tgindex
ABRET PRO

የአብሬት እንዲሁም የቃዲሪይ ሲልሲላ መንዙማዎችን ፣ ከአካቢሮች የሰማናቸውን ቀሰሶች ፣ እንዲሁም ከመሻኢኾቻችን ኪታቦች አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን የምንማማርበት አጠቃላይ የሀድራ ስራዎችን የምንዘክርበት ቻናል ነው @Abretpro

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 538
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 459
22 постов
Вовлечённость
54,2%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 22
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
739
1/48двое суток
846
1/72трое суток
913

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ሐጂዬ የረቢዑ ድምቀት ነበሩ:: የመውሊድ መድረኮች ሁሉ ሙፍቲን ይናፍቁ ነበር:: እሳቸው የገቡበት መውሊድ ነቢﷺ ገብተውበታል ማለት ይቻል ነበር:: ጣፋጭ እጅግ መካሪ መልእክቶቻቸው ሁሌም ይናፈቃሉ:: መልካም ስራዎቻቸውን አላህ ይውደድላቸው:: ወሩ ነቢﷺ የተወለዱበት ወር ነው:: ሰዋቡን ለወዳጃቸው ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ገነቴ ነይተን ሰለዋት ብናወርድ ትርፉ እጥፍ ድርብ ነው::

  • ለነብያችንﷺ ዊላዳ ካኢናቱ ሁሉ በደስታ ተወዛወዘ ፣ መላኢካው ሁሉ በኢሽቅ ተንቀጠቀጠ ፣ ሁሉም የጀነት በሮች እጅግ ግሩም በሆነ መአዛ ታጅበው ተከፈቱ:: የነብያችንንﷺ መወለድ አላህ እራሱ ነው ቀድሞ ያከበረው:: واهتز كل اكوان الله عاشقا ونزهة وتراجفت به الملإكة بالغرام والوجد وفتح الجنان والعطر يتباهر لمولد طه العربى المجتبى الأمجد

  • 12 авг.1 0415132

    ሰፈር ወር ውስጥ ስላለው የመጨረሻ እሮብ አብሬትዮች ይህንን ቀን በየአመቱ ተህሊል በመክተብ በዱዓና ሰደቃ እንድናሳልፈው ተርቲብ አድርገውልናል ከአሪፎች ከፊሎቹ የከሽፍና የተምኪን ባለቤት የሆኑት ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ:- በእያንዳንዱ አመት ሶስት መቶ ሺ በላ(የአላህ ቁጣ) ይወርዳል ከነዚህ ውስጥ ሀያ ሺ የሚሆኑት በላዎች በሰፈር ወር የመጨረሻው እሮብ ነው የሚወርደው ለዚህም ነው አመቱ ውስጥ ካሉት ቀናት ውስጥ የሰፈር ወር የመጨረሻው እሮብ አሳሳቢ የሚሆነው በዚያ ቀን 4ረከአ የሰገደ ሰው በእያንዳንዱ ረከአ ከፋቲሀ በኃላ ኢና-አእጠይና 17 ጊዜ፣ ቁል ሁወላሁ አሀድ 5ጊዜ እንዲሁም ሙአውዘተይን አንዳንድ ጊዜ ከቀራ በመቀጠል በዱአኡል ሙአዘም አላህን ከለመነ አላህ በቸርነቱ የዚያን ቀን ከሚወርደው በላ በአጠቃላይ ይጠብቀዋል:: ኢሄን ሰው በላ የሚባል ነገር በዙሪያው ለአንድ አመት ድረስ መጠጋት አይችልም። እንዲሁ ሱራ*ያሲን* አንድ ግዜ እንድንቀራ…(سَلامٌ قَوْلا مِنْ رَبٍّ رَحِيمٍ) የሚለውን 313 ግዜ ደጋግመን እንድንቀራው አመላክተውናል ዱአኡል-ሙአዘም:- ቢስሚላሂ ረህማኒረሂም ወሰለላሁ ተአላ አላ ሰይዲና ሙሀመዲን ወአላ አሊሂ ወሳህቢሂ ወሰለም። አላሁመ ያሸዲደል ቁዋ ወያ ሸዲደል ሚሀል ያ አዚዝ ዘለት ሊኢዘቲከ ጀሚአ ኸልቂክ። ኢክፊኒ ሚን ጀሚአ ኸልቂክ ያ ሙህሲን ያ ሙጅሚል ያ ሙተፈዲል ያ ሙንኢም ያ ሙክሪም ያ መን ላኢላሀ ኢላ አንተ ኢርሀምኒ ቢረህመቲከ ያአርሀመራሂሚን አላሁመ ቢሲሪ ሀሰን ወአኺሂ ወጀዲሂ ወአቢሂ ወኡሚሂ ወበኒሂ ኢክፊኒ ሸረ ሀዘ የውም ወማ የንዚሉ ፊሂ ያ ካፊየል ሙሂማት ያዳፊአል በሊያት (ፈሰየክፊኩሁሙላህ ወሁወ ሰሚኡል አሊም) ሀስቡነላህ ወኒእመል ወኪል ወላሀውል ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል አሊዪል አዚም ወሰለላሁ ተአላ አላ ሰይዲና ሙሀመዲን ወአላ አሊሂ ወሳህቢሂ ወሰለም

  • 10 авг.1 5301218

    ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን የአብሬቶቹ የዘር ፍሬ ፣ የሸይኻችን ሠይዲ ሚቅባሰል ኑር(ቀ.ሢ) የልጅ ልጅ ፣ ተወዳጁ ወንድማችን ሱነን በድንገት ተለየን አላህ በረሕመቱ ይሸፍንልን ፣ ሩሁን በአባት አያቶቹ አካቢሮቹ ጥላ ስር ከነቢﷺ ጋር ያኑርልን🤲

  • 4 авг.2 169476

    <የሙላት ተረፍ..> ✍️በነሲም ሚራዥ ራስን ለሌሎች በማኖር ውስጥ ሊቅነትን አንድ ገፅ ማድረግ፤ ወይም በሊቅነት ውስጥ ያወቁትን መኖር፤ ራስን አልቆ ለማህበረሰብ ማስጣት፣ ፋና ወጊ ሆኖ ወደ አላህ መምራት፤ ከሰይዳችን ﷺ ጋር በውዴታ እና በግብር ማስተሳሰር፤ ቀደምት የሐበሻ ጉምቱ ሊቃውንት የተከታተሉበት የአኗኗር ዘይቤ ነው። እሳቸውም ያን ፈለግ ተከትለው የፈሰሱ፤ ኖረው ለማለፋቸው ማሳያ እና አረጋጋጭ ሆነው የነጉ፤ ከሙላት ተትረፍርፈው፤ የዘመንን ጭጋጋግ ጠርገው፤ የተስፋን ጭላንጭ የሚያስጮልቁን ዛሬያችንም ትላንታችንም ነበሩ። ሸይኽ ሰይድ ሚቅባስ አል-ኑር አል- አብሬቲይ ( 1933- 2015) መውላና ሸይኽ ናዚም አል ሃቃኒ (ቁዲሰ ሲረሁ) ' The Safety of the Soul in Troubled Times' በሚለው መፅሃፋቸው.. "A true leader is one who, without fearing the storms of their era or abandoning the riches of history, stands between time and humanity to act as a bridge guiding the generation toward truth.." የሚልን ጥቂት ግን ሰፊ የሆነ ትርጓሜን የያዘ ቃል አስፍረዋል። ለዚህ ገለፃ ሰይዲ ሁነኛ ምሳሌ፤ ተጨባጭ ማሳያ ናቸው። የዘመን ተጋሪዎቻቸው፤ የህይወት ተጣማሪዎቻቸው "ተራማጅ ነበሩ" ይሏቸዋል። ከወቅት መሸሽ አያውቃቸውም። "እኔነት" አይገኝባቸውም። እኔነታቸው ለሌሎች የተሰዋ ነበር። በዚህም ሳቢያ ዘመንን ሳይመስሉ ዘመን እነሱን እንዲመስል ማድረግ፤ በትላንት እና በዛሬ መሐል ሚዛን ማድረግ፤ በዚያው ውስጥ መኖር፤ በመኖር ውስጥ ለብዙሃኑ ማመላከት በህይወት መዝገባቸው ውስጥ ጎልቶ የሚነበብ፤ ደምቆ የሚታይ እውነት ነው። ዛሬም የመታገል እና ፀንቶ የመቆም ምሳሌ ሆነው ይነሳሉ። ከህይወታቸው የተሻለ ምስክር ባያሻውም፤ ጥቂት የሚያውቃቸው ሁሉ ለዚህ ህያው ምስክር ነው። ለሌሎች መሆናቸው በዚህ አይገደብም። መፍትሄ ለጋሽነታቸው እምነት እና መንፈዊነት ላይ አይገታም። በመንፈሳዊ መሪነታቸው የማያውቃቸው በመድኃኒት ሰጪነታቸው ያውቃቸዋል። በራቸው ታማሚ አይለይም። ሐይማኖት፤ ዘር፤ ቀለም ታሳቢ ሳይደረግ ሰው በሰውነቱ የሚስተናገድበት፤ እርዳታ ከጅሎ የገባ "ማነህ?" "ምን ይዘሃል?" ተብሎ የማይጠየቅበት፤ የሰብዓዊነት አፀድ፤ የመሻር ቤት ሆነው ነው የኖሩት። አዛኝነታቸው አይነጥፍም። አባትነታቸው ሰው አይመርጥም። አሸማግይነታቸው ሚዛኑ አይዘንፍም። ሁሉን ሆነው ለሁሉ የበሩ ፀሃይ ናቸው። መምህር ሆነው በስራቸው ተማሪዎችን ኮልኩለዋል። ኪታብ ዘርግተው ያላቸውን ያለመሰሰት ሰጥተዋል። በጥበብ እና ልስላሴ ቁርዓንን ሰብከዋል። ሸሪዓን አስቀድመዋል። ሊቃእ መስርተው ፍቅርን ዘርተዋል። የሰይዳችንን ልቅና እና ምልኣተ-ህይወት፤ ፍቅር እና ናፍቆት በእያንዳንዱ ቅፅበት አስተጋብተዋል። ሐድራ እና አውራድ፤ ዱዓ እና ተስሊም አነብረዋል። ሻካራ ቀልቦችን በአላህ እና በሰይዳችን ﷺ ፍቅር ወልውለዋል። የአባታቸው ሰይድ ባዑ ሳኒ(ረዲየሏሁ ዐንሁ) ህይወት ተራኪ፤ የውጣ ውረዶቻቸው ማጣቀሻ፤ የገድሎሉቻቸው አረጋጋጭ፤ የሙሪዶቻቸው ሰብሳቢ፤ የናፋቂዎች መታገሻ፤ የልቅናቸው ነፀብራቅ በመሆን ነው ክራሞታቸውን ያሳለፉት ። ለስነ-ፅሁፍ ስስ ጎን ነበራቸው። በከታቢነቱም ደርጅተዋል። አግራሞትን የሚያጭሩ መድብሎችን ሰንደዋል። ገና በአፍላነት፤ በጉልምስና ዘመን ቀለም አቅልመው፤ መድ ነክረው "ያ ኑረል ሙቀደም" ሲሉ ብዕራቸውን አፍታተዋል። በ"አልመንዑቲል ጋሊ.." ተቀናጥተዋል። በቡርዳ ሙኸመሳቸው እጅ በአፍ አስጭነዋል። "ያረቢ ሶሊ ዓላ.." ብለው አጀሙን በሚገባው አናግረዋል። የቀደምቶቻቸውን ፋና ተከትለው የሰይዳችንን ﷺ ህይወት እና ልቅና በርብረዋል። መውደድ እና ናፍቆታቸውን ተናዘዋል። ለአባታቸው ባዑ ሳሊስ(ረዲየሏሁ ዓንሁ) የነበራቸውን ውዴታ እና ብርቱ ናፍቆት ከመግለፅ አልሰሰቱም። የህይወት ተግዳሮታቸው መስፋት እሳቸውን ከማወደስ አላናጠባቸውም። ማዕረግ አክለው፤ ስንኝ ደርድረዋል። "ታጁል ኩበራ" የተሰኘው መወድስ የዚህ ፈንጣቂ መውደድ ማሳያ፤ "ሚስባሁል ሪጃል.." ማሟያው ነው። ስለ ሰርሳሪ እይታቸው፤ አትኩሮ ለማየት ስለማያስደፍረው ገፅታቸው፤ መለየት እና ትቶ መሄድ ስለማያሰኘው ግርማቸው፤ ቦታ ስለማይመርጠው ሆደ ቡቡነታቸው፤ ጘፍላን ስለሚጠርገው ፈገግታቸው፤ ስለመተናነስ እና ስለ ማቅረባቸው፤ በምክንያት ስለማይተነተነው መውደዳቸው የተዳበሰ ተመልካች ያውራው። ሰይዲ ይሄንን ወይም ያን ብቻ አልነበሩም። የተፃፈውን ወይም ያልተፃፈውን ብቻም አልነበሩም። በጥቅሉ ትርጉም ካሻን፤ ከትላንት ሳይነጠሉ፤ ከዛሬ ሳይኳረፉ፤ ለሁሉ በሁሉ ሆነው የኖሩ፤ በዚህም ከጥቂት የዘመን አቻዎቻቸው ጋር ተለይተው የፈነጠቁ አንኳር ስብዕና፤ ወዲህም የአባታቸው ሰይድ አበልራሙዝ(ረዲየሏሁ ዐንሁ) Successor ናቸው። የትልቅ ሰው ግኝ ሆኖ መኖር የሚያበቃ አይመስልም። ውዴታ እና ስስት ያን የተፈጥሮ ዑደት በእነሱ ላይ እንድናስብ በር አይከፍትም። ተፈጥሮ ግን ስራውን አልዘነጋም። እኛን ከነጅምራችን ትቶ፤ ለእርሳቸው እረፍትን ለግሷል። ቀላል አይደለም። መለየታቸው ያጎደለው ብዙ ነው። እሳቸውን የማጣት ስንጥቃት በምንም የሚጠገን አልሆነም። የህይወት ፍልስፍናቸው እና አሻራቸው ግን ህያው ሆኖ ይኖራል። አመደነሏሁ ቢአምዳዲሂም፣ ወነፈዐነ ቢዑሉሚሂም፣ ወአዓደ ዐለይና ሚን በረካቲሂም፣ ወሐሸረና ፊ ዙምረቲሂም..! - ማሳረጊያ ዘርፈ ብዙው፤ ሁሉን የነካካው፤ ትውልድ የቀረፀው፤ ስኬታማ የህይወት ዘይቤን ያሰመረው ኑረታቸው መማሪያ ይሆን ዘንዳ፤ በወጉ ሊሰነድ፤ የመወያያ መድረክ ሊፈጠርለት ይገባል። ይህ የእኔ መልእክት ነው።

  • 31 июл.2 211892

    ወቅቶች ሁሉ አንቱን ያስታውሱናል:: በደስታም በሀዘንም ሁሌ ትውስ ፣ ዒድም መውሊድም ሲመጣ ከፊት ድቅን:: ዱዓው ነሻጣው መደዱም ያላንቱ አልሆን አለን:: ሩህዎ አይለየን🤲 💚መደድ ያሠይዲ

  • 30 июл.2 2584817

    እጅግ ልዩ የሆነ ሰለዋት ✿❀ ✿❀ ✿❀ ✿❀ ✿❀ المرة الواحدة من هذه الصيغة تفوق غيرها أربعين مرة اه مؤلف የጊዛኡል ዓቢዲን ሙአሊፍ አብሬትዩ ሳኒ(ቀ.ሢ) አምስት ግዜ ደጋግመን እንድንቀራው ምልክት ያደረጉበት እጅግ ልዩ ሰለዋት ነው... ይህንን ሰለዋት በዚህ መልኩ አንድ ግዜ ማለት(መቅራት) ሌላ ሰለዋትን አርባ ግዜ ከማለት ይበልጣል ብለው ከሰለዋቱ ታች በኩል ባስቀመጡት ማብራሪያ ተናግረዋል:: አርባ ግዜ ወይንም በአርባ እጥፍ ይበልጣል ማለትንም ሊያሲዝ ይችላል:: 📚ጊዛኡል ዓቢዲን

  • 24 июл.2 4752

    без подписи

  • 24 июл.2 628762

    የተወዳጁ ሸይኻችን ሠይዲ ሸይኽ ሚቅባሰል ኑር አልአብሬትይ (ቀ.ሢ) አመታዊ የቁርአን ኸትም እና ዱዓ ፕሮግራም በዛሬው ቀን ሰፈር 10 ከጠዋቱ ጀምሮ እይተካሄደ ነው:: አላህ ኑር አድርጎ ያድርስላቸው:: እኛንም በመንገዳቸው ያፅናን🤲

  • 23 июл.2 632637

    ጥማቱ እንዲ ነው ተብሎ በማይባለት በዛ የጭንቅ ቀን ሰዎች ወደ ሐውዱ ይመጣሉ... በእኔ ላይ አብዝተው ሰለዋት ከሚያወርዱት በቀር አላውቃቸውም ብለዋል ሐቢባችንﷺ ‎ﷴﷺ ❤️ ዘንድ መታወቅ ከፈለግክ ሶላት አለ ነቢ አብዛ 🙏

  • 22 июл.2 459926

    የዛሬ ሁለት አመት በሰፈር ወር 10ኛው ቀን 1446 እንደ አመተ ሂጅራ ነበር ተወዳጁን ፣ ታላቁን የአላህ ወልይ ፣ በሻሻው ሸይኻችንን ከጎናችን ያጣነው:: ወፋታቸው ለወዳጅ ቤተሰባቸው እጅግ ከባድ ሀዘን ቢሆንም ለእሳቸው ግን ኻሊቃቸውን የተገናኙበት ፣ ከዚህች ከንቱ አለም ጣጣ ያረፉበት ፣ የናፈቋቸውን ሁሉ ያገኙበት ትልቅ ቀን ነው:: አልፋቲሓ 🤲

  • 21 июл.2 316693

    ያስያዙንን ይዘናል:: ኢሻአላህ አንለቅም! ☆ ☆ ☆ እናንተ የባእ ቤተሰቦች ሆይ ከሠይድ ባኡ ሳኒ (ቀ.ሢ) የተዘረጋ የሆነ ገመድ (መንገድ) አለላቹ... እሱን አጥብቃችሁ ያዙ ! አብሬትዩ ሳሊስ (ቀ.ሢ) በአንድ መድሀቸው ካሰፈሩት يا بن باء إن لكم بحبيبي الله سيدكم حبل ودي من اكبركم فالزمه يا اولو الحمم

  • 18 июл.2 370625

    ያንዳንዶቹ እጣ እንደው ለጉድ ነው:: በመላው አለም የሱፍይ ጠሪቃዎች የሠይዲ አብዱልቃዲር ጂላኒይ ስም እንደሚወሳው ሁሉ በሀበሻ ዳር እስከዳር የዳናው ጌታ ይወሳሉ:: ትልልቅ የተባሉ እጅግ ብዙ ሀሪማዎች ሁሉ የዳኖቹ አሻራ አርፎበታል:: መገን ሺሀቡ ዳንይ💚 شي لله شي لله شهاب الداني محراب مدور النور العرشي

  • 16 июл.4 01520

    без подписи

  • 16 июл.4 19520

    без подписи

  • 16 июл.3 6506919

    ለኸሚሱ ከዚህ የተሻለ ስጦታ አጣሁ በድጋሚ የተፖሰተ ✦✦✦ በሸዋል ወር ከዙሁር ሶላት ራቲባ በሁዋላ ምንም አይነት ሌላ ንግግር ሳላስከትል ተኛሁ... በመናሜ የዚህ ሰለዋት ዋሪዳ የተስተካከለ ሆኖ መጣ "እኔ የተሻልኩ ምርጥ የሆንኩ ሶለዋት ነኝ... ኪብሪተል አሕመር እባላለው..." አለኝ:: ቀራሁት መለኮታዊ የሆነ ኑር ሞልቶ አየሁ... ከአሥራሩ ክብደት የተነሳ መቆም አልቻልኩም፣ ምንም እንኳን የጀምዓ ሰላት ቦታ ቅርብ ቢሆንም ለአስር፣ ለመግሪብ ፣ ለኢሻ እና ለሱብሂ ሶላት ወደ መስጂድ መሄድ አልቻልኩም። ከዚያም ኃጢአቴን አስታወስኩና ኪብሪትን መክተብ ለመተው ወሰንኩ፣ የዛኔ ሸክሙ ቀለለኝ... የረጀብ ወር ሲገባ(ወራቶች አልፈው) ኪብሪተል አህመር የተከተበች ሆና ዳግም አየሗት... በውስጧ ብዙ እንግዳ የሆኑ ግሩም ሚስጥሮችን አየሁባት... እያንዳንዱ ሀርፏ እንደ ዋንጫ ባለ እቃ በውስጧ ብዙ አይነት መጠጥ ያለበት ሆና ዙሪያዋ ቀይ ብርሀን በሚያበሩ ሲማሮች ተከባለች፣ የኪብሪተል አሕመር ቀለሞቿ እንደ ነጭ ከዋክብት የሚያንፀባርቁ ሆነው ወደፈለጉበት እየበረሩ ሄደው ያበራሉ። ከነቃሁ በሁዋላ ምንም እንኳ እንዲህ ያሉ ሚስጥሮችን ለማየት ብቁ ባልሆንም ይህን ጉዳይ ማሰላሰሌን ቀጠልኩ። ለነቢﷺ ኡመት ከፍተኛ የሆነ ጥቅም እንዳለው የቂን ባልኩ ጊዜ ከመተው ተቆጠብኩ። ብቁ ባልሆንም ለመጻፍ ፍቃድ ጠየቅሁና መፃፍ ጀመርኩ። አላማዬ የአላህን እና የነብዩንﷺ ውዴታ መፈለግ ብቻ ነበር:: አላህም እንደሚፈቅደው ተስፋ አደርጋለሁ። 🤍ሠይዲ አባ ራሙዝ ቀ.ሢ

  • 14 июл.3 0228116

    አብሬትዬ (ቀ.ሢ) በወአዛቸው ስለ አጅ ነቢ ካስተማሩበት ☆ ☆ ☆ በነቢ ኢሳ አለይሂ ሠላም ዘመን ዝናብ ጠፋ:: ዱዓ ቢለመን ቢለመን ጭራሹኑ ዝናብ ታጣ:: ኢስቲስቃእ ብለው ሰዉን ሰበሰቡ... ተራ በተራ ዱዓ ይለምን አሉ:: ሁሉም ሰው ለምኖ አንድ አይነ ስውር ሰውዬ ተራ ደረሰው:: ዱዓ አድርግ ተባለ... "እኔ ብዙ ወንጀል ሰርቻለው... ዱዓ ማድረግ እፈራለው" አላቸው:: ምን አደረግክ ብለው ጠየቁት... አንድ ቀን አጅነቢ አየሁና ለጀዛአው ብዬ አይኔን አጠፋሁት" አላቸው:: ዱዓ ለምን አሉት:: ወዲያው እጁን ቢዘረጋ በዛው በዘረጋው እጁ ዝናብ ዘነበ::

  • 7 июл.2 867482

    የጌቶ ሸይኽ ሙሐመድ ያሲን ሻንዳ በተባለ ቦታ እጅግ ሸሪዓ አጥብቀው ዒባዳቸውን አጥብቀው ይዘው ተቀምጠው ነበር ይላሉ... በጣም ተቂይ አላህን የሚፈሩ ሰው ነበሩ:: አንድ ፉቀራ የሚመስል ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ሰው መጥቶ ገባ:: ይህ ሰው ሸይኽ ሙሐመድ ያሲን እያታለሉህ ነው... ሸሪዐ እንዳልሆነ እየመሩህ ነው... ተዋቸው አትከተላቸው ብሎ ሰበከ:: ከየት እንደመጣ እንኳን የማያውቀው ጃሂል ሰው ስለነገረው ብቻ ለሰላት እሳቸው ጋር መግባት ትቶ እንዲሁ ባከነ:: ከሠይዲ አባ ራሙዝ (ቀ.ሢ) ወአዝ የተወሰደ

  • 6 июл.2 75549

    ምንም እንኳ የምንለያይባቸው አንዳንድ ነጥቦች ቢኖሩም እንደ ህዝብ ፣ እንደ ሙስሊም ኡማም አለም ከኢራኖች እጅግ ብዙ ብዙ መማር ይኖርበታል:: (ረሒመሁላህ)

  • 4 июл.3 460677

    የሀገራችን ሀቂቃ መሻኢኾች ቁርአንን መስለው ተገኙ... ሁለመናቸው ሁሉም እንቅስቃሴያቸው ወደ እስልምና ተጣሪ ዳእዋ ሆነ:: ያያቸው ሁሉ በንፁሁ ፍቅራቸው ወድቆ ተማረከ... መንገዳቸውንም ወደደ:: ትክክለኛ ሙስሊም ሆነው ተገኙ... ብዙሀኑም ሰለመላቸው:: እነሱን በሀቅ ወዶ.. ኮቴ ብኮቴ የተከተለ ሰው በእርግጥ የሁለቱንም ሀገር ስኬት አገኝ::