- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 133
- 1/48двое суток
- 152
- 1/72трое суток
- 164
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ሲራጀን ሙኒር ﷺ 💚 በአንድ ወቅት ሰይዲና አባስ ረዲየላሁ አንህ ለወንድማቸው ልጅ: «ያ ረሱለላህ! በተወሰኑ የግጥም ስንኞች እንዳሞግስህ ፍቀድልኝ።» ይሉታል። እርሳቸውም ለአጎታቸው ይፈቅዳሉ። አባስ'ም እንዲህ በማለት የረሱለላህ'ን ወደ ምድር የመምጣት ብስራት ውብ በሆነ መልኩ ይገልፃሉ። **** وأنت لما ولدت أشرقت الأرض وضاءت بنورك الأفق . فنحن في ذلك الضياء وفـــي النور وسبل الرشاد نختــرق *** እርሶ የተወለዱ ጊዜ ዓለም ፍንትው ብላ አበራች፤ አድማሱም በብርኃን'ዎ ተሞላ። እኛ’ም በእርሶ የብርኃን እና ግልፅ በሆነው የመመራት(ሁዳ) መንገድ ተጓዝን። ይላሉ 💚 በእርግጥም የሐቢበላህ ﷺ ወደ ምድር መምጣት ከውኑን ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ የሰው ልጅን ከክስረት ወደ ስኬት፣ ከጅህልና ወደ እውቀት፣ ከጭንቀት ወደ ሰላም አምጥቷል። በእውነቱ የሐቢበላህ ﷺ መምጣት ባዶ የነበረው ነፍስ ላይ ሩሕ ዘርቷል። አላህ'ም ረሱለላህ ﷺ ወደዚህ ምድር የመጡበትን አንድ አላማ እንዲህ በማለት በቁርኣኑ ይገልፃል: يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا «አንተ ነቢዩ ﷺ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን ላክንህ፡፡» ሱረቱል አህዛብ: 45 وَدَاعِيًا إِلَى اللَّهِ بِإِذْنِهِ وَسِرَاجًا مُّنِيرًا «ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪ ብርሃንም (አድርገን ላክንህ)፡፡» ሱረቱል አህዛብ: 46 ይላቸዋል። እርሳቸው ብርኃን ብቻ አይደሉም አብሪ ብርኃን እንጂ። የህይወታችን ኑር ማግኘት የመላካቸው ሰበብ ነው። ጌታዬ እራሱ አንተ ነብይ ሆይ! ብርሃንን ታፈነጥቅ ዘንድ ላክንህ ይላቸዋል። ወደ አላህ ለሚደረገው ጉዞ አብሪ ብርሃናችን ናቸው። ውዴ ﷺ አብሪ ናቸው። ያበራሉ። ንግግራቸው ልብ ላይ ብርሃን ይፈጥራል። ኑር የሆነው መልካቸው የጨፈገገውን ፊት በሙሉ ያስፈታል። በፍቅራቸው ያስቀልጣል። ነብዬ ﷺ አብሪ ኮኮብ ናቸው። ብርሃናቸው ዓይን አይወጋም ይልቅ ብርሃናቸው ለዓይን መድኃኒት ነው። ከእርሳቸው ጋር በጥልቀት መተሳሰር፣ እርሳቸውን መከተል፣ በሰለዋት ከእርሳቸው ጋር መቅረብ ህይወትን ይቀይራል፤ በበረካ የተሞላ ህይወትን ይሰጣል። ሰይዳة ሐሊማ ቤቷ ድርቅ ገብቶ አልነበር? የሚበላ ጠፍቶ አንድ ከሲታ ግመልና አህያ ብቻ አልነበራት? ህይወቷ በቅፅበት የተቀየረው ሸፊኢን ﷺ ለማሳደግና ለማ*ጥባት የወሰደች ጊዜ አልነበር? በረካ ቤቷ የገባው እኮ በእርሳቸው ምክንያት ነበር። ለእናታቸው አሚነት መልሳ መስጠት ያልፈለግችው እኮ የዓለሙ ብርኃን ህይወቷን ስለቀየሩላት ነበር። መገን ነብዬ ﷺ 💚 መዲናስ ሐቢበላህ ﷺ ሲገቡባት አይደል ከተማው ላይ ገብቶ የነበረው የወረርሽኝ በሽታ የተነሳው። የስሪብ'ስ መዲነተል ሙነወራ የሆነችው፤ ብርሃን የለበሰችው በእርሳቸው መምጣትም አልነበር? ... ካዒኑ ሁሉ ያበራው በእርሳቸው ምክንያት ነው። በድሩ ዱጃ 💚 አዎ'ን እኛም በሸፊዒ ﷺ ምክንያት አምረናል፤ አብርተናል ወብርተናል። በሳቸው ሱና አሸብርቀናል። በሰለዋታቸው ደምቀናል። ህይወታችን በደስታ የሚሞላው ከእርሳቸው ጋር ያለን ትስስር ሲጠብቅ፣ እንቅስቃሴያቸውን ኮቴ በኮቴ ስንከተል ነው። መጪው ረቢእ ደግሞ ለዚህ ትልቅ እድል ነውና አላህ ይወፍቀን 🥰 اللهم صل وسلم عل سيدنا وحبيبنا محمد 💚 #Welcoming_ረቢዑል_አንዋር 💚
видео или голосовое, без подписи
ረሱሉን ﷺ ከሪም 💚 በአንድ ወቅት ረሱለላህ ﷺ ዘንድ አንድ ሰሐቢይ ይመጣና የሚበላ ነገር እስኪያጣ እንደተቸገረ ይነግራቸዋል። በሰዓቱ ቤታቸው ውስጥ ምንም የሚበላ ነገር የሌላቸው የኛ ብርሓን ባልደረቦቻቸውን ጠየቁ። «በኔ ፋንታ ይህን እንግዳዬን የሚያስተናግድልኝ ማነው?» በማለት ጠየቁ። የዛኔ የቤቱን ሁኔታ ሳያውቅ አፍቃሪያቸው አቡ ጦልሓ «እኔ ያ ረሱለላህﷺ» አለ። እንግዳቸውንም ቤት ይዞት ሄደና ሚስቱን የሚበላ ካለ ጠየቃት። ለልጆቹ ብቻ የሚበቃ ምግብ እንጂ ምንም እንደሌለ ነገረችው! አቡ ጦልሓ'ም የውዴታውን እና የክብሩን ጥግ የሚያሳይ ንግግር ተናገረ። «ልጆቹን እያለቀሱም ቢሆን ቀደም ብለሽ፤ ቀስ ብለሽ አባብለሽ አስተኛቸው፤ ከዛም ኩራዙን አጥፍተሽ ምግቡን አቅርቢለት። እኔ እና አንቺ እንደምንበላ መስለን ድምፅ እናወጣለን። የዛኔ ይህ የረሱለላህ ﷺ እንግዳ ይበላል።» አላት! ... ጉድ እኮ ነው የመሐባ ነገር! 💚 አላህ ግን ከሰማየ ሰማያት የቁርኣን አያህ አወረደ። ጌታዬ የአቡ ጦልሓን እና የሚስቱን ስራ አደነቀ። ሱረቱል ሐሽር ላይ እንዲህ ይላል: وَيُؤْثِرُونَ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ وَلَوْ كَانَ بِهِمْ خَصَاصَةٌ «በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ፡፡» ... الله الله 🥺💚 ደግነት እንዲህ ነው። ረሱለላህ'ን መውደድ ልክ እንደ ሰሐቦች ነው። ከረም የሚጀምረው ለቤተሰባችን ከምንውለው ነው። ከዛ ለዘመድ፣ ለጎረቤት እያለ ወደ ማህበረሰብ ያድጋል። ደግነት ሁሌም ከኢማን ጋር ተሳስሮ እናገኘዋለን። አንድ ቦታ ላይ: «መን ካነ ዩዕሚኑ ቢላሂ ወልየውመል አኺር ፈልዩክሪም ጃራ: በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ለጎረቤቱ በጎ'ን ይዋል።» የሚል ሐዲሳቸውን እናገኛለን በተመሳሳይ መልኩ ለምስኪኖች በጎ ይዋል በሚልም እናገኛለን። 💚 ከረም ሌላ ፍቺው ክብር ነው። ደግነት ክብር ነው፤ ንፉግነት ደግሞ ዝቅ ማለት ነው። በእርግጥ መስጠት የቂን ይፈልጋል፤ ከሰጠሁት በላይ አላህ ይተካልኛል የሚል ሙሉ ለሙሉ የሆነን ተወኩል ይሻል። ልክ ሸፊዒ ﷺ: «አላህ ከሪም ነው፤ በጎ ሰሪዎችንም ይወዳል።» እንዳሉት ነው።... ለሰዎች በጎ መዋል በአላህ ዘንድ ያስወድዳል። የረሱለላህ ﷺ ቸርነት ከቃላት በላይ ነበር። አንዴ አንዲት የአንሳር ሴት ረሱለላህ ﷺ የሚለብሱትን ልብስ አይታ ቆንጆ ቶብ ልስራላቸው ብላ በእጅ ሰርታ ስጦታ ሰጠቻቸው። ሐቢበላህ'ም ለብሰውት ሰሐቦቻቸው ጋር ገቡ፤ በዚህ መሓል አንድ ሰሐቢይ ብድግ አለና: «ያ ረሱለላህﷺ! የለበሱትን ቶብ እንደ ሐዲያ ስጡኝ።» አላቸው። እርሳቸው'ም ምንም ሳያቅማሙ አሮጌ ልብሳቸውን ለብሰው አዲሱን ልብስ ሰጡት። 🥹 ሰሐቦች ይህንን በጠየቀው ሰው ተቆጡ ረሱለላህ ﷺ የተጠየቁትን ነገር አይሆንም እንደማይሉ እያወቅክ እንዴት ትጠይቃቸዋለህ አሉት። ሰውየው'ም: «እኔ እኮ ልብሱን የፈለግኩት በዚህ ዓለም ባለኝ ቆይታዬ ልለብሰው ሳይሆን፤ ስ*ሞት ከፈኔ እንዲሆን ሽቼ፤ በዚህም የእርሳቸውን ሸፈዓ ካገኘሁ ብዬ ነው።» ብሎ መለሰ። እንዳለው'ም የውዱ ነብይ ﷺ ቶብ ከፈኑ ሆነ!.. የመሐባ ነገር 💚 ሸፊዒ ﷺ እኮ ከዚህ ዓለም ሊሰናበቱ ትንሽ ጊዜ በቀራቸው ጊዜ ላይ እናታችን አዒሻ'ን: «ያ አዒሻ! ምን ያክል ገንዘብ አለን?» ብለው ጠየቋት። እርሷም: «ሰባት የብር ሳንቲሞች አሉ ያ ረሱለላህ!» አለቻቸው። ረሱሉል ከሪም'ም: «ያ አዒሻ! ይህ ገንዘብ በእጄ እያለ እንዴት አላህን እገናኘዋለሁ? ሁሉንም ለፉቀራዎች ስጪ።» አሏት!... እንግዲህ ይህ ምን ይባላል?....ይህንን አኽላቃቸውን'ስ ማን ችሎ ይወስፈዋል? اللَّهُ قَد صلّى عليهِ وسلّما هوَ سيّدُ الرسلِ الكرام محمّدُ أَولاهمُ بِعُلا المحامد أحمدُ وَأجلُّهم قدراً وأمجدُ أسعدُ አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሐቢቢና ሙሐመድ ﷺ 💚 #Welcoming_ረቢዑል_አንዋር 💚
видео или голосовое, без подписи
ሒራ'ን ጠይቁት 💚 የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ወህዩ ከመምጣቱ በፊት ቀን በቀን እውን የሚሆኑ ህልሞችን መመልከት ጀመሩ። አያታቸው አብዱልሙጠሊብ አግኝተውታል ተብሎ ወደሚነገርለት የጋሩ ሂራ ዋሻ መገለልንም መረጡ። አንዳንዴ ለሳምንታት፤ አንዳንዴም ለወራቶች ይቆዩ ነበር ይላሉ። ይህንን የመገለል ተግባር «التحنث» ይሉታል። ልክ እንደ እናታችን ኸዲጃ አጎት ወረቃ ወደ አንድ አምላክ ብቻ ተቅጣጩ። ጥሞናን መረጡ። ከማህበረሰቡ ተገለው ማስተንተንን ወደዱ 💚 የጋሩ ሂራ ዋሻ ልክ እንደሌላ ዋሻ ሰፊ ቀዳዳ ያለው አይነት ሳይሆን አንድ ሰው ብቻ የሚያስቀምጥ ነበር፤ ወደ ከዓባ'ም የዞረ መሆኑ ይበልጥ አስደናቂ ያደርግዋል። ዋሻው ካለበት ተራራ በታች ከዓባ ግልፅ ሆኖ ደምቆ ይታያል። የሪሳላው መጀመሪያ ከሆነ ቦታ ላይ የመልዕክታቸው ማገባደጃ የሆነውን ከብዙ መከራ በኃላ ድል የሚያደርጉትን የአላህ ቤት ይመለከታሉ። 😍 የነህጀል ቡርዳ ሻዒር አህመድ ሸውቂ ስለ ጋሩ ሂራና ስለነበረው እንዲህ በማለት ይገጥማሉ: **** سائل حراء وروح القـدس هـل علمـا مصـون سـر عـن الإدراك منكـتـم كـم جيئـة وذهـاب شرفـت بهـمـا بطحـاء مكـة فـي الإصبـاح والغسـم 💚 *** ያንን ሂራ ዋሻ፣ ያንን ሩኸል ቁዱስ የሆነውን'ም ጂብሪል ለሙሐመድ እንጂ ከሁሉም ስለተደበቀው ሚስጥር ያውቁ እንደሆን ጠይቋቸው፤ *** በእርሳቸው ጠዋትና ማታ መመላለስ የመካ ጠጠሮች ምን ያክል እንደተከበሩ ጠይቋቸው። ይላሉ.. ሒራ ጉድ ይዛለችና! ሐቢበላህ ﷺ ስለ ዋሻው ጊዜ ቆይታቸው እንዲህ በማለት ይናገራሉ: «ወህይ ከመምጣቱ በፊት ድንጋዮችና ጠጠሮች ወደ ጋሩ ሂራ በምሄድበት መንገዴ ላይ ሰላምታን ያደርሱልኝ ነበር።» ይላሉ! በዚህ የዋሻ ቆይታቸው መሐል ረሱሊﷺ ለብዙ ጊዜያቶች ሚስታቸውን እና ልጆቻቸውን ጥለው መውጣታቸውን ያስተዋሉ የመካ ሴቶች እናታችን ኸዲጃ ላይ ያፌዙ ጀመር። «ሁሉንም ነገርሽን ሰጥተሽው አሁን አንቺን ጥሎሽ ሄደ።» ይሏታል። ውዷ ሚስታቸው ግን የእነሱን ወሬና አሉባልታ ከቁብ አትቆጥረውም ነበር። «ለምን ሄዱ? ዋሻው ውስጥ ምን አለ? ዝምታን ለምን ወደዱ?» ብላ ጠይቃ አታውቅም። ፍቅር የሚገለፀው በዚህም አይደል? አላህ ከሁሉም ሴቶች የመረጣትም ለዚህ አይደል? ✨💚 ይልቅ እንደውም ያንን ረጅም ተራራ፤ ፀሐዩና አቧራው ሳይበግራት ቀን በቀን እየወጣች ምግብ ትወስድላቸው ነበር። በሁሉም እንቅስቃሴያቸው ላይ አጋዣቸው ናት፤ ታምናቸዋለች፤ ከነፍሷ በላይ ታፈቅራቸዋለች። ኣህ ያ ኸዲጃ! ጊዜው መጣ፤ ከብዙ ወራቶች መገለል በኃላ በህልማቸው በተደጋጋሚ የሚያዩት አካል(ሰይዲና ጂብሪል) ሒራ ዋሻ ውስጥ ባሉበት ወደእርሳቸው ይመጣል። በዚህ ድንቅ ዋሻ የመጀመሪያው የአላህ ቃል ይነበባል!... ነቢየላህ'ም ጨለማውን በተሰጣቸው መለኮታዊ ብርሓን ሊያበሩ የነብይነት ተልዕኮ እዚህ ቦታ ላይ ተሰጣቸው። ... ይህ ቦታ የዓለሙን መድኅን አቅፎ ያስተናገደ ድንቅ ቦታ ነው። የጋሩ ሒራ ሲር የሚገርም ነው። ረቢዑ እየመጣልን ነው ሞቅ ሞቅ አድርጉት! 🥰 አላሁመ ሰሊ አላ ሰይዲና ወሸፊዒና ወሐቢቢና ሙሐመድ ﷺ 💚 #Welcoming_ረቢዑል_አንዋር 💚
видео или голосовое, без подписи
ባልደረቦቻቸው ﷺ 💚 የሁደይቢያ ስምምነት አውርቼም ሰምቼም የማልጠግበው የሲራ ክፍል ነው። እያንዳንዱ ክስተት የሚሰጠው lesson በየጊዜው ይለያያል።... ሚስጥሩ አይዘለቅም! ... እንደሚታወቀው ሐቢበላህ በህልማቸው ሐጅ እያደረጉ ሲመለከቱ ባልደረቦቻቸውን ዘንድሮ ሐጅ እንደሚያደርጉ አሳውቀው ለጉዞ እንዲዘጋጁ አዘዙ። በድር ላይ መስዋዕትነት ለመክፈል ወደኃላ ያላሉት፤ ኡሁድና አህዛብ ላይ ከጎናቸው ያልተለዩት ሰሐቦች አሁንም ውዱ መልዕክተኛቸውን በመታዘዝ ኢህራማቸውን ለብሰው ወደ መካ ጉዞ ጀመሩ። ወደ ትውልድ ሐገራቸው የመመለስ ጉጉት፤ ሲናፍቁት የቆዩት ጊዜ መሆኑ ይበልጥ ደስ የሚል ስሜት ውስጥ ከቷቸዋል። ነገር ግን ጉዳዩ በተቃራኒ ሆኖ ሁደይቢያ ላይ ሰፍረው፤ ከመካ ሙሽሪኮች ጋር እጅግ ያልተዋጠላቸውን ስምምነት ተፈራርመው፤ መካ እንኳን ሳይገቡ ፀጉራቸውን ተላጭተው ወደ መዲና ሲመለሱ እጅግ በጣም ንዴት ውስጥ ገብተው ነበር። «ሰማን ታዘዝንም» በማለት የሚታወቁ የረሱሉ ﷺ ባልደረቦች ለእሳቸው ፊዳ ለመሆን የማያንገራግሩት ሰሐቦች መልዕክተኛው «በአሁኑ ሐጅ አናደርግም ወደ መዲና እንመለስ።» ሲሏቸው ደማቸው በንዴት የተንተከተኩ፤ ለመታዘዝ ጊዜ የፈጀባቸውን ሰሐቦች ይህ ከባድ ክስተት አስመለከተን!... ነገር ግን ቢናደዱም፤ ጉዳዩ ባይገባቸውም በመጨረሻ ነብያቸውን በመከተል ወደ መዲና ጉዞ ጀመሩ። የዚህን ጊዜ ጥበበኛው ጌታ ምርጡን ሱራ(ሱረቱል ፈትሕ'ን) አወረደ!... «ለቀድ ረዲየሏሁ አኒል ሙዕሚኒን... ፡ከምእምናኖቹ በዛፊቱ ሥር ቃል ኪዳን በሚጋቡህ ጊዜ አላህ በእርግጥ ወደደ፡፡» በማለት ከፍታቸውን መሰከረ። ሁደይቢያ በእርግጥ ቅርብ ፈትሓቹ ነው ተባሉ። ጌታዬ በዚህ ክስተት ላይ የነበሩትን ባልደረቦቻቸውን በሰፊው ካሞገሰ በኋላ ምዕራፉን ሲያጠናቅቅ እንዲህ ይላል! ... ይህ አያህ አሁን ላለንበት reality'ም ዓይንን ከፋች ነው ብዬ አምናለሁ! مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ تَرَاهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا (29) [Al-Fath: 29] «የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፡፡» • የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ ﷺ እነዚያም ከእርሱ ጋር ይሉት(ወዳጆቹ) 💚 አላህ ይህንን አያህ ሲቋጭ በዚህ ሁሉ ውሳኔዎች ውስጥ፤ ስምምነቱ ወደ ሙሽሪኮች ያዳላ በመሰላቸው ሰዓት ሐቢቢ ﷺ ተመለሱ ማለታቸው ንዴት ውስጥ ቢከታቸውም፤ እንደ ኡመር ያሉ ሰሐቦች «ሐቅ ላይ አይደለንም እንዴ?: እርሶስ የአላህ ነብይ ﷺ አይደሉም?» ብለው የጠየቁበት ክስተት እንደመሆኑ ዛሬም ሁሌም የመልዕክተኛቸውን ትዕዛዝና ውሳኔ ይቀበሉ ዘንዳ ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንደሆኑ በሱራው መደምደሚያ እንደ አዲስ አስታወሰን። ሱብሓነላህህህ 🥹💚 ሌላው የሚገርመው አላህ እዚህ አያህ ላይ ባልደረቦቻቸውን የገለፀበት መንገድ ይለያል!... «ወለዚነ አመኑ: ከእርሱ ጋር ያመኑ» ማለት ይችል ነበር፤ አላህ ግን «ወለዚነ መዓሁ:ከእርሱ ጋር ያሉት(ወዳጆች) ብሎ extinction ሰጣቸው!... የሁደይቢያ ክስተት ይህንን ልዩ ማዕረግ ቸራቸው። ስሜታቸው እጅግ በተረበሸበትና ሁኔታው ባበሳጫቸው ሰዓት እንኳን ባሳዩት ታዣዥነትና Loyalty ባልደረቦች ብቻ ሳይሆን ወዳጆች እንደሆኑ መሰከረላቸው።... የሳቸው ህመም ህመማቸው፡ የሳቸው ደስታ ደስታቸው የሆኑ ሰሐቦች እንደሆኑ ገለፀ! ... ይህንን ካለ በኃላ እንዲህ ይላል! 💚 •ከሓዲዎች ላይ ብርቱዎች፤ በመካከላቸው አዛኞች ናቸው። 💚 አላህ እዚህ ጋር «ከሓ*ዲዎች»ሲል አማኝ ያልሆኑትን በሙሉ ለማለት ሳይሆን ጠላ*ቶችን ለመግለፅ እንደሆነ እንደ ኢብን አባስ ያሉ ሙፈሲሮች ይተነትኑታል። በሰዓቱ ሁደይቢያ ለጠላቶቻቸው ጥሩ ቢመስልም፤ መካውያን ያንን ስምምነት ሲፈርሙ የዘመን ማብቂያቸውን ፊርማ እንዳሰፈሩ አልተረዱም ነበር። 😊 የእስልምና መርሕ ጠላቶቻ*ችን ላይ ብርቱዎች እርስ በእርስ ግን አዛኞች መሆን እንዳለብን ይገልፃል!...ሐቢበላህ'ና ባልደረቦቻቸው የዚህ ማሳያ ናቸው። አሁንስ? የ Cult mindset’ን የመገንባታችን ብዛት ወንድሞቻችን የሚመስሉን እራሱ የኛ ጀመዓ ውስጥ ያሉ ሰዎች ብቻ ናቸው። ሌላ ጀመዓ ውስጥ ያለን ሰው ስንመለከት፤ ወይንም የትኛውንም ጀመዓ ሳይቀላቀል የሚኖርን ሙዕሚን ሲመለከት የጠመመው መንገድ ላይ እንዳሉ የሚያስቡ ሰዎች ተፈጥረዋል! ጠላቶቻችን ላይ ብርቱዎች ከመሆን ይልቅ አማኙ ላይ እንሆናለን!… በአንድ ተልዕኮ ላይ ሊኖረን የሚገባን alignment ለአንድ ጀመዓና ድርጅት ለማድረግ እንጥራለን። አሁን ጉዳዩ የተቃራኒ ሆኖ ሙዕሚኖች ላይ ብርቱዎች፤ ለጠላቶ*ቻችን ደግሞ አዛኞች ሙናፊ*ቆችን በግልፅ እየተመለከትን እንገኛለን!... የዚህ ዑማ ኪሳራም ይህ ነው። ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ ምዕመን መሳይ አስመሳይ አየሩን ሞላው!... አላህ ይሁነን ብቻ! ጌታዬ ይህንን ባህሪ ከገለፀ በኃላ የሚያስከትለው ይበልጥ ውብ ነው 😍 • አጎንባሾች: ሰጋጆች ኾነው ታገኛቸዋለህ። ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ 🥹💚 አላህ አላህ! 💚... እነዚህ ለአንድ አላማ የተሰበሰቡ የመልዕክተኛው ወዳጆች እርስ በእርስ አዛኞችና ጠላት ላይ ጠንካራ ቢሆኑም surrender የሚያደርጉትና እራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡት ለአላህ ብቻ ነው!...ጌታዬ እዚህ ቦታ ላይ ሰጋጆች ብቻ ማለት ይችል ነበር አይደል?.. ግን የሰላቱን ክፍል ማንሳት ወደደ!…. «ركعاً : سجدًا» 💚 ለአላህ የሚኖረነንን መተናነስ የሚያሳየው የሰላት ክፍል ለእርሱ የምናጎነብስበት ነው። የሁሉም ሙዕሚን ግብ ለጌታችን አላህ ማጎንበስ፤ ተልዕኮውን ለማሳካት የእርሱን ውዴታ መፈለግ ላይ ያተኮረ እንደሆነ እንረዳለን። እነሱም ከአላህ የሆነውን «ፈድል:ችሮታ» እና «ሪድዋን:ውዴታን» ከምንም ነገር በላይ ይሻሉ! … Recognition’ን ከአላህ እንጂ ከሰው አይጠብቁም ነበር!... አላህ'ም በእርግጥ ስራቸውን ወደደ!... እኛንም አላህ ያስረዳን!...ስራችንንም በእርሱ ዘንድ ያስወድድልን! 😊 አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ሙሐመድ ﷺ 💚 መልካም ጁመዓ 💚
видео или голосовое, без подписи
ሰላሜ: ወዳጄ ﷺ ያ ረሱለላህ! ﷺ , የኔ ውድ መልዕክተኛ ﷺ, Our soul was designed to love you. to praise you. to know you. to be lost in your divine beauty, to feel the peace by calling your name day to night, to see you in our dreams 🥰💚 የረሱለላህﷺ ፍቅር ህይወትን ያበራል በዚያው ልክም እርሳቸውን መናፈቁ የማይረግብ ሸውቅ ውስጥ ይከታል። ህመም'ም አለው። ሰውባኑ ትዝ አላችሁ? ሐቢበላህ'ን ለቀናቶች ባይመለከት የገረጣው፤ ፊቱ የተለወጠው፤ የናፍቆት፤ የፍቅር ህመም የታመመው ሰውባን ትዝ አላችሁ?.. ሐቢበላህﷺ ሲያገኙት ሁኔታውን አይተው ምን እንደሆነ ቢጠይቁት «ያ ረሱለላህﷺ! እንዲህ የሆንኩት ህመም ወይንም ችግር ገጥሞኝ አይደለም። ነገር ግን እንዲህ የተጎሳቆልኩት እርሶን ለቀናቶች ባላመመልከቴ ነው። አይኔ እርሶን ባለመመልከቱ እረፍት አጣ። በየቀኑ አንቱን ማየት ሰላም ይሰጠኛል፤ አጠገብዎ ስቀመጥ እና የሚናገሩትን ሳደምጥ ልቤ በፍቅር ይሞላል። እደሰታለሁ። እርሶን ሳላይ ስቆይ እስካገኞት አንዳች ሐዘን ይከበኛል። ይናፍቁኛል፤ ከዛም የውመል አኺርን አስባለሁ፤ እኔ ጀነት ብገባ እንኳን የምገባው ከእርሶ በታች ባለው ደረጃ ላይ ነው፤ አንቱ ደግሞ ከነብያቶች ጋር በላይኛው ደረጃ ላይ ኖት። የዛኔ ባላዬትስ፤ ባላገኞትስ ብዬ እሰጋለሁ። እሱ ነው ያከሳኝ።" በማለት የቀለጠ ፍቅሩን የገለፀላቸው ሰውባን رضي الله عنه ትዝ ይለኛል። 💚 አላህም ለዚህ ፍቅር ምላሽ ይሰጣል። «አላህና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፤ ከፃድቃንም፤ ከሰማዕታትም፤ ከመልካሞቹ ጋር ይኾናሉ። የእነዚያም ጓደኝነት አማረ።» የሚል አያህ ወረደ። ... አላህ የአፍቃሪያቸው ሰውባንን ከልብ የመነጨ ፍቅር ተመለከተ። ምስክርነቱንም ሰጠ። ሽልማትንም አስከተለ የረሱለላህ ﷺ ፍቅር ያሸልማልና። ከልብ የናፈቀ ከናፈቀው ጋር መገናኘቱ አይቀርምና። የእርሳቸው ፍቅር የጀነት ደጃፍ ያደርሳል። ወንድም ዛሒድ በአንድ ግጥሙ ላይ እንዲህ ይላል: በነገው የሹመት ሸንጎ ከሁሉም ፍቅር ያነግሳል፣ የጀነት እጣ ሲታደል አፍቃሪም ብቻውን ኣይቀር! ካፈቀረው ጋር ይነሳል። 💚💚💚💚 አላህ በፍቅራቸው ያቅልጠን! በጌታችን ዘንድ እውቅና ያለው፤ ምስክርነት የሚሰጠው መሐባን ይለግሰና 🥰 اللهم صل على سيدنا محمد طب القلوب ودوائها، وعافية الأبدان وشفائها، ونور الأبصار وضيائها، وقوت الأرواح وغذائها، ونضارة الوجوه وبهائها، وأس العقول وصلاحها، وعين الحقائق ومفتاحها، وهدي الكائنات وفلاحها، وسر الألباب ومصباحها، وروح الجنان ورواحها، وعطر المجالس وفواحها، وبهجة النفوس وانشراحها، وعلى والديه وآله وصحبه أجمعين #Welcoming_ረቢዑል_አንዋር 💚
видео или голосовое, без подписи
ስማቸው ﷺ ብቻውን ተዓምር ነው 💚 እናታችን ኡሙ ሰለማ እጅግ በጣም የምትወደውን ባለቤቷን አቡ ሰለማን በሞ*ት ካጣች በኃላ የብዙ ሰዎችን የትዳር ጥያቄ እምቢ አለች። ከአቡ ሰለማ የበለጠ ማን አለ'ም አለች። የዚህን ጊዜ የከውኑ ብርሓን የሆኑት ነብይ ለትዳር ጠየቋት። መልዕክተኛውም ﷺ ካገቧት ከቆይታ በኃላ ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: "فقد أبدلني الله بأبي سلمة خيرا منه رسول الله" «አላህ ከአቡ ሰለማ በላቀ ሰው ካሰኝ(ሸለመኝ)፤ የአላህ መልዕክተኛ'ን።» በማለት ትመሰክራለች። በእዚህ ሰበብ'ም አገልጋይዋ የነበረውን ትክክለኛ ስሙ ወይ ረባሕ፣ ወይም ሚህራን ወይም ደግሞ ሩማን የሆነን ሸፊዒ በአንድ አጋጣሚ ሰፊና የሚል ስያሜ የሰጡትን ሰሐቢይ ከባርነት ነፃ ታደርጋለች። ይህንንም ያደረገችው በአንድ ቅድመ መስፈርት ነበር፤ ህይወቱ እስክታበቃ ድረስ የነቢየላህ ﷺ ኻዲም እንዲሆን ነበር። ሰፊና'ም መስፈርቱን በደስታ ተቀበለ። የነቢየላህ መውላ(በእርሳቸው ከባርያነት ነፃ የሆነ) የሚል ስያሜ'ም ተሰጠው። ከዛ በኃላ ረሱለላህ ﷺ መንገድ ሲወጡ አብሯቸው ይወጣል፣ የሚያስፈልጋቸውን ለማሟላት ይሞክራል። በአንድ የጉዞ አጋጣሚም ሰፊና የሚለውን ስያሜ ያገኛል። እንዲህ በማለት ይናገራል: «በአንድ ወቅት ሁላችንም በጉዞ ላይ እያለን ከሁሉም ባልደረባ ይበልጥ አጋዥ እኔ መሆን ስለፈለግኩ የሁሉንም እቃ ለመሸከም ሞከርኩኝ። ሁሉም ጎራዴውን እና ጋሻውን እየሰጠኝ መንገዱን ይቀጥላል የዚህን ጊዜ ረሱለላህ ﷺ የያዝኩትን የእቃ ብዛት አይተው ተገረሙና ፈገግ ብለው: «ما أنت إلا سفينة: አንተ መርከብ እንጂ ሌላ አይደለህም።» አሉኝ። ከዛ በኃላ ሰዎች ስሜን ሲጠይቁኝ እኔ ሰፊና ነኝ ብዬ ነበር የምመልሰው። ይለናል 🥹💚 ረሱለላህ ﷺ ካረፉ በኃላ ሰፊና ዝም ያለ ህይወትን ይመራ እንደነበር ይገለፃል። የፊትናው ጊዜም በኺላፋው ጉዳይ ላይ እራሳቸውን ካገለሉ ሰሐቦች መካከል ነበር። የሰፊና የህይወት ቆይታ ውስጥ የሚነሳ ትልቅ ክስተት አለ። የእርሱ ከራማት የታየበት፤ የሸፊዒ ﷺ ስም ኃያልነት የተንፀባረቀበት ክስተት ነበር። በአንድ ወቅት ሰፊና እና ባልደረቦቹ በመርከብ እየተጓዙ ባለበት መርከባቸው መንገድ ስቶ ወደ አንድ የባህር ዳርቻ ይወስዳቸዋል። ዳርቻው ላይ እንደወጡም ፊትለፊታቸው አንበሳ ይመጣል። አንበሳው ሲጠጋቸውም ሰፊና እንዲህ ይላል: يا أبا الحارث، أنا سفينة مولى رسول الله صلى الله عليه وسلم «ያ አበል ሐሪስ(የአንበሳው ኩንያ)! እኔ በረሱለላህ ﷺ ነፃ የወጣሁ ባሪያ ሰፊና ነኝ።»አለ። ይህንን እንደሰማም አንበሳው ባለበት ቆመ። የነብዩን ስም ሲሰማ በክብር አንገቱን አዘቀዘቀ። ሰፊና'ም መንገዱን እንዲመራቸው ጠየቀው። አንበሳውም ሰፊና'ን እና ባልደረቦቹን መንገድ መራቸው። ሱብሓነላህ 💚💚 የሐቢበላህ ﷺ ስም በእንስሳቶች ዓለም ንጉስ የሚባልን ኃያል አንበሳ ያንቀጠቅጣል። ስማቸው፣ ፍጥረታቸው ለእንስሳውም፣ ለቅጠሉም፣ ለአዕዋፉም ለሰማዩም መድኃኒት ነው። አላህ ነቢየላህ ለዓለማት እዝነት ነው የተላኩት ሲለን የሚገባን እንዲህ ያሉ ክስተቶችን ስናነብ ነው። ነቢ መሻሪያችን ናቸው። ነቢ ትርታችን ናቸው። ሐቢበላህ ﷺ ሽልማታችን ናቸው 🥰💚 አላሁመ ሶሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ወሐቢቢና ሙሐመድ ﷺ 💚 #Welcoming_ረቢዑል_አንዋር 💚
видео или голосовое, без подписи
ኢማሙል ሙተቂንﷺ : ሸፊዓል ሙዝኒቢን ﷺ 💚 ሐቢበላህ ኢማም ናቸው፣ የከውኑ ሰይድ ናቸው፣ የአምላካችን ተወዳጅ ናቸው ግን ለይሉን እግራቸው ውሃ እስኪቋጥር ይቆማሉ፤ ጌታቸውን ይማፀናሉ፣ ለህዝባቸው ያለቅሳሉ። ደግሞ'ም ብዙ አጋጣሚዎች ላይ ዘይኔ ይራባሉ። ከሰሐቦቻቸው ጋር ሆነው ምግብ ፍለጋ ሆዳቸውን በድንጋይ አስረው ረሃባቸውን ያስታግሳሉ። ሩሂ ፊዳክ ያ ነቢየላህ ﷺ 😭 ሐቢበላህ ኢማም ናቸው፣ የከውኑ ሰይድ ናቸው፣ የአምላካችን ተወዳጅ ናቸው ግን ለይሉን እግራቸው ውሃ እስኪቋጥር ይቆማሉ፤ ጌታቸውን ይማፀናሉ፣ ለህዝባቸው ያለቅሳሉ። ደግሞ'ም ብዙ አጋጣሚዎች ላይ ዘይኔ ይራባሉ። ከሰሐቦቻቸው ጋር ሆነው ምግብ ፍለጋ ሆዳቸውን በድንጋይ አስረው ረሃባቸውን ያሳልፋሉ። ለማን?... ለእኔ እና ለመሰሎቼ!.. ሸፊዒ ﷺ ለዑመታቸው ብዙ ነገርን ሆኑ ይህ ያብከነከናቸው ሰይድ ቡሰይሪ'ም በቡርዳቸው ላይ እንዲህ አሉ: ظلمت سنة من أحيا الظلام إلــــــــــى أن اشتكت قدماه الضر مــــــن ورم وشدَّ من سغب أحشاءه وطــــــــــوى تحت الحجارة كشحاً متـــــرف الأدم 😭 ረቢዑ እየመጣልን ነው የዚህን ሰፈር ድባብም ወሩ ላይ ብቻ ሳይሆን ቀድመን መቀየር ስላለብን ከግጥሞችም: ከሲራቸውም እየተጎነጨን መርሐበን ያ ረሱለላህ ﷺ እንላለን 🥰💚 አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ሙሐመድ ﷺ 💚 #Welcoming_ረቢዑል_አንዋር 💚
видео или голосовое, без подписи
💚💚 ስለ ፍቅር ብዙ ተነግሯል፤ ተዤሞዋል፤ ተገጥሟል። ግን ስለ ፍቅር ማውራት አይጠገብም። አያሌ ደራሲዎች የፍቅር ታሪኮችን መክተባቸውን አያቆሙም። እዚህ አለም ላይ መዋደድ፤ መፋቀር ባይኖር ምን ይሆን ነበር ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ?! ማሰቡ እንኳን ከባድ ነው። አላህን ሳናፈቅር ማምለክ፤ ሸፊዒን ሳናፈቅራቸው መከተል አይቻለንም! ለዛም ነው የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በአንድ ወቅት «ከእናንተ ውስጥ አመነ አይባልም እኔን ከነፍሱ፤ ከቤተሰቡ እና ከልጆቹ በላይ እስካልወደደ ድረስ።"»ያሉት! ከእምነቱ በፊት እሳቸውን መውደድ ቀድሟል። ሰይዲና አባበክር ሸፊዒን ﷺ ባያፈቅሩና በፍቅራቸው ባይለከፉ ኖሮ እነዛን ሁሉ መስዋዕትነት ይከፍሉ ነበር? ሰይዲና አሊይ ፍቅራቸው ባይጠልፋቸው በልጅነታቸው በሳቸው ፋንታ ፊዳ ለመሆን አልጋቸው ላይ ይተኙ ነበር? ... ያ አዕራቢይ «የውመል አኺር መች ነው?» ብሎ ሲጠይቅ፤ ነቢየላህ ﷺ «ምን አዘጋጅተኻል?» ሲሉት «ምንም አላዘጋጀሁም ነገር ግን አላህን እና መልዕክተኛውን ﷺ እወዳለሁ።» ብሎ ሲመልስ ሐቢበላህ "المرء مع من احب : አንድ ሰው ከወደደው ጋር ነው።» ብለው የመለሱለት የፍቅር'ን ሐይል ስለሚያውቁ አይደል?! 💚 ከመዲና የነበረው ረቢዓ ኢብን ከዓብ ሸፊዒ ﷺ ሒጅራ ከማድረጋቸው በፊት ስለሳቸው በተነገረው ነገር ብቻ ሳያያቸው ወዷቸው፤ ሒጅራ ሊያደርጉ ነው ሲባል መዲና ላይ ሆኖ እንደሌሎቹ መጠበቅ ቢያቅተው የመዲና ዳርቻዎቹ ላይ ጠብቋቸው ልክ እንደተመለከታቸው «ለመጀመሪያ ጊዜ አይኔ ረሱለላህን ﷺ ሲመለከት አካሌን ሙሉ ለሙሉ የሚቆጣጠር ፍቅር አካበበኝ፤ ወደድኳቸውም።» በማለት ፍቅሩን መግለፁ የመሐባ'ን ረቂቅነት ያሳይ አይደል?! ፍቅር ከፍ እያለ ሲመጣ ኢሽቅ ይሆናል። ለዛም ነው ኡለሞች «አንድ ሰው የኢሽቅ ደረጃ ላይ ከደረሰ በአላህና መልዕክተኛው ፍቅር ይሰጥማል! እነሱን መገናኘትን፤ ጉርብትናቸውን ለማግኘት እጅጉኑ ይጓጓል። የመገናኛው ጊዜ በረዘመ ቁጥር ሸውቁ ያቃጥላቸዋል፤ ይታመማሉ! ህመማቸው የሚድነው ደግሞ የወደዱትን ሲያገኙ ብቻ ነው።» ይላሉ! የአላህ መልዕክተኛን ﷺ መውደድ እሳቸውን በማወቅ ይጀምራል! እሳቸውን በመቅረብ፤ ሰለዋት ለማውረድ ካለመሰሰት ይነሳል! የምንወደውን ሰው አይደል በብዛት የምናስታውሰው?! ሸፊዒ'ን ﷺ እጅጉኑ የወደድን ሰአት በብዛት የምናስታውሰው እሳቸውን ይሆናል። መልካም መዓዛ፤ ቆንጆ ቦታ፤ መልካም ስነምግባር እና ሰዎች ሁሉ እሳቸውን ያስታውሱናል! የሳቸው ስም ያልተጠቀሰባቸው ስብስቦች ሁሉ ይጨንቁናል። ስማቸው ሲጠራ ልባችን አብሮ ይነቃነቃል! አይኖቻችን እንባ ያቁራሉ። በሐሳብ እሳቸው ጋር ይወስደናል! የዛኔ የሳቸውን ሱና በፍቅር እንከተላለን። የሰሩት፤ የነኩትን ሁሉ ለማድረግ እንጓጓለን። ከምንም ነገር በላይ ደግሞ የእሳቸውን የጀነት ላይ ጉርብትና እጅጉኑ እንመኛለን። 🥹💚 አላሁመ ሰሊ አላ ሐቢቢና ወሸፊዒና ሙሐመድ 💚 በሰለዋት እና ዱዓ አሽቁ! 💚
видео или голосовое, без подписи