- Последний пост
- 2 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🚀 ET Alchemist Trader 🇪🇹 🚀 📈 Forex ትሬዲንግን በትክክለኛ አቅጣጫ ጀምር! 🎁 በቻናላችን የምታገኙት፦ ✅ Free Funded Account እድሎች ✅ Free Forex Signals ✅ Market Analysis & Trade Setups ✅ SNR Trading Course (FREE) ✅ Risk Management Tips ✅ Trading Psychology & Discipline ✅ 24/7 support እና የትሬደሮች community 💯 አዲስም ሆነ ልምድ ያለው ትሬደር ከሆንክ ይህ ቻናል ለአንተ ነው። በነፃ ተቀላቀል እና የትሬዲንግ ጉዞህን ጀምር። 📲 Join Now: https://t.me/et_alchemist_trader 🔥 Trade Smart. Stay Disciplined. Grow Steady.
☝️THΣ ҜIΠG IS βΔCҜ🙌🔥 ❄️Wave መግባት ምትፈልጉ❄️ ⚠️Above 1k የሆናችሁ ⚡️እዲሁም ከ 5k ጀምሮ ያላችሁ አዲስ folder create ስላደረግን መመዝገብ ትቺላላችሁ 🔰ትንሽ ቦታ ነው ያለን ቶሎ ተመዝገቡ ✨️ @KINGS_WAVER ✨️ @KINGS_WAVER
ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ ፳፻፲፰ ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ ! 🌼🌼🌼 ~~🌼🌼🌼~~~ @yegtm_medbl
#የቀንድ_አውጣ_ኑሮ ✍️ይስማዕከ ወርቁ @yegtm_medbl
በየመን በደረሰው የመርከብ መስመጥ ለሞቱት ከ68 በላይ ኢትዮጵያውያን ሞት የተሰማንን ሀዘን እንገልፃለን! 🕯🕯🕯 @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~ እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ:: የበጎ ሰው ሀሳብ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር :: ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ ታረደ ነደደ ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ ፥ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው ፥ በርግጎ ሲሸበር በዚህ ምድር መኖር፥ አያስመኝም ነበር ፤ አዎ ለጊዜውም ቢሆን ግፍ ያደነዝዛል በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፥ ወደ ፊት ይጓዛል በልብ ሰሌዳ ላይ፤ ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፥ ሚስቱን ያስረግዛል :: ይቅርታና ምህረት ፍቅርና ህብረት ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፥ ቢሆን የሞት ሽረት ዳገት ይወጣሉ፥ በንጥፍጣፊ አቅም የመኖር ፍላጎት ዘመም ይላል እንጂ ፥ተገርስሶ አይወድቅም :: •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ #አዳምኤል ✍️Bewketu Seyoum @yegtm_medbl
#Scam_Alert 🚨 ሰላም የTech with Naty አባላት ሰሞኑን እይተስፋፋ ያለ ነገር አለ። እሱም ስካሚንግ ነው አሁን ደግሞ ፊቱን አዙሮ ወደ ነጋዴዎች መጥቷል። ♦️በዚ ግዜ አብዛኛው ሰው በ ካሽ ከመገበያየት ወደ የተለያዩ ዲጂታል ክፍያ መፈፀምያ ዘዴዎች ተጠቃሚ ሆኗል ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ብዙ ሌቦች በጣም ብዙ ሰዎችን ለማጭበርበር እየጣሩ ይገኛሉ። ከዚ ቀደም ትራንዛክሽን ሂስቶሪውን በ ፎቶ ሾፕ ኤዲት በማድረግ ይሰሩት የነበረን የማጭበርበር ስልት አሁን ደግሞ ዘዴውን ቀይረው የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ የሚመስል አፕልኬሽን በመስራት እና ትራንዛክሽን ሪፓርት በማውጣት ሰውን እያጭበረበሩ ይገኛሉ። ♦️ማንኛውም ሰው የሚላክለት screenshot ብቻ ተመልክቶ ትክክለኛነቱን ሳያረጋግጥ ምንም አይነት ግብይት እንዳይፈፅም ❗️ ♦️ትራንዛክሽን ቁጥር ይዞ ካጣራ በኋላ ወይንም ስልካችሁ ላይ ቴክስት እስኪገባ በትእግስት ጠብቃችሁ ብቻ የምታስረክቡትን አስረክቡ❗️ ♦️አጭበርባሪው ግለሰብ ሊያሳምናችሁ የሚችለውን ምክንያት ቢያቀርብ ከመቀበል ተቆጠቡ❗️ ይሄን መረጃ በማጋራት ሌሎችንም ከመጭበርበር ይታደጉ 🙏 Join & Share 👇 @techwithnaty @techwithnaty @techwithnaty @techwithnaty @techwithnaty @techwithnaty
•~•~•~•~•~ ለሰው ምድር አሳቅፋው ሽቅብ ያንጋጥጣል ምኞቱን ፍለጋ እቅፉን ይጥላል፡፡ ሰማይን አውርሰው ልቡን ለማግኘት ለካ ምንም ቢሆን ልብ አይታቀፍም ሆድ በተለካበት ተከፍቶ ቢከደን ተከድኖ ቢከፈት፡፡ ሙሉነት የማያውቅ አንስቶ ያስጣለው የሸክሙ ጌታ በፍለጋ ያኖራል የጠፋ እርካታ፡፡ •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ #የማይረካ_ልብ @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~ ማዘን ለኛ ነው ፣በባከነ ደቂቃ በራሳችን ግብን ለምናስቆጥር ፣ በህፃናቱ ሞት ላልደነገጥን ፣ ሞት በእርጅና መስሎን በንስሃ ላልጠበቅን ፣በስፍር እድሜ ለቀለድን፣ ነግ ለኔ ላላልን፣ሳንኖር ለሞትን፣ ሳይነጋ ለመሸብን፣ ብልጭልጩ እያታለለ ያጎደለን፣ ጠብ በሚል ስኳር፣እንደ በግ በአሞሌ ለተነዳን፣ ለኛ ነዉ ማዘን:-ሞት አፋፍ ላይ ለምንጨፍር ከእድሜ ቁጥር ላልተማርን ክንደ ብርቱን እያየነዉ ሞት ሲነጥቀዉ: ባለሀብቱን በገንዘቡ መችአፈረዉ:ዘረብዙን ከሰዉ መንጋ ሲነጥለዉ:ታዋቂዉን ስለ እዉቅናዉ አዋቂዉን ስለ እዉቀቱ መቼ ተወዉ:ባለ ስልጣን ለስልጣኑ አትለወጥ ሞት ከቀኑ ማልቀስ ለራስ ነዉ : ከዚህ ሁሉ ከአለም እዉነት ላልተማረ ማዘን ለራስ ነዉ:ለማይቀር ሞት ተዘጋጅቶ ላልጠበቀ ነብስ ይማር ለነብሴ •~•~•~•~•~•~••~•~•~•~ @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~ ችኩል ነፍሶች አሉ ጥቂት እውነት ይዘው ብዙ ያስባሉ ለውሸት ሰንኮፋቸው መሀላ ይምላሉ ያደናግራሉ የደናብራሉ! አይጣል ነው የእነሱ ነገራቸው ሁሉ አይጠብቅ አይላላ ገረጣህ ይሉሀል ምንም ሳያዩብህ ሳትጠቁር ሳትቀላ በል ታረቅ ይሉሀል ምንም ሳትጣላ የቸገረ ነገር የጠፋ ለመላ! •~•~•~•~•~•~•~•~•~ #ችኩል_ነፍሶች | አብርሃም ፍቅሬ @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ የሚያሳክክ ነገር እንዳይቀር አስታውሶ ስንቆርጠው ከፍ ይላል ጥፍር ተመልሶ •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ #ነብይ_አካል | ዮሃንስ ፍስሃ @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ ካ'ናት ስንወጣ ፀሐይ አመላቸው ፣ ማቅለጥ ማውረድ ላይተው "ቅቤ ተገፍቶ ነው አናት ላይ የወጣው " ፥ በማለት ተርተው ረግተን ቢያገኙን ፣ ቅቤ አረጉን ገፍተው። እስከመቼ ይሆን ቀልጦ ወውረድ ላይቀር ፣ ለመገፋት መርጋት ፍራሹ እሾህ ነው ፣ ብርድ ልብሱ ውጋት ጦርነቱ ችጋር ፣ ሀገሪቱ ስጋት ምን ላይ ተተኝቶ ፣ ይታለማል ንጋት?! •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ በላይ በቀለ ወያ @yegtm_medbl @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ አንጋጠሽ ወደ ላይ ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው !! አፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ መስኩ ከነጎርፉ ፥ ሰማይ ከነዶፉ ፥ ለጌቶች ተሽጦ አተር ነው እያሉ፤ አፈር ዘግኖ መፍጨት ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት ይህንን ማን ሰጦሽ ገና በልጅነት፤ ልጅነት አምልጦሽ፡፡ በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ በክራር ተማግሮ በቆመ ከተማ እምባሽ ቅኝት የለው ፤ ለሰው አይሰማ፡ ጠዋት የፎከረ ፤ ቀትር ላይ ሲረታ ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ ትናንት የበረታ ኑሮን ያህል ሸክም ፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡ ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡ •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ ላንዲት ማስቲካ ሻጭ ህፃን በእውቀቱ ስዩም @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~• ቃላት ተደርድሮ ሀሳብ ቢያመነጩ ሆሄያት ተጨምቀው ስንኝን ቢቋጩ የሀረግ ስብስብ ጥዑም ዜማን ቢረጩ ሰሚ አጠው ቢንጫጩ ፋይዳ ካላመጡ አንባቢን ካልቀጡ ትምህርት ካልሰጡ ሆሄያት ይቆጠብ ባዶ ገፁን አምጡ። •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ #ባዶ_ገጽ | በዮናታን @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~• እውነት ቤት ስትሰራ :- ውሸት ላግዝ ካለች ፣ ጭቃ ካራገጠች ፣ ሚስማር ካቀበለች ፣ ቤቱም አልተሰራም ፣ እውነትም አልኖረች ፣ •~•~•~•~•~•~•~•~• #የማይቻል_ነገር @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ ደመወዙን ቢጥል አንስተው ጠጡበት ባርኔጣውን ቢጥል ወስደው ደመቁበት ከዘራውን ቢጥል ተመረኮዙበት በሄደበት ሁሉ እየተከተሉ በጣለው ሲደምቁ በጣለው ሲያተርፉ ራሱን ሲጥል ግን አይተውት አለፉ፡፡ •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ በዕውቀቱ ስዩም @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ ከጨለመ አይደል... ኩራዝ ትዝ ሚልህ መሸት ሲል አይደል... የብርሃን ጥቅሙ የሚገለጥልህ ሲበርድህም አይደል... ፀሀይ ምትናፍቀው እንግዲህ እሷንም ያጣሃት እለት ነው... ፍቅሯን እምታውቀው •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~ @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~• አይኔ አፈጠጠ ረጅም አብርቶ በክህደትሽ ቁና ስትሰፍሪኝ አይቶ ልብሽ ከባእድ እጅ ሰተት ብሎ ገብቶ በብረቱ ብረት አይኔ ተመልክቶ ዉዴ ይሄንንማ አታደርግም ከቶ ብሎ የሚመሰክር አይቶ በብረቱ ክዶ 'ሚከራከር ያየውን የሚክድ ያልፈራ ኩነኔ ይሄ ከንቱ አይኔ ያንቺ ወይስ የኔ? •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~• #አይኔ ያሬድ መላኩ @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~• ይሄ ሌባ እድሜዬ እንዴት አርጎ ናቀኝ በመልኬ ስገረም ሳቄንም ነጠቀኝ •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~• #እድሜ @yegtm_medbl
•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~• ችግርህ ጠንክሮ ያለቅጥ ቢሰፋ ጨለማው አይሎ ብርሃንህ ቢጠፋ ጸሃይዋ ጠልቃብህ ካፊያውም ቢያካፋ የለት ውጣ ውረድ ቢሆንም ሚያለፋ መሸማቀቅ በዝቶ አንገትህ ቢደፋ ሁሉም ያልፋል የሚል እንዳታጣ ተስፋ •~•~•~•~•~•~•~•~•~•~•~• #ተስፋ @yegtm_medbl