tgindex
ዳዕዋ እና ተብሊغ - Da'wah and Tabligh

ዳዕዋ እና ተብሊغ - Da'wah and Tabligh

Статистика

ዳዕዋ እና ተብሊግ - Da'wah and Tabligh ስለ ዳእዋ ወተብሊغ የምንማርበት እና ኢስላማዊ የሆኑ መረጃዎችን የምናገኝበት ፔጅ ነዉ

Последний пост
13 дек. 2024 г.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
1 088
+1 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 328
22 постов
Вовлечённость
214,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • لاتنسوا فى يوم الجمعة الصلاة على النبى ﷺقالﷺ:"البخيلُ مَن ذُكرت عِندهُ ثُم لَم يُصَلِّ عليَّ". قال الحسن بن محمد:رأيت أحمد بن حنبل في المنام . فقال لي: يا أبا علي لو رأيت صلاتنا على النبي ﷺ في الكتب كيف تزهر بين أيدينا. قال ابن القيم: "لَو صلَّى العبد على النَّبي ﷺ بِعدد أنفاسه,لم يكن موفيا لحقه" 📚جلاء الأفهام قال رسول اللهﷺ: (من قرأ سورة الكهف في يوم الجمعة، أضاء له من النور ما بين الجمعتين. ) رواه الحاكم والبيهقي وصححه الألباني. كان الإمام أحمد يقرأ سورة الكهف وهو يذهب لصلاة الجمعة. المغني قال ابن دقيق رحمه الله : "مات صديق لي فرأيته في منامي فقال: ""لما مكثت في قبري، اقترب مني كلب بري، فزعت كثيراً، فأتى شخص جميل وأخذه بعيداً، وجلس معي، وأعطاني قلبه"" قلت: من أنت؟ قال: "أنا أجيد قراءة سورة الكهف" الدرر لبن الحجار ﷺ صلى الله على محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه وسلم @tebligda

  • видео или голосовое, без подписи

  • አላህዬዋ ከኋላው ህመም የሌለበት ጤና ከኋላው ሀዘን የሌለበት ደስታ ከኋላው ስጋት የሌለበት ሰላም ከኋላው ችግር የሌለበት ምቾት ከኋላው ድህነት የሌለበት ሀብት በዱንያም በአኼራም ደስታን ኑሯችንም ሞታችንንም በላኢላሀኢለላህ አድርግልን ኸይሩን ሁሉ ወፍቀን!!🤲 አሚን ሰሉ አለ ነቢ:- አላሁመሰሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐላ ሰይዲና ሙሐመድ ﷺ @tebligda

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🦋ሠይደል ዉጁድ ﷺ🩵 ይደገፉት የነበረው የተምር ጉቶ ሚንበር ከተሰራላቸው በኋላ ዛት እና ዚክራቸውን ናፈቀ ..ናፍቆት መግለጪያውን ከሰውኛው መንደር ተውሶ ማልቀሱን ያዘ አንዳንዶቹ እንዳሉት ❝ እንደ እርጉዝ ግመል በአሳዛኝ ድምጽ ጮኸ❞ የትኛው ይሆን ግን የሚደንቀው? የእንጨቱ ማልቀስ ወይስ የሶሃባዎቹ ለቅሶውን መስማት? 🦋የሚደንቀውማ የኛ ኸበሩን ሰምቶ ዳግም መገፈላችን ነው👐 💚💚💚 اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِك علــى نَبِيِّنَـــا مُحمَّدﷺ ሰሉ አለ ነቢ😘 @tebligda

  • видео или голосовое, без подписи

  • ወለል ያለው ባሕር የማይደፈርሰው፣ የታመነው ገመድ የማይበጠሰው! እንደ‘ሳቸው ያለ ደግና አዛኝ መሪ ማንም እናት አልወለደችም። ሰይዱና ዓሊ ረ.ዓ ከመካ ተነስተው መዲና የገቡ ጊዜ ያንን ረጅም ርቀት የተጓዙበት እግራቸው ቆሳስሎ ነበር። ሁኔታቸውን ያዩት የኔ ነቢ አለቀሱና ዝቅ ብለው እግራቸውን በሃር እጃቸው ያሹ ጀመር። እንዲህ ነው ለሁሉም እንስፍስፍ የሚሉት። የኔ አንጀተ ቀጭን! ደረጃቸው ዓለም ካነገሰቻቸው ነገስታት ሁሉ እጅጉን የላቀ ሆኖ ሳለ፣ መለክ የተባለ ሊታዘዝ ሊያገለግላቸው የሚጋፋላቸው ሆነውም እርሳቸው የመረጡት ግን ቀለል ብሎ መኖርን ነው። የሚተኙበት ትራስ ከሌሎች በተለዬ እንዲለሰልስ አይፈልጉም። መሪ ቢሆኑም ሰዎች በአጀብ ከኋላቸው ሲከተሏቸው ደስ አይላቸውም። ይልቁኑ እሳቸው ከኋላ ይሆኑ ነበር። ከሌሎች ተለይተው ከፍ ብለው መቀመጥ አይወዱም። ከባልደረቦቻቸው ጋር በተቀመጡበት እንግዳ ቢመጣ ነቢ የትኛው እንደሆኑ ሳይነገረው ማወቅ አይችልም። መገኛቸው የድሆች ቤት ነው። ሚስኪኖች ጠርተዋቸው አይቀሩም። አቅመ ደካሞችን ይቀርባሉ። ቀለል ያለ ምግብ ይመገባሉ። ቴምርና ወተት ያዘወትራሉ። ምንም ባይኖራቸውም፣ የሰሙት ድንገት ቢሆንም ሰው ታመመ ከተባሉ ሲከንፉ ይሄዳሉ። ባሮች ለጉዳያቸው እንደሳቸው የሚሆንላቸው ሰው አልነበረም። ጊዜ ሰጥተው ሁሉንም ያዳምጣሉ። ክብር ተነፍጓቸው የኖሩት ሴቶች ቀና ከፍ ያሉት በረሱሉሏህ ነው። ችግራቸውን ይፈታሉ። ሃዘን ህመማቸውን ይሸከማሉ። ጭንቃቸውን ያቀላሉ። ጦርነት ሲገቡ በቅድሚያ ባልደረቦቻቸውን ይመግባሉ። እነሱ ሳይጠግቡ እህል በአፋቸው አይዞርም። ከዛም ለራሳቸው ትንሽ ይቀምሳሉ። ሌሎች ምቾት ከሚያጡ መርራብን ነበር የሚመርጡት። ለፈለጋቸው ሁሉ በራቸው ምንጊዜም ክፍት ነው። የሁሉ ደህንነት ያሳስባቸዋል። ስለ ሁሉም ሰው ይጠይቃሉ። የሚዘነጉት፣ ችላ የሚሉት የለም። ረዳት የሌላቸውን ደግሞ ራሳቸው ይንከባከባሉ። ባልደረቦቻቸው ከነፍሶቻቸው አብልጠው ይወዷቸዋል። ይሳሱላቸዋል። ምንም ይፈልጉ ምን ሰዎች እንዲያደርጉላቸው አይጠብቁም። ትእዛዝ አያበዙም። ራሳቸው መሥራት ይቀናቸዋል። የቀዬው ነዋሪ ጉዳይ ካለው ይሳተፋሉ። ግንባታ ቢጀምር አናጢ ይሆናሉ። የመስጅድ ምሰሶ በእጆቻቸው ያቆማሉ። ለጋስ ናቸው። ቸርነታቸው ላይ የሚደርስ የለም። ከእርሳቸው ምንም ነገር ፈልጎ ያጣ ማንም የለም። ከእጃቸው ጠይቆ ያልተሰጠው አንድም የለም። ፈፅሞ አይሆንም ወይም እምቢ ብለው አያውቁም። ከልጆች ጋር እንደ ልጅ ይጫወታሉ። ታላላቆቻቸውን አብዝተው ያከብራሉ። ለእንሰሳት ያዝናሉ። እኛን ደግሞ ገና እዚህ ምድር ሳንመጣ ነው የወደዱን የናፈቁን። ቆንጆ ናቸው። "እንደሱ የሚያምር ማንም ማን አይወልድ!" ያስባሉ። ጀማላቸው የዩሱፉል ጀሚልን ውበት ያስከነዳ፣ ድምፃቸው የጀሊሉን ዳውድ የዘባ፣ ንግግራቸው ልብ የሚሰረስር። ዓይን ከሳቸው የተሻለ አላየችም። ምድር የሳቸው አይነት አላበቀለችም። ሸኽ ሠይድ ጫሌ ፊትም አላለፈ በኋላም አይመጣም፣ መልኩን ያዬው ችሎ ካለበት አይወጣም። ብለዋቸዋል። ስለ ምግባርና መልካቸው ላውጋ ያለ ቀድሞ ቀለምና መድ ያልቅበታል እንጂ ወጉን አይጨርስም። የሩሕ ቀለቡ፣ የለሕድ መብራቱ፣ ሲራጥን አሻጋሪው፣ የጭንቁ ቀን አማላጁ፣ የሐውድና ከውሰር ጠላቂው፣ የጀነት ድግስ አሳላፊው ሙስጦፈል አሚን። #ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ! አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚 @tebligda

  • видео или голосовое, без подписи

  • ሸህ ሰአድ ከኒዛሙዲን መርከዝ ከኢሻ ሰላት ቡሀላ ሀያቱ ሰሀባ ያለ ትርጉም @tebligda

  • ️የሰላተል ጀናዛ አሰጋገድ‼️ ******************* ወደ ሰላት ከመገባቱ በፊት 💫እንደ የትኛውም ሰላት ሙሉ የሆነ ውዱእ ይደረጋል። 💫እንደ የትኛውም ሰላት ወደ ቂብላ ይቀጣጫል። 💫እንደ የትኛውም ሰላት ሰፍ ይስተካከላል። 💫እንደ የትኛውም ሰላት ማእሙኖች ኢማሙን ተከትለው ይቆማሉ። 🔘የሰላቱ አሰጋገድ ✍️የመጀመሪያው ተክቢራ ይባልና… ሱረቱል ፋቲሃ ይቀራል። {بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ} {الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ} ይህንን ሲጨርስ ሁለተኛው ተክቢራ ይላል። ✍️ከሁለተኛው ተክቢራ በኋላ…… በነብዩﷺ ላይ ሰለዋት ያወርዳል። «اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد» ይልና ሶስተኛው ተክቢራ ይላል ✍️ከሶስተኛው ተክቢራ በኋላ…… ለሟቹ ዱዓ ያደርግለታል። ለምሳሌ ከመጡ ዱዓዎች መሃል…… «اللهم اغفر له وارحمه، وعافه واعف عنه، وأكرم نزله، ووسع مدخله، واغسله بالماء والثلج والبرد، ونقه من الخطايا كما ينقى الثوب الأبيض من الدنس، اللهم أبدله دارًا خيرًا من داره، وأهلًا خيرًا من أهله، اللهم أدخله الجنة، وأعذه من عذاب القبر، ومن عذاب النار، ووسع له في قبره، ونور له فيه» ከዚህም ውጪ ያሉ ዱዓዎች የቻለውን ያደርግለታል። ይህንን ሲጨርስ አራተኛው ተክቢራ ይላል። አላሁመላተህሪመ አጅረሁ ወላ ተፍትና በእደሁ ወግፊር ለና ወለሁ ✍️ከአራተኛው ተክቢራ በኋላ… ቲንሽ ዝም ይልና እዛው በቆመበት ወደ ቀኝና ወደ ግራው ያሰላምታል። «السلام عليكم ورحمة الله, السلام عليكم ورحمة الله» ይላል። 🔘አንዳንድ ነጥቦች 💫ጀናዛው ከኢማሙ ፊት ይቀመጣል። ጀናዛው የወንድ ከሆነ; ኢማሙ ጭንቅላቱጋ ይቆማል። ጀናዛው የሴት ከሆነ; ኢማሙ ወገቧ አካባቢ ይቆማል። 💫ባለው የሰጋጆች ብዛት ረዥም ሰፍ ከመስራት ይልቅ ሰፎቹ መብዛታቸው ይመረጣል። 💫አራቱንም ተክቢራዎች ሲባሉ እጅ ማንሳቱ የተሻለ የተወደደ ነው። 💫አንድ ሰው ኢማሙ የተወሰነ ከሰገደ በኋላ ደርሶ ወደ ሰላቱ ቢገባ የሚጀምረው ኢማሙ ከደረሰበት ቦታ ሳይሆን ከመጀመሪያው ቦታ ነው። ለምሳሌ፦ ኢማሙ የሁለተኛው ተክቢራ ሲያደርግ ቢደርስ እሱ የሚያደርገው ሰለዋት ማውረድ ሳይሆን ፋቲሃን መቅራት ነው; በመጨረሻ ኢማሙ ሲያሰላምት ቶሎ ቶሎ ብሎ ይጨርስና ያሰላምታል። 💫አንድ ሰው ጀናዛ ቢያመልጠውና መስገድ ቢፈልግ ጀናዛው ቢቀበር እንኳ ቀብሩ አጠገብ ሄዶ ይሰግድበታል። @tebligda

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ጀማዓተ ተብሊغ የዳዕዋ ማኒፌስቶ አንድ ገጽ አይሞላም:: ስድስት የሶሃቦች ጉልህ ባሕሪያት እና ሀያ ስነሥርዐት ይላል:: ከ100 ዓመታት በላይ በዚህ ሕገ-ዳዕዋ ተንቀሳቅሰው ከምሥራቅ ፀሐይ መውጫ እስከ ምዕራብ ፀሐይ መጥለቂያ ተጉዘዋል:: ነቢያት እና አውሊያኡላህ ዱንያን ከአጠገባቸው እንዳራቁት በጀማዓተ ተብሊغ ዘንድ ዱንያ ቦታ የላትም:: ስሟ እራሱ "አስባብ" ነው የሚሏት:: ጊዜ እና ገንዘብ ከፍለህ ነው የምትሳተፈው:: የደመወዝ ፔይሮል አላህ ዘንድ ነው:: ከፍጡር ደመወዝ ልትከጅል ቀርቶ አስባብ (በጀት) ከኪስህ ነው የምትመድበው:: የጀማዓተ ተብሊغ ኑሮ የተረጋጋ ነው:: የእንቅስቃሴ መታወቂያቸው ፊታቸው ላይ ያለ ብርሃን ነው:: ፊታቸውን አይተህ ከሕዝብ መሀል ትለያቸዋለህ:: በፈገግታቸውና በብርሃናቸው የትኛውንም ጥብቅ ኬላ ያልፋሉ:: አሁንም ዱንያን ተጠንቀቁት:: ፈላህና ነጃህ በዲን እንጂ በዱንያ አይደለም:: ከመካከላችሁ የዱንያ ሰዎች ካሉ ተለዩዋቸው:: በሸይኾቹ ሕገ-ዳዕዋ መስመር ላይ ቀጥ በሉ:: ሰርጎ ገብ በዚህ ማኒፌስቶ ነው የሚበጠረው:: ከሲፈተ ዳዕዋ እና አዳብ ሲያፈነግጥ ትይዙታላችሁ:: ✍በዐብዱልቃዲር ኑረዲንተጻፈ 👉 https://t.me/tebligda

  • ኡስታዝ ረመዳን ምርጥ ሙዛከራ @tebligda

  • ለትዉስታ @tebligda

  • ይህ የዒድ ተክቢራ አይደለም። ጎህ ሲቀድ ለሱብሒ ሰላት የተሰበሰበው የዲመሽቅ ነዋሪ ከግፍ አገዛዝ በመላቀቁ ያሰማው የደስታ ድምፅ ነው። ፅልም ሆነ ክብር በብዕር ሳይሆን በጥይት እንደሚገኝ ሶሪያ አስመሰከረች። መሳርያን ሸክፎ መፋለም ስለኢስላም ገድሎ መሞት ሸረፍ መሆኑን አሳየች። የሸሂዶቿ ደም ከንቱ አለመፍሰሱንም እንዲሁ። ምን ያህል ጊዜው ቢረዝም የኢስላም ጮራ ዳግም መፈንጠቁ አይቀርም። አዎ ይህ የጭላንጭል ብርሀን በሶርያ አቆጥቁጧል። የምዕራቡ ዓለም የጂሃድ ትግሉን ሰርቀው ሊያጠፉን ቢያሴሩም አላህ በሴራቸው ጠልፎ ይጥላቸዋል ኢንሻ አላህ። ዘመኑ የኢስላም ነው የፍትህ አርማ የሚውለበለብበት በደልና ቅጥ ያጣው ስርዓት አልበኝነት የሚታረምበት ርሀብ ችግር መከራ የደቆሰው ህዝብ በኢስላማዊ ሸሪዓ ፍትህ የሚያገኝበት ዘመን እየመጣ ነው ኢንሻ አላህ ➖➖➖➖➖➖ ➖➖➖➖➖➖ ቴሌግራም 👇👇👇👇 @Tebligda

  • አልሀምዱሊላህ የሰሃቦች ዋና ከተማ እና የትላልቅ አኢማዎች መፍለቂያ የሆነችዉን ሻም(ደማስ 'ቆ) ከዛሊሙ መሪ አላህ ነፃ አወጣት ። ታላቁ ሰሃቢይ ሙዓዊየዕ ለ 40 አመት አስተደድረዋት ለ20 አመት ደግሞ ኸሊፋ ሁኖ ሲየገልግላት ነበር። ደማስቆ የነ የኢማም (ሻፊዕይ፣ ነዋዊይ ፣ ዘሃቢ ፣ ፣ እብኑ ከሲር ፣ ሱብኪ ፣ ጀዘሪ ፣ እብኑ ሰላህ ፣ ቁርጢቢ ፣ እብኑ ረጀብ ፣ እብኑ አሳኪር ፣ኢብኑ ቁዳማዕ እና ሌሎች በኢስልምና ከባድ ሚዛን የሚሰጣቸዉ ለቃዉንቶች ሀገር ነት። አላህ ለሙስሊሙ ኡማ ድሉን ያከታትልልን የተቀሩ ግዛቶቻችንንም ቃል በገባዉ መሰረት በቅርቡ ኑስራዉን የምጣልን። አልሀምዱሊላለህ ።

  • ዱዓ! ዱዓ በአላህና በባሪያው መካከል ያለ ሚስጥር ነው። ዱዓ ኢባዳ ነው። ዱዓ የአንቢያዎች ሁሉ ሱና ነው። ዱዓ የባርነት መገለጫ ነው። ዱዓ የኸይር በር መክፈቻ ቁልፍ ነው። ዱዓ የኢማንና የየቂን ማረጋገጫ ነው። ዱዓ ከጭንቀትና ከጥበት መውጫ ነው። ዱዓ የሲህር የባላእ የሁሉ ችግር መመከቻ ጋሻ ነው። ዱዓ የሙእሚኖች ሁነኛ መሣሪያ ነው። ዱዓን ችላ ማለት እራስን ለጠላት አሳልፎ መሰጠት ነው። ዱዓ ማድረግ ውጤት እንዳለው ሁሉ ዱዓን መተው ሙሲባ ነው። የዱዓችንን ውጤት በፍጥነት ወይም እኛ በምንፈልግበት ወቅት ውጤቱን ባናገኝ እንኳ ዱዓችንን አላህ አልተቀበለንም ማለት አይደለምና ዱዓ ከማድረግ መሠላቸት አይገባንም። ዱዓ ከማድረግ መዘናጋት ተከታታይና ተደራራቢ ሙሲባዎችን ያስከትላል። ዱዓ ሳናደርግ ከሚመጣ ስኬት ዱዓ አድርገን የሚመጣው ስኬት ዋስትና አለው። ዱዓ የነፍሲያ መድሓኒት ነው። አላህ የጠላውን ሰው ዱዓን ይወስድበታል። አላህ ዱዓን የሚያገራው ለሚወደው ብቻ ነው። አላህ ዘንድ የተጠላ ሆነን ስኬታማ ከምንሆን አላህ ዘንድ የተወደድን ሆነን ነገራቶች ባይኖሩን ይሻላል። ከሰላት በፊትና ቡሗላ፤ በሌሊትም በቀንም እንዲሁም በየትኛውም ሁኔታ ላይ ሆነን ዱዓ ማድረግን አላህ ያግራልን!! @tebligda

  • ~ዛሬ በኢማን ጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘትህ ፣ነገ በዚሁ ላይ መጽናትህን አያመለክትም፣ አላህ እንጂ ራስህ ለራስህ ዋስትና መሆን አትችልም። ስለዚህ የደከሙትን አትናቅ። ባልገራላቸው አትሳቅ። የሰው ልጅ ቀልብ ሁሉ በአላህ እጅ ናት። እሱም እንደሻው ይገለባብጣታል። በኃጢአተኛ ላይ አትጀነን። እኔ ከሱ የበለጥኩ ነኝ አትበል። በንቀት ዐይንም አትመልከተው። አላህ ለዚህ ለተከበረው የኢስላም መንገድ ሲመርጥህ አንተ የተለየህ ፍጡር ስለሆንክ አይደለም። ወይም ባንተ ምርጫ አይደለም እስልምናን ያገኘኸው። በእዝነቱ ስለጎበኘህ ነው። ግን ይህን እዝነቱን ባነሳዉ ጊዜ ሊወስድብህ ይችላል። ስለዚህ በመልካም ሥራህም ሆነ በዒባዳህ አትመፃደቅ። ጠመሙ የምትላቸዉን አትጠየፍ። ሁሌም አላህ እስልምናን ስለሰጠህ አልሐምዱ ሊላህ በል። የሱ እርዳታ ባይደርስልህ አንተም እንደነርሱ ትሆን ነበር። ኢስቲቃማን ስኬቴ ነው፣ በራሴ ጥረት ነው ለፍቼ የገኘሁት ብለህ አታስብ። @tebligda

  • የነቢያችን_ሰለሏሁ_ዐለይሂ_ወሰለም_የአመጋገብ ሱና ✏️➊➭ ነቢያችንﷺ ከምግብ በፊት ይታጠቡ ነበር። ✏️➋➭ ነቢያችንﷺ ተደግፈው በልተው አያውቁም። ለምግብ ሲቀመጡ ወይ ተሸሁድ ላይ አይነት፣ ወይም እንዲሁ ተቀምጠው አንድ እግራቸውን ጉልበት ደረታቸው ላይ በማቀፍ ወይ ደግሞ ቁጢጥ በማለት ነበር። ✏️➌➭ ነቢዩﷺ ምግብ ሲጀምሩ ቢስሚላህ ወአላ በረከቲላህ በማለት ነው። ✏️➍ ➭ነቢያችንﷺ ምግቡን ካልወደዱት ስለምግቡ ምንም ሳይናገሩ መመገብ ይተው ነበር። ✏️➭ የማያውቁት ምግብ ከገጠማቸው አስቀድመው ስለምግቡ ይጠይቁ ነበር። ✏️➏ ➭ነቢያችንﷺ ምግባቸውን አሽትተው አያውቁም። ጥሩ ያለሆነ ልምድ እንደሆነም ይቆጥሩታል። ✏️➐ ➭በጣም የሞቀ ምግብ አይመገቡም ያቀዘቅዙት ነበር። «አላሁ ተዐላ እሳት አይመግበንም» ይሉ ነበር። በጣም የሞቀ ምግብ ውስጥ በረካ የለውም ብለዋል። ✏️➑➭ ነበዩﷺ ምግብም ሆነ መጠጥ ላይ ተንፍሰው አያውቁም። መጠጥን በትንፋሽ ማቀዝቀዝ አይወዱም ነበር። ✏️➒ ➭ነቢዩﷺ ሀብታሞች ቤት እንደሚሆነው በብዙ ሳህን የሚቀርብ ምግብ አይወዱም ነበር። ✏️➓ ➭በአብዛኛው ነቢዩﷺ ሲመገቡ በሶስት ጣታቸው (አውራ፣ ጠቋሚና መሐል ጣታቸውን) በመጠቀም ሲሆን ምግቡ ቀጠን ያለ ከሆነ ቀለበት ጣታቸውን ይጨምሩ ነበር። ✏️➊➊➭ አንድ አይነት ምግብ ከቀረበላቸው ከፊታቸው ይመገባሉ የተለያየ አይነት ከሆነ ግን ከሌላ ቦታ ከመመገብ አይቆጠቡም ነበር። ✏️➊➋ ➭ነቢዩﷺ ከሰው ጋር እየበሉ ከሆነ የሚነሱት በመጨረሻ ነበር። ቀስ ብለው የሚመገቡ ሰዎችን ላለማሳፈር። ✏️➊➌➭ ሲጨርሱ ጣታጫውን በአፋቸው ያፀዱ ነበር። ✏️➊➍➭ ነቢዩﷺ ተመግበው ሲጨርሱ እንዲህ ይሉ ነበር👇👇👇 «الحمد الله الذي أطعم وسقى وسوغه و جعل له مخرجا» ✏️➊➎➭ ነቢዩﷺ ምግብ ለተሰባሰቡ ሰዎች የሚያከፋፍሉ ከሆነ በቀኝ ይጀምሩ ነበር። በግራ መጀመር ከፈለጉ በቀኝ ያለውን ያስፈቅዱ ነበር። ✏️➊➏ ➭ነቢያችን ﷺ ስጋ ወደ ቤት ሲያመጡ ጎረቤት እንዲበቃ ተደርጎ እንዲሰራ ያደርጉ ነበር። ✏️➊➐➭ ነቢዩ ﷺ ሀለዋ፣ ማር፣ ኮምጣቴ፣ ተምር፣ ሀብሀብ፣ ኪያር እና ዝኩኒ ይወዱ ነበር። 📲 ለሌሎችም ሼር በማድረግ የነብያችንን ሱና እናሳውቃለን👌 ┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹✿🌹»‌‌✽‌┉┉┄ ┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹✿🌹»‌‌✽‌┉┉┄ #صلوا_على_النبيツ #ኸሚስ #ጁመዓ T.me/tebligda

ዳዕዋ እና ተብሊغ - Da'wah and Tabligh — tgindex