tgindex
Best kerim
@Bestkerimарабский

اهدنا الصراط المستقيم ، فلقد تعبنا من الطرق الملتوية #شمس التبريزي +251938704306

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
15
Всего постов
26
Тип
открытый
Язык
арабский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 401
+9 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
456
26 постов
Вовлечённость
19,0%
к подписчикам
Постов в день
2,1
всего 26
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
370
1/48двое суток
424
1/72трое суток
457

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • #ረቢዕ_ሙባረክ በኢስላማዊ ታሪክ ውስጥ እጅግ ዝነኛና ተወዳጅ ከሆኑ የሰለዋት (ውዳሴ) ግጥሞች መካከል የኢማም ሸረፈዲን አልቡሰይሪ (ቁዲሰ ሲረሁ) «ቀሲደቱል ቡርዳህ» በቀዳሚነት ይጠቀሳል። የግጥሙ መነሻ ታሪክ ግን እጅግ አስገራሚና ልብ የሚነካ ነው። ኢማም አልቡሰይሪ በጠና ታመው በከፊል ሽባ ሆነው በነበረበት ወቅት፣ አላህ ፈውስ እንዲሰጣቸው በመሻት ነቢዩ ሙሐመድን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሚያወድስ ድንቅ ግጥም ማዘጋጀት ጀመሩ። ግጥሙን እየጻፉ ሳሉ ግን አንድ ስንኝ ላይ ደርሰው መቀጠል አቃታቸው፤ ስለእርሳቸው ሲያስቡ "ሰው ናቸው ግና እንደ ሰው አይደሉም።" የሚል ስሜት ጋር ደርሰው መቀጠል አቅቷቸው ቆሙ ስንኙ እንዲህ ይል ነበር፦ «فَمَبْلَغُ الْعِلْمِ فِيهِ أَنَّهُ بَشَرٌ...» (ፈመብለጉል ዒልሚ ፊሂ አነሁ በሸሩን...) ሲተረጎም "ስለ እርሳቸው ያለን እውቀት መጨረሻ እርሳቸው ሰው መሆናቸው ነው..." የሚል ነበር። በዚያው ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንቅልፍ ወሰዳቸውና በሕልማቸው ነቢዩ ሙሐመድን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አዩ፤ በሕልማቸውም ያዘጋጁትን ግጥም ለእርሳቸው እያነበቡላቸው ልክ እዚህ ስንኝ ላይ ሲደርሱ መቀጠል አቅቷቸው ቆሙ። በዚህ ጊዜ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቀሪውን ሁለተኛ ስንኝ ራሳቸው እንዲህ በማለት አሟሉላቸው፦ «...وَأَنَّهُ خَيْرُ خَلْقِ اللَّهِ كُلِّهِمِ» (...ወአነሁ ኸይሩ ኸልቂላሂ ኩሊሂሚ) "...እንዲሁም እርሳቸው ከአላህ ፍጥረታት ሁሉ በላጭ መሆናቸውን ነው።" በሕልማቸውም ውስጥ ነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የታመመውን የአልቡሰይሪን አካል አሻሹት፤ እንዲሁም የለበሱትን ካባ (ቡርዳህ) ጣሉላቸው። ኢማም አል ቡሰይሪ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ሙሉ በሙሉ ከህመማቸው ድነው፣ እግራቸውን በሙሉ ጤንነት ቆመው አገኙት! ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ድንቅ ግጥም «አል-ቡርዳህ» (የካባው ግጥም) ወይም «አል-ከዋኪቡ ድ-ዱሪያህ ፊ መድሒ ኸይሪል በሪያህ» በሚል ስያሜ በመላው ዓለም በሰፊው የሚታወቅ ሆነ። በሐገራችንም በአራቱም ዐቅጣጫ የሚገኙት ቀደምት ዑለማዎች በእንዲህ ዓይነት ተዓምራት ታግዘው የቀዲሞቻቸውን ፈለግ ተከትለው በርካታ የመውሊድ ተርቲቦችን አበጅተዋል። የሰለዋትና የዱዓ ኪታቦችን አልፈው ከስር መሠረት የማይጠፋ የማይደበዘዝ መንገድን አኑረው አልፈዋል። #መውሊድ በአራቱም ዐቅጣጫ ያለውን ማሕበረሰብ የሰበሰበ ድንቅ እሴታችን ነው፣ መውሊድ ሰዎች ከተለያየ ፖለቲካዊና ጥቅማዊ ግጭት ከፍ የሚሉበት ፍጹም መንፈሳዊ ማዓድ ነው፣ መውሊድ የዒልምና የጁህድ ሐለቃ ነው። በሐገሪቱ እየነፈሰ ያለውን ከባድ ችግር የሚቀረፍበት ዑለማ የሚከበርበት፣ ዑለማ የሚሰበሰብበት ረቢዕ ያድርግልን። እንኳን አደረሳችሁ ♥ #መውሊድ_ለሐገር_ሠላም اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين

  • видео или голосовое, без подписи

  • #ሰውነት ሰው ምግብ ከመመገብና ከመራባት አኳያ እንደ ዕፅዋት ነው። ስሜት ከመሰማትና ከመንቀሳቀስ አንጻር ደግሞ እንደ እንስሳ ነው። ውጫዊ ቅርጹን ብቻ ከተመለከትን ደግሞ በግድግዳ ላይ እንደተሳለ ስዕል ነው። የሰው ልጅ ትልቁ ልዕልናውና ብልጫውን ያገኘው በመናገርና በማሰብ ችሎታው፣ በኃይሉና ባለው ትርጉሙ ውስጥ ነው። ለዚህም ነው «ሰው የማሰብና የመናገር ችሎታ ባይኖረው ኖሮ የተተወ እንስሳ ወይም ምስል ብቻ ይሆን ነበር» የተባለው። ስለዚህ ሰው በመናገር፣ በዕውቀትና በማስተዋል ኃይሉ ከመላእክት ጋር ይመሳሰላል፤ በምግብና በሩካቤ ሥጋ ፍላጎቱ ደግሞ ከእንስሳት ጋር ይመሳሰላል። የሰው ልጅ ሙሉ ትኩረቱንና ጥረቱን አእምሮውን በዕውቀትና በበጎ ሥራ ለማነጽ ያዋለ ጊዜ ከመላእክትነት ደረጃ ጋር ለመድረስ የተገባው ነው፤ መልአክና መንፈሳዊም ይባላል። አላህ እንዲህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) እንዲህ አለ፦ «ይህ ያማረ መልአክ እንጂ ሌላ አይደለም» (ዩሱፍ፤ 31) ነገር ግን ሙሉ ትኩረቱን የስሜት ህዋሳትንና አካላዊ ምኞቶችን በመከተል ላይ ብቻ ያዋለ ጊዜ ልክ እንደ እንስሳት የሚበላ ሰው ከእንስሳት ደረጃ ጋር ይገናኛል፤ ወይ እንደ በሬ ተላላ፣ ወይም እንደ አሳማ ሆዳም፣ ወይም እንደ ውሻ አጎብጓቢ፣ ወይም እንደ ግመል ቂመኛ፣ ወይም እንደ ነብር ትዕቢተኛ፣ ወይም እንደ ቀበሮ አታላይ፣ ወይም እንደ ዶሮ ስሜታዊ፣ ወይም እነዚህን ሁሉ አጣምሮ የያዘ እንደ አመጸኛ ሰይጣን ይሆናል። አላህም እንዲህ ብሏል፦ «ከእነርሱም ዝንጀሮዎችን፣ አሳማዎችንና ጣዖት ተገዢዎችን አደረገ .... » (አልማኢዳህ፤60) ቁመናቸው የሰው ሆኖ ነገር ግን እውነታቸው እንደ አንዳንድ እንስሳት የሆኑ ሰዎች በርካታ በመሆናቸው ምክንያት አላህ ስለ እነዚያ ከአላህ ድንጋጌዎች የማያስተውሉ ሰዎች ሲናገር፦ «እነርሱ እንደ እንስሳዎች እንጂ ሌላ አይደሉም፤ ከቶውንም እነሱ ይልቅ መንገድን የተሳሳቱ ናቸው።» (አል-ፉርቃን፤44) እንዲሁም፦ «ከሚንቀሳቀሱት እንስሳዎች ሁሉ አላህ ዘንድ ይበልጥ ክፉዎቹ እነዚያ ዘወትር የካዱት ናቸው።» (አልአንፋል፤55) በማለት አላህ የሰጣቸውን የማሰብ ኃይል ያልተጠቀሙ ሰዎች ከተንቀሳቃሾች ሁሉ የከፉ መሆናቸውን ገልጿል። በዚህ የተነሳ የሰው ልጅ በአስተሳሰቡና በሰዋዊ ድርጊቱ አንጻር ሊበላለጥ ይችላል። በዚህ አተያይ አንድን ሰው ከአሥር ሰዎች ጋር እኩል፣ ወይም አሥር ሰዎችን ከመቶ ሰዎች ጋር እኩል ልታይ ትችላለህ። እንዲያውም አንዱ ሰው እንደ መቶ ሆኖ፣ ሌሎች አስር ሰዎች ደግሞ ከአንዱም በታች ዋጋቢስ ሆነው ታገኛለህ። እንዲያውም አንዱ ሰው እንደ አሥር ሺህ ሆኖ ልናይ እንችላለን፤ አሥር ሺህ ሰዎችም ከአንድ ሰው በታች ሆነው ልናት እንችላለን። ነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ «ሰዎች ልክ እንደ መቶ ግመሎች ናቸው፤ ከእነሱ መካከል አንዲትም ለጉዞ የምትሆን ግመል ላታገኝ ትችላለህ።» በዐረቦች ዘንድ «ኢቢል» የመቶ ግመሎች ስም ነው፤ ስለዚህ «መቶ ኢቢል» ማለት አስር ሺህ ግመሎች ማለት ነው። እንዲያውም አንድ ሰው እንደ ዓለም፣ ዓለምም እንደ አንድ ሰው» ሊታይ ይችላል ቢባል ትክክል ነው። ነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፦«ከሕዝቦቼ (ኡመቴ) ጋር ተመዘንኩ፤ እኔም ከበድኩባቸው (በልጬ ተገኘሁ)» እንዳሉት ማለት ነው። በዚህም ላይ አቡ ኑዋስ እንዲህ ብሏል፦ «አላህ መላውን ዓለም በአንድ ሰው ውስጥ እንዲሰበስበው ማድረግ ለእርሱ አያስደንቅም።» *** እያለ ይቀጥላል ..... ከአንድ ኪታብ ላይ የወሰድኩትና አጥሮ የቀረበ ሐሳብ ነው። ሰው ያድርገና ♥

  • ከሚሰማውም ከሚወራውም ፈተና አላህ ይጠብቀን! ወደ አላህ ቀርበን በምንማጸንበት በዚህ ወቅት ሰዎች ከእምነታቸው ተስፋ ቆርጠው በባዶ ሜዳ እየተፈላሰፉ ወደራሳቸው ገደል እንዲገቡ የሚደረገው ሌላኛው የ #ጘፍላ ዓይነት ነው። የእስልምናን ግንዛቤና ፊቅህ ያልተረዳ፣ በእምነቱ ውስጥ የተነሱ በርካታ ሊቃውንቶች ያበረከቱትን መንፈሳዊ ብሎም ፍልስፍናዊ መረዳት የሌለው ሰው፣ አይደለም ሃይማኖትን የሚሞግት መጠይቅ ሊያቀርብ ይቅርና ራሱን አስተማሪ አድርጎ ባያቀርብ ይመረጣል። ብዙ የእምነቱን ሕግጋት የምንረዳቸው ራሳችንን የበለጠ ለአላህ ባርነት ስናስገዛ፣ መንፈሳዊነትን ስንለማመድና ስንረዳ ነው:: ከተለያዩ አምልኮዎች፣ ከሰለዋት፣ ከአዝካርና ከቁርኣን ሸሽተን የትኛውም መለኮታዊ ምስጢር በቀላሉ ሊገለጥልን አይችልም። ከተፈጥሮ በደንብ ለማውራት የሚጥርና ተፈጥሮን ለመረዳት የሚጥር፣ ከውስጡ (ነፍሲያው) ፍላጎት ከፍ ብሎ ለመብረር ለሚጥር ኹሉ እውነት መገለጧ አይቀርም። ስለሆነም፣ ከአእምሮ በላይ የሆኑ አጀንዳዎችንና የማይገባንን ነገር አላህ እንዲያስረዳን ወደ እርሱ በመቃረብ መጣርና መልፋት ተገቢ ነው። ሰባሓል ኸይር!

  • ያሉብን ግዴታዎች ብዛታቸው፤ ያለን ጊዜ ማነሱ ... በረካ ካልለገሰን ሩጫው አይበቃም! አላህ ይባርክልን ♥ ሰላም ለይል

  • видео или голосовое, без подписи

  • #የልብ_እረፍት በፈጣሪ ደጃፍ ላይ በመቆም ይገኛል! اِلْزَمْ بَابَ رَبِّكْ የአላህ በራፍ ላይ በባርነት ኾኖ መጠባበቅ ታላቅ የልብ ብርታት ነው። የሁሉ ነገር አድራጊ አላህ ነው ብሎ በማመን፣ ማስተናበሩን (ተድቢሩን) ለእርሱ መስጠት ከአላስፈላጊ ሐሳብና ጭንቀት ራስን ማቀብ የውስጥ ሰላም ይገኝበታል። "ኢልዘም ባበ ረቢክ" (اِلْزَمْ بَابَ رَبِّكْ) በመባል የሚታወቅ አንድ ታዋቂ የተሪሞች ስንኝ አልለ። የተደረሰው በ17ኛው ክፍለ ዘመን በታላቁ መንፈሳዊ መሪ ኢማም ዐብዱልላህ ቢን ዐለዊ አል-ሐዳድ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) ነው። ኢማሙ ይህንን ስንኝ የጻፉት በወቅቱ ሰዎች በኑሮ ውጣ ውረድና በየጊዜው በሚከሰቱ ኹነቶች ምክንያት ከሚገጥማቸው የልብ ጭንቀትና ፍርሃት ወጥተው፣ ነገሮችን ሁሉ ለፈጣሪ የመተው እና በአላህ ውሳኔ (ቀዷ ወቀደር) ሙሉ በሙሉ የመርካት መንፈሳዊ እርጋታን እንዲያገኙ ለማስተማር ነው። اِلْزَمْ بَابَ رَبِّكْ ، وَاتْرُكْ كُلَّ دُونْ وَاسْأَلْهُ السَّلَامَةْ مِنْ دَارِ الفُتُونْ (የጌታህን ደጃፍ ያዝ፤ ከእርሱ ውጭ ያለውን ሁሉ ተው፤ ከፈተና ቤትም ሰላምን ለምነው።) لا يَضِيقُ صَدْرُكْ ، فَالحَادِثْ يَهُونْ اللهُ المُقَدِّرْ، وَالعَالَمْ شُئُونْ (ደረትህ አይጠብ፤ የሚከሰተው ነገር ሁሉ ያልፋልና። አላህ ወሳኝ ነው፤ ዓለምም የሁነቶች ስብስብ ናት።) لا يَكْثُرُ هَمُّكْ .. مَا قُدِّرْ يَكُونْ (ጭንቀትህ አይብዛ .. የተወሰነው ነገር መከሰቱ አይቀርምና።) فِكْرَكْ وَاخْتِيَارَكْ دَعْهُمَا وَرَاكْ وَالتَّدْبِيرَ أَيْضًا ، وَاشْهَدْ مَنْ بَرَاكْ (ሐሳብህንና ምርጫህን ከጀርባህ ጣላቸው፤ ማስተናበሩንም እንዲሁ፤ የፈጠረህንም አምላክ መስክር።) مَوْلَاكَ المُهَيْمِنْ ، إِنَّهُ يَرَاكْ فَوِّضْ لُهْ أُمُورَكَ ، وَاحْسِنْ بِالظُّنُونْ (እርሱ ተጠባባቂው ጌታህ ነው፤ ያይሃልም። ነገሮችህን ለእርሱ አስረክብ፤ መልካም ጥርጣሬም ይኑርህ።) لا يَكْثُرُ هَمُّكْ .. مَا قُدِّرْ يَكُونْ (ጭንቀትህ አይብዛ .. የተወሰነው ነገር መከሰቱ አይቀርምና።) لَوْ وَلِمْ وَكَيفَ قَوْلُ ذِي الحَمَقْ يَعْتَرِضْ عَلَى اللَّهِ الَّذِي خَلَقْ (‘ቢሆን ኖር’፣ ‘ለምን’ እና ‘እንዴት’ የሞኝ ንግግሮች ናቸው፤ እነዚህ ቃላት ነገሮችን በፈጠረው አላህ ላይ ተቃውሞ የሚቀርቡበት ንግግሮች ናቸው።) "ቢሆን ኖር"፣ "ለምን" እና "እንዴት" እያሉ በፈጣሪ ውሳኔ ላይ ማጉረምረም የልብ እረፍት ያሳጣል። በአላህ ውሳኔ ላይ እነዚህን መጠይቆች እየጠየቁ ውስጥን መረበሽ፣ የሰውን ልጅ ስጋትና ጭንቀት ከመጨመር ውጭ አንዳች ነገር የሚቀይሩ አይደሉም፤ ሁሉንም ነገር ለፈጣሪ መስጠት ግን የልብ ሰላምና የሕይወት እርጋታን ያጎናጻፋል። ይህ #ተስሊም ይባላል፤ በልብ ዕውቀት የመጠቁ ዑለማዎች ማሕበረሰብን በመሳሰሉ ዕውቀቶች የውስጥ ሰላሙን ይጠብቁለት ነበር። አላህ ያስረዳና 🤲🤲

  • #የንጋቱ ትንፋሽ የአዲስ ተስፋ ምልክት ነው! በቁርኣን ላይ አላህ "ወሱብሒ ኢዛ ተነፈስ" ንጋት በተነፈሰ ጊዜ! ብሎ ይምላል። የሌሊቱ ጨለማ ተገፎ ንጋት እፎይ ብሎ ሲተነፍስ፣ ተፈጥሮ በሙሉ አዲስ ህይወትና ብርሃን ትላበሳለች። ያንን ንጹህ የንጋት ነፋስ ጥቂት ደቂቃ እንኳን ውስጣችንን ሞልተን እንተንፍሰው፤ መንፈሳችንን ያድሰዋል። ይህ ድንቅ ሰአት በእንቅልፍ አያምልጥህ! ይህ ሰአት በሩ ክፍት ነው።ቀንህን በዚክርና በዱዓ በአዎንታዊ እይታ ጀምር! መልካም እና የበረከት ቀን ይሁንልን!

  • 9 авг.418152

    « ወደ [ውስጥ] የሚደረገውን ጉዞ በተሳካ ሁኔታ የጀመረ ሰው ምልክቱ በውስጡ ያለው በጣም ፈታኝ ነገር ግን ደግሞ በጣም አስደሳች ኾኖ ስለሚያገኘው፣ የሌሎችን ጥፋት ወይም ጉድለት ለመመርመር (ለመፈለግ) የሚያስችል በቂ ጊዜ አይኖረውም።» ሸይኽ ዐብዱልሐኪም ሙራድ ወደ ውስጡ የዘለቀ ሰው ያስተምራል፣ ካገኘው ብርሃንና ነፈሀት ኢማንያ ያጋራል እንጂ በግለሰቦች ጥፋት ብዙ አይወጠርም። የሰዎች ነውር ላይ ብዙ መቆየት የራስን (የውስጥን) [አሁን] ያሳጣል። ትልቁና ከባዱ ጉዞ ወደ ውስጥ የምንሄደው ነው የሚባለው ለዚህ ነው! ሰላም ለይል ♥ አላህ ያስረዳና ♥

  • видео или голосовое, без подписи

  • በእስልምና እይታ #የሴት ልጅ መንፈሳዊ ልዕልና እና የዘመኑ የግራ መጋባት አጀንዳዎች! በኢስላማዊ አስተምህሮ እና በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ሴት ልጅ በደካማነትና በዝቅተኝነት አትታይም። የሰው ልጅ መንፈሳዊ ጉዞ እና የወልይነት ማዕረግ በጾታ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በልብ ንጽህና፣ በተቅዋ እና በኢማን ጥረት ላይ የተመሰረተ ነው። ታላቁ ሊቅ ኢብኑ ዐረቢ (ቀ.ሲ) እና ሌሎችም የእስልምና መሻይኾች እንደሚያብራሩት ሴቶች በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ከወንዶች ያልተናነሰ እንዲያውም በይበልጥ ለአላህ እዝነት እና እውቀት ቅርብ የሚያደርግ ልዩ መንፈሳዊ ድርሻ አላቸው ይላሉ። ሆኖም ግን፣ በአንድ በኩል የእስልምናን ጥልቅ መንፈሳዊ መሠረት በትክክል ካለመረዳት የተነሳ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ባህላዊ በደሎች እና ጨቋኝ አመለካከቶች ይስተዋላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የምዕራቡ ዓለም ከኢማን እና ከፈጣሪ መንገድ ያፈነገጠውን፣ ሁሉንም ነገር በቁሳዊ መስፈርት ብቻ የሚለካውንና የሰው ልጅን ተፈጥሮአዊ ማዕረግ የሚያሳንሰውን ፍልስፍና እንደ መፍትሔ አድርጎ የማቅረብ አዝማሚያ ይታያል። እውነታው ግን የመፍትሔው ቁልፍ የሚገኘው በባህላዊ ጭቆናም ሆነ በምዕራቡ ቁሳዊና ፌሚኒስታዊ አጀንዳዎች ውስጥ ሳይሆን፣ የእስልምናን ትክክለኛ መንፈሳዊ መሠረት በተረዳው አስተምህሮ ውስጥ ነው። በተፈጥሮ (ፊጥራ) ከመረጋጋት አንጻር ስንመለከተው እስልምና የወንድ እና የሴት ተፈጥሮአዊ ልዩነትን ያከብራል፤ ሁለቱም የተሟላ ሰብዕና እና የየራሳቸው ድርሻ ያላቸው እንጂ አንዱ ከሌላው ይበልጣል ወይም ያነሳል አይልም። ከባህላዊ በደል ከመላቀቅ ዕይታ ሴቶችን እንደ ቁሳቁስ ወይም ሁለተኛ ደረጃ (እንደ ትርፍ) የማየት ባህላዊ ድንቁርና ከእስልምና መንፈሳዊ ልዕልና ጋር በፍጹም አይገናኝም። ከምዕራቡ ቁሳዊ እና ፌሚኒስታዊ አጀንዳ መጠበቅ ደግሞ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። መንፈሳዊነትን ያገለለው፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮን የሚክደው እና የጾታ ወሰኖችን ለማፍረስ የሚሰራው የምዕራቡ አፈንግጦ የወጣ አስተሳሰብ የሰውን ልጅ መንፈሳዊ ሚዛን የሚያበላሽ እንጂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። በአንዳንድ ቤተሰቦች ወይም ማሕበረሰቦች ውስጥ የሚከሰቱ በደሎች ከመጥፎ ባህሎች የሚመነጩ እንጂ ከመለኮታዊ መመሪያ ጉድለት የመጡ አይደሉም። በእስልምና ታሪክ ውስጥ የመካ እና የመዲና ሴቶች በባህልም በአመለካከትም የተለያዩ እንደመሆናቸው፣ መለኮታዊው መመሪያ የሰዎችን የተለያየ አፈጣጠርና ማሕበራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ፍትሐዊ መዋቅር ዘርግቷል። መለኮታዊ መመሪያዎች ቅዱስ ባህርይ ያላቸው ቢሆንም፣ በአተገባበር ላይ የሚነሱ የመረዳት ልዩነቶች ልክ በሌሎች የእምነቱ ክፍሎች ላይ እንደሚከሰቱት ሁሉ የሚጠበቁ ናቸው። ይህ ደግሞ ኪታብ ላገላበጠ እና ድንጋጌዎችን ላጠና ሰው አዲስ ነገር አይደለም። ትክክለኛው መንገድ የሴት ልጅን አላህ የሰጣትን ክብር፣ መንፈሳዊ ማዕረግ እና ሰብዓዊ ልዕልና በራሳችን ጥልቅ አስተምህሮ ውስጥ ተረድቶ መተግበር እንጂ፣ በባህላዊ በደል እና በምዕራቡ ቁሳዊ አጀንዳዎች መካከል መላተም አይደለም። የምንከተለው መመሪያ (ርዕዮት) እስልምና ከሆነ፣ መለኮታዊ መመሪያዎችን እና አወቃቀሩን በትክክል መረዳት ይቀድማል እንጂ ከሌሎች ምድራዊ እሳቤዎች ጋር ለማስማማት መታገል መፍትሔ አይሆንም። ያስረዳን 🤲🤲

  • 6 авг.658243

    በዚህ ዘመን ያሉ ወጣቶችን እንደማውራት ደስ የሚለኝ ነገር የለም። ለምን? ከልብ ካወራሀቸው ከልብ ያደምጡሃል። የውሸት ከዘባረቅክባቸው ይከሽፉሃል? ወልይ ናቸው እንዴ?! ስለ እሴት ለአንድ ወጣት እየመከርሁ ነበር .... ለአንዳንድ ሰዎች እንዲጠቅም ወደ ጽሑፍ ቀየርኩት እንዲህ ይነበባል። እንደ ተራ የመንገድ ላይ ፌስታል፣ ነፋስ እንደሚያወዛውዘው ክብደት አልባ አትኹን። በእሴት፣ በሥነምግባር፣ በዕውቀትና በክህሎት ክብደት ይኑርህ። ይህን ጊዜ ማንም ወደፈለገው ሊወስድህና ሊስብህ አይችልም። በዘመናችን ምንም ዋጋ፣ እሴት(ክብደት) የሌላቸው ሰዎች በየቀኑ አንተን የሚጎትቱት አንተ ለራስህን እሴት ከሌለህ ብቻ ነው። ሁሉንም ነገር የመከታተል ግዴታ የለብህም፣ የምትተወው ነገር መብዛት አለበት፣ የሚመለከትህን አነስተኛ ነገሮች አውቀህ እነርሱ ላይ ትኩረት ማኖር አለብህ። የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦ «አንድ ሰው የማይመለከተውን ነገር መተዉ የእስልምናው ማማር ነው።» ቲርሚዚ ዋጋ እንዲጨምር፣ እሴትህን ለመገንባት ወደ ሚመለከትህ በይበልጥ ወደ ምትጠየቅበት ቤትህ፣ ልጆችህ፣ አከባቢህ፣ ሥራህ ላይ ትኩረት አድርግ። በቀጥታ አንተ የማትጠየቅበት ነገር ላይ ተጠምደህ ራስህን እንዳታጣ። ታዋቂነት አልያ ዝነኝነትን አጥብቀህ አትመኝ ፈልገኸው ባይመጣ ይመረጣል ከመጣም እንዴት እንደምታስተዳድረው ተጨነቅ። ይህ ዝና ከሚያመጣቸው ከባባድ አደጋዎች ውስጥ አንዱ ራስን አልመሆንና ራስን አለመምሰል ነው። አበቃሁ! አላህ ያስረዳና ♥

  • 6 авг.675127

    «አላፊው (ጠፊው) በሚጠፋ ነገር ልቡ የተንጠለጠለ ጊዜ ያጠፋዋል፤ አላፊው በዘላቂው (በማያልፈው) ልቡ ሲንጠለጠል ግን ያኖረዋል። ስለሆነም ቁርኝትህ ከአላህ ጋር መሆኑ መዳን ነው፤ ከአላህ በስተቀር የሚያድንህስ ማን ነው?» ሸምስ ተብሪዝ ( ቁዲሰ ሲረሁ) በተለያዩ ቁሳዊ ነገሮች ልብን ማንጠልጠል የልብ መጥፊያዋ ነው። በአላህ ላይ ልብን ማኖር ሕያው መሆኛዋ ነው። ልባችን ንጉሥ ነው። ጥበቃ ይፈልጋል። ካዕብ አል-አሕባር እንዲህ ማለቱ ተዘግቧል፦ ወደ ዓኢሻ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ዘንድ ገብቼ እንዲህ አልኳት፦ «የሰው ልጅ ዓይኖቹ መሪ (መሪ መንገድ የሚያሳዩ) ናቸው፣ ጆሮዎቹ ማፍሰሻ (መቀበያ) ናቸው፣ ምላሱ አስተርጓሚ ነው፣ እጆቹ ክንፎች ናቸው፣ እግሮቹ መልእክተኛ (አዳራሽ) ናቸው፣ ልቡ ደግሞ ንጉሥ ነው። ንጉሡ በጥሩ ሁኔታ ላይ ከሆነ (ከተስተካከለ) ሠራዊቱም ጥሩ ይሆናል።» እሷም እንዲህ አለች፦ «ከአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ።» ልባችንን በአይሆኑ ነገር ከማንጠልጠል ይጠብቀና! ያ አላህ ♥

  • 5 авг.659231

    የመጀመሪያውን ለሊት ማለትም ከ 4:00 በኃላ እስከ 7:00 ድረስ ግድ ካልኾነ በስተቀር እንዲሁ ያለምንም ጥቅም በተለይም በስክሪን ላይ ረጃጅም ሰአታት ማሳለፍ ጥቅም የሌለው በረከት የሚያሳጣ ልማድ ነው። ውጤታማ እንቅልፍ የሚገኝበት ሰአት ነው። ለሊትም ለመንቃት፣ የፈጅር ሰላትም በንቃት ለመስገድም ወሳኝ ነው። በተለምዶ ያለምንም ጥቅም የምናመሽበት ይህ ሰአት ለማረም መሥራት ተገቢ ነው። ይህን ለማሳካት ወደ ከመግሪብ ጀምሮ ወደ ቤት የመሰብሰብ ልማድ የግድ ይላል። በተለያየ ምክንያት ሰዎች ከዚህ ልምድ ቢሸሹም ከባድ ግን አይደለም። ለራስም ጊዜ ለመስጠት ይህን መተገበር ላይ እናተኩር። ሰላም ለይል ♥

  • ዘመናዊ መዝናኛ ወይስ የትኩረት ስርቆት (ጘፍላ) "ሰው ሁልጊዜ የሚያየውን ይመስላል" ይባላል። በዘመናችን ለየት ባለ መልኩ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ የሚደረጉ የድብድብና የሁከት መድረኮች (በተለይ ድራማዊ የሪንግ ድብድቦች/ሬስሊንግ እና መሰል ትርኢቶች) ከስፖርትነት ይልቅ ዓላማቸው ምን እንደሆነ ጠይቀን እናውቃለን?! እንዲህ አይነት ፕሮግራም አዘጋጆች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አእምሮ በደስታ፣ በቁጣ እና በከፍተኛ ውጥረት (Adrenaline) አስረው የሚያቆዩት በምክንያት ነው፡ ዋናው ትኩረትን መስረቅ (ጘፍላን) ማስፋፋት ነው። የሰው ልጅ አእምሮ በጊዜያዊና ከንቱ ውጥረቶች ሲጠመድ ከዋናው የዐለም ህይወቱ ዓላማ፣ ከፈጣሪው፣ ከስራው እና ከዕድገቱ እንዲዘናጋ ይደረጋል። ይህ ዐሪፎቹ በአብዛኛው ሰው ሐም (ሐሳብ) ውስጥ መውደቅን የሚያመጣ ጘፍላ ስለኾነ እንድንጠነቀቅ የመከሩን ነው። ሌላኛው ሙሽኪላ የሥነምግባርና አደብ መሸርሸርን ማስፋፋትና ማለማመድ ነው። የሰውን ልጅ ህመም፣ ውርደት እና ግጭት እንደ መዝናኛ ማየት ቀስ በቀስ በአእምሯችን ውስጥ የሰዎችን ህመም የመረዳት (Empathy) አቅማችንን ያደከመዋል ጋጠወጥነት ይስፋፋል ማሕበረሰባዊ ሐያእ ድራሹ እየጠፋም ይሄዳል። ሦስተኛውና ዋነኛው የንግድና የጥቅም ትስስር ነው። በጀርባው ያለው ትልቅ የገንዘብ እንቅስቃሴ የሰዎችን መንፈሳዊ እና አእምሮአዊ ሰላም በመሸጥ ላይ ትርፍ ያስባል። አእምሯችንን እና ጊዜያችንን በምን እንደምንይዘው በጥንቃቄ ልንመርጥ ይገባል። ትኩረታችን የሚሰረቅበት ሳይሆን፣ አእምሯችን እና ስነ-ምግባራችን የሚገነባበት ቦታ ላይ እንገኝ ለማለት ነው። በነገራችን ላይ የሰዎችን ትኩረት በመሳብ እነርሱ ወደ ጓፍላ የሚሳብበት መንገድ ሁሌ ከመጥፎ አንደበቶች መጠበቅ የለብንም በተለይም በዘመናችን እውነትና ውሸት መለየት በቸገረን ዛሬ ጊዜ በእስልምና ስም የተለወሱ በደዕዋ የታጀቡ ኾነውም ጘፍላን ሊሰብኩ ይችላል። ሰዎች እምነታቸውን ከመሰል ተኩላዎች መጠበቅ የሚችሉት ወደ ውስጣቸው የሚያስገቡትን በጥንቃቄ መምረጥ ሲችሉ ነው። አላህ ይጠብቀና 🤲🤲

  • видео или голосовое, без подписи

Best kerim — tgindex