Estifanos Getahun Info
Статистика- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 21
- Всего постов
- 47
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 51
- 1/48двое суток
- 58
- 1/72трое суток
- 63
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በመሪዎቿ መቀያየር የማይለወጠው ዘመናትን የተሻገረው የግብፅ ሴራ ዓባይ ለሰሜን ምሥራቅ እና ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሕይወት እና የኢኮኖሚ ደም ስር ቢሆንም፣ የዘመናት የጂኦ-ፖለቲካዊ ጦርነት እና የዲፕሎማሲ ፍጥጫ አውድማ መሆኑ አልቀረም:: የውኃው 85 በመቶ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ አንዲት ጠብታ ለማታመነጨው ግብፅ ሁሌም እንደ ትልቅ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት ትታያለች
"ለግብርናው ዘርፍ ወሳኙ ግብዓት ማዳበሪያ በመሆኑ፣ ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችሉ ሥራዎችን እየሠራን ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ ብቻ የሆነው ዋልያ፦ ቁጥሩ እየጨመረ ነው በመላው ዓለም ቢዞር በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብቻ የሚገኘው ዋልያ፣ አሁን ቁጥሩ ከ270 ወደ 306 አድጓል።
видео или голосовое, без подписи
ፑቲን የወታደራዊ ደንብ ልብስ በመልበስ ለምዕራባውያን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላለፉ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የፓሲፊክ ውቅያኖስ የጦር መርከቦች ወታደራዊ ልምምድ አካል በሆነው "ቫርያግ" የጦር መርከብ ላይ ተገኝተው ለምዕራባውያን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጡ። ፑቲን በስፍራው ባደረጉት ንግግር የኔቶ (NATO) በፓሲፊክ ቀጠና ውስጥ ወታደራዊ እንቅስቃሴውን ማሳደግ እና አዳዲስ ጥበቃዎች መመስረት በቀጠናው የግጭት ስጋትን እያበዛው ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ምዕራባውያን አገራት የሩሲያ የንግድ መርከቦችን ለመያዝ ወይም ለመውረስ የሚሞክሩ ከሆነ ሞስኮ ተመጣጣኝ ምላሽ እንደምትሰጥ አስጠንቅቀዋል። ይሁን እንጂ የሩሲያ ምላሽ የግድ ክስተቱ በተከሰተበት ቀጠና ብቻ ላይወሰን እንደሚችል ጠቁመዋል። በሌላ በኩል ፑቲን ሩሲያ ለጃፓን ስጋት እንዳልሆነች እና ምንም ዓይነት የቦታ ይገባኛል ጥያቄ እንደሌላት ገልጸው፣ ሆኖም ቶኪዮ ሩሲያን በወታደራዊ ሰነዶቿ ውስጥ እንደ ዋና ስጋት መፈረጇን ተችተዋል። ከሐምሌ መጨረሻ ጀምሮ በተካሄደው የፓሲፊክ ውቅያኖስ ልምምድ ላይ 60 የጦር እና የሰርጓጅ መርከቦች፣ 30 አውሮፕላኖች እና ከ13,000 በላይ ወታደሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
видео или голосовое, без подписи
"ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ልጠቅልል የሚለውም ሆነ ልገንጠል የሚለው ኢትዮጵያን አላወቃትም፤ መገንጠልም መጠቅለልም አይሰራም፤ መስማማት በትብብር ሁሉም ያለውን ሃብት እያወጣ እንዲለማ አድረጎ መኖር ብቻ ነው የሚያዋጣው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
видео или голосовое, без подписи
እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ ሆን ብላ የሰደድ እሳት እያስነሳች መሆኑን የነፍስ አድን ሰራተኞች ተናገሩ። የነፍስ አድን ሰራተኞች፣ ነዋሪዎች እና የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች እንዳሉት ወታደሮቹ ደኖችን እና ሰብሎችን ለማጥፋት ተቀጣጣይ ቁሶችን እየጣሉ ነው ብለዋል። የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች በቅርብ ሳምንታት የተነሱት እሳቶች የሊባኖስን የተፈጥሮ አካባቢ ዒላማ የማድረግ የረዥም ጊዜ የእስራኤል ልምድ አካል ናቸው ብለዋል። ማክሰኞ ዕለት የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ ከኪያም ውጭ ባለ ጫካ ውስጥ ተቀጣጣይ ቁሶችን በመጣል እሳት አስነስቷል። የነፍስ አድን ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት ሲሞክሩ አንድ ድሮን በአቅራቢያቸው ጥቃት በመፈጸሙ ወደ ኋላ ለማፈግፈግ መገደዳቸውን በናባቲዬ ክልል የሲቪል መከላከያ ኃላፊ የሆኑት ሁሴን ፋኪህ ተናግረዋል። ኃላፊው እንደተናገሩት "ትክክለኛው መረጃ ባይኖረኝም ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆነው መሬት በእሳት ተጎድቷል" ብለዋል ። ከሰኔ 17ቱ የተኩስ አቁም ወዲህ ባሉት ሁለት ወራት የእስራኤል ጦር በመላው ደቡብ ሊባኖስ በተለይም በወይራ ዛፎች እና በእርሻ መሬቶች ላይ እሳት አስነስቷል። ጦሩ ስለ እያንዳንዱ የሰደድ እሳት ክስተቶች አስተያየት እንዲሰጥ ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም ምላሽ አልሰጠም።
видео или голосовое, без подписи
ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም! የህዝባችን የእድሜ ስብጥር እንደሚያመላክተው ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው፣ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለማፅናትም ታላቅ እድል ነው። የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው! የኢትዮጵያ ወጣት የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ ይገኛል። ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ የአሁን ወጣት በልማት ላይ አተኩሯል፣ ድህነትን ተጠይፏል። የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግ ሁላችሁም በንቃት እየተጋን፣ በፍቅር እንድንመላለስ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
የመደመር አንቀጽ “ተስፋ ቢስ ሰው ምኞቱ የመንደሩ አለቃ ከመሆን አያልፍም። የመንደሩ አለቃ መሆን ሲያቅተው ደግሞ የቤተ ክርስቲያኑ አለቃ ለመሆን ይመኛል። ምኞቱ እየጠበበ እንጂ እያሰፋ አይመጣም። ተስፋ በሌለው ምኞትን እያጠበበ ይመጣል። ሆኖም ምኞትን ቢያጠብበውም ያ የጠበበው ምኞት አይሳካም። ምክንያቱም ጠባቧንም ምኞት ለማሳካት ተስፋ ይፈልጋልና። ተስፋ ያለው ሰው ግን ምኞቱም ያድጋል፤ ምኞቱን የማሳካት ዕድሉም ያድጋል። ተስፋ ችግሮችን ሁሉ የመሻገሪያ ብርታትን ይሰጣል። ተስፋ ቆርጦ እጅ መስጠት የለብንም። ‘ኢትዮጵያ፡- አዲስቷ የተስፋ አድማስ’ ስንል የምታድገዋን እና ነገን የምትሆነዋን የምንወዳትን ኢትዮጵያ በምኞታችን አስቀምጠን ነው።” የመደመር መንገድ - ገጽ 360
"ዛሬ የምንኖር ኢትዮጵያውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን ሞተው ያቆሙልንን ሀገር በአንድነትና በፍቅር በመኖር ማስቀጠል አለብን፡፡ ከእነሱ ተምረን ድህነትን፣ መከፋፈልንና ኋላ ቀር አስተሳሰብን አሻፈረኝ በማለት ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ልናሻግር ይገባል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
видео или голосовое, без подписи
በየቀኑ 1,200 ሰዎች ሚሊየነር የሚሆኑባት አገር! በአሜሪካ ውስጥ በየቀኑ 1,200 ሰዎች አዳዲስ ሚሊየነሮች ይሆናሉ። የዩቢኤስ የሀብት ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ አሜሪካ በ2025 ብቻ ከ440,000 በላይ አዳዲስ ሚሊየነሮችን ያፈራች ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተፈጠሩት አዳዲስ ሚሊየነሮች ግማሹን ያህሉን ይሸፍናል። በአሁኑ ወቅት ከ23.6 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሀብት አላቸው፤ ይህም ሀገሪቱን በዓለም አንደኛ ሲያደርጋት፣ ቻይና በ5.3 ሚሊዮን ሚሊየነሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። እነዚህን ሰዎች ሚሊየነር ያደረጋቸው የሚያገኙት ወርሃዊ ደሞዝ ሳይሆን የያዟቸው ንብረቶች ናቸው። ከአሜሪካ የሀብት መጠን ውስጥ 79 በመቶ የሚሆነው ድርሻ የሚገኘው ከአክሲዮንና ከቦንድ ሲሆን፣ ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ ያለው የአክሲዮን ገበያ ለዚህ ሀብት መፈጠር ትልቁን ድርሻ ተወጥቷል። ሆኖም ግን አሳሳቢ ነገር አለ። ከ2020 እስከ 2025 ባሉት ዓመታት የአሜሪካውያን አማካይ ሀብት ወደ 10 በመቶ አድጎ የነበረ ቢሆንም፣ የመካከለኛው ማኅበረሰብ ሀብት ግን ወደ 20 በመቶ ገደማ ቅናሽ አሳይቷል። ይህም የሚያሳየው የሚሊየነሮች ቁጥር መጨመሩ እውነት ቢሆንም፣ የሀብቱ ዕድገት ግን አሁንም በጥቂት ከፍተኛ ሀብታሞች እጅ ላይ ብቻ የተከማቸ መሆኑን ነው።
видео или голосовое, без подписи
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል። የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁለተኛው ዙር ተግባራዊ የሚደረጉ 11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶችን ለመተግበር እየተደረገ ያለውን ዝግጅት የተመለከተ መመሪያ አስተላልፏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፓሊሲ ላይ "የሙያና ቴክኖሎጅ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜያቸው ጋር የተመጣጠነ ሆኖ እንዲሰጥ ይደረጋል" በሚል አቅጣጫ መቀመጡን ያመለክታል። በዚህ መሰረት በየደረጃው የሥራና ተግባር ትምህርት ከሌሎች ትምህርቶች ጋር ተቀናጅቶ እንዲሁም 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ በሚያስችል መልኩ እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል በተለያዩ የሙያ አይነቶች ከቀለም ትምህርታቸው ጎን ለጎን ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ12 የሙያ አይነቶች እየተሰጠ እንደሚገኝም ሰርኩላሩ ያትታል። ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ደግሞ በሁለተኛው ዙር እንዲተገበሩ ለተለዩት 11 የሙያ አይነቶች ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ ትምህርቶች እንዲሁም ለ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችና የመምህር መምሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል። በመሆኑም እነዚህን ተጨማሪ የሙያ አይነቶች ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ለማስጀመር :- • የክልሉ/የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት እና እቅዱን ለማከናወን በጀት በመያዝ የሙያ አይነቶችን በትምህርት ቤት እና በተማሪዎች ደረጃ በማስመረጥ፣ • የየሙያ አይነቱ መምህራንን በመቅጠር፣ • የመማሪያ ማስተማሪያ ግብዓት በሂደት በማሟላት፣ • መምህራንን እና የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠን እና የህዝብ ንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን ትምህርቱን ለማስጀመር ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል። የሙያ አይነቶቹ ፦ - ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ፣ - አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ - አልባሳት ቴክኖሎጂ፣ - ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት፣ - ቧንቧ ስራ፣ - ሶፍትዌር ማበልጸግ፣ - ሰብል አመራረት፣ - ጤና ክብካቤ አገልግሎት፣ - ሆቴል አገልግሎት፣ - ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት እንዲሁም ምግብ ዝግጅት ናቸው።
видео или голосовое, без подписи
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ዙሪያ የተዘጋጀውን የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ይጠብቁን