ግጥም ፍቅር ቅኔ
Статистикаለማንኛዉም አስተያየት👉 @hollynba ግጥም ቃላትን በንዝረት በምትሃት በዉበት እና በእዉነት አበጃጅቶ እፈጥርልናል ቁስልን ማከም ተስፋን ማለምለም አቅም አለዉ ፍቅር ዉበት እንደ ተመልካቹ እንደሆነዉ ሁሉ ፍቅርም በዚዉ ሊገለፅ የሚችል በተለያየ አንደበት በተለያየ ትሩጋሜ ሊገለፅ የሚችል ረቂቅ የፈጣሪ ልግስና ነዉ ቅኔ ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ።
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Криптовалюты (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 139
- 1/48двое суток
- 159
- 1/72трое суток
- 171
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በጨለማ ውስጥ ተደብቆ የነበረ እውነት ታሪኩ የብዙዎችን ቀልብ የሰረቀ ነው። ዘይነብ ዓለምን አይታ አታውቅም፤ ነገር ግን ጭካኔዋን በእያንዳንዱ ትንፋሿ ታውቀዋለች። ውበትን ከምንም በላይ በሚያከብር ቤተሰብ ውስጥ ዕውር ሆና ተወለደች። ሁለቱ እህቶቿ በሚያማምሩ ዓይኖቻቸውና በቆንጆ ቁመናቸው ሲደነቁ፣ ዘይነብ ግን እንደ ትልቅ ሸክም እና ከበር በስተጀርባ እንደሚደበቅ አሳፋሪ ምስጢር ትቆጠር ነበር። እናቷ ስትሞት ገና የአምስት ዓመት ልጅ ነበረች፤ ከዚያ ቅጽበት ጀምሮ አባቷ ሙሉ በሙሉ ተቀየረ። መራራ፣ ተናዳጅ እና ጨካኝ ሆነ — በተለይም በእሷ ላይ። በስሟ ጠርቷት አያውቅም። “ያ ነገር” ይላት ነበር። በምግብ ሰዓት አብራቸው እንድትቀመጥም ሆነ እንግዶች ሲመጡ እንድትታይ አይፈልግም ነበር። የተረገመች እንደሆነች ያምን ነበር። ዕድሜዋ ሃያ አንድ ሲሞላ ግን፣ ያንን የተሰበረ ልቧን ዳግም የሚያደቅ ውሳኔ ወሰነ። አንድ ቀን ጠዋት፣ በብሬል መጽሐፍ ያረጁ ገጾች ላይ ጣቶቿን እያሸራተተች በዝምታ ወደተቀመጠችበት ጠባብ ክፍሏ ገባና የታጠፈ ጨርቅ ጭኗ ላይ ጣለላት። “ነገ ታገቢያለሽ” አላት ያለምንም ስሜት። ደነገጠች። ቃላቶቹ ምንም ትርጉም አልሰጧትም። ጋብቻ? ከማን ጋር? “ከመስጂዱ ደጃፍ የሚለምን ለማኝ ነው” ሲል አባቷ ቀጠለ። “አንቺ ዕውር ነሽ፣ እሱ ደግሞ ምስኪን ደሃ። ፍጹም ጥምረት!” ፊቷ ላይ ያለው ደም ሁሉ የኮበለለ መሰላት። መጮህ ፈለገች፣ ነገር ግን ምንም ድምፅ ሊወጣላት አልቻለም። ምንም ምርጫ አልነበራትም። አባቷ ምርጫ ሰጥቷት አያውቅም ነበር። በማግስቱ በችኮላና በቀላል ስነ-ስርዓት ተዳረች። በእርግጥ ፊቱን አይታ አታውቅም — ማንም ደግሞ ሊገልጽላት አልሞከረም። አባቷ ወደ ሰውየው ገፋትና ክንዱን እንድትይዝ ነገራት። በገዛ አካሏ ውስጥ እንዳለ መንፈስ ታዘዘች። ሰዎች ከጀርባዋ በእጅዎቻቸው አፋቸውን ይዘው ይስቁባት ነበር። “ዕውሯና ለማኙ!” ከስነ-ስርዓቱ በኋላ አባቷ ጥቂት ልብሶች ያሉበትን ትንሽ ቦርሳ ሰጣትና ድጋሚ ወደ ሰውየው ገፋት። “ከእንግዲህ እሷ ያንተ ችግር ናት” አለውና ዘወር ብሎ ሳያይ ጥሏት ሄደ። ዩሻ የሚባለው ለማኝ በመንገዱ ላይ በዝምታ እየመራት ተጓዘ። ለረጅም ጊዜ ምንም አልተናገረም። በመንደሩ ዳርቻ ላይ ወደሚገኝ አንዲት አነስተኛና የተሰባበረች ጎጆ ደረሱ። ጎጆዋ የረጠበ አፈር እና የጭስ ጠረን ታስተናግድ ነበር። “ብዙም የሚረባ ቤት አይደለም” አላት ዩሻ በርኅራኄ። “ግን እዚህ ምንም አደጋ አይደርስብሽም።” እንባዋን እየተቆጣጠረች በክፍሉ ውስጥ ባለው አሮጌ ምንጣፍ ላይ ተቀመጠች። አሁን ህይወቷ ይህ ነበር — ከለማኝ ጋር የተዳረች እውር ሴት፣ በጭቃና በሚሰባበር ተስፋ በተሰራች ጎጆ ውስጥ መኖር። ነገር ግን በዚያው የመጀመሪያ ምሽት አንድ ያልተጠበቀ እንግዳ ነገር ተከሰተ። ዩሻ በጥንቃቄና በለስላሳ እጆቹ ሻይ አፈላላት። የራሱን ብርድ ልብስ ሰጣትና እሱ ግን ንግስቱን እንደሚጠብቅ ታማኝ ጠባቂ በር ላይ ተኛ። ትልቅ ቦታ እንዳላት ሰው አድርጎ ያነጋግራት ነበር — ምን ዓይነት ታሪኮችን እንደምትወድ፣ ምን ህልሞች እንዳሏት፣ እና ምን ዓይነት ምግቦች ፈገግ እንደሚያሰኟት ይጠይቃት ነበር። ቀደም ሲል ማንም ሰው እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቋት አያውቅም ነበር። ቀናት ወደ ሳምንታት ተቀየሩ። በየቀኑ ጠዋት ዩሻ ወደ ወንዙ ይዟት ይሄድና ፀሐይን፣ ወፎችንና ዛፎችን በግጥም መልክ ይገልጽላት ነበር፤ በቃላቱ አማካኝነት ማየት የቻለች ያህል እስኪሰማት ድረስ። ልብስ እያጠበ ይዘፍንላት፣ ማታ ማታ ደግሞ ስለ ከዋክብትና ስለ ሩቅ ሀገራት ታሪክ ይነግራት ነበር። ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳቀች። ልቧ ቀስ በቀስ መከፈት ጀመረ። በዚያች እንግዳ በሆነች ትንሽ ጎጆ ውስጥ ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ — ዘይነብ በፍቅር ወደቀች። አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ፣ እጁን ለመያዝ ስትሞክር በለስላሳ ድምፅ ጠየቀችው፡ “ሁልጊዜ ለማኝ ነበርክ?” አመነታ። ከዚያም ቀስ ብሎ “ሁልጊዜ አይደለም” አላት። ነገር ግን ሌላ ምንም አልተናገረም። እሷም አልወተወተችውም። እስከዚያ ቀን ድረስ። አትክልት ለመግዛት ብቻዋን ወደ ገበያ ሄደች። ዩሻ ጥንቃቄ የተሞላበት መመሪያ ሰጥቷት ነበር፣ እሷም እያንዳንዱን እርምጃ በቃሏ ይዛው ነበር። ነገር ግን ግማሽ መንገድ ላይ ስትደርስ፣ አንድ ሰው ክንዷን በኃይል ጨበጠው። “ዕውር አይጥ!” የሚል ድምፅ ተተፋባት። እህቷ አሚና ነበረች። “እስካሁን በህይወት አለሽ? አሁንም ለለማኝ ሚስት ሆነሽ እየተጫወትሽ ነው?” ዘይነብ እንባዋ ሊመጣ ሲል ታገሿትና ቀና ብላ ቆመች። “እኔ ደስተኛ ነኝ” አለቻት። አሚና በጭካኔ ሳቀች። “እሱ ምን እንደሆነ እንኳን አታውቂም። እንደ አንቺው የማይረባ ፍጡር ነው።” ከዚያም ሙሉ በሙሉ የሚያደቃት ነገር በጆሮዋ አንሾካሾከችላት። “እሱ ለማኝ አይደለም ዘይነብ። ተዋሽተሻል።” ልቧ በኃይል ይመታ ጀመር... ታሪኩ ይቀጥላል።
#ጭንቅ_የፈጠረው_አማኝ ! . የተካበ ንዋይ አቅም ጉልበት ሲያጣ፤ ሥልጣንን አክሳሚ ሀሩር ቀን ሲመጣ፤ እግር ላይጓዝበት፣ መንገድ ላይደርስበት፣ ነፍስ ውጪ ዓይነት. . . ጩኸት ሲበረክት፤ የሕይወት ውል ሚዛን እንዳይሆን ሲሳከር፤ የጥመት ጋርዮሽ አጥብቆቱ ሲከር፤ እጆቼን አንስቼ፣ ዓይኔን አስነብቼ፤ "ተለመነኝ!" አልኩህ መጠጊያ አጥቼ። ለምንድነው ይሆን? አነሳሱን ሳያውቅ የጣለውን እምነት፤ በደጉም ቀን ሳለ ያንተ አምላክነት፤ ሲዘል የከረመ 'ሚያደርገው ሲያሳጣው፤ ምርጫ የጠፋ ዕለት ዳጃፍህ 'ሚመጣው?! ብቻ. . .በጥበብህ. . . ብቻ. . .በሰበብህ. . . ምርጫዬ በርክቶ መርጬህ እስክመጣ፣ ጠርዜን መሐል አ'ርገው ለገባሁት ጣጣ! እናም በዚህ ኅፍረት፣ ፀሎቴን ገታሁት ለመመለስ ምዬ፤ "መግቢያ ሲያጣ መጣ!" ትለኛለህ ብዬ! #ፈይሠል_አሚን
እንዴት ነሽ ስላት ሳቅ ታበዛለች ትጫወታለች ፤ < አለሁ ! > ትላለች - እንደሞላላት ቁስሏን የማላውቅ እዬመሰላት ፤ የዐይኗ መደፍረስ የገጿ ሽክረት የአንጀቷ ማረር የልቧ ቁስለት ጥልቅ ስቃይዋን እዬነገረኝ ፤ እርሷ ግን ሁሌም አንድ የምትለኝ ፤ - - - - - - - - - አለሁ ደህና ነኝ ! ልዩ ፍጥረት ናት አይደረሱባትም ፤ ስሟ ሕይወት ነው ካልተሸከሟት አይረዷትም ፤ በሕመሟ መሳቅ በቁስሏ ማጌጥ ታውቅበታለች ፤ ልክ እንደ መሬት ውኃ'ን ከእሳት ጋር ታቻችላለች ፤ ከራስ ቅራኔ ከራስ ጋር ሙግት ቢኖርባትም ፤ ከመሳቅ በቀር በሰው ፊት ማልቀስ አይኾንላትም ፤ ደህና ነኝ ከሚል ከአንድ ቃል በቀር —— ሌላ አይወጣትም ፤ እወድዳታለሁ ፤ ደህና ነኝ ስትል ደህና እንዳልሆነች አውቅባታለሁ።
#ፖለቲካዊ_ኮንትሮባንድ😂 የሩሲያ ዜጋ ነው። አንድ ልጁን ይዞ ወደ አሜሪካ ሊጓዝ፡ ሞስኮ በሚገኘው የሼሬሜቲቮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የፍተሻ ክፍል ደረሰ። ሻንጣው ተፈተሸ ፡ በውስጡ የሌኒንን ምስል የያዘ ቅርጻ ቅርጽ ነበረው። የአየር መንገዱ የፍተሻ ሰራተኛ፡- "ምንድን ነው ይሄ ?" በማለት ጥያቄ አቀረበ። መንገደኛው ሩስኪ፥- "ጓድ ጥያቄህን ያቀረብክበት መንገድ ስህተት ነው። «ይህ ማነው?» ብለህ እንጂ «ምንድን ነው ይሄ ?» ብለህ መጠየቅ አልነበረብህም። ለማንኛውም ይህ ሰው ለዓለም ጭቁን ህዝቦች ሲል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የታገለ የኮሚዩኒስት ስርዓት አርበኛ ነው፡፡ ለአዲሲቷ ሩሲያ ምስረታ ደግሞ ቁልፍ ሚና የነበረው ታላቁ አብዮታዊ መሪያችን ኮምሬድ ቪላድሚር ሌኒን ነው። የእሱን ገድል ለመዘከርና በረከቱን ለመቋደስ ስል፡ በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ምስሉን በእቅፌ ይዤ እዞራለሁ !" በማለት ምላሽ ሰጠው። . ሩሲያዊው የኢሚግሬሽን ፍተሻና ቁጥጥር መኮንን፡ አጠገቡ ቆሞ በሚናገረው የሃገሩ ዜጋ አስተሳሰብ እጅግ ተደመመ። በግለሰቡ ጽኑ የሌኒን ፍቅርና እምነትም ክልቡ ተደሰተ። እናም፡- "መልካም ! ማለፍ ትችላለህ ጓድ !" ሲል በክብር ሸኘው። * ሩስኪው አሁን USA ደርሷል። የአሜሪካ አየር መንገድ ተርሚናል የፍትሻ ክፍል ውስጥ እየተፈተሸ ነው። የፍተሻ ኦፊሰሩ ሻንጣ ውስጥ ያለውን ቅርጻ ቅርጽ ተመለከተ። . "ምንድን ነው ይሄ ?" በማለት አሜሪካዊው የጉሙሩክ ኦፊሰር ከሩሲያዊው መኮንን ጋር ተመሳሳይ ጥያቄ አቀረበለት። ሩሲኪውም፡- "ይቅርታ ጌታየ ! ጥያቄህን ያቀረብክበት መንገድ ትክክል አይደለም። «ይህ ማነው?» ብለህ እንጂ «ምንድን ነው ይሄ ?» ብለህ መጠየቅ አልነበረብህም። . ለማንኛውም አገሬን ለቅቄ ወደዚች ሰላማዊ ምድር የመጣሁት፡ በዚህ ጠማማና እርኩስ ግለሰብ ምክንያት ነው። የዚህ ከይሲ ሰው ፍልስፍና ነው ዓለምን በሁለት ጎራ ክፍሎ ህዝቦችን ባላንጣ ያደረገው። በዚህም ምክንያት ለበርካታ ሃገራት የብጥብጥና የቀውስ ምንጭ ሆኗል። በዚህ ሰው ርዕዮት-ዓለም አያሌ ዜጎች አልቀዋል። ይህ ሰው የዲያቢሊስ ደቀ መዝሙር ነው። ሌኒን ይባላል ! ቅርጻ ቅርጹን በዞርኩበት ቦታ ሁሉ ከኔ አልነጥለው። ምክንያቱም ሁሌም ስመለከተው ለመርገም እንዲያመቸኝ ብዬ ነው ከጎኔ የማለየው !" ሲል ምላሽ ሰጠው። . አሜሪካዊው የፍተሻ ክፍል ኦፊሰር፡ በሩሲያዊው እንግዳ ቅን እና ስሜት የሚነካ ንግግር ተመሰጠ። እናም፡- . "ጌታየ ! እንኳን በሰላም የአሜሪካን ምድር ረገጡ። አሁን ማለፍ ይችላሉ !" አለው በክብር። . መንገደኛው ሩስኪ ወደ ማረፊያው አመራ። የአረፈበት ሆቴልም ቅርጻ ቅርጹን አውጥቶ አስቀመጠው። ልጁም ቅርጻቅርጹን ከተመለከተ ብኋላ፡- . " አባዬ ይህ ማነው ?" ሲል አባቱ በሚፈልገው መንገድ ጥያቄ አቀረበለት። ሩስኪውም፡- " የኔ ልጅ ! «ይህ ማነው?» ብለህ ጥያቄ ማቅረብህ ስህተት ነው። መጠየቅ የነበረብህ እንደ ሩሲያዊውና አሜሪካዊው የፍተሻ ሰራተኞች «ምንድን ነው ይሄ ?» ብለህ ነበር። ለማንኛውም ይህ የምትመለከተው ቅርጻቅርጽ፡ 10 ኪሎ ግራም ባለ 24 ካራት ወርቅ ሲሆን፡ እኔ አባትህ ያለ አንዳች ቀረጥ ነው ወደዚህ አገር በሰላም ያስገባሁት። ገባህ የኔ ልጅ !" ሲል ብልጠቱን ሳይሆን እውነቱን ለልጁ ነገረው። ፖለቲካዊ ኮንትሮባንድ ! . ብልጥ ሰው የሚሰራውን ሳይሆን መስማት የምትፈልገውን እየነገረህ ነው ፍላጎቱን የሚፈጽመው !! .😄😄😄😄😄
ጥሩ ሴት ሁኚ ታማኝ ሴት ሁኚ የራስሽ መርህና ክብር ይኑርሽ ክብርሽን ጠብቂ ሐያእ (ጨዋነት) ይኑርሽ ራስሽን በእውቀት አንጪ ለራስሽ እንክብካቤ አድርጊ በደንብና ጤናማ ተመገቢ የአእምሮ ሰላምሽን ጠብቂ ሰላትሽን በወቅቱ ስገጂ በአላህ ላይ ሙሉ በሙሉ ተመኪንፁህ ልቦና (ኒያ) ይኑርሽ የቀረውን ነገር በሙሉ ለአላህ ተይው
ነፃነት ኦሾ ሙሉ በሙሉ ነፃ ለመሆን ሙሉ በሙሉ ግንዛቤ ማግኘት አለብን ምክንያቱም የባርነት ስር መሠረቱ ያለው ባለማወቃችን ውስጥ ነው። ጠልቀን ስንመረምረው ነፃነትህን የሚያሳጣህ ነፃነትን ለማግኘት ያለመፈለግህ ነው። ነፃነትህን የሚያሳጣህ ጥገኝ የመሆን ፍላጎት ነው። ራስህን የመሆን ኃላፊነት ላለመሸከም ያለህ ፍላጎት ነው። ሰው ለራሱ ኃላፊነት ለመውሰድ በፈቀደ ጊዜ በነገራችን ላይ ይህን ማድረግ ሙሉ በሙሉ አስደሳች ነገር አይደለም በውስጡ እሾህና መራር ነገሮች ይገኙበታል። ጣፋጫ ነገር ሁሉ ሚዛናዊ ነገር እኩል በእኩል ተከትለው ይመጣሉ። ጽጌሬዳዎች ያለ እሾህ አይበቅሉም ቀናትን ሌሊትን ተከትለው ክረምቱ አብቅቶም ፀሐይ ትወጣለች። ሕይወት የተቃራኒ ነገሮች ሚዛን አጣጥማ ትኖራለች። ራስን የመሆን ኃላፊነትን ከውበቱና ከመራርነቱ ፣ከደስታውና ከስቃዩ ጋር ለመቀበል ፍቃደኛ የሆነ ሰው ነፃ መውጣት ይችላል። ነፃ ሊሆን የሚችለው ይህን መሠል ሰው ብቻ ነው።
https://youtube.com/shorts/y2fwZTmCxqo?si=XbeuZ7JkGJ95XDWl
ዳዊት ኤፍሬም ……ይለበድ ###### አዳምና ሄዋን አይናቸው ሲከፈት ቀድሞ የተሰጣቸው የቀለም ትምህርት ምራፍ አንድ ላይ የራቁት ምንነት በገፅ ሁለት ላይ በመራቆት ምክንያት የሚመጣ ሃፍረት በስተመጨረሻ ማጠቃለያው ላይ እራቁትነትን ሸፍኖ ሚደብቅ አይነተኛ መንገድ የሚሉ ነበሩ ገና ከጅምሩ ያኔም እሱን አውቀው ትምህቱ ገብቷቸው ቅጠሉን ለበሱት ላስከፊው በሽታ እጅ ላለመስጠት ግና የቅጠል ልብስ ዋጋም እንደሌለው የገባው ፈጣሪ የሁላችን ሰሪ ወዶ አለበሳቸው ከፀሃይ ከውርጩ በሚጋርዳቸው ያኔም ተደሰቱ ከጊዜ በኋላም ቆዳው በመድረቁ ስሱ ገላቸውን እጅግ በመፋቁ ቁርበቱን አስቀምጠው በጨርቅ ደመቁ ታዲያ በኛ ዘመን ጅንስ በሞላበት ቀበቶ ምናምን ወገብ ማሳመርያ ጌጣጌጥ በሆነበት ሃፍረት ሚባል ነገር ጭራሹን ተረሳ ሆኖ ቀረ ዘበት እሱም ይባስ ብሎ ራቁትነት መጣ ፋሽን ተመስሎ የት ሄደን እንጩህ ለማን እንናገር በተንበረከኩ ዝቅ ባሉ ቁጥር የማንፈልገውን የምንጠላውን ቻነል እያሳዩን በጣም ተቸገርን ልንገርህ ወዳጄ አድምጠኝ እውነቱን ስርአቱን ጠልቶ ያፈተለከውን መሸፈን ሰልችቶት የሚያጮልቀውን እባክህ በማምላክ ፈስ-ቡኩን ዝጋልን
#ክባዳም_ትረካዎች . (#ፈይሠል_አሚን) . የአባቴ የጉንጭ ሥርጉድ ከየት የመጣ ነው? እናቱ ሲሥቁ ብዙ ጊዜ ዐይቻታለሁ።አያቴ ጉንጯ እንደ ገብስ ገንፎ የነጣና የሞላ ነው።አባቱም ቢሆኑ ጉንጫቸው የተለመደ አዘቦታዊ ጉንጭ ነው። አባቴ የጉንጭ ሥርጉዱን ከየት አገኘው? . በመሠረቱ የጉንጭ ሥርጉድ የሚገኝ ነገር አይደለም።ሳይንሱ "ጉንጭ ላይ ሥርጉድ የሚፈጠረው ጉንጭን ጉንጭ የሚያደርጉ ጥቃቅን ሴሎች በቁጥር ሲጎድሉ ነው!" ይላል። . አባቴ ጉንጩ የሠረጎደው ሴል አንሶት ነው።ከእናቱም ከአባቱም እንዲሁም ከኔ ውዱ ልጁም በሴል ቁጥር ያንሳል። ምስኪኑ አባቴ! . ግን አባቴ ከእናቱም ከአባቱም እና ከኔ ውዱ ልጁ የበለጠ የሚማርክ ፈገግታ አለው።ፈገግ ሲል ያየ ማንም ሰው ይደነግጣል፣ይደነቃል፣ ጉንጩንም ያደንቃል። በጉድለት ሰው እንደሚያሸበርቅ ያየሁት ከአባቴ ነው። ሰዎች ያላቸው የሌለው ሰው ካላቸው የበለጠ ውብ እንደሆነ ያስተዋልኩት በወላጄ ነው። . እመኛለሁ። ጉንጬ ላይ ባይሆንም ሕይወቴ ላይ የጎደለ ነገር አለ።እንደ አባቴ ባሸበርቅበት ብዬ እመኛለሁ።ሰዎች ጉደለቴን ዐይተው በአድናቆት ቢመለከቱኝ፣በጎደለኝ ነገር ሰዎች ቢቀኑብኝ. . .እንደ አባቴ. . .እመኛለሁ! . 👇👇❤👇👇 @HOLLYPOEM @HOLLYPOEM @HOLLYPOEM @HOLLYPOEM
የባሰ ቀን ሲመጣ . (#ፈይሠል_አሚን) . "ያልፋል!" ብዬ ቻልኩ፤ "ያልፋል!" ብዬ ተውኩ፤ "ባያልፍስ?!" በሚል ስጋት ራሴን ብዙ ቀጣሁ፣ ስብዕናዬን ጥዬ ከሰው ዓለም ወጣሁ! ዛሬ አለፈና. . . ነገ ደረሰና. . . "ይኼም ያልፋል!" ለማለት ብበቃም፤ ካሳደረኝ እንቅልፍ ደርሼ ብነቃም፣ ባላፈኝ ማግስቴ፣መንፈሴ አልረካም! . ያለፈው ምን አለው? መጪው ምን ጎደለው? የዛሬው እንባዬ አሁን እያሣቀኝ፣ ያለፈ ሥቃይ ነው፤ዛሬም 'ሚናፍቀኝ! . 👇👇👇👇 @siletibeb @siletibeb @siletibeb
https://youtube.com/shorts/Ebc4XtLU2n8?si=Auisj4r3baOwvFHz
የማይወዳደር እኩያ የሚያጣ ከልቤ ግርጌ ስር አንዳች ስሜት ወጣ ተሰማኝ ወደድኩህ ያንተን ጣዕም ለየሁኝ ቆዳዬ ቀመሰህ ምላሴን ከዳሁኝ ከየትኛው አካሌ ፍቅርህ የወደቀው የሚያርበተብተኝ ጥፍሬን የሚነዝረው አካልስ አለ ወይ የሚታይ ሚቀመስ ሴትነት ገላዬን ነክቶ ሚያጎለምስ ንገረኝ አንተዬ ከደጅ እንዳያድር ዳስም ልጣልለት እንዲህ ያለ ፍቅር አያድርም ከኔ ቤት በአዳፋዬ ባያድፍ ንፁህ ጥሩ ፍቅርህ ከቆሸሸ ገላ ከዚህ በድን ይሽሽ እንዲህ ያለ ልመና ሚዛን አያነሳም የፍቅር ባህሪ ዙፋንን አይሻም የት ጋር ነው የሚሰማኝ ምኔን ነው የያዝከው የት ጋር ነው ያገኘኸኝ ምኔን ነው ያጣኸው ብቻ ከልቤ ስር ስሜቴ ይፈልቃል የደረስክበትን ያልደረስክበትን ረቂቁ ፍቅርህ እሱ ብቻ ያውቃል ✍ረድኤት ተረፈ
https://youtube.com/shorts/M4MdN435WGo?si=1jM__Qixc6E2XNl8
#በሃገሩ_ባዳ ! ዩኒቨርሲቲ የላኩት ልጄ... ሃገሩን አምኜ፥ ምንም አይቸገርም.. ወገኑ ነው ብዬ... "ተደበደበ!" አሉኝ እንዲያው እንደዋዛ! "ሊሞትብሽ ነው፡፡" የሚል - መርዶ አርጂ በዛ። ............................................... ምነው ሆዴም ባባ... አንጀቴ ሳሳብኝ ያጠባሁት ጡቴን ክፉ ጦር ወጋብኝ፥ የምሰማው ነገር ገዳይ መርዝ ሆነብኝ፤ ፍርሃት ... ፍርሃት አለኝ.. ሊማር እንደወጣ - ልጄ እንዳይቀርብኝ፤ ……………………………………………………………. በላቤ ነው ያደገው - በጭስ ውስጥ አልቅሼ - ባነባሁት እንባ እንጀራ ጋግሬ - ቆጮውን ጠፍጥፌ - ጡቶቼን ሳጠባ፥ ነበር መፅናኛዬ - የአይኔ ማረፊያ አይኑ እስኪቀላ - በኩራዝ አንብቦ - ግቢ እስኪገባ፤ ታዲያ ዛሬ... ያለኝን ቋጥሬ - ከሌለኝ ቆጥሬ፥ ስሜ የሸኘሁት ልጄ - ድግሪ ይጭናል ብዬ! ሃገሩን አምኜ! ወገኑ ነው ብዬ! "ተደበደበ!" አሉኝ እንዲያው እንደዋዛ፥ "ሊሞት ነው" የሚል ባለመርዶ በዛ! …እኔን ይደብድቡኝ - ይሁን ለናትህ! …እኔን ከርታታዬ... እኔ ልሙትልህ! ልጄ ላንተስ አይሁን! እኮ እንዴት ተደርጎ? ምንስ አጠፋና... ምስኪን ድሃው ልጄ - ወዶ ባልመረጠው - በብሔሩ ይቀጣ? ምን አይነት ጭካኔ - ጊዜ ያመጣው ጣጣ፤ ለትምህርት የሄደ - ህይወቱን የሚያጣ?! እኔስ አልችለውም - የሃዘኑን ነገር፥ ሌላ ባዕድ ሲሆን በወገኑ ሲገፋ - ሰው በራሱ ሐገር! __( አንድ ሃገር/ቢያ ቶኮ/ ገጽ 33-34 ... በዶ/ር ኤልያስ ገብሩ/ ህይወታቸውን ለመለወጥ ዩኒቨርሲቲ ሄደው በጎሣቸው ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን በሙሉ መታሰቢያ የተፃፈ፤) @hollypoem
https://youtube.com/shorts/5weMDpS1mxg?si=cDu4W-w1aFPIr1zN
https://youtube.com/shorts/8GmQsS_qxm4?si=t9MTJSiITN1DCKYE
https://t.me/boost/hollypoem
без подписи
без подписи
ተገላቢጦሾ -------------- ሞኝ ነክ ካለህ ሞኝ ነኝ በለው ላንተ የከበደው እርሱ ከናቀው አንተ የጣልከውን እርሱ ካነሣው ላንተ የበራው ከጨለመበት እረፍት ከነሣው እውነት ሞኝነት ይሔ ከሆነ ሞኝ ነኝ በለው፡፡ እውነትን መያዝ ለውነት መታዘዝ ምክንያት ከሆነ ለስር ለመጋዝ ብልጥ ነኝ ያሉት ሞኝነት ካሉት በእውራን መሀል ማየት ባይደላም መዋሸት ከሆነ ብልጥነት ሞኝነት አይከፋም፡፡ ንቃ ከተኙት መሀል ተለይ ሞኝ ነው ተባል ብልጥነት እንዳይገላቸው ሳትኮንናቸው ሳትፈርድባቸው ቀድመህ ንቃና ከሞት ከብልጥነት አንቃቸው፡፡ ............. ቢንያም ደሳለኝ 🙋♂