tgindex
🌹አል ፋሩቅ የሙፍቲዬ ትውልድ💚

🌹አል ፋሩቅ የሙፍቲዬ ትውልድ💚

Статистика

አሰላሙ አለይኩም ውድ የአል- ፍሩቅ ቤተሰቦች ይህ ቻናል እስላማዊ ጥበብ እና ትምህርቶች ላይ ይሰራል ሀሳብ አስተያየት ስህተት ካለብንም አርሙን 👇👇👇 @abukiyezeynu

Последний пост
23 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 441
−9 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 107
17 постов
Вовлечённость
24,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
375
1/48двое суток
429
1/72трое суток
463

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ከአላህ የኾነ ሰላምና እዝነት ፣ ክብር በሚከበርባቸው፣ ልቅና በሚደሳባቸው፣ ለዓለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት ፣ ለዚያ የብርሃን ዘውድ ፣ የሀቅ አገልጋይ ፣ ለቃል ኪዳኑ አክባሪ ፣ የፍጥረታት ዕንቁ ፣ የአላህ ወዳጅ የኸልቁ አማላጅ በሆኑት ባለ ታላቅ ጠባይ በነብዩል አሚን ሰለዋቱላሂ አለይሂ ወአሊሂ ወሰለም ላይ ይሁን 💚 اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ 💚

  • 9 июл.745154

    አህመድ: ያሲን: ጧሃ 💚💚 በስሙ ሚገኘው ክብረቱ ማዕረጉ፤ ትንሽ ያሉት ሁላ ባንቱ ነው ማደጉ። የቀን መንገዳችን ሲመሽ ብርሓናችን በማዕሸር ሜዳ ላይ ጠበቃ ዋሳችን። ይላል ዛሒዳችን... ባወደስነው ቁጥር ማወደስ አነሰን የሐቢበላህ ﷺ ፍቅር ያንገበገበው በደዊን ደግሞ ቀብራቸው ፊት ቁሞ ይህንን ልብ የሚሰቅዝ ግጥም ይገጥማል፤ ይህ በአል ኡትቢ የተዘገበው የበደዊኑ ግጥም የሐቢበላህ መስጂድ ውስጥ ተከትቦ እናገኘዋለን يَا خَيْرَ مَنْ دُفِنَتْ فِي الْقَاعِ أَعْظُمُهُ فَطَابَ مِنْ طِيبِهِنَّ الْقَاعُ وَالأَكَمُ የአላህ ሰላትና ሰላም በውዱ ነብይ ﷺ፣ ከነፍሴ በላይ በምወዳቸው መልዕክተኛ ላይ ይውረድ 💚 ረቢእ season is coming 🥰🥰

  • Live stream started

  • ✨እያንዳንዱ ሰው በራሱ የውስጥ ጉዞ ላይ ተሳፋሪ ነው። ✨ውጭ የምትፈልገውን ከውስጥ ታገኛለህ። @limugenet 🍁 @limugenet 🍁

  • 26 мая1 096102из medina_tube

    እንኳን አደረሳችሁ 🥳

  • 24 мая1 083132из MuhammedNessim

    ተሰውፍ ተሰውፍን ለማያውቁ ፦ ተሰውፍ በእስልምና ውስጥ ያለ መንፈሳዊ መንገድ ነው። ዋና ግቡ ሰው ከሃያሉ አላህ ﷻ ጋር የቅርብ መንፈሳዊ ግንኙነት እንዲኖረው ልቡን ማጥራት እና ፍቅር፣ ትሕትና፣ ሰላም እና መልካም ሥነ-ምግባር ማበረታታት ነው። ● የሱፊይነት እውነተኛ መንገድ ሸሪዓና የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ሱና ነው። ● ተሰውፍ ከአላህ ጋር በኢህሳን ሥርዓት አደብ (ስነ-ምግባር) ማሳየት ነው። ● ተሰውፍ የተወዳጁን ነቢይ ﷺ ፈለግ መከተል ነው። ● ተሰውፍ ለወንድምህ ለራስህ የምትወደውን መውደድ ነው። ● ተሰውፍ ልብህ ከአላህ በስተቀር ከሁሉም ነገር ንጹህና ጥሩ እንዲሆን ማድረግ ነው። ● ተሰውፍ አላህን እንደምታየው ማምለክ ነው፤ እርሱን ባታየውም እርሱ እንደሚያይህ ማመን ነው። ● ተሰውፍ የነቢዩን ﷺ ቤተሰቦችና የመልእክተኛውን ሰሓቦች መውደድ ነው። ● ተሰውፍ ነፍስህን ከኃጢአት ለመራቅ መታገልና ስነ-ምግባሯን ማስተካከል ነው። ● ተሰውፍ ፍቅር፣ መልካም ስነ-ምግባር፣ ፈገግታና ጀግንነት ነው። ● ተሰውፍ ሁሉንም መልካም ስነ-ምግባር መላበስና ሁሉንም መጥፎ ስነ-ምግባር መተው ነው። @MuhammedNessim

  • 17 мая94281из Dinel_islam

    የዙል ሂጃ ፆም ከሰኞ ይጀምራል የቻለ ይፁም...✨

  • 29 апр.1 317123из Dinel_islam

    ንጋታችንን በዚች ዐያ ተደቡር እናስውበውማ ادْخُلُوهَا بِسَلَامٍ ۖ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُلُودِ                             «በሰላም ግቧት ይህ የመዘውተሪያ ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡(50:34) 1."በሰላም ግቧት" ይህ አቀባበል በራሱ ትልቅ ትርጉም አለው። እዚህ ጋር "ሰላም" ሲባል፡- ከጭንቀት ነፃ መሆን፡ ከዱንያ ፈተና፣ ከሞት ስጋትና ከትንሣኤ ቀን ድንጋጤ በኋላ የሚመጣ ፍጹም እረፍት ነው። ከጥላቻ መጽዳት፡ በገነት ውስጥ ባሉ ሰዎች ልብ ውስጥ ምንም ዓይነት ቅያሜ ወይም ጥላቻ እንደማይኖርና በመካከላቸው ሰላማዊ ፍቅር ብቻ እንደሚሰፍን ያሳያል። 2. "ይህ የመዘውተሪያ ቀን ነው" ይህ ቃል በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ያለውን ትልቁን ፍርሃት ማለትም "ይህ ደስታ ያልቅ ይሆን?" የሚለውን ስጋት ያስወግዳል። ዘላቂነት፦ በምድራዊ ሕይወት ማንኛውም ደስታ አላፊ ነው፤ በጀነት ግን ደስታው አያልቅም፣ ነዋሪዎቿም አይወጡባትም። ፍጹም እርካታ፦ "የመዘውተሪያ ቀን" (የዘላለም ቀን) መባሉ፣ ከዚያ በኋላ ለውጥ ወይም መጨረሻ እንደሌለ ማረጋገጫ ነው። አንቀጹየሚያስተምረን በምድር ላይ በትዕግስትና በጽናት ለፈጣሪ የታዘዙ ሰዎች፣ መጨረሻቸው ፍጹም ሰላምና የማይቋረጥ ዘላለማዊ ደስታ መሆኑን ነው። ይህ "በሰላም ግቧት" የሚለው ጥሪ ለደጋግ ሰዎች የሚቀርብ የድል እና የደስታ አቀባበል ነው። "በሰላም ግቧት"  ከሚባሉት ባሮችህ ኢላሃ

  • 20 мар.1 54014из Dinel_islam

    🌺ሸዋልን እንፁም .....አቡ አዩብ ረ.አ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል።።።። ረመዷንን የጾመና እርሱን አስከትሎም ከሸዋል ወር ውስጥ ስድስት ቀናትን ያከለ አመቱን ሙሉ እንደጾመ ይቆጠርለታል! @Dinel_islam @Dinel_islam

  • 20 мар.1 2275из medina_tube

    መልካም ዒድ ለሁላችሁም!!! تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

  • 10 мар.1 415172

    ✨ስለ አላህ ፍቅር ​"إذا اشتغل القلب بذكر الله، أضاءت الروح بنور المحبة." 🌟🌙 ​"ልብ በአላህ ዝክር (ውዳሴ) ከተጠመደ፣ ነፍስ በፍቅር ብርሃን ትበራለች። —✨🦋 ሀቢብ ኡመር ኢብን ሀፊዝ✨🦋 ​#ዝክር #ፍቅር #መንፈሳዊነት ያሸሐበ ዳኒ

  • 9 мар.958из alhadratube1

    видео или голосовое, без подписи

  • 7 мар.1 07582из Al_beyan_midya

    ከቀደምት ደጋጎቹ አንድ ሳሊህ ሰው ነበር። በቀን ውስጥ ወንጀል ከሰራ ወንጀሉን በግጥም ይፅፍ ነበር። ከእለታት ባንዱ ለት ጥፋትን አጠፋና ግጥሙን ሊያሰፍር ብዕሩን ጨብጦ ለመፃፍ ቢሞክርም  فَأُولَٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا " ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ " : ከሚለው አንቀፅ ውጪ ሌላን መፃፍ አልቻለም። ይቅር ባይ፡ ወንጀለኛን የሚምር ፡ ጥፋቱን በመልካም ሚቀይር...ለተመላሾች የምህረቱን በር የከፈተው መሀሪው አላህ ይታረቀን

  • 5 мар.1 04892из Dinel_islam

    ለይለተል በድር و ኸሚስ 💚 ••••• የአላህ መልዕክተኛና ﷺ ሰሐቦቻቸው የፆም ወቅት ላይ ናቸው። ከገዛ ሀገራቸው ከተባረሩ ሰነባብተዋል፤ ቂብላው ወደ መካ ከተቀየረ በኃላም መካ በሙስሊሞች እጅ አለመሆኑ የቀን ተሌት ጭንቀታቸው ከሆነ ቆይቷል። አቡ ሱፊያን የቁረይሽ ባለሟሎችና ህዝቦች የሆነው ቅፍለት አደጋ ላይ እንደሆነና እሱን ማስመለስና ማስጠበቅ እንዳለባቸው ዜና ባደረሳቸው ሰአት ቁረይሾች በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን፤ የሚያዝናንዋቸውን ሴቶች፤ በየቀኑ የሚያርዱትን ግመል ይዘው ወጡ! የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ቅፍለቱን ማጥቃት ላይ ከሰሐቦቻቸው ጋር ውይይት ሲያደርጉ ኡመርና አቡበከርን ጨምሮ በሀሳባቸው ተስማሙ ! የአቀባ ስምምነት ላይ ቃል የገቡላቸውንም አንሳሮች ሀሳብ ጠየቁ ! ለዚህኛው ዘመቻ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ዘመቻዎችም የሚኖራቸውን ታዛዥነት ለማወቅ ጠየቋቸው የበድር ዘመቻ ሙሐጂሮችና አንሳሮች ለሸፊዒ የነበራቸው መሐባና ስስት የታየበት ታላቅ ገዝዋ ነበርና ሂጅራ ካደረጉ በሁለተኛው ዓመት ይህ ያልተጠበቀ ዘመቻ ተከሰተ፤ ውስን መሆናቸው ከዘመቻው እንዲሸሹ አላደረጋቸውም! 313ቱም ሰሐቦች ሐቢበላህ ጎን መሰለፍ'ን፣ መስዋዕት መሆንን በፍቅር ተቀበሉ። ከሙሐጂሮች ሚቅዳድ፣ ከአንሳሮች ደግሞ ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ ተነስተው ቃልኪዳናቸውን ሰጡ። ሚቅዳድ'ም ከፍ ባለው ድምፁ ንግግሩን እንዲህ ጀመረ: يا رسول الله, لا نقول لك كما قال قوم موسى لموسى: اذهب أنت وربك فقاتلا إنا هاهنا قاعدون ، ولكنا نقاتل عن يمينك وعن شمالك ، ومن بين يديك ومن خلفك «ያ ረሱለላህﷺ! እኛ ልክ እንደ ሙሳ ህዝቦች ነቢዩላህ ሙሳን "ሂዱ! አንተና አምላክህ በጋራ ጠላታችሁን ተጋደሉ።" እንዳሉት የምንል አይደለንም። ይልቁኑ በቀኝህም፣ በግራህም፣ ከፊትህም ፣ከኃላህም አብረንህ በመሆን እንዋጋቸዋለን።» በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጠ። 💚 ቀጥሎ'ም ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ የአንሷሮች ውዴታና የሱ አይነታነት የታየበትን ድንቅ የፍቅር ንግግር ተናገረ: "يا رسول الله! فقد آمنا بك وصدقناك ، وشهدنا أن ما جئت به هو الحق ، وأعطيناك على ذلك عهودنا ومواثيقنا ، على السمع والطاعة .... 🥹 «ያ ረሱለላህ ﷺ! ባንቱ አምነናል። እውነትን እንደሚናገሩ መስክረናል። አንቱን ለመጠበቅ፤ መስዋዕት ለመሆንና ታዛዥ ለመሆን፤ ሰማን ታዘዝንም ለማለት ቃላችንን ሰጥተናል። እንግዲያውስ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሆይ! እውነትን እንዲያሰፍኑ በላኮት አምላክ ትዕዛዝ መሰረት ሰራዊቶን አሰልፉ፤ ባህርን ልሻገር ነው ቢሉን እንኳን አንዳችንም ሳንቀር አብረንዎት እንሻገራለን፤ ነገ ጠላቶቻችንን ብንገናኝ የምንጠላ አይደለንም። በእውነቱ በጦርነት ላይ ታጋሾች ነን የጦር ሜዳ ላይ ግን ኀይለኞች ነን። በጦርነቱ ወቅት እኛን አይተው የሚደሰቱበት ያድርግልዎ። በአላህ ፍቃድ አብረንዎ እንድንዘምት ይፍቀዱልን።»በማለት ተናገረ! ረሱለላህ ﷺ በሰዓድ’ም በሚቅዳድም ንግግር እጅግ በጣም ተደሱ። ድል'ም የእነሱ ኾነ💚 ኣህ በድር!... እንግዶችሽ ምነኛ አማሩ። ከሰዎች ሁሉ ምርጥ ሰዎችን፣ ከመላእክቶች ሁሉ ምርጥ መላእኮችን አስተናገድሽ። በአንድ ባንዲራ ስር መልዕክተኛው ከሰይዲና ጂብሪል ጋር ሆነው ጠላትን አንበረከኩ። ሰሐቦችም ለጌታቸውና ለጌታቸው ሐቢብ ﷺ ያላቸውን ውዴታ በግልፅ አሳዩ! ... ምንዳቸውም ከፍ አለ። 🥰 በድር ላይ የተሳተፉ ሙስሊሞች 'አፍደሉል ሙስሊሚን' ሲባሉ በድር ላይ የተሳተፉ መላዒኮችም እንደዛው ምርጥ ተባሉ። 💚 ከዓብ ኢብኑ ማሊክ ረዲየላሁ አንህ የነበረውን ውብ ትዕይንት ባማረ መልኩ እንዲህ ይገልፀዋል: وبيوم بدرٍ حين تمحى وجوههم جبريل تحت لوائنا ومحمدُ 🥰 በዛ የበድር ቀን፤ በዛ ፊታቸው(የቁረይሽ ሀይሎች) የተዋረደበት ቀን!...ጂብሪልና ሙሐመድ ﷺ ባንዲራችን ስር ቆመው የነበሩበት! 🥰✨ ድልን መንሳት አሸናፊና ጥበበኛ በኾነው አላህ ዘንድ እንጂ በሌላ አይደለምና ድልን አጎናፀፋቸው! ውሸት ከእውነት የተለየበት ዘመቻ ሆነ። ብርሃን ጨለማን ገረሰሰ! ኢማን በክህደት ላይ ነገሰ። ጉረኞችን አሳፈረ! ትዕቢተኞችን አዋረደ! እንደ አቡ ጀሃልና ኡቅባ ኢብን ሙዒጥ አይነት ካሐዲዎች ህይወትም አበቃለት! 💚 የነህጁ አህመድ ሸውቂ እንዲህ ይላሉ: ••••💚 محبة الله ألقاها وهيبته على ابن آمنة في كل مصطدم «ጠላቶች እሳቸውን ለመዋጋት በሞከሩ ቁጥር፣ አላህ ፍቅሩን እና ግርማው'ን በአሚና ልጅ ሙሐመድ ﷺ ላይ ያደርጋል።» ••••💚 كأن وجهك تحت النقع بدر دجى يضيء ملتثما أو غير ملتثم «በዛ አቧራ በሞላው ዘመቻ፣ በዛ ጨለማ ምሽት፣ ሰማዩ በደመናዎች ተሸፍኖም ሳይሸፈንም ፊትዎ ﷺ እንደ ሙሉ ጨረቃ ያበራ ነበር።» ••••💚 بدر تطلع في بدر فغرته كغرة النصر تجلو داجي الظلم «ልክ እንደሙሉ ጨረቃ(በድር) ሙሐመድ ﷺ በድር ላይ አፈኩ፣ ገፅታቸውም ጨለማ በኾነው ምሽት ውስጥ ድል'ን እንደሚያበስር አዲስ ጨረቃ ያበራ ነበር።» ይላል ነህጁ ላይ! አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ሙሐመድﷺ 🥰💚 እንደ በድር ያሉ ድሎች ይመላለሱብና! በዱኣችሁ 🤲🏽

  • 28 февр.1 07474из fiqshafiyamh

    ኢላሂ! ወንጀል የሚያስምር፤ አዲስ ሕይወት የሚያስጀምር፤ ጠባይ የሚያሳምር፤ የነፍስያና የሸይጣንን ተንኮል መና የሚያስቀር፤ ከመልካሞችና ከተወዳጆችህ ጋር የሚያስተሳስር፤ ከክፉዎች እና ካንተ ጠላቶች የሚያቃቅር፤ ተውበት ለግሰን! አሚን!

  • 18 февр.1 519112из zumer_media

    🌹 የፆም ንያ🌹 🥀ኒያው የሚደረግበት ጊዜም ፀሀይ ከጠለቀችበት ሰዐት ጀምሮ እስከ ፈጅር ባለው ጊዜ ነው። በልቡ እንዲህ ብሎ ይነያል: 🥀(  نويت_صوم_غد_عن_أداء_فرض_رمضان_هذه_السنة_إيمانا_واحتسابا_لله_تعالى 🥀(ነወይቱ_ሶውመ_غገዲን_ዐን_አዳኢ_ፈርዲ_ረመዷኒ_ሀዚሂ_አስ_ሰነቲ_ኢማነን_ወህቲሳበን_ሊላሂ_ተዓላ) 🥀ትርጉም  ከረመዷን ወር የነገውን እለት ለመፆም ኒያ አድርጊ 🥀እንደ ኢማም አል ሻፊዒይ መዝሀብ ኒያ በእያንዳንዱ ምሽት ማሳደር አለበት  ረስቶት ኒያን ካላሳደረ ያለ ንያ ፆም የለም። 🥀በኢማም ማለክ መዝሀብ ደግሞ የወሩ የመጀሪያ ላይ በአንድ ጊዜ ለሁሉም መነየት ይችላል ነገር ግን በመሀል ከ 30ው ቀን አንድ ቀን ካልፆመ ካቋረጠ ኒያውም ይቋረጣል ከዚያ በሗላ በየቀኑ መነየት ይኖርበታል ። 🥀(نويت صيام ثلاثين يوما عن شهر رمضان هذه السنة) 🥀ትርጉም፦ (የዚህን አመት የረመዷን ወር ሰላሳውን ቀን ለመፃም ኒያ አድርጊያለሁ) https://t.me/zumer_mereja

  • видео или голосовое, без подписи

  • 17 февр.1 25161из medina_tube

    ረመዷን ነገ ይጀምራል። በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የታላቁና ቅዱሱ የረመዳን ወር ጾም ነገ ረቡዕ ይጀምራል። #TikvahEthiopiaFamily @medina_tube

  • Live stream finished (1 minute)

  • Live stream started

🌹አል ፋሩቅ የሙፍቲዬ ትውልድ💚 — tgindex