ሄላንሳን
Статистикаይህ ኦርቶዶክሳዊ ስብከቶችንና ጥበባዊ ጽሑፎችን የሚያገኙበት ምኅላፍ (ቻናል) ነው። ይቀላቀሉ! ያተርፋሉ! #ሄላንሳን ማለት #የክብር ልብስ ማለት ነው። በቃሉ ጸንተን የክብር ልብስን ለመደረብ ያብቃን። join us @helansane https://telegram.me/helansane
- Последний пост
- 14 нояб. 2024 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🤑💵 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር የምትፈልጉ የሚገርም የ Forex ቻናል ያውቃሉ❓ 💶 𝗖𝗶𝘁𝘆 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 💶 @City_Forex_Ethiopia ይባላል ። ተመዝገባችሁ መማር የምትፈልጉ አናግሯቸው እስከ 𝟰𝟬% Discount የሚደርስ ቅናሽ አድርገዋል ! ☎️ +251977338586 🇪🇹 ☎️ +251977338586 🇪🇹 ይህን ይጫኑት ይህን ይጫኑት ይህን ይጫኑት 👇👇 ይህን ተጭነው መመዝገብ ይችላሉ !👇👇 ❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎ ❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎ ❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎ ❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎ 💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸💸 👆 ይህን ይጫኑት ይህን ይጫኑት ይህን ይጫኑት 👆 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 🇹 🇷 🇦 🇩 🇮 🇳 🇬 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 🇹 🇷 🇦 🇩 🇮 🇳 🇬 🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹 ➕ 👇 ምርጥ ምርጥ ቻናሎችን ከፈረጉ ከስር ያለውን ይጫኑ 👇
https://t.me/+29L4a2JccSUyOGY0
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን 👉 ከምኩራብህ ግባ ! 👈 ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ #ከምኩራብ ግባ! በሚል ርዕስ እግዚአብሔር አምላክ ያስተምረናል።በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምዕሮ ሦስት ነገሮች ቤተክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ። #ህንጻ ቤተክርስቲያኑ #የክርስቲያን ምዕመናን ህብረት እንዲሁም ደግሞ #የእኛ የገዛ አካላችን ቤተክርስቲያን ይባላል። ስለዚህ የእኛን ቤተመቅደስ(ቤተክርስቲያን) ወይም ምኩራብ እንዴት አድርገን እናቅናት? ፈጽመን እናሰናዳትና የምኩራባችንን አለቃ ና ግባ!!! እንበለው። (🙏 በፍጹም ትጋት እስከ ፍጻሜው ጸንታችሁ አንብቡ🙏 ) @helansane 👉 አባታችን ባሕታዊው ቴዎፋን የተናገሩትን ነገር መሠረት አድርገን ወደ እኔና እናንተ ቤተመቅደስ እናምራ። #የሰው ነፍስን በንጉሥ የሚመስሉት ሲሆን ሥጋውን ደግሞ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ይመስሉታል። ይህ ቤተ መንግሥት #አምስት መስኮቶች አንድ በር አለው። እነዚህ አምስት መስኮቶች አምስቱ የስሜት ሕዋሳት ናቸው። በሩ ደግሞ #አእምሮ ነው። ታድያ የእኛ ቤተመቅደስም አወቃቀሩ እንዲኹ ነው። #በር በተሰኘው አእምሮአችን ቅድሚያ ማንን ይሆን አስገብተን ከውስጣችን ያነገስነው ንጉሥ ? በውስጣችን ላነገስነው ንጉሥ ምን ይሆን አምስቱን መስኮቶች ከፍተን ከውጪ ልንቀበል የከጀልነው? 👉 እኛ ደካሞች ሁለት ንጉሦችን በአንድ ቤተ መንግሥታችን አንግሰን ግራ እየተጋባን አለን። #ዘለዓለማዊውን ንጉሥ ክርስቶስን በአእምሮአችን ዙፋን አስቀምጠን በጎን ደግሞ የዚህች የከንቱ ዓለም ገዢ (የክፋት ሃሳቦች ሁሉ ንጉሥ) የሆነውን የዲያብሎስን #ሃሳብ በውስጣችን ጨምረን እያነገስን እንገኛለን። ምክንያቱም ደግሞ እኛ በምንውልባቸው ቦታዎች መስኮት በተባሉት የስሜት ሕዋሶቻችን ፊት ለፊት የኃጥአት ነጋዴ ዲያብሎስ ልዩ ልዩ ልምምዶችንና ነፍስን የሚያስደስቱ ስሜቶችን ያመጣል። በዚህም የተነሳ #ክርስቶስን በቅጡ ያላነገስንባት አእምሮ ከመስኮቱ ማይረባትን ሁሉ ትሸምታለች። መቼም ሁለት ንጉሥ በአንድ ቤተ መንግሥት አንግሳ እንደማትኖር ዘለዓለም እንደማትጸና ታውቃለች። 👉 አሁን ከምኩራባችን (ከቤተመቅደሳችን) ቅድሚያ እኛ ገብተን ውስጡዋን በመስኮት በኩል በምንቀበላቸው ከሄላንሳን ማዕድ ከምንሸምታቸው የቅዱሳን አባቶች ምክርና ተግጻጾች እናዘጋጃትና የምኩራባችንን አለቃ #ከምቡራብህ ግባ! እንለው ዘንድ እንውጣ።(#የምኩራብ አለቃ ሉቃ 13፥14) ኤርምያስ በትንቢቱ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል። (9፥21) ብሎ እንደተናገረ የዘለዓለማዊ ሞት ምክንያቶችን በስሜት ሕዋሶቻችን ወደ ነፍሳችን ከምናስገባ ይልቅ እውነተኛ ብርሃን የሆነውን ሕይወትና መንፈስ የሆነው የክርስቶስን ቃል እናስገባ ዘንድ እንዘጋጅ። ✍ ፥- ዓይናችንን መቆጣጠር ቤተ መቅደሳችንን በብርሃን ሆነን ለማስተካከል ተቀዳሚው ነገር ዓይናችንን መቆጣጠር ነው። በማቴ 6፥22-23 < #የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል። ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል።> በእዚህች አይን በተባለችው መስኮት ከፍተህ የምታስገባው ነገር ጨለማ ብቻ ከሆነብህ መክፈቻ እንዳላት ሁሉ መዝጊያም አላችና ዝጋት። በማቴ ላይ #ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት ሙሉ መቅደስህን ጨለማ ከምታደርግብክ አንድም በሲዖል እሳት ከምትማግድህ ዛሬ ዝጋት ጠርቅማት ሲል ነው። (#ቢቻልህስ በእያንዳንዱ ሰውና በእያንዳንዱ ነገር ውስጥ አምላክን መፈለግና ማየት ልመድ ተለማመድ። ) ✍ ፥- ጆሮን መቆጣጠር የጆሮአችን ዋነኛ ጠላቶች ዘፈን ስድብና ነቀፋን የተሞሎ ግጥሞች ቀልዶች ወሬዎች ናቸው።ሁሉም ከጆሮአችን አልፈው ዓይኖቻችንን በፍትወታዊ ትርዒቶታቸውም ጭምር ያሳድፋብናል። አልፎም ፍጹም ጥፋትን ያስከትሉብናልና ስለዚህ ቅድሚያ ምንሰማውን መምረጥን አስከትለን ደግሞ ፍጹም ወደ መተው ማደግ አለብን። ወደ ቤተ ክርስቲያን ስታመሩ ድንገት የሰማችኹት ዘፈን ቤተ ክርስቲያን ደርሳችኹ እንኳን እየጸለያችኹ በውስጣችኹ እንደሚመጣ አስተውሉ። ዳግመኛም #ሽንገላን መቀበል ኃጢአት ነው። ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ ወዮላችሁ። (ሉቃ 6፥26 ት.ዳን 11፥21-34 ተመልከቱ) (#ቢቻልህስ አሉባልታ/ሐሜትን/ ከመስማት መቆጠንብ ልምድ አድርግ! ያን ጊዜ ተናጋሪው ይጠፋልና።) ✍ ፥- ምላስን መቆጣጠር በምላሳችን #ጥምር ስህተቶችን (ኃጥያቶችን) ነው ምንሰራው ይበልጥ እንጠንቀቅ በነገሮች ሁሉ እናስተውል። እናታችን ሔዋንን አንዴ ብቻ ዕፀ በለስ በመቅመሷ ምን ያክል ክፋት ውድመትን አስከትሏል። የዓለም ከንቱ የሆነውን ነገር ሁሉ #አታጣጥም ማንኛውንም ምግብ ማጣጣምን ለምላስህ አስለምድ ነገር ግን ወሬን ማስለመድ ግን ፈጹሞ አቁም። <<እኔ እላችኃለሁ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል።ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።(ማቴ 12፥36) >> 👉 ከአበው ቅዱሳን መካከል አንዱ የማውራት ፍላጎት ሲፈትነው በአፋ ውስጥ ጠጠሮችን እስከመጨመር ደርሶአል። ✍ ፥- አፍንጫን መቆጣጠር በምናሸተው ነገር የፍትወት ሐሳቦችንና ስሜቶችን ሊያነቃቃ ይችላል።ጥሩ አሽተን ምንፈጽማቸው ከንቱ ስሜቶች አልፈው በሽቱ ፈንታ ግማት እንዳይሆንባችሁ ተጠንቀቁ። (ኢሳ 3፥24) የሚያውድህ ሽታ ወደ ዝሙት ሐሳብ ከመራህ እየተመኘኸው ያለኸው ሥጋ ኢሳይያስ እንዳለው እንደሚበሰብስና ወደ ከፋ ሽታ እንደሚለውጥ አስታውስ። ይልቅ አንተ ዘወትር የቅዱሳንን መዓዛ ለማሽተት ከእቤትህ ውጣ መስኮትህንም ክፈት። (#በመንገድ ሳለህ በጎ መዓዛ አፍንጫህን ባወደው ጊዜ ልዩ መዓዛ ባለው ውድ ሽቱ ጌታዋን የቀባችውን ማርያምን አስባት።<ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ> ዮሐ 12፥3 ✍ ፥- የምንነካውን ነገር መቆጣጠር እግዚአብሔርም አለ፥- #እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ #አትንኩትም። ስለዚህ ለመውደቅዋ ምክንያት ቀዳሚው ነገር መንካትዋ እንደሆነም ተመልከት። በመንካት የሚሰማን ስሜት ቢያስደስትም ኅሊናችንን ግን ወዳልተቀደሱ ሃሳቦች መምራቱ አይቀርምና እንጠንቀቅ።(በጾታዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጡኑ ተጠንቀቁ)። ቅዱስ ይሁዳም በመልዕክቱ ላይ 1፥23 #አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። ይህም ማለት እርቃንን ከሚያሳዩ ከሚያጎሉ ልብሶች ፍላጎትና ንክኪም ፈድማችሁ ራቁ ተጠበቁም። እርሱን አመንዝራዎች እርቃናቸውንና ኅፍረታቸውን ለማሳየት ያደርጉትማል ኃጥያትንም ይፈጽሙበታልና እናንተ ግን መልካሙን ልብስ ተሸለሙ። መቅደሳችሁን ውስጡን እንዳሳመራችሁት ሁሉ ገጽታውም ፍጹም ያማረና በቅዱሳን ዘንድም የተወደደ ወደ መልካም ሃሳብ ብቻ የሚስብ ይሁን ዘንድ ተሰሩ። @helansane ውድ ቤተሰቦቻን አሁን ቅድሚያ ወደ ምኩራባችን ገብተን ውስጡን አስተካክለን የልቡናችንን ወጣ ገባ(#በውስጤ እንዳላኖርክ የልቤ ግርግዳዎች ይጎረብጡሃል) ብለው እንደተናገሩ ቅዱሳን አባቶቻችን እኛም ይህን አባጣ ጎርባጣችንን አቅንተን የመስኮቶቻችንን አከፋፈት አስተካክለን እደ አእምሮአችንን አዘጋጅተን #ከገባ ላናስወጣው አንተ የምኩራባችን አለቃ ንጉሥ ሆይ ግባ!!! እንለው ዘንድ ዛሬ ከኃጥአት ወጥመድ እንወጣ!!! 🙏ሳምንቱን የሰላም የፍቅር የጤና ያድርግልን።🙏 ሼር በማድረግ ማካፈል የዘወትር ተግባራችሁ ይሁን። ።ቸር ያቆየን።
https://youtu.be/7vncH51xlpk
እንኳን ደስ አላችሁ ውድ የበገና ቤተሰቦቼ እንደምን ናችሁ? አዲስ የበገና ትምህርት ቤት እነሆ ተከፈተ ውዳሴ በተሰኘ ስያሜ ከካህናት አባቶችና ከወረዳ ቤተ ክህነት በማናገር ስመ ስያሜውንም በካህናት አባቶች ምርጫ በመድኃኔዓለም ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ተከፈተ በቅርብ ወራት በካቴድራሉ ህንጻ ላይ መሸጫና ማምረቻን በማዘጋጀት ላይም እንገኛለን:: ከዚህ ቀድሞ በበገና ትምህርት የሚታወቁ ከቁጥር እስከ አድቫንስ ግርፍ እንዲሁም ከቁጥር በተለየ መልኩ በገናን በቀላሉ በዜማ የሚያስተምሩ ዲያቆናት የበገና ዘማሪያን መምህራን በማምጣት ከህጻናት እስከ አዋቂዎች ድረስ ምዝገባ በመመዝገብ ላይ እንገኛለን:: ለአድቫንስ እና ግርፍ በቶሎ ይመዝገቡ ለጀማሪዎችም በጥልቀት በዜማ እናስተምራለን በስልክ ቁጥር 0928043768 0979178378 0968217778 ይደውሉልን ለአብይ ጾም በአሰላ ከተማና ቅርብ ከተሞች የበገና ዝማሬ አገልግሎት ላይ በጋራ እናቀርባለን ኑ ሰማያዊውን ጣዕመ ዜማ እንማማር
https://youtu.be/lkjNeU1dr0w?si=D1jCSD3HQiTSKKME
አሁን ከሣቴ ብርኃን ገ/ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም ሊያገባ ነው ቢባል ማን ያምናል ብቻ ረቡኒ እኔ ደስ ብሎኛል። እንግዲ እህታችን ሜሮን ታዋቂ ሰው ማግባት ምን አይነት ፈተና እንዳለው አላውቅም ግን ስልኩ በጠራ ቁጥር መደንገጥ የለብሽም። እስከዛሬም ስትሞክሩ የነበራቹ ካላቹ መሞከሩ ስተት አይደለም ከዚ በውኋላ ግን ሜሮን ምትባል ልዕልቱን አግብቷል እንዳደውሉ ብደውሉም ለጉዳይ ብቻ ። አሉ መጋቢ ሐዲስ መምህሬ ጓደኛዬ መካሪዬ እንኳን ለዚህች ቀን አደረሰክ ያንተን ዘር የአብርሃም የሷን ፍሬ የሳራ አርጎ ይሥኃቅን ይስጠን በድጋሚ አሉ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እንኳን አደረሳችሁ ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ በአሰላ ከተማ የመጀመሪያው አድቫንስ የበገና ትምህርት ቤት ተከፈተ ኑ አብረን እግዚአብሔርን በበገና ዝማሬ እናመስግነው 🙏🙏🙏🙏🙏
🛑🛑የምስራች እንኳን ደስ አላችሁ የተዋህዶ ልጆች አክሊል ሚዲያ ተተኪ ዘማርያን የምናፈራበት መዝሙራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች የተለያየ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ሚዲያ ተከፈተ አሁኑኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ ለነፍስዎ ብዙ ነገር ያተርፋሉ@aklil media https://youtu.be/-S_ZG86A9Bc?si=0HlMPv5UnuqJ9Vv4
https://youtu.be/YVhWQgL2WHM?si=qgLT8LjuCCGmU1aa
https://youtu.be/1upthY0NBG4
ኒቆዲሞስ ሰው ሥልጣን ቢኖረው ዕውቀት ሊጎድለው እንዲሁም ሀብት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ማካበት ያዳግተዋል፡፡ ሀብት ቢኖረውም እንኳን ዕውቀት ይጎድለዋል፤ ሥልጣንም አይኖረውም፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ሦስቱንም አንድ ላይ አስተባብሮ የያዘ የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡ ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነው ኒቆዲሞስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያስተማረውን ወንጌልን ለመማር ከአይሁድ ሁሉ ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ይሄድ ነበር፡፡ ፈሪሳውያን ማመን በተሳናቸው በዚያን ጊዜ ጆሮውን ለቃለ እግዚአብሔር፣ ልቡን ለእምነት የከፈተ ሰው ነው፡፡ እናውቃለን በማለት የሚመካኙ በርካታ ሰዎች ከመልካም ነገር ሲከለከሉ እርሱ ግን “ዐዋቂ ሳለ ራሱን ዝቅ አድርጎ፣ እምነት በማጣት የነጠፈችውን የፈሪሳውያንን ኅብረት ጥሎ፣ ሐዋርያትን መስሎ ጌታውን አግኝቶታል፡፡” ቀርቦም እንዲህ አለው፤ ‹‹መምህር ሆይ፥ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርግ የሚችል የለምና፡፡›› ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም›› አለው፡፡ ነገር ግን ኒቆዲሞስ ምሥጢሩ ስላልተገለጠለት ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?›› በማለት ጌታን መልሶ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡›› አሁንም ግን ኒቆዲሞስ ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና ‹‹ይህ ሊሆን እንዴት ይቻላል?›› በማለትም ጌታን ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ፤ ነገር ግን እንዴት ይህን አታውቅም? በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም…›› በማለት አስረድቶታል፡፡ (ዮሐ.፫፥፪-፲፭) የዓለም መድኃኒት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በለየባት በዚያች ሰዓት፣ ሐዋርያት በተበተኑባትና አይሁድ በሠለጠኑባት ጊዜ እንኳን ከጌታችን ሳይል በድፍረት ከእግረ መስቀሉ የተገኘ እንዲሁም ቅዱስ ሥጋውን በድርብ በፍታ ገንዞ የቀበረ ሰው ኒቆዲሞስ ነው፤ ስለዚህም ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት በእርሱ ስም ተሰይሟል፡፡ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን ገልጾ ያዳነውና ያከበረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛም ምሥጢሩን ይገልጽልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አራተኛ የአብይ ጾም ሳምንት https://t.me/helansane ቅዱስ ያሬድ የዐቢይ ጾምን በሰየመበት አጽዋማት ላይ አራተኛው ሳምንት መፃጉዕ በመባል ይታወቃል፡፡መፃጉዕ ማለት ትርጓሜው በቁሙ ሲፈታ “ጐባጣ” ማለት እንደሆነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ላይ ፈትተውታል፡፡ መፃጉዕ የስያሜው ዋና ታሪክ፥በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ በምትባልና አምስትም መመላለሻ በነበረባት አንዲት መጠመቂያ ሥፍራ ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ ስለታመመ አንድ ሰው የሚተርክ ነው፡፡ ጌታ ወደዚህ ሥፍራ የመጣው በሰንበት ቀን ነው፡፡ በዚያም የመጠመቂያውን ቦታ ውኃ የእግዚአብሔር መልአክ ባንቀሳቀሰው ጊዜ ቀድሞ በመግባት ለመፈወስ ወደ ውኃው ይሄዱ ነበር። የታሪኩ ሙሉ መልዕክት በዮሐንስ ወንጌል ም 5 ቁ 1-15 ላይ እንዲህ ይነበባል : - ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ። ልትድን ትወዳለህን? አለው።ድውዩም- ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።ያም ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው። ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት።እርሱ ግን፦ ያዳነኝ ያ ሰው። አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው።እርሱም፦ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ሰው ማን ነው? ብለው ጠየቁት።ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ስለ ነበሩ ኢየሱስ ፈቀቅ ብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰው ማን እንደ ሆነ አላወቀም።ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና። እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው።ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ። ምንባባት መልዕክታት (ገላ. 5÷1-ፍጻሜ ምዕ.) እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትኑሩ፡፡እነሆ÷እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፤ “ብትገዘሩም በክርስቶስ ዘንድ ምንምአይጠቅማችሁም፡፡” ...... (ያዕ.5÷14- ፍጻሜ ምዕ.) ከእናንተ የታመመ ሰው ቢኖር በቤተ ክርስቲያን ያሉቀሳውስትን ይጥራና ይጸልዩለት፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጸለየበትንም ዘይት ይቀቡት፡፡ ....... ግብረ ሐዋርያት (የሐዋ.3÷1-11) ጴጥሮስና ዮሐንስም በዘጠኝ ሰዓት ለጸሎት በአንድነት ወደ ቤተመቅደስ ወጡ፡፡ ከእናቱ ማኅፀንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተወለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደመቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ ሁል ጊዜ እየተሸከሙ መልካም በሚልዋትበመቅደስ ደጃፍ ያስቀምጡት ነበር፡፡(ተጨማሪ ያንብቡ) ምስባክ https://t.me/helansane (መዝ.40÷3) “እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ፡፡ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎምስካቢ ሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ ትርጉም፦ እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ ከበሽታውየተነሣ ይለውጥለታል፡፡ ወንጌል (ዮሐ. 5÷1-24) ከዚህም በኋላ በአይሁድ በዓል እንዲህ ሆነ፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ መጠመቂያ ነበረች፤ ስምዋንምበዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉአታል፤ አምስት እርከኖችም ነበሩአት፡፡ ቅዳሴ: - ቅዳሴ ዘእግዚእነ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ https://t.me/helansane
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ሶስተኛው ሳምንት https://t.me/helansane #ምኩራብ ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡ ትርጉም:- ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው፡)፡ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን 👉 ከምኩራብህ ግባ ! 👈 ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ #ከምኩራብ ግባ! በሚል ርዕስ እግዚአብሔር አምላክ ያስተምረናል።በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምዕሮ ሦስት ነገሮች ቤተክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ። #ህንጻ ቤተክርስቲያኑ #የክርስቲያን ምዕመናን ህብረት እንዲሁም ደግሞ #የእኛ የገዛ አካላችን ቤተክርስቲያን ይባላል። ስለዚህ የእኛን ቤተመቅደስ(ቤተክርስቲያን) ወይም ምኩራብ እንዴት አድርገን እናቅናት? ፈጽመን እናሰናዳትና የምኩራባችንን አለቃ ና ግባ!!! እንበለው። (🙏 በፍጹም ትጋት እስከ ፍጻሜው ጸንታችሁ አንብቡ🙏 ) @helansane 👉 አባታችን ባሕታዊው ቴዎፋን የተናገሩትን ነገር መሠረት አድርገን ወደ እኔና እናንተ ቤተመቅደስ እናምራ። #የሰው ነፍስን በንጉሥ የሚመስሉት ሲሆን ሥጋውን ደግሞ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ይመስሉታል። ይህ ቤተ መንግሥት #አምስት መስኮቶች አንድ በር አለው። እነዚህ አምስት መስኮቶች አምስቱ የስሜት ሕዋሳት ናቸው። በሩ ደግሞ #አእምሮ ነው። ታድያ የእኛ ቤተመቅደስም አወቃቀሩ እንዲኹ ነው። #በር በተሰኘው አእምሮአችን ቅድሚያ ማንን ይሆን አስገብተን ከውስጣችን ያነገስነው ንጉሥ ? በውስጣችን ላነገስነው ንጉሥ ምን ይሆን አምስቱን መስኮቶች ከፍተን ከውጪ ልንቀበል የከጀልነው? 👉 እኛ ደካሞች ሁለት ንጉሦችን በአንድ ቤተ መንግሥታችን አንግሰን ግራ እየተጋባን አለን። #ዘለዓለማዊውን ንጉሥ ክርስቶስን በአእምሮአችን ዙፋን አስቀምጠን በጎን ደግሞ የዚህች የከንቱ ዓለም ገዢ (የክፋት ሃሳቦች ሁሉ ንጉሥ) የሆነውን የዲያብሎስን #ሃሳብ በውስጣችን ጨምረን እያነገስን እንገኛለን። ምክንያቱም ደግሞ እኛ በምንውልባቸው ቦታዎች መስኮት በተባሉት የስሜት ሕዋሶቻችን ፊት ለፊት የኃጥአት ነጋዴ ዲያብሎስ ልዩ ልዩ ልምምዶችንና ነፍስን የሚያስደስቱ ስሜቶችን ያመጣል። በዚህም የተነሳ #ክርስቶስን በቅጡ ያላነገስንባት አእምሮ ከመስኮቱ ማይረባትን ሁሉ ትሸምታለች። መቼም ሁለት ንጉሥ በአንድ ቤተ መንግሥት አንግሳ እንደማትኖር ዘለዓለም እንደማትጸና ታውቃለች። 👉 አሁን ከምኩራባችን (ከቤተመቅደሳችን) ቅድሚያ እኛ ገብተን ውስጡዋን በመስኮት በኩል በምንቀበላቸው ከሄላንሳን ማዕድ ከምንሸምታቸው የቅዱሳን አባቶች ምክርና ተግጻጾች እናዘጋጃትና የምኩራባችንን አለቃ #ከምቡራብህ ግባ! እንለው ዘንድ እንውጣ።(#የምኩራብ አለቃ ሉቃ 13፥14) ኤርምያስ በትንቢቱ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል። (9፥21) ብሎ እንደተናገረ የዘለዓለማዊ ሞት ምክንያቶችን በስሜት ሕዋሶቻችን ወደ ነፍሳችን ከምናስገባ ይልቅ እውነተኛ ብርሃን የሆነውን ሕይወትና መንፈስ የሆነው የክርስቶስን ቃል እናስገባ ዘንድ እንዘጋጅ። ✍ ፥- ዓይናችንን መቆጣጠር ቤተ መቅደሳችንን በብርሃን ሆነን ለማስተካከል ተቀዳሚው ነገር ዓይናችንን መቆጣጠር ነው። በማቴ 6፥22-23 < #የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል። ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል።> በእዚህች አይን በተባለችው መስኮት ከፍተህ የምታስገባው ነገር ጨለማ ብቻ ከሆነብህ መክፈቻ እንዳላት ሁሉ መዝጊያም አላችና ዝጋት። በማቴ ላይ #ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት ሙሉ መቅደስህን ጨለማ ከምታደርግብክ አንድም በሲዖል እሳት ከምትማግድህ ዛሬ ዝጋት ጠርቅማት ሲል ነው። (#ቢቻልህስ በእያንዳንዱ ሰውና በእያንዳንዱ ነገር ውስጥ አምላክን መፈለግና ማየት ልመድ ተለማመድ። ) ✍ ፥- ጆሮን መቆጣጠር የጆሮአችን ዋነኛ ጠላቶች ዘፈን ስድብና ነቀፋን የተሞሎ ግጥሞች ቀልዶች ወሬዎች ናቸው።ሁሉም ከጆሮአችን አልፈው ዓይኖቻችንን በፍትወታዊ ትርዒቶታቸውም ጭምር ያሳድፋብናል። አልፎም ፍጹም ጥፋትን ያስከትሉብናልና ስለዚህ ቅድሚያ ምንሰማውን መምረጥን አስከትለን ደግሞ ፍጹም ወደ መተው ማደግ አለብን። ወደ ቤተ ክርስቲያን ስታመሩ ድንገት የሰማችኹት ዘፈን ቤተ ክርስቲያን ደርሳችኹ እንኳን እየጸለያችኹ በውስጣችኹ እንደሚመጣ አስተውሉ። ዳግመኛም #ሽንገላን መቀበል ኃጢአት ነው። ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ ወዮላችሁ። (ሉቃ 6፥26 ት.ዳን 11፥21-34 ተመልከቱ) (#ቢቻልህስ አሉባልታ/ሐሜትን/ ከመስማት መቆጠንብ ልምድ አድርግ! ያን ጊዜ ተናጋሪው ይጠፋልና።) ✍ ፥- ምላስን መቆጣጠር በምላሳችን #ጥምር ስህተቶችን (ኃጥያቶችን) ነው ምንሰራው ይበልጥ እንጠንቀቅ በነገሮች ሁሉ እናስተውል። እናታችን ሔዋንን አንዴ ብቻ ዕፀ በለስ በመቅመሷ ምን ያክል ክፋት ውድመትን አስከትሏል። የዓለም ከንቱ የሆነውን ነገር ሁሉ #አታጣጥም ማንኛውንም ምግብ ማጣጣምን ለምላስህ አስለምድ ነገር ግን ወሬን ማስለመድ ግን ፈጹሞ አቁም። <<እኔ እላችኃለሁ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል።ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።(ማቴ 12፥36) >> 👉 ከአበው ቅዱሳን መካከል አንዱ የማውራት ፍላጎት ሲፈትነው በአፋ ውስጥ ጠጠሮችን እስከመጨመር ደርሶአል። ✍ ፥- አፍንጫን መቆጣጠር በምናሸተው ነገር የፍትወት ሐሳቦችንና ስሜቶችን ሊያነቃቃ ይችላል።ጥሩ አሽተን ምንፈጽማቸው ከንቱ ስሜቶች አልፈው በሽቱ ፈንታ ግማት እንዳይሆንባችሁ ተጠንቀቁ። (ኢሳ 3፥24) የሚያውድህ ሽታ ወደ ዝሙት ሐሳብ ከመራህ እየተመኘኸው ያለኸው ሥጋ ኢሳይያስ እንዳለው እንደሚበሰብስና ወደ ከፋ ሽታ እንደሚለውጥ አስታውስ። ይልቅ አንተ ዘወትር የቅዱሳንን መዓዛ ለማሽተት ከእቤትህ ውጣ መስኮትህንም ክፈት። (#በመንገድ ሳለህ በጎ መዓዛ አፍንጫህን ባወደው ጊዜ ልዩ መዓዛ ባለው ውድ ሽቱ ጌታዋን የቀባችውን ማርያምን አስባት።<ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ> ዮሐ 12፥3 ✍ ፥- የምንነካውን ነገር መቆጣጠር እግዚአብሔርም አለ፥- #እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ #አትንኩትም። ስለዚህ ለመውደቅዋ ምክንያት ቀዳሚው ነገር መንካትዋ እንደሆነም ተመልከት። በመንካት የሚሰማን ስሜት ቢያስደስትም ኅሊናችንን ግን ወዳልተቀደሱ ሃሳቦች መምራቱ አይቀርምና እንጠንቀቅ።(በጾታዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጡኑ ተጠንቀቁ)። ቅዱስ ይሁዳም በመልዕክቱ ላይ 1፥23 #አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። ይህም ማለት እርቃንን ከሚያሳዩ ከሚያጎሉ ልብሶች ፍላጎትና ንክኪም ፈድማችሁ ራቁ ተጠበቁም። እርሱን አመንዝራዎች እርቃናቸውንና ኅፍረታቸውን ለማሳየት ያደርጉትማል ኃጥያትንም ይፈጽሙበታልና እናንተ ግን መልካሙን ልብስ ተሸለሙ። መቅደሳችሁን ውስጡን እንዳሳመራችሁት ሁሉ ገጽታውም ፍጹም ያማረና በቅዱሳን ዘንድም የተወደደ ወደ መልካም ሃሳብ ብቻ የሚስብ ይሁን ዘንድ ተሰሩ። @helansane ውድ ቤተሰቦቻን አሁን ቅድሚያ ወደ ምኩራባችን ገብተን ውስጡን አስተካክለን የልቡናችንን ወጣ ገባ(#በውስጤ እንዳላኖርክ የልቤ ግርግዳዎች ይጎረብጡሃል) ብለው እንደተናገሩ ቅዱሳን አባቶቻችን እኛም ይህን አባጣ ጎርባጣችንን አቅንተን የመስኮቶቻችንን አከፋፈት አስተካክለን እደ አእምሮአችንን አዘጋጅተን #ከገባ ላናስወጣው አንተ የምኩራባችን አለቃ ንጉሥ ሆይ ግባ!!! እንለው ዘንድ ዛሬ ከኃጥአት ወጥመድ እንወጣ!!! 🙏ሳምንቱን የሰላም የፍቅር የጤና ያድርግልን።🙏 ሼር በማድረግ ማካፈል የዘወትር ተግባራችሁ ይሁን። ።ቸር ያቆየን።
ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ 👉👉ቅድስት👈👈 @helansane የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የሚጀመርበት ሁለተኛው ሰንበት #ቅድስት ይባላል።ከዛሬ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ቀለሙ ""ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ"" ይች ቀን የተቀደሰች ናት ዳግመኛም #ሰንበትየ ቅድስትየ እንተ አዕረፍኩ #ቅዱሳነ ኩኑ እስመ አነሂ ቅዱስ አነ #አብ ቀደሳ ለሰንበት (አብ ሰንበትን አከበራት ቀደሳት ) እያለ የሰንበትን ቅድስና እያነሣሣ ስለሚዘምር ይህ ሳምንት #ቅድስት ተብሏል።ስያሜውም ሰንበት የዕረፍት ቀን እንድትሆን በኦሪትም በሐዲስም እግዚአብሔር የባረካት የቀደሳት ዕለት መሆኑዋን የሚያሳስብና እግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆነ የፈጠረውም ሰውም ቅድስናን መያዝ የሚገባው መሆኑን የሚያሳስብ ነው።(ዘፍ 2፥3 ዘፀ 20፥8-11 ዘሌ 19፥2-3 1ኛ ጴጥ 1፥15-16 ) 👉 አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደመሰከርንላችሁ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል። ለርኩሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና።እንግዲህ የሚጥል ሰውን የጣለ አይደለም መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ነው እንጂ። (1ኛ ተሰ 4፥6-13 ) ውድ ቤተሰቦቻችን ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመሪያ መልዕክቱ 1፥13-15 ሲናገረን ""ስለዚህ የልቦናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን እየኖራችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ። እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።ዳሩ ግን #እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ እንደተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። @helansane ለሰው ፊትም ሳያዳለ በእያንዳንዱ ላይ እንደሥራው የሚፈርደው አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ከሙታን ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ። መዝ 95፥5 እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሰናይት ቅድሚሁ ቅዱሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ 👉ይህም ማለት፥- እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። ምስጋናና ውበቱ በፊቱ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው። @helansane በመጨረሻም፥- ማቴ 6፥16-25 #ስትጦሙም እንደግብዞች አትጠውልጉ እንደጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና እውነት እላችኃላሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። #አንተ ግን ስትጦም በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ በስውር የሚያይ አባትህ በግልጥ ያስረክብሃል። ( እናንተ እስከ ፍጻሜው አንብቡ ) 🙏🙏🙏 አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ሳምንቱን የሰላም የፍቅር የይቅርታ እንዲሁም ከምናያቸውና ከምንሰማቸው መጥፎ ነገሮች በሙሉ በምህረቱ ብዛት ይጠብቀን። ሁላችንም ስለ #ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም እንጸልይ።🙏🙏🙏 ቸር ያቆየን✍️
видео или голосовое, без подписи