- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 16
- 1/48двое суток
- 18
- 1/72трое суток
- 19
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ❤️ ነሐሴ (7) ቀን ❤️ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን! ✝️ ✝️ ✝️ 📖 የእመቤታችን የፅንሰት አጭር ታሪክ ጻድቁ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና በ እግዚአብሔር ፊት በቅንነትና በደግነት የሚኖሩ እውነተኛ አማኞች ነበሩ። ነገር ግን በጋብቻ ዘመናቸው ልጅ ባለመውለዳቸው ምክንያት እጅግ ያዝኑ ነበር። በወቅቱ የነበሩ የእስራኤል ልጆችም “ልጅ ያልወለደ ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው” እያሉ ያቃልሏቸውና ይነቅፏቸው ነበር። ቅዱሳኑ ግን በሰው ነቀፌታ ተስፋ ሳይቆርጡ፣ “የአባቶቻችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ለአይናችን ማረፊያ፣ ለልባችን ተስፋ የሚሆን ፍሬ ስጠን” እያሉ ዘወትር በጾምና በጸሎት ወደ አምላክ ይለምኑ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ቅድስት ሐና በቤቷ አትክልት ስፍራ ሳለች፣ አንዲት ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ተመለከተች። በዚያን ጊዜ ልቧ ተነክቶ፦ “አቤቱ ጌታዬ! ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ፣ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ?” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ወደ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ዘንድ በመሄድ ታላቅ ስዕለት ተሳሉ፦ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን እንዲያገለግል፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ፣ መሶበ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ እናደርጋለን” አሉ፤ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስም ጸሎታቸውን አሳርጎ ባረካቸው። ሐምሌ 30 ቀን ቅዱሳኑ አስደናቂ ራእይ አዩ፦ ጻድቁ ኢያቄም፦ “ሰባት ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው፣ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” አለ። ቅድስት ሐና፦ “እኔም ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ፣ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ” አለችው። ይህንን ራእይ ካዩ በኋላ “ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን” ብለው ዕለቱን አልጋና ምንጣፍ ለይተው ለሰባት ቀን ያህል በጸሎት ተለይተው ሰነበቱ። በሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለጻድቁ ኢያቄም በተራራ ላይ ሲጸልይ በተገለጸለት ጊዜ፦ “ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች፤ ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን፣ ለብዙዎች የሕይወት ብርሃንና ድኅነት የምትሆን ሴት ልጅ ትወልድልሃለች” ሲል አበሰረው። መልአኩ ለቅድስት ሐናም ተገልጦ የጌታን ፈቃድ ነገራት። በብስራተ መልአክና በፈቃደ እግዚአብሔር፣ እሁድ ዕለት በነሐሴ 7 ቀን ከሰው ሁሉ የበለጠች፣ ከመላእክትም የከበረች፣ የዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነችው አምላክን የምትወልደው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማኅፀነ ሐና ተፀነሰች። ✝️ ✝️ ✝️ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና በረከት፣ የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና ጸሎት አይለየን።🙏 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ TikTok | Instagram | YouTube
видео или голосовое, без подписи
† † † በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † † ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ 📖 ከመጽሐፍ አንደበት 📖 ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ ድክመቶቼን ማወቄ ምንድነው የሚጠቅመኝ? ካልን አንድ ሰው ድክመቶቹን ካወቀ እግዚአብሔርን ያውቃል። ''ስደክም ያንጊዜ ኃይለኛ ነኝና'' 2ቆሮ 12፡10። ኃጢአቴ ምን ያህል አስነዋሪ እንደሆነ ሳረጋግጥ የእግዚአብሔርን ፀጋ እሻለሁ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ብሏል ''ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ እና ከእኔ ተለይ'' ሉቃ 5፡8። ቅዱስ ጴጥሮስ ምን አይነት ችግር ውስጥ እንዳለ ተሰምቶታል። ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አለው ''አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ'' ሉቃ 5፡10 ቅዱስ ጴጥሮስ ለታላቅ ተልእኮ እና አገልግሎት የበቃው መቼ ነበር? ይህ የሆነው ራሱን ባወቀ ቅጽበትና "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ" ብሎ በተናገረ ጊዜ ነበር። የሰው ልጅ በእንዲህ ዓይነት ስሜት ውስጥ በሆነ ጊዜ እግዜአብሔር እንዲህ ይላል። "አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ"። ስለዚህ ራሳችንን ማወቅ ማለት እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ነው። የሕይወት መዓዛ አቡነ ሺኖዳ ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † †
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ! 🕊✨ 📌 ጾመ ፍልሰታ ምንድን ናት? ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 16 ቀን የሚጾመው ይህ ጾም፣ በቅዱሳን ሐዋርያት ሥርዓት የተሠራ፣ ሁላችንም በኅብረት ወደ እግዚአብሔር አምላካችንና ወደ እመቤታችን በጸሎትና በሱባኤ የምንቀርብበት መንፈሳዊ ወቅት ነው፡፡ 📖 የጾሙ ታሪክና አመጣጥ · እመቤታችን በ64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን ሊያሳርፉ ሲሄዱ አይሁድ በተንኮል ሥጋዋን ሊቀሙ በመሞከራቸው፣ መላእክት ክቡር ሥጋዋን ወደ ኤደን ገነት ወሰዱት፡፡ · ሐዋርያት በጾምና በጸሎት ሱባኤ ሲይዙ፣ በ14ኛው ቀን ጌታችን ሥጋዋን ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ሥጋዋን አሳረፉ፤ በ3ኛው ቀንም እንደ ልጇ ሞትን ድል አድርጋ ተነሣች፡፡ · ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን በደመና ስታርግ ተመልክቶ ሰበኗን (መቀነቷን) ተቀበለ፡፡ · ሐዋርያትም ቅዱስ ቶማስ ያየውን ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን እንደገና ሱባኤ ገብተው በ16ኛው ቀን ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ለማየት በቅተዋል፡፡ 💡 ኦርቶዶክሳውያን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዕረፍትና ትንሣኤ በማሰብ፣ ከልጇ ከወዳጇ የሚገኘውን ጸጋና በረከት ተስፋ በማድረግ የአባቶቻችንንና የእናቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በየዓመቱ ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን፤ የምንችል ደግሞ ንስሐ ገብተን አስቀድሰን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እንቀበላለን፡፡ በዚህ ጾም በተለይ አረጋውያንና ሕፃናት ብቻ ሳይሆኑ፣ መላው ኦርቶዶክሳውያን ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል መንግሥቱን ለመውረስ መዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ 🔔 በጾሙ ወቅት የሚደረጉ መንፈሳዊ አገልግሎቶች 🌌 ሌሊት፦ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የሰዓታት ጸሎት ይደረጋል፡፡ ☀️ ቀን፦ የቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ይነበባል፡፡ ⛪️ ቅዳሴ፦ የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያም ይቀደሳል፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት አይለየን፡፡" 🙏 መልካም የሱባኤ ጊዜ ይሁንልን! ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ 📥 @gibigubaeHasabon_bot ጻፉልን 🏷 @aastugibigubae ተከታተሉን 📷 @GGgallery1 የፎቶ ማኅደራችን ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
видео или голосовое, без подписи
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሰርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሰርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሰርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡ በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፡ ክፍል 1 "ሥርዓት"፡ ሕግ፣ ደንብ፣ አሠራር እና መርሐግብርን ያመለክታል። "ቤተክርስቲያን"፡ የክርስቲያኖች ቤት፣ መሰብሰቢያ እና መገናኛ ቦታ ነው፤ የክርስቲያን ወገን ( የእስራኤል ወገን "ቤተ እስራኤል እንደሚባል)። ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፡ የቤተክርስቲያን ሕግ፣ ቀኖና እና የአሠራር መርሐግብር ነው። የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ምንጮች፡ መጻሕፍተ ብሉያት፣ መጻሕፍተ ሐዲሳት፣ የሐዋርያት ሲኖዶስ፣ ሥርዓተ ጽዮን፣ አብጥሊስ፣ ትዕዛዝ፣ ዲድስቅልያ፣ ፍትሕ መንፈሳዊ፣ ዓለም አቀፍ ጉባኤያት፣ የሥርዓት መጻሕፍት እና የብሉይ ኪዳን ሥርዓት (ሥርዓተ፡ ደብተራ ኦሪት፣ መቅደሰ ኦሪት፣ ካህናተ ኦሪት) ናቸው። በብሉይ ኪዳን የነበሩ ነገሮች እና በሐዲስ ኪዳን ያሉ ነገሮች፡ - መቅደሰ ኦሪት በሶስት ክፍል የተከፋፈለ ሲሆን፣ ቤተክርስቲያንም በሶስት ክፍል ትሰራለች። - በብሉይ ኪዳን ታቦተ ሕግ በመቅደሰ ኦሪት ውስጥ የነበረ ሲሆን፣ በሐዲስ ኪዳንም ታቦተ ሕጉ በመቅደስ ውስጥ ይገኛል። - በብሉይ ኪዳን መስዋዕት ሲቀርብ፣ በሐዲስ ኪዳንም አማናዊ መስዋዕት ይቀርባል። - በብሉይ ኪዳን ካህናት፣ ነገስታት እና ንዋያተ ቅድሳት ወደ ቤተመቅደስ ሲገቡ ቅብዕ ቅዱስ ይቀቡ ነበር፤ በሐዲስ ኪዳንም ሰው ሲጠመቅ፣ አዲስ ጽላት ሲቀረጽ፣ አዲስ ቤተክርስቲያን ሲገነባ፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ካህናት ሲሾሙ እና በተክሊል ሥርዓት ወቅት ቅብዐ ሜሮን ይቀባሉ። - በብሉይ ኪዳን ክህነት ይሰጣል፤ በሐዲስ ኪዳንም ሢመተ ክህነት ይከናወናል። - በብሉይ ኪዳን ስርዓተ ጋብቻ ነበር፤ በሐዲስ ኪዳን ሥርዓተ ተክሊል ይከናወናል። ምንጭ፡ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን (ጸሐፊ፡ ሊቀ ካህናት ክንፈገብርኤል አልታየ) +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ++++ ++++ ወወላዲተ ድንግል ++++ ++++ ወመስቀሉ ክቡር++++ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ ሐምሌ ፳፬ /24/ በዚች ቀን ከደቡባዊ ግብጽ ከታችኛው ምድር አውራጃ ከንሒሳ ከተማ ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት ሆኖ ሞተ ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ቅዱሳን ንጹሐንና የሚራሩ ነበሩ ። ይህንንም ቅዱስ ኖብን በወለዱት ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት እስኪሆነው ፈሪሀ እግዚአብሔርን እያስተማሩ አሳደጉት ። አንድ ቀን ቄሱንም ምእመናንን እንዲህ እያለ ሲያስተምራቸውና ሲያበረታቸው “ጣዖታትን ከምታመልኩ ክብር ይግባውና ስለ መድኃኒታችን ስለ ክርስቶስ ነፍሳችሁን ለሞት አሳልፋችሁ ብትሰጡ ለእናንተ መልካም ነው” ሲላቸው ሰማው። ከዚህ በኋላ ያለውን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ ። ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ገምኑዲ ሔደ በዚያም ላለው መኮንን ስለ ጌታችን አምላክነት መሰከረ። በዚህም ብዙ አሰቃየው የእግዚአብሔርመልአክተገልጦ አጽናናው። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ ሰሜን አገር ሲጓዝ የከበረ ኖብን ከእርሱ ጋራ በመርከብ ወሰደው በመርከቡም ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ ሰቀለው የእግዚአብሔር መልአክም አዳነው። በዚህም ወታደሮቹ አምነው ሰማዕትነትን ተቀበሉ። መኮንኑ ግን በብዙ አሰቃየው አቅፋሐስ ከሚባል አገርም ዮልዮስ መጣ ከእርሱም እንደ ተረዳ ገድሉን ጻፈ ። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። እንዲሁም አደረጉበትና ሰማዕትነትን ተቀበለ። ጌታችንም ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት። ሥጋውንም ቅዱስ ዮልዮሰ አንሥቶ ከሁለት አገልጋዮቹ ጋራ ንሒሳ ወደ ሚባል አገሩ ላከው። +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ++++ ++++ ወወላዲተ ድንግል ++++ ++++ ወመስቀሉ ክቡር++++ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን
† † † በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † † ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ 📖 ከመጽሐፍ አንደበት 📖 ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ የኅሊና ዳኛ እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ኅሊና ውስጥ፣ ኹል ጊዜ ንቁና ትጉ የኾነ ዳኛ ያስቀመጠው ስለ ምንድን ነው ብለኅ ብትጠይቀኝ፣ ከሰው ወገን ይኽን የ'ኅሊና ዳኛ'ን የመሰለ፣ እንቅልፍ የለሽ ዳኛ ስለሌለ ነው ብዬ እመልስልሃለኹ፤ ዳግመኛም፣ የውጪ ዳኞች በገንዘብ፣ በውሸት በመደለል፣ የሐሰት ፍርድ እንዲሰጡ በማስፈራራት፣ እንዲኹም በሌሎች መጠነ ብዙ ምክንያቶች፣ ርቱዕ የኾነ (ያልተዛባ) ውሳኔአቸውን ሊያጣምሙ ይችላሉ፤ የ'ኅሊና ዳኛ'ን ግን በእነዚኽ በገለጽናቸው ምክንያቶች በምንም መንገድ የሚደለል አይደለም፤ ጉቦ ብንሰጠው፣ ልንዋሸው ብንሞክር፣ ብናስፈራራው፣ ሌላ ሌላም ብናደርግ እንኳ፣ ይኽ የ'ኅሊና ዳኛ' ለምናስበውና ለምንሠራው ኀጢአት ምንም ሳይጠመዝዝ እውነተኛ ፍርድን ይሰጣል፤ ኀጢአት የሠራ ሰው፣ ሌላ ሰው ባይወቅሰውም እንኳ፣ ርሱ ራሱ ራሱን ይወቅሳል፤ አንዴ ወይም ኹለቴ ብቻ አይደለም፣ መላ ዘመኑን እየደጋገመ ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ኅጢአት የሠራነው ከረዥም ዘመናት በፊት ሊኾን ይችላል፤ የኅሊናችን ዳኛ ግን ያን የሠራነው ጥፋት ፈጽሞ አይረሳውም። ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 49 ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † †
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ እናት አለኝ እናት አለኝ በመንገዴ... ከኔ ቀድማ የምትገኝ ቀን ሲከዳኝ ሲያሻኝ ማረፍ ቀሚሷ ነው የኔ መዳፍ እናት አለኝ ቃል ኪዷኗ 'ሚደግፈኝ ክንዴ ሲዝል ለመኖር ስደክም እኩል ከኔ ታማ ቁስሌን የምታክም ሳዝን የሚጨንቃት ሲከፋኝ የማትወድ በሄድኩበት ሁሉ አብራኝ የምትሄድ እናት አለኝ በሀዘን ተከብቤ እንዳልታይባት የኔን ድካም ወስዳ የምትሰጠኝ ብርታት እናት አለኝ ገጣሚ፡ መኳንንት ከ @Mgetem የተወሰደ ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † †
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ ✨እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአል አደረሳችሁ✨ ሐምሌ ፲፱ /19/ በዚችም ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው ። ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ እርሱን ጠይቅ አለችው ። ሕፃኑም በተጠየቀ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር አምላክነት እና ስለ ጣዖታቱ ከንቱነት ተናገረ። ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ። መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በዚህም ሕፃኑን እና እናቱንን በብዙ አሰቃያቸው እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው በሰማዕትነት ሞቱ። በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው። ከዚህም በኋላ በፈላውሀ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ++++ ++++ ወወላዲተ ድንግል ++++ ++++ ወመስቀሉ ክቡር++++ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን
† † † በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † † ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ 📖 ከመጽሐፍ አንደበት 📖 ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ ለሞት የቀረበ ሰው ጸሎት “ታላቅና ልዩ የሆንክ የኃይላት ሁሉ ጌታ ፤ ኃይልህ የተደነቀ ቸርነትህ የማይመረመር፤ በምሕረትና በይቅርታ ባለጠጋ የሆንክ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ከንቱና ኃጢአተኛ የምሆን እኔን ጆሮህን አዘንብለህ ስማኝ፡፡ ዮናስን ከዓሣ አንበሪ ሆድ ያወጣኸው፤ ዳንኤልንም ከአናብስት አፍ ያዳንከው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የክፋት አለቃ ከሠለጠነበት አስፈሪ ጨለማ በምሞትበት ጊዜ አድነኝ፡፡ ነፍሴ ከሥጋዬ ልትለይ ስትቀርብ ወደ ምንጣፌ (አልጋዬ) ርጉም ዲያብሎስ ይቀርብ ዘንድ አትፍቀድ። በዚህ ዓለምም ቢሆን በወዲያኛው ዓለምም ቢሆን፤ በሞት ጣዕር ሳለሁም ቢሆን፤ ወደ ሰማይ ከሥጋዬ ተለይቼ ስወጣም ቢሆን፤ አቤቱ ጌታዬ ሆይ ነፍሴ የዲያብሎስን ኅሱም ገጹን አትይ፡፡ ይህን ጎስቋላ ሥጋ ተለይታ በምትወጣ ሰዓት የተጣለው ዘንዶ በነፍሴ ላይ አይዘባበት፡፡ ጠረናቸው እጅግ የሚከረፋ የምኞት መናፍስት ነፍሴን በክርፋታቸው ይበክሏትና ይናጠቋት ዘንድ አትፍቀድ፡፡ ጌታዬ! ንጉሤ! መድኃኒቴ! አምላኬ! ብርሃኔ ሆይ! ከዘላለም ፍርድ ለይተህ አውጣኝ፡፡ ራእየ ኒፎን ቀሲስ ታምራት ውቤ ገጽ 111 ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † †
† † † በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † † መዓዛሽ ልዩ ነው ⭐️ ስምሽም ጥዑም ሽቶ በሽታ እንዳይወስደኝ ክረምት አገርሽቶ የመስከረም ተስፋ የብርሃን ዘንጋችን በዓለም እንዳንጠፋ ሸሻጊ ዘውጋችን፤ ይዘረጋል ፊደል ይከደናል ገደል ይነሳል ተማሪ፣ ስምሽን ሊያነሳ ከወቅቱ ጋር ያልፋል የእኔም ጣ'ር አበሳ ዘይት ነሽ ቅባ ኑግ ለአመዳም ገጻችን ወዛችን፣ ወንዛችን ማብሪያ መታጠቢያ ለተስፋ ማሰሪያ፣ የሸለመን አንቺን። አዘክሪ ድንግል እንደቀኙ ወንበዴ ተዘከረኝ ልበል፣ ምህረቱን ልማጸን ልላቀቅ ከልምዴ ልገላገል አንዴ ከዓለም ማህጸን ከጥፋት፣ ከጉዴ፤ ልጅ ልኹን ልወለድ ሰው ልኹን ልወደድ! ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † †
видео или голосовое, без подписи
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ 🗓 ሐምሌ 5 ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ የሁለቱ ብርሃናት የሰማዕትነት ቀን የሰማይና የምድር ጌታ፣ የሐዋርያት መምህር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ዓለምን ታበራላችሁ" ብሎ የሾማቸው የሁለቱ አዕማድ ሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት በዓል በቤተክርስቲያን በየዓመቱ ሐምሌ 5 ቀን በታላቅ ክብር ይታሰባል። ይህ ቀን የሥጋ መለየት፣ የነፍስ ግን ወደ ዘለዓለማዊው መንግሥት መሸጋገሪያ የድል ቀን ነው። የዓለቱ ሐዋርያ፡ ቅዱስ ጴጥሮስ "ጴጥሮስ" ማለት "ዓለት" ማለት ነው። ከቤተሳይዳ የመጣው ዓሣ አጥማጁ ስምዖን፣ በጌታ ጥሪ የሰው አጥማጅ ሆነ። እርሱ የዋህ፣ ታማኝ፣ በአንድም በኩል ደግሞ እጅግ ቀናዒና ፈጣን ነበር። በቂሣርያ ፊልጶስ ጌታን "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ በማመን የቤተክርስቲያን መሰረት የመሆኑን ምስክርነት አገኘ። በሮም አደባባይ፣ ጌታውን ለመከተል የነበረው መውደድ ወደ ሰማዕትነት መራው። አረማዊው ንጉሥ ኔሮን በፈረደበት ጊዜ፣ ጴጥሮስ ከጌታው ክብር አንፃር ራሱን አሳንሶ በማሰብ፣ ጌታዬ እንደተሰቀለ አትስቀሉኝ፤ እንደ እርሱ መሆን አይገባኝምና ብሎ በትሕትና በመጠየቅ ቁልቁል ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት ፈቀደ። ሐምሌ 5 ቀን፣ ጴጥሮስ በመስቀል ላይ የነበረው ሕይወት ወደ ሰማያዊው መንግሥት ተሸጋገረ። የተመረጠው ዕቃ፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሳውል የተባለው ጳውሎስ፣ ከጠርሴስ የተገኘ የእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ነው። በጥበብ፣ በትምህርትና በሕግ አዋቂነት የተመሰከረለት ይህ ሐዋርያ፣ መጀመሪያ ላይ የወንጌል ተቃዋሚ የነበረ ቢሆንም፣ በደማስቆ መንገድ በተገለጠለት የክርስቶስ ብርሃን ሕይወቱ ሙሉ በሙሉ ተቀየረ። ጳውሎስ ክርስቶስን የሰበከበት ትጋት፣ የፃፋቸው መልእክቶችና ያነጻቸው አብያተ ክርስቲያናት ዓለምን አናወጡ። ሮም ውስጥ በኔሮን እጅ በሰይፍ እንዲገደል በተፈረደበት ጊዜ፣ የክርስቶስን ፍቅር ተሞልቶ ነበር። የሮማውያን ሰይፍ የሱን ሥጋ ቢቆርጠውም፣ እርሱ ግን ሕይወት ክርስቶስ ነውና መሞትም ለእኔ ረብ ነው ብሎ በደስታ ተቀበለው። በሰማዕትነቱ ጊዜ የፈሰሰው ደም፣ ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት የመንፈሳዊ ልምላሜ ዘር ሆነ። የሁለቱ ሐዋርያት ቅርስ አይሁድና ሮማውያን "ገደልናቸው፣ አጠፋናቸው" ቢሉም፣ እነዚህ ቅዱሳን ግን እንደ ስንዴ ተፈጭተው የክርስቶስ አካል የሆኑትን ምእመናን ህይወት የሚመግቡ ሕያው ሆነው ቀሩ። የጴጥሮስ ትሕትና ራስን ለክርስቶስ ዝቅ ማድረግን አስተማረ። የጳውሎስ ቅንዓት ወንጌልን እስከ ዳርቻው ማድረስን አሳየ። የእነርሱ ሞት የክርስቲያኖች የሕይወት ዘር ነው። የሐዋርያቱ ሞት የሮም አደባባይን በደማቸው ቅድስና ቀባው፤ ጨለማን በብርሃን፣ ክፋትን በፍቅር፣ ዲያብሎስንም በትሕትና ድል ነሱ። ዛሬም፣ እነዚህ ታላላቅ አባቶች በምናደርገው ጸሎትና በምንከተለው ምግባር አብረውን አሉ። የቅዱስ ጴጥሮስ የዋህነትና የቅዱስ ጳውሎስ ጥበብ በሕይወታችን እንዲጠቅመን፣ የቅዱሳኑ ጸሎትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። እንኳን ለዚህ በረከት አደረሰን! ✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨ ▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬▬ +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ++++ ++++ ወወላዲተ ድንግል ++++ ++++ ወመስቀሉ ክቡር++++ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን
† † † በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † † ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ 📖 ከመጽሐፍ አንደበት 📖 ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ "ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡ ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ኦሎምፒያስ ከላከው መልእክት የተቀነጨበ ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † †
† † † በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † † ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ 📖 ከመጽሐፍት አንደበት 📖 ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ በመስቀል ምልክት ሳታማትብ ከቤትህ አትውጣ፡፡ በትር፣ መሳሪያ፣ የማይበገር ምሽግም ይሆንሀል፡፡ ሰውም ሆነ ጋኔን አንተን ለማጥቃት አይደፍሩም፤ እንደዚህ ያለ ኃይለኛ የጦር ትጥቅ ታጥቀሃልና፡፡ ይህም አንተ ልክ እንደ ወታደር እንደሆንክ፣ ከአጋንንት ጋር ለመዋጋት ዝግጁ እንደሆንክ፣ በድልም አክሊልን እንደምታገኝ ምልክት ነው፡። መስቀሉ ያደረገውን አታውቁምን? ሞትን አሸንፏል፣ ኃጢአትን አጥፍቷል፣ ሲኦልን ባዶ አድርጓል፣ ሰይጣንን ከዙፋን አውርዷል፣ አጽናፈ ዓለሙንም ወደ እግዚአብሔር መልሷል፡፡ ታዲያ ኃይሉን ትጠራጠራለህ? መስቀሉ ይህን ኹሉ ድንቅ ነገር አድርጎልናል፤ መስቀል በአጋንንት ፊት የቆመ የሽንፈታቸው መታሰቢያ ነው፤ ክርስቶስ እባቡን የገደለበት ሰይፍም ነው:: መስቀል የአብ ፈቃድ፣ የአንድያ ልጁ ክብር፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣ የመላእክት ውበት፣ የቤተክርስቲያን ጠባቂ ነው፡፡ ጳውሎስም እንዳለው መስቀል የቅዱሳን መከታ ነው፤ የዓለም ኹሉ ብርሃንም ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የነፍስ ምግብ ገጽ 78 ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † †
† † † በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † † ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ 📖 ከመጽሐፍ አንደበት 📖 ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ ....በምትጸልይበት ጊዜ ከከሰስህ ራስህን ክሰስ፡፡ ምላስህን ብትስልና ብታሾል በገዛ ኃጢአቶችህ ላይ ይኹን፡፡ አንተ ራስህ በገዛ ራስህ ላይ ያደረግኸውን እንጂ ሌላው በአንተ ላይ ያደረገብህን ክፉ ነገር አትናገር። እጅግ የሚከፋው ጉዳት አንተ ራስህ በራስህ ላይ የምታደርሰው ጉዳት ነውና፡፡ አንተ ራስህ ራስህን ካልጎዳኸው በቀር ሌላው አንተን ሊጎዳህ አይችልምና። ስለዚህ የሚበድሉህን ትበቀላቸው ዘንድ ብትሻ፥ መጀመሪያ በራስህ ላይ ተነሣሣ፤ ያን ጊዜም ማንም የሚደበቅ የለም። ሌላውን ለመክሰስ ብለህ ፍርድ ላይ ብትቀመጥ በአንተ ላይ ትልቁን ጉዳት ያደረስኸው አንተው ራስህ መኾንህ ተፈርዶብህ ትመለሳለህና፡፡ እንደው እስኪ ንገረኝ! እገሌ “በድሎኛል'' ብለህ መጥቀስ የምትችለው በደል ምንድን ነው? ያ እገሌ ያልኸው ሰው እንደ ሰደበህ፣ እንደ ቀማህ፣ ብዙ የብዙ ብዙ በኾኑ ሥጋቶችም እንደ ከበበህ ነው የምትጠቅስውን? ተው ይህ በደልን መቀበል አይደለም:: እኛ በመጠን ብንኖር ትልቁን ጥቅም የምናገኘው እኛው ነን፡፡ የሚጎ'ዳው እንዲህ ያደረሰው ሰው ነው እንጂ እንዲህ የተቀበለው ሰው አይደለም። ተጎጂውና ጎጂው ማን እንደ ኾነ ለይቶ ፍጹም አለማወቅ ደግሞ ለክፋታችን ኹሉ መንሥኤ ከኾኑ ነገሮች ኹሉ ቀዳሚው ነው። ይህንን በደንብ ብናውቀው ኖሮ ራሳችንን ባልጎዳነው ነበር፤ ሌላውን ሰው ልንጎዳው እንደማንችል ዐውቀን ያ ሌላው ሰው እንዲጎ'ዳ ብለን ባልጸለይን ነበር:: በደል ዕዳ የሚኾንብን ሌላው ሰው ሲበድለን ሳይኾን እኛ ሌላ ስውን ስንበድል ነውና። ስለዚህ ሌላውን በድለህ እንደ ኾነ ራስህን መርምር፤ ተበድለህ እንደ ኾነ ግን ከኹሉ የሚበልጠውን በጎ ነገርን አድርጎልሃልና ለበደለህ ሰው ጸልይለት፡፡ ምንም እንኳን የበዳዩ ሕሊና እንደዚያ ያልነበረ ቢኾንም፥ አንተ ግን በአኰቴት የታገሥኸው እንደ ኾነ ከኹሉ የሚበልጠውን ረብ ጥቅም ታገኛለህ፡፡ የበደለህን ስው ጻድቃን ሰዎችም ሕግጋተ እግዚአብሔርም ክፉ ግብሩን ይመሰክሩበታል የተበደልከው አንተን ግን አክሊል ያጎናጽፉሃል፤ ከፍ ከፍ አድርገውም ያመሰግኑሃል። የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ገጽ 25 ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † †
#ሰኔ_12_የቅዱስ_ሚካኤል_ዓመታዊ_በዓል!! 👉 እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ። •• 👉 በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡ •• 👉 ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን ፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡ •• 👉 ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ •• 👉 ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ •• 👉 ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡ •• 👉 በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡ •• 👉 ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “ የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ? ” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡ •• 👉 ለጊዜው “ በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም ” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ ድረስልኝ ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡ •• 👉 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡ 👉 ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡ •• 👉 ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው፡፡ •• 👉 ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን ፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን ፣ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † 📩@gesem24bot https://t.me/gesem24
видео или голосовое, без подписи