🍁 ኑራ✨ሪያ🌴የፍቅሮት🌿ምርኮኛ 💞
Статистика#እንኳን_በደህና_ወደ_ኑራ_ሪያ_መጡ #Welcome_to_Nura_Riya_official_Channel 🌴ለዲኑ ሰበቡ የሆኑት ቅመሙ💚 🌴 ነብዬ ናቸው ያለሙ ሹሙ💚 በ ዩቲዩብ👇 Http://www.youtube.com/channel/UCu2h5yFgosPZfsuNkYEE3Mg ምክሮች አስተያየቶች ካሏቹ Channel bot 👉 @riyad_nubot Cross @ketbere Cross @Riyuback
- Последний пост
- 9 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አህመድ: ያሲን: ጧሃ 💚💚 በስሙ ሚገኘው ክብረቱ ማዕረጉ፤ ትንሽ ያሉት ሁላ ባንቱ ነው ማደጉ። የቀን መንገዳችን ሲመሽ ብርሓናችን በማዕሸር ሜዳ ላይ ጠበቃ ዋሳችን። ይላል ዛሒዳችን... ባወደስነው ቁጥር ማወደስ አነሰን የሐቢበላህ ﷺ ፍቅር ያንገበገበው በደዊን ደግሞ ቀብራቸው ፊት ቁሞ ይህንን ልብ የሚሰቅዝ ግጥም ይገጥማል፤ ይህ በአል ኡትቢ የተዘገበው የበደዊኑ ግጥም የሐቢበላህ መስጂድ ውስጥ ተከትቦ እናገኘዋለን يَا خَيْرَ مَنْ دُفِنَتْ فِي الْقَاعِ أَعْظُمُهُ فَطَابَ مِنْ طِيبِهِنَّ الْقَاعُ وَالأَكَمُ የአላህ ሰላትና ሰላም በውዱ ነብይ ﷺ፣ ከነፍሴ በላይ በምወዳቸው መልዕክተኛ ላይ ይውረድ 💚 ረቢእ season is coming 🥰🥰
https://t.me/Noor_Musela?livestream
#ሸዕባን = ሰላት ዐለን’ነቢይ ___ የሸዕባን ወር በሰዪዳችን ﷺ ላይ አላህና መላአክቶቹ ሰላትና ሰላም ዘውትር እንደሚያወርዱ ያሳወቀበትና፣እኛም እንድናወርድ ያዘዘበት የቁርኣን አንቀፅ የወረደበት ወር ነው !!! _ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ [ ሱረቱ አል- አሕዛብ - 56 ] ____ اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين في كل لمحة ونفس عدد ما وسعه علم الله. 🌴🌴🌴🌴
ፏ በሉበት አሏህ አሏህህህህህ ✨✨✨ በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ ከፍ ያለ መጠን ያለው የጧሃ ፍቅር ይኑር እርሳቸው ለነፍስ እውነተኛው መድኃኒትና ተቀባይነት ያለውም ዱዓእ ናቸው የጧሃ ፍቅር ይጣፍጣል ያ የነቢዩ ክብር ምንኛ ያምራል! እርሳቸው ለፍጡራን ሁሉ የተከማቸ ሀብት ናቸው ለበጎ ነገሮች ሁሉ ደጃፍ ናቸው እርሳቸው ሰላምና መረጋጋት ምግብና መጠጥም ናቸው እርሳቸው ዕንቁና ውድ ሀብት የነገሮች ሁሉ አስኳልና ጭማቂ ናቸው የጧሃ ፍቅር የሌለባት ምድር ደረቅና ባዶ ናት የጧሃ ፍቅር የሌለባቸው ልቦችም የወደሙና ባድማ ናቸው ስለዚህ በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ ከፍ ያለ መጠን ያለው የጧሃ ፍቅር ይኑር http://t.me/sufiyahlesuna
видео или голосовое, без подписи
ጥሩ ስራ የሚሰራ ሰው ሲያዩ ካንተው ጋር ነኝ ሲሉት ጥሩ ነው... በማኢዳ መጥተው ሲቀመጡ ጥሩ ነው... ሙእሚን የሆነ እንደሆነ የጥሩ ነገር ማኢዳ አይቶ ትቶ አይሄድም... መ.ጥ.ፎ ስራ የሚሰራ ሰው ሲያይ ሊያስተወው እንጂ ትቶ አይሄድም:: {ሠይዲ አባ ራሙዝ(ቀ.ሢ)} አብሬት መሄድ ከጥሩም ጥሩ ስራ ነው:: አብሬት የጀነት ማኢዳ ነው:: በዚህ ማኢዳ መገኘት እድለኝነትን ነው:: መውሊደ_ነቢﷺ የፊታችን እሁድ 💚🔥አብሬድ
የዛሬዋ ለይል- ለይለቱ ረጋኢብ __✍️ Aymeni Zulfiqar የረጀብን የመጀመሪያ ኸሚስ እና ጁምዐ አህሉሏሆች በስስት ይጠባበቋቸዋል። የሠይዳችን ኑር ከሰይዲና አብዱሏህ አል መይሙን ግንባር ወደ ሰይደቲ አሚናህ አል መእሙናህ ማህጸን (የአሏህ ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈን) የተሸጋገረበት ሌሊት......,ሳዳቶቹ ይህንን ማብሰራቸው ብቻ ለዚህ ለይል ታላቅት እና የመቅቡሊያ ወቅትነት በቂ ነው። መላኢካዎች ካዕባን እሚያጨናንቁበት እና ለነቢ ኡመት ምሕረትን የሚለምኑበት - አሏህ የአማኞችን ቀልብ ሲፈትሽ ወንጀል እየሰሩ ከሆነ የሚምርበት- ኢባዳ ላይ ከሆኑ ተሓድራው እሚያከርምበት- ሙጃሂዱንም አርሂብ እሚልበት የ4ቱ ክቡር ወራቶች ታጅ! ረጀቢዩን የሚባሉ ኢላሂይ ዋሪዳታቸው ከ1ኛው ለይል እስከ ረጀብ ግማሽ አካላቸውን እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርቃቸው አውሊያኦች አሉ- ሰይዲ ዩሱፉ ነብሃን ቀደሰሏሁ ሲረሁ ከሸይኹል አክበር ሱልጧኑል አውሊያእ የዐሪፎቹ ሻኛ ኢብኑል ዐረቢይ ቁዲሰ ሩሁሁል አዚይዝ ነቅል አድርገው ጃሚኡል ከራማት ላይ አስፍረውታል። የኚህ የረጀብ ዉጥቦች መደድ ከ15ተኛው እስከ ወሩ መጨረሻ ለአብናኡል አዘሎች ይከፋፈላል........አሏህ በኢስቲዕዳድና ሂማችን ሳይሆን በራህመቱ ይወፍቀን እኚህ አውሊያኦች የሚያደርጓትን ኢስቲግፋር እናብዛ! የ ያ ሃዩ ያ ቀዩምን ትጥቅ እንታጠቅ - ነብየዋን ያ ሃፊይ(በሻሻው ተቀባይ) በሚለው ስም እንጥራቸው - ከቅዱስ ቁርዐን ሱረቱል ሙናፊቁንን እናብዛ!...... (ለችኩል አጻጻፌ አውፍ በሉኝ ታክሲ ውስጥ ተጣብቄ ነው ያለሁት።) የረጀቢዮቹን ዱዐ ጀባ! اَعُوْذُ بِاللهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيْمِ بِسْمِ اللهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيْم اَلَّلهُمَ اِنِّيْ أَسْتَغْفِرُكَ مِنْ كُلِّ مَا تُبْتُ عَنْهُ اِلَيْكَ ثُمَّ عُدْتُ فِيْهِ، وَأَسْتَغْفِرُكَ مِنْ كُلِّ مَا أَرَدْتُ بِهْ وَجْهَكَ فَخَالَطَنِيْ فِيْهِ مَا لَيْسَ فِيهْ رِضَائُكَ. وَأَسْتَغْفِرُكَ لِلنِّعَمِ الَّتِي تَقَوَّيْتُ بِهَا عَلَى مَعْصِيَّتِكَ، وَأَسْتَغْفِرُكَ مِنَ الذُّنُوْبِ اَلَّتِيْ لَا يَعْلَمُهَا غَيْرُكَ وَلَا يَطَّلِعُ عَلَيْهَا أَحَدٌ سِوَاكَ، وَلَا تَسَعُهَا اِلَا رَحْمَتِكَ، وَلَا تُنْجِيْ مِنْهَا اِلَا مَغْفِرَتُكَ وَحِلْمُكَ. لَا اِلَهَ اِلَا أَنْتَ سُبْحَانَكَ، اِنِيْ كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينْ. اَلَّلهُمَ اِنِّيْ أَسْتَغْفِرُكَ مِنْ كُلِّ ظُلْمٍ ظَلَمْتُ بِهِ عِبَادِكَ، فَأَيَّمَا عَبْدٍ مِنْ عِبَادِكَ أَوْ أَمَةٍ مِنْ إِمَائِكَ، ظَلَمْتُ فِيْ بَدَنِهِ أَوْ عِرْضِهِ أَوْ مَالِهِ، فَأعْطِهِ مِنْ خَزَائِنِكَ الَّتِيْ لَا تَنْقُصْ. وَأَسْأَلُكَ اَنْ تُكْرِمَنِيْ بِرَحْمَتِكَ الَّتِيْ وَسِعَتْ كُلَّ شَيِءٍ. وَلَا تُهِيْنَنِيْ بِعَذَابِكَ وَتُعْطِيَّنِيْ مَا أَسْأَلُكَ فَاِنِيْ حَقِيْقٌ بِرَحْمَتِكَ يَا أَرْحَمَ الرَّاحِمِينْ. وَصَلَّى اللهُ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ و عَلَى َآلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينْ. وَلَا حَوْلَه وَلَا قُوَّةَ إِلَا بِاللهِ الْعَلِيِ الْعَظِيْم. ሠው እምንሆንበት ሌሊት ያድርግልን!አሚንን! ሰላም ይድረሶት ሆዴ 👳🏻♂️Anuman 🥁
ዳቦ እና ቡና ሲሆን ሽርክ ሆኖ ኬክ ሲሆን ሱና ነው የምትሉን Allah is watching. ከክርስቲያን ሉካንዳ መግዛት ሀራም ሆኖ ሸራተን ሀላል የሚሆንላችሁ Allah is watching በአማርኛው ወለድ ሲባል ሀራም ሆኖ በእንግሊዝኛው ኮሚሽን ሲባል ሀላል የሚመስላችሁ Allah is watching በዓረብኛ ሊቃእ ሲሆን ቢድዓ ሆኖ በእንግሊዝኛው ኮንፈረንስ ሲባል ሀላል የምታደርጉ Allah is watching ዳዕዋ ለ10 ቀናት ቢድዓ ሆኖ ዑምራ ለ10 ቀን ሱና የምታደርጉ Allah is watching የሌላ ብሔር ዘፈን ሀራም ሆኖ የራስ ብሔር ላይ የምትጨፍሩ Allah is watching ሁል ጊዜ Allah is watching.
በመንገዱ ጨለማ ውስጥ.... የሚታዩ የነበሩ ገፅታዎች ሲሰተሩ ፣ መንገዱ ሲጠፋ፣ ንፋሱም በበረታ ጊዜ አላህ ለተሳሳቱት መሪ፣ ለተበደሉት ብርሃን፣ ለወደቁትም ብቸኛ ረጅ ሆኖ ይቀራል...እውነተኞች የምእመናንን ትዕግስት እና የእውነትን ተስፋ በልቦቻቸው ውስጥ ተሸክመው በአማኞች ፈለግ ይሄዳሉ። ከማጣት በኋላ መሰጠት፣ ከጭንቅ በኋላ እፎይታ ፣ ከድካምም በኋላ ሌላ ነገር እንደሚመጣ እርግጠኞች ናቸው... ወደ አላህ የሚሄድ ሰው የዱንያ በረሃዎች ከአቅጣጫው አያስቱትም; የመንገዱም ርዝማኔ አቅም አያሳጣውም። يَا قَوْمِ إِنَّمَا هَٰذِهِ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا مَتَاعٌ وَإِنَّ الْآخِرَةَ هِيَ دَارُ الْقَرَارِ «ወገኖቼ ሆይ! ይህቺ ቅርቢቱ ሕይወት (ጥቂት) መጣቀሚያ ብቻ ናት፡፡ መጨረሻይቱም ዓለም እርሷ መርጊያ አገር ናት፡፡»
ኢማሙ ሺሊላ😍 ፏያ ያለ ምሽት👏👏😍 ሰሉ አለ ነቢ #صلوا_عليه_وسلموا_تسليماﷺ አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይሂ 💚fuad Alburda 💚sualih muhamned @limugenet 🍁 @limugenet 🍁
ሺሊላ❤ 💚ሺሊላ ❤️ሺሊላ ሺሊላ🥰 አለችው ስራዬ ታይ ገና ሙሀመድ 😊 አለችው ስራዬ ታይ ገና ሙሀመድ 😊 «اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ»🍃 #صلوا_عليه_وسلموا_تسليماﷺ @limugenet 🍁 @limugenet 🍁
видео или голосовое, без подписи
‹ከተጠቀሱት ነብያት ጋር ንክኪ ያለዉ፣ከጀነት የወረደዉ፣የጀነት ሽታ እንዳለዉ የተዘገበለት ይህ ቀሚስ የያዕቆብን የዓይን ብርሀን በበረከቱ መለሰ› እያለን ነዉ ቁርአን፡፡ ነቢ ያዕቁብም ‹ዓይነናስን› ከልጃቸዉ ላይ ለመከላከል ተጠቀሙበት፡፡ ከዚህ የቁርአን አንቀጽና ከተያያዥ ታሪኮቹ የሚከተሉት ቁም ነገሮች ይጎላሉ፡- 1. አላህ ባሮቹን የሚረዳባቸዉ መንገዶች ብዛት፣ 2. የቀሚሱ ልቅና፣ 3. የነብያት ቅርስ ያለዉ ክብርና በረካ፣ 4. ቅርሱን በመጠበቅና ለትዉልዶች በማስተላለፉ ሂደት የታላላቅ ነብያት ተሳትፎ፣ 5. የነብያትን ቅርስ የመጠበቅ ፋይዳ፣ 6. በነብያት ቅርስ የመበረክ ትምህርት፣ማለትም የዕቁብና ዩሱፍ በዚህ ቀሚስ ተበሩክ አድርገዋል፡፡ የዕቁብ በቀሚሱ በረካ ልጃቸዉን ከሰዉ አይን ተከላክለዋል፡፡ ዩሱፍም በቀሚሱ በረካ የአባታቸዉን አይን አብርተዋል፡፡ ከነብያት ጋር የተገናኙ ቁሶች ክብር የተጎናጸፉት በነብያቶች አማካይነት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ በነርሱ በረከት ጉዳይን መፈጸም ከተቻለ በነብያቱ በራሳቸዉ ክብርስ? ተበሩክን የተወሱል አካል አድርገዉ የሚወስዱ ዑለሞች አንደኛዉ አመክንዮ ይህ ነዉ፡፡ በጥቅሉ ከነብያት ጋር ግንኙነት ያላቸዉ ቦታዎች፣ቁሶች ወዘተ ባለበረካ ስለሆኑ ከነርሱ በረካ መሻት ሸሪዐዊ ነዉ፡፡ ሐ.በግመሏ መጠጫ ቦታ መበረክ ናፊዕ እብን ዑመርን ዋቢ አድርገዉ እንዳስተላለፉት ሰዎች ከአላህ መልዕክተኛ ጋር ሆነዉ ከሰሙድ አገር ዘንድ ሠፈሩ፡፡ ከጉድጓዶችዋም ዉሀ ቀዱ፡፡ ሊጥም አቦኩበት፡፡ የአላህ መልዕክተኛምe የቀዱትን ዉሀ እንዲደፉና ሊጡንም ለግመሎች እንዲመግቡ አዘዙ፡፡ የሳልህ ግመል ትጠጣበት ከነበረዉ ጉድጓድ እንዲቀዱም አመላከቷቸዉ፡፡[12] ኢማም አልነወዊ (631-676 ሂ) ከዚህ ሀዲስ የሚገኙ ትምህርቶችን ሲዘረዝሩ እንዲህ ብለዋል፡- ومنها مجانبة آبار الظالمين والتبرك بآبار الصالحين ‹‹ከዚህ ታሪክ የበዳዮችን ጉድጓዶች የመታቀብና በደጋጎች ጉድጓዶች የመበረክ ትምህርት ይቀሰማል፡፡››[13] ኢማም ቁርጡቢም ይህን ክስተት ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፡- أمره صلى الله عليه و سلم أن يستقوا من بئر الناقة دليل على التبرك بآثار الأنبياء والصالحين وإن تقادمت أعصارهم وخفيت آثارهم ‹‹ነብዩ ሶሀቦቻቸዉን ከግመሏ ጉድጓድ እንዲጠጡ ማዘዛቸዉ በነብያትና በደጋጎች ቅርሶችና ቅሪቶች መበረክ-የቱን ያህል የጥንት ቢሆኑና ምልክታቸዉ ቢጠፋ እንኳ- ሸሪአዊ ለመሆኑ መረጃ ነዉ፡፡››[14] እነዚህና ሌሎች ቁርአናዊ መረጃዎች ባሉበት ሁኔታ አንዳንድ ወገኖች ለ"ተውሂድ" በጣም "ከመቆርቆራቸው" የተነሳ ራሱን ቁርአንን በሽርክ የጠረጠሩት ይመስላል። የህዳግ ማስታወሻዎች [1] አልበቀራህ 248 [2] አልበቀራህ 247 [3] ሂ የምትለዋ ፊደል በዚህ ጽሁፍ ዉስጥ እንደ ሂጅሪያ አቆጣጠር የሚለዉን መልዕክት ትወክላለች፡ [4] እብን ከሲር፣አልቢዳየቱ ወኒሀያ፣ቅጽ 2፣ገጽ 8 [5] ያለፈዉ ምንጭ [6] ተፍሲር ቁርጡቢ-ለአንቀጹ የተሰጠ ማብራሪያ [7] እብን ከሲር እብን ዐባስን፣ዒክሪማን፣ረቢዐን፣አነስንና ሌሎችን ጠቅሰዉ እንደዘገቡት-ለአንቀጹ በሰጡት ማብራሪያ፤ [8] አልቁርጡቢ ለአንቀጹ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ [9] ዩሱፍ 93 [10] ዩሱፍ 96 [11] አልቁርጡቢ ለአንቀጹ ከሰጡት ማብራሪያ፤ [12] ቡኻሪና ሙስሊም [13] አልነወዊ፣አልሚንሀጅ ሸርህ ሙስሊም እብንል ሀጃጅ፣ዳሩ ኢህያእ ቱራሰል ዐረቢ፣ቤይሩት፣ሁለተኛ ዕትም፣1392 ሂጅሪያ፣ 18/112 [14] አልጃሚዕ ሊአህካሚል ቁርአን 10/42 https://t.me/hassentaju
አጋጣሚዎችን ለመማማር መጠቀም ብልህነት ነዉ፡፡ ሰሞኑን አጀንዳ ሆኖ ከሰነበተው ጉዳይ ጋር በተያያዥነት ሲነሳ የነበረው አንዱ ጉዳይ ተበሩክ፣ ማለትም ከአንድ ደግ ሰዉ ወይም ከርሱ ጋር ግንኙነት ካላቸዉ ነገሮች ወይም ከተቀደሰ ቁስ ላይ በረካ መሻት ነው። ለአንዳንድ ወገኖች ሽርክ መስሎ መታየቱ ስህተት መሆኑንና እንዲያውም ሱናና የደጋጎች የዘመናት ልምድ መሆኑን ለማሳየት ይህ ተከታታይ ጽሁፍ ተዘጋጅቷል። በዛሬው ጽሁፍ የተበሩክን ቁርአናዊ መሠረቶች እንመለከታለን። ቁርአን ስለተበሩክ ሸሪአዊነት በታሪኮች እያዋዛ በበርካታ ቦታዎች ላይ አስተምሯል። ሦስቱን ብቻ ለአብነት እንመለከታለን። በሐዲስና በዑለሞች የዘመናት ልምዶች ያለውን ቦታ በቀጣይ ጽሁፎች የምናይ ይሆናል። ሀ. የነብያትን ቅርስ የያዘዉ ሳጥን በረካ አላህ የበኒ እስራኤልን ታሪክ ሲዘክር እንዲህ ይላል፡- وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ آيَةَ مُلْكِهِ أَن يَأْتِيَكُمُ التَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ آلُ مُوسَىٰ وَآلُ هَارُونَ تَحْمِلُهُ الْمَلَائِكَةُ . إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ ‹‹ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሳ ቤተሰብና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ ሳጥኑ ሊመጣላችሁ ነው፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አልለ» አላቸው፡፡››[1] እስራኤላዉያን ነብያቸዉን፡- ‹‹አብረነዉ በአላህ መንገድ እንዋጋ ዘንድ ንጉስ አስነሳልን›› በማለት ጠየቁ፡፡ ንጉሱም፤- ‹‹አላህ ጧሉት የተባለ ንጉስ አስነስቶላችኋል›› አላቸዉ፡፡[2] ምልክቱም ስክነትና መረጋጋት ያለበትና የሙሳንና የሀሩንን ቤተሰቦች ቅርሶች የያዘ መሆኑን ነገራቸዉ፡፡ ይህን ሳጥንና በዉስጡ የያዛቸዉን የነብያት ቅርሶች በተመለከተ ኢማም እብን ከሲር (700-774 ሂ[3]) አልጦበሪን (224-310 ሂ) ዋቢ አድርገዉ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡- ‹‹ከጠላት ጋር በሚፋለሙ ጊዜ ይህን ሳጥን ይይዙታል፡፡ በርሱ በረከት፣ አላህ ከዉስጡ ባኖረዉ ስክነት፣ እንዲሁም በሙሳና በሀሩን ቤተሰቦች ቅርሶች ሰበብ ድልን ይጎናጸፋሉ፡፡››[4] እብን ከሲር የአልጦበሪን ትንታኔ ካወሱ በኋላ የሚከተለዉን ማብራሪያ አክለዋል፡- ‹‹በዚህ ሳጥን ሰበብ በጠላቶቻቸዉ ላይ ድል ይጎናጸፉ ነበር፡፡ ከዉስጡም የነብያት ቀልብ የሚታጠብበት ጥሽት /ሳህን/ ነበረበት፤ /እብን ዐባስ እንደተናገሩት/፡፡››[5] ከሳጥኑ ዉስጥ ከአላህ የሆነ እርጋታ እንደነበረበት የሚገልጸዉን የአንቀጹን ክፍል በተመለከተ የተሰጡ አስተያየቶችን ኢማም ቁርጡቢ (600-671 ሂ) ከጠቃቀሱ በኋላ የሚከተለዉን ማጠቃለያ አስፍረዋል፡- والصحيح أن التابوت كانت فيه أشياء فاضلة من بقايا الأنبياء وآثارهم فكانت النفوس تسكن إلى ذلك وتأنس به وتقوى ‹‹ሳጥኑ ከዉስጡ ከነብያት ቁሳቁሶች ቅሪቶችና ቅርሶች ነበሩበት፤ ነፍሶች በነርሱ ይረጉ፣ይደሰቱና ይበረቱም ነበር፡፡››[6] ከሳጥኑ ዉስጥ የነበሩ የነብያት ቅርሶችን ይዘት አስመልክቶም ከተሰጡ አስተያየቶች መሀል እብን ከሲር የሚከተሉትን ዘርዝረዋል፡- ‹‹የሙሳና የሀሩን ዘንጎች፣ሁለት የተዉራት ሰሌዳዎች፣የሙሳ ልብሶች፣ሁለት ጫማዎች…››[7] አል ቁርጡቢ እንደጻፉት፡- ‹‹ከላይ የተዘረዘሩ ቁሶችና ስክነት እንዳለበት የተገለጸዉን ይህን ሳጥን አላህ ለአደም ሰጣቸዉ፡፡ እስከያዕቁብ ድረስም ለትዉልዶች ሲሸጋገር ቆየ፡፡ እስራኤላዉያን በርሱ አማካይነት ጠላቶቻቸዉን ያሸንፉ ነበር፡፡ ሀጢአት ባበዙ ጊዜም ይህን ሳጥን ተቀሙ፡፡››[8] ከዚህ አንቀጽና በዑለሞች ከተሰጠዉ ማብራሪያ የሚከተሉት ቁም ነገሮች ይቀሰማሉ፡- 1. አላህ ከነብያት ጋር ትስስር ላላቸዉ ቅርሶች የሰጠዉ ክብር፤ 2. በነብያት ቅርሶች ዉስጥ በረከትን አኑሯልና በረከታማ ናቸዉ፤ 3. ስለዚህ በነርሱ መበረክ በአላህ ዘንድ የሚፈለግና የሚበረታታ ነዉ፤ 4. እስራኤላዉያን በነዚህ ቅርሶች በረከት ጠላቶቻቸዉን ያሸንፉ ነበር፤ 5. የነብያት ቅርሶች ለአንድ ህዝብ የድል ምክንያቱ ስለሆኑ መጠበቅ አለባቸዉ፤ 6. የነብያትን ቅርሶች ማየት ለቀልብ ስክነትን፣ደስታንና ብርታትን ይጨምራል፤ 7. የነብያት ቅርሶች መዉደም በሀጢአት ሰበብ የሚከሰት ቅጣት ነዉ፡፡ ስለዚህ ነብያት ትተዋቸዉ በሄዱት ቅርሶችና ዉርሶች መበረክ ቁርአናዊ መሠረት ያለዉ መሆኑን ይህ አንቀጽ በማያሻማ ሁኔታ ያስተምራል፡፡ ይህ የየትኛዉንም ነብይ ቅርስ የተመለከተ ሲሆን የነብያት ቁንጮ የሆኑት የሰይዱል በሸር ቅርስ ደግሞ ከሌሎች ነብያት በበለጠ ሁኔታ ስክነትን የሚለግስ፣ብርታትን የሚያጎናጽፍ በረከታማ መሆኑ እሙን ነዉ፡፡ ለ. የቀሚሱ በረካ ከጥንት ነብያት ጋር ግንኙነት ካላቸዉ ነገሮች በረከትን መፈለግ ሸሪዐዊ መሆኑን ከሚያስተምሩ የቁርአን መልዕክቶች መካከል ሌላኛዉ ከነቢ ዩሱፍ ጋር የተገናኘዉ ነዉ፡፡ ይኸዉም ዩሱፍ በባርነት ተሸጠዉ ከሄዱባት ግብጽ ሀገር ትልቅ ባለስልጣን ሆነዉ፣በወቅቱ በተከሰተዉ ድርቅ አማካይነት ከወንድሞቻቸዉ ጋር ተገናኝተዉ ከተወቃቀሱ በኋላ ዩሱፍ እንዲህ ሲሉ ወንድሞቻቸዉን አዘዙ፡- اذْهَبُوا بِقَمِيصِي هَٰذَا فَأَلْقُوهُ عَلَىٰ وَجْهِ أَبِي يَأْتِ بَصِيرًا وَأْتُونِي بِأَهْلِكُمْ أَجْمَعِينَ «ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ሊዱ፡፡ በአባቴ ፊትም ጣሉት የሚያይ ሆኖ ይመጣልና፡፡ ቤተሰቦቻችሁንም ሰብስባችሁ አምጡልኝ»[9] የዩሱፍ ወንድሞች እንደታዘዙት ቀሚሱን ወስደዉ ከአባታቸዉ ፊት ላይ ሲያኖሩት የሆነዉን ቁርአን እንዲህ ዘግቧል፡- فَلَمَّا أَن جَاءَ الْبَشِيرُ أَلْقَاهُ عَلَىٰ وَجْهِهِ فَارْتَدَّ بَصِيرًا ‹‹አብሳሪውም በመጣ ጊዜ (ቀሚሱን) በፊቱ ላይ ጣለው፡፡ ወዲውም የሚያይ ኾነ፡፡››[10] የነቢ ዩሱፈ አባት ነቢ ያዕቁብ በልጃቸዉ መጥፋት ሀዘናቸዉ በርትቶ የዓይናቸዉን ብርሀን አጥተዉ የነበረ ቢሆንም በዚህ ቀሚስ በረካ ብርሀናቸዉ ተመለሰ፡፡ የቀሚሱን ምንጭና ታሪክ በተመለከተ ኢማም ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል፡ ذلك قميص إبراهيم الذي ألبسه الله في النار من حرير الجنة وكان كساه إسحق وكان إسحق كساه يعقوب وكان يعقوب أدرج ذلك القميص في قصبة من فضة وعلقه في عنق يوسف لما كان يخاف عليه من العين ‹‹ይህ ቀሚስ አላህ ለነቢ ኢብራሂም ከእሳቷ ዉስጥ በነበሩ ጊዜ ከጀነት አዉርዶ ያለበሳቸዉ ቀሚስ ነዉ፡፡ ኢብራሂም ለኢስሀቅ፣ኢስሀቅ ለየእቁብ አለበሱ፡፡ የዕቁብም ዩሱፍን የሰዉ ዓይን እንዳይበላዉ በሰጉ ጊዜ በብር አሰናስለዉ ከአንገቱ ላይ አንጠለጠሉለት፡፡››[11] ነቢ ዩሱፈ ይህን ቀሚስ ከአንገታቸዉ ላይ ልክ እንደ ሂርዝ አንጠልጥለዉት ነበር፡፡ ተግባሩም የሰዉ ዓይን እንዳያገኛቸዉ መከላከል ነበር፡፡ የኢማም ቁርጡቢ ገለጻ ይህን ያረጋግጣል፡፡
ሙፍቲ ዑመር በህይወት ሳሉ ሰው ሁኑ ፣ ሰውነት ይቀድማል በማለት ሰው መሆንን ሳይታክቱ ሰበኩን። ሸይህ ዐዲል አህመድ ሰሞኑ እንዲህ ሲሉ ተደመጡ:- “እሳቸው በህይወት ሳሉ ሰው መሆንን አስተማሩን፣ በሞታቸው ደግሞ ሰው የሆነውንና ሰው ያልሆነውን ለይተን አየንበት።” ገራሚ ንግግር (ከ Yamin Amin ገጽ)
#እስስት(ኢኽዋን) የኡስታዝ ያሲን ኑሩ መልዕክት ፍጹም ሀላፊነት የጎደለው ሁከት እና ብጥብጥ ጥሪ ነው'' አምባሳደር ኡስታዝ ሀሰን ታጁ ፍጹም ሀላፊነት የጎደለው ሀሳብ፣ የሁከት እና የብጥብጥ ጥሪ፣ የሰብአዊና ህገመንግስታዊ መብት ጥሰት፤ በማስተዋልና በአደብ ያልታሹ እንዲህ ዓይነት መልዕክቶች የመስጅድ ሚንበሮችን አይመጥኑም። ብዙ መዘዞችን ማምጣታቸውም አይቀሬ ነው። የራስን ወገን ብቻ የዲን ተቆርቋሪ፣የተውሂድ ጠበቃ አድርጎ ከማሰብ መቆጠብ፣ የሌላኛውን አካል ሀሳብ በጥሞና ማድመጥ፣ስጋቶቹን መጋራት፣መብቶቹንና የፊቅህ ምርጫዎቹን ማክበርና ሌሎችን ያለአግባብ ከማውገዝ ይልቅ ከነርሱ ጥበብና መረጃ ለመቅሰም መትጋት ከስክነት ይመነጫል። በመርጊያ እድሜ እንደ ወይፈን መጎፍላትን ለነፍስያችን ልንፈቅድላት አይገባም። እኛ ትክክል ያልነው ስሀተት፣ተውሂድ ያልነው ሽርክ፣ጽድቅ ያልነው ኩነኔ ሆኖ ሊገኝ ስለሚችል መረጋጋትን የመሰለ ነገር የለም። በርካታ የኑሮ ውጣ ውረዶችንና ሌሎች ውጥንቅጦችን ለተሸከመ ህዝብ በሀይማኖት ስም ሌላ ሸክም ልንጭንበት አይገባም። ለማንኛውም የሙፍቲን ኑዛዜ ሸሪዐዊነትና ጥበብ የሚያጸና እና በየአቅጣጫው የተስተዋሉ ህጸጾችን የሚያርም ጽሁፍም አስነብባለሁ ብለዋል። Via:- አምባሳደር ኡስታዝ ሀሰን ታጁ MEDIBA TUBE https://t.me/medina_tube
እነዚህ በተቀዳሚ ሙፍቲ ዑመር ሕልፈት የተሳለቁና ስድ^ባቸውን በቪዲዮም ጭምር በድፍረት የለቀቁ ናቸው:: እነዚህ ለሙት እንኳ የማያዝኑ አረ^መኔ በመሆናቸው ሕጋዊ የክስ ሒደቱ እስኪደራጅ ድረስ በሚኖሩበት, ለአገልግሎት በሚሄዱበት ቦታና መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም አውሮፕላን ሲሳፈሩ ከፍተኛ ክትትል ፍተሻ ቢደረግባቸው ጥሩ ነው:: ለሞተ ሰው ካላዘኑ በሕይወት ላለ ሊያዝኑ አይችሉም::
ቀብር ኮልፌ ሳይሆን ሀሪማቸው በሚገኝበት ሰፈራ ኃይል ጋርመንት በተባለው አከባቢ ነው !! ➡️አስር ላይ ነው
ለኛ ከየትኛውም ሰው ሞት በላይ የሷሊሆች፣ የዓሪፎች፣ የወሊዮች ህይወት ማለፍ በከባዱ ያሰጋናል። ካለንበት ተጨባጭ ሁናቴ ላይ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆንብናል። ከነምናምናችን እስካሁን የተዘገየነው በደጋግ የአላህ ባሪያዎች በረከትና ፀሎት መሆኑ ለማንም የማይሰወር እውነታ ነው! የአንድ ዓሊም ወደ ቀጣዩ ህይወት መሸጋገር በቁም ለሞተው ድርብ ሀዘን ነው። በመኖራቸው ሰበብ የደፈኑትን ክፍተት፣ የመለሱትን መቅሰፍት፣ ያቆዩትን ሰላም በተለዩን ቁጥር ያስተዋለ ይታዘበዋል! #አላህ ይኹነን 🤲
ታላቁ ዐሊም ፣ የዐይን ብሌናችን ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ኢድሪስ የጤና እክል አጋጥሟቸው ህክምና ላይ ይገኛሉ ፤ ስለሆነም መላው የሙስሊሙ ማህበረሰብ በዱዐ እንዲበረታ ጥሪ ቀርቧል አሏህ ሆይ ! ለሙፍቲያችን ዐፊያቸው መልስላቸው ፤ በእዝነትህ ይሁንብህ አሚን 🤲🤲🤲