የኡስታዝ አቡ ዐብዱልመናን ኻሊድ ቢን ጠይብ ቻናል
Статистика📌 ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ የተወዳጁ ኡስታዝ አቡ አብዱልመናን ኻሊድ ጠይብ:- 🔛 ተቀርተው ያለቁ እና እየተቀሩ ያሉ ደርሶች 🔛 በፊት የተደረጉ እና አዳዲስ ሙሀደራዎች 🔛 ኹጥባዎች ጭምር የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 633
- 1/48двое суток
- 725
- 1/72трое суток
- 782
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
🍒 ከምላስ ጣጣ እራሳችንን ነፃ እናውጣ❗️ አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنْ جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا﴾ «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አንድ ነገረኛ ሰው ወሬን ቢያመጣላችሁ፣ አረጋግጡ።» [አል-ሑጁራት፡ 6] በሌላም አንቀፅ እንዲህ አለ:- ﴿وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ﴾ «ስለ በእርሱ…
🍒 ከምላስ ጣጣ እራሳችንን ነፃ እናውጣ❗️ አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنْ جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا﴾ «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አንድ ነገረኛ ሰው ወሬን ቢያመጣላችሁ፣ አረጋግጡ።» [አል-ሑጁራት፡ 6] በሌላም አንቀፅ እንዲህ አለ:- ﴿وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ﴾ «ስለ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል።» [አል-ኢስራእ፡ 36] የአላህ መልእክተኛም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «كَفَى بِالْمَرْءِ كَذِبًا أَنْ يُحَدِّثَ بِكُلِّ مَا سَمِعَ» «አንድ ሰው የሰማውን ሁሉ ማውራቱ ብቻ ውሸታም ለመባል ይበቃዋል።» ሙስሊም ዘግቦታል። ይህ ማለት ሰው የሚናገረው ነገር ሁሉ ውሸት ነው ማለት አይደለም። ትርጉሙ ግን፦ ሰው የሰማውን ሁሉ ሳያረጋግጥ የሚያስተላልፍ ከሆነ፣ በእርግጥ ውሸት የሆነውንም ያስተላልፋል፤ በዚህም ውሸት ውስጥ ይወድቃል። 👂 ምክንያቱም ሰው የሚሰማው ነገር ሁሉ እውነት አይደለም፤ እውነትም አለ፣ ውሸትም አለ። ስለዚህ ሁሉንም የሚያስተላልፍ ሰው ውሸትንም ሳያውቅ ያስተላልፋል። 👌 በተለይ የሰዎችን ክብርና ስም በሚመለከት ጉዳይ አንድ ሰው ስለ ሌላ ሰው፦ 👉 እንዲህ አደረገ፣ 👉 እንዲህ ተናገረ፣ 👉 እንዲህ ነው፣ 👉 እንዲህ ተብሎ ሰምቻለሁ፣ ብሎ ከመናገር ጠንቃቃ መሆን አለበት በተለይ ሳያረጋግጥ ማስተላለፍ በጣም አደገኛ ነው። 🫵 ወሬን ለሚያስተላልፍ ሰው ምክር ወንድሜ ሆይ! ከሰማኸው ነገር ሁሉ ተጠንቀቅ። ሰው ነገረኝ ብለህ የሰማኸውን ሁሉ ወዲያውኑ ለሌላ ሰው አትንገር። ከመናገርህ በፊት ራስህን ጠይቅ፦ 1. ይህ ነገር እውነት መሆኑን አረጋግጫለሁን? 2. የነገረኝ ሰው ታማኝ ነውን? 3. ይህን ነገር ለሌላ ሰው መናገር በሸሪዓ ይፈቀዳልን? 4. ማስተላለፌ ጥቅም አለው ወይስ ጉዳት ያመጣል? 5. ይህ ነገር ስለ እኔ ቢነገር እኔ ራሴ ሌሎች እንዲያስተላልፉት እወዳለሁን? አንዳንድ ጊዜ በአንድ ደቂቃ የተነገረ ቃል የብዙ ዓመታትን ወዳጅነት ሊያፈርስ ይችላል። ወንድሞችን ሊያለያይ፣ ቤተሰብን ሊያፈርስ፣ በሰዎች መካከል ጥላቻን ሊዘራ ይችላል። በተለይ የአንድ ሙስሊምን ክብርና ስም የሚነካ ነገር ከሆነ ይበልጥ መጠንቀቅ አለብህ። «እኔ የሰማሁትን ብቻ ነው የተናገርኩት» የሚለው ሰበብ ከአላህ ዘንድ አያድንህም። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ፦ «ለአንድ ሰው የውሸታምነቱ ምልክት የሰማውን ሁሉ ማውራቱ ነው» ብለዋል። 👇ስለዚህ መመሪያህ ይህ ይሁን👇 👉 መልካም ከሆነ ተናገር፤ ጎጂ ከሆነ ዝም በል፤ እውነቱን ካላወቅክ አረጋግጥ፤ የሙስሊምን ክብር የሚነካ ከሆነ ደግሞ በእጥፍ ተጠንቀቅ። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿مَا يَلْفِظُ مِنْ قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ﴾ «ማንኛውንም ቃል አይናገርም፤ ከእርሱ ጋር የሚጠብቅና የሚመዘግብ ቢኖር እንጂ።» [ቃፍ፡ 18] 👅 ምላስ ትንሽ ነው፤ ነገር ግን በእርሱ የሚመጣው ኃጢአት ትልቅ ነው። አንድ ቃል ሰውን ሊያስከብረውም፣ ሊያዋርደውም ይችላል። አዛኙ ነብያችን ﷺ እንዲህ አሉ:- «وَهَلْ يَكُبُّ النَّاسَ فِي النَّارِ عَلَى وُجُوهِهِمْ ـ أَوْ قَالَ: عَلَى مَنَاخِرِهِمْ ـ إِلَّا حَصَائِدُ أَلْسِنَتِهِمْ؟» «ሰዎችን በፊታቸው — ወይም በአፍንጫቸው — ወደ እሳት የሚደፋቸው ምላሶቻቸው በሚሰበስቡት ነገር በስተቀር ምንድነው?» 🤲 አላህ ከምላሳች ክፋት ይጠብቀን 🤲 ✍ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/2100
🍒የሰለፉዮች መድረሳዎች የተማሪዎች ሙሐደራ ፕሮግራም አጠር ያለ ግጥም 👌 ልጆች በሙሐደራዎቻቸው ላይ ባሳዩት ብቃት የተደሰተ ወላጅና የወላጆች ተወካይ የሆነ ወንድም የቋጠራቸው ስንኞች 👇አንባቢ👇 🎙 ኡስታዝ አቡ አብድልመናን ካሊድ ጠይብ አላህ ይጠብቀው 📅 ቅዳሜ : 2/12/2018/E.C🗓 🕌በአል-ፈላሕ መስጂድና መርከዝ (ዳለቲ) 🎧 ሙሐደራውን በድምፅ ለማግኘት 🎧 📎https://t.me/merkezalfellah/7837 https://t.me/Abuabdlmenan/2099
🍒የሰለፉዮች መድረሳዎች የተማሪዎች ሙሐደራ ፕሮግራም 👌 ስለፕሮግራሙ አመርቂነት የተሰጠ ሐሳብ 🎙 በኡስታዝ አቡ አብድልመናን ካሊድ ጠይብ አላህ ይጠብቀው 📅 ቅዳሜ : 2/12/2018/E.C🗓 🕌በአል-ፈላሕ መስጂድና መርከዝ (ዳለቲ) 🎧 ሙሐደራውን በድምፅ ለማግኘት 🎧 📎https://t.me/merkezalfellah/7838 https://t.me/Abuabdlmenan/2098
Live stream finished (1 hour)
Live stream started
🌎ቀጥታ ስርጭት Live straem💥 📖የዛሬው እለት ከመግሪብ እስከ ዒሻ የተፍሲር ፕሮግራም 📖 ሱረቱ አን-ነሕል 📖 📚 ከ101ኛው አንቀፅ ይጀምራል 🎙የኡስታዝ አቡ ዐብዱልመናን ኻሊድ ቢን ጠይብ አላህ ይጠብቀው። 🕌በታላቅዋ ፉርቃን መስጂድ አላህ ይጠብቃት። 📚የኪታቡ pdfለማግኘት👇👇 https://t.me/Al_Furqan_pdf/694 🛜ለቀጥታ ስርጭት👇👇 https://t.me/Abuabdlmenan?livestream https://t.me/Abuabdlmenan/2031
🤲 ዱዓ አብዛ ለመልሱ አትቸኩል❗️ ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ይላሉ፦ لا تقل: «دعوت الله كثيرًا ولم يستجب لي» على وجه الاعتراض واليأس؛ لأن الشيطان قد يستغل تأخر الإجابة فيُلقي في قلبك اليأس، ويقول لك: كم مرة دعوتَ الله ولم تحصل على ما تريد؟ والواجب أن يبقى العبد حسن الظن بالله، صابرًا، موقنًا بحكمة الله ورحمته. فقد يتأخر المطلوب، وقد يُعطى العبد خيرًا منه، وقد يُصرف عنه بسبب دعائه شرٌّ لا يعلمه. “የዱዓህ መልስ ስለዘገየ እንዳትቸኩልና ‘ዱዓ አደረግሁ፣ ዱዓ አደረግሁ፣ ግን አልተመለሰልኝም’ እንዳትል። ምክንያቱም ሸይጣን ይህንን ሀሳብ በልብህ ውስጥ ሊጥል ይችላል፤ ‘ስንት ጊዜ አላህን ለመንክ ነገር ግን የጠየቅከው አልመጣም’ ይልሃል። ከዚያም ከአላህ እዝነት ተስፋ እንድትቆርጥ ያደርግሃል። ስለዚህ የዱዓህ መልስ ቢዘገይም ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጥ።” ዱዓ ካደረክ በኋላ በትዕግሥት ጠብቅ፣ በአላህም ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኑርህ። የአላህ መልስ መዘግየት ማለት አልሰማህም ወይም አይወድህም ማለት አይደለም። አዛኙ ጌታችንእንዲህ ይላል:- ﴿وَلَا تَيْأَسُوا مِنْ رَوْحِ اللَّهِ إِنَّهُ لَا يَيْأَسُ مِنْ رَوْحِ اللَّهِ إِلَّا الْقَوْمُ الْكَافِرُونَ﴾ [يوسف: 87]. «ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ እነሆ ከአላህ እዝነት ከሓዲ ሕዝቦች እንጂ ተስፋ አይቆርጥም» ነብያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል:- "ከእናንተ አንዱ በዱዓው እስካልተቻኮለ ድረስ ዱዓው ተቀባይነት ይኖረዋል። እርሱም፦ «ዱዓ አደረግሁ፣ ግን ዱዓዬን አልተቀበለኝም» ብሎ እስካልቸኮለ ድረስ።" 👌የዱዓው መልስ ቢዘገይ እንኳ ይሄኔ ስንት የማታውቀው በላእ ተመልሶልሀል አልያም ደግሞ በኼራ ይከማችልሀል ብቻ ተስፋ ቆርጠህ ዱዓን ከማድረግ አታቁም❗️ ✍ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/2093
https://t.me/Abuabdlmenan/2089
Live stream finished (1 hour)
Live stream started
🌎ቀጥታ ስርጭት Live straem💥 📖የዛሬው እለት ከመግሪብ እስከ ዒሻ የተፍሲር ፕሮግራም 📖 ሱረቱ አን-ነሕል 📖 📚 ከ95ኛው አንቀፅ ይጀምራል 🎙የኡስታዝ አቡ ዐብዱልመናን ኻሊድ ቢን ጠይብ አላህ ይጠብቀው። 🕌በታላቅዋ ፉርቃን መስጂድ አላህ ይጠብቃት። 📚የኪታቡ pdfለማግኘት👇👇 https://t.me/Al_Furqan_pdf/694 🛜ለቀጥታ ስርጭት👇👇 https://t.me/Abuabdlmenan?livestream https://t.me/Abuabdlmenan/2031
Live stream finished (56 minutes)
Live stream started
👍 እውነተኛና ታማኝ መካሪ ሁን❗️ 👉 እንደ ነቢያትና እንደ መልካም ሰዎች ታማኝ መካሪ ሁን፤ ለልጆችህና ለቤተሰብህም መልካም አስተማሪና መካሪ ሁን። ምክር ታላቅ የሆነ ዒባዳ (አምልኮ) ነው። 🍒 ነቢዩ ኢብራሂም (ዐለይሂስ ሰላም) ለልጁ ታማኝ መካሪ ነበር። ከሁሉ በፊት ወደ ተውሒድና አላህ ወደ መታዘዝ ጠራው። አላህ እንዲህ ይላል፦ يَٰبَنِىَّ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰ لَكُمُ ٱلدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ «ልጆቼ ሆይ! አላህ ለናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ» (አላቸው)፡፡ [አል-በቀራህ፥ 132] 🍒 ሉቅማንም ለልጁ ታማኝ መካሪ ነበር። ምክሩን በተውሒድ ጀመረ፤ يَٰبُنَىَّ لَا تُشْرِكْ بِٱللَّهِ إِنَّ ٱلشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ ልጄሆይ ! በአላህ ላይ ማንንም አታጋራ፤ ሽርክ ታላቅ በደል ነውና።﴾ [ሉቅማን፥ 13] ከዚያም ሶላትን እንዲጠብቅ፣ በመልካም እንዲያዝ፣ ከክፉ እንዲከለክል፣ በፈተና ጊዜ እንዲታገሥ፣ ትሕትናንና መልካም ሥነ-ምግባርን እንዲላበስ መከረው። ነቢያችን ሙሐመድ ﷺ ደግሞ ከሰዎች ሁሉ በላይ ለሰዎች በጎ ምክር የሚሰጡ ነበር። እንዲህ አሉ፦ «ሃይማኖት ሁሉ በታማኝ ምክር ላይ የተመሠረተ ነው።» ሰሓቦችም፦ « የአላህ መልእክተኛ ሆይ ለማን?» ሲሉ ጠየቁ። እርሳቸውም፦ «ለአላህ፣ ለመጽሐፉ፣ ለመልእክተኛው፣ ለሙስሊሞች መሪዎችና ለሁሉም ሙስሊሞች።» አሉ። ስለዚህ በቤትህ ውስጥ መልካም መካሪ ሁን፤ ልጆችህን ተውሒድን፣ ሶላትን፣ መልካም ሥነ-ምግባርንና የነቢዩን ﷺ ሱና አስተምራቸው። ወላጆች ለልጆቻቸው ጥለው ከሚያልፉት ርስት ሁሉ የበለጠው ኢማንን፣ ጠቃሚ ዕውቀትንና መልካም ሥነ-ምግባርን ትተው ማለፋቸው ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦ وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱصْطَبِرْ عَلَيْهَا "ቤተሰብህን ሶላትን እንዲሰግዱ እዘዛቸው፤ አንተም በእርሷ ላይ ጽና።" [ጣሃ፥ 132] ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦ «كُلُّكُمْ رَاعٍ، وَكُلُّكُمْ مَسْؤُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ...» متفق عليه عن عبد الله بن عمر «ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፤ ሁላችሁም ስለ እረኝነታችሁ ትጠየቃላችሁ።» 👌 ስለዚህ አንደበትህ የበጎ ምክር ባለቤት ፣ ልብህም ለሰዎች የሚራራ ይሁን። ነብዩ ኢብራሂምን፣ ሉቅማንን፣ነቢያችን ሙሐመድን ﷺ እንዲሁም ሌሎች መካሪዎችን አርአያ አድርግ። በታማኝነት የሚመክር ሰው አላህ መጨረሻውን ያሳምርለታል፣ በእርሱም ቤተሰቡንና ሌሎችን እንዲጠቅም ያገራለታለል። 🤲 አላህ ሁላችንንም ከታማኝ መካሪዎች ያድርገን፤ የሙስሊሞችንም ልጆችና ዘሮች ያስተካክል። ✍ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/2085
🍒 የዲን ደህንነት ከአካል ደህንነት ይበልጣል❗️ ሸይኽ ፈይሰል አል-ሐሻዲ አላህ ይጠብቀው እንዲህ ይላል:- ዲንህንና ልብህን ጠብቅ፤ የጥመት ሰዎች ድረ ገጾችን አትግባ፣ የተጣመሙ ሰዎች መጽሐፎችን አታንብብ፣ ጥርጣሬን የሚያስፋፉ ሰዎችን በማኅበራዊ ሚዲያ አትከታተል፣ የሚያሳስቱ ድምፆችን አትስማ፣ ሃይማኖትን ከሚያበላሹ መድረኮች እውቀትን አትውሰድ። ምክንያቱም የዲን መበላሸት ከአካል ብልሽት የበለጠ ከባድ ነው፤ ጥርጣሬም በልብ ውስጥ ከተቀመጠ ልብን ያበላሻል። ሰው አካሉን ለመጠበቅ ከተላላፊ በሽታ ተጠቂ እንደሚሸሽ ሁሉ ዲኑን ከሚያበላሽበት ሰው መራቅ ደግሞ ይበልጥ ያስፈልጋል። ✍️ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/2084
🍒 የሸይኻችን የሕያ አልሐጁሪይ ማንኛውም እንቅስቃሴ ሒዝብዮችን እንቅልፍ ነሳቸውኮ❗️ ምን ይደረግ አላህ ሞገስን አላበሰው ለእውቀትና ለሐቅ ቆሟልና አላህ ይጠብቀው❗️ ሸይኻችን አቡ የማን ዐድናን ቢን ሑሴን አል-ሙስቀሪ አላህ ይጠብቃቸው የሚከተለው ጥያቄ ቀረበላቸው ፦ ጥያቄ፦ «ሸይኽ ያሕያ ራፊዳዎችን በመዋጋት ላይ ይገፋፋል እርሱ ግን ወደ ሳውዲ ሸሽቶ ሄዷል። ወይስ የእውቀት ክብሩ ከእርሱ ተወግዷል?» እያሉ ለሚናገሩት ሰዎች ምን እንመልስ? መልስ፦ «በአላህ እምላለሁ፣ ውሸት ነው። ከዑምራና ከዚያራ በኋላ፣ እንዲሁም አላህ ኡማውን የሚጠቅምባቸውን አንዳንድ ጠቃሚ ጉዳዮች ከፈጸመ በኋላ እርሱ እነሆ ወደ ቤቱ ተመልሷል። በአላህ ላይ የሚተማመን ታጋይ ሆኖ ተገኝቷል ወደ ተማሪዎቹም ተመልሶ ማስተማሩንና ማነፁን ቀጥሏል። በመካ የነበረበት ቦታም አብረነው ተቀምጠናል። በእርሱ ዘንድ ትህትና፣ ጀግንነት፣ በአላህ ላይ መተማመን፣ መልካምን መውደድ፣ ሰዎችን መጥቀምና ኢባዳ የሚያስደንቅ መሆኑን አይተናል። ብዙ ሰዎችም “ለምን ወደ የመን ትመለሳለህ? በአንተ ላይ እንፈራልሀለን” ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም “እኔ በአላህ ላይ እተማመናለሁ፤ ያለ ዕውቀትና ያለ ማስተማር መኖር አልችልም” ይላቸው ነበር። እንዲሁም “መውጣቴ በአላህ ላይ በመተማመን ነው፤ ጠባቂውም አላህ ነው። አላህ እንደ ጠባቂ በቂ ነው፣ እንደ ረዳትም በቂ ነው” ይል ነበር። በእርሱ ዘንድ ልግስና፣ ቸርነት፣ መልካም ስነ-ምግባር፣ ሰዎችን መጥቀም፣ ወደ እርሱ የሚመጣውን በትህትና መቀበል፣ ቁርኣንን መቅራት ከፈተናዎች ዓይኑን መስበር፣ ከዓለም ፍቅር ሰዎች መራቅ፣ ከዑለማዎች ጋር መቀመጥን መውደድ፣ የዕውቀትና የፈትዋ ሰዎችን ጥሪ መቀበል አይተናል። አላህም በእርሱ ብዙዎችን ጠቅሟል፣ ክብርና ሞገስ ሰጥቶታል። አንዳንድ ሒዝቢዮች “ከሸይኹ የዕውቀት ክብር ጠፍቷል” ሲሉ ይህ በእነርሱ ራሳቸው ላይ ያለ ችግር ነው። የተከበረ ሰው ክብርን የሚያውቀው እንደ እርሱ የተከበረ ሰው ብቻ ነው። ❌ ሲያደርጉ የነበረው የቡድን ወገንተኝነት (ሒዝቢያ) አበላሽቷቸዋል፤ የዕውቀትን ክብር እንኳን አያውቁም። ዕውቀትን የማያከብሩ ከሆኑ፣ እንዴት የዕውቀት ባለቤቶችን ያከብራሉ? 👌 እነርሱ የቡድን ሰዎች፣ የካሜራዎች እና ገንዘብ ሰብሳቢዎች ሆነዋል። እውነትንም አልረዱም፣ ሐሰትንም አላጠፉም። 👇 ስለዚህ አላህ 👇 🤲 ሸይኻችንን ከፊቱና ከኋላው እንዲጠብቀው፣ በሰጠውም ነገር በረከት እንዲያደርግለት፣ ተማሪዎቹንም እንዲጠብቅላቸው እንለምናለን 🤲 👍 በሰላምና በድል ወደ ተማሪዎቹ ስለተመለሰም ለአላህ ምስጋና ይገባው። ✍ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/2083
🍒ዲናችንን ተምረን ከአጥፊና ከአሳሳቾች ሴራ እራሳችንን ከዚያም ዲናችንን እንጠብቅ❗️ 👇 ይህንን ያማረና ከማር የጣፈጠ የኢማሙ አሕመድን ንግግር አስተውሉ! الحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي جَعَلَ فِي كُلِّ زَمَانِ فَتْرَةٍ مِنَ الرُّسُلِ بَقَايَا مِنْ أَهْلِ العِلْمِ، يَدْعُونَ مَنْ ضَلَّ إِلَى الهُدَى، وَيَصْبِرُونَ مِنْهُمْ عَلَى الأَذَى، يُحْيُونَ بِكِتَابِ اللَّهِ تَعَالَى المَوْتَى، وَيُبَصِّرُونَ بِنُورِ اللَّهِ أَهْلَ العَمَى. فَكَمْ مِنْ قَتِيلٍ لِإِبْلِيسَ قَدْ أَحْيَوْهُ، وَكَمْ مِنْ ضَالٍّ تَائِهٍ قَدْ هَدَوْهُ! فَمَا أَحْسَنَ أَثَرَهُمْ عَلَى النَّاسِ، وَمَا أَقْبَحَ أَثَرَ النَّاسِ عَلَيْهِمْ! يَنْفُونَ عَنْ كِتَابِ اللَّهِ تَحْرِيفَ الغَالِينَ، وَانْتِحَالَ المُبْطِلِينَ، وَتَأْوِيلَ الجَاهِلِينَ، الَّذِينَ عَقَدُوا أَلْوِيَةَ البِدْعَةِ، وَأَطْلَقُوا عِنَانَ الفِتْنَةِ، فَهُمْ مُخْتَلِفُونَ فِي الكِتَابِ، مُخَالِفُونَ لِلْكِتَابِ، مُجْمِعُونَ عَلَى مُفَارَقَةِ الكِتَابِ، يَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ، وَفِي اللَّهِ، وَفِي كِتَابِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ، يَتَكَلَّمُونَ بِالمُتَشَابِهِ مِنَ الكَلَامِ، وَيَخْدَعُونَ جُهَّالَ النَّاسِ بِمَا يُشَبِّهُونَ عَلَيْهِمْ، فَنَعُوذُ بِاللَّهِ مِنْ فِتْنَةِ المُضِلِّينَ ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው፤ በነቢያት መካከል የመልእክት መቋረጥ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፣ ከዕውቀት ባለቤቶች የቀሩ ሰዎችን ያኖረ፤ እነርሱም የተሳሳቱ ሰዎችን ወደ ቅኑ መመሪያ ይጠራሉ፣ ከእነርሱም የሚደርስባቸውን ጉዳት በትዕግሥት ይሸከማሉ።በአላህ መጽሐፍ የልብ ሙታኖችን ሕያው ያደርጋሉ፤ በአላህም ብርሃን ዓይነ ልባቸው የታወረ ሰዎችን ሐቅን እንዲያዩ ያደርጋሉ።ሰይጣን የገደላቸውን ስንቶች እነርሱ ሕያው አደረጓቸው! የጠፉና የተወናበዱ ስንቶችንም ወደ ትክክለኛው መንገድ መለሷቸው! 👌በሰዎች ላይ ያላቸው ተፅእኖ እንዴት ያማረ ነው! ነገር ግን የሰዎች በእነርሱ ላይ የሚያሳድሩት ተፅእኖ እንዴት የከፋ ነው❗️ እነርሱ የአላህን መጽሐፍ ከወሰን አልፈው የሚያጣምሙትን፣ ውሸት የሚፈጥሩትን እና ባለማወቅ የሚተረጉሙትን ይከላከላሉ። እነዚያ ሰዎች የቢድዓን ዓላማ ተሸክመው፣ የፈተናን በር ከፍተዋል። በቁርኣን ውስጥ ይጋጫሉ፣ ቁርኣኑንም ይቃረናሉ፤ ቁርኣንን በመተውም ላይ ተስማምተዋል። ስለ አላህ፣ በአላህ ላይ፣ እንዲሁም በአላህ መጽሐፍ ላይ ያለ እውቀት ይናገራሉ። የተምታቱና አወናባጅ ንግግሮችን በመጠቀም የማያውቁ ሰዎችን ያታልላሉ።ስለዚህ እኛ ከአሳሳች ሰዎች ፈተና በአላህ እንጠበቃለን አዎን❗️ 💯 በየዘመኑ ዲናችንን የሚያበላሹ አስተምዕሮቱን የሚበክሉ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚያወናብዱ የውስጥ ጠላቶች ይመጣሉ ነገር ግን አላህ በእዝነቱ የነዚህን አጥፊዎች ተንኮል የሚያኮላሹ ሴራቸውን የሚያመክኑ ጀግና ዑለማዎችን ይፈጥራል ምስጋና የተገባው ሀያል ጌታ ነው 👌 ግን አንተ ከነዚህ የዲን ጠባቂዎች ለመሆን እውነተኛ ተማሪ ሁን አንቺም ሁኚ 👇ይህንንም እወቅ👇 👉 ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች መንሀጅ ከምር ጠንክረህ ካልተማርክ ግን እራስህንም መጠበቅ አትችልምና የመጣው መሀበል ሁሉ ይወስድሀል❗️ 🤲 አላህ ከፈተና ይጠብቀን 🤲 ✍ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/2082