tgindex
የፍቅር ጥቅስ

የፍቅር ጥቅስ

Статистика

እንኳን ፍቅር ወደ ሆነው የፍቅር ጥቅስ ቻናል መጣችሁ በዚህ ቻናል ❤ስሜትዎን የሚገልፁ #የፍቅር ጥቅሶች ❤አጓጊ #የፍቅር ታሪኮች አንዲሁም ግጥሞች ያገኙበታል ይመቻችሁ

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
14
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
1 811
+6 за 5 дн.
Сутки
+3
+0,17%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
304
29 постов
Вовлечённость
16,8%
к подписчикам
Постов в день
2,0
всего 29
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
221
1/48двое суток
253
1/72трое суток
273

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • በተሳሳተ ባቡር ውስጥ ካለህ አቅራቢያህ ባለው ማቆሚያ ውረድ።ለመውረድ እረጅም ጊዜ በፈጀብህ ቁጥር የመመለሻ መንገዱ ውድ ይሆንብሃል። እና ምን ለማለት ነው አንድ የማያስፈልግህን ሰው ከህይወትህ ለማስወጣት ጊዜ በወሰድክ ቁጥር መውጫህን እያጠበብክ ትሄዳለክ።

  • ♥️ተማሪዋ♥️ 🌹...ክፍል 21...🌹 አይ ኤፏ እኔ የባረኩትን ዳቦ ያልሽው ነገር ግን የመጨረሻ ነው የተመቸኝ ግንኮ ኤፋ አንተ ትባርካለህ እንጂ አትበላም ኤፊ ሙት አንተ ጀማምረህ የተውከውን ወይ የባረከውን እንጂ የቀመስከውን ግን ነክቼ አላውቅም!" አለኝ ሳቅ እየተናነቀው። "በናትህ ኪያ ተወኝ በቃ፣ እራስህ ነህ ነካክተህ ወደዛ የወሰድከኝ እንጂ  እኔ ስላለፈ ነገር የማውራት ፍላጎቱም የለኝም ።" "እሺ አሁን ስለተፈጠረው ነገር በቁም ነገር እናውራ በቃ እስቲ ያለህበትን ሁኔታ በግልፅ በተን ተንተን አድርገህ ንገረኝ " "ትቸዋለሁ!" "ለምን ኤፊ?" "እህም ገና ፍቅር ያዘኝ ስልህ ጥሩንባ ይዘህ መለፈፍ የቃጣህ ፣ ሙሉውን ስሰማ እማ በድሬ ትቪ አልያም በድሬ ኤፍ ኤም ለሙሉ የድሬዳዋ ሰው ካልተናገርኩ ማለትህ የማይቀር ነው። እኔ የተለወጥክ መስሎኝ እንጂ ላንተ ሚስጥር ብሎ ማውራት  እኔን ለማብሸቅ ተጠቀምበት እንደማለት እንደሆነ እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም ጓደኛችህ የሚያውቁት አመልህ ነው!" ስለው ኪያም በተራው ተናደደደ። እስካሁን ሳቅ ሳቅ የሚለው ፊቱ ደመነ። "አቦ እንግዲህ አታብዝዛዋ ሀይ ኤፊ ደሞ ፣ እስቲ ነገረኝ አንተ ቁም ነገር ኖሮህ ያውቃል እንዴ ? ሲጀመር ከየትኛዋ ሴት ጋር ነው ቁም ነገር ኖሮህ የሚያውቀው፣ ነካክቶ መተው አይደል እንዴ አመልህ ። ምነው ከሌላ ሰው ጋር የምታወራ መሰለህ እንዴ  ከልጅነት እስካሁን አብሮህ ከኖረ ከኔ ከኪያ ጋር እኮ ነው እያወራህ ያለኸው። እስቲ አንተ ሚስጥር ወይ ቁም ነገር ብለህ የነገርከኝን አንድ ነገር ንገረኝ ፌዘኛ እድሜ ልክህን ስታፌዝ አደል እንዴ የኖርከው !" አለኝ። ወደኃላ ሄጄ ማሰብ ጀመርኩ። ክያ እውነት አለው። በቁም ነገር ያፈቀርኩት ቃልዬን ብቻ ነው። "ለማንኛውም ልነግርህ ያሰብኩትን ትቸዋለሁ!" "አቦ ተወዋ ታድያ !" ብሎኝ ወጣና አራት ቢራ ይዞ መጣ። አንዱን ለኔ አንዱን ለራሱ ከፍቶ መጠጣት ጀመረ። ለብቻዬ በሀሳብ መወዝወዙ ቢቀልልኝ፣ ለኔ ያልታየኝን ለኪያ ቢታየው፣  እኔ ቃልዬን ማወቅ ከብዶኛል ፣ ቃልዬ ባህሪዋ እንዲህ ነው ብሎ አንድ ቦታ  መርጋት ተስኖኛልና ለኪያ ስለ ቃልዬ ስነግረው ፣ ከነገርኩት ነገር ተነስቶ ስለቃልዬ ያሚኖረው  መረዳት ምን ሊመስል እንደሚችል ፣ እንደጋደኛ እንደውንድምም እንዲነግረኝ ፈልጊያለሁና ለትንሽ ደቂቃዎች በዝምታ ከቆየን በኋላ በራሴ ፍላጎት  የኔን እና የቃልዬን የስድስት ወር የፍቅር ታሪክ ድንገት ከተዋወቅንባት ከዛች ምሽት ጀምሬ እስከዛሬዋ ቀን ያለውን ፣ የሚሰማኝን ስሜት፣ የሷን ባህሪና ሁኔታ ጭምር አንድ በአንድ በግልፅ ነገሩክት። "እውነተም እየቀለድኩ መስሎት ነበር እንዴ ?" እስክል ድረስ በተገረመ ፊቱ ማውራት ከጀመርኩ ጀምሮ ቢራውን አንዴ እንኳን ሳይጎነጭ በተመስጦ ሲያዳምጠኝ ቆየ። እንደጨረስኩ በመዳፉ ፊቱን ጠራረገ፣ በረጅሙ ተንፍሶ ወደጀርባው ጋለል ብሎ ግርግዳውን ተደግፎ ቢራውን በማንሳት አንዴ ተጎነጨና ••• "አቦ ይገርማል!" ብሎ ባዶው ወለል ላይ አይኑን ተክሎ ትንሽ ቆየና ፎቶዋን እንዳሳየው ጠየቀኝ ከሞባይሌ ላይ አሳየሁት። "ዋው አስማት የሆነ ውበት ነው ያላት!" አለ። "አስማት አስማት አስማት የሆነ ውበት ምን ማለት ነው?" አልኩት የእውነት አስማት የሆነ ውበት ምን አይነት እንደሆነ ስለማላውቅ ነው የጠየኩት ኪያ ግን "አቦ ኤፍዬ አታልምጣ በቃ የሚገርም ነው ለማለት ነው " አለኝና አሁንም ወለሉ ላይ ተትክሎ ሲያስብ ቆየና "ወንዶች ስንባል ግን እንገርማለን   አይ ወንዶች " አለ ። መልስ አልሰጠሁትም። "አብዛኞቻችን ማለት ትችላለህ በቃ በፍቅር የምታጦዘን ሴት ልክ እንደቃልኪዳን አይነት ሴት ነች ። እውነቴን ነው እኔ ከታዘብኩት  አፈቀርኩህ ብላ ስሜቷን የምትገልፅ ፣ ናፈቅከኝ ብላ በየደቂቃው የምትደውል ፣ ሲብስባት ፍለጋ የምትመጣ፣ ለመገናኘት አንተ እንገናኝ እስክምትላት የማትጠብቅ ፣ ልታገኝህ ስትፈልግ የምታገኝህ፣ ልትስምህ ስትፈልግ የምትስምህ ሌላም ሌላም የሚሰማትን ሁሉ ይንቀኛል ይሰለቸኛል ሳትል  ፍቅሯንም ድርጊቷንም ስሜቷንም በግልፅ የምታሳየን ሴት ላይ መንጠባረር ያምረናል አደል? ሌሎቹን ተዋቸው መክሊትና ቤትን የተንጠባረርክባቸው ለዛ ነው አደል?" "ኪያ ኪያ ኪያ እባክህ ከኔ ጋር በሰላም ማውራት ከፈለክ ስለቃልኪዳን ብቻ እናውራ ምነው አንተ ከነዚህ ሴቶች አናት ላይ አልወርድ አልክ እኔ እንኳን አናታቸው ላይ  ምናቸውም ላይ ተፈናጠህ መዋል ማደር ትችላለህ ግን ኪያ በቃ ስለነሱ እኔ ፊት አታውራ!" "ኪኪኪ እሺ ቱግ አትበላ ምንድን ነው እኔ እነሱን ያነሳሁት እነሱ ያው የድሬ ሴቶች ግልፅ ናቸው። በመልክ ያው ከቃል ኪዳን አያንሱም፣   በነሱ እና በቃል ኪዳን መካከል ያለው የባህሪ ልዩነት በአዱገነትና በድሬ ሴቶች መሀል ያለውን ልዩነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል ለማለት ነው ለምሳሌ •" ብሎ ሊያብራራልኝ ሲሞክር ምን ለማለት እንደፈለገ ስለገባኝ ደሜ ፈላ። ሳይጨርስ አቋረጥኩት። "ኪያ እኔ የሚያስጠላኝና ብዙ ሰው ላይ የማየው ስህተት ምን እንደሆነ ታውቃለህ?" "አላውቅም!" "በአንድ ወይም በውስን ሰዎች ሁኔታ ላይ ተነስቶ ድፍን የከተማውን ሰው ለመፈረጅ የሚንጠሯሯጥ  ሰው በጣም ያስጠላኛል። መክሊት እና ቤቲ እዚህ መጥተው ስለተነፋረቁ ድፍን የድሬ ሴቶች ነፍራቃ ናቸው ማለት ነው?   ቃል ኪዳን የማትያዝ የማትጨበጥ ወፍ ስለሆነች ድፍን የአዱገነት ሴቶች ወፍ ናቸው ብሎስ መደምደም ይቻላል? እንደዛ ማሰብ  ሁላችንም እንደ ጣት አሻራችን የተለያየ ባህሪ እንደለን ካለመገንዘብ  ወይ ከመጀዘብ የመጣ ድፍረት እንደሆነ  ነው የሚገባኝ። ያንተ አክስት መንታ ሴት ልጆች አሏት አደል?  የሁለቱ ባህሪ ግን ምን ያህል እንደሚለያይ እኔም እንተም እናውቃለን ።ኪያ ንፅፅሩንም ውድድሩንም ተወውና በቃልዬ ዙርያ ብቻ የምትለኝ ነገር ካለህ በለኝ፣  ከለልህ በቃ ይህን ጉዳይ እንተወውና ሌላ ነገር እናውራ" "እሺ ኤፊ ቆይ ከቃል ኪዳን ጋር የመጀመሪያ ቀን እዛ ሆቴል አድራችሁ ጥዋት ላይ ካወራችሁት ወሬ ምን ተረዳህ እኔ እንኳን አሁን ስትነግረኝ አንድ ነገር ተረድቻለሁ አንተስ?" አለኝ። " ያው ከዚህ ቀደም ከሌላ ወንድ ጋር ምንም ግኑኝነት እንዳልነበራት እና ድንግል ልትሆን እንደምትችል ፍንጭ ይሰጥ ነበር የዛን ቀን አውራሯ ቢሆንም ከአንደበቷ እንዲህ ነኝ የሚል ነገር ስላልወጣ ከመጠራጠር አያልፍም ስለዚህ እርግጠኛ መሆን ይከብዳል!" "አይ ኤፊዬ በአንደበቷ እንድትነግርህ ለምን ትፈልጋለህ? አንደበቷ ምን ያደርግልሀል ? ከንግግር በላይ ማረጋገጥ የሚቻልበት ወሳኝ መንገድ አለኮ ይልቅ እዛ ላይ ፍጠን!" "ማለት ምኑ ላይ የምፈጥነው?" "ኤፍሬም ደሞ  እንደህፃን ልጅ ይሄ ኡፉ ነው እሺ ያቃጥላል እንዳትነካው ተብሎ ካልተነገረኝ  የምትለው ነገር አለህ ። በቃ ማድረግ ያለብህን አድርጋ ምን ብዬ እንድነግርህ ነው የምትጠብቀው?" "ኪያ ደሞ  ዞረህ ዞረህ  ከሱ አናት ላይ አትወርድም እኔ እኮ ቃልን አፈቅራታለሁ። እስከመጨረሻው የኔ እንድትሆን እፈልጋለሁ ፣ ዋናው ፍላጎቴም ያ ነው ። እሷም ውስጤ ያለው ፍላጎት ገላዋን የመሻት ግዚያዊ ስሜት ሳይሆን  ዘላቂ አብሮነት  እንደሆነ እንድትረዳኝ ነው የምፈልገው። በሷም ውስጥ ያ ፍላጎት እንዲኖር ነው ምኛቴ የተቸገርኩትም በኔ ልክ እሷም ያንን የኔን ምኞት የመኖር ፍላጎት እንዳላት ማወቅ ነው ። ክፍል 22 በቶሎ እዲለቀቅ ላይኩን በዛ አርጉት ቤተሰብ 🌹🌹♥️♥️

  • አቧራ ገብቶብኝ አይኔን ስጨፍን የጠቀስኳት መስሏት ጠቀሰችኝ... የሰፈራችን አቧራ ጥቅም ላይ ይውላል ብሎ ማን አስቦ ያቃል🤔🤔

  • ♥️ ተማሪዋ ♥️ 🌹...ክፍል 20...🌹 የሳቁ ድምፅ  ያለንበትን ቤት ጣራ ገንጥሎ እቴቴ ቤት ድረስ የሚሰማ መስሎኝ እስክደነግጥ ድረስ ሳቀብኝ። ምን ሳቀብኝ ቆሌዬ እስኪገፈፍ አንባረቀብኝ ። "ቆይ ከሳቅክ ስንት ግዜ ሆነህ ኪያ? ረዥም ግዜ ሆኖሀል እንዴ? " አልኩት ከሳቁ ረገብ እንዳለ። "ካካካ •••ገና መች ተሳቀና ኤፊዬ በዚህ ጉዳይማ ቢያንስ በትንሹ ሶስቴ ከልቤ እንደምስቅ እርግጠኛ ነኝ!" " ለምን አመት ሙሉ አትስቅም ለደንታህ ነው ባክህ!" "ኪኪኪኪ የምሬን ነው ኤፊዬ አንተ አሁን መሳቄ ነው አደል የገረመህ....? ለቤቲ ስነግራት ከዚህ በላይ ነፍራለሁ ፣ ለመክሊት እማ ይህን ዜና ስነግራት በሳቅ ጧ ብላ ስትፈነዳ አብሪያት እንዳልፈነዳ ነው የምፈራው ካካካ•••!" ሲለኝ "ድሮም ይሄን ነበር የፈራሁት !" የሚልለው ዘፈን ትዝ ያለኝ ። የኪያ እንደዚህ ማሰብና  ማለት አብግኖኝ እኔ እራሴ በንዴት ጧ ልል ምን ቀረኝ? ምንም። ቤቲና መክሊት አስራ ሁለተኛ ክፋል እያለሁ በተለያየ ግዜ መልካቸውን አይቼ ፍቅር ብጤ ልጀምር ልሞክር ብዬ ብቀርባቸውም  ፍቅር እራሱ ካልያዘኝ በቀር እኔ ስለፈለኩ ብቻ አሳድጄ ልይዘው  አልችልምና ሳንግባባ ቀረን ፍቅር በግዢ አይመጣ ምን ላድርግ እነሱ ሙዝዝ ንዝንዝ ሲሉ እኔ ፍዝዝ ድንግዝ  ችላ አልኳቸውና ተለያየን። ያው ሴቶች ደሞ ችላ ሲባሉ እልህ ይሁን ፍቅር ብቻ የሆነ ሙጫ የሚያደርጋቸው ነገር አለ አይደል ሰፈር እና እቤት ድረስ እየመጡ መግቢያ መውጫዬን ሲዘገብኝ  እኔ ደሞ ጭራሽ እነሱን ባየሁ ቁጥር እሩጥ አምልጥ ይለኝ ጀመር። ውስጤ እሩጥ፣ ተደበቅ፣ የለም አስብል፣ እያለ ካዘዘኝ ደግሞ ገና ሳያቸው ከመሸሽ፣ከመደበቅ፣ እያለሁ የለም ከማስባል በስተቀር ምርጫ የለኝም። እኔ ሳመልጥ ያላቸው እጣ ፋንታ ከጓደኛዬ ከኪያ ጋር መፋጠጥ  ሆነ፣ መፋጠጡን ይፋጠጡ  ነገር ግን ኪያ አጋጣሚውን ይጠቀምበታል። ኪያ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን በመጠቀም በመላ ጓደኞቹ የተመሰከረለት እና ሰርተፍኬት የተበረከተለት ልጅ ነው። እሱ ተዋውቆ ከጠበሳቸው ሴቶች ይልቅ የሚበዙት በጓደኞቹ ምክንያት የተዋወቃቸው ናቸው። የኪያ መጥበስ አንሶላ ስር እስከመደባበስ ነው ረጅሙ እድሜ።  በኔ ምክንያት ኪያን ማግኘት ከጀመሩ በኃላ ንግግራቸው ኤፊ የት ሄዶ ነው? ለምንድን ነው ስልኬን የማያነሳው? ከሚል ጥያቄና ብሶት ወደ  መሞላፈጥ ትንሽ ቆይተው "አማነው ኬያዬ? አንተም ዘጋኸኝ ምነው?"  ወደሚል መቆለማመጥ ይቀየራል። ኪያም የሚለውን ይላል ቀመሩን ይቀምራል። ትንሽ ቆይቶ የራሱን መረብ ይዘረጋል፣ የቻለሁን ያህል አጥምዶ እሱም ይጠመዳል። ትንሽ ቆይቶ ይጣዳል። እኔ የተውኳት ሴት ላይ መጣድ ልማዱ ነው። ያ ግን አይመለከተኝም። አሁን ኤፍሬምን  ፍቅር ጥባጥቤ እየተጫወተበት ነው ብሎ ስቆ መክሊትን ሊያስቅብኝ ሲጣደፍ ሳየው ግን  ነደድኩ ስማ ኪያ አንተ ሳቅ ግድ የለም ለነሱ ካወራህ  ግን ከኔ ጋር የመጨረሻችን ነው እወቀው!" "እንዴ ኤፊ ምን ችግር አለው ። ምነው እነሱ መስማታቸው እንዲህ አሳሰበህ ፍቅር ያዘህ እንጂ ስሰርቅ አልተያዝክ ፣ መናገሬማ  አይቀርም ሁለቱም እንደዛ አፍቅረውህ እየየ ሲሉ ስታላግጥባቸው እነሱን የማፅናናት ሀላፊነት እኔ ላይ ነበር የወደቀው። በተለይ መክሊት " ኤፍሬም በኔ ሳይሆን በፍቅር ላይ እንደቀለደ አንድ ቀን  ፍቅር ሲቀልድበት ያሳየኝ ይሆናል ፈጣሪ"  ስትል ኧረ ሀሳብ አይግባሽ ኤፍሬም ፍቅር ይዞት እንዳየሁ እኔ እራሴ  እነግርሻለሁ ያኔ አንቺ በተራሽ ትስቂበታለሽ  ብዬ ቃል ገብቻለሁ። ቃል ደሞ ቃል ነው መክሊትማ መስማት አለባት ። አሁን ትልቁ ነገር ያልከኝ ነገር እውነት መሆኑን ማረጋገጥ ብቻ ነው። ግን የምርህን ነው አደል?  እውነት ፍቅር እያንደፋደፈህ ነው••? ግን ማን ትሆን ልጅቷ በናትህ ? የእውነት ጀግና ነች! እማዬን ነው እምልህ አቦ ባገኛት እሸልማታለሁ።ግን የምር ፍቅር ያዘህ ኤፊ•••?" "እንጃልህ! ቆይ አንተ ግን ምን አይነት ጓደኛ ነህ •••? ባንተ ቤት መቀለድህ ነው አደል? ስማ መቀለድ ሁሌ አያስቅም እሺ የምትቀልድበትን ቦታ እና ሁኔታ ካልመረጥቅ የሚያሸማቅቅበትም ግዜ አለ። እኔ በማይቀለድ ነገር ስትቀልድ እጅ እጅ ነው የምትለኝ።  ስድስት ወር ሙሉ ትንፍሽ ሳልልልህ የቆየሁትም ለዚህ ነበር። ላንተ መንገሩ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አውቃለሁ የተለወጥክ የበሰልክ መስሎኝ ነበር !" "አቦ ኤፊ ደሞ ምንድን ነው እንደዚህ ማካበድ ፍቅር አመልህን  ቀየረው እንዴ አባቴ ተረጋጋ እንጂ ፣ ቆይ አንተ ፍቅር ያዘኝ ማለትህ  ያዘኝ ብቻ ሳይሆን አንደፋደፈኝ ስትል እንደመስማት የአመቱ ምርጥ ቀልድ አለ እንዴ ? እና አንተ ስትቀልድ እኔ ብቀልድ ምን ክፋት አለው በዛ ላይ ቃል ገብቻለሁ" "ዝም በል ባክህ ወደዛ ቃል ገብቻለሁ ምናም ይላል እንዴ መክሊት ከኔ ጋር ስትጣላ በአፅናኝ ሙድ ገብተህ እትት እያልክ ቆይተህ የት ይዘሀት እንደዋልክ እና ምን እንዳደረጋችሁ የማላውቅ መሰለህ እንዴ•••? እኔ ግን እኔ ያልፈለኩትን እና የተውኩትን ነገር ሌላው ሲያነሳው የምንጨረጨር ተራ ሰው ስላልሆንኩ ስለዚህ ጉዳይ መስማቴን ላንተ እንኳን አልነገርኩህም ። ባንተ ቤት ጉድህን አላውቅም ቃል ስለገባህላት ነው አደል የምትነግራት? ሃሃሃ  በዚህ ሰበብ ጠርቻት የማደርገውን ላድርግ አትልም ወራዳ። ቆይ ቆይ ካሁን በኋላ ያቀመስኩህን ነገር የምደግምህ ስለኤፍሬም ስታወራልኝ ነው ብላሀለች እንዴ? ለምን እራስህን ችለህ አትንቀሳቀስም ሁሌ እንደዚህ አይነት ሙድ አይደብርህም እንዴ?  እውነትም ጣሰው በቃ አንተ የማትጥሰው ህግ የለም ማለት ነው? ያልተፃፈም ቢሆን የጓደኝነት ህግ የሚባል ነገር አለ እሺ ትክክለኛ ጓደኛ ብትሆን ተዋትም አብሯት ሆነም  የጋደኛህ ከነበረች ሴት ጋር አንሶላ መጋፍፍ በዘጋህ ነበር። ደሞ ቃልዬን ባገኛት ሸልማት ነበር ስትል አታፍርም አብጄ ነው ላንተ የማስተዋውቅህ !" ስለው ኪያ ሆዱን ይዞ ፍራሹ ላይ እየተንደባለለ ሲስቅ በንዴት ከፊቴ ያለውን ባዶ የቢራ ጠርሙስ አንስቼ ወገቡን ልለው ምንም አልቀረኝም። ስቆ ሲወጣለት •••" መስማትሽን ግን በዚህ አጋጣሚ መተንፈስሽ ደስ ይላል ዛሬ ነገ ሰማ እአልሰማ እያልኩ ከመሳቀቅ ገላገልሽኝ ካሁን ወዲህ በነፃነት   ኪኪኪ•••! "ተው ባክህ አንተ ነህ የምትሳቀቀው ምነው እንዲህ ስታደርግ መክሊት የመጀመሪያህ ነች ምነው የመክብብን እና የአማረን ምን እንዳደረክ ረሳኸው እንዴ?" "ካካካካ እነሱ እኮ ጀንጅንልን ብለው ልከውኝ ነው በቃ ሴቶቹ አንዳንዴ አስጅኝጃኙን ሳይሆን ጀንጃኙን የሚመርጡበት ግዜ አለ እኔ ምን ላድርግ? ካካካካ" ስለነሱ አያገባኝም አንተ ሲጀመር እኔ ያልባረኩትን ዳቦ በልተህ ታውቃለህ እንዴ ? ልማድህ እኮ ነው!" ስለው "ኧረ ኤፍ ፍቅር ስይዝ ምላስም ይረዝማል እንዴ ዛሬ አልቻልኩህም ኪኪኪኪኪ•••" ቃልዬ ትስቃለች፣ ጋደኛዬ ይስቃል •••በቃ አለም ሁሉ እየሳቀ ነው ማለት ነው! የኔ ጋር ብቻ ነው ሳቅ ምንጩ የደረቀው፣ ቆይ ፍቅር የሳቅ ምንጭ ያደርቃል እንዴ አልኩት ለራሴ። መልስ የለም ጥያቄ ብቻ። . . ክፍል 21 በቶሎ እዲለቀቅ ላይኩን በዛ አርጉት ቤተሰብ 🌹🌹♥️♥️

  • ትሁን ብዬ አልወደድኳትም።  በፈገግታዋ እያመነታሁ ፥ በወሬዋ እንደ ሀይቅ ደለል ሸርተት እያልኩ ገባሁ እንጂ። “ተስፋ አድርጐ ማጣት ያማል። አግኝቶ ያጣ ካላገኘ በላይ ያሳዝናል” ይላሉ። እውነትም ማፍቀር ፈሪ ያደርጋል! ይኸው “አይገደኝም” ያልኳትን ልጅ “እንዳላጣት” ማለት ጀመርኩ እንደያዝኳት ሁሉ. . . .🪞

  • 11 авг.21341из Amazing_factsETудалён 13 авг.

    ✍️ አንድ በእድሜ ገፋ ያለ ሽማግሌ ለሚስቱ ለሊት ላይ የማንኮራፏቷ ድምፅ አስቸግሮት ስሞታ ያቀርብላታል። ሚስቱም እኔ የለብኝም ብላው ትክድ ነበር። ይህ ነገር ሲደጋገምበት አንድ ለሊት ላይ ሆን ብሎ ይጠብቅና ለንግግሩ እውነታ ማስረጃ እንዲሆንለት ስታንኮራፋ ለመቅረፅ አሰበ። እንዳሰበውም ቀረፀና አስቀመጠው። ሌቱ ሲነጋ እሷ ተኝታ ነበር የቀረፀውን ሊያሳያት ይቀሰቅሳታል። እሷ ግን የመጨረሻ ለሊቷ ስለነበር መነሳት አልቻለችም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያቺ የማንኮራፋቷ ድምፅ ማታ ማታ ሁሌም ልክ እንደ አዝካሩን-ነውም እየደጋገመ ይሰማታል። ... 💔😪 ๏ ከቅርብ ወዳጅህ የሚመጣብህን ችግር ቻለውና እለፈው ምናልባት ይህ ችግር አለኝታ እንዲሆንልህና ያንን ሰው ከጎንህ እንዳታጣው የምትመኝበት ጊዜ ሊመጣ ይችላልና ። 🙏 ★📍• @SAK_ZONE1 •📍★

  • 11 авг.182из Amazing_factsETудалён 13 авг.

    የማርልቦሮ የትምባሆ ኩባንያ ባለቤት የሆነው ፊሊፕ ሞሪስ ከዚህ አለም በሞት የተለየው በዚሁ በራሱ ምርት ባመጣበት የሳምባ ካንሰር ምክንያት ነው በራሱ ምርት የሞተ የመጀመሪያው ሰው ተብሏል🫡 ★📍• @SAK_ZONE1 •📍★

  • 11 авг.1721из Amazing_factsETудалён 13 авг.

    💔ፍቅርሽ አስጨንቆኝ እንደዛ ስቸገር አንቺ ዘና ብለሽ ትበያለሽ በርገር🍔                #የሆንሽ_ጅብ_ነገር🐻

  • 11 авг.18621из Amazing_factsETудалён 13 авг.

    ይህን ታሪክ አንብባቹ ህይወታቹን ቀይሩ!😂😉የምር አነብቡት በናታቹ ልብ የሚነካ መሳጭ ታሪክ ጋፉር በህንድ ውስጥ ይኖር የነበረ የ- 4ኛ ክፍል ተማሪ ነው በትምህርቱ ግን ደካማ ነው። አስተማሪው ክላስ ውስጥ በጣም ትጮህበታለች 😡 እንዲያሻሽል ትመክረዋለች አልፎ 😒 አልፎም ትቀጣዋለች 😡 ከባሰም ትረግመዋለች 😩 . ጋፉር ቤት ውስጥም ከእናቱም ጋር አይስማማም አንድ ቀን ወላጅ ይጠራና እናቱ ት/ቤት ሄደው ለልጃቸው ክትትል እንዲያደርጉ ለመምህሯ ይነግራሉ መምህሯ ግን ጋፉር እድሜ ልኩን አንደማይለወጥ ለእናትየው ትነግራቸዋለች . በዚ ንግግር አዕምሯቸው የተነካው የጋፉር እናት በብስጭት ልጃቸውን ይዘው ወደ ሌላ ዴልሂ ምትባል ከተማ ይሄዳሉ። . ከ 25 አመት በኋላ የጋፉር የ4ኛ ክፍል መምህር የነበረችው የልብ ህመምተኛ ሆና ወደ ሆስፒታል ትሄዳለች ከዛ ግን ዶክተሮች ከባድ ቀዶጥገና እንደሚያስፈልጋትና በ ህንድ ውስጥ ዴልሂ የሚገኝ አንድ ሀኪም ብቻ ቀዶጥገናውን እንደሚሰራ ይነግሯታል። . ከዛም ዴልሂ በመሄድ ቀዶጥገናው ተደረገላት። ከማደንዘዣ ልክ እንደነቃች ከፊቷ በጣም ቆንጆ ፡ ሳቂታና ፡ መልከመልካም የሆነ ዶክተር ቁሟል። . እንዴት ነሽ? ብሎ ጠየቃት . እሷ ግን በመመለስ ፋንታ እጇን እያወራጨች ልትናገር ስትል መናገር የምትፈልገውን ነገር ሳትናገር በዛው አሸለበች 😱😔😢😱 . ዶክተሩ በጣም ደንግጦ ሰውነቱ በሙሉ ተንቀጠቀጠ ፡ ወዲያው ዞር ሲል . . ለካስ ጋፉር ሆዬ የጽዳት ልብሱን ለብሶ ማፅጃ ማሽኑንን ለመሰካት ብሎ ኦክስጅን መስጫ ማሽኑን ነቅሎባት ትንፋሽ አጥታ ነው የመረሸችው😂😔😂😔😂 . . . ጋፉር ዶክተር ሆኗል ብላችሁ ከጠበቃችሁ የህንድ ፊልም በጣም በጣም ታያላቹ ማለት ነው😭😂 ኸረረረረረ ሼር ሼር ሼር😂😁

  • 11 авг.25491из Amazing_factsET

    "መሽቶ ሲነጋ" ደሞ ነጋ ብሎ ሚያማርር ሳይሆን እሰይ ነጋ ብሎ ሚያመሰግን ልቦና ይስጥህ ❤️ አሜን በል 🙏

  • 11 авг.191из Amazing_factsETудалён 13 авг.

    ለፈገግታ 😁 የድሬዳዋ ልጅ ከአባቱ ጋ ሲጣላ Be like... ታያለክ ሰው በተሰበሰበበት ጫት አልቅምም ብዬ ባላዋርድክ እናቱ_Be_like ደስ ይበልህ ከዚ ቡሃላ ጫት መቃም ያቆምና አልባሌ ቦታ ይውልልሀል😭😅

  • ስናስታውሰው ፈገግ የሚያደርገን ትዝታ አለን🥰

  • ♥️ ተማሪዋ ♥️ ...            .            . 🌹...ክፍል 19...🌹 . . . . . . . ነገ እንገናኝ ስትለኝ ዛሬ ካላገኘሁሽ ሞቼ እገኛለሁ ብዬ ወትውቼ አምጥቻት አስከፍቼ ስለመለስኳት ከፋኝ። መስራት ብፈልግም ደበረኝ፣ ጭራሽ ድውክውክ አልኩ። ቀጥታ ወደ ቤቴ በማምራት ያን መጥፎ ስሜት እያባረረ ይገርፍልኝ ይመስል ሰፈር ውስጥ ካለች መደብር አምስት አባ ቢራ ገዛሁና ወደ ቤት ገባሁ። ፍራሼ ላይ ቁጭ ብዬ መጠጣት ጀመርኩ። ገረዥ የሚሰራው ጋደኛዬ እስካሁን አልገባም ። ነገር ግን መምጫው ደርሷል። ጋደኛዬ አባቱ "ጣሰው" እያሉ ሲጠሩት እናቱ ደግሞ "ኪያ" ብለው ነው የሚጠሩት። እኩያዬ ነው። እስከዚህ እድሜው እናቱ እና አባቱ በልጃቸው መጠሪያ ስም ላይ መስማማት አልቻሉም። እናቱ የልጄ ስም ኪያ ነው ስትል አባቱ ደግሞ ጣሰው ነው ብያለሁ ጣሰው ነው እንዳሉ እሄው ሀያምናምን አመት አንዳቸው በአንደኛው ስም ሳይግባቡ ቀጥለዋል። እሱም ኪያ እንጂ ጣሰው ሲባል ደስ አይለውም። አባቱ ጣሰው ብለው ሲጠሩት ሶስቴ ካልተጣርሩ ባንድ ጥሪ ብቻ አቤት ባለማለት በጣሰው ሲጠራ ደስ እንደማይለው ለመግለፅ ቢሞክርም አባትየው አቤት እስከሚላቸው  አስሬ ይጠርቷል እንጂ ተሳስተው እንኳን  ክያ ብለው አይጠሩትም። በአንድ እለት ግራ ግብት ብሎት " ኤፊ !  አባዬ ግን እዚህ ስም ላይ መጭጭ ያለበት ምክንያት እንቆቅልሹ መች እንደሚፈታልኝ ነው ግራ የገባኝ !" አለኝ። ሳቄን ስጨርስ ••• "እንቆቅልሹን እኔ ልፍታልሃ! አልኩት። " ኤፊ ሙት እየቀለድኩ አደለም!  ። አቦ እስቲ አስበው የምጠራበት እኔ፣   ስሜን የመምረጥ መብት ያለኝ እኔ ፣ የሱን ካልፈለኩት እና እማዬ ባወጣችልኝ ስም መጠራት ከፈለኩ የሱ ሙጭጭ ማለት ሚስጥሩ ምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም!" "እኔ ገብቶኛል ልንገርሀ ምን መሰለህ አባትህ ከሁለት ልጅ በላይ የመውለድ ሀሳብ አልነበራቸውም  ማዙኳሽ ደግሞ አራት ልጅ የመውለድ ፍላጎት ነበራቸው ። ስለዚህ ፋዙካሽ እሷ አራት መውለድ ስለምትፈልግ  ላለማርገዝ አትጠነቀቅም ብለው ስላሰቡ የራሰቸውን ጥንቃቄ ለማድረግ  ካንተ በላይ ያሉት ሁለቱ ከተወለዱ በኋላ ከማሚ ጋር ግኑኝነት የሚፈፅሙት  ኮንዶም እየተጠቀሙ ነበር። አንተ ግን እንቢ እወለዳለሁ አልክና ኮንዶሙን ጥሰህ ወጣህ። እናትህ  አባትህ ሳይፈልጉ ስለተወለድክ ኪያ (የኔ) አሉህ ።   አባትህ  ደሞ የዚህ ልጅ ስም ከታሪካዊ አመጣጡ ጋር የተቆራኘ መሆን አለበት ብለው ስላሰቡ  ኮንዶም ጥሶ የተወለደ ልጅ ስሙ ማን መባል እንዳለበት ሲያስቡ ጣሰው የሚል ስም መጣላቸው። ተመቻቸው። " አልኩት ጋደኛዬ እንደዛን ቀን ሲናደድ አይቼው አላውቅም። ላብ በላብ እስክሆን አሯሯጠኝ። ግን አልያዘኝም። ከቆይታ በኋላ ስንገናኝ። " አላውቅም ስልህ እውነት መሰለህ እንዴ ? ሀይ አባዬ እንደዛ ብሎ ያወጣልኝ እኔ እስክወለድ በጣም ተቸግሮ ስለነበርና እኔ ስወለድ ችግሩ ስለተቀረፈ ችግሩን ጣሰነው ለማለት ነው ጣሰው በቀለ ብሎ ከራሱ ስም ጋር አዋህዶ ሲጠራኝ ደስ ይለዋል አለቀ ። አንተ ቀልድ ችግር የለውም  ኤፊ ይሄን ነገር በቀልድም መልክ ከኔ ውጪ ለሌላ ሰው ታወራና እንጣላለን ። አንተ እየቀለድክ ነው። ሰው ግን እውነት ነው የሚመስለው፣ እውነት መሰላቸው አልመሰላቸው ለደንታቸው ነው፣ ነገር ግን በተለይ እዛ የምሰራበት ገረዥ ውስጥ እንዲህ ብለህ ብታወራ እያበሸቁ ስራ አያሰሩኝም ፣ በተለይ ደሞ ያ ግልፍጥ ትዛዙ የሚባል ልጅ ይህን ቢሰማ ጭራሽ አይፋታኝም። አመቱን ሙሉ ለመጣው ሰው ሁሉ እያወራ ነው የሚያበሽቀኝ " አለኝ። ሁላችንም የሰፈር ጓደኞቹ ኪያ ብለን ነው የምንጠራው። አንዳንዴ በጣም ሲያበሽቀኝ አፉን ለማዘጋት። "ተው እንጂ ጣሰው!" አለዋለሁ ። ያኔ ወይ ዝም ይላል ወይ ሰድቦኝ ይወጣል። እኔና ጋደኛዬ ብዙ ግዜ የማንግባባው በሴት ዙርያ ነው እሱ ለሴት  ያለው አመለካከት እና የሚያራምደው ሙድ ከኔ ጋር ተቃራኒ ነው። እስካሁንም ስለቃል ያልነገርኩት ለዛ ነበር። ዛሬ ግን በቃል ዙርያ ባሰብኩ ቁጥር የሚሰማኝ ስሜት በራሴ ሀሰብ እና እስካሁን በመጣሁበት አካሄድ ትክክለኝነት እምነት እንዳጣ አድርጎኛልና ሲመጣ ልንገረውና የሚለኝን ልስማ ወይስ ይቅርብኝ ?  እያልኩ ስወዛገብ ቆየሁ። በዛ ሰአት እቤት ውስጥ ሊያውም ቢራ ይዤ በፍፁም አድርጌው አላውቅም። ኪያ  በሩን ገፋ አድርጎ ሲገባ••• ሁለት ተጠጥተው ያለቁ፣ አንድ የተጋመሰ፣ ሁለት ገና ያልተከፈቱ የቢራ ጠርሙሶች ከፊት ለፊቴ እንደተመለከተ አይኑን አሸት አሸት አደረገና•••• " እኔ አላምንም አንድ ነገር እማ አለ ኤፊ ምንድን ነው የሆንከው ••••?" አለኝ። ምን እንደምለው  ግራ ገብቶኝ ዝም ብዬ ሳየው•••• እንባ ይሁን ብሶት ፣ ስካር ይሁን ፍቅር ብቻ የሆነ  የሚተናነቅ ነገር ተናነቀኝ .. ምን እንደሆንኩ ለራሴ ግራ እስኪገባኝ እርብሽብሽ አልኩ። ዝም ስለው ጥያቄውን ደገመው። "ምንም አልሆንኩም!" አልኩት። "ኧረ ኤፊ በጤናህማ ስራ ትተህ ፣ በመሪው ፋንታ ቢራ ጨብጠህ ፣ እዚህ ቤት ውስጥ ብቻህን አትቆዝምም ነበር። እየተዝናናሁ ነው አትለኝም መቸስ መዝናናት ብትፈልግ የት እንደምትጠጣ ጠንቅቄ አውቃለሁ። ምን እንደሆንክ ባላውቅም የሆነ ሙድ ውስጥ እንዳለህ መጠርጠር ከጀመርኩ ቆይቻለሁ !" "ምን የተለየ ነገር አይተህ ነህ መጠርጠር ከጀመርክ የቆየኸው? "እንዴ ምን ያላየሁት ነገር አለ ኤፍዬ መለዋወጥህ ላንተ አልታወቀህም እንዴ? ስንት ወር ሆነህ  ከኔጋ ካወራህ? ስንት ወር ሆነህ  ዛሬ እሄን ያህል ሰራሁ ፣ ዛሬ እንዲህ አጋጠመኝ፣ ዛሬ እገሌን አገኘሁት ወይ እገኘሁዋት ብለህ ማውራት ከተውክ? ቆየህ እኮ  እኔ እቤት ውስጥ እያለሁ ከነመፈጠሬ ረስተኸኝ ሙዚቃ ከፍተህ ወይ አብረህ ትዘፍናለህ ወይ በሆድህ ተደፍተህ ታዳምጣለህ። እኔስ ስንት ወር ሆነኝ ኤፊን ምን አድርጌው ነው ብዬ ማሰብ ከጀመርኩ ? አንዳንዴ ብቻህን ሁላ ታወራለህ  በፊት አይደለም ለእቁቡ የሚጣል ለሌላ የሚተርፍህ ልጅ በየሳምንቱ ለህትህ የምትሰጣት የዕቁብ ብር እስክታጣ ገንዘብ ታጠፋለህ ። ባለፉት  አራት እና አምስት ወራት ውስጥ ከኔ ጋር የምታወራኮ ብድር መጠየቅ ስትፈልግ ብቻ ነበር ። ቆይ መለወጥህ ደመነፍሷዊ ነው እንዴ አልታወቅህም ? ቆይ ምን አስቀይሜህ ነው ግን ወንድሜ ለምን በግልፅ አትናገርም? ከመች ወዲህ ነው በኔና ባንተ መሀል ድብብቆሽ የተጀመረው?" አለኝ ። በረጅሙ ተነፈስኩና•••"ተለውጬ ሊሆን ይችላል ነገርግን ካንተ ጋር የተያያዘ አይደልም ። ኪያ ሙት የምሬን ነው ካንተ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም!" "እሺ መለወጥህን ማመንህ ነው ዋናው። ግን ለምን በምን ምክንያት ?" "ፍቅር እያንደፋደፈኝ ነው ባክህ ኪያ ወንድሜ የምሬን ነው ። በቃ ፍቅር ቁም ስቅሌን እያሳየኝ ነው !" ስለው... . . ክፍል 20 በቶሎ እዲለቀቅ ላይኩን በዛ አርጉት ቤተሰብ 🌹🌹♥️♥️

  • "እደውልልሃለሁ"  የሚለውን #text #እወድሃለሁ  ብዬ አንብቤው..... ቀኑን ሙሉ #ስሸኮረመም ዋልኩ አሁን እኮ ነው ማነበው 😭