tgindex
የነብዩ ☪ S, A, W ☪ ሀዲሶች❤️

የነብዩ ☪ S, A, W ☪ ሀዲሶች❤️

Статистика

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን✔ JOIN 👇 @Adnan567mh 🌐💚💛❤️

Последний пост
25 июн.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
2 870
+1 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
5 499
20 постов
Вовлечённость
191,6%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • Hi everyone! 👋 Thank you for using the best Telegram anti-spam bot! Building and improving it over the past 9 years has been a real pleasure, and today we have something big to share. 🎉 We've completely rewritten telegram-bot.app from the ground up: faster, easier to use, and better at protecting your groups than ever. Here's what's new: • Sharper spam filtering: new, more accurate detection that catches more spam with fewer false positives. • In-house AI moderation: our own models scan images, videos and GIFs for unwanted content in real time, on our own servers and at speed. • File antivirus: attachments are scanned before malware can spread. • Malicious link scanning: dangerous and unwanted links are caught automatically. • External invite detection: links to other groups and channels get flagged. • Captcha & join checks: stop spam bots at the door. And by popular demand, more ways to pay: alongside cards, we now accept crypto (BTC, LTC, ETH, XRP) and Telegram Stars. Explore everything new at telegram-bot.app. Thank you for nine years of trust. Here's to many more. 🙏

  • 20 мар.2 430185

    🌙 በተክቢራው እንደመቅ! ✨​"አላሁ አክበር.. አላሁ አክበር.. ላ ኢላሀ ኢለላህ.."✨ 🕋ተክቢራው ይቅደም፣ ይውጣ ድምጻችን፣ በአላህ ይደሰት፣ ዛሬ ልባችን። ውጭም ያላችሁ፣ ሀገርም ያላችሁ፣ ተክቢራው ይሙላው፣ በየቤታችሁ።🕋 ​ይህ ድምፅ የትውስታ ብቻ አይደለም፤ የልባችን ትርታ፣ የእምነታችን ቃል፣ የህብረታችን መገለጫ እንጂ! ​ሀገር ውስጥ ያላችሁ በየመስጂዱና በየቤቱ ድምፃችሁን ከፍ አድርጉት፤ በስደት ያላችሁም የሀገር ናፍቆትና ብቸኝነት ሳይበግራችሁ በኩሽናችሁ በየኢጃዛ ቤታችሁ ሁናችሁ በኩራት አላህን አላቁት።      "ተክቢራው ሰማይና ምድሩን ያድምቀው!" ​🌟 ለምን እናከብረዋለን? ​የአንድነት ድምፅ፦ ቋንቋ፣ ዘርና ድንበር ሳይገድበን በአንድ ቃል የምንቆምበት ነው። ​የደስታ ምንጭ፦ ከረመዳን ጾም በኋላ አላህ ስላገራልን የምናመሰግንበት ነው። ​የኩራት መግለጫ፦ የትም እንኑር የት፣ እምነታችንን በኩራት የምናውጅበት ድምፅ ነው። ​"ኢድ ማለት ደስታ ብቻ አይደለም፤ ኢድ ማለት እርስ በርስ መተሳሰብ፣ በአንድነት መቆም እና ፈጣሪን ማላቅ ነው!" ​ናሁኑ! በያላችሁበት ተክቢራውን አድምቁት፤ ቪዲዮውን በማጋራት የኢዱን ድባብ ለዓለም እናዳርሰው። ​መልካም የኢድ በዓል ለሁላችንም ይሁን! 🎉 @Adnan567mh

  • 20 февр.2 823174

    ☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን✔ JOIN 👇 @Adnan567mh 🌐💚💛❤️

