tgindex
የሀድራው ዙመር

የሀድራው ዙመር

Статистика

እኛም በቻልነው ለሰዎች ሀቅን ለማድረስ ይሄን ቻናል ከፍተናል ምክንያቱም ኡለማዎች እንዲህ ይላሉ ሀቅን የያዙ ሰዎች ዝም ሲሉ ባጢልን የያዙ ሰዎች ሀቅ ላይ ያሉ ይመስላቸዋል። ሼርርርርርርርርርርርርር t.me/tekiyu05

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
16
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 486
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
154
29 постов
Вовлечённость
10,4%
к подписчикам
Постов в день
2,3
всего 29
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
97
1/48двое суток
111
1/72трое суток
119

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 📖سورة الكهف📖 🌹جمعة مباركة🌹 ደስ በሚል አቀራር👌 ቃሪዕ፦ ሸይኽ ሐሰን ኢድሪስ https://t.me/tekiyu05

  • ๏ከቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁሙዓህ ቀን ነው። በጁምአ ሱናዎች እንበርታ! ✅ ገላን መታጠብ ✅ ሽቶ መቀባት ለወንድ ✅ ልብስ መቀየር ✅ ጥፍርን መቁረጥ ✅ በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ ✅ ሶለዋት ማብዛት ✅ ሱረቱል ካህፍን መቅራት ✅ ሲዋክ መጠቀም ✅ ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ ✅ ከጁምዐህ ሶላት በኋላ የሱና ሶላት መስገድ ✅ ዱዓዕ ማድረግ تقبّل اللهُ طاعاتكم جُمعَةٌ طيبةٌ مُبارَكةٌ علَينَا وَعَلَيكُم وَعَلَى أهْلِكُم وَمَنْ تُحِبُّون وَرَزَقَنا اللهُ وإِيّاكُم من خَيْرَاتِ وبَرَكاتِ وأسْرَارِ هَذَا اليْوْمِ المُبَارَك አሏህ አምልኮዋችሁን ይቀበላችሁ። ๏ መልካም ጥሩ የተባረከች ጁሙዐህ ለኛም ለናንተም ለቤተሰቦቻችሁም ለምትወዱትም ይሁን።አሏህ መልካም ነገሮችን በረካዎችን ይወፍቀን። "يا ربي إن ذنوبي في الورى عظمت وليس لي عمل يوم القيامة ينجيني إلا أنت" "ጌታዪ ሆይ ወንጀሌ በፍጡራኖች ዘንዳ በእርግጥም በዝታለች ለኔም ስራ የለኝም የትንሳኤ እለት የሚያድነኝ አንተ እንጂ" ┈•✿•˚•❀•˚•✿•˚•❀•˚•✿•┈         የተባረከች ጁምዓህ ይሁንልን🤲 🌹جمعة مباركة🌹 https://t.me/tekiyu05

  • بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ{٩}فَإِذَا قُضِيَتِ الصَّلَاةُ فَانتَشِرُوا فِي الْأَرْضِ وَابْتَغُوا مِن فَضْلِ اللَّهِ وَاذْكُرُوا اللَّهَ كَثِيرًا لَّعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ{١٠}وَإِذَا رَأَوْا تِجَارَةً أَوْ لَهْوًا انفَضُّوا إِلَيْهَا وَتَرَكُوكَ قَائِمًا ۚ قُلْ مَا عِندَ اللَّهِ خَيْرٌ مِّنَ اللَّهْوِ وَمِنَ التِّجَارَةِ ۚ وَاللَّهُ خَيْرُ الرَّازِقِينَ{١١} سورة الجمعة{٦٢} እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በጁምዓ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አሏህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነዉ፡፡ ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲኾኑ ወደእርሷ ይበተናሉ፡፡ አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፡፡ «አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጭ ነው» በላቸው፡፡ 🌹جمعة مباركة🌹 🌹 ቁርዓን የቀልብና የጀሰድ ፈዉስ ነዉ። 🌹 https://t.me/tekiyu05

  • 🌹جمعة مباركة🌹 بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا{٥٦} سورة الأحزاب{٣٣} አሏህና መላእክቱ በነቢዩ عليه الصلاة والسلام ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ በነብያችን صلى الله عليه وسلم ላይ ሶለዋት ማዉረድን አንዳትረሱ ዉዶቼ❣💕 መልካም ጁምዓ ይሁንልን ዉዶቼ❣💕 جمعة مباركة🌹 https://t.me/tekiyu05

  • بسم الله الرحمن الرحيم وَالْعَصْرِ{١}إِنَّ الْإِنسَنَ لَفِي خُسْرٍ{٢}إِلَّا الَّذِينَ ءَامَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَتَوَاصَوْا بِالْحَقِّ وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ{٣} سورة العصر{١٠٣} صدق الله العاظيم በጊዜያቱ እምላለሁ፡፡ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካምን ስራ የሠሩት፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡ 🌹جمعة مباركة🌹 https://t.me/tekiyu05

  • السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ياجماعة 🌹جمعة مباركة🌹

  • 🔷 ርዕስ "መራቲቡል ዑለማእ :-የዑለማኦች ደረጃ እና ማን ተቀዳሚ እንደሆነ የሚያብራራ  ወሣኝ  ደርስ  🧏‍♀🧏‍♀ በኸሚስ ፕሮግራማችን የተሰጠ ልዩ ደርስ 🔵 አድራሻ "ሀድሙ ጀማዐቲል ወሀቢያ" የኢሞ ላይቭ ግሩፕ ⏰ ሰዓት: ከምሽቱ 3 : 30 🟢 በሸይኽ አንዋር አልከሚስይ /حفظه الله تعالى/ 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄  | https://t.me/tekiyu05

  • አሰላሙ  አለይኩም  ወራህመቱሏሂ  ወበረካቱሁ ውድና የተከበራችሁ የሀቅ ባለቤቶች እንዴት ናችሁልን? ➡️ ማስረጃ የሚያዘው ከቁርአን እና ከሀድስ ከኢጅማእ ነው ። የኡለሞችን ንግግር ከማስረጃዎቻቸው ጋር እንዴት እንገነዘባቸዋለን ? ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተሠጠበት ወሣኝ  ደርስ በኸሚስ ፕሮግራማችን የተሰጠ ልዩ ደርስ 🔵  አድራሻ "ሀድሙ ጀማዐቲል ወሀቢያ" የኢሞ ላይቭ ግሩፕ ⏰ሰዓት :ከምሽቱ 3 : 30 🟢በሸይኽ አንዋር አልከሚሲይ /حفظه الله تعالى / 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄  | https://t.me/tekiyu05

  • አሰላሙ  አለይኩም  ወራህመቱሏሂ 🔷 ቁርኣንን መኽሉቅ የሚሉት ወሀብያ ለመሆናቸው ሰፊ ማብራሪያ 🧏‍♂🧏‍♂🧏‍♂🧏‍♂🧏‍♂ በኸሚስ ፕሮግራማችን የተሰጠ ልዩ ደርስ 🔵  አድራሻ "ሀድሙ ጀማዐቲል ወሀቢያ" የኢሞ ላይቭ ግሩፕ ⏰ሰዓት :ከምሽቱ 3 : 30 🟢በኡስታዝ ሰዒድ ሙሀመድ/حفظه الله / 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄  | https://t.me/tekiyu05

  • #የረሱል(ﷺ) የመጨረሻ ቃል ''ሰዎች ሆይ'' ሶላትን አደራ'' ሶላትን አደራ'' ሶላትን አደራ'' ነቢዩ ሙሐመድ(ﷺ) ኡማ ሆይ ! ይህ የነቢያችን ምክር ነው ! https://t.me/tekiyu05

  • ሀረር አከባቢ የምተገኙ አህባቦች ሸይክ ከይሩዲን የምታቋቸው አናገሩን በጣም አሰፈላጊ ነው @hayder015

  • "እስኪ አንዴ ብቻችንን ሆነን የተመቻቸ ቦታ ላይ ሆነን ይቺን መልእክት እናስተንትናት👇👇👇 " ​ከ100 ዓመት በፊት የት ነበርን? ያኔ የነበሩትስ ሰዎች ዛሬ ላይ  የት ናቸዉ ⁉️" ​እነሱም እኮ እንደኛ ብዙ ሕልምና ዓላማ ያላቸው፣ የሚወዱት ንብረት፣ ውበትና ወዳጆች የነበሯቸው ነበሩ፤ ነገር ግን ሞት ሁሉንም በጣጥሷቸዋል አዉድሟቸዋል። አሁን ምን ላይ እንዳሉ አናውቅም።  ዛሬ አጥንታቸው በጨለማ መቃብር ውስጥ ፈርሶ ታሪክ ሆነዋል ዉበታቸዉም አፈር ሆኖል ! ​ለዲኑ ሲል የተራበው ደሃ፣ በመከራ የኖረው ችግርተኛ፣ እንዲሁም ልቡ በዱንያ ፍቅር የታወረዉ ሀብታም… ሁሉም በአንድ ላይ ተጠራርገው ጠፍተዉ ሁሉም ከሠራዉ ስራ ጋር ተገናኝቷል !!! ​ልክ እንደነሱ እኛም ተራችን ደርሶ አንድ ቀን ታሪክ ሆነን እንቀራለን፤ የእኛ የምንለዉን ነገር ሁሉ ትተንዉ አንሄዳለን፤ አብሮን የሚሄደው ሥራችን ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ምን እንደሚጠብቀን አናውቅም—ዘላለማዊ ስቃይ ወይስ ዘላለማዊ ፀጋ? ​👉 ኧረ ለጠፊዋ ዱንያ አንድከም! አንጣላ ፣ ከሰዉነት አንዉጣ ፣ አንኮራረፍ !  እሪዝቃችን ፣ አንዲሁም ከማን ጋር እንደምንኖር  ፣ ማን የትዳር አጋራችን እንደሚሆን ፣ ሁሉም ከመፈጠራችን በፊት ተወስኗል -ከሞት እንደምንሸሸዉ ከሪዝቃችን ብንሸሽ እንኳ የተወሰነልንን ነገር አናጣዉም ልክ ሞትን በሽሽት አንደማናመልጠዉ ሁሉ ከኛ የሚጠበቀዉ ሰበቦችን በሀላል መልኩ ማድረስ ብቻነዉ እንጂ ለዚች ለምትወገድ ዱንያ ብለን ሠበቦችን በሀራም ላይ አናድርግ -የተፃፈልንን እንጂ ሌላ ስለማናገኝ ነገር ግን አሏህ ፊት ስለምንጠየቅበት ትተንዉም አንሄዳለን እና  ፣ ችግራችንም፣ በሽታችንም፣ ስቃያችንም በሞት ያበቃል። የጀሃነም እሳት ግን በምን ይወገዳል?👈 ​🍑 ከወዲሁ እውነተኛውን የዘላለም ሀገራችንን (አኼራን) በመልካም ሥራ፣ ወንጀልን በመራቅና ላለፈው ጥፋታችን እውነተኛ ተውበት በማድረግ እንዘጋጅ ! ለተፈጠርንበት ታላቅ ዓላማ ትኩረት እንስጥ እንትጋ ! 🍑 ​በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ፣ ስለ አኼራ የሚያነሳ፣ ስለተፈጠረበት ዓላማ የሚያስብ፣ ዲኑን የሚማርና የአላህን ክልከላዎች የሚርቅ ሰው እንደ ጅል፣ እንደ ሞኝና ሥራ ፈት ሚስኪን ተደርጎ የሚቆጠርበት ዘመን ላይ መድረሳችን ነው። ነገር ግን ለገባዉ አካል ይህ ነዉ ከሁሉም የተሻለ ሰዉ ብሎ ማለት  ይህ ነዉ  ምክንያቱም ጠፊዋን ትቶ ለዘዉታሪዋ ለእዉነተኛይቱ ሀገሩ የለፋ ነዉና ዉዶቼ ሚስኪን ፣ ሞኝ ሰዉ ይህ ሳይሆን የዉመል ቂያማ መልካም ስራዎቹን ለበደላቸዉ ላማቸዉ ሰወች አስረክቦ ወደ እሳት የሚወረወር ፣ በጠፊዋ ሀገር ተታሎ የዘላለማዊ ህይወቱን ያበላሸ ፣ ለጠፊዋ ለዱንያ ለፍቶ አኸራዉን የዘነጋ  ፣  ደጋጎች ወደ ጀነት ሲነዱ እሱ ወደ እሳት የሚነዳ ነዉ!!!! አሏህ ከዚ ይጠብቀን🤲 قال تعالى : وَسِيقَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِلَى جَهَنَّمَ زُمَرًا ...الآية وقال : وَسِيقَ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ إِلَى الْجَنَّةِ زُمَرًا...الآية   "إِنَّ هَذَا لَهُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ 🔴لِمِثْلِ هَذَا فَلْيَعْمَلِ الْعَامِلُونَ" [سورة الصافات : 61-60] ​اللَّهُمَّ نَجِّنَا مَعَ النَّاجِينَ، وَأَدْخِلْنَا بِرَحْمَتِكَ فِي زُمْرَةِ الصَّالِحِينَ، اللَّهُمَّ إِنَّا مُقَصِّرُونَ فَاغْفِرْ لَنَا ولا تفضحنا يوم لقائك.🤲 እህቴ/ወንድሜ… ይህች ምክር ምናልባት የአንድን ሰው የተዘጋ ልብ የምትከፍት ቁልፍ ልትሆን ትችላለች! እናም ለወዳጅ ዘመዶቻችን ሼር እናድርጋት፣ እናሰራጫት። በስልካችን ላይ ላሉ ወዳጆቻችን እንላክላቸው፤  ቻናል ያለንም በቻናላችን እናሠራጫት ፣በእሷ ምክንያት አንድ ሰው እንኳ የዱንያ እውነታ ግልጽ ሆኖለት፣ የዱንያን ፍቅር ከልቡ አውጥቶ በዲኑ ላይ ቢጠነክር፣ ቆም ብሎ አስቦ ከወንጀሉ ቢቶብትና የወደፊት ሕይወቱን ቢያስተካክል፣ አላህ ዘንድ ትልቅ አጅርና ምንዳ አለን ! ​ይህን መልእክት በማሰራጨት የተጋራችሁ በሙሉ፡ ​🤲 አላህ ወንጀላችሁን ይማርላችሁ ! 🤲 ነውራችሁን ይሸፍንላችሁ ! 🤲 ደረጃችሁን  በጀነት ከፍ ያድርግላችሁ ! 🤲 መከራችሁንና ችግራችሁን ይገላግላችሁ ! 🤲 ዱዓችሁን ተቀባይ ያድርግላችሁ ! ​آمين اللهم آمين. ​اللَّهُمَّ إِنَّا نَسْأَلُكَ بِأَسْمَائِكَ الْحُسْنَى، وَصِفَاتِكَ الْعُلْيَا، وَبِاسْمِكَ الأَعْظَمِ الَّذِي إِذَا دُعِيتَ بِهِ أَجَبْتَ، وَإِذَا سُئِلْتَ بِهِ أَعْطَيْتَ؛ أَنْ تَسْتَجِيبَ دُعَاءَنَا، وَأَنْ تَشْرَحَ صُدُورَنَا لِذِكْرِكَ وَطَاعَتِكَ، وَأَنْ تُثَبِّتَنَا عَلَى الْحَقِّ حَتَّى نَلْقَاكَ"🤲 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄  | https://t.me/tekiyu05

  • ወንጀል ሰርተን ሰዎች ካላዩን ከኛ ብልሀት እና መደበቅ ሳይሆን አላህ ወደ እርሱ መመለሻ (ተውበት) እድል እየሰጠን ነው : : https://t.me/tekiyu05

  • "ኢንሻ አላህ ይህን ወንጀል ነገ እተወዋለሁ..." ይቺ ቃል የብዙዎቻችን ማደንዘዣ ሆናለች። መጀመሪያ "ስህተት" ብቻ ነበር፤ ቀጥሎ "ልምድ" ሆነ፤ ዛሬ ነገ ስንል ግን ተዋህዶን "ሱስ" ሆኗል። ዉዶቼ ! የሞት መልአክ "ነገ እመጣለሁ" ብሎ ቀጠሮ አይሰጥም። ዛሬ ነገ እያልን የቀጠሮ ሰንሰለት ስንሰራ፥ ልባችን በወንጀል እንዳይዝግና የመመለስን በር እንዳንረሳው እፈራለሁ። እንመለስ ! አላህ አሁንም በራህመቱ ይጠብቀናል። መመለሻችን "ነገ" ሳይሆን "አሁን" ይሁን። አላህ ካለንበት መጥፎ ልምድ ተላቀን፣ ወደርሱ ከሚመለሱት ባሮቹ ያድርገን🤲 https://t.me/tekiyu05

  • 🧎‍♂ኢላሂ…በወንጀል የቆሸሸ ማንነቴን፣ በኃጢአት የዛለ ጉልበቴን ይዤ ከደጅህ ወድቄያለሁ። ወደ አንተ ካልሸሸሁ ወደ ማን እሄዳለሁ? ከአንተ ካልተጠጋሁ ማን ያስጠጋኛል? 🧎‍♂ኢላሂ... ስራዬን ስመለከት ተስፋ እቆርጣለሁ፤ እዝነትህን ሳስብ ግን ልቤ ይረጋጋል። እኔማ ባዶ ነኝ... ለጀነትህ የሚያበቃ ስራ የለኝም፤ ነገር ግን ጌታዬ ሆይ... እሳትህን የምቋቋምበት አቅምም የለኝም። 🧎‍♂ኢላሂ... በዛች ማንም ለማንም በማይሆንበት ቀን፣ እናት ልጇን በሚሸሽበት ቀን፣ አንተ አትሽሸኝ። ወንጀሌ ከሰማይ ቢገዘፍም፣ የአንተ ምህረት ግን ከዛም በላይ ሰፊ ነው። ካንተ ውጭ መሸሸጊያ የለኝምና በምህረትህ እቅፍ ስር አኑረኝ🤲 ለጀነትህ የሚያበቃ ስራ ባይኖረኝኳ እንኳ በራህመትህ ከእሳትህ ጠብቀኝ፤ ጀነትንም ወፍቀኝ🤲 እኔ ደካማ ባሪያህ ነኝና እዘንልኝ🤲🥺 https://t.me/tekiyu05

  • بسم الله الرحمن الرحيم الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على رسول الله ﷺ መዉሊድን ማክበር ሸሪዐዊ ድጋፍ እንዳለው የሚገልጹ የዑለማእ ንግግሮች ✅✅✅✅✅✅✅ 1⃣  ሸይኹል ኢስላም’ና " አሚሩል ሙእሚኒን ፊል ሐዲስ " የሚል ማዕረግ ያላቸው ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል–ዐስቀላኒይ [ረሕመቱሏህ ዐለይሂ] እንዲህ ይላሉ ፦ " መውሊድ (አሁን ባለው አፈጻጸሙ)  መሠረቱ በ, 3 ክ/ዘመናት ውስጥ በነበሩ ሰለፎች ያልተገኘ አዲስ ጅማሮ ነው ፣ ሆኖም ግን መልካምና ተቃራኒውን በውስጡ ይዟል ፣ ከተግባሮቿ ውስጥ መልካሙን ብቻ በመስራት ተቃራኒውን የተወ ስራው " ቢድዐህ ሐሰናህ " ይሆንለታል ፤ ካልሆነ ግን አይሆንም ። በእርግጥ ከተረጋገጡ የቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘገባዎች ውስጥ (ለሑክሙ ) ማጠናከሪያ የሚሆን ሐዲስ መጥቀስ እንዳለብኝ ይታየኛል ፦ ነብዩ (ﷺ) ወደ መዲና በደረሱ ጊዜ አይሁዶች የዓሹራን ቀን ሲፆሙ አገኟቸው ፤ ምክኒያቱን ሲጠይቁ አሏህ ፊርዐውንን አስምጦ ሙሳን ያዳነበት ቀን በመሆኑ አሏህን ለማመስገን ቀኑን በጾም እናሳልፈዋለን አሏቸው " ይህ ሐዲሥ አሏህ ፀጋን በመለገስም ሆነ ቅጣትን በማስቀረት ውለታ የዋለበትን ቀን ለይቶ ማመስገን እንደሚቻል’ና ይህንንም በያ’መቱ ቀኗን ጠብቆ መደጋገም ይቻላል የሚል ፋኢዳ ይሰጣል ። ለአሏህ የሚቀርብ ምስጋና እንደ ሶላት ፣ ጾም ፣ ሶደቃህ ፣ ቁርአንን በመቅራት’ና በመሳሳሉት ዒባዳዎች ሊገኝ ይችላል ። ደሞስ ይህ የዕዝነት ነቢይ (ﷺ) መገለፁን የሚመጥን ፀጋ የትኛው ፀጋ ነው ?! ይህ በመሆኑም በእዚያች ቀን ቁርአን በመቅራት ፣ ምግብ በማብላት ፣ በልብ ውስጥ የሚገኝ የመልካም ስራ ፍላጎትን የሚቀሰቅሱ’ የነቢይ ውዳሴዎችን ማቀንቀንን በመሳሰሉ የምስጋና መገለጨዎች ብቻ ተገድበን ልናሳልፈው ይገባል ። እነዚህን ተከትለው ሊመጡ የሚችሉ ነገሮችን በተመለከተም እንዲህ ሊባል ይገባል ፦ > በዚያች ቀን ደስታን የሚገልፁ (ሙባሕ) ሸሪዐዊ ፍቃድ ያላቸው ነገሮች ቢደረጉ ችግር አይኖረውም ፣ > በሸሪዐ ‘ሐራም ’ ወይም ‘መክሩህ’ ወይ ደሞ ከመስራቱ መተዉ የተሻለ አማራጭ የሆነ ነገር ከተፈፀመ ሊከለከል ይገባል።   (ፈታዋ አል–ኩብራ 1/196) 2⃣  ኢማም ሱዩጢይ (ረሕመቱሏህ ዐለይሂ)  እንዲህ ይላሉ ፦ እሱ (መውሊድ አሁን ባለው አፈጻጸሙ)  ‘ቢድዐህ ሐሰናህ’ ቢሆንም ነብዩን (ﷺ) ማላቅ’ና በውልደታቸው  ሀሴት ማድረግ ያለበት ስለሆነ ፈጻሚው ምንዳ ያገኝበታል ። " (አል–ሓዊ ሊል ፈታዋ 1/292) ኢማሙ እንዲህም ብለዋል ፦ " በነብዩ (ﷺ) ውልደት መደሰታችንን ይፋ ማድረግ ፣ መሰባሰብ ፣ ምግብ ማብላት’ና የመሳሰሉት ወደ አሏህ መቃረቢያ የሆኑ ነገራቶችን መፈፀም  (በሸሪዐ) ይወደድልናል "  (አል ሓዊ ሊ _አል–ፈታዋ 1/196) በተጨማሪም ኢማም ሱዩጢይ እንዲህ ይላሉ ፦ " ማንኛውም ቤት ፣ ቦታም ሆነ መስጂድ የነብዩ (ﷺ) መውሊድ የሚቀራበት ከሆነ የዛን ቦታ ባለቤቶች  መላኢኮች ያካብቧቸዋል ፣ የአሏህ እዝነት’ና ውዴታውም ያዳርሳቸዋል " (አል ወሳኢል ፊሸርህ አል–መሳኢል ሊ_አስ–ሱዩጢይ) 3⃣ ኢብኑ ሐጀር አል ሀይተሚይ (ረሕመቱሏህ ዐለይሂ) እንዲህ ይላሉ ፦ ቢድዐህ ሐሰናህ " የሆነን ነገር መስራት የተፈቀደ በመሆኑ ላይ የዑለማኦች ስምምነት አለበት መውሊድን መዘከር’ና ሰዎችን መሰብሰብም በዚሁ አግባብ የሚታይ ነው ። 4⃣ የታላቁ ሙረቢ’ና ሙሐዲሥ ኢማም አን–ነወዊ ሸይኽ የሆኑት ኢማም አቡ ሻምማህ እንዲህ ይላሉ ፦ " በዘመናችን  ከተጀመሩ እጅግ ያማሩ  ጅማሮዎች ውስጥ በያ’መቱ ነብዩ (ﷺ) በተወለዱበት ቀን ሶደቃን በመስጠት ፣ መልካም ስራዎችን በመስራት’ና የውልደታቸውን ደስታ ይፋ በማድረግ የሚሰራው ስራ አንዱ ነው ። በእነዚህ ስራዎች ውስጥ ለድሆች መልካም መዋል ፣ በመውሊድ አድራጊው ልብ ውስጥ ያለውን የነብዩ (ﷺ) ፍቅር’ና ልቅናን መግለፅ እንዲሁም አሏህ የዓለማት እዝነትን በማስገኘት ለዋለው ውለታ ምስጋናን ማቅረብ ያለበት በመሆኑ ነው ።" 5⃣ ኢማም ሰኻዊይ እንዲህ ይላሉ ፦ " በ’ርግጥ በ,3 ክ/መናት ውስጥ በነበሩ ሰለፎች አልተተገበረም ፤ ከዛ በኋላ የመጣ ነው ። ከዚያ ግን በሁሉም አገራት’ና አከባቢ የሚገኙ ሙስሊሞች መውሊድ ማዘጋጀትን ፣ ለሊቱን በተለያዩ የምጽዋት አይነቶች ማሳለፍን ፣ የውልደታቸውን ሁነት በትኩረት ማንበብን ትተው አያውቁም ። (አስ–ሲራህ  አል–ሐለቢያህ ሊዐሊይ ኢብኑ ቡርሀኑዲን  አል–ሐለቢ 1/83_84) 6⃣ ኢብኑ አል–ጀውዚይ እንዲህ ይላሉ  ፦ " መውሊድን የሚያዘጋጅ ለየት የሚያደርገው በዚያ ዓመት ላይ ሰላም ይሆናል ፣ የምኞቱን ሁሉ በሚያገኝበት ቅርብ ብስራት ይበሰራል "   (አስ–ሲራህ አል–ሐለቢያህ 1/83/84 " ) 7⃣ ኢብኑል ሓጅ (ረሕመቱሏህ ዐለይሂ) እንዲህ ይላሉ ፦ " በረቢዕ አል–አወል 12,ኛው ቀን አሏህ ለታላቅ ፀጋ የተገባን ስላደረገን ምስጋናን ለመግለፅ ዒባዳዎችን’ና መልካም ተግባሮችን በማብዛት ልናሳልፈው ይገባል ፤ ከፀጋዎች ሁሉ በላጩ የሙስጠፋ (ﷺ) ውልደት ነውና ። " (አል–መድኸል 1/361) 8⃣ ኢብኑል ሓጅ በሌላ ቦታ እንዲህ ይላሉ፦ " በውልደታቸው ለሊት መደሰት’ና መውሊዳቸውን መቅራት ነብዩን (ﷺ) ከማላቅ ይቆጠራል ። " 9⃣ ሓፊዙል ዒራቂይ (ረሕመቱሏህ ዐለይሂ) እንዲህ ይላሉ ፦ "በመሠረቱ ድግሶችን ማዘጋጀት’ና ምግብ ማብላት (በሸሪዐችን) የተወደደ ተግባር ነው ፤ በዚህ የነብዩ (ﷺ) ኑር በፈነጠቀበት ክቡር ወር ውስጥ ሲተገበር ደሞ ይበልጥ የተወደደ እንደሚያደርገው አያጠያይቅም!  አዲስ ጅምሮ መሆኑ ብቻ የግድ የተጠላ ተግባር ሊያደርገው አይችልም ! ስንትና ስንት ‘ሙስተሐብ’ የሆኑ እንደውም ‘ዋጂብ’ የሆኑ አዳዲስ ስራዎች አሉ ። "  ( ሽርሕ አል–መዋሁብ አድ–ዲኒይያህ ሊ_አዝ–ዘርቃኒይ 1⃣0⃣ ኢብኑ ዓቢዲን (ረሕመቱሏህ ዐለይሂ) እንዲህ ይላሉ ፦ " ዕወቅ ! ነብዩ (ﷺ) በተወለዱበት ወር መውሊድ ማዘጋጀት ከ ‘ቢድዐህ መሕሙዳህ ’  ይቆጠራል  (ሸርሕ ዓላ መውሊድ ኢብኑ ሐጀር)  ኢብኑ ዓቢዲን እንዲህም ብለዋል ፦  "የታላላቅ ተዐምራት ባለቤት የሆኑትን ነብይ (ﷺ) ታሪክ ለመስማት መሰባሰብ በውስጡ ብዙ ሶለዋትና ተዐምራቶችን በመያዙ ከታላላቅ አምልኮዎች ውስጥ ይቆጠራል ።" 1⃣1⃣ ሸይኽ ሑስኒን ሙሐመድ መኽሉፍ (የአዝሀር ሸይኽ) እንዲህ ይላሉ ፦ " እኚህ የመውሊድ ምሽት’ና ሙሐመዳዊው ብርሀን የፈነጠቀባቸው ክቡር ለሊቶች አሏህ አይነታውን ነቢ ወደ ፍጥረተ–ዓለሙ በማዝለቅ ለዚህች ዑማ ታላቅ ውለታ የዋለባቸው ለሊቶች በመሆናቸው በዚክር’ና በምስጋና እንዲሁም በስነ–ስርአት ፣ በስክነት ፣ መጤ’ና የተጠሉ ከሆኑ ነገራቶች በመራቅ ፣ በፍቅር የመታደልን ምስጋና ይፋ በሚያደረጉ ነገራቶች ፣ የምስኪኖችን ችግር ሊያቃልሉ በሚችሉ ነገሮች ፣ ዝምድናን በመቀጠል ታስበው ሊውሉ ይገባል ። በ’ርግጥ መውሊድን በዚህ መልኩ አስቦ መዋሉ በነብዩም ሆነ በሰለፎች ዘመን ያልተለመደ ቢሆንም በሸሪዐ ምንም ችግር የሌለው ‘ሱናህ ሐሰናህ ’ ነው ። "  (ፈታዋህ ሸርዒያህ 1/131) 1⃣2⃣ ሸይኹል ኢስላም ሙበሺር አጥ–ጢራዚይ (ረሕመቱሏህ ዐለይሂ) እንዲህ ይላሉ ፦ "አሁን ባለንበት ጊዜ የተጀመሩ የአዳዲስ በዓላትን ጎጂ (ተፅእኖ) ለመከላከል ሲባል መውሊድ ሸሪፍን ማክበር ዋነኛ ግዴታችን ሆኗል ። https://t.me/tekiyu05

  • https://vt.tiktok.com/ZS4p6TEw1/

  • 📖سورة الكهف📖 🌹جمعة مباركة🌹 ደስ በሚል አቀራር👌 ቃሪዕ፦ ሸይኽ ሐሰን ኢድሪስ https://t.me/tekiyu05

  • ๏ከቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁሙዓህ ቀን ነው። በጁምአ ሱናዎች እንበርታ! ✅ ገላን መታጠብ ✅ ሽቶ መቀባት ለወንድ ✅ ልብስ መቀየር ✅ ጥፍርን መቁረጥ ✅ በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ ✅ ሶለዋት ማብዛት ✅ ሱረቱል ካህፍን መቅራት ✅ ሲዋክ መጠቀም ✅ ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ ✅ ከጁምዐህ ሶላት በኋላ የሱና ሶላት መስገድ ✅ ዱዓዕ ማድረግ تقبّل اللهُ طاعاتكم جُمعَةٌ طيبةٌ مُبارَكةٌ علَينَا وَعَلَيكُم وَعَلَى أهْلِكُم وَمَنْ تُحِبُّون وَرَزَقَنا اللهُ وإِيّاكُم من خَيْرَاتِ وبَرَكاتِ وأسْرَارِ هَذَا اليْوْمِ المُبَارَك አሏህ አምልኮዋችሁን ይቀበላችሁ። ๏ መልካም ጥሩ የተባረከች ጁሙዐህ ለኛም ለናንተም ለቤተሰቦቻችሁም ለምትወዱትም ይሁን።አሏህ መልካም ነገሮችን በረካዎችን ይወፍቀን። "يا ربي إن ذنوبي في الورى عظمت وليس لي عمل يوم القيامة ينجيني إلا أنت" "ጌታዪ ሆይ ወንጀሌ በፍጡራኖች ዘንዳ በእርግጥም በዝታለች ለኔም ስራ የለኝም የትንሳኤ እለት የሚያድነኝ አንተ እንጂ" ┈•✿•˚•❀•˚•✿•˚•❀•˚•✿•┈         የተባረከች ጁምዓህ ይሁንልን🤲 🌹جمعة مباركة🌹 https://t.me/tekiyu05