tgindex

Addis Ababa Design And Construction Works Bureau

описание

Government Organization

21 186
подписчиков
Охват к подписчикам
13,3%
ERR
Реакции к просмотрам
0,11%
121 на 50 постов
Пересылки к просмотрам
0,05%
53
Постов в день
11,3
всего 183

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 14 авг.በከተማዋ የፍጆታ አቅርቦትን በማሳደግና ሕገ-ወጥ ንግድን በመቆጣጠር የኑሮ ውድነትን መከላከል ተችሏል- አቶ ጃንጥራር አባይ በከተማዋ የተጀመረው የገበያ ማረጋጋት እና የሕገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር ሥራዎች የፍጆታ አቅርቦትን በማሳደግና የኑሮ ውድነትን ትርጉም ባለው መንገድ በመከላከል ረገድ ስኬታማ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አስታወቁ። የአዲስ አበባ የገበያ ማረጋጋት፣ ሕገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የ”አዲስ አበባ ታምርት” ግብረ-ኃይል ባለፉት ሁለት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግሟል፡፡ ግብረ-ኃይሉ በከተማዋ የኑሮ ውድነትን ለመከላከል ከሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሶስት ወራት ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ የገባ ሲሆን፣ ባለፉት 60 ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት መድረክ ገምግሟል። በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በከተማዋ የፍጆታ አቅርቦትን ማሳደግ እና ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን መከላከል በመቻሉ ገበያውን ማረጋጋት እና የኑሮ ውድነትን ትርጉም ባለው መንገድ መከላከል ተችሏል ብለዋል። ባለፉት ሁለት ወራት ሕጋዊ የንግድ ሥርዓትን በማስፈን ረገድ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውንም ተናግረዋል። ምክትል ከንቲባው አያይዘውም የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት በኩል የነዋሪውን እርካታ ማሳደግ ያስቻሉ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው፣0,95%
  • 14 авг.የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በአዲስ አበባ ጉብኝት አደረጉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራንን ያካተተ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ:: የልዑካን ቡድኑ የአብርሆት ቤተ መጽሀፍ፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ የአራዳ ፓርክ፣ የወንዝ ዳር ልማት እና የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል:: በጉብኝታቸው ባዩት የቱሪዝም ሀብትና በአዲስ አበባ ፈጣን የልማት ጉዞ እጅግ መደነቃቸውን ገልጸዋል:: አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም በከተማዋ የሚገኙ ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የልማት ስራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋት እና የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።0,94%
  • 11:42የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማቶች ገጽታን ከመቀየር ባለፈ በአእምሮ፣ በጤና እና በአካል የበለጸገ ትውልድን ለመገንባት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው በአዲስ አበባ የተገነቡ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ገጽታን ከመቀየር ባለፈ በአእምሮ፣ በጤና እና በአካል የበለጸገ ትውልድን ለመገንባት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ነዋሪዎች ገለጹ። በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች የከተማዋን መሠረተ ልማት ከዘመኑ ጋር በማስተሳሰር፣ የነዋሪዎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ማሻሻልና አረንጓዴ ቦታዎችን በማስፋፋት ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ችለዋል። ከተማዋን ለቱሪስቶች ማራኪ ከማድረጉም በላይ በወንዞች ዳርቻዎች ላይ የነበሩ የጎርፍ አደጋ ስጋቶችን በመቀነስ ህብረተሰቡ ንጽህናው የተጠበቀ የመኖሪያ እና መዝናኛ ስፍራዎችን እንዲያገኝ አድርጓል። በዚህም ዘላቂ የከተማ ልማት እውን እንዲሆን በማስቻል የዜጎችን የኑሮ ጥራት ከፍ አድርጓል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ሥራ ከፍተኛ የገጽታ ግንባታ ከመፍጠሩም በላይ ሁሉንም ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ አካታች ልማት መሆኑን ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሳይ ተስፋዬ እንደገለጹት፤ የተከናወኑት ግዙፍ የልማት ሥራዎች ለንባብ፣ ለምርምር እና ለህፃናትና ወጣቶች መዝናኛ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። በተለይም የቱሪዝም ፍሰትን በማሳደግና የውጭ ምንዛሬ ገቢን በመጨመር ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት እምነታቸውን ገልጸዋል።0,83%
  • 16 авг.እንኳን ደስ አለን!! ዛሬ በከተማችን በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዮብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያመርት እና በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዮብ ፍሳሽ የሚያጣራ የኮዬ ፍሳሽ ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን አስመርቀን አገልግሎት አስጀምረናል። ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ በቱሉ ጉዶ፣ ለገዳዲ ክፍል 2፣ በረከት የጋራ መኖሪያ አካባቢ፣ ቦሌ አራብሳና ሌሎችም በርካታ ጉድጓዶችን አልምተን በከተማችን ከአምስት ዓመት በፊት የነበረው 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ በቀን የማምረት አቅም ዛሬ ላይ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ አድርሰናል፡፡ በተመሳሳይ ለረጅም ዘመን በከተማችን የሚገኙ ወንዞች በፍሳሽም፤ በደረቅ ቆሻሻም ሲበከሉ ቆይተዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት የፍሳሽ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና የማጣራት አቅምን ለማሳደግ ከለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በሰጠነው ከፍተኛ ትኩረት በ2009 ዓ .ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ ከ253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ማሳደግ ችለናል፡፡ ፕሮጀክቶቹ የነዋሪዎቻችንን ጤናና ንጽህና የሚጠብቁ፣ የወንዞቻችንን ብክለት የሚቀንሱ፣ የአካባቢ ጥበቃችንን የሚያጠናክሩ ናቸው። አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ውብ፣ ጽዱ፣ ጤናማ፣ አረንጓዴ፣ ዘመናዊና ለትውልድ የምትመች ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ግብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት እውን ላደረጋችሁ፤ በተለይ ደግሞ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ የብድር አገልግሎት እየሰጠን ያለውን የዓለም ባንክ፣ እንዲሁም የውሃው መገኛ አካባቢዎችን በትብብር እንድናለማ ላገዘን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ ከሁሉ በላይ ዘላቂ ኑሯቸውን ሲመሩበት የነበረውን መሬት ለዚህ ታላቅ ልማት የለቀቁ አርሶ አደሮች እና ለፕሮጀክቱ ስኬት ሌት ተቀን ያለእረፍት የተጉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አመራሮች እና ባለሙያዎችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ አመሰግናለሁ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ0,70%
  • 17 авг.አዲስ አበባ፥ -ህፃናት በአስተማማኝ ደህንነት እና እንክብካቤ የሚታነፁባት ምቹ–ውብ ከተማ!0,55%
  • 14 авг.ስለ #አረንጓዴዐሻራ መርሃግብር ማወቅ ያለብዎት 10 እውነታዎች፦ ለለመለመች ኢትዮጵያ ተስፋን መትከላችንን እንቀጥል!0,53%
  • 17 авг.የመዲናችን አዲስ አበባ ያሳለፍነው ሳምንት ዐበይት ተግባራት:-0,50%
  • 16 авг.ኢትዮጵያ የዘመናት ስብራቶቿን ለመጠገን እየመከረች ነዉ! የአንዲት ሀገር የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ጉዞ አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው በህዝቦች የጋራ መግባባትና በጠንካራ ሀገራዊ አንድነት ላይ ሲገነባ ብቻ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ በገለልተኛ ተቋም የጀመረችው ሀገራዊ ምክክር የቆዩና የተወሳሰቡ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ፈትተን፣ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የተከፈተ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነዉ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገልተኛ ሆነ ከተመሰረተ ጀምሮ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። አሁን ላይ ሂደቱ እጅግ ተስፋ ሰጪና ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ኮሚሽኑ በመላው ሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መዋቅሩን ዘርግቶ፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ግብዓቶችንና አንገብጋቢ ሀገራዊ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራን በስኬት አጠናቋል። አሁን ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ ከ4,000 በላይ ተወያዮቹ ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ከትጥቅ ትግል ወደ ሳላም አማራጭ የተመለሱ ሃይሎች ፣ የዲያስፖራ አባለት፣ ምሁራንና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተገናኝተው ታሪካዊ ምክክሩን እያሳለጡ ነዉ። ሀገራዊ ምክክር የጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ የወደፊት እጣ-ፈንታ የሚወሰንበት ብሄራዊ መድረክ ነው። ሀገራዊ ምክክርን በአግባቡ በመጠቀም ከተወሳሰበ ቀውስና ከእርስ በርስ ጦርነት ወጥተው ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት የተሻገሩ በርካታ ሀገራትን ማንሳት ይቻላል። ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓት ካደረሰባት ጥልቅ ማህበራዊ ቁስልና የርስ በርስ ጦርነት ስጋት የወጣችው በሀገራዊ ምክክር (CODESA) አማካኝነት ነው። የፖለቲካ ሃይሎች በጥላቻ ፈንታ ይቅርታንና እርቅን በማስቀደማቸው ዛሬ ደቡብ አፍሪካ ጠንካራ ዲሞክራሲ መገንባት ችላለች። ቱኒዚያ እ.ኤ.አ በ2011 ከነበረው ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ፣ የሀገር መፍረስ ስጋትና አለመረጋጋት ህዝቧን የታደገችው በሲቪል ማህበራት መሪነት በተደረገ ብሄራዊ ምክክር ነው። ይህ ምክክር ሀገሪቱን አዲስና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ለማርቀቅ አብቅቷታል። የእነዚህ ሀገራት ተሞክሮዎች የሚያሳየን በቅንነትና በቁርጠኝነት በጠረጴዛ ዙሪያ ከተቀመጥን የማይፈታ የትኛውም ውስብስብ የፖለቲካ ቀውስ እንደሌለ ነዉ። ስለዚህ የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግና ከልቡ የሚሻ ሁሉ ዜጋ ሀገራዊ ምክክሩ የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ የሚወስን ስለሆነ በሃሳብ፣ በዕውቀት፣ በንቁ ተሳትፎና በጸሎት መደገፍ የሁላችንም የዜግነት ግዴታ ነው።0,41%
  • 16 авг.без подписи0,27%
  • 16 авг.без подписи0,15%
  • 11:42без подписи0,00%
  • 11:42без подписи0,00%