  • 19 февр.2 6832512

    በረመዳን ውስጥ በየቀኑ ሦስት ሰዓታት አሉ ምንም ይሁን ምን እንዳያመልጧቸው‼ ✅ እነዚህን ሦስት ሰዓታት በወር ዘጠና ሰአታት ይሆናል እንደሚከተለው፡- ⏰ #ኢፍጣር_ሰዓት ይህንን ጊዜ ለዱአ አድርጉት፣ ምክንያቱም ጾመኛ ሰው ጾሙን በሚያፈጥርበት ጊዜ ዱአው አይመለስም ፣ እናም በጾምህ ውስጥ ሁሉ ምልጃዎችህ ይመለሳሉ።☑️ ⏰ ሁለተኛው ሰዓት #የሌሊቱ_የመጨረሻ_ክፍል ነው። ከአላህ ጋር የኸልዋ ጊዜ ያድርጉት። ⏰ ሦስተኛው ሰዓት #ከፈጅር_ሰላት_በኋላ እስከ ፀሐይ መውጫ ድረስ መስገጃችን ላይ እናሳልፍ ረሱል ﷺ"#ፈጅርን በጀመአ ሰግዶ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ #በዚክር ቆይቶ #ሁለት ረከአ #የሰገደ ሰዉ ሙሉ #ሀጅና #ኡምራ እንዳደረገ ይቆጠርለታ።" ✋ እነዚህ ዘጠና ሰዓታት ተጠቀምባቸው፣ የቀሩትን ጊዜያት ዚክር እናብዛ፣ ቁርአን እንቅራ፣ ሐሜትን እንራቅ ሃሜት መልካም ስራዎችን ያጠፋል። ☞ምንም አይነት የፈርድ ሰላት እንዳያመልጥዎ በጀመአ ይስገዱ፣ የሱና ሰላቶችን እናብዛ(ምንዳዎች በእጥፍ ሚባዙበት ወር ነው) ✋ እነዚህ 30 ቀናት ይበልጥ ወደ አላህ በመቅረብ ኢማናችንን እናድስ ጊዜው ፈጣን ነው አንድ ደቂቃ በከንቱ አናሳልፍ የመጨረሻ ረመዳናችን እንደሆነ አስበን እንጠቀምበት ለሚቀጥለው አመት ለማግኘታችን ምንም ዋስትና የለንም። አላህ ከምንጠቀምበት ያድርገን🤲 ☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን✔ JOIN 👇 @Adnan567mh 🌐💚💛❤️

  • Live stream finished (1331 days)

  • 17 февр.2 3912810

    አልሀምዱሊላህ ...ወላሂ ኒዕማ ነው ዳግም ረመዳን ጋ  መገናኘት አምና አብረውን የነበሩ ስንቶቹ ዱኒያን ተሰናበቱ ..ስንቶቹ ዲነል ኢስላምን ተሰናበቱ አልሀምዱሊላህ እኛ ግን ረመዳንን ተቀብልናል ..ጀሊሉ ከሚጠቀሙት በአፊያ በኢማን ከሚጨርሱት ያድርገን ...በዱአ አንረሳሳ ወዳጆቼ 🙌@Adnan567mh

  • 6 нояб.4 1645310

    ትኩረት የነፈግነው ሐቅ ~~ "ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው" ብለዋል ነብያችን (ﷺ)። [ቡኻሪ] ይሁን እንጂ ብዙ ቁርኣን ያልቀራ ወገን እያለን ለጉዳዩ የሰጠነው ትኩረት ግን ለችግሩ የሚመጥን አይደለም። ስለሆነም ችግሩን በመቅረፍ ላይ ከራሳችን ልንጀምር ይገባል። እና * ቁርኣን ካልቀራን ለምን አንቀራም? * ያልቀራ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ ወዘተ. ካለ ለምን አናቀራም? * ይህም ካልሆነልን የሚያቀሩትን በምንችለው አቅም ለምን አናግዝም? ዛሬ ዛሬ ቁርኣን ማስተማር የሰነፎች ወይም እውቀታቸው የደከሙ ሰዎች ስራ እየመሰለ ነው። ☪️ ቁርኣን ያልቀራህ ወገኔ ሆይ! የትኩረት ማነስ እንጂ እውነት ቁርኣን ማንበብ መቻል ይህን ያክል ከባድ ነገር ሆኖ ነው ወይ? እስከ መቼ ነው 28 የዐረብኛ ፊደላትን አገጣጥሞ ማንበብ ተራራ የሚሆንብህ? ወላሂ! ተገቢ ትኩረት ብንሰጠው ቁርኣን ፈፅሞ ዛሬ በሃገራችን የሚወስደውን የጊዜ መጠን የሚጠይቅ አልነበረም። ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም ይባላል። ☑️ እና ወንድሜ ሆይ! በነፃ የሚያስተምርህ ካገኘህ እሰየው። ☑️ ካልሆነ ግን በክፍያ የሚያስተምሩ ወንድም/እህቶች ካሉም ደስ እያለህ ከፍለህ ተማር። ☑️ ለሚያሳንፉ ሰዎች ጆሮ አትስጥ። ቁርኣን መማር ዲግሪና ዲፕሎማ ከመማር በታች ነውንዴ????????? ቁርኣን መማር ቋንቋ፣ ኮምፒተር፣ ... ከመማር በታች ነውንዴ???????? ☑️  እነዚህን ነገሮች ለመማር ስንትና ስንት እያወጣን ቁርኣን ለመማር የሚወጣው ላይ ለቅሶ ማብዛት ምንድነው???? ይልቅ በጊዜ ቁርጠኛ ውሳኔ ወስን። ከዜሮም ብትነሳ እሩቅ አይደለም ትደርሳለህ። ማረም ማስተካከል ከሆነም በአጭር ጊዜ ትጋት ሁነኛ ለውጥ ታያለህ። አላህ ያግዘን። @Adnan567mh

  • 📖📖 ቁርዓን📖📖 وَذَا النُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَاضِبًا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقْدِرَ عَلَيْهِ فَنَادَىٰ فِي الظُّلُمَاتِ أَن لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ (ዓሳም ዋጠው)፡፡ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ፡፡ ☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን✔ JOIN 👇 @Adnan567mh 🌐💚💛❤️

  • 💜 ጓደኛውን ሰላት ስገድ እያለ ሲያቅተው ወደ መስጂድ ይዞት ይሄድና በውስጡ “ ጌታዬ ሆይ! እኔ አካሉን ይዤ ወደ አንተ አምጥቼዋለሁና አንተ ደግሞ ቀልቡን ወዳንተ አዙራት ። " ብሎ ዱዓ አደረገለት ። #መልካም_ጓደኛ

  • ተፍሲሩ👇 አሰላሙ አለይኩም። ደህና እንደሆናችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ይህንን መልእክት በጥንቃቄ ለማንበብ ጊዜዎን ይውሰዱ። በጣም ከባድ ነገር ነው። በአላህ ይሁንብኝ እስከ ማልቀስ ድረስ አስፈራኝ። ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ ይሁንብኝ 60 አመት እንደምትኖር አስብ። ለነዚያ 60 አመታት በቀን 8 ሰአት ከተኛህ 20 አመት ተኝተሃል። በቀን 8 ሰአት ከሰራህ 20 አመት ሰርተሃል። የልጅነት ጊዜዎ ወደ 15 ዓመታት ያህል ቆይቷል። በቀን ሁለት ጊዜ በምግብ ለመብላት ትቀበጣለህ ግማሽ ሰዓት ያህል ካሳለፍክ, 3 አመታትን ህይወትህን በመብላት ብቻ አሳልፈሃል. ስለዚህ የእንቅልፍህ፣ የስራህ፣ የልጅነትህ እና የመብላትህ ድምር፡ 58 አመት ከ60። እና 2 አመት ብቻ ነው የቀረው! በህይወትህ ለአላህ ለማምለክ ስንት ሰአት አሳልፈሃል? አላህ በፍርድ ቀን ህይወቶን እንዴት አሳለፍክ ብሎ ሲጠይቅህ ምን ትመልሳለህ? ይህ ጥያቄ100% እውነት የሆነ ጥያቄ ነው። ቁርኣን ከ600 ገፆች አይበልጥም (ወይንም 604 ገፆች እውነት ነው)። ካላመንከኝ በፍጥነት ወደ ቁርኣን  ሂድና ለራስህ ተመልከት። ስንት ገጾች እንዳሉ ታያለህ? እሺ፣ እንቀጥል... ቁርአን 600 ገፆች ነው። በ 30 ቀናት ውስጥ ለማንበብ ከፈለጉ በቀን ስንት ገጾች ማንበብ አለብዎት? በጣም ቀላል ነው፡- 600 ÷ 30 = 20 ገፆች በቀን. ያ ቀላል ስሌት ነው። በቀን 20 ገፆች ማለት ነው። በቀን 5 ወቅት ሰላቶች ስላሉን፡- 20 ÷ 5 = 4 ገፆች ከእያንዳንዱ ሰላት በኋላ። ከእያንዳንዱ ሰላት በኋላ 4 ገጾችን ካነበብክ በቀን 20 ገጾችን ታነባለህ። በአንድ ወር ውስጥ ቁርኣንን በሙሉ በቀላል እና በተረጋጋ መልኩ ታጠናቅቃላችሁ። ቆይ ግን መልእክቱ ገና አላለቀም... የቸኮላችሁ ይመስላል... እስከ መጨረሻው አንብቡ; ብዙ የቀረ ነገር የለም። ለወንድሞቻችሁ፣ ለጓደኞቻችሁ፣ እና ለሌሎች ሰዎች ሁሉ ይህን መልእክት ብታደርሱስ? ከአላህም  ባንተ ምክንያት ቁርኣንን ጨረሱ። ምን ታላቅ አጅር እንደምታገኝ ታውቃለህ? አላህ