Ye Haybaw Mender
Статистикаاللهم صل عل سيدنا ونبينا وحبيبنا وشفيعنا محمد 💚💚💚
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 278
- 1/48двое суток
- 318
- 1/72трое суток
- 343
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የረቢዕ ነገር ይደንቃል። በወር መጠሪያነት፤ በወቅት ስያሜነት መገደብ ይጠናል። ብራማነቱ ልብን ይዘልቃል። መዓዛው ሩህን ያነቃል። ስፋቱ ሽምጥ ያስጋልባል። አንድምታው ምናብ ያባክናል። "እንዲህም ነው ..እንዲያም ነው.." እያሰኘ ያብከነክነናል። ብዙ ማለትን፤ ብዙ መክተብን ያሰኛል። ልክ እንደ ያኔው፤ እንደ አለማቱ ብስራቱን የመጠባበቅ ሂደት ውስጥ መንፈስን ይደባልቃል። ጉጉትን አስቀድሞ በናፍቆት ይንጣል። ለዚህም መድረስ ..ለዚህም መታጨት ..ይህም ከረቢዕ ነው። እንኳንም ደረስን..! አላሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐላ ሩሂል ውጁድ 🤍
ረቢዑ ከጁመዐ ጋር ክብር ላይ ክብር ውበት ላይ ዉበት ሀይባ ላይ ሀይባ የገጠሙበት ዕለት ረቢዕ አንድ እና ጁመዐ 🥰 እኛም ከአላህ ጋር ከነቢያችን ﷺ ጋር የምንገጥምበት ዕለት ያድርግልን .. ከሌላ ጊዜ በተሻለ ሰለዋት በማብዛት እናሳልፈው ኢንሻአላህ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ الَّذِي أَشْرَقَتْ بِمَوْلِدِهِ الأَنْوَارُ، وَتَزَيَّنَتْ بِظُهُورِهِ الأَعْصَارُ، رَحْمَةِ اللَّهِ لِلْعَالَمِينَ، وَنُورِهِ الْمُبِينِ، وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينَ
..የረቢዑ ሽታ🥹💚🙌 እንኳን ደስ አለን🌿🌿 በሰለዋት እናድምቀው አፉ እንባባል ወደ ኸይር ስራ እንሽቀዳደም ..
የረቢዑን አወል ወር የመጀመሪያውን ለይል ምክንያት በማድረግ ከመግሪብ በኋላ ለየት ያለ የሰለዋት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል https://t.me/al_wird_al_mohammedi ለሌሎችም share እናድርግ
без подписи
በዛሬው ዕለት ማለትም በሰፈር በመጨረሻው እሮብ የሚባሉ ዱዐዎችን የያዘ ነው በምንችለው አቅም ለማሟላት እንሞክር !
🌿 አል-ዊርድ አል-ሙሐመዲይ 🌿 ይህ ቻናል በሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐብደላህ አል-ሙሐመዲይ የበላይ ጠባቂነትና መሪነት የሚመራ ሲሆን፤ ከሙሐመዳዊው መስመር ጋር የተያያዙ አውራዶችን፣ ዚክሮችን እና መንፈሳዊ ዕውቀቶችን በስርዓቱ ለማሰራጨት የተቋቋመ ልዩ የሱሉክ ማዕከል ነው። የቻናሉ ዋና ዓላማ ሙሪዶች ከሙሐመዳዊው ማንነት ጋር ጠንካራ መንፈሳዊ ቁርኝት እንዲፈጥሩ፣ በታላቁ ነብያዊ ስነ-ምግባር እንዲቀረጹ፣ እንዲሁም ያንን እውነታ በተግባር እንዲያረጋግጡ መርዳት ነው። በዚህ ቻናል ላይ የሚከተሉት ይዘቶችና አገልግሎቶች በስርዓት ይቀርባሉ፦ የሰለዋት ቻሌንጆች (ውድድሮች)፦ ተከታዮች በጋራና በነጠላ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት በማውረድ መንፈሳዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩባቸው ልዩ መርሐ-ግብሮች። የተመረጡ አውራዶችና ዚክሮች፦ ለልብ መርጊያ እና ለመንፈሳዊ ከፍታ የሚያገለግሉ ትክክለኛ ዚክሮች። የሙሐመዳዊ ዕውቀት ጥቅሞች፦ ጥልቅ የሆኑ መንፈሳዊ ምስጢራት፣ የታላላቅ ዑለማኦች ምክሮች እና የዕውቀት በረከቶች። የሱሉክ እና የተርቢያ መመሪያዎች፦ አንድ ሙሪድ በመንፈሳዊ ጉዞው ሂደት ውስጥ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ ተግባራዊ ስንቆች። ይህ መድረክ በሸይኻችን የዕውቀትና የሂክማ እቅፍ ስር የሚመራ የነፍስ ማረፊያ እና የታላቁ መስመር መጋቢ ነው። ክቡራን ተከታዮቻችን የዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ተቋዳሽ እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን። #إدارة_القناة #الورد_المحمدي_الشريف
✨ 📢 ታላቅ የላይቭ (LIVE) ፕሮግራም ጥሪ! 📢 ✨ 🌹🌙 ለውድ የአል-ዊርድ አል-ሙሐመዲይ ቤተሰቦች በሙሉ 🌙🌹 🕊️ በአላህ ፈቃድ ዛሬ በጉጉት የሚጠበቅ እጅግ ልዩና መንፈስን የሚያድስ ታላቅ የደርስ ፕሮግራም ይዘንላችሁ ቀርበናል! 📚 የዛሬው የደርስ ርዕስ፦«ስለ አህሉ በይቲ ረሱሊላህ (የመልክተኛው ﷺ ቤተሰቦች)፦ ከነቢዩ ጋር ያላቸው ትስስር እና ከሰለዋት ጋር ስላላቸው ጥልቅ ግንኙነት» የምንመለከትበት እጅግ ውብ ማዕድ ይሆናል። 🌹📿━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📌 የተሳትፎ ጥሪያችን፦ 🫵 በመጀመሪያ ራሳችን በተሻለ ዝግጁነት በዚሁ ውድ ማዕድ ላይ ቀድመን በመገኘት በረከቱን እንሸምት!እንዲሁም...👨👩👧👦 በቅርባችን የምናውቃቸው የመልክተኛው ﷺ ዘሮች (የአህለል በይት አባላት) ካሉ፣ ይህንን ውድ መንፈሳዊ ማዕድ እንዲታደሙ በክብርና በፍቅር እንጋብዛቸው! ⏰ የፕሮግራሙ ሰዓት፦ ምሽት 3፡00 📍 የሚተላለፍበት ቦታ፦ በአል-ዊርድ አል-ሙሐመዲይ የቴሌግራም ቻናል ላይ 🔴 LIVE ✨ የነብያችንን ﷺ እና የውድ ቤተሰቦቻቸውን በረከትና ፍቅር ለመቋደስ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል! አደራ! ለሌሎች ሙሂቦች በማጋራት (Share) የኸይር ስራው ተካፋይ ይሁኑ! 🔄 اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه وسلم 🤍📿━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
አላህ ሆይ ! በትዕዛዛትህ ላይ እንደ ሀጀራ ታጋሽ አድርገን ! ነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) እሷን እና ልጇን ሰው ዝር ማይልበት አዝዕርት እንኳ ማይበቅልበት ሸለቆ ፣ የመጠጥ ውሀ ሆነ እህል፣ አጫዋች ጓደኛ በሌለበት ምድረ በዳ ጥለዋት ሲሄዱ ያስጨነቃት እኚህ ሁሉ ምድራዊ ችግሮች አልነበረም። ይልቁኑ አንድ እና አንድ መሰረታዊ ጥያቄዋ "የአላህ ትዕዛዝ ነውን ?" የሚል ነበር ። እርሳቸውም " አዎን እንዴታ" ሲሏት እንግዲያውስ ሂድ አላህ ብቻችንን አይተወንም ነበር መልሷ ። አላህ ሆይ ! የዚህ አይነት ልብ የዚህ አይነት ኢማን የዚህ አይነት የቂን የዚህ አይነት ትዕግስት ስጠን
قال القاضي عياض رحمه الله في «ترتيب المدارك»: عن الإمام مالك رحمه الله أنه قال: «كانت أمي تُعَمِّمُني، ثم تقول: اذهب إلى ربيعة فتعلَّم من أدبه قبل علمه.» "ኢማም ማሊክ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይሉ ነበር፦ «በልጅነቴ እውቀትን ለመማር ከመውጣቴ በፊት እናቴ ጥምጣሜን ትጠመጥምልኝና፦ ‘ወደ ረቢዓ ሂድ፤ ከእውቀቱ በፊት ከአደቡ ተማር ትለኝ ነበር።» قال الإمام مالك رحمه الله: «تَعَلَّمِ الأَدَبَ قَبْلَ أَنْ تَتَعَلَّمَ العِلْمَ.» "ከዕውቀት በፊት አደብን ተማር።" وقال عبد الله بن المبارك رحمه الله: «نحنُ إلى قليلٍ من الأدبِ أحوجُ مِنَّا إلى كثيرٍ من العلم.» "ከብዙ ዕውቀት ይልቅ ትንሽ አደብ የበለጠ እንፈልጋለን።"
የዳሩል ሙስጠፋ (ተሪም) የኸሚስ ሐድራ በጣም ነው የሚያምረው። የተለያዩ መሳጭ ዳዕዋዎች ይቀርቡበታል። የሙረቢ ሸይኽ ሐቢብ ሒዳያትና የተለያዩ የሰለዋትና ሐድራዎች ይቀርባሉ። ከእኛ ሐገር አንጋፋ መስጂዶች ጋር ከሚቀርቡት የኸሚስ ሐድራዎች ጋር ይመሳሰላል። በየመጅሊሱ ላይ ከተለያዩ የምዕራቡ ሐገራት የሰለሙ ነጮች ተውበው በተሪም ደርስ ጌጤው የሚያቀርቡት ዳዕዋ በጣም መሳጭ ነው። ከነዚህም ውስጥ "አላ ያ አላህ ቢነዝራህ ..." ይህንን ቀሲዳ ያዘጋጁት (ከሂጅራ 1044 – 1132 ) በየመን፣ ሐድራመውት ይኖሩ የነበሩት ታላቁ አሊም፣ ዐሪፍ ቢላህ አል-ኢማም አል-ሐቢብ ዐብደላህ ቢን ዐለዊ አል-ሐዳድ (ረሒመሁላህ) ናቸው። ኢማም አል-ሐዳድ በርካታ ኢስላማዊ ኪታቦችን አዝካሮችን ያበረከቱ ታላቅ ሸይኽ ናቸው። የዚህ ግጥም ጥንስስ እጅግ የሚወዷት ባለቤታቸው በሞት ስትለያቸው በገጠማቸው ብርቱ ሐዘንና የልብ ስብራት በተነሳ የሰደሩት እንደሆነ ይነገራል። ቀሲዳው እንዲህ እያለ ይጀምራል .. ألا يَا الله بِنَظْرَة مِنَ العَيْنِ الرَّحِيمَة تُدَاوِي كُلَّ مَا بِي مِنْ أَمْرَاضٍ سَقِيمَة አላህ ሆይ! በውስጤ ያለውን ሕመም፣ ጭንቅና በሽታ ሁሉ የሚፈውስልኝ በሆነች እዝነት አይንህ ተመልከተኝ፤ أَلاَ يَا صَاحِ يَا صَاحِ لاَ تَجْزَعْ وَتَضْجَر وَسَلِّمْ لِلْمَقَادِير لِكَيْ تُحْمَدَ وَتُؤْجَر ወዳጄ ሆይ! አትደንግጥ፣ አታማርር፤ ምንዳንም ታገኝ ዘንድ ለአላህ ውሳኔዎች (ቀደር) እጅህ ሰጥ። وَكُنْ رَاضِي بِمَا قَدَّرَ المَوْلَى وَدَبَّرْ وَلَا تَسْخَطْ قَضَا الله رَبِّ العَرْشِ الأَكْبَرْ ጌታህ በወሰነው ነገር ሁሉ ወዳጅ ሁን፤ የታላቁ ዐርሽ ጌታ በሆነው በአላህ ውሳኔ ላይም አትቆጣ፤ وَكُنْ صَابِر وَشَاكِر ... (أَلاَ يَا الله بِنَظْرَة) تَكُنْ فَائِز وَظَافِر ... (أَلاَ يَا الله بِنَظْرَة) وَمِنْ أَهْلِ السَّرَائِر ... (أَلاَ يَا الله بِنَظْرَة) ታጋሽና አመስጋኝ ሁን፣ ስኬታማና አሸናፊ ትሆናለህ፣ የውስጥ ምስጢር ( ንጹህ ልብ )ከላቸው ሰዎችም ትመደባለህ። ይህ ቀሲዳ በየመን ብቻ ሳይወሰን በምስራቅ አፍሪካ (በኢትዮጵያ፣ በሱማሊያ፣ በኬንያ) እንዲሁም በማሌዥያና ኢንዶኔዢያ ባሉ ማህበረሰቦች ዘንድ የታወቀ ነው። በኢትዮጵያ በተለይም በመውሊድ፣ በሐድራና በነሺዳ ስነ-ስርዓቶች ላይ በአረብኛና አንዳንዴም ወደ ሀገርኛ ዜማ ተተቀይሮ በስፋት ሲያንጎራጉሩት ይስተዋላል።
ናፋቂዎች በጉጉት የሚጠብቋት ዳራቸውን ይዘው ስለ ሰይዲ ﷺ የሚያወጉባት ሰለዋት የሚያበዙበት ተንቢሁ የሚንቧቧበት ዱዐ ሚጎርፍበት ምሽት ኸሚስ 💚 خميسكم مبارك، وجعل الله ليلتكم نورًا ورحمةً وبركة. اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا محمد، وعلى آله وصحبه، صلاةً تملأ بها قلوبنا نورًا، وتشرح بها صدورنا، وتيسر بها أمورنا، وتغفر بها ذنوبنا، وترفع بها درجاتنا ፏ ያለ ኸሚስ☘
ቻናል ብለን ስንጠራው ሀያእ ይይዘናል ለኛ መድረሳችን ነው ብዙ ነገር የተማርንበት የምንማርበት የሸይኻችን የማይጠገቡ ንግግሮች የምንሰማበት እዚሁ ሆነን ተሪም ያለን ያህል እንዲሰማን የሚያደርገን የጠዋቱ አዝካሩ የማክሰኞ ሀድራው የኸሚሱ ኺትም የጁመዐው ቡርዳ የቅዳሜ ረውሀ እና የእሁድ ደርስ ቀናችንን እና ሳምንታችንን የሚያሳምርልን ለሩሀችን ቻርጅ ማድረጊያ ቦታ ነው... የሚላኩት ንግግሮች ቀልብን የሚያርሱ ለአብዛኛው ሰው የዱሀ ሰላት ለመጀመር ሰበብ ከፈጅር በኋላ ላለመተኛት ምክንያት የሆነ ነው.... {ብቻ ለኛ ሀያትችን ነው} https://t.me/Noor_Musela
ሴቶች በደጋጎች ቤት ውስጥ ንግሥቶች ናቸው! ኢብኑል ጀውዚ «አል-ሙድሂሽ» በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦ «ሴቶች የነጻ ሰዎች አደራዎች ናቸው። ከተከበረ ሰው በስተቀር ማንም አያከብራቸውም ፤ ከተዋረደ ሰው በስተቀር ማንም አያዋርዳቸውም።» ወዳጄ ሆይ! ሴቶች በደጋጎች ቤት ውስጥ እንደ ንግሥት ናቸው! የጥንት አባቶቻችን ለአንድ ሰው “ወንድ” የሚለውን መጠሪያ አይሰጡትም ነበር ። የገዛ ሚስቱ በእርሱ ጥላ ሥር በክብርና በኩራት ትኖር እንደሆነ ወይም ተዋርዳ እንደሆነ እስኪያዩ ድረስ! ክብርን መንፈግ ማንኛውም ሰው ሊያደርገው የሚችለው ቀላል ነገር ነው፤ ክብር መስጠት የሚችሉት ግን እነዚያ ደጋግ የሆኑት ብቻ ናቸው! መበቀል ማንኛውም ሰው ሊያደርገው የሚችል ተራ ነገር ነው፤ መበቀልና መቅጣት እየቻለ ግን ማለፍና ይቅር ማለት የደጋግ ሰዎች መለያ ነው፤ ሴት ልጅ አንተ ዘንድ የተቀመጠች አደራ እንጂ በገንዘብህ የገዛሃት ባሪያ አይደለችም። ስለዚህ አማናህን በክብር ጠብቀህ አቆይ ካልሆነ ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ወደ ቤተሰቦቿ መልሳት።
በዚህ ዘመን በጣም የሚያስፈልገን እና ማብዛት ያሉብን ነገሮች -ኢስቲግፋር -ሠለዋት -ሠደቃ ከዛሬው ከሸይኹና አዲል ደርስ የተወሰደ✍
ቁጣ በኛ ላይ የሚያመጣቸው ጉዳቶች 1Anxiety (ጭንቀት ,መረበሽ) 2 Stroke 3 የልብ ምት መዛባት 4 የእንቅልፍ ማጣት 5 Stress(ውጥረት) 6 የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም 7 ራስ ምታት እና ማይግሬን 8 የጡንቻ መወጠር እና ስር የሰደደ ህመም 9 የደም ስኳር መቆጣጠር መቸገር በተለይም ለስኳር ታማሚዎች # የነዚህን ሁሉ ችግሮች መከላከያ እጅጉን ቀላል ነው :-አውፍ ማለት እና አዑዙቢለሂ ሚነ ሸይጧን ረጂም ማለት ነው ከሸይኹና አዲል ደርስ የተወሰደ✍
ሩህ ስክነቷን የምታገኝበት ምሽት ኸሚስ ምላስ በሰለዋት የምትላወስበት ቀልብ የምትረጥብበት ናፋቂዎች ናፍቆታቸውን በመግለፅ የሚጠመዱበት ምሽት💚 ──────⊱◈◈◈⊰─── شَمْسُ الْخَمِيسِ إذا تغيب زِد في الصّلاةِ على الحبيب ──────⊱◈◈◈⊰─── اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى نُورِ الْأَنْوَارِ، وَسِرِّ الْأَسْرَارِ، وَتِرْيَاقِ الْأَغْيَارِ، وَمِفْتَاحِ بَابِ الْيَسَارِ، سَيِّدِنَا وَمَوْلَانَا مُحَمَّدٍ الْمُخْتَارِ، وَعَلَى آلِهِ الْأَطْهَارِ، وَأَصْحَابِهِ الْأَخْيَارِ، عَدَدَ نِعَمِ اللَّهِ وَإِفْضَالِهِ.
Depression (ድባቴ ,ጭንቀት )አለንጋ ነው ከአላህ ስንርቅ የምንገረፍበት !! ከሸይኹና አዲል ንግግሮች ✍
عن أبي هريرة رضي الله عنه أن النبي ﷺ قال: «إيّاكم والحسد، فإنَّ الحسدَ يأكلُ الحسناتِ كما تأكلُ النارُ الحطبَ» أو قال: «العُشبَ». رواه أبو داود، باب في الحسد، رقم: ٤٩٠٣. Meaning in English: "Beware of envy, for envy consumes good deeds just as fire consumes wood." (Or, according to another wording: "grass.") አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ አንሁ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል አደራችሁን ምቀኝነትን ተጠንቀቁ ! እሳት እንጨትን ወይም ሳርን እንደምትበላው (ምቀኝነት ) ኸይር ስራን ትበላለችና [አቡ ዳውድ]
^^ዛፍ ፍሬዎቹ በበዙ ቁጥር ወደታች እያጎነበሰ ይመጣል ....ሰውም እንደዛው ነው ዒልሙ በጨመረ ቁጥር ያለማወቁን መረዳት ስለሚጀምር ተዋዱዑ ይጨምራል^^