- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 14
- Всего постов
- 28
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 5 349
- 1/48двое суток
- 6 129
- 1/72трое суток
- 6 611
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ በአንድነት በሶስትነት እግዚአብሔር መርጦ ያነገሰው ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ዘኢትዮጵያ ይድረስ ለእንግሊዝ ንግሥት ቢክቶሪያ እንዴት አሉ ፤ እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። እስከዛሬ ድረስ አባቶች ነገስታቱ ፈጣሪያችንን ቢበድሉ ለጋላ እና ለቱርክ አሳልፎ ሰጥቶባቸው ነበረ። ዛሬ ግን እኔ ከተወለድሁ ወዲህ ፈጣሪየ ከአመድ አንስቶ ሀይል ሰጥቶ በአባቶች መንግስት አቆመኝ። በእግዚአብሔር ሀይል ጋሎችን አስለቅሗቸው ። ቱርኮች ግን የአባቴን መሬት ልቀቁ ብላቸው እምቢ ብለውኝ በእግዚአብሔር ሀይል ይኸው ልታገል ነኝ። እነ አቶ ቡሳዲን እነ ሊቀመኳስ ዮሐንስ የክርስቲያን ንጉስ ታላቅ ሰው ክርስቲያን የሚወዱ አሉ እናስተዋውቅህአለን አሉኝ። እጅግ እወዳቸው ነበር የርሶን ወዳጅነት ያገኘሁ እየመሰለኝ ። ሞት አይቀርምና የጠሉኝ ሰዎች እኔን ይክፋው ብለው ገደሏቸው ። እኔም በእግዚአብሔር ሀይል ደመኞችን አንድም ሳልተው ፈጀሗቸው። የገዛ ዘመዶቼን የርሶዎን ዝምድና ስፈልግ በእግዚአብሔር ሀይል ፈጀሗቸው ። ቱርኮች ከባህር ላይ ሆነው መልእክተኛየን አናሳልፍም ብለው ቸግሮኝ ሳለ ቁንስል ኬሜሮን መጣልኝ ወረቀትና የፍቅር በረከት ይዞ ። በእግዚአብሔር ሀይል እጅግ ደስ አለኝ ። ደህንነትዎንና ፍቅርዎን ብሰማ ።የሰደዱልኝንም የፍቅር በረከት ተቀበልሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ። አሁንም መልእክተኛየን ከቁንስል ኬሜሮን ጋር የፍቅር በረከት ይዞ እንዳልሰደው ቱርኮች በባህር ላይ የማያስተላልፉኝ ሆነ ። አሁንም እንዲህ ያለ ስፍራ እከሌ ይቀበለው ብለው ይላኩብኝ ምላሹን ኮንስል ኬሜሮን ይዞልኝ ይምጣ ። እናንተም ተገፉልኝ ክርስቲያኑን እስላም አጠቃህ ሲለኝ" ተፃፈ በ ሺህ ስምንት መቶ 54 በዘመነ ሉቃስ በወርሀ ጥቅምት በጎጃም በይባባ ከተማ 👉 t.me/Seidsocial
አፄ ቴዎድሮስን ለውድቀት ከዳረጉት ነገሮች ዋነኛው የዋህ አማኝነት ነው ብሎ መናገር ይቻላል። አፄ ቴዎድሮስ ለሀይማኖቱ በጣም ቀናኢ ከመሆኑ የተነሳ ሌሎች ሀይማኖቶችን በተለይም ኢስላምን አጥፍቶ አንዲት ክርስቲያናዊት ሀገር ብቻ መመስረት ያልም ነበር። የርሱ የዋህነት ታዲያ በርሱ ብቻ ሳያበቃ ይህን ግቡን ያሳካ ዘንዳ ክርስቲያን ሀይሎች ሁሉ ለርሱ የማገዝ ግዴታ እንዳለባቸው ያምን ነበር። በተለይም የጊዜው ሀያል ሀገር እንግሊዝ እስላሞችን ለመታገል እርሱን የመርዳት ግዴታ እንዳለባት አስቧል። የአለምን እውነተኛ ፖለቲካ ከአካባቢያዊነት ባልወጣው የፖለቲካ እይታው ሊረዳው አልቻለም ነበር። እናም እንግሊዝን መሳሪያ ካልሰራሽልኝ ፤ የጦር መሳሪያ እዚሁ የሚያመርቱ ጠበብቶችሽን ካላክሽልኝ እዚህ ሀገሬ የሚገኙ እንግሊዛዊያን ሚሲዮናዊያንና ዲፕሎማቶችን አግታለሁ ብሎ አገተ ። ልቀቅ ቢባል አልለቅም ብሎ ግግም😁 ታዲያ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበትና ቱርኮችን ለመዋጋት የእንግሊዝን እርዳታ እየጠየቀ ባለበት ወቅት አንድ ያልጠበቀው ነገር ተከሰተ። እንግሊዝ ኦቶማን ቱርክ እና ፈረንሳይ በጋራ አንድ ግንባር ፈጥረው የሩሲያን ጦር ሴቫስቶፐፖል ከተማ ላይ ከበው ደመሰሱት። አፄ ቴዎድሮስ ደነገጠ ተገረመ። ያየውን የሰማውን ሁሉ ማመን አቃተው። " እንደት ክርስቲያን መንግስት ከእስላም መንግስት ጋር አብሮ ሌላ ክርስቲያን መንግስትን ይወጋል" አለና ተደነቀ አዘነም። ሩሲያ አሳዘነቺው። የተመታችበትን ከተማ ለማሰብም በእንግሊዝ ሚሲዮናዊያን ብረት አስቀጥቅጦ የገነባውንና አንዴም ያልተኮሰውን የመጀመሪያውን መድፍ " ሴቫስቶፖል" ሲል ሰየመው። አፄ ቴዎድሮስ እንኳንስ ኢትዮጵያን ኢየሩሳሌምንም ከእስላሞች ነፃ አወጣለሁ ብል ነበርና የወሎ ሙስሊሞች ላይ ለ 6 ጊዜ ባደረገው ወረራ ሀይሉ ክፉኛ ተዳከመ። በጎጃም በጎንደር አመፅ ስለበረታበት በሸዋ መቆየት ስለተሳነው ከ 10,000 የማይበልጥ ጦሩን ይዞ የእንግሊዝ ሚሲዮኖችን አግቶ መቅደላ ላይ ተወሰነ። ያው በመጨረሻም ግትር አቋሙና የሀይማኖት ጀብደኝነቱ ዋጋ አስከፍሎት እንግሊዝ በቀላሉ አሸንፋው የቴዎድሮስ መጨረሻ ሆነ። እንግሊዝን በማገዝና መንገድ በመምራት አፄ ዮሐንስ ቁልፍ ሚና ነበረው። አፄ ቴዎድሮስ ትክክለኛ ስሙ ካሳ ሀይሉ የነበረ ሲሆን ቴዎድሮስ የሚባል ንጉስ ይመጣል የሚለውን ትንቢት ለመሙላት ሲል ነበር ስሙን ወደ ቴዎድሮስ የቀየረው። የሚያያሳዝነው ከ ሁለት ክፍለዘመናት በሗላም አሁንም በትንቢት የሚያምኑ ፖለቲከኞችን መያዛችን ነው። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
ኔታኒያሁ እንግሊዝ በቅርቡ ኢስላማዊት ሪፐብሊክ መሆኗን መግለፁ በአለምአቀፍ ሚዲያዎች ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። የወራሪዋ እና ህገወጥ ሰፋሪዋ ሀገር መሪ እንግሊዝን ኢስላማዊት ሪፐብሊክ ብሪታኒያ ሲል ጠርቷታል። ናታኒያሁ አክሎም እንግሊዝ የኑክሌያር መሳሪያ የታጠቀች ሙስሊም ሀገር ናት ብሏታል። ኔታኒያሁ ይህን ያለው የእንግሊዝ ፖለቲካ በከፍተኛ ሁኔታ መቀየሩን ተከትሎ ነው። በእንግሊዝ ውስጥ በርካታ ሙስሊም ባለስልጣናት ወደ ፊት እየመጡና የሙስሊሞች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ከመሆኑም ሌላ እንግሊዝ የቀድሞ ድጋፏን ለእስራኤል መቀነሷን ተከትሎ ኔታኒያሁ በኢስላማዊነት ፈርጇታል። አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርን በእስራኤል አመራሮች ፣ ተቋማትና ሰፋሪዎች ላይ ማእቀብ እንደሚጥሉ መናገራቸውን ተከትሎ እስራኤል ቁጣዋን ገልፃለች። የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊስተን ቸርች ልጆች ከእስራኤል ጎን ተሰልፈው ለመዋጋት የተጓዙበትን ታሪክ አስተዋሶ እንግሊዝ ምን ያክል የእስራኤል ጠበቃ እንደነበረች የገለፀው ናታኒያሁ አሁን ላይ ያንን ማሰብ እንኳ አይቻልም አሁን ያለቺው ኢስላማዊቷ ሀገር እንግሊዝ ነች ብሏል። የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስም በሰጠው መግለጫ እንግሊዝ በኢስላሞች ትዋጣለች አሜሪካም ቀጣይ ፕሬዚዳንቷ ሙስሊም ሊሆን ይችላል በማለት የተሰማውን ስጋት ተናግሯል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
видео или голосовое, без подписи
RSF ሱዳንን ከኢትዮጵያ የምታጎራብተውንና ቁልፎ ስትራቴጂካዊ ከተማ የሆነቺውን የኩርሙክ ከተማን በመቆጣጠር በሱዳን ጦርነት በህወሐት አጋሩ ላይ ከፍተኛ ድል ሲቀዳጅ የሱዳን ጦር ደግሞ በሰሜን ኮርዶፋን የተከፈተውን የ RSF ጥቃት መመከቱን አስታውቋል። የሱዳን ጦርነት በማይሸናነፉ ሁለት ሀይሎች ተሰንጥቆ የሱዳንን ህብን እየጨረሰ ሱዳንንም ፍርስራሿን እያወጣ ይገኛል። የብሉናይል ግዛት ቁልፍ ከተማ የሆነቺውን ኩርሙክን የተቆጣጠረው የሀሜቲው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ቀጣይ ግስጋሴውን ወደ ማእከላዊ ሱዳን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የ RSF ዋና መሪ ጀኔራል ሙሀመድ ሀምዳን ዳጌሎ ሀሜቲ ጦሩ ካርቱምን እንዲቆጣጠር ትእዛዝ አስተላልፏል። ይህን ተከትሎም የ RSF ጦር ካርቱምን በድሮን እየደበደበና የሱዳንን ጦር ሰንሰለት ለመስበር እየተዋጋ ይገኛል። የሱዳን ጦርነት ከኢትዮጵያ ጦርነት ጋር እየተሰፋ ሲሆን የ RSF ጦር ከኢትዮጵያ ጋር አጋር እንደሆነ ሲነገር የሱዳን ጦር ደግሞ ከህወሓት እና ኤርትራ ጋር አብሮ ይሰራል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
አፄ ዮሐንስ ህይወቱን በሱዳኖች ያጣው ለግብፅ እና ለእንግሊዝ ሲል ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው። በሙሀመድ አህመድ የሚመራው የሱዳን መህዲስት ጦር ሱዳንን የወረረውን የግብፅ ጦር አሸንፎ በከሰላ አማዲድ እና በኤርትራ ሰንሂት ላይ ከበውት ነበር። ግብፅ ደግሞ በጊዜው የእንግሊዝ የሞግዚት ግዛት ወይንም ተዘዋዋሪ ቅኝ ግዛት ስር ነበረች። እናም በሱዳን ጦር የተከበበውን የግብፅ ጦር ለማውጣት እንግሊዝ መላ ቢጠፋባት አፄ ዮሐንስን ማሸማገል ፈለገች። ግብፅና ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ የነበሩ ቢሆንም እንግሊዝ አስታርቃ የኢትዮጵያ ጦር የተከበቡትን የግብፅ ጦር እንዲያወጡ ለማድረግ ዲፕሎማቷን ዊሊያም ሂወትን ወደ አስመራ ከዚያም ወደ አድዋ ላከች። እናም አፄ ዮሑንስ በሶስት መስፈርት የግብፅን ጦር ከከበባ ለማውጣት ተስማሙ። የመጀመሪያው ኢትዮጵያ የምፅዋ ወደብን እንዲትጠቀም ሁለተኛው ግብፅ ጳጳሳቶቿን ወደ ኢትዮጵያ መላኳን እንዲትቀጥል ሶስተኛ ግብፅ የያዘቺውን የቦጎት ግዛት ለኢትዮጵያ እንዲትመልስ ነበር። አፄ ዮሐንስ የግብፅን ጦር ካስመለጠ በሗላ እንግሊዝ ለዮሐንስ የገባችለትን ቃል አፈረሰች። እናም ምፅዋን ከኢትዮጵያ ነጥቃ ለኢጣሊያ ( ጣልያን) ሰጠቻት። ግብፅ የለቀቀቻቼውን የኤርትራ መሬቶችም ኢጣልያ ተቆጣጠረቻቼው። ከስምምነቱ ሌላ አደገኛ ከግብፅም የባሰ ጠላት እንጅ ምንም ያላተረፈው የአፄ ዮሐንሱ የኢትዮጵያ ጦር የግብፅን የተከበበ ሰራዊት ከሱዳን ከበባ አውጥቶ ለግብፅና እንግሊዝ አስረከበ። ሱዳን በዚህ ጊዜ እንደት ለግብፅ አግዛ ትወጋኛለች በማለት ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት አወጀች። ፕሮፌሰር ያቆብ አርሳኖ "Theory and Practice of Diplomacy" ን ሲያስተምሩን ክስተቱን ሲገልፁት " ዮሐንስ በአንፃራዊነት ትንሹን ጠላት ታርቆ ከትልቁ ጠላት ጋር ተላተመ" ነበር ያሉን። በርግጥ ሱዳን ከግብፅ የበለጠ አስፈሪ ነበልባል ሀይል አደራጅታ ነበር። ምእራብ ኢትዮጵያን ጀምሮ ሱዳን እያጠቃች እስከ ጎንደር ድረስ ከፍተኛ ውድመት አደረሰች። ለአመታት የሱዳን ጦር የኢትዮጵያ ግዛቶች እያጠቃ ቤተክርስቲያን እያወደመ የበቀል በትሩን እያሳረፈ ከቆየ በሗላ ጦርነቱን ከመግጠም ውጭ አማራጭ ያልነበራቸው አፄ ዮሐንስ የሱዳንን ጦር መተማ ላይ ጥራቸውን እየመሩ ገጠሙ። የሱዳን ጦርም ዮሐንስን አንገቱን ቆርጦ በመውሰድ አሸናፊነቱን ደመደመና በቀሉን አጣጣመ። አፄ ዮሐንስ ይህን ያደረጉት ከግብፅ ጳጳሳት እንዲላኩላቸውና ምፅዋን እንዲጠቀሙ ከግብፅና እንግሊዝ በቀረበላቸው ግብዣ ነበር። አፄ ዮሐንስ ከግብፅ ጳጳስ ካልመጣ ሀገሪቱ አደጋ ላይ እንደምትወድቅና የርሳቸው የስልጣን ሄጋዊነትም ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ ያስቡ ነበር። ግብፅ በጳጳሳቶቿ አማካኝነት ለሺህ አመታት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ስትዘውር መኖሯ የሚያስገርም እውነታ ነው። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
видео или голосовое, без подписи
መከላከያ ሰራዊቱ የትግራይን ህዝብ ከህወሓት እና ሸእቢያ መያዦነት ነፃ የሚያወጣበትን ሁኔታ ብዙ የትግራይ ወጣትም ሳያልቅ ብዙ መስዋዕትነትን ሳይጠይቅ ቢያከናውን እመኛለሁ። ለዚህ አይነተኛው መፍትሄ ደግሞ የማይለወጡ የማይቀየሩና በትግራይ ወጣቶች ደም መኖር የሚፈልጉ አመራሮችን ታላሚ ያደረገ ኦፕሬሽን ማካሔድ ነው። ዛሬ የትግራይ ህዝብ የሚፈልገው ሰላም እንጅ ጦርነት እንዳልሆነ እያለቀሱ ከሚማፀኑ የትግራይ እናቶች ፤ መድረሻ አጥተው ከሚሰደዱ የትግራይ ወጣቶች እያየን ነው። ከቅጥረኞቹ ውጭ አብዛኛው የትግራይ ወጣት መዋጋት አይፈልግም። እየተገደደ እየታፈነ ነው ለስልጣን ተሰዋ እየተባለ ያለው። በመሆኑም መንግስት ይሄ ህዝብ ከመያዣነት የሚወጣበትን ስልቶች አጢኖ ካለ ጦርነት መኖር የማይችሉ የህወሓት አመራሮችን ኢላማ ማድረግ ይኖርበታል። ለነርሱ ስልጣን ሲባል ስንት መቶ ሺህ ወጣት እንደገና ይለቅ! የትግራይ እናቶች የድረሱልን ጥሪን መንግስት ዘላቂ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
видео или голосовое, без подписи
ግብፅ የመካ ጥምረትን እንደምትቀላቀል ቱርክ ገልፃለች ። የቱርኩ ውጭጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን እንደገለፁት ግብፅ የሶስቱ ሀገራት ተፈጥሯዊ አጋር ነች። እናም ጥምረቱን የመቀላቀሏ ጉዳይ የሚቀር አይደለም። ሀካን ፊዳን እንዳሉት ከሆነ ግብፅ ጥምረቱን ለመቀላቀል የቀራት የተወሰኑ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ብቻ ናቸው። እነዚያ እንዳለቁ ቱርክ የጥምረቱ አባል የማትሆንበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል። ቱርክና ግብፅ አሁን የአጋር ያክል እየሰሩ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ በጋራ የምንጋፈጣቸው የጋራ ጠላቶች አሉን ብለዋል። የመካ ወታደራዊ ጥምረት በሶስቱ ሀገራት ብቻ እንደማይገደብ የገለፁት ሀካን ፊዳን ጥምረቱ የቀጠናውንና ሀገራትና ሌሎችንም ያቀፈ ትልቅና ሀያል ጥምረት ይሆናል መካከለኛው ምስራቅንም የሚያረጋጋ ሀይል ይሆናል ብለዋል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
ለእኔ የብልፅግና ስርአት መውደቅ አለመውደቁ አይደለም የሚገደኝ። የሚገደኝ አወዳደቁና ከወደቀ በሗላስ ማን የተሻለ ይተካዋል የሚለው። እኔ የብልፅግና መንግስት ከወደቀ እንዲወድቅ የምፈልገው በተሻለ መንግስትና ሲቀየርም በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲሆን ነው። ሰላማዊ የትግል ስልቶችን ተከትሎ ብቻ እንዲወድቅ! እኔ የብልፅግና ተቃዋሚ እንጅ ደጋፊም አባልም አይደለሁም። እዚህ ለምፅፈው እያንዳንዷ ፅሁፌም አይደለም ክፍያና እውቅናም አላገኝበትም! ግና ለሀገርና ስርአተ መንግስቷ ህልውና መስዋዕትነት ለሚከፍለው የሀገሬ አለኝታ ለሆነው መከላከያ ሰራዊቴ ለመፃፍ ክፍያና እውቅናንም አልሻም። እናም በልበ ሙሉነት እንዲህ እላችሗለሁ! ይሄ መከላከያ ሰራዊት ባይኖር የሚደርስብንን ውድመት ስላላያችሁት መስዋትነቱን ዋጋ አልሰጣችሁትም ተወደደም ተጠላም ይህ መከላከያ ሰራዊት በመስዋዕትነቱ ሀገር አትርፎልናል! ህዝባችን ከዚህም በላይ ይደርስበት ከነበረው ውድመት እልቂት ታድጎልናል! እንደ ሀገር አስቀጥሎልናል! ያሉብን ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች በርካታና ዘርፈ ብዙ ፤የተጋፈጥነው የኑሮ ውድነትና ሰላም ማጣት ትእግስትን የሚፈታተን ቢሆንም እንደ ሀገር ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለችን እንድንል ይሄ መከላከያ ሰራዊት ነው የህይወት መስዋዕትነት ከፍሎ ያቆየልን እንደ ሀገር ስለቀጠልን ወደፊት ተስፋ እናደርጋለን ! ነገሮች እንዲስተካከሉ እንመኛለን ! ሰላም እንዲፀናልን እናልማለን! ከዚህ ውጥንቅጥ እንደምንወጣ ተስፋ እናደርጋለን ለምን ከተባለ በዚህ ሰራዊት መስዋዕትነት! ይህ ሰራዊት ባይኖር ሱዳንን የሚያስንቅ እልቂት ውስጥ በገባን ነበር! ሀገራችን ኢትዮጵያ እርስበርስ በብሔርና ሀይማኖት ለመጠፋፋት በሚታገሉ ነፃ አውጭ ነን ባይ ብሔሮተኞች የተሞላች ሀገር ነች። ፋኖ እና ኦነግ በየክልሉ ሀይሉን ቢይዙ የሚፈጠረውን ማሰብ አለመቻል ይገርመኛል። መተላለቁ የበርካታ ዙር መተላለቅ ነበር አይደለም በአማራና ኦሮሞው አይደለም በአማራና በትግሬው ይቅርና በጎጃምና በጎንደር ታጣዊዎች መካከል የሚደረገው መተላለቅ እንኳ ቀላል አይሆንም ነበር። ልትሸፋፍኑት አትሞክሩ በዚህ መከላከያ ሀይል ውስጥ ያሉ ወታደሮች ወንጀል ቢሰሩ ያንን በማስረጃ ይዞ መሞገትም መክሰስም ይቻላል መላው መከላከያ ሰራዊትን ስም ማጥፋት ግን ተጠያቂነት የሚያስከትል ወንጀል መሆን አለበት። መከላከያ የዋለለትን የሚያውቀው የደረሰለት ህዝብ ብቻ ነው! ለሀገር መስዋዕትነት ከፍሎ ያቆየውን የቀድሞውን መከላከያ ሰራዊታችን የደርግ ብለው እንዳኮሰሱት በመከላከያችን ላይ እንዲደግሙት አንሻም! ደግሞም ተስፋ አደርጋለሁ ! የዚህን ጀግና ሰራዊት መስዋዕትነት የሚረዳ ትውልድ እንደሚፈጠር! ይሄ መንግስት የመከላከያውን መስዋዕትነት ከንቱ የማያስቀሩ ፖለቲካዊ ማሻሻያዎችን ፤ ኢኮኖሚያዊ መሻሻሎችን ያደርግ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ትእቢተኛ ባለስልጣኖቹን አደብ ያሲዝ እንደሆነ ፤ የመከላከያውን ደም ከንቱ የሚያስቀሩ የውስጥ ተላላኪ ጥቅመኞችን ነቅሎ እንደሚያወጣ! መንግስታት ይቀያየራሉ መከላከያ ሰራዊት የአንድ ሀገር የመኖር ህልውና ነውና በፍፁም አንደራደርበትም! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
"ይሄ መከላከያ ሰራዊት የስርአቱ ታዛዥ እንጅ የሀገርና የህዝብ መከላከያ ባሀመሆኑ የብልፅግና ሰራዊት ነው እንጅ የኢትዮጵያ አይደለም" ይላሉ መከላከያ ሰራዊቱን የሚተቹና የሚያወግዙ አካላት። ይህ የአንድን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ተግባርና ሚና ፤ የአንድን ሀገር መንግስት ስልጣንና ወሰን ፤ የአንድን ሀገር መሪ የማዘዝ ገደብንም ካለማወቅ የሚመነጭ ወቀሳ ነው። አንድ መከላከያ ሰራዊት የአንድ ሀገረ መንግስት አካል ነው። እናም የአንድን ሀገር መንግስት በህገወጥ መልኩ ከመውደቅ ሀገር እርስበርስ ጦርነት እንዳትገባ ፤ በውጭ ጠላቶቿም እንዳትወረር ይጠብቃል። የአንድ ሀገር መከላከያ ሰራዊት አዛዦችና ጀኔራሎች ያሉት ሲሆን የዚያ ሰራዊት ጠቅላይ አዛዢና ውሳኔ ሰጪ ደግሞ የሀገሪቱ መሪ ነው። ለምሳሌ የአሜሪካን ጦር የመጨረሻ ትእዛዝ የሚያዘው ትራምፕ ነው። የቱርክን ኤርዶጋን ፤ የቻይናን ዢ ጂንፒንግ ፣ የሩሲያን ፑቲን ፣ የዩክሬይንን ዜሌንስኪ ፤ የእስራኤልን ኔታኒያሁ ወዘተ እያልን መቀጠል እንችላለን። እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለአብይ አህመድ አይታዘዝም ብለህ አስበህ ከሆነ አንተ ሀገረ መንግስትነት አልገባህም። የትኛውም ሀገር መሪ በመሪነት እስከቆየ ድረስ በሀገሪቱ ጦር ውሳኔ ላይ የመጨረሻውን ውሳኔ የሚወስነው እርሱ ነው። አብይ አህመድም የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆኑ የመወሰን ስልጣንና መብቱ የርሱ ነው። ሌላው ሁሉም ከርሱ ስር ነው። ጠቅላይ ማለት ትርጉሙ አይገባህም እንዴ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልህኮ የመከላከያውም የኢኮኖሚውም የፖለቲካውም የሁሉም ሚኒስትር ማለት ነው። ካቢኔዎችን የሚያዋቅረው ስልጣን የሚሰጠው ጠቅላዩ ነው። እናም መከላከያ ሰራዊት በሀይል መንግስትን ለመገልበጥ የሚታገሉ የትኛውም ሀይሎች ላይ በሀይል አፀፋ የመመለስ ግደታ አለበት። የሀገሪቱን ስርአት ማፅናት አንዱ ምሰሶው ነው። መከላከያ ጣልቃ የማይገባው በምርጫ ፤ የህዝብ ጥያቄ ፤ ሰላማዊ ሰልፍ ፤ አድማ ፤ ህዝብ በመንግስት ላይ በሚያነሳቸው ተቃውሞዎች ወዘተ ጣልቃ አይገባም። በፖለቲካ አደረጃጄቶች ፤ በሲቪል ማህበራት ወዘተ ጣልቃ አይገባም። ግን መንግስትን በሀይል እገለብጣለሁ ባለ የትኛውም አካል ላይ ጣልቃ ገብቶ ሀገር ያድናል ያረጋጋል። ያ መንግስት አምባገነናዊ ሊሆን ይችላል ፤ ዲሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል ፤ ሀይማኖታዊ ሊሆን ይችላል በምንም መልኩ መንግስት እስከሆነ ድረስ አለምአቀፍ እውቅና ያለው ሀገሪቱን የሚመራ መንግስት እስከሆነ ድረስ ሰራዊቱ መንግስት በሀይል እንዳይናድ የመጠበቅ ሀላፊነት ይወስዳል። አለም ከዚህ ተጨባጭ ውጭ የምትመስላችሁ ወገኖቻችን ወይ አንብቡ ወይ ተመልከቱ። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
በዚህ ጦርነት በዋናነት አራት ሀይሎች ሲሳተፉ ከአራቱ ሶስቱ የሚታገሉለት አላማ ሲኖራቸው አንዱ ግን ምንም አይነት ግልፅና የጋራ ግብ ፣ የትግል እና ፖለቲካዊ አላማ ፣ ስትራቴጂ ፣ ብቁ አመራር እና ግዛታዊ ስልጣን የለውም። መከላከያ ሰራዊት በአንድ ወገን ሸእቢያ ፣ ህወሓት እና ፋኖ ደግሞ በሌላ በኩል እያደረጉ ባሉት ጦርነት ሶስቱ ግልፅ አላማ አላቸው። 1 የሸእቢያ አላማ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በተዘዋዋሪ በማዳከምና ሀገር ውስጥ ጦርነት ላይ ሙሉ ትግሉን እንዲያደርግ በማድረግ ጦርነቱን አማራ እና ትግራይ መሬት ላይ አድርጎ ኤርትራን መታደግ ነው። በዚህም በአማራ እና የትግራይ ወጣቶች መስዋዕትነት ኤርትራን ማትረፍና የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ማምከን ይፈልጋል ። በተለይም ኤርትራ የኢትዮጵያ ጦር መከላከል የሚያስችል የጦር አቅም ፣ ተዋጊ የሰው ሀይል እና ኢኮኖሚ ስለሌላት ባለ በሌላ ሀይሏ በመደገፍ ጦርነቱን እዚሁ ማስቀረት ትፈልጋለች ። ኤርትራ ህዝብ አልባ ወጣት አልባ ሀገር እየሆነች ሲሆን ኤርትራ ውስጥ ከሚኖረው ይልቅ የሚሰደደው ህዝብ የሚበልጥባት ሀገር ነች። እናም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኤርትራ ላይ ጦርነት ቢያውጅ እንደማትቋቋም ስጋት አላት። ለዚህም ነው ኢሳያስ አፈወርቂ የፅምዶ ሀይልን የፈጠረው። 2 ህወሓት የህወሓት ዋነኛ የትግል ግብ እና አላማ በአማራ ተይዞብኛል የሚላቸውን የወልቃይት ፣ ሁመራ ፣ ራያ ወዘተ አካባቢዎችን አስመልሶ ከኢትዮጵያ ገንጥሎ አንዲት አዲስ ሉአላዊት ሀገር መመስረት ነው። እናም የህወሓት ግብ በምስራቅ አፍሪካ ሀገረ ትግራይ የምትባልን ሀገር መውለድ። ህወሓት ሀገረ ትግራይን ከመሰረተ በሗላ በሚፈጥረው አቅም ከኤርትራ የባህር በርን መውሰድ እንደሚችል ተስፈኛ ነው። በመሆኑም ለሞቹን ወልቃይ ፀገዴን ሁመራን ራያን ጠቅልሎ ከቀይ ባህር ተግራብቶ አንድት ውህድ የሀይማኖት እና ብሔር ማንነት ያላት ሀገር መመስረት ግቡ ነው። ለዚህም ሸእቢያን እንደ ታክቲካል አጋር የሚመለከተው ሲሆን ፋኖን ደግሞ ሀገር የመመስረት ተልእኮውን ለማሳካት ቁልፍ መጠቀሚያ አድርጎ ይገቀማል። 3 የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግብ የኢትዮጵያን የሀገር ሉአላዊነት ማፅናት ፤ ሀገረ መንግስቱን ማፅናትና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የአማፂያን ትግል ቀልብሶ ኢላማውን ወደ ውጭ ጠላቶች ማዞር ነው። በዚህም መከላከያ ሰራዊት ሶስቱንም ሀይሎች የሚመክትና የሚያሸንፍ አቅም ገንብቻለሁ እያለ ሲሆን በሰሞኑ ጦርነት ያሳየው ቀድሞ የመምታት አቅም በርግጥ የመከላከያ ሰራዊቱን ዝግጅት ያሳየ ነው። 4 ፋኖ ይህን ስብስብ የትግል ስንቆች የሌለው መተኮስና መግደል ብቻ ትግል የሚመስለው በስልጣን በተጠሙ በትንቢትም ንጉስ ትሆናላችሁ ተብለው በተቀቡ አጉል መንፈሳዊያን የሚመራ የጠራ ግብም አላማም ውህደትም መዋቅርም የሌለው ቡድን ነው ብሎ መፈረጅ ይቻላል። እየተከፋፈለ እርስበርስ እየተገዳደለ በሄደ ቁጥር " ትግሉ እየጠራ ነው" የሚሏ አደንዛዦች የሚያስጮሁለት አንድ ጎኑን በሀይማኖት ሌላ ጎኑን በብሔር ቀለም የቀባ ሲያሻው ከኔ በላይ ኢትዮጵያዊ ላሳር የሚል ሲሻውም ለአማራ ያልሆነች ኢትዮጵያ ትፍረስ ብሎ የሚኮፈስ ከትጥቁ ይልቁ ፕሮፓጋንዳው የገነነ የትጥቅ ቡድን ነው። አሁን ላይ ይህን ቡድን ከሁሉም ነገር ወጥቶ የተላላኪነት አሳይመንትን ከህወሓት እና ሸእቢያ ተረክቦ እታገልለታለሁ የሚለውን ህዝብ መሰረታዊ ጥዬቄዎች ቅርንጫፋዊ እና አብነት የሌላቸው ብሎ ፈርጆ ቁጭ ያለ ድርጅት ነው። የአማራ ብሔርተኝነት ትግል እንደ ዋና ማቀንቀኛ ይታዩ የነበሩትን የነ ወልቃይት ፤ ጠገዴ ፣ ሁመራ ፣ ራያ የመሳሰሉ ግዛቶችን " ትግላችን የቁራጭ መሬት አይደለም" ብሎ አይኑን በጨው አጥቦ ተላላኪነቱን በክብር የተረከበ ቡድን ነው። ይህ ቡድን ሲነሳና ሲቀሰቅስ ለአማራ ህዝብ ነፃነት የሚል ስትራቴጂ አልባ የማማሟቂያ ትግል እንጅ የጠራ ግብና የትግል ፍኖት ሳይኖረው ነው የጀመረው። የቡድኑ አመራሮች ሲሻቸው 4 ኪሎ እንገባለና ኢትዮጵያን ነፃ እናወጣለን የአባቶቻችን ቤተመንግስት እንገባለን ሲሉ ሲሞቃቸው እኛ አማራ እንጅ ሌላው ምናገባን ሲሉ አሁን ላይ ወርደው ወርደው ከአማራ ፋኖነት ወደ ጎጃም ፋኖነት ፤ ጎንደር ፋኖነት ፤ ሸዋ ፋኖነት ተሰነጣጥቀው የጎጃሙ የህወሀትና ሸእቢያ የማደጎ ልጅነትን ያገኘ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የአማራ ጥቅም ላይማ ከህወሓት ጋር አናብርም ብለው ቃታ ተሳስበው ፤ የመናናቂያ ስያሜ ተሰያይመው ቁጭ ብለዋል። አሁን ላይ እነዚህ ሀይሎች የሚቆጣጠሩት የክልልም የዞንም የወረዳም ከተማ ካለመኖሩ በተጨማሪ ብዙዎቹ የትግሉ መሪዎች ወደ ትግራይ እና ኤርትራ የመሸጉና የሸሹ ናቸው። አሁን ላይ የጎንደር ፋኖ ከመንግስት ጋር አብሮ ለመስራት እየተለሳለሰ ሲሆን አይበለውና ውጊያው ከተጧጧፈ አብዛኛው ፋኖ ወይ ከመንግስት ያብራል ወይ እጁን ይሰጣል ከጎጃም ፋኖ ውጭ! እናም የአራቱ ተፋላሚዎች የትግል መልክና አላማ ይሄን ይመስላል። ጦርነቱ በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የበላይነት እንደሚጠናቀቅ ሸክ የለኝም! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
ቱርክ የመካ ጦር ጥምረት ኢላማ ኢራን አለመሆኗን ገልፃለች። የቱርኩ ውጭጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጥምረቱ ኢራንን በባላንጣነት እንደማይፈርጅና ኢራን ኢላማ ያደረገ እንዳልሆነ አስታውቀዋል። ጥምረቱ የኔቶ አይነት መልክ እንደሚኖረው የተናገሩት ሀካን ፊዳን የሶስቱ ሀገራት ጦር ጥምረት በአንድ እዝ የሚመራ በጠቅላላ ጀኔራል እንደሚታዘዝም አስታውቀዋል። ጥምር ጦሩን የሚመራ ሚኒስትርና አመራር እንደሚፈጠርም ገልፀዋል። ከዚያ በተጨማሪ የትኛውም ሀገር በሶስቱ ሀገራት ላይ ጥቃት እስካፀመ ድረስ ኢላማ እንደማይሆን የገለፁ ሲሆን ጥቃት ለመፈፀም ያሰበ ሀገር ግን በጋራ ይመታል ብለዋል። ይህም የኔቶን አንቀፅ 5 ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ገልፀዋል። የመካ ጦር ህብረት የሙስሊም ኔቶ እየተባለ እየተጠራና ከፍተኛ አለማቀፋዊ ትኩረት ያገኘ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ ሙስሊም ሀገራትን ያካትታል ተብሎ ይጠበቃል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
የአሜሪካ ኮንግረስ የሆነው አንዲ ኦግሌስ የአሜሪካ ሙስሊሞችን ከተሳደበ በሗላ በምርጫ ተሸንፏል። ኮንግረሱ አንዲ ኦግሌስ የጥላቻ ቅስቀሳን በመጠቀም ከፍተኛ ድምፅ ለማግኘት ቢሞክርም ውጤቱ ግን በተቃራኒው ሆኗል። ኮንግረሱ ኦግሌስን ትራምፕ እንዲመረጥ ኢንዶርስ አድርጎት የነበረ ቢሆንም ተሸንፏል። በዚህም በዚህ ሳምንት ብቻ ትራምፕ የደገፋቸው ሁለት ፅንፈኞች በምርጫ መሸነፋቸው የትራምፕና የፂዮናዊያን አቀንቃኞች ምን ያክል በአሜሪካ ፖለቲካ እየተጠሉ መሆኑን አመላካች ነው። የትራምፕ አስተዳደር ፅንፍ በወጣ እስራኤል ወዳድነቱ በአሜሪካ ብዙሀን ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠላ ሲሆን ለእስራኤል ማቀንቀን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የምርጫ መሸነፊያ እየሆነ ይገኛል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
видео или голосовое, без подписи
የቱርክ ሳኡዲ ፓኪስታን ጥምረትን ቀላል አድርገው ወይንም የይምሰል አድርገው የሚያዩት አሉ። እኔ እንደዚያ አላየውም። እንደተባለው ሶስቱ ሀገራት በየሴክተሩ ግዙፍ አቅም ያላቸው ከመሆኑም በላይ የጂኦፖለቲካዊ አቀማመጣቸው እጅግ ስትራቴጂካዊ ነው። በተለይ ለቱርክ ወታደራዊ መስፋፋት ሰፊ መንገድ የሚጠርግ ሲሆን ፓኪስታን ከቀጠናዋ አልፋ እስከ ቀይ ባህር ተፅእኖዋን እንዲታሳርፍ የሚያደርጋት ነው። ሳኡዲ በዚህ ሁሉ እንቅስቃሴ የፖለቲካና ወታደራዊ አቅሟ ይፈረጥማል። የቱርክ ጦር በሶሪያ ፤ በሊቢያ ፤ በኳታር ፣ በሶማሊያ ፣ በአዘርባይጃን ሰፊ የጦር ሰፈር አለው። አሁን ደግሞ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ይገባል ማለት ነው። የፓኪስታን ጦር ከሶማሊያ ጋር ስምምነት ማድረጉን ተከትሎ ጦሯን ሶማሊያ ላይ የምታሰፍርበት ሁኔታ ተመቻችቷል። እናም የቱርክ እና ፓኪስታን ጦር ሶማሊያ ላይ ይሰፍራል ማለት ነው። በተፃራሪው የሚቆሙት እስራኤል እና ኢማራት ናቸው። ነገሩ ጥልፍልፍ ነው። እዚህ የኢትዮጵያ - ኢማራት-እስራኤል -ሶማሌላንድ አሰላለፍ አለ በሌላ በኩል የቱርክ-ሳኡዲ-ፓኪስታን-ሶማሊያ ጥምረት አለ። በሶስተኛነት ደግሞ በኢራን የሚመራው የኢራን ሁቲ ጥምረት አለ። ሶስቱም እርስበርስ ተፈላላጊና ተፃራሪ ጥምረት ነው። ህንድ በንቃት የነ እስራኤል ጥምረት ውስጥ ትሳተፋለች ወይ ወደፊት የምናየው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ከነ ቱርክ እና ሳኡዲ ተፃራሪ በይፋ መሰለፍም አትፈልግም። ከነዚህ ሀገራት ጋር ጠንካራ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ስላላት። በመሆኑም ኢትዮጵያ passive ተሳታፊ ነው የምትሆነው። ዋናው ፍጥጫ ግን በቱርክ መርነትና በእስራኤል መርነት ላይ ይሆናል። ግብፅ በዚህ አሰላለፍ ውስጥ ከነ ቱርክና ሳኡዲ ጋር እንደምትሰለፍ አያጠያይቅም። t.me/Seidsocial
#የመካ_ጥምረት - ሶስቱን ታላላቅ ሙስሊም ሀገራት ያጣመረው ወታደራዊ ጥምረት ተስፋና ተግዳሮቱ! ስምምነቱ ለምንና አሁን አስፈለገ? ላለፉት ጥቂት አመታት የመካከለኛው ምስራቅ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ በእጅጉ ተገለባብጧል። በተለይም የሀማስ እና እስራኤል ጦርነት የቀጠናውን መልክ ላይመለስ ቀይረውታል። ያ ጦርነት በርግጥ የመካከለኛው ምስራቅን ብቻ ሳይሆን መላው የአለምን ፖለቲካ የቀየረ ክስተት ነው። የአሜሪካን ውስጣዊ ፖለቲካ ሳይቀር! የሀማስ-እስራኤል ጦርነት የሊባኖስ እስራኤል ጦርነትን ፣ የየመን እስራኤል ጦርነትን ፣ የየመን አሜሪካ ጦርነትን እና የአሜሪካና እስራኤል ከኢራን ጋር ያደረጉትን ጦርነት ወልዶ ቀጠናውን የሚሳኤል ንዳድ ማእከል የጦር ጄቶች ማጓሪያና የድሮኖች ህልቆ መሳፍርት የሌለው የጥቃት ማእከል አድርጎታል። በዚህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ሲያልቁ የኢራን የጋዛ የሊባኖስ እና የየመን በርካታ አመራሮች ተሰውተዋል። ይህ ጦርነት ያረጋገጠው አንዱ ነገር ታዲያ አሜሪካ እጠብቃችሗለሁ ብላ የምትመዘብራቸውን የአረብ ሀገራትን በእውነተኛው ጦርነት ጊዜ መጠበቅ እንደማትችል ተፈትና የወደቀችበት መሪር ፈተናዋ መሆኑ ነው። እናም ሳኡዲን የመሳሰሉ የቀጠናው ሀያላን ሀገራት ያላቸውን ወታደራዊ ጥምረት እንደገና ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያስገድድ ክስተት ነበር። ለዚያም ነው ሳኡዲ ቱርክ እና ፓኪስታን ተጣምረው አዲስ ሀይል አዲስ አሰላለፍን ለመፍጠር የወሰኑት። ጥምረቱ ምንን ይዟል? ጥምረቱ የመከላከል ጥምረት መሆኑን ሶስቱም ሀገራት ገልፀዋል። እናም ከሶስቱ አንዱ ሀገር ሌላ ሀገር ላይ ጥቃት ቢፈፅም ጥምረቱ የጋራ እርምጃ አይወስድም። ግን ከሶስቱ ሀገራት በአንዱ ላይ የሚፈፀም ጥቃት በሁሉም ላይ እንደተፈፀመ ይቆጠራል። ይህም የኔቶ አይነት ባህሪ ይኖረዋል። ወታደራዊ ስምምነቱ የጋራ ደህንነት መገንባትን ፤ የጋራ የስለላ መረጃዎችን መለዋወጥን እና በጋራ የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎችን ማምረትን ያካትታል። የጋራ ወታደራዊና የደህንነት ፖሊሲ ፤ የጋራ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎችንም ይገነባሉ። ቱርክ በኔቶ ሁለተኛዋ ሀያል ጦር ና በጦር ኢንዲስትሪም ከአለም ቀዳሚ ሀገሮች ናት። ፓኪስታን ግዙፍ የጦር ሰራዊት ሲኖራት ከሙስሊም ሀገራት ብቸኛዋ የኑክሌያር ባለቤት ነች። ሳኡዲ ግዙፍ የፋይናንስ አቅምና በአለምም ቀዳሚዋ ነዳጅ ላኪ ሀገር ነች። እናም ሶስቱ ሀገራት ይህንን አቅማቸውን ማቀናጀት ነው የፈለጉት። ሳኡዲ አረቢያ የጦር መሳሪያ በገፍ የምትገዛ ሀገር በመሆኗ በአሜሪካ ላይ ጥገኛ ነች። እናም ይሄንን ጥገኝነቷን ለመቅረፍ አልማለች። ጥምረቱ እነማንን ታላሚ አድርጓል? ሶስቱም ሀገራት ጥምረቱ መከላከልን እንጅ ማጥቃትን መሰረት ያደረገ አይደለም ቢሉም ነገር ግን የሶስቱ ሀገራት ባላንጣ ተደርገው የሚወሰዱ በዋናነት ሶስት ሀገራት አሉ። እነርሱ እስራኤል ፣ ህንድ እና ኢራን ናቸው። ሶስቱም ሀገራት ጥምረቱን በቀላሉ አይመለከቱትም። ቱርክ ከእስራኤል ጋር ቃላት መወራወር ከጀመረች ቆይታለች። የእስራኤል ባለስልጣናትም ከኢራን የበለጠ ለእስራኤል አደገኛዋ ጠላት ቱርክ ነች ማለት ከጀመሩ ሰነባበቱ ። ቱርክና እስራኤል የመካከለኛው ምስራቅ ሀያል ጦሮች እንደመሆናቸው ቀጣዩ ፍጥጫ በነርሱ መካከል መሆኑ አያጠያይቅም። ህንድና ፓኪስታን የለየለት ጠላትነት ያላቸው ሀገራት ናቸው። ህንድ ይህንን ጥምረት በቀላሉ አትመለከተውም። ሁለቱ ሀገራት በቅርቡ በፓኪስታን አሸናፊነት የተጠናቀቀ ጦርነትን ማካሔዳቸው የሚታወቅ ነው። ሳኡዲ እና ኢራን የቀጠናው ባላንጣዎች ናቸው። ኢራን ከሳኡዲ ጋር በየመኑ ሁቲዎች በኩል ትዋጋለች። ሳኡዲ የአሜሪካን ጦር ሰፈር በማስፈሯ ኢራን በበጎ አታያትም። በሳኡዲ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን በተደጋጋሚ ስትመታ የምናየው ነገር ነው። ኢራን የሶስቱን ሀገራት ጥምረት አስመልክቶ ይፋዊ መግለጫ ባታወጣም የኢራኑ ፓርላማ አባልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮሚቴ ኢብራሂም ሬዛኢ በትዊተር ገፃቸው እንደፃፉት " ሳኡዲ ከቱርክና ፓኪስታን ጋር የፈፀመቺው የወረቀት ስምምነት ደህንነቷን እንደማያስጠብቅላት ማወቅ አለባት ልክ ከአሜሪካ ጋር ያደረገቺው ። ሳኡዲን ደህንነቷን የሚያስጠብቀው ፖሊሲዋን ስታስተካክል እንጅ የሌሎችን ከለላ በመለመን አይደለም " ብለዋል። የሆነው ሆኖ ይህ ስምምነት ከስምምነት ባሻገር ገቢር የሚሆን ከሆነ የአለምን የሀይል አሰላለፍ ከሚቀይሩ ክስተቶች አንዱ ይሆናል። ስምምነቱ ሌሎች ሀገራትን የማካተት እድሉ ሰፊ መሆኑን የዘርፉ ተንታኞች ይናገራሉ። በተለይም ኳታር በቅርቡ ልትቀላቀል ትችላለች። ግብፅ ሌላኛዋ ተጠባቂ ሀገር ነች። የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጠው መግለጫ ስምምነት በኢስላማዊ ወንድማማችነች ማገር የታሰረ ፤ በጋራ ፍላጎቶችና ታሪኮች የተጋመደ ፤ ሀገራቱ የጋራ ስትራቴጂካዊ ግቦቻቼውን በጋራ የሚያሳኩበት ታሪካዊ ጥምረት ነው" ብሎታል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial
видео или голосовое, без подписи