጥረው ነው ። እንኳን ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ ደስታን ፡ ወዳመጣችው ዕለት ፡ አደረሳችሁ ፡ አደረሰን
#ማርያም_መግደላዊት #ነሐሴ_6_ቀን ማርያም መግደላዊት ሽሙጥን፣ ስድብን፣ መንገላታትንና ግርፋትን ታግሣ መልካሙን ገድል ተጋድላ ሰማዕትነትን ፈጽማ ያረፈችበት ቀን ነው። ይቺ ሴት ቀድሞ ሰባት አጋንንት ተቆራኝተዋት ሰባት አይነት ኀጢት ያሠሯት የነበረች ኋላ ግን ክርስቶስ ሰባቱን አጋንንት አስወጥቶላት ከሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ጋር የቀላቀላት ቅድስት ሴት ናት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ በተነሣ ጊዜም ትንሣኤውን ለመጀመሪያ ጊዜ የገለጸው ለማርያም መግደላዊት ነበር። ማርያም መግደላዊት ባደረባት እርኩስ መንፈስ ብዙዎችን ስታታልል ስትሸነግል የኖረችና በሐሰት ወጥመድ ጠልፋ የጣለቻቸው ብዙዎች ነበሩ። ማርያም መግደላዊት በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ከኖረች በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ወራት አጋንንትንም በሥልጣኑ ያወጣል ብለው ነገሯት። ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት ፈጥና ወደ እርሱ ሄደች ጌታችንም ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውና በፍቅር አቀረባት። በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን ሰባት ነገደ አጋንንትን ጠራርጎ አስወጣላት። በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕፃን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ ሆነች ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ። በሃምሳኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ «በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮቹ ላይ ቅዱስ መንፈሴን አሳድራለሁ» ብሎ በኢዩኤል ላይ አድሮ ትንቢት እንደ ተናገረ ከሐዋርያት ጋር ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ጸጋና በረከት የተካፈለች ቅድስት ሴት ናት። በመጨረሻም ማርያም መግደላዊት የሐዲስ ኪዳን ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች። የቅድስት መግደላዊት ማርያም ጸሎቷና በረከቷ አይለየን!🙏
#ወንጌላዊ_ቅዱስ_ዮሐንስ ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በጌታችን እግረ መስቀል ስር እስከ መጨረሻው በመጽናት የተገኝ ታማኝ ሐዋርያ ነው ። ለዚህም እንደሽልማት ከኃዘኑም ይጽናና ዘንድ ጌታችን በመስቀል ላይ ሆኖ እመቤታችንን ለቅዱስ ዮሐንስ በእናትነት ሰቶታል ለእሱም ብቻም አይደለም ለእኛም ለሁላችንም በእሱ ምሳሌነት እናት ትሆነን ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰቶናል ። ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን ወደ ቤቱ ከወሰዳት በኃላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታችን ጋር የነበራትን ታሪክ ስትነግረው እሱም ሲያገለግላት 15 ዓመት በእሱ ቤት ቆይታለች ። በቆይታቸውም እንደ ሰኔ ጎለጎልታ እና ራዕይ ማርያም ያሉ መጽሐፍትን ከእሷ እየሰማ እንደጻፈ ብዙ የቤተ ክርስቲያናችን መጸሐፍት ይናገራሉ ። ፍ ቁ ረ : እ ግ ዚ እ : የ ተ ባ ለ : የ ቅ ዱ ስ : ዮ ሐ ን ስ : ወ ን ጌ ላ ዊ : በ ረ ከ ቱ : ረ ድ ኤ ቱ : ከ ሁ ላ ች ን : ጋ ር : አ ድ ሮ : ለ ዘ ላ ለ ም : ይ ኑ ር ።
без подписи
"+የአንቺን ደም ግባት ማመስገን እንዴት ይቻለኛል+" ❤አንቺ ሙሽራ ነሽ፡፡ ዐይኖችሽም እንደሚያንጸባርቅ የኮከብ አወጣጥ ያስደስታሉ፡፡ ❤ጉንጮችሽም በሰሜናዊ ምሥራቅ በወጣ ጊዜ እንደሚያበራ እንደ ሚያዝያ ፀሐይ ናቸው፡፡ ❤አንገ ትሽም በዝሆን ቀንድ እንደተሠራ እንደዳዊት ቤት ነው፡፡ ❤ሆድ ሽም ሥንዴ የተጨመረበት በአበባም የታጠረ ነው፤ ❤ጣቶች ሽም የሚያማምሩ፣ በወርቅም የተለበጡ ናቸው፡፡ .......ያንችን ደምግባት የአንቺን ማማር ማመስገን እንዴት ይቻለኛል፡፡ የፊትሽ ደም ግባት ቀይ ነው፡፡ ድንግል ሆይ በውዳሴ አመሰግንሻለሁ፡፡ የአፍሽ ሽታ ከሽቱ መዓዛ ይልቅ ያስደስታል፡፡ =======አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ====
без подписи
#ጾመፍልሰታ/ጾመ ማርያም/ #ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ ተሰደደ፤ ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡ #ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡ #ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤ እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡ #የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡ #ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡ #ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤ እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡ #በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሐዋርያት በመንፈሰዊ ቅናት ተነሳስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡ የጾሙ እና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድረገን፤ አሜን
без подписи
ጀርባው በግመል ጸጉር የተሸፈነ ቀኙ የሚያቃጥል መለኮትን የዳሰሰች በጣፋጭ አንደበቱ ወንጌልን የሚሰብክ የቅዱስ ዮሐንስን ደግነት ፈጽመን እንናገራለን ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት በበርሐ 30 ዓመት የተቀመጠ ፡፡ ከልብስ ተለይቶ የግመል ጠጉር ከምግብ ተለይቶ የበረሐ ማር የተመገበ ። ሰውነቱ እስኪደርቅ የተጋደለ እርሱ ብቻውን የጌታ መንገድ ጠራጊ የሆነና ጌታውን ያጠመቀ ። የንስሐ በርን ከጌታው አስቀድሞ የከፈተና ጌታ ከኋላው ይከተለው ይመጣ ዘንድ እርሱ መልእክተኛ የሆነ ። ይህንን የንጋት ኮከብ የሚመስል በሰማይም ሆነ በምድር ሌላ ማን አለ ? ጌታውን ፈጣሪውን ያጠመቀ ከዮሐንስ በቀር ሌላ የለምና! ይህ ለመጥምቀ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ብቻ የተሰጠ ነውና ። ቅድስት በረከቱ ትደርብን 🙏
ምነው ልጆች መቁጠሪያ አደረጋችሁትሳ! ሐሳቧ ብትደገምም ለጾም ትጠቅማለችና አንብቧት😍 በአንድ ወቅት እግዚአብሔር ፈቅዶልኝ ጾመ ፍልሰታን በአንድ ቦታ በሱባዔ የማሳለፍ እድል አግኚቼ ነበር እናም ሱባዔውን የያዝንበት ክፍል ሰፋ ያለ አዳራሽ ስለነበረ ብዙ ሰዎች ታድመንበታል በዚህ ቦታ አያታቸውን ተከትለው ሱባዔ የገቡ ሦስት ልጆች ነበሩ እኒህ ልጆች በሰፊ እጅ የለመዱ ከደህና ቤተሰብ የተገኙ ናቸውና በብዙ ምቾት የኖሩ እንደሆነ ቁመናቸውና አለባበሳቸው ያስታውቃል ያው ገዳም ውስጥ ደግሞ በሶ እና ጥራጥሬ ስለሆነ ምግቡ ለእነዚህ ልጆች ምቾት አልሰጣቸውም በተለይ በሶውን ከበጠበጡ በኋላ እየሰለቻቸው ቀምሰው ለእኛ ይሰጡናል ካልሆነም ይደፉታል ቆሎውም ቢሆን ጥርሳቸውን ከማድከሙ ውጪ ሆዳቸው ላይ ጠብ አልል እያለ ተቸግረዋል ለእነሱ የተመቻቸው አንድ ነገር ቢኖር ዳቦ ቆሎው ነበር ይህ ዳቦ ቆሎ አንደኛ ስለሚጣፍጥ ሁለተኛ ጥርሳቸውን ስለማያደክመው ሆድም ላይ ጠብ ስለሚል ዳቦ ቆሎውን ወደውታል እናም ቅዳሴ እንዳለቀ ይመጡና ዳቦ ቆሎ መብላት ይጀምራሉ እኒህ እናት በወጡ በገቡ ቁጥር ተኝተውም በተነሱ ቁጥር ይህንን ዳቦ ቆሎ ሙጥኝ ብለው የሚቆረጥሙ ልጆችን በሁኔታቸው ተደንቀውና ተበሳጭተው ምነው ልጆች ይህንን ዳቦ ቆሎ በወጣችሁ በገባችሁ ቁጥር የምትዘግኑት ለምንድን ነው? ምንድን ነው እቴ ይሄ ዳቦ ቆሎ ከእጃችሁ የማይለየው? መቁጠሪያ አደረጋችሁት እንዴ?🤣 ብለው ሲናገሩ በአጋጣሚ እኛም ይህን ሲናገሩ ስለሰማን በሁኔታው ብዙ ፈገግ አልንና ልጆቹን ባየንና ዳቦ ቆሎ በቀረበ ቁጥር በአያታቸው ንግግር ፈገግ እያልን ሱባዔውን ጨረስነው ልጆቹም ከተቀለደባቸው በኋላ የዳቦቆሎ ፍቅራቸው እየቀነሰ ሄደና ዳቦ ቆሎውም ለእኛ መትረፍ ጀመረ። ዛሬ በሱባዔና በጾም ወቅት እስከ ምሳ ሰዓት ብቻ ጾመን ብፌ የምንዞር ሰዎች ቁርሳችንን ቆጥበን ምሳ ሰዓት አይነት በአይነት ደርድረን የምግብ ዕቁብ የምንጥል ሰዎችን ከበላነው ይልቅ ተርፎን የሚነሳው ፍርፋሪ ሦስትና አራት የእኔቢጤ የሚያጠግ ሰዎችን የአጿጿማችንን ሁኔታ ቢያዩ እኒህ እናት ምን ይሉን ይሆን? ተወዳጆች ሆይ ከጾምን በኋላ የምንበላው እህል ጾማችንን የሚያስረሳ ሳይሆን እርሀባችንን ማስወገጃ ብቻ ይሁን። ጾምን ያወጀልን አምላክም በነቢዩ ኢሳይያስ ላይ አድሮ የጾምን ትርጉምና አላማ ምን እንደሆነ ሲናገር " እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህን ለተራበ ትቆርስ ዘንድ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታስገባ ዘንድ የተራቆተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን? የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል። ብሎ ተናግሯል ኢሳ 58:6 ተወዳጆች ሆይ ስንጾም እየመጸወትን ይሁን ጾም ማለት በጾም በኩል የድሆችን ርሃብ ለእኛ ወስደን በምጽዋት በኩል የእኛን ጥጋብ ለድሆች መስጠት መሆኑን አንዘንጋ። በተለይም ሱባዔ ማለት የአካል ብቻ በአንድ ቦታ መወሰን ሳይሆን የልብ እርጋታና የአእምሮ ዕረፍት ነውና ለአእምሯችን የሚያስበውን ለአንደበታችን የሚናገረውን በጎ የሆነ የጾም ምግብ ብቻ እንምረጥለት። አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ጾም ጸሎታችንን የዲያብሎስ ድል መንሻ የኃጢያት መደምሰሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን። ለሐዋርያት የልባቸውን መሻት የፈጸመችላቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለእኛም በጎ መሻታችንን ትፈጽምልን መልካም ሱባዔ። መጋቤ ሐዲስ ዘለዓለም ሐሳቤነህ
без подписи
አቡነ : እጨጌ : ዮሐንስ #ሐምሌ_29_ቀን የአባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ በዓለ እረፍታቸው ሲሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ድምቀት ልጆቾን ሰብስባ ታከብራቸዋለች አባታችን እጨጌ ዮሐንስ ከእናታቸው እምነ ጽዮን እና ከአባታቸው ዲናሶር በሀገረ እየሩሳሌም ቅርብ በምትሆን በፍልስጤም አውራጃ ሣሬራ በምትባል ከተማ ተወለዱ ፡፡ ጻድቁ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ ሲሆን ምንኩስናንም የተቀበሉት በደብረ ሊባኖስ ገዳም ነው፡፡ በመላው ኢትዮጵያ ተዘዋውረው ያስተማሩ ሲሆን ከቅድስናቸው የተነሳ በሰማይ እንደ አእዋፋት ፀሀይና ጨረቃ ይዘው ጸልየዋል ከሰማይ መሰቀል የወረደላቸው አባት ናቸው ፡፡ ከጸለዩበት ባህር ውስጥ ደረቅ አፈር ይወጣል ፀበላቸው ሽባ ይተረትራል፤ ድውያንን ይፈውሳል ፡፡ የከበረ አጽማቸው መንዝ በፍረኮታ ኪዳነምህረት ይገኛል ፡፡ የአባታችን : የአቡነ : እጨጌ : ዮሐንስ በረከት : በሁላችንም : ላይ : ይደርብን ።
🥰"እግዚአብሔር በመቅደሱ ይባረክ፤ በእጁ ያደረገው ድንቅ ሥራ ሁሉ ይመስገን!"🥰 "እግዚአብሔር ሆይ አንተ እስከ ሽበቴ ድረስ እኔን ትደግፈኛለህ እስከ ሽበቴ ድረስ ትሸከመኛለህ እኔም እነግራቸዋለሁ የክንድህን ብርታት ለሚመጡት ሁሉ አወራለሁ።" መዝ፡ 70፥18 ዛሬ ልደቴ ነው አሉ😊 ታድያ የልደቴን ቀን ሳስብ በመጀመርያ የምለዉ ነገር ይኽ ነው "አቤቱ ቅዱስ አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሃለሁ!"🙏🙏🙏 ይኽ የሕይወቴ ዘመን የእኔ ብቃት፣ የእኔ ጥንካሬ ወይም የእኔ ጽድቅ ውጤት አይደለም አምላኬ ለኔ የሰጠኝ የማይገባኝ ምሕረት፣ የማይጠናቀቀው ፍቅሩ እና የማይለወጠው ቸርነቱ ውጤት ነው ብዙ ጊዜ በደካማነቴ ወድቄ፣ በእርሱ ጸጋ ግን እንደገና ተነስቻለሁ🥰 ዛሬ የሰጠኝን የሕይወት ዕድሜ ሳስብ ከሁሉ በላይ የምጠይቀው የዓለምን ሀብትና ክብር ሳይሆን ተጨማሪ የንስሓ ዕድሜ፣ በቅድስና የምመላለስበት ጊዜ፣ በቤቱ የማገለግልበት ዘመን እና ስሙን የማከብርበት ዕድሜ እንዲሰጠኝ ነው። "እኔ ምን ነበርኩ? አንተስ ምን አደረግህልኝ?" ብዬ ሳስብ የመድኃኔዓለምን ቸርነት መቁጠር አልችልም። የማይገባኝን ጸጋ ሰጠኝ፤ የማልችለውን ኃላፊነት በእርሱ ኃይል እንድሸከም አደረገኝ፤ ድምፄን ቅዱስ ንዋዩ አድርጎ ወንጌሉን እንድናገር፣ አንደበቴን ማስተጋብያ አድርጎ የስሙን ቃል እንድመሰክር ፈቀደልኝ።😍 "እኛ ራሳችን ብቁ እንደሆንን አይደለም፤ ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው።" 2ኛ ቆሮ፡ 3፥5 እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ የልደቴ ቀን መድኃኔዓለም አባቴን አምላኬንም አመሰግነዋለሁ🙏 ለእኔ በማይገባኝ ፍቅሩ የሸፈነኝ፣ በማይገባኝ ምሕረቱ የጠበቀኝ፣ በመቅደሱ አገልግሎት እንድሳተፍ የጠራኝ ጠባቂ እረኛ እባትም እናቴም ነውና ይመስገን🙏 የሚቀጥለው ዘመኔ የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የእርሱ ፈቃድ የሚፈጸምበት፤ ሕይወቴ ለራሴ ሳይሆን ለክርስቶስ የሚኖርበት፤ አገልግሎቴ ለሰው ምስጋና ሳይሆን ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆንበት ዘመን ይሁን🙏🥰 "እኔ በእግዚአብሔር ቸርነት ዛሬ ያለሁ ነኝ፤ የሚመጣውም ዘመኔ በእርሱ እጅ ነው።" አቤቱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ ዕድሜዬን በበረከት ሙላ🙏 ልቤን በትሕትና አኑር🙏 አእምሮዬን በጥበብ ምራ🙏 እጆቼን ለቅዱስ አገልግሎት አቅርብ🙏 አንደበቴንም የፍቅርህና የወንጌልህ ማስተላለፊያ አድርገው🙏🥰 ልዑል ሆይ ለአንተ ክብር ይሁን ለእኔ ደግሞ የንስሓና የቅድስና ዕድሜ ይሁን🙏 መልካም ልደት ለእኔ😊😊😊 "የቸርነትህን ዓመታት አስታውሳለሁ የጌታ ምሕረት ለዘላለም ነው።" መዝ፡ 102፥17
без подписи
የተመረጠ : ታማኝ : አገልጋይ : አረጋዊው : ቅዱስ : ዮሴፍ #ሐምሌ_26 ቀን መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ጠባቂ ሆኖ ሲያገለግላት የቆየው በተወለደ ጊዜም ቅዱሱ መልአክ መጥቶ ለወላጆቹ ‹‹ ይሆናል ›› ተብሎ የተነገረለት አረጋዊው ጻድቁ ዮሴፍ በክብር ያረፈበት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ነው ። #አረጋዊ_ዮሴፍ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ከቤተ ዳዊት ሲሆን አባቱ ያዕቆብ ይባላል እግዚአብሔርን የሚፈራ ለሰው የሚራራ ደግ ሰው ነበር ድግር ጠርቦ ጥርብ አለዝቦ ሽጦ ይኖር የነበር ጻድቅ ሰው ነው ። #አረጋዊ_ዮሴፍ ያዕቆብ ፣ ዮሳ ፣ ስምዖን ፣ ይሁዳ የተባሉ አራት ወንዶችና ሶስት ሴት ልጆች ነበሩት ሚስቱ ከሞተችበት በኋላ አይሁድ በእመቤታችን ላይ በጠላትነት ተነስተው ከቤተ መቅደስ ትውጣልን ባሉ ጊዜ « ልማ በሥሉስ ጥፋ በሥሉስ » እንዲሉ በሶስት ነገር ተመስክሮለት እመቤታችንን ወስዶ ከቤቱ አስቀምጧታል ። #አረጋዊ_ዮሴፍ ታማኝ አገልጋይ በመሆን ብዙ ዘመን ከእመቤታችንና ከጌታችን ጋር በረሃ ለበረሃ ሲንከራተት ኖሯል ይህም ጻድቅ አረጋዊ እመቤታችንና የተወደደ ልጇን መድኃኔዓለምን በእጆቹ ሥራ ይመግባቸው ነበር ። #አረጋዊ_ዮሴፍ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ከእመቤታችን ጋር ሆኖ በደስታዋም በኀዘኗም ጊዜ አልተለያትም ጌታን በወለደች ጊዜም ዳስ ሠርቶ ግርግም አዘጋጅቶ አገልግሏታል ። #አረጋዊ_ዮሴፍ እመቤታችን በስደቷ ወቅት ልጇን ከሄሮድስ ሰይፍ ለማዳን ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ረሀቡን ጽሙን ሐሩረ መዓልቱን ቁረ ሌሊቱን ታግሣ በረሀ ለበረሀ በተንከራተተችበትም ወቅት አልተለያትም ነበር ፡፡ ከስደት ከተመለሱም በኋላ ጌታችንን እንደ አባት ሆኖ አሳድጎታል አይሁድ ጌታን « ወልደ ዮሴፍ » ማለታቸው ቅሉ ይህን ይዘው ነው ። #አረጋዊ_ዮሴፍ በመጨረሻ የእድሜ ዘመኑ ታሞ ሊያርፍ ሲል ጌታችን ተገልጦለት ‹‹ ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ ? ›› ቢለው ‹‹ በሞትኩ ጊዜ ሥጋዬን በምድር አታስቀርብኝ ›› አለው ። ጌታችንም ‹‹ እሺ እንዳልክ ይሁንልህ ›› ብሎት መላእክቱን አስከትሎ ደቀ መዛሙርቱን በደመና አምጥቶ ካለበት ሰብስቦ ክብርት ነፍሱን ከሥጋው ለይቶ በእጁ ዳሶ እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ አድርጎ ሐምሌ 26 ቀን በክብር እንዲያርፍ አድርጎት ሥጋውን ብሔረ ብፁዓን አስገብቶለታል ። የአረጋዊ : የቅዱስ : ዮሴፍ : በረከቱ : ከእኛ ከሁላችንም : ጋር : ለዘላለም : ትሁን🙏
без подписи
#ሐምሌ_25 ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ድንቅ ተአምር ያደረገበትና ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ልደቱም በዚሁ ዕለት ነው፡፡ መርቆሬዎስ ማለት « የአብ ወዳጅ ማለት ነው፣ እንደገናም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ » ማለት ነው። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከአረማዊነት ወደ ክርስትና ከመጡ ቤተሰቦች ተወለደ። ለጣኦታት አልሰግድም አምላኬን አልክድም ብሎ ዓለማዊ ሥልጣኑን የናቀ ቅዱስ ነው። ለእግዚአብሔርና ለሰማያዊው መንግሥት የቀናው ቅዱስ መርቆሬዎስ የንጉሡን ትዕዛዝ አልተቀበልክም ተብሎ ተይዞ በብዙ ተሰቃየ። በንጉሥ ዳኬዎስ ትዕዛዝም ህዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ መስዋዕትነትን ተቀበለ። በኋላም የቅዱስ መርቆሪዎስን አንገቱን ቆርጠው ከገደሉት በኋላ ፈረሱ ለ7 አመት ወንጌልን አስተምሯል። ጌታችን ቅዱስ መርቆርዮስን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጥሎ ሁለተኛው ሊቀ ሰማዕት ተደርጎ ተመርጧል። የቅዱስ ፡ መርቆሬዎስ ፡ ሰማዕት ፡ በረከቱ አማላጅነቱና ፡ ቃል ፡ ኪዳኑ ፡ ከሁላችንም ፡ ጋር ፡ ይሁን
ከ90 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬው ቀን... ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም.! ቁመታቸው ረዘም ያለ - ፊታቸው ዘለግ ያለ - መልካቸው ጠየም ያለ - ዐዋቂነታቸው እና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ -ጥቁር እና በጭቃ የተለወሰ የጵጵስና ካባ የለበሱ ታላቅ አባት ችሎት ፊት በአደባባይ ቀርበዋል - አቡነ ጴጥሮስ! “አቡነ ቄርሎስ የጣሊያንን መንግሥት ገዢነት ሲቀበሉ እርስዎ ለምን አመጹ? ለምንስ ብቻዎን አፈንጋጭ ኾኑ?" ሲል ዳኛው ጠየቃቸው፡፡ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስም በቆራጥነት እና ሀገሩን እና ሃይማኖቱን እንደሚያፈቅር በሚያስታውቅ አንደበት “አቡነ ቄርሎስ ግብጻዊ ናቸው ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ! ኃላፊነትም ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚኽ ስለሀገሬና ስለቤተክርስቲያኔ እቆረቆራለኹ፡፡ ከዚኽ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደወሰናችኹ አውቃለኹ፡፡ ስለዚኽ በእኔ ላይ የፈለጋችኹትን አድርጉ ግን ተከታዮቼን አትንኩ" አሉ፡፡ ይኽንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲመለከት ታዝዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልዕክት አስተላለፉ! “አረማዊ የኾነው የፋሺስት መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው እንጂ በጎ ለመሥራት ስላልመጣ ለዚኽ ግፈኛ አትገዙ!!! ስለውድ ሀገራችኹ - ስለቀናች ሃይማኖታችኹ ተከላከሉ!!! ነጻነታችኹ ከሚረክስ ሙታችኹ ስማችኹ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብርን ታገኛላችኹ!!! የኢትዮጵያ ሕዝብ ኾይ! ለጠላት እንዳትገዛ አውግዣለው!!! የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትኹን!!! በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተረገመች ትኹን!!!" ወዲያውም የእረፍታቸው ሰዓት መድረሷን ስለተረዱ ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ፡፡ ምንም ፍርኃት በገጻቸው አይነበብም ነበር፡፡ የሞታቸውን ፍርድ የሚያነበው ጣልያናዊ ዳኛ ግን ልቡ በሽብር ተሞልቶ ፍርዳቸውን ሲያነብ ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ የፈረዱባቸውንም ዳኞች ጸልየው በመስቀል ባረኳቸው፡፡ ከዚያም በስምንት ጥይት ተኩሰው መቷቸው፡፡ ነገር ግን በስምንቱ ጥይት ባለመሞታቸው ሌላ ወታደር ተጠርቶ በሦስት ጥይት የራስ ቅላቸው ላይ መትቶ ገደላቸው። አስክሬናቸውንም ማንም እንዳይወስድ በምሥጢር ተደብቀው ተቀበሩ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥም በየቤቱ ለቅሶ እና ዋይታ ኾነ፡፡ በዛሬው ዕለት ሰማዕትነትን የተቀበሉት የአባታችን የብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ረድኤት በረከት ይደርብን! ጽናታቸው አርአያ ኾኖን እስትንፋሳችን ለኾነችው ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በእምነት እና በጽናት እንድንቆም ያድርገን!!