የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
СтатистикаContact= +251901629875 ✍️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ ✍️ የቤተክርስትያኗን ትክክለኛ አስተምህሮዋን የያዙ መጽሐፍት ✍️ አጭርና ተከታታይ ትምህርቶች ✍️ ለመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ ✍️ ወቅታዊ መረጃዎች ✍️ ስብከቶችን የሚያቀርብበት ገፅ ነው፡፡ በመርሐግብሩ ላይ አስተያየት ፥ ሐሳብ ፥ ጥያቄ ካለዎት ይጻፉልን @gibigubae_hasab_bot
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 26
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 753
- 1/48двое суток
- 862
- 1/72трое суток
- 930
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
✨እነሆ ገጸ በረከት ✨ መዓዛ ቅዱሳን ዲጂታል መጽሔት 6ተኛ ዕትም ተለቀቀ !! 👆👆👆👆 መልካሙን የእግዚአብሔርን ቃል እያሰብን እናነብ ዘንድ ተጋብዘናል ። https://online.fliphtml5.com/xuhyi/vaxd/ ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም በመጽሔቱ ላይ ማንኛውም ዓይነት ሐሳብ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላችኹ @meaza_kidusan_metshet_bot ላይ ያገኙናል። ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube
видео или голосовое, без подписи
ተወዳጁ መዓዛ ቅዱሳን ዲጂታል መጽሔት 6ተኛ እትሙን እነሆ ለፍልሰታ በረከት ሊለን ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀሩት! 🌟 በ6ኛው እትም የሚያገኙዋቸው ይዘቶች፡ 🌧️ ዘመነ ክረምትና የቤተክርስቲያን አስተምህሮ 📜 ዜና ሐዋርያት (ክብራቸው፣ ቅድስናቸውና ተጋድሏቸው) 🎨 ኪነ-ጥበብ (ፍልሰታና ክረምት ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር) 🕊️ መዓዛ ቅዱሳን (የፍልሰታ ጾም የልጅነት ትዝታዎች) 🔬 ነገረ-ሰብእ (ስለ ሰው ልጅ ተፈጥሮ በሳይንስ እይታ) 🕯️ ሱባዔ (ሱባዔ ለምንና እንዴት ) ☦️ ፍልሰታ ለማርያም (የእመቤታችን ዕረፍትና መፍለስ) መዓዛ ቅዱሳን ፮ኛ እትም ነገ ይጠብቁን! ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ❤️ ነሐሴ (7) ቀን ❤️ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን! ✝️ ✝️ ✝️ 📖 የእመቤታችን የፅንሰት አጭር ታሪክ ጻድቁ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና በ እግዚአብሔር ፊት በቅንነትና በደግነት የሚኖሩ እውነተኛ አማኞች ነበሩ። ነገር ግን በጋብቻ ዘመናቸው ልጅ ባለመውለዳቸው ምክንያት እጅግ ያዝኑ ነበር። በወቅቱ የነበሩ የእስራኤል ልጆችም “ልጅ ያልወለደ ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው” እያሉ ያቃልሏቸውና ይነቅፏቸው ነበር። ቅዱሳኑ ግን በሰው ነቀፌታ ተስፋ ሳይቆርጡ፣ “የአባቶቻችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ለአይናችን ማረፊያ፣ ለልባችን ተስፋ የሚሆን ፍሬ ስጠን” እያሉ ዘወትር በጾምና በጸሎት ወደ አምላክ ይለምኑ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ቅድስት ሐና በቤቷ አትክልት ስፍራ ሳለች፣ አንዲት ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ተመለከተች። በዚያን ጊዜ ልቧ ተነክቶ፦ “አቤቱ ጌታዬ! ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ፣ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ?” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ወደ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ዘንድ በመሄድ ታላቅ ስዕለት ተሳሉ፦ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን እንዲያገለግል፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ፣ መሶበ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ እናደርጋለን” አሉ፤ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስም ጸሎታቸውን አሳርጎ ባረካቸው። ሐምሌ 30 ቀን ቅዱሳኑ አስደናቂ ራእይ አዩ፦ ጻድቁ ኢያቄም፦ “ሰባት ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው፣ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” አለ። ቅድስት ሐና፦ “እኔም ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ፣ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ” አለችው። ይህንን ራእይ ካዩ በኋላ “ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን” ብለው ዕለቱን አልጋና ምንጣፍ ለይተው ለሰባት ቀን ያህል በጸሎት ተለይተው ሰነበቱ። በሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለጻድቁ ኢያቄም በተራራ ላይ ሲጸልይ በተገለጸለት ጊዜ፦ “ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች፤ ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን፣ ለብዙዎች የሕይወት ብርሃንና ድኅነት የምትሆን ሴት ልጅ ትወልድልሃለች” ሲል አበሰረው። መልአኩ ለቅድስት ሐናም ተገልጦ የጌታን ፈቃድ ነገራት። በብስራተ መልአክና በፈቃደ እግዚአብሔር፣ እሁድ ዕለት በነሐሴ 7 ቀን ከሰው ሁሉ የበለጠች፣ ከመላእክትም የከበረች፣ የዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነችው አምላክን የምትወልደው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማኅፀነ ሐና ተፀነሰች። ✝️ ✝️ ✝️ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና በረከት፣ የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና ጸሎት አይለየን።🙏 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube
видео или голосовое, без подписи
የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «የ Freelance አገልጋይነት በይፋ ተጀምሯል! 💡 ለመሆኑ ‘ችሎታ የለኝም’ በሚል ሰበብ ከበረከት እየሸሻችሁ ነው🤔? . . .ነቢዩ ዮናስም እኮ ባህር ውስጥ እስኪገባ ድረስ ሰበብ ይደረድር ነበር! 😊 እኛ ጋር ግን ‘የምችለው ነገር የለም’ ብሎ መጨነቅ አይሰራም፤ ዋናው ፍላጎቱ ይኑር እንጂ እዚያው እያገለገላችሁ ፣ እየተማራችሁ ልምድ እያካበታችሁ ምርጥ ባለሙያ ትሆናላችሁ ። እንዲያውም የትም ቦታ…»
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ! 🕊✨ 📌 ጾመ ፍልሰታ ምንድን ናት? ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 16 ቀን የሚጾመው ይህ ጾም፣ በቅዱሳን ሐዋርያት ሥርዓት የተሠራ፣ ሁላችንም በኅብረት ወደ እግዚአብሔር አምላካችንና ወደ እመቤታችን በጸሎትና በሱባኤ የምንቀርብበት መንፈሳዊ ወቅት ነው፡፡ 📖 የጾሙ ታሪክና አመጣጥ · እመቤታችን በ64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን ሊያሳርፉ ሲሄዱ አይሁድ በተንኮል ሥጋዋን ሊቀሙ በመሞከራቸው፣ መላእክት ክቡር ሥጋዋን ወደ ኤደን ገነት ወሰዱት፡፡ · ሐዋርያት በጾምና በጸሎት ሱባኤ ሲይዙ፣ በ14ኛው ቀን ጌታችን ሥጋዋን ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ሥጋዋን አሳረፉ፤ በ3ኛው ቀንም እንደ ልጇ ሞትን ድል አድርጋ ተነሣች፡፡ · ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን በደመና ስታርግ ተመልክቶ ሰበኗን (መቀነቷን) ተቀበለ፡፡ · ሐዋርያትም ቅዱስ ቶማስ ያየውን ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን እንደገና ሱባኤ ገብተው በ16ኛው ቀን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ለማየት በቅተዋል፡፡ 💡 ኦርቶዶክሳውያን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዕረፍትና ትንሣኤ በማሰብ፣ ከልጇ ከወዳጇ የሚገኘውን ጸጋና በረከት ተስፋ በማድረግ የአባቶቻችንንና የእናቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በየዓመቱ ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን፤ የምንችል ደግሞ ንስሐ ገብተን አስቀድሰን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እንቀበላለን፡፡ በዚህ ጾም በተለይ አረጋውያንና ሕፃናት ብቻ ሳይሆኑ፣ መላው ኦርቶዶክሳውያን ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል መንግሥቱን ለመውረስ መዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ 🔔 በጾሙ ወቅት የሚደረጉ መንፈሳዊ አገልግሎቶች 🌌 ሌሊት፦ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የሰዓታት ጸሎት ይደረጋል፡፡ ☀️ ቀን፦ የቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ይነበባል፡፡ ⛪️ ቅዳሴ፦ የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያም ይቀደሳል፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት አይለየን፡፡" 🙏 መልካም የሱባኤ ጊዜ ይሁንልን! ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube
видео или голосовое, без подписи
የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned «የ Freelance አገልጋይነት በይፋ ተጀምሯል! 💡 ለመሆኑ ‘ችሎታ የለኝም’ በሚል ሰበብ ከበረከት እየሸሻችሁ ነው🤔? . . .ነቢዩ ዮናስም እኮ ባህር ውስጥ እስኪገባ ድረስ ሰበብ ይደረድር ነበር! 😊 እኛ ጋር ግን ‘የምችለው ነገር የለም’ ብሎ መጨነቅ አይሰራም፤ ዋናው ፍላጎቱ ይኑር እንጂ እዚያው እያገለገላችሁ ፣ እየተማራችሁ ልምድ እያካበታችሁ ምርጥ ባለሙያ ትሆናላችሁ ። እንዲያውም የትም ቦታ…»
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፤ እንዴት ናችሁ! በመጀመሪያ መልእክቱን ለማድረስ በመዘገየታችን ይቅርታ እንጠይቃለን🙏 ውድ የ2018 ዓ.ም የግቢ ጉባኤያችን ተመራቂ አባላት፤ እንዲሁም ከዚህ በፊት ተመርቃችሁ እስካሁን ወደ ምሩቃን ኅብረት የቴሌግራም ግሩፕ ያልተቀላቀላችሁ፣ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን የተለያዩ የሥራ ዕድሎችን እና አስፈላጊ መረጃዎችን መከታተል ትችላላችሁ። የግሩፑ ሊንክ፦ https://t.me/+UWw7z5kW0cI1OTU0 ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube
የ Freelance አገልጋይነት በይፋ ተጀምሯል! 💡 ለመሆኑ ‘ችሎታ የለኝም’ በሚል ሰበብ ከበረከት እየሸሻችሁ ነው🤔? . . .ነቢዩ ዮናስም እኮ ባህር ውስጥ እስኪገባ ድረስ ሰበብ ይደረድር ነበር! 😊 እኛ ጋር ግን ‘የምችለው ነገር የለም’ ብሎ መጨነቅ አይሰራም፤ ዋናው ፍላጎቱ ይኑር እንጂ እዚያው እያገለገላችሁ ፣ እየተማራችሁ ልምድ እያካበታችሁ ምርጥ ባለሙያ ትሆናላችሁ ። እንዲያውም የትም ቦታ ሆናችሁ፣ ባመቻችሁ ሰዓት በዲጂታል ዓለም ተጠቅማችሁ የምታገለግሉበት ልዩ የፍሪላንስ ዕድል ነው። አሁን ከምታውቁት የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም በላይ በተግባር የምታዩበትና ጥበብን ለክርስቶስ የምትሰጡበት ጊዜው አሁን ነው!" 🤔 እስኪ አስቡት! እናንተ በምታዘጋጁት ድንቅ የግራፊክስ ዲዛይን፣ በምትቀርጹት ቪዲዮ፣ በምታቀናብሩት ድምፅ ወይም በምትጽፉት ልብ የሚነካ ጽሑፍ ምክንያት አንድ ሰው በመርሐግብሩ ተማርኮ ወደ ቤተክርስቲያን ቢመጣና ቢቀደስ... ከዚህ በላይ ምን ትልቅ ጸጋ አለ? ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማቅረብ ማለት እኮ ትውልድን ማዳን ነው! ቴክኖሎጂንና ሰማያዊ በረከትን በአንድ ላይ አጣምሮ ፍቅርና አንድነት ባለው የወንድማማችነት ኅብረታችን ውስጥ ለማገልገል አሁኑኑ ይቀላቀሉን። ፍላጎት ብቻ ይበቃናል፤ የቀረውን እኛ ጋር ታገኛላችሁ። ‘እኔን!’ ብላችሁ ዛሬውኑ በሚዲያ ክፍላችን ተመዝገቡና የጥበብ ባለቤት ለሆነው አምላክ እናገልግል!😊 🎯 በሚዲያ ቲማችን ውስጥ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዘርፎች ለማገልገል ፦ 📝 Content Creator 🎥 Cameraman 🎬 Video Editor 🎨 Graphics Designer 🎙️ Social Media Host & Scriptwriter ለበለጠ መረጃ : 0905496768 0983329770 ይደውሉልን 📌 ለመመዝገብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፦ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf6ix5ckLZRxDvE8xiPvWYxvtoXP61o9gi4KyOm5_NbivLD2w/viewform?uspsharinouid= ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube
видео или голосовое, без подписи
በመምህራችን ኢዩኤል ሀብታሙ የተሰጠ ከባለፈው ትምህርት የቀጠለ 2ኛ ክፍልን በዩቲዩብ ቻናላችን እንድትከታተሉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል። 🎥👇 https://youtu.be/QoyiKoRG7jo?si=dhkp2LQX3pWigwHg TikTok | Instagram | YouTube
видео или голосовое, без подписи
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም አሜን። ሐምሌ 19 የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከሚነደው እቶን እሳት በተአምራት ያዳነበት ዕለት ነው፡፡ ሦስት ዓመት ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በሕዳር 15 ቀን የተወለደ ሲሆን ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ ሀንጌቤን ይባላል፡፡ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ነበርና መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ቅዱስ ቂርቆስም በከሃዲው ንጉሥ ፊት የጌታችንን ክብር በመሰከረ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን በውስጡ ጨምሮ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ። ንጉሡ እስክንድሮስ ጭፍሮቹን "ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረትን፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምሩበት" ብሎ አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮችም ያዘዛቸውን ከፈጸሙ በኀላ መጥተው "ያዘዝከንን ሁሉ ጨምረንበት ነዶ ፈልቷል" አሉት፡፡ "ድምፁም እንደ ነጎድጓድ ይሰማል፤ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ ያንፀባርቃል፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ይወጣል፡፡ በውስጡ የሚጣሉትን ሰዎች እዘዝ" አሉት፡፡ ያንጊዜም ህፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይዘው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በክርስቶስ ስም ስላመኑ በእስር ቤት አግብተው አስረዋቸው ነበርና ፍላቱ ወደ ላይ በሚዘል በብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው በዚያን ጊዜም እልፍ ከአንድ ሺህ አራት መቶ ሰዎች እንዲወጡና በፈላው የብረት ጋን ውስጥ የቅዱሳንን አሟሟት እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡ "ነገር ግን እናቴ ሆይ አናንያንና አዘርያን፣ ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከዕቶን እሳት እንዳወጣቸው እወቂ፤ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትሺ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ ሶስናን ከሀጢያተኞች እጅ ያዳናት እኛንም ከብረት ጋን ያድነናል፡፡ ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ ያዳነ እርሱ ያድነናል፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችን ልንፈፅም ፈቅዶም እንደሆነ የኢዮብን ነፃነት (ትእግስት) ልናገኝ ይገባናል፡፡ እርሱ ልጆቹንና ሚስቱን ያገኘው ገንዘብ ሁሉ አጥቶ በመጨረሻው ሰውነቱን አጥቶ ነበርና ምንም ምንም የቀረበለት አልነበረምና እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ከማለት በቀር ያለው ነገር የለም እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔርም ወሰደ አለ፡፡ የእግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም ይመስገን አለ፡፡ እኛም ይህንን መከራ ልንታገስና የተጠበቀልንን ልንከተል ይገባናል..." እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገር ግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋቸት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ "እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከህይወት መፅሐፍ እኔን ፋቀኝ አለ፡፡ አቤቱ ይህነን ነገር ልታደርግ አይገባህም፤ አቤቱ እርሻውን ልታቃጥል ፍሬውንም ልትባርክ ትወዳለህን፡፡ አቤቱ እንጨቱን ቁረጡና አንድዱት ቅጠሉን ጠብቁ ብለህ ልታዝ አይገባህም፡፡ እንጨቱንም ቅጠሉንም ጠብቁ ብለህ እዘዝ እንጂ ይህ አይገባህም ያመነብህ ሁሉ ይህን ያየ ዘንድ፡፡ ማዳን የሚችል አምላክ ኑሮአቸው ቢሆን ከዚህ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ እንዳይጠራጠር፡፡ ዲያብሎስ ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኑም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ፣ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማሁ እንዳይል አቤቱ የኃይል መንፈስ ለእናቴ ስጣት አበርታት..." ብሎ ጸለየ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፡- በመንግስተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ስጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈፅምና ድል እንነሣ" አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ ቅዱሳንም ይህንን ሲነጋገሩ አንስተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡ የራማው ልዑል የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው አይለየን! ከበዓሉ በረከት ይክፈለን! ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube
የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned a photo
✨ ሰላም፣ የግቢ ጉባኤያችን አባላት በሙሉ፤ 🔔 መምህራችን ኢዩኤል ሀብታሙ በሁለተኛው መንፈቀ ዓመት ዐብይ ጉዞ ላይ የሰጡትን ድንቅ ትምህርት በዩቲዩብ ቻናላችን እንድትከታተሉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል። 🎥👇 https://youtu.be/-fxJpw3nkV0?si=4icxaHgTxZXpyflX ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube https://youtu.be/-fxJpw3nkV0?si=8V2IX3vwbN3lxF4V
የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ pinned a photo
AASTU Gibigubae is recruiting! We're building tech products to serve the Ethiopian Orthodox Church — and we want you on the team. Looking for: React + TypeScript Express + TypeScript Flutter UI/UX Design Get real hands-on experience, work on live products with real users, and receive a certificate recognizing your work. Program runs for approximately 2 months. 📌 Open to AASTU students only 📅 Deadline: July 22 🔗 Apply on: https://career.aastugibigubae.com/apply/summer2018 Don't see your skill listed? We'll be opening a new application for other roles soon — stay tuned." ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ። እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6) የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው:: የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል:: መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ፣ እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ የጌታችንን መንገድ የጠረገ፣ ጌታውን ያጠመቀና፣ ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰዉ ነው:: ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች:: "ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ:: መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና:: እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ:: ይሕም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው::" (ሉቃ. 1:76) አምላካችን ከቅዱሱ ቤተሰብና በረከት ይክፈለን:: ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube