አቤል ተፈራ በላይ
Статистика- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 171
- 1/48двое суток
- 195
- 1/72трое суток
- 211
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ትምህርታችን የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው እየተማርን እንገኛለን። ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት 3ተኛው (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ሆናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠናውና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው። በዚህ ክፍል ሦስት ሰነድ ውስጥ፦ የሰዎች ውድቀት፦ አዳምና ሔዋን በሕግ መተላለፋቸው ያስከተለውን መዘዝ ጥንተ አብሶ እና ምልዕተ ኃጢአት፦ የቃሉን ምስጢራዊና መጽሐፋዊ ትርጉም፣ የባሕርይ መጎስቆልና ሞት፦ የሰው ልጅ ከኃጢአት በኋላ ያጣውን ክብርና የደረሰበትን የባሕርይ ውድቀት ኃጢአት በዘር ይተላለፋልን? የሚለውን ጥያቄ ከነቢያትና ከአበው ትምህርት አንጻር አዳኝ ማግኘት አለመቻሉን፦ ነቢያት፣ መላእክት፣ የመሥዋዕተ ኦሪትና የኦሪት ሕግ ሰውን ሙሉ በሙሉ ማዳን ያልቻሉበትን ምክንያቶች ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር በዚህ ሃንዳውት አስቀምጠናል። ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀና የእግዚአብሔር አምላክ የማዳን ሥራ ምን ያህል አስፈላጊና ድንቅ እንደሆነ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል። እናንተም ይህንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ሆናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ። የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። አቤል ተፈራ በላይ ሐምሌ 30 2018 ዓ/ም
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቁልቢ ገብርኤል ከሐምሌ 17-20 ለአራት ተከታታይ ቀናት ትኬት ለመቁረጥ 0935256161 መሌ አርሴማ ጉንደር በር 0963678818 ጌጤ ጫማ ማደሻ አዳጎ 0967383005 ኤርምያስ ግእዝ ፎቶ ቤት ለበለጠ መረጃ 0909802404 0967522055
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት የሁለተኛው ሳምንት ትምህርታችን የነበረውን መሠረታዊ የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው ተምረናል። በክፍል 1 ትምህርታችን የላኩላችሁን PDF እንዳነበባችሁት ተስፋ አደርጋለሁ። ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት ክፍል 2 ጽሑፍ (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ኾናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠኑትና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው። በዚህ ክፍል ሁለት ሰነድ ውስጥ የሰውን ልጅ ውድቀትና የስደት ታሪክ ከመመልከታችን በፊት ፈጣሪ በጥንተ ተፈጥሮ ለሰው ልጅ የሰጠውን ወደር የለሽ ክብርና ልዕልና በ22ቱ ፍጥረታት አውድ ውስጥ እንመለከታለን። በመቀጠልም ምንም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀጥተኛው ቃል ባይቀመጥም በባሕርዩ ሙሉ በሙሉ መለኮታዊ ውል የነበረውን የአዳምና የእግዚአብሔርን ግንኙነት የቃል ኪዳኑን አራት መሠረታዊ ዓምዶች (የቃል ኪዳን ሰጭ ተቀባይ ተስፋና ምልክት እንዲሁም የሚጸናበትን ሁኔታ) ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር እንመረምራለን። ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል። በዚሁ መሠረት በሚቀጥሉት ሳምንታት የምንማራቸውን ተከታታይ ትምህርቶች በሙሉ እያዘጋጀን በማኅበራችን ይፋዊ የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናል ላይ የምንለቅ መሆኑን እንገልጻለን። እናንተም ይሀንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ኾናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ። የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። አቤል ተፈራ በላይ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓልን በቅዱስ ስፍራው አብረን ለማክበር በዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ማኅበር ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ተዘጋጅቶልዎታል። 📅 የጉዞ ቀናት፡ መነሻ ቀን፦ ሐምሌ 17 መመለሻ ቀን፦ ሐምሌ 20 📍 ትኬት የሚሸጥባቸው ቦታዎች፦ ፒያሳ፦ ፎቶ ግዕዝ አዳጎ፦ ጌጡ ጫማ ቤት ጎንደር በር፦ ቴድሮስ ኤሌክትሮኒክስ 📞 ለበለጠ መረጃ እና ቦታ ለመያዝ፦ 📱 0921046532 📱 0909802404 📱 0967522055 📱 0923738629 “በረከቱን አብረን እንቀበል!” ቦታዎች ሳይሞሉ ፈጥነው ትኬቶን ይቁረጡ።
የደስታ ቀን ወደ ጥቁር ሐዘን የተቀየረበት አስደንጋጭ አደጋ የህይወት አጋርነታቸውን በጋብቻ ያጸኑት መምህር አብርሃም ግዛው እና ባለቤታቸው መምህርት ራሄል አክሊ በሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አልፏል። ረጅም የድካም ዘመኗን በኮሌጅ ምረቃ አጠናቃ የደስታዋ ተካፋይ ከሆነው ባለቤቷ ጋር የየቀኑን ድል አክብረው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ ነበር ይህ ያልታሰበ መቅሰፍት የገጠማቸው። ከቦንጋ ወደ ሺሾ በመጓዝ ላይ የነበረው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በካፋ ዞን ሺሾ እንዴ ወረዳ (ዋና ቦላ ቀበሌ) መንገድ ስቶ ወደ 50 ሜትር ገደል በመግባቱ ጥንዶቹ እዚያው ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል። የወደፊት ህልማቸውንና የትዳር ህይወታቸውን ገና መገንባት በጀመሩበት የምረቃ ሳቅና ጨዋታ በሞላበት በዚያው ቅጽበት የሁለቱም ህይወት በአንድነት ተቀጥፏል። ለሟች ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመዶች እና ለስራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑር።
ምሽቱን በጥያቄ እና መልስ እንቆይ። ለመጠየቅ የምትፈልጉ ሰዎች ጥያቄ መምረጥ ትችላላችሁ። 1) የቤተ ክርስቲያን ታሪክ 2) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት 3) ነገረ ድኅነት 4) ገዳማዊ ሕይወት 5) የቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ ጉባኤያት ተከታታይ አምስት ጥያቄዎችን የመለሰ"ሥላሴ በተዋሕዶ" የተሰኘውን ዳጎስ ያለና እጅግ ጠቃሚ መንፈሳዊ መጽሐፍ ይሸለማል! የመጀመሪያው ጥያቄ አሁን ይጀምራል! ለመሳተፍ ዝግጁ የሆናችሁና ርዕስ መምረጥ የምትፈልጉ በኮመንት (Comment) መስጫው ላይ የርዕሱን ቁጥር በማስቀመጥ ተሳትፎአችሁን አሳውቁ! ለመጠየቅ ይቀላቀሉ 👉https://t.me/Stpoulos
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምሀርት መርሐ-ግብር መሠረት የመጀመሪያው ሳምንት ትምህርታችን የነበረውን ጥልቅና መሠረታዊ የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው ተምረናል። ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው ጽሑፍ (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ኾናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠኑትና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ሳምንት የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው። በዚሁ መሠረት በሚቀጥሉት ሳምንታት የምንማራቸውን ተከታታይ ትምህርቶች በሙሉ እያዘጋጀን በማኅበራችን ይፋዊ የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናል ላይ የምንለቅ መሆኑን እንገልጻለን። እናንተም ይህንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ኾናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ። የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። አቤል ተፈራ በላይ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወልድያ ኢትዮጵያ
እንኳን ለአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሰተ አጽም ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! የቅዱስ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ጸሎት "... አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የመንግስተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ትቼ ወጣሁ ጌታዬ ሆይ እንግዲህ ለችግረኛው ለእኔ ያላንተ ረዳት የለኝም ለደካማው ለኔ ያላንተ የሚያፅናናኝ የለኝም ከመውደቅም ያለንተ የሚያነሳኝ የለኝም ላዘንኩ ለእኔም ካላንተ የሚያረጋጋኝ የለኝም ለደሃው ለእኔ ያለንተ መጠጊያ የለኝም አቤቱ ፊትህን እሻለሁ ያንተን ፊት እሻለሁ ፊትህን ከኔ አትመልስ አምልኮትህን ፈለግኩ አታሳፍረኝ ረዳት ሁነኝ እንጂ አትጣለኝ ..." ገድለ ተክለ ሃይማኖት ም.29 ❤️
እመቤታችን የተወለደችበት መታሰቢያ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ከሞቀው ቤታችን ወጥተን ድንኳን በመጣል ወደ ውጭ እንወጣለን የሚያሳዝነው ነገር ግን ድንኳኖቻችን በዝማሬ መድመቅ ሲገባቸው እኛ ግን የልደቷን ባለቤት በማይመጥን መልኩ የዘፈን ዳንኪራ ቦታ እናደርጋቸዋለን። አካባቢያችሁን ቃኝታችሁ እስቲ ንገሩኝ ተወዳጆች ተሳስቻለሁ ? በየመንደሩ በዚህ የተነሳ ድኅነት የሚገኝባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እና ክብሯ ይጎድፋል። በዓላቶቻችን ሁሉ የጌታን ክብር የመግለጥ አባቶቻችን እስከ ሙሉ መንፈሳዊ ሞገሳቸው ቢሰጡንም እኛ ግን የኃጢአት እና የዓለማዊነት ፍላጎታችን መፈጸሚያ የርኩሰት ሜዳ እያደረግናቸው መሆኑ ሲታይ ያሳዝናል።
ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም። ሉቃስ ፳፬:፭ እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ትንሣኤው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።🙏
ኢየሱስ ቃል በቃል የት ላይ ነው አምላኩኝ ያለው 🤔
"መሬት ረገጥኩሽ መልሼ ቀልሼ፤ ኋላ እታረቃለሁ ሙሉ አካሌን ክሼ።" አለ ባለ ዘለሰኛው! ዘንድሮስ መሬትም ናት እንደ ሰው ከፋችብን💔 በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባን ወረዳ በተከሠተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቍጥር ከ102 በላይ ኾኗል💔 በተለያዩ ገዳማት ያሉ መናንያን መነኰሳትና የአብነት ተማሪዎች እንዲኹም ኦርቶዶክሳዊው የገጠር ማኅበረሰብ በተጠናና በታቀደ መዋቅር በከባድ የጦር መሣሪያ እያለቀ ነው💔 በተፈጥሮም ኾነ በሰው ሠራሽም አደጋ በየቦታው ያረፉ የወገኖቻችንን ነፍስ ይማርልን! ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይስጥልን። (ለእኛ ለተረኞች ደግሞ የንስሓ ጊዜ ያድርግልን!!! የአበውን ቃል አስታውሱ! ጦርነት፣ ረኀብ፣ መቅሠፍት ወረርሽኝ (በሽታ) ገና ወደፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ገና ለቀጣዮቹ 2 ዓመታት ያህል እጅግ እየከፋ እንደሚሔድ አበው የተናገሩትን አንርሳ! መፍትሔው ንስሓ ነው። የምድሩ ቢቀር ከሰማዩ ከቅዱሳኑ ርስት የተለየን እንዳንኾን።)
ልብ ይሰብራል ዛሬ የተፈጸመው ነገር ያሳዝናል አባ አይናለም የወልድያ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ትናት ማታ በሁለት ጥይት ተመተው ተገድለዋል። ማታ በግምት ከ2:30 - 3 ሰዓት ጥይት ተመተው ሰው በሰዓቱ ባለመድረሱ የተነሳ ደማቸው ፈሶ ነፋሳቸው ተለይታ ጠዋት ሬሳቸው ተገኝቷል። የወልድያ ምዕመናን ልብ የሰበረ ጉዳይ ሁኗል።
ቲክቶክ በክርስትና እይታ ክፍል 1 በአቤል ተፈራ የቲክቶከ ታሪክ ልከ እንደ አፕሊኬሽኑ ፈጣንና አስገራሚ ጉዞ የታየበት ነው። ይሄ ታዲያ ለክርስቲያኑ ማኅበረሰብ በረከት ወይስ መርገም ነው ይዞበት የመጣው ? ትምህርቱ ይሄንን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክራል ሌሎች ትምህርቶችን ለማገኘት 👉 https://t.me/Abelltefera
https://youtu.be/0PPcVyf90J8?si=F3iafi1CqrQzc1hH
https://youtu.be/kf33ry7-n6Y?si=zo_303oiGqFh_0Qj
https://youtu.be/M1grpvIG-PQ?si=Gxy9uOx_YAn6RfRA
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи