Circle View- ሰርክል
Статистика- Последний пост
- 1 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 46
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኤርትራ መንግሥት ዜጎች በእጃቸው ያለ ገንዘብን በአንድ ወር ወደ ባንክ እንዲያስገቡ አዘዘ የኤርትራ መንግሥት ዜጎቹ በእጃቸው ላይ ያለ ገንዘብን በሙሉ እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ ወደ ባንክ እንዲያስገቡ ጥብቅ ማሳሰቢያ አወጣ። የኤርትራ ማዕከላዊ ባንክ ማክሰኞ ዕለት ባወጣው ጥብቅ ማሳሰቢያ፤ በአገሪቱ ውስጥ በግለሰቦች እና በተቋማት እጅ የሚገኝ የአገሪቱ መገበያያ ገንዘብ (ናቅፋ) በሙሉ ዛሬ የጀመረው የአውሮፓውያን ሐምሌ ወር መጠናቀቂያ ድረስ ወደ ባንክ እንዲገባ አዝዟል።
የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደሚከስሱ ሲናገሩ የነበሩት የቦንድ አበዳሪዎች እንዴት ከስምምነት ደረሱ? ከአንድ ወር በፊት ለኢትዮጵያ ገንዘብ ያበደሩ ባለሀብቶች የአገሪቱን መንግሥት እንደሚከስሱ አስታውቀው ነበር። ትናንት ሰኞ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም. ግን የገንዘብ ሚኒስቴር ከባለሀብቶቹ ጋር የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት መደረሱን አስታውቋል።
አዲሱ የሌብነት ስልት‼️ በቴክኖሎጂ የታገዘው አዲሱ የሌብነት ስልት፦ የሐሰት የዲጂታል ክፍያ ደረሰኞች ነጋዴዎችን እንዴት እያከሠሩ ነው? በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትና የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ አማራጮች በከፍተኛ ፍጥነት መስፋፋታቸውን ተከትሎ፣ አጭበርባሪዎች የቴክኖሎጂ ክፍተቶችን በመጠቀም አዳዲስ የሌብነት ስልቶችን እየቀየሱ ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት በርካታ ነጋዴዎችንና የንግድ ተቋማትን ለአሳሳቢ ኪሳራ እየዳረገ ያለው ዋነኛው መንገድ፣ የተለያዩ የባንክና የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎችን የክፍያ ማረጋገጫ ምስሎችንና የጽሑፍ መልዕክቶችን የሚመስሉ የሐሰት ሶፍትዌሮችን መጠቀም ነው። እነዚህ መተግበሪያዎች በአጠቃላይ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቱን ደኅንነት አደጋ ላይ የጣሉ ሲሆን፣ ኅብረተሰቡ ስለ አሠራራቸው በቂ ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎች ያሳስባሉ። እነዚህ "Fake Payment Receipt Generators" በመባል የሚታወቁ የሐሰት ሶፍትዌሮች በሁለት ዋና ዋና መንገዶች እንደሚሠሩ ይነገራል። የመጀመሪያው ዘዴ ትክክለኛ የዲጂታል ክፍያ መተግበሪያዎችን ገጽታ ሙሉ በሙሉ በመቅዳት የተዘጋጁ የክሎን (Clone) መተግበሪያዎች ናቸው። አጭበርባሪዎች በእነዚህ መተግበሪያዎች ውስጥ የተከፋዩን ስም፣ የገንዘብ መጠን፣ የተከናወነበትን ቀንና የግብይት መለኪያ ቁጥር (Transaction ID) ራሳቸው በመሙላት፣ ገንዘቡ በስኬት እንደተላለፈ የሚያሳይ የተደናገረ የሐሰት ምስል በሰከንዶች ውስጥ ይፈጥራሉ። ይህንን ምስል ለነጋዴው በማሳየትም ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ያለምንም ክፍያ በመውሰድ ያጭበረብራሉ። ሁለተኛውና ይበልጥ የተራቀቀው ዘዴ ደግሞ የሐሰት የጽሑፍ መልዕክት (SMS Spoofing) የሚባለው የቴክኖሎጂ አሠራር ነው። በዚህ መንገድ አጭበርባሪዎች የፋይናንስ ተቋማትን ይፋዊ የላኪ ስም በማስመስል፣ የገንዘብ መግባት መልዕክት በቀጥታ ወደ ተጎጂው ስልክ እንዲደርስ ያደርጋሉ። ተጎጂው ነጋዴ መልዕክቱ የመጣው ከትክክለኛው የጽሑፍ መስመር መስሎ ስለሚታየውና ላኪው ላይ የታወቁ ተቋማት ስም ተጽፎ ስለሚመለከት፣ የሂሳብ ቀሪውን ሳያረጋግጥ በሐሰተኛው መልዕክት ብቻ በመተማመን በቀላሉ ይሸወዳል። እነዚህ መተግበሪያዎች ሙሉ በሙሉ ሕገ-ወጥ በመሆናቸው በይፋዊ መተግበሪያ መደብሮች ላይ በፍጹም አይገኙም። ይልቁንም አጭበርባሪዎች እነዚህን አደገኛ የሶፍትዌር ፋይሎች በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ቻናሎች እና የደኅንነት ቁጥጥር በሌላቸው የድረ-ገጽ ማውረጃዎች ላይ በድብቅ እርስ በርስ እየተቀባበሉ ያሰራጯቸዋል። ይህ ዓይነቱ አሠራር የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ሲሆን፣ መተግበሪያዎቹን መያዝም ሆነ መጠቀም ከፍተኛ የወንጀል ድርጊት ነው። ይህንን በቴክኖሎጂ የታገዘ ማጭበርበር ለመከላከልና ራስን ከኪሳራ ለመጠበቅ፣ ነጋዴዎች ከደንበኞች የሚመጡላቸውን ስክሪንሾቶች (Screenshots) ወይም በስልካቸው ላይ የሚደርሱ የጽሑፍ መልዕክቶችን ብቻ አይቶ በፍጹም መተማመን የለባቸውም። የፋይናንስ ተቋማትና የደኅንነት ባለሙያዎች በተደጋጋሚ እንደሚያሳስቡት፣ አስተማማኙ የመከላከያ መንገድ የራስን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመክፈት ወይም በይፋዊ የአጭር ቁጥሮች (USSD Codes) አማካኝነት የሂሳብ ሒሳቡን በቀጥታና በእርግጠኝነት ማረጋገጥ ብቻ ነው። ሰርክል ቪውን ሰብስክራይብ በማድረግ አስተማሪና አነጋገሪ የኾኑ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ • መረጃዎችን ተቋደሱ https://t.me/mneny1 http://www.youtube.com/@circleview-%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8A%AD%E1%88%8D
видео или голосовое, без подписи
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብፁዕ አባ ሄኖክ አባታዊ ጥሪ አቀረቡ በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ ከተሞች በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተቀሰቀሱ ወቅታዊ ውጥረቶችና በሀገሪቱ ዜጎች በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ምክንያት ከፍተኛ ሥጋት ውስጥ መውደቃቸውን ተከትሎ፣ የደቡብ አፍሪካና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባ ሄኖክ አስቸኳይ የአባታዊ ጥንቃቄና የጽናት መልዕክት አስተላለፉ። በደቡብ አፍሪካ በተፈጠሩ ወቅታዊ ውጥረቶች እና ከሀገር እንድትወጡ በሚሉ ሰልፎች ምክንያት ወገኖቻችን በከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ጫና ውስጥ እንዳሉ እንረዳለን ያሉት ሊቀ ጳጳሱ፣ ተፈታኝ በሆነው ማዕበል ውስጥ የማይናወጥ መጠጊያ በሆነው በእግዚአብሔር ቃል እንዲጸኑና ልባቸው በፍርሃት እንዳይናወጥ ጥሪ አቅርበዋል። ወቅቱ ወንድም ወንድሙን ለሞት አሳልፎ የሚሰጥበት የፈተና ጊዜ መሆኑን በማስታወስ፣ ምዕመናን በመንፈሳዊ ጥንካሬና በጸሎት ወደ ፈጣሪ እንዲጠጉ አሳስበዋል። ብፁዕ አባ ሄኖክ በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖች አሁን ላይ ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን የሚገቡ አራት ዋና ዋና የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንደሚከተለው አደራ ብለዋል፦ ውጥረቶችና ሰልፎች በሚበራከቱባቸው አካባቢዎችና የንግድ ማዕከላት ያለ በቂ ምክንያት ከመንቀሳቀስ መቆጠብና በተለይም በምሽት ሰዓት እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት። የአካባቢውን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ፣ ከኤምባሲም ሆነ ከማኅበረሰብ መሪዎች የሚወጡ ይፋዊ መግለጫዎችንና የደኅንነት ማስጠንቀቂያዎችን በንቃት መከታተል። ከሌሎች ወገኖችና ከቅርብ ጓደኞች ጋር ያለውን የመረጃ ልውውጥ ማጠናከርና ድንገተኛ አደጋ ቢከሰት እንኳ በፍጥነት የሚደርስ የሰንሰለት መረጃዎችን መዘርጋት። በማኅበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ በአካል ከሚደረጉ አላስፈላጊ ክርክሮችና ግጭትን ሊቀሰቅሱ ከሚችሉ አነቃቂ ሁኔታዎች ራስን ማራቅና በትዕግሥት መጠበቅ። ሊቀ ጳጳሱ በደቡብ አፍሪካና በምዕራብ አፍሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ያስተላለፉትን መልዕክት ሲያጠቃልሉ፣ እግዚአብሔር መከራውን አሻግሮ የፀጥታና የማረፍ ጊዜ እንዲሰጥ በመጸለይ ኢትዮጵያን፣ ደቡብ አፍሪካንና ምዕራብ አፍሪካን ባርከዋል። Fast Mereja.
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የህወሓት ታጣቂዎች በአፋር አብአላ አካባቢ በፈፀሙት ድንገተኛ የከባድ መሣሪያ ጥቃት 16 ግመሎች ተገደሉ። በአፋር ክልል አብአላ ከተማ አስተዳደር ሙርጋ ቀበሌ በ“አሳልጌ” በተባለ አካባቢ ላይ የህወሓት ታጣቂዎች ለሶስት ቀናት የተከታታይ የከባድ መሣሪያ ተኩስ መፈፀሙን የአካባቢው ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን ጥቃቱ በምሽት 11 ሰዓት አካባቢ የተፈጸመ ሲሆን በዚህም 16 ግመሎች መገደላቸውን እና 4 ግመሎች እስካሁን ድረስ አለመገኘታቸውን ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፣ ጥቃቱ ሰዎችና እንስሳት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ የተሰነዘረ ሲሆን በአካባቢው ስጋትና ውጥረት ፈጥሯል። ሰርክል ቪውን ሰብስክራይብ በማድረግ አስተማሪና አነጋገሪ የኾኑ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ • መረጃዎችን ተቋደሱ https://t.me/mneny1 http://www.youtube.com/@circleview-%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8A%AD%E1%88%8D
ውሻዉን ያልገደለ ግለሰብ በ50000 ብር እና በእስራት እንዲቀጣ ታውጇል በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሆሳና ከተማ እያንዳንዱ ግለሰብ በቤቱ ያለዉን ዉሻ አውጥቶ እንዲገድል በታወጀው መሰረት ዉሻ ያላቸው ግለሰቦች ዉሻቸውን ገመድ በማጥለቅ በንንጨት ላይ በማንጠልጠል ዉሾችን እየገደሉ ይገኛሉ። በከተማው ከሰሞኑ በውሻ ምክንያት በሽታ ተከስቷል የተባለ ሲሆን ይህ የውሻ ግድያ ዘመቻ የተጀመረው አንድ ውሻ የ13 አመት ልጅ ነክሳው ከሞተ በኋላ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል። (አዩዘሀበሻ) ሰርክል ቪውን ሰብስክራይብ በማድረግ አስተማሪና አነጋገሪ የኾኑ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ • መረጃዎችን ተቋደሱ https://t.me/mneny1 http://www.youtube.com/@circleview-%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8A%AD%E1%88%8D
በኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በመታችው ቬንዝዌላ የሟቾች ቁጥር 589 ደረሰ፤ የተጎዱትም ወደ 2,980 ቁጥራቸው ከፍ ብሏል። አደጋው ከደረሰ በ34 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው ርብርብም በርካቶችንም በሕይወት እያሉ ማትረፍ መቻሉን የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ዴሊሲ ሮድርገስ ተናግረዋል። ረቡዕ ምሽቱን በ39 ደቂቃዎች ልዩነት በተከታታይ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ መላ ሀገሪቱን አናውጧል። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በካሬቢያን የባሕር ዳርቻ አካባቢ የሚገኘው የ ላ ጓይራ ግዛት ሲሆን ዋና ከተማ ካራካስ እና በሌሎች ግዛቶችም ሕንጻዎች ተደርምሰዋል ቤቶች እንዳልነበሩ ሆነዋል። የሕይወት አድን ሥራው ቀጥሏል፤ በፍርስራሾቹ ሥር መውጫ አጥተው የሚገኙ መኖራቸውን በመገመትም ባለሥልጣናት የሟቾችና የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። ዓለም አቀፍ የእርዳታ ቡድኖች ወደ ደቡባዊ አሜሪካዊቱ ሀገር እየገቡ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለም የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ሲከሰት ቬንዝዌላ ውስጥ የነበሩ የሌላ ሃገራት ዜጎችን ፍለጋውም ቀጥሏል።
17 ፍቅረኞች በአንድ አልጋ – የመኪና አደጋ ያጋለጠው ቻይናዊ! በፈረንጆቹ 2015 በቻይና ሁናን ግዛት የሚኖረው ሚስተር ዩዋን የገጠመው ድንገተኛ የመኪና አደጋ፣ ለዓመታት በምስጢር የያዘውን አስገራሚ ጉድ በአደባባይ አጋልጦበታል። አደጋውን የሰሙ 17 ቆነጃጅት ታካሚውን ለመጠየቅ በአንድ ጊዜ ሆስፒታል ሲከሰቱ፣ እያንዳንዳቸው እራሳቸውን የዩዋን "ብቸኛ የሕይወት አጋር" አድርገው የሚያስቡና አንዳንዶቹም ለጋብቻ የደረሱ ፍቅረኛሞቹ ሆነው ተገኙ። እርስ በርሳቸው የማይተዋወቁት እነዚህ ሴቶች እውነታውን ሲረዱ የሆስፒታሉ ክፍል በድንጋጤና በከፍተኛ ቁጣ ተናውጦ ነበር። የፊልም ትዕይንት የሚመስለው ይህ ክስተት በሐኪሞችና በነርሶች ዘንድም ትልቅ መደነቅን ፈጥሯል። ይህ በአንድ ጀንበር የፈረሰው የክህደት ማማ ለዩዋን የአካል ጉዳት ብቻ ሳይሆን የፍቅር ህይወት ቀውስም አስከትሎበታል። ታሪኩም በወቅቱ በዓለም ዙሪያ በከፍተኛ ጉጉት የተነበበ «የዓመቱ አስገራሚ የክህደት ታሪክ» ሆኖ ተመዝግቧል።
የትግራይ ክልል ምክር ቤት የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትን የያዘው አወዛጋቢ አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን አዘዘ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ወደ ሥራ የመለሰው የትግራይ ክልል ምክር ቤት የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትን እና በሞት የሚያስቀጡ ድንጋጌዎችን የያዘው አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጠ
የተፈናቃዮቹ መሬት ለሚሊሻ ተሰጠ‼️ ከምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው አልተመለሱም በሚል መሬታቸው ለሚሊሻ መስጠት መጀመሩ ተገለፀ። ተፈናቃዮቹ ካልተመለሳችሁ መሬታቸሁ ለአካባቢው ሚሊሻ ሊሰጥ መሆኑን ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልፀው ነበር። ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ተፈናቅለው በወሎ፣ ጃራ መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች ለቅቀው ወደ ወጡበት አካባቢ ባለመመለሳቸው መሬታቸውን ለሚሊሻና ኮሬ ነጌኛ ለተባለው ኃይል እንዲሁም ለስራአጥ ወጣቶች ማከፋፈል መጀመሩን ገልፀዋል። እነዚህ ተፈናቃዮች በአካባቢው በነበረው ጥቃት ሸሽተው ወደ የወጡ ሲሆን ወደ ቀያቸው ለመመለስ አሁንም ስጋት እንዳለባቸው ይገልፃሉ። አ ዩ ዘሐበሻ
ሊቢያ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያ እና የሱዳን ዜጎች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ ከለከለች የሊቢያን ምሥራቃዊ ክፍልን የሚቆታጠሩት ባለሥልጣናት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳን እና የሶማሊያ ዜጎች ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ የሚከለክል ዕግድ ጣሉ። ከፊሉን የሊቢያ ግዛትን የሚቆጣጠሩት በኻሊፋ ሃፍታር የሚመሩት አስተዳዳሪዎች የአራቱን የአፍሪካ ቀንድ አገራት ዜጎች እንዳይገቡ የከለከሉት በሊቢያ የባሕር ዳርቻ በኩል በሕገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚጓዙ ስደተኞችን ለማስቆም መሆኑ ተነግሯል።
የመንግሥት አልባነት አስደንጋጭ ያልተለመደ የእገታ ወንጀል በመሐል አዲስ አበባ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እምብርት ውስጥ በሚገኘው የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጎሮ አትሌቶች መንደር፣ በሀገሪቱ እምብዛም ያልተለመደና እጅግ አስደንጋጭ የዕገታ ወንጀል መፈጸሙ ተሰምቷል። ሦስት የፓኪስታን ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በተከራዩት የመኖሪያ ቤት ውስጥ የህንድና የባንግላዴሽ ዜጎችን በገመድ በማሰርና አፋቸውን በፕላስተር በማፈን፣ ከ15 እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ከፍተኛ የገንዘብ ማገቻ (ራንሰም) ሲጠይቁና አሰቃቂ ድብደባ ሲፈጽሙባቸው ከርመዋል። ይባስ ብሎም በቅርቡ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ አራት የህንድ ቱሪስቶችን ጭምር በማሰርና በመደብደብ፣ ከቤተሰቦቻቸው የህንድ ሩፒ እንዲያስመጡ ሲያስገድዱ እንደነበር በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ባደረጉት ቃል ተጋልጧል። ይህ በቅንጦት መንደር ውስጥ የተሸሸገው ዘግናኝ ወንጀል ሊጋለጥ የቻለው በአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ንቃትና ጥቆማ ሲሆን፣ ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ለወንጀል ማደናገሪያነት ከተጠቀሙባቸው ቢላዋዎች፣ ገመዶች፣ ፕላስተሮችና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ጋር እጅ ከፍንጅ ይዟቸዋል። ይህ ዓይነቱ በተደራጁ የውጭ ዜጎች የሚፈጸም አደገኛ የዕገታ ወንጀል በሀገሪቱ የቱሪዝም ገጽታና ደህንነት ላይ አዲስ ስጋት የሚደቅን በመሆኑ፣ ማኅበረሰቡ በአካባቢው የሚታዩ ማናቸውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን በከፍተኛ ንቃት ሊከታተልና ሊያጋልጥ እንደሚገባ ትልቅ ማሳያ ሆኗል። አዩዘሀበሻ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፓርቲ በምርጫው ማሸነፍ እና የአዲስ ግጭት ስጋት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም. በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፓርቲ ብልጽግና አብዛኛውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን በማሸነፍ የበላይነትን ይዟል። ይህም ማለት ዐቢይ ለሁለተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን በመሪነት መቀጠላቸውን የሚያረገግጥ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥልጣን ላይ መዝለቅ በተለይ በምርጫው ባልተሳተፈችው ትግራይ ውስጥ ከህወሓት ጋር ለተፈጠረው ውጥረት ምን ዓይነት መፍትሄ ያስገኝ ይሆን? ሰርክል ቪውን ሰብስክራይብ በማድረግ አስተማሪና አነጋገሪ የኾኑ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ • መረጃዎችን ተቋደሱ https://t.me/mneny1 http://www.youtube.com/@circleview-%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8A%AD%E1%88%8D
ብልፅግና 438 ወንበሮችን አሸነፍኩ ሲል ድራማውን ቋጨ አጠቃላይ የምርጫ ውጤት (ፓርላማ) 1. አዲስ አበባ ከተማ (23 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 20 መቀመጫዎች - ኢዜማ 2 መቀመጫዎች - የግል ዕጩ 1 መቀመጫ 2. አፋር ክልል (8 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 7 መቀመጫዎች - የአፋር ህዝብ ፓርቲ 1 መቀመጫ 3. አማራ ክልል (ምርጫ የተካሄደባቸው 130 የፓርላማ መቀመጫዎች ) - ብልጽግና 117 መቀመጫዎች - አብን 6 መቀመጫዎች - አዲህን 3 መቀመጫዎች - አርጎባ አንድነት ጀበርቲ ፓርቲ 1 መቀመጫ - ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 1 መቀመጫ - ኢዜማ 1 መቀመጫ - ነጻነትና እኩልነት 1 መቀመጫ 4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ (9 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 8 መቀመጫዎች - ጉሙዝ ብሔራዊ ንቅናቄ 1 መቀመጫ 5. ድሬዳዋ (2 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 2 መቀመጫዎች 6. ጋምቤላ ክልል (3 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 3 መቀመጫዎች 7. ኦሮሚያ ክልል (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 173 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና 167 መቀመጫዎች - 5 የግል ዕጩዎች 5 መቀመጫዎች - አዲስ ትውልድ ፓርቲ 1 መቀመጫ 8. ሐረሪ ክልል (2 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 2 መቀመጫዎች 9. ሲዳማ ክልል (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 16 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 13 መቀመጫዎች አሸንፏል - መድረክ 3 መቀመጫዎች 10. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (20 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 17 መቀመጫዎች - ኢዜማ 1 መቀመጫ - ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ 1 መቀመጫ - ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት 1መቀመጫ 11. ደቡብ ኢትዮጵያ (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 45 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 35 መቀመጫዎች - ኢዜማ 7 መቀመጫዎች - የጌድዮ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 1 መቀመጫ - የወላይታ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ 1 መቀመጫ - የግል እጩ 1 መቀመጫ 12. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ (ምርጫ ውጤት ይፋ ከተገለጸበት 33 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልጽግና ፓርቲ 28 መቀመጫዎች - ኢዜማ 2 መቀመጫዎች - የግል ዕጩ 1 መቀመጫ - ትብብር ለኢትዮጵያ 1 መቀመጫ - ነጻነትና እኩልነት 1 መቀመጫ 13. ሶማሌ ክልል (22 የፓርላማ መቀመጫዎች) - ብልፅግና ፓርቲ 19 መቀመጫዎች - የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር 1 መቀመጫ - ሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ 1 መቀመጫ - ህብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት ፓርቲ 1 መቀመጫ ሰርክል ቪውን ሰብስክራይብ በማድረግ አስተማሪና አነጋገሪ የኾኑ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ • መረጃዎችን ተቋደሱ https://t.me/mneny1 http://www.youtube.com/@circleview-%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8A%AD%E1%88%8D
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи