- Последний пост
- 23 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Видео (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 133
- 1/48двое суток
- 152
- 1/72трое суток
- 164
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በርካታ የዱንያን ፈተናዎች እና ደስ የማይሉ የሚረብሹ ስሜቶችን በየቀኑ እንታገላለን ። በዚህ ሁሉ መሀል ደህና መስለን ለመታየት የምናደርገው ጥረትም ሌላው ከባድ ትግል ነው። © https://t.me/abuhanif1446
ወንጀል በውስጥህ ተደብቆ አይቀርም፤ የሰራኸው ወንጀል ፊትህ ላይ ይመሰክርብሃል! የአላህን ትዕዛዝ መጣስና በፈጸምከው ወንጀል መዘፈቅ ገና በወጣትነትህ የፊትን ኑር ይገፍፈዋል። ውበትህን አጥፍቶ፣ ፊትህን አጨልሞ፣ በቁምህ እንደበሰበሰና እንደጠወለገ አስፈሪ ሬሳ ያደርገዋል። ከአላህ ቅጣትና ቁጣ በፊት፣ ፊትህ ላይ የሚታየው የወንጀልህ ክፋትና ውርደት ለሰው ሁሉ ማሳፈሪያ ይሆንብሃል!» ሸይኽ ሙሐመድ ሙኽታር አሽ-ሺንቂጢ © https://t.me/abuhanif1446
💡 ኢብኑል ቀይይም رحمه الله እንዲህ ብለዋል፦ 🛑 “ከሰለፎች አንዳንዶቹ እንዲህ ብለዋል፦ የዱንያ መከራዎችና ፈተናዎች ባልነበሩ ኖሮ፣ በቂያማ ቀን እጅግ ድሆች (ከመልካም ምንዳ የተራቆትን) ሆነን እንመጣ ነበር።” 📚 عدة الصابرين ص ٥١ 📚 ማለትም : ሙእሚን በዱንያ የሚያጋጥሙት መከራዎች፣ ሕመሞች፣ ችግሮችና ፈተናዎች ኃጢአቱን ያስወግዳሉ፣ ደረጃውንም ያሳድጋሉ፤ ስለዚህ እነዚህ መከራዎች በእውነቱ ለአኼራ ትልቅ ሀብት ናቸው። ስለዚህ ሰው በፈተና ጊዜ መታገስና በአላህ ላይ መተማመን ይገባዋል❗️ ✍ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/1919 https://t.me/abuhanif1446
የአሹራ ቀን ፆም! ➖ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿صيامُ يومِ عاشوراءَ، إنِّي أحتَسِبُ على اللَّهِ أن يُكَفِّرَ السَّنةَ الَّتي قبلَهُ﴾ ➖“የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።” ሙስሊም ዘግበውታል: 1162 በሌላ ሀዲስ ➖ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾ የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።” ሙስሊም ዘግበውታል: 1134 የዘንድሮ (1448 ዓ.ሂ) ዓሹራ ጾም የፊታችን ሀሙስ ሰኔ 18/2018 ነው የሚውለው። ቀኑን መፆሙ የ አንድ ዓመት ያለፈ ወንጀልን ያስምራል። ከፊት 9ነኛውን ቀን ወይም ከኋላ 11ኛውን ቀን መጾም ተወዳጅ ነው። እና በዱአቹ እንዳትረሱኝ አደራ አላህ ደርሰው ከሚፆሙት ያድርገን🤲አሚን
⭐️ ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ዘንድ ለእኔ የምታወርደውን ማንኛውንም በጎ ነገር በጣም የምፈልግ ድሀ ነኝ። ሁሉንም ጭንቀትህን፣ ሀዘንህንና ህመምህን ይዘህ ለአላህ ብትሰግድ ከዚህ ታላቅ ቁርኣናዊ ዱዓ ውጭ ምንም ባትደጋግም እንኳ፣ ይህ ዱዓ በውስጡ ያንተን ፍላጎትና ድህነት የሚገልጽ ታላቅ ትርጉም ይዟል። አላህም ጉዳይህን ያስተካክልልሃል፣ ያበለጽግሃል፣ ታላላቅ የሆኑ የበጎ ገፀበረከት መክፈቻዎችንም ታያለህ። ﴿ربِّ إنّي لمَا أنزلتَ إليَّ من خَيرٍ فَقِيرٌ﴾ "ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ዘንድ ለእኔ የምታወርደውን ማንኛውንም በጎ ነገር በጣም የምፈልግ ድሀ ነኝ።" የነብዩ ሙሳ ልብ በፍርሃትና በሀዘን ተጭኖ ሳለ በዚህ ዱዓ ተጓዘ። እውነተኛ ደግ ባሮች ወደ አላህ የሚጓዙበትን የፍላጎትና የመተማመን ጣፋጭነትን ይዞ ወደ አላህ በልቡና በነፍሱ ተመለሰ ። 👉 አላህም ዱንያን ሰጠው፣ ደህንነትን አጎናጸፈው፣ በአእምሮው እንኳ ውል ብሎ የማያውቀውን መልካም በሮችንም ከፈተለት። እኔም ምንም ያህል በመልካም ሁኔታ ውስጥ ብሆን "ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ዘንድ ለእኔ የምታወርደውን ማንኛውንም በጎ ነገር እጅግ የምፈልግ ድሀ ነኝ❗️ ✏️ አቡ አብድልመናን https://t.me/Abuabdlmenan/1870 https://t.me/abuhanif1446
📌 ያለ ሂሳብ የሚሰጠው ታላቅ ምንዳ! 📖 አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፦ «ታጋሾች ምንዳቸውን ያለ ልክ (ያለ ሂሳብ) ሙሉ በሙሉ ይሰጣሉ።» [አዝ-ዙመር፡ 10] ኢማም አል-በገዊ ይህንን አንቀጽ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦ «በዕለተ ቂያማ በዱንያ ላይ በፈተናና በመከራ ያለፉ (ታጋሽ) ሰዎች ይመጣሉ ለእነሱ የሚቆም ሚዛን አይኖርም የሚዘረጋም የሥራ መዝገብ አይኖርም። ይልቁንም ምንዳቸው ያለ ምንም ሂሳብና ልክ በላያቸው ላይ ይዘንብላቸዋል። እነዚያ በዱንያ ላይ በሰላምና በጤንነት የኖሩት ሰዎች እነዚህ የፈተና ባለቤቶች ያገኟትን ያንን ታላቅ ትርፍና ምንዳ ባዩ ጊዜ፦ "በዱንያ ላይ ሳለን ሥጋችን በመቀስ ተቆራርጦ በነበረ ኖሮ!" ብለው እስኪመኙ ድረስ።» 📙 ተፍሲር አል-በገዊ © https://t.me/abuhanif1446
ታላቁ ታቢዒይ ሐሰን አል በሰሪይ رحمه الله እንዲህ በማለት ዱዐ ያደርግ ነበር “አላህ ሆይ! በህመም ጊዜ ከሚጸጸቱ፣ሀብት ሲመጣ ከሚፈተኑ፣ በድህነትም ጊዜ ከሚያዝኑ ሰዎች አታድርገኝ።” © https://t.me/abuhanif1446
አላህ ዘንድ ካልሆነ አብዛኛው “ታዋቂነት” ፈተና ነው። © https://t.me/abuhanif1446
🎯በካምፓስና በከፍተኛ ት/ቤቶች በጀመዓ ስራ ላይ ከሴቶች በኩል በአሚሮችና ኡስታዞች ደረሰብን ካሉት ግፍ ጀርባ በመጠኑ ካስተዋልኩት እውነታ! 🔍የሴቶች ድርሻና የ"ተጎጂነት" ስነ-ልቦና እፀፅ በእስልምና ሴት ልጅ የክብር ማማ ላይ የተቀመጠች ዕንቁ ናት። በጀመዓ ስራ ውስጥ የምታበረክተው አስተዋፅኦም ለዲኑ ህያውነት ወሳኝ ነው። ሆኖም ግን፣ "ጀመዓ" የሚለውን ጥላ እንደ መሸሸጊያ በመጠቀም፣ ከወንዶች ጋር የሚደረጉ መረን የለቀቁ ንክኪዎች የሴቷን ክብርና ማንነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥሉ ናቸው። ብዙ ጊዜ ሴቶች በዚህ ሂደት ውስጥ የሚፈፅሙት ትልቁ እፀፅ "አለማስተዋል" እና "ራስን በከንቱ መተማመን" ውስጥ መጣል ነው። አንዲት ሴት ከወንድ ጋር በጀመዓ ስራ ሰበብ ስትቀራረብ፣ ንግግሯን ማለስለሷ፣ በየማህበራዊ ሚዲያው በግል (Inbox) የምታደርገው የለቀቀ ወሬ እና "ወንድሜ ነው" በሚል ሰይጣናዊ ትብታብ ውስጥ መውደቋ ለጥፋቱ ዋነኛ በር ከፋች ነው። እዚህ ላይ የሚታየው ትልቁ ግድፈት ደግሞ ጥፋቱ ተከስቶ ካለቀ በኋላ የሚመጣው የ"ተጎጂነት" ድራማ ነው። ሴት ልጅ እንደ እኩል ተሳታፊነቷ፣ ለተፈጠረው ወንጀል ኃላፊነቱን ከመውሰድ ይልቅ፤ "አታለለኝ፣ እኔ የዋህ ስለሆንኩ ነው፣ እርሱ ኡስታዝ/አሚር ስለሆነ አመንኩት" የሚሉ የዝሆን እንባዎችን በማፍሰስ ራሷን ከጥፋተኝነት ነጻ ለማውጣት ትሞክራለች። ይህ አይነቱ አካሄድ ሁለት ትልልቅ ችግሮችን ይይዛል። አንደኛው፣ ወንጀሉን ቀልሎ እንዲታይ ማድረግ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ሴት ልጅ ለአእምሮዋና ለድርጊቷ ኃላፊነት የማይሰማት ደካማ ፍጥረት አድርጋ እንድትቆጠር ማድረጉ ነው። ወንድ ልጅ ስሜታዊ ፍጡር እንደመሆኑ፣ ሴት ልጅ አጥር ካልሆነችለትና የራሷን ክብር ካላስጠበቀች፣ የዲን እውቀቱና የማዕረግ ስሙ ከመሳሳት ሊያድነው አይችልም። ስለሆነም፣ እህቶች በጀመዓ ስራ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ከሀያእ (እፍረት) እና ከኢስላማዊ ስነ-ምግባር ጋር ማጣመር ይኖርባቸዋል። "ችግሬን ሊረዳኝ ቀረበኝ" የሚለው ሰበብ ለብቸኝነት እና ለሐራም ግንኙነት መንገድ መጥረጊያ እንጂ መፍትሄ ሊሆን አይችልም። እውነተኛ ጥንካሬ ያለው አላህን በመፍራት እና ለራስ ክብርን በመስጠት ውስጥ እንጂ፣ ጥፋት አጥፍቶ በሰው ላይ በማላከክ አይደለም። ጀመዓው የዒባዳ ቦታ እንዲሆን፣ ሴቶች የራሳቸውን ድንበር ጠብቀውና ለክብራቸው ዋጋ ሰጥተው በመንቀሳቀስ ግንባር ቀደም ተቆርቋሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል። C https://t.me/abuhanif1446
•እነዚያ እንቅልፍ አጥታችሁ ያሳለፋችኋቸው ረዥም ሌሊቶች፣ ዓይኖቻችሁ እስኪዝሉ የተለዋወጣችኋቸው መልዕክቶች፣ የልብን ሰላም የነሱት እነዚያ ማለቂያ የሌላቸው ወሬዎች... ዛሬ የት ደረሱ? ለካስ በአላህ ጥላ ስር ያልተመሰረተ ፍቅር መጨረሻው ባዶነት፣ ትርፉም የደረቀ ቀልብና የቆሰለ ህሊና ብቻ ነው። ያ ሁሉ የጊዜ መስዋዕትነት አንዳችም መልካም ነገር ሳይጨምርላችሁ እንደ ጉም በኖ ቀረ አይደል!? © https://t.me/abuhanif1446
📌 አንዳንድ መጠበቆች ልባችሁን እያነደዱትም ቢሆን የሚሰጧቹ ፍፁም ሀሴት አለ! 🔗 ስሙኝማ! የምንጠብቀው አላህን ብለን አይደል!? 🔥 በዙሪያችን ሀራም እንደ ጎርፍ ተትረፍርፎና ተዝረክርኮ ሳለ ፤ አንድ ጊዜ እንኳ ዞር ብለን ሳንመለከተው ፤ በቀጭኗ የሀላል ድልድይ ላይ ተጠንቅቀን የምንራመደው አላህን ብለን አይደል!? 🔥 መንገዱን ለይቶ ባላወቀ መንጋ መሀል ብቻችንን ባይተዋር የሆንነው ፤ ከነሱ የምንሻል ሆነን ሳለ በብዙዎች እንደ ፋራ የምንታየው ለአላህ ብለን አይደል!? 🔥 እየታገስን ፣ እየጠበቅን ፣ እየፀናን ፣ እየበረታን ያለነው አላህን ብለን አይደል!? 🥇 አዎ በአላህ ይሁንብኝ ለሱ ስንልማ ነው! ሰለዚ እንቀጥላለን ፤ በያዝነው መንገድ መጨረሻ ላይ አላህን እንደምናገኘው ስናስብ ልባችንን የሚሞላውን ፍፁም ሀሴት ይዘን እንፀናለን! 📌 ወዳጆቼ ከዱንያ ይልቅ አኼራን መርጠናልና በርቱ መከፋታችሁን ውጣቹ ፅኑ ለእኛ አላህ አለን ኢንሻአላህ وَعَجِلْتُ إِلَيْكَ رَبِّ لِتَرْضَىٰ © https://t.me/abuhanif1446
🌴በኢማሞች የተነገሩ ወርቃማ አባባሎች፦ 🔹እርግጠኛ እስከምትሆን ድረስ መውሰድ የሌለብህ ሶስት ነገሮች፦ “ማር፣ የገንዘብ ብድር እና ሚስት”። 🔹ከሦስቱ ነፃ ካልሆንክ በስተቀር እውነተኛ ሰላም አታገኝም፦ “ከልክ ያለፈ ሀሳብ፣ ከዕዳ እና ከመጥፎ ጓደኛ”። 🔹ቢዘገዩ አላማውና ጥቅሙ የሚጠፋባቸው ሶስት ነገሮች፡- “የሰርግ ድግስ፣ የለቅሶ ታዕዚያ እና የመግሪብ ሶላት”። 🔹ሁለት ነገሮች ዘላቂነት የላቸውም፡- “ወጣትነት እና ጥንካሬ”። 🔹ሁለት ነገሮች ጠቃሚ ናቸው፡- “ጥሩ ባህሪ እና ይቅርባይነት”። 🔹ሁለት ነገሮች ወደ ከፍታ ያመራሉ፡- “ትህትና እና የሰዎችን ሃጃ ማሟላት”። 🔹ሁለት ነገሮች አደጋን ለመመለስ ሰበብ ናቸው፡- “ሰደቃ እና የዝምድና ትስስርን መጠበቅ”። © https://t.me/abuhanif1446
ሞት ማለት እንዲህ ነው። የቱንም ያህል ብትወደድ፣ የቱንም ያህል ብትከበር፤ መጨረሻህ ግን «ፀሐይ ሳይበረታ ቀብረን እንመለስ» በሚል መመሪያ ይቋጫል። ሁሉም ወደ ራሱ ኑሮ ለመመለስ ይቸኩላል። © https://t.me/abuhanif1446
без подписи
без подписи
የሃላል ሐዘን ከሀራም ደስታ ይበልጣል!! © https://t.me/abuhanif1446
без подписи
➞ማለዳ መልዕክት ««ህይወት ሚስጥር ናት። ምን እደሚጠብቅህ ፣ምን እንደሚያጋጥምህ አታውቅም። ሁሉንም ነገር ለመቀበል እራስህን ዝግጁ አድርግ። ደግም ሲያጋጥምህ አመስግን፣ ክፉም ሲያጋጥምህ ታጋሽና አመስጋኝ ሁን ። ከችግርም ጋር ምቾት አለና እራስህን አፅናና። ይቺ ምድር የፈተና ቦታ መሆኗን ላፍታም አትዘንጋ። አላህም እንዲህ ይለናል፦ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ 📖 አል-አንቢያ: 35 📖 ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡ «አስታውስ! አላህ ከታጋሾች ጋር መሆኑን። አላህን በኸይር ጠርጥረው ኸይር ይሰጥሃል። وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ 📖አል ዱሃ :5📖 ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡ እናም አላህ እዳለው:- فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا 📖 አል-መዓሪጅ:5📖 መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡ وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ 📖አሊ-ዒምራን:146 📖 አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል። https://t.me/abuhanif1446
አንዳንድ ጊዜ ያሰፈልጉናል የምንላቸው ሰዎች፤ከአላህ ውጪ ማንም እንደማያስፈልገን ያስተምሩናል። © https://t.me/abuhanif1446
የወንድ ድንግልና... ~ ዛሬ ላይ ስለ ትዳር ስታስብ የጭንቀት ጥላ የሚያጠልባት፣ በትላንት የጥቃት ጠባሳ ወይም በወጣትነት ስህተት ምክንያት የውስጥ ስብራት ያጋጠማት እህቴ ሆይ፤ አንቺ ለሰዎች የፍርድ ሚዛን ሳይሆን ለፈጣሪሽ ሰፊ እዝነት ቅርብ ነሽ። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፤ "ቢክራ" (ድንግልና) የሴት ልጅ ብቻ መለያ ተደርጎ መወሰዱ የማህበረሰባችን ትልቁ የዕይታ ስህተት ነው። ወንድ ልጅም ድንግልና አለው፤ እርሱም የነፍሱ ንፅህናና ከዝሙት የራቀ ማንነቱ ነው። ልዩነቱ ግን የሴቷ ጉዳይ በሰዎች ዘንድ ግልጽ መሆኑና የወንዱ ግን በምስጢር መጋረጃ መሸፈኑ ብቻ ነው።አንድ ወንድ ሺህ ጊዜ ዝሙት ላይ ወድቆ ራሱን እንደ ንፁህ አድርጎ ሲያቀርብ፣ አንዲት ሴት ግን በትላንት ቁስሏ ምክንያት የጥፋተኝነት ስሜት ተሸክማ ስትማቅቅ ማየት የፍትህ መዛባት ነው።በተለይም በልጅነት ዕድሜያቸው ጥቃት ለደረሰባቸውና በጭካኔ መዳፍ ውስጥ አልፈው ድምፅ ላጡ እህቶች «አማራጭ የላችሁም» የሚል ማህበራዊ ጫና መፍጠር የድንቁርና ቅሪት ነው። አላህ ዘንድ በትክክለኛ ተውባ የተመለሰች ነፍስ፣ ከቶውንም ስህተት ካልሰራች ነፍስ ጋር እኩል የምትሆንበት ሰፊ የራሕመት ደጅ አለ። ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) አግብተው የፈቱትንም ሆነ የተለያየ የታሪክ ዳራ ያላቸውን ታላላቅ እናቶቻችንን በማግባት ያስተማሩን ትልቁ ቁምነገር፤ ሴት ልጅ መመዘን ያለባት በሽፋኗ ሳይሆን በውስጥ ማንነቷ መሆኑን ነው። እህቴ ሆይ፤ አላህ አንቺን የሚመዝንበት መስፈርት ከሰዎች እይታ እጅግ የላቀ ነው። እርሱ የልብሽን ስብራት ያውቃል፣ በምስጢር የምታፈስሽውን የእንባ ዘለላ ያያል። ዛሬ ላይ ብዙዎች ትኩረታቸው አካላዊው ምልክት ላይ ብቻ ሆኖ፣ ከበስተጀርባው ያሉትን ሺህ የሕመም ታሪኮችና የተሰበሩ ተስፋዎችን ዘንግተውታል። ስለዚህ በትላንት ቁስልሽ ውስጥ ሆነሽ ዛሬን አትቅበሪው። አንቺን በትላንት ታሪክሽ ሳይሆን ዛሬ በያዝሽው የኢማን ጥንካሬና የልብ ንፅህና የሚወድሽ፣ ክብርሽን የሚጠብቅ አማኝ ወንድ አታጪም። አላህ ለታገሱትና ወደ እርሱ ለተመለሱት ድልንና ደስታን ያዘጋጃልና ተስፋ አትቁረጪ። የፈጣሪ እዝነት ከሰዎች ወሬ ይገዝፋል! © https://t.me/abuhanif1446