tgindex
Mohammed Ahmed Official

Mohammed Ahmed Official

Статистика
@abuafnanmohВидеоанглийский

ለጥያቄ እና አስተያየት 👉 @afhasmen youtube.com/@gharuhira

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
02:37
Постов за неделю
1
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Видео
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 960
+16 за 5 дн.
Сутки
−5
−0,10%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 220
20 постов
Вовлечённость
24,6%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
537
1/48двое суток
615
1/72трое суток
663

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ሁሌም የምታሳዩት በቃላት ለመግለጽ የሚከብድ ደግነትና ፍቅር ነው። ይኸው በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ በእህታችን ዘሀራ አብዱ አካውንት ውስጥ 1,320,000 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ሺህ) ብር ገቢ ሆኗል። ይህ ህዝብ የኑሮ ውድነት እያጎሳቆለው እንኳን «ከእኔ ይልቅ ለወገኔ» ብሎ የእዝነት እጆቹን መዝርጋቱን ብዙ ጊዜ አስመስክሯል። ​እባካችሁ ... «እኔ የምሰጣት ትንሽ ናት» አትበሉ። የእያንዳንዳችን 100 እና 200 ብር ተደምራ ነው ይህን ተአምር የሰራችው። የውኃ ጠብታዎች ቋጥኝን የሚበሱት በኃይል ሳይሆን በማያቋርጥ ጽናትና ተደጋጋሚነት ነው። የማያቋርጥ ጥረትና እልህ ደግሞ ከትልቅ ጉልበት ይልቅ ትልቅ ውጤት ማምጣቱ አይቀሬ ነው። የቀረውንም በጋራ እንሙላው ! ZEHARA ABDU SEID CBE 1000783784266 Mobile +251988316057

  • እስኪ እነዚህን ለዓይን የሚያሳሱ ህጻናት ተመልከቷቸው፤ የራሳችሁን ልጆች አስቧቸው። ስቃያቸውን በእነሱ ጫማ ሆናችሁ ተረዱት። እናታቸው እንዲህ አልጋ ላይ ወድቃ የምትሞትበትን ቀን እንዲጠብቁ ብቻቸውን አንተዋቸው። የልጆቹን እንባ አብሰን እናታቸውን ለማትረፍ በጋራ እንረባረብ። ZEHARA ABDU SEID CBE 1000783784266 Mobile +251988316057

  • 7 авг.1 0808

    ይህን ቤተሰብ አስታወሳችሁት ? 👇👇👇 https://www.facebook.com/share/p/1898HGbowW/

  • 3 авг.1 57181

    ለሐያት ነስሩ የተደረገው ድጋፍ ውጤቱ ይህን ይመስላል። 👇👇👇 https://www.facebook.com/share/p/1BoXU8aY6V/

  • 2 авг.1 62014

    https://www.facebook.com/share/p/1K31f1nxWy/

  • 31 июл.1 666302

    ትላንት በዚሁ የፌስቡክ ገጼ ላይ ለተስፈኛው ተማሪ ለኢብራሂም ሙሐመድ ኢብራሂም የአሜሪካ የካርሌተን ኮሌጅ የትምህርት ጉዞ የሚሆን የአየር መንገድ ትኬት መቁረጫ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር ድጋፍ እንድናደርግ ጥሪ ማቅረቤ ይታወሳል። እንደተለመደው በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ የተጠየቀውን ግብ ሙሉ በሙሉ በማሳካት 240,000 (ሁለት መቶ አርባ ሺህ) ብር በወንድማችን አካውንት ውስጥ ገቢ አድርጋችኋል። ከዚህ በተጨማሪ Kha Lid የተባለው ውድ ወንድማችን ደግሞ «ኢብራሂም ወደ አሜሪካ ሲሄድ እኔ ጋር አምጣው፤ ይዞት የሚሄደውን ሙሉ ልብስ እኔ እችላለሁ» በማለት ደስታችን እጥፍ እንዲሆን አድርጓል። እኔም በበኩሌ ካላቸው ላይ የሚያካፍሉ ቅን ወንድሞች ሲያጋጥሙኝ አይቼ ማለፍ ስለማልችል፣ ወደ ቡቲኩ በአካል ሄጄ ሥራውን በነፃ ለማስተዋወቅ ቃል ገብቻለሁ። ለጊዜው ግን የወንድማችንን ሱቅ መጎብኘት ለምትፈልጉ፦ ልደታ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው «ፖስት የገበያ ማዕከል» 1ኛ ፎቅ ላይ ለባና አታየር ብላችሁ ታገኙታላችሁ። ለኢብራሂም ህልም እጃችሁን የዘረጋችሁ... በገንዘብ ... በልብስ ድጋፍ ... ጽሁፉን በማጋራት (Share) ... በሃሳብ እና በዱዓ ከጎኑ የቆማችሁ በሙሉ ... ቃላት ከሚገልጹት በላይ እናመሰግናለን። ኢብራሂምም የተሰጠውን ይህን ትልቅ አደራ እና የህዝብ ፍቅር እንደ ስንቅ ቆጥሮ በትምህርቱ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ለወገኑ እና ለአገሩ ኩራት እንደሚሆን አንጠራጠርም።

  • 30 июл.1 133163

    без подписи

  • 30 июл.1 196252

    ኢብራሂም ሙሐመድ ኢብራሂም ይባላል። ትውልድና እድገቱ በታሪካዊቷ የገርባ ከተማ ነው። በ2017 ዓ.ል የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና (ESSLCE) ላይ ከተፈተኑ በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ተማሪዎች መካከል በጣት ከሚቆጠሩት እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ብርቅዬ ተማሪዎች አንዱ ነው። ኢብራሂም ከተሰጠው 600 አጠቃላይ ነጥብ ውስጥ 576.39 በማስመዝገብ የነገዋ ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በተግባር አስመስክሯል። ይበልጥ የሚያስደንቀው ደግሞ እጅግ ፈታኝ በሚባሉት የሒሳብ (Maths) እና የፊዚክስ (Physics) ትምህርቶች ላይ ሽራፊ ነጥብ እንኳ ሳይጥል 100 ከ 100 በመድፈን ታሪክ ሰርቷል። በብሔራዊ ፈተና ደረጃ ይህንን ያህል ከፍተኛ ውጤት  ማስመዝገብ በጣም አልፎ አልፎ የሚታይ ጠንካራ ጥረትና ችሎታን ይጠይቃል። ይህ የላቀ ውጤቱ እና ለኮምፒውተር ሳይንስ (Computer Science) ያለው ጥልቅ ፍቅር የዓለም አቀፍ ትምህርት ተቋማትን ቀልብ ስቧል። በዚሁ ጥረቱ በሰሜን አሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚገኘውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር የሆነው ካርሌተን ኮሌጅ (Carleton College) በኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርቱ ከፍተኛ የስኮላርሺፕ እና የፋይናንስ እርዳታ ዕድል ሰጥቶታል። ኮሌጁም ይመጣ ዘንድ ይፋዊ የጥሪ ደብዳቤ ልኮለታል። ነገር ግን አንድ ትልቅ አጥር ከፊቱ ተደቅኗል። ​ኢብራሂም ከገርባ ተነስቶ ይህንን ትልቅ ህልሙን ለማሳካትና እስከ አሜሪካ ለመብረር የሚያስችለው የአየር መንገድ ትኬት መቁረጫ ገንዘብ እጁ ላይ የለውም። ይህንን የነገ አገር ተረካቢ ብሩህ አእምሮ በመደገፍ ረገድ በተለይም የገርባ ህዝብ እና በጎ አድራጊዎች ከጎኑ እንደማይለዩ ሙሉ እምነት አለኝ። የገርባ ህዝብ ቁጥሩ አነስተኛ ቢሆንም በጎነቱና ደግነቱ ግን ድንበር ተሻጋሪ እንደሆነ በተግባር ያስመሰከረ ህዝብ ነውና። ለኢብራሂም የአየር ትኬቱ የሚያስፈልገን 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር ብቻ ነው። ​ይህ ወጣት ወደ ላቀ ደረጃ ተሸጋግሮ ለወገኑ እና ለአገሩ ትልቅ ባለ ውለታ እንዲሆን የእያንዳንዳችን ትንሽ አስተዋጽኦ ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል። ​«እኔ ከጎኑ እቆማለሁ!» የምትሉ እና ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር (Inbox) ብታናግሩኝ፣ የኢብራሂምን ሙሉ አድራሻ፣ የትምህርት ማስረጃዎች እና የስኮላርሺፕ ሰነዶቹን በሙሉ ግልጽነት የማቀብላችሁ ይሆናል። በተለይ ገርባዎች ብቅ ብቅ በሉማ  !

  • 25 июл.1 447172

    без подписи

  • без подписи

  • 22 июл.1 60019

    ከመዲና ተነስተን መካ ብንገባም የሸይኽ ኸዲር ልብ ግን እዚያው መዲና ቀርቷል። የልባቸው መወደድና ፍቅር አሁንም መዲና ላይ ተንጠልጥሏል። መካ በተያዘላቸው ዘመናዊ ሆቴል ኮሪደር ውስጥ ከግራ ወደ ቀኝ እየተንጎማለሉ፦ «መዲና የሚመልሰኝ ሰው ካለ ንገሩኝ ፤ ካልሆነ ግን እጠፋለሁ!» እያሉ በየዋህነት እያስፈራሩን ይገኛሉ። ለመሆኑ ሰው ሀገር ላይ እርሳቸውን የሚከታተልና የሚጠብቅ ልዩ ዘበኛ እንቀጥር እንዴ?! ☺️ 🌳🌳🌳 አውላ ቱር ኤንድ ትራቭል (Awla Tour & Travel) በቀጣይ 5ኛ ዙር ከነሐሴ 13/2018 ዓ.ል እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ል ለሚኖረው የዑምራ መርሃ ግብር ምዝገባ መጀመሩን በደስታ ይገልጻል። ከእኛ ጋር ፍጹም ቤተሰባዊ እና መንፈሳዊ ቆይታ ለማሳለፍ ከወዲሁ ይመዝገቡ! ​📞 ለበለጠ መረጃ እና ምዝገባ +251 911 95 58 87 ​+251 943 98 99 99 ​+251 921 55 51 58 ​ በማህበራዊ ሚዲያ (Telegram & WhatsApp)፦ ​+251 921 55 51 58 ​+966 55 861 5423 ​Telegram User: @afhasmen ​📍 አድራሻችን፦ ቤተል፣ ፊውቸር ሞል (Future Mall)፣ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 305

  • 22 июл.1 11410

    በመዲና ቆይታችን ከገጠሙን አስቂኝ ትዝታዎች መካከል አንዱን ላጋራችሁ፦ ​በመዲና የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን ለመጎብኘት በተዘጋጀልን ዘመናዊ መጓጓዣ ተሳፍረን እየሄድን ሳለ፣ ሸይኽ ኸድር ነጃሽ የከተማዋን የኪነ ህንጻ ውበት፣ የቀለበት መንገዶቿን ጥራት እና የአስፓልቷን ድንቅ አሰራር እያዩ እጅግ ተደነቁ። በመገረም ስሜት እጃቸውን አፋቸው ላይ ጭነውም፦ «በሕይወቴ እንዲህ አይነት በኪነ ህንጻ ያሸበረቀ ውብ ከተማ አይቼ አላውቅም!» በማለት ተናገሩ። ​ይህንን የሰሙት በፎቶው በግራ በኩል የቆሙት የሸይኽ ኸዲር መምህርና ወዳጅ ሸይኽ ማሕሙድ ፈቂህ ምን ቢሉ ጥሩ ነው ? ​«መጀመሪያ የት አገር ሄደህ ታውቃለህና ነው ህንጻ የምታወዳድረው!» 😂 🌳🌳🌳 አውላ ቱር ኤንድ ትራቭል (Awla Tour & Travel) በቀጣይ 5ኛ ዙር ከነሐሴ 13/2018 ዓ.ል እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ል ለሚኖረው የዑምራ መርሃ ግብር ምዝገባ መጀመሩን በደስታ ይገልጻል። ከእኛ ጋር ፍጹም ቤተሰባዊ እና መንፈሳዊ ቆይታ ለማሳለፍ ከወዲሁ ይመዝገቡ! ​📞 ለበለጠ መረጃ እና ምዝገባ +251 911 95 58 87 ​+251 943 98 99 99 ​+251 921 55 51 58 ​ በማህበራዊ ሚዲያ (Telegram & WhatsApp)፦ ​+251 921 55 51 58 ​+966 55 861 5423 ​Telegram User: @afhasmen ​📍 አድራሻችን፦ ቤተል፣ ፊውቸር ሞል (Future Mall)፣ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 305

  • በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አንድ ፈገግ የሚያሰኝና የናፍቆትን ጥልቀት የሚያሳይ ክስተት ተፈጥሮ ነበር። ወደ ጅዳ የሚወስደው በረራ ከተባለለት ሰዓት ለአንድ ሰዓት ያህል በመዘግየቱ በጉጉት የነደዱት ወንድማችን ሸይኽ ኸዲር በበረራ ማረፊያው ላይ መረጋጋት አቅቷቸው ልባቸው ቀድሞ መዲና ገብቶ ነበር የዋለው። ​ከእኛ ጋር አብሮ የተጓዘውን ወንድም ሙሐመድ መኪንን ምን እንደሚሉት እስኪ አዳምጡልኝ! በትራፊክ መጨናነቅ ውስጥ በሚኒባስ ተሳፍረው ከባቲ ወደ ኮምቦልቻ የሚጓዙ ይመስል፦ «ሙሐመድ መኪን... ይኼ አውሮፕላን አይበርም እንዴ ? ንገርልኝማ፣ እኔ ቸኩያለሁ!» እያሉ ሲወተወቱት ነበር 😂 ​ይቺ አንዲት ሰዓት ለዓመታት ካሳለፏት የናፍቆት ዘመን በላይ ረዝማባቸዋለች። የመዲና ፍቅር እንዲህ ነው። አውሮፕላኑ በምድር ላይ ቆሞ ሰዓት ሲያባክን የሳቸው ልብ ግን በጉጉት ሰማይ ላይ እየበረረ መዲና ገብቶ ነበር። 🍀🍀🍀 አውላ ቱር ኤንድ ትራቭል (Awla Tour & Travel) በቀጣይ 5ኛ ዙር ከነሐሴ 13/2018 ዓ.ል እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ል ለሚኖረው የዑምራ መርሃ ግብር ምዝገባ ጀምሯል። ከእኛ ጋር ፍጹም ቤተሰባዊ ቆይታ ለማሳለፍ ከወዲሁ ይመዝገቡ ! ​📞 በቀጥታ መስመር፦ +251 911 95 58 87 ​+251 943 98 99 99 ​+251 921 55 51 58 ​ በማህበራዊ ሚዲያ (Telegram & WhatsApp)፦ ​+251 921 55 51 58 ​+966 55 861 5423 ​Telegram User: @afhasmen ​📍 አድራሻችን፦ ቤተል፣ ፊውቸር ሞል (Future Mall)፣ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 305

  • без подписи

  • 22 июл.1 2931

    без подписи

  • በቅርቡ በባቲ ከተማ፣ በዚያ የቁርኣን መቅሪያ መደብ ላይ ከወንድም ኸዲር ነጃሽ ጋር ለቀረጻ አብረን ተቀምጠን ሳለ ነበር ያ ያልተጠበቀ የምስራች ጆሮውን ያንኳኳው። በዚያች ቅጽበት ከልቡ የፈለቀውና አንደበቱን የሞላው ድምፅ ግን አንድ ብቻ ነበር፦ «አላሁ አክበር!» ይኸው ዛሬ ያ የናፍቆት እንባ በደስታ ተቀይሮ ወንድማችን ኸዲር ነጃሽ ምድርን ተሰናብቶ ከደመና በላይ እየተጓዘ ነው። በአካል በሰማያት ላይ እየቀዘፈ ቢሆንም በሐሳብ ግን ቀድሞ በመስፈንጠር የመዲናን አፈር በናፍቆት እየሳመ ይገኛል። የዓመታት የልብ ምኞት ሲሰምር፣ የናፍቆት እንባ በጥሩ ትውስታ ሲተካ ማየት እንዴት መታደል ነው !? 🍀🍀🍀 አውላ ቱር ኤንድ ትራቭል (Awla Tour & Travel) በቀጣይ 5ኛ ዙር ከነሐሴ 13/2018 ዓ.ል እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ል ለሚኖረው የዑምራ መርሃ ግብር ምዝገባ ጀምሯል። ከእኛ ጋር ፍጹም ቤተሰባዊ ቆይታ ለማሳለፍ ከወዲሁ ይመዝገቡ ! ​📞 በቀጥታ መስመር፦ +251 911 95 58 87 ​+251 943 98 99 99 ​+251 921 55 51 58 ​ በማህበራዊ ሚዲያ (Telegram & WhatsApp)፦ ​+251 921 55 51 58 ​+966 55 861 5423 ​Telegram User: @afhasmen ​📍 አድራሻችን፦ ቤተል፣ ፊውቸር ሞል (Future Mall)፣ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 305

  • 20 июл.1 35919

    ከጎኔ የሚታዩት እናት ወ/ሮ አስናቀች አሰፋ ካብትህ ይመር ይባላሉ። የ60 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ የሆኑት እኚህ እናት፣ ከባለቤታቸው ከአቶ አማከለው አየለ ጋር ለረጅም ዘመናት የዘለቀ የጋብቻ ህይወት መስርተው ሰባት ልጆችን ያፈሩ ጀግና እናት ናቸው። የትዳር አጋራቸው አቶ አማከለው ደግሞ በህይወት ዘመናቸው በድምሩ 16 ልጆችን ለማፍራት የታደሉ ቆራጥ አባት ነበሩ። የእምነት መሪ ብርሃን (ሂዳየህ) የቤተሰቡን በር በስሱ ማንኳኳት ሲጀምር ልባቸው ለሐቅ ተከፈተ። ከወ/ሮ አስናቀች ልጆች መካከል ስድስቱ ለእስልምና እጅ ሰጡ። ፈቅደውና ወደው በእስልምና አጸድ ውስጥ ተጠለሉ። የልባቸውን መሬት በኢማን ዘር አረጠቡ። አንዱ ልጃቸው ደግሞ አሁንም ወደዚያው ብርሃን ለመድረስ የአላህን የምሪት ቁልፍ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። በአቶ አማከለው በኩል ከሌላው የቤተሰብ ክፍል ከተወለዱት አምስት ሙስሊሞች ጋር በአጠቃላይ ከዚህ የተባረከ ቤተሰብ ውስጥ 11 ሙስሊሞች ቤተሰቦች አሉ። ይህ ሁሉ ለውጥ ሲፈጠር ወ/ሮ አስናቀች እና ባለቤታቸው አቶ አማከለው በክርስትና እምነት ውስጥ ነበሩ። ግና የወ/ሮ አስናቀች ልብ ለረጅም ዘመናት በእስልምና ፍቅር ሲነድ ከርሟል። የነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ስም እና የኢስላም እሴቶች በውስጣቸው ተቀርጸዋል። የህይወት መሰረታቸውን በእስልምና ላይ ማደላደል የጀመሩት ገና በውስጣቸው የነበረው የእምነት ፍንጣሪ ነበር። እናት አስናቀች ይህን የተሸከሙትን እምነት ለማን እንደሚናገሩ ግራ ተጋብተው በነበረበት ወቅት፣ አንድ ቀን በድፍረት ለባለቤታቸው ለአቶ አማከለው ገለጹላቸው። በወቅቱ የአቶ አማከለው ልብ የብርሃኑ ጭላንጭል ባይሰርጸውም ባለቤታቸው ወደ ጽድቅ መንገድ እንድታመራ ፈቀዱላት። ወ/ሮ አስናቀች አሰፋም ከመንፈሳዊ እርካታ ጋር እስልምናን በይፋ ተቀበሉ። ከሁለት ሳምንት በፊት፣ በጂጂጋ ዩኒቨርሲቲ በባዮሜትሪ እና ጄኔቲክስ የዶክትሬት (Ph.D.) ዲግሪ ያለው ልጃቸው ረዳት ፕሮፌሰር ሱለይማን አማከለው ስልክ ደወለልኝ። «ሙሐመድ! እናታችንን በህይወት እያሉ ዑምራ ማስደረግ አለብን። መቼም እንደ እናትህ ተመልክተህ በእንክብካቤ እንድታደርስልን በአደራ እንጠይቅሃለን» በማለት በስሜት ነገረኝ። አክሎም «አባታችን ይህንን ዕድል ሳይጎናፀፉ ወደ ዘላለማዊው ዓለም ተሻግረዋል። እናታችንን ግን በእድሜዋ እያለች ዑምራ እንድታከናውን ቱርክ ያለችው እህታችን ፎዚያ ስፖንሰር አድርጋታለች» አለኝ። ይህንን የልጅ አደራ በደስታ ተቀብዬ ዛሬ በዙልሑለይፋ መስጂድ ግቢ ውስጥ ከእናታችን አስናቀች ጋር ይህንን ታሪካዊ ፎቶ ለመነሳት በቃን። ከሁሉ በላይ ልብን የሚያጠግበውና የሚያስደንቀው እውነታ ግን ይህ ነው፡- የወ/ሮ አስናቀች ባለቤት አቶ አማከለው አየለ፣ በምድር ላይ 107 ዓመት ዕድሜ ቆይተው ይህችን ዱንያ ሲሰናበቱ፣ 103 ዓመት ሲሞላቸው እስልምናን ተቀብለው ነበር። ከእስልምና በኋላ በምድር ላይ የቆዩት ለ5 ዓመት ብቻ ነው። ወ/ሮ አስናቀችም እስልምናን ከተቀበሉ 5 ዓመት ከስምንት ወራት አስቆጠሩ። ይህ ታሪክ ለአላህ እዝነት ዕድሜ እንደማይገድበው፣ ልብ ወደፈጣሪዋ በተመለሰች ቁጥር አላህ የሂዳያውን በር እንደሚከፍት ታላቅ ምስክር ነው። አልሐምዱሊላህ! 😍😍 🌳🌳🌳 አውላ ቱር ኤንድ ትራቭል (Awla Tour & Travel) በቀጣይ 5ኛ ዙር ከነሐሴ 13/2018 ዓ.ል እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ል ለሚኖረው የዑምራ መርሃ ግብር ምዝገባ መጀመሩን በደስታ ይገልጻል። ከእኛ ጋር ፍጹም ቤተሰባዊ እና መንፈሳዊ ቆይታ ለማሳለፍ ከወዲሁ ይመዝገቡ! ​📞 ለበለጠ መረጃ እና ምዝገባ +251 911 95 58 87 ​+251 943 98 99 99 ​+251 921 55 51 58 ​ በማህበራዊ ሚዲያ (Telegram & WhatsApp)፦ ​+251 921 55 51 58 ​+966 55 861 5423 ​Telegram User: @afhasmen ​📍 አድራሻችን፦ ቤተል፣ ፊውቸር ሞል (Future Mall)፣ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 305

  • без подписи

  • без подписи

  • 8 июл.1 70912

    ገቢ ያደረገበት የ20,000 ብር ደረሰኝ ይኸው