Nejashi TV // ነጃሺ ቲቪ
Статистикаየነጃሺ ቲቪ ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን ። የተለያዩ መረጃዎችና እውቀቶች ይገበያሉ ። ተቀላቀሉን ! Facebook: https:// Jeilumedia.com Telegram: https://t.me/nejashitvofficial E-mail: nejashitvaddis@gmail.com https://youtube.com/@nejashitva?si=O8pqOoIDjDmMBX74
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 28
- Всего постов
- 44
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 152
- 1/48двое суток
- 1 188
- 1/72трое суток
- 1 281
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ከግማሽ በላይ የሚሆነው የጋዛ ነዋሪ ለከፋ የውሀ እጥረት እና የንፅህና ችግር መጋለጡን ተመድ አስታወቀ ነጃሺ ቲቪ || ነሐሴ 7/ 2018 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ አብዛኛው የጋዛ ነዋሪ በቂ የንጹህ ውሃ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና የፍሳሽ ማስወገጃ አገልግሎቶችን ማግኘት ባለመቻሉ ለከፋ የጤና እና የሰብዓዊ ችግር መጋለጡን አስታወቀ። ተቋሙ በሪፖርቱ እንዳመለከተው፤ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የጋዛ ህዝብ በቀን ከ6 ሊትር በታች፣ እንዲሁም 700 ሺህ የሚጠጋው ነዋሪ ደግሞ ከ9 ሊትር ያነሰ ውሃ ብቻ እያገኘ ይገኛል። ይህ አቅርቦት በድንገተኛ ጊዜ ለአንድ ሰው ከሚያስፈልገው 15 ሊትር መደበኛ መጠን ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ በመሆኑ፣ ነዋሪዎቹ የግል ንፅህናቸውን ለመጠበቅም ሆነ የልጆቻቸውን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት በእጅጉ መቸገራቸውን ገልጿል ። በውሃ ማደያዎች አካባቢ ከፍተኛ መጨናነቅ መፈጠሩን ያመለከተው ሪፖርቱ፤ በቂ የውሃ መያዣ ባለመኖሩ ምክንያት ውሃ የማመላለሱ አድካሚ ስራ በህፃናት ላይ መውደቁን አስታውቋል። በአሁኑ ወቅትም ከአራት የጋዛ ነዋሪዎች ሦስቱ በውሃ ጫኝ መኪኖች ላይ ጥገኛ መሆናቸው ተገልጿል። ከውሃ እጥረቱ በተጨማሪ የንፅህና አገልግሎት መጓደል ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጸው ሪፖርቱ፤ በጋዛ ከሚገኙ አባወራዎች መካከል መሰረታዊ የንፅህና መጠበቂያ ያላቸው ግማሽ ያህሉ ብቻ መሆናቸውን አብራርቷል። በዚህም ከ900 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች በመኖሪያ አካባቢያቸው በሚከማች ቆሻሻ ምክንያት ለከፋ የጤና ቀውስ መጋለጣቸውን አስገንዝቧል። በቃለላህ ሳዲቅ
ቱርክ "እስራኤል ቀጠናዊ ግጭቶችን በመጠቀም የፍልስጤምን ጉዳይ ከዓለም አቀፍ አጀንዳነት ለማስወጣት እየሰራች ነው" ስትል ወቀሰች ነጃሺ ቲቪ || ነሐሴ 6/2018 የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርጋን፣ የቤንጃሚን ኔታንያሁ አስተዳደር በቀጠናው የተፈጠሩ ግጭቶችን እና ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቶችን በመጠቀም የፍልስጤምን ጥያቄ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አጀንዳነት ለማስወገድ እየሰራ መሆኑን ከሰዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ከፍልስጤም አቻቸው ማሕሙድ አባስ ጋር በአንካራ በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። ኤርዶጋን በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፣ "የኔታንያሁ መንግስት ዋነኛ ስትራቴጂካዊ ዓላማ በቀጠናው ከተፈጠረው ትርምስ እና አዳዲስ ግጭቶች ፖለቲካዊ ትርፍ በማጋበስ የፍልስጤምን ጉዳይ ከሰው ልጅ የጋራ አጀንዳነት ማጥፋት ነው" ብለዋል። አክለውም የቱርክ መንግስት ሉዓላዊት የፍልስጤም ሀገር እንድትመሰረት የሚያደርገውን ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል መግባታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። በማህበረ-ፖለቲካዊ ስነ-ልቦና አውድ የእስራኤልን መዋቅራዊ ጫና በተመለከተ ኤርዶጋን ሲያብራሩ፤ "እስራኤላውያን ምንም ዓይነት ማወናበጃ ቢሰሩም ሊሳካላቸው አይችልም፤ የፍልስጤምን ጉዳይ ለማጥፋት በሚሞክሩበት ቁጥር፣ ጉዳዩ በሰዎች ልብ ውስጥ ይበልጥ ስር እየሰደደና እያደገ ይሄዳል" ብለዋል። የፍልስጤሙ መሪ ማሕሙድ አባስ የዲፕሎማሲ አማካሪያቸውን ማጅዲ ኻሊዲን፣ የደህንነት ኃላፊውን ማጀድ ፋራጅን እና ከፍተኛ የፍልስጤም ባለስልጣን ዚያድ አቡ አምርን አስከትለው ትናንት ማክሰኞ አንካራ የገቡ ሲሆን፣ ከቱርኩ ፕሬዚዳንት ጋር ያደረጉትን ወቅታዊ የቀጠናው ጂኦ-ፖለቲካዊ ጉዳዮች እና የሁለትዮሽ ውይይት "እጅግ ወሳኝ እና ፍሬያማ" ሲሉ ገልፀውታል። በ ሐቢብ በሽር
без подписи