Tofik Bahiru
Статистика- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 793
- 1/48двое суток
- 908
- 1/72трое суток
- 980
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ወዳጅ ስለሚወደው ሰው ለመናገር የሚጋብዘውን ማንኛውንም ምክንያት ይጠቀማል። እናም ወዳጃችንን [ﷺ] የሚወድ ሰው እርሳቸውን አብዝቶ ለመዘከር የተከበረው የልደታቸው መታሰቢያ እንደ ማኛ ምክንያት ይቆጥረዋል!… : በዚህ ታላቅ ክስተት፣ ልቅናቸው ከፍ ብሎ በታየበት የውልደታቸው ዜና ለፍጥረታት የተረፉ ስንት የአላህ ጸጋዎች ተገኙ!? #አባቴና #እናቴ #ፊዳ ይሁኑላቸውና…
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] አንድ ሰው: ‐ «ያዘልጀላሊ ወል‐ኢክራም (የክብርና የታላቅነት ባለቤት ሆይ!)» እያለ በዱዓው ላይ ሲጣራ በአጠገቡ አለፉና፦ «ተመልሶልሃል፤ አሁን ጠይቅ» አሉት።» 📚 ኢማም አህመድና ቲርሚዚ ዘግበውታል፤ ቲርሚዚም ሐዲሱን 'ሐሰን' ብለውታል።
ታላቁ ታቢዒይ አቡ ዐብዲር‐ረሕማን አስ‐ሱለሚይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ከጁሙዐ በፊት አራት ከበስተኋላዋ አራት እንድንሰግድ ያዙን ነበር።» ዐብዱረዛቅ "አል‐ሙሶነፍ" በተሰኘው ኪታባቸው ዘግበውታል። አል‐ሀይተሚይ "ዘጋቢዎቹ ታማኞች ናቸው።" ብለዋል።… ይህ የሱፍያን ሰውሪይ፣ የዐብዱላህ ኢብኑል‐ሙባረክ እና የሌሎቹም የሰለፍ ልሂቃን መዝሀብ ነው። ጁሙዐ እንደ ዙህር ከበስተፊቷ አራት ከበስተኋላዋ አራት ረከዐ ሱና አላት። «ሶላት [በአላህ] ከተደነገጉ ዒባዳዎች ሁሉ ምርጧ ናት!» ባረከላሁ ፊኩም!
አላህ ነቢዩን ﷺ በመላኩ በሰጠን ፀጋ ተመጻድቋል። በርሳቸው ውስጥ የተሰጠንን ስጦታ እንድናውቅ፣ እንድናስብና ደጋግመን እንድናስታውስ አዞናል። በዚህም አላህን ማመስገን እና አበክረን ማውሳት እንደሚገባን አመልክቶናል። አላህ እንዲህ ይላል፦ ( كَما أَرسَلنا فيكُم رَسولًا مِنكُم يَتلو عَلَيكُم آياتِنا وَيُزَكّيكُم وَيُعَلِّمُكُمُ الكِتابَ وَالحِكمَةَ وَيُعَلِّمُكُم ما لَم تَكونوا تَعلَمونَ فَاذكُروني أَذكُركُم وَاشكُروا لي وَلا تَكفُرونِ) «በመካከላችሁ ከእናንተው የሆነን መልእክተኛ እንደላክንባችሁ ሁሉ፤ እርሱም አንቀጾቻችንን ያነብላችኋል፣ ያጠራችኋል፣ መጽሐፉንና ጥበብን ያስተምራችኋል፣ የማታውቁትንም ያስተምራችኋል። እንግዲህ አስታውሱኝ፤ እኔም አስታውሳችኋለሁ፤ ለእኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም።»(አል-በቀራህ፣ 151–152) : እነዚህ ሁለት አንቀጾች አላህ ተዐላ ነቢያችንን ﷺ በመላክ በሰጠን ታላቅ ጸጋ ምክንያት፣ አላህን በብዙ ዓይነት መልካም ሥራዎችና ለርሱ ያለንን ታዛዥነት በሚገልጹ ተግባራት በብዛት እንድናወሳውና እንድናመሰግነው እንደሚፈልግ በግልጽ ያሳያሉ። የልዕልናው ባለቤት ታላቁ ጌታ ነቢያችንን ﷺ ላከልን። የአላህን አንቀጾች እንዲያነቡልን፣ መጽሐፉንና ጥበብን እንዲያስተምሩን እና ከክፉ ጠባዮች እንዲያጠሩን እርሳቸውን ለገሰን። ለዚህም አብዝታችሁ አውሱኝ፤ በጥብቅ አመስግኑኝ ሲል አዘዘን። ይህ ትዕዛዝ በይዘት አጠቃላይነት [ዑሙም] አለው። በሰፊ ተግባራት ትዕዛዙን መፈጸም ይቻላል። ትዕዛዙን መሰረት በማድረግ በመልካም መታዘዝ ከሚያካትታቸው ተግባራት መካከል፣ ከፍጥረታት ሁሉ ምርጥ ስለሆኑት ነቢይ ﷺ ልዩ ነገር ሲነሳ፣ አላህን በተለያዩ መልካም ነገሮች ልናወሳውና ልናመሰግነው ይገባል። የአላህን መልእክተኛ ﷺ ማውሳት፣ ሕይወታቸውንና ውብ ባሕርያቸውን የሚያወሱ መጽሐፍትና መድብሎችን አብዝቶ ማንበብ፣ የተባረከው የልደታቸው ወር ሲመጣ እርሳቸውን ለማውሳት መሰብሰብ፤ አላህ በነቢያችን ﷺ ላይ የሰጠንን ታላቅ ጸጋ ማስታወስ ተገቢ ነው። በእርግጥም እነዚህ አንቀጾች ግልጽ ናቸው! በእውቀትና በጥልቅ ማስተዋል ለሚመለከታቸው ሰው ጉዳዩን በግልጽ ያሳያሉ። እናም ጸጋን ማሰብና ማመስገን ነውር አይደለም!
የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል፦ «ማንኛውም ሙስሊም በንጽሕና (ዉዱእ) አላህን የዘከረ ሆኖ ካደረ፣ በሌሊት ከእንቅልፉ ቢነቃና ከዱንያም ሆነ ከአኺራ መልካም ነገርን ከአላህ ቢለምን፣ አላህ የለመነውን በእርግጥ ይሰጠዋል።» አሕመድና አቡ ዳውድ በሶሒሕ ሰነድ ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል፦ «ለሰዎች [ጆሮ እንዲደርስለት ብሎ ሥራውን] የሚያሰማ ሰው አላህም በቂያማ ቀን ያሰማበታል።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። 🔸መልካም ሥራን ሰዎች እንዲሰሙለትና እንዲያወድሱት ብሎ የሚሠራ፣ ለአላህ፣ የቂያማን ምንዳ ሽቶ ብቻ ያልሠራ ሰው፣ አላህ በቂያማ ቀን የውስጥ ዓላማውን በሰዎች ፊት ይገልጥበታል። ሚስጥሩን ለፍጥረት አሳውቆ ያዋርደዋል።
ሰይዲና ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «ነቢዩ [ﷺ] ወደ ደረታቸው አስጠጉኝና: «አላህ ሆይ! ጥበብን አስተምረው።» አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል። : ያ ረቢ እድያህን ስጠን!
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለው ዱዓ ያደርጉ ነበር፦ "رَبِّ تَقَبَّلْ تَوْبَتِي وَاغْسِلْ حَوْبَتِي وَأَجِبْ دَعْوَتِي وَثَبِّتْ حُجَّتِي وَسَدِّدْ لِسَانِي وَاهْدِ قَلْبِي وَاسْلُلْ سَخِيمَةَ قَلْبِي" «ጌታዬ ሆይ! ተውበቴን ተቀበለኝ፤ ኃጢአቴን እጠብልኝ፤ ዱዓዬን ተቀበለኝ፤ ማስረጃዬን አጽናልኝ፤ ልቤን ምራልኝ፤ ምላሴን አስተካክልልኝ፤ ከልቤም ጥላቻንና ጠላትነትን አስወግድልኝ።» 📚 በአሕመድና ሌሎችም ዘግበውታል። : ''ማስረጃዬን አጽናልኝ'' ማለት በዱንያ ላይ በጠላቶችህ ላይ የማቀርበውን ማስረጃ፣ የምናገረውን የእውነት ቃል የጸና አድርግልኝ። በቀብር ጥያቄ ላይ የማቀርበውን መልስ የጸና አድርግልኝ።… : 💛 ይህ ዱዓ ተውበትን፣ የልብ ንጽሕናን፣ ትክክለኛ ንግግርንና በሐቅ ላይ መጽናትን በአንድነት የሚያካትት እጅግ ውብ የነቢዩ [ﷺ] ዱዓ ነው። የዛሬ ጁሙዐ ዱዐችን እናድርገው። በዱዓችሁ ውስጥ አካትቱን!
Tofik Bahiru pinned «ዋጋህ ስንት ነው? «قيمتك قيمة ما أنت مشغول به.» «ዋጋህ የሚለካው በተጠመድክበት ነገር ልክ ነው።» ሰይዲ ኢብኑ ዐጧኡላህ አስ‐ሰከንደሪ : የሰው ልጅ ሁልጊዜ በተለያዩ ነገሮች ተጠምዶ ይኖራል። አንዳንዱ በዱንያ ጌጥ፣ ሌላው በወሬና በክርክር፣ ሌላው ደግሞ በቁርአን፣ በዒልም፣ በዚክርና በዳዕዋ ይጠመዳል። የልብህ ስራ የአንተን ዋጋ ይገልጣል። ስለዚህ ጊዜያችንን አላህን በሚያስደስት ሥራ…»
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
📚አል‐አዝካር ሚን ከላሚ ሰይዲል‐አብራር 📗 ክፍል 48:‐ በእንቅልፉ የሚደነግጥ ሰው የሚለው ዚክር፣ ህልም የተነገረው ምን ይላል?፣ በየሌሊቱ ሁለተኛ አጋማሽ ዱዓና ኢስቲግፋር ማድረግ፣ የኢስቲጃባ ሰዓትን ለማግኘት ሌሊቱን በሙሉ ዱዓ ማድረግ 📆 ሀምሌ 30/ 2018 ዓ. ል.
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
📚አል‐አዝካር ሚን ከላሚ ሰይዲል‐አብራር 📗 ክፍል 50:‐ አላህን ሳይዘክሩ መተኛት እንደሚጠላ፣ ሌሊት ነቅቶ ተመልሶ መተኛት የቸገረው የሚለው ዚክር እንቅልፍ ያስቸገረው ሰው የሚለው ዚክር 📆 ሀምሌ 29/ 2018 ዓ. ል.
ዋጋህ ስንት ነው? «قيمتك قيمة ما أنت مشغول به.» «ዋጋህ የሚለካው በተጠመድክበት ነገር ልክ ነው።» ሰይዲ ኢብኑ ዐጧኡላህ አስ‐ሰከንደሪ : የሰው ልጅ ሁልጊዜ በተለያዩ ነገሮች ተጠምዶ ይኖራል። አንዳንዱ በዱንያ ጌጥ፣ ሌላው በወሬና በክርክር፣ ሌላው ደግሞ በቁርአን፣ በዒልም፣ በዚክርና በዳዕዋ ይጠመዳል። የልብህ ስራ የአንተን ዋጋ ይገልጣል። ስለዚህ ጊዜያችንን አላህን በሚያስደስት ሥራ እንሙላው። ተወዳጃችን [ﷺ] እንዲህ ብለዋል፦ «نِعْمَتَانِ مَغْبُونٌ فِيهِمَا كَثِيرٌ مِنَ النَّاسِ: الصِّحَّةُ وَالْفَرَاغُ» «ብዙ ሰዎች የሚጎዱባቸው ሁለት ጸጋዎች አሉ፤ ጤናና ነፃ ጊዜ።» ቡኻሪ ዘግበውታል። : እስኪ ብድግ ብለን ዱሓ ሶላታችንን እንስገድና እንዲህ ብለን ዱዓ እናድርግ: ‐ አላህ ሆይ! አንተን በመዘከር፣ በቁርአን እንድንጠመድ አድርገን። በነቢያችን [ﷺ] ሐዲሶች ልባችንን አርካልን። በዑለማዎች ውዴታና በሷሊሖች ጉድኝት ልባችንን አብራልን። ሥራችንን ሁሉ ላንተ ብቻ የተወሰነ አድርግልን። አሚን!
ታዋቂው የእናታችን ኸዲጃ [ረዲየላሁ ዐንሃ] ንግግር ታላቅ የፍቅር እና የታማኝነት ትምህርት አለው።… የአላህ ነቢይ [ﷺ] የመጀመሪያውን ወሕይ ከተቀበሉ በኋላ በፍርሃት ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፣ እናታችን ኸዲጃ [ረዲየላሁ ዐንሃ] እንዲህ በማለት አጽናናቻቸው፦ «كَلَّا وَاللَّهِ لَا يُخْزِيكَ اللَّهُ أَبَدًا...» «በፍጹም አይሆንም! በአላህ እምላለሁ፣ አላህ ፈጽሞ አያዋርድህም፤ ዝምድናን ታፀናለህ፣ እንግዳን ታከብራለህ፣ ችግረኞችን ትረዳለህ፣ በእውነተኛ መንገድ ላይ በሚደርሱ ድንገተኛ መከራዎች ላይም ሰዎችን ታግዛለህ።»… ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። እነዚህ በጎ ሥራዎች ብዙ ወጪና ሀብት ይጠይቃሉ። ይህን ሁሉ ለማከናወን ነቢዩ [ﷺ] በኸዲጃ [ረዲየላሁ ዐንሃ] ሀብትና ድጋፍ ተጠቃሚ ነበሩ። ነገር ግን ኸዲጃ የራሳቸውን ድርሻ አላጎሉም፤ ክብሩን በሙሉ ለነቢዩ [ﷺ] ሰጡ፣ ሁሉንም የእርሳቸው መልካም ባሕሪ አድርገው ገለጹ። ይህ የታላቅ ሚስት ባህሪ ነው፤ ሥብዕናው የተሟላ፣ የልቅናን ከፍታ የረገጠ ወንድ ስታገኝ፣ በዚያ ላይ ለራሷም ጉዳይ ታማኝና ተንከባካቢ፣ በፍቅር ከባቢ፣ በውዴታው ተንከባካቢ ሆኖ ሲገኝ፣ ባሏን ለመደገፍ የምታደርገውን ነገር ወደራሷ አቅርባ አታይም። ባሏን ታበረታታለች፣ በአቅሟ ትደግፋለች። ነገርግን ስኬቱንም የገዛ ራሱ ክብር አድርጋ ታየዋለች። ለባሏ ካላት ክብር ጋር ሲወደር የሰጠችው ገንዘቧም ሆነ የለገሰችው ልፋት ኢምንት ሆኖ ይታያታል። የግርማው ባህር ውስጥ የሰመጠ፣ ያለምንም አማካይ ወደርሱ የተለጠፈ ክብር ታደርገዋለች። ምክንያቱም እርሷ ከእርሱ ናት፣ እርሱም ከእርሷ ነው!… የዓለም ሴቶች እመቤት፣ የምርጡ መልክተኛ ባልንጀራ፣ የታላቁ ሰው ረዳት፣ የፍቅር አጋር የሆኑትን እናታችን ኸዲጃን [ረዲየላሁ ዐንሃ] አላህ እንዲወድ እለምናለሁ። ከበረካቸው እና ከመልካም ባህሪያቸው ድርሻችንን እንዲያደርግልን እለምነዋለሁ። አሚን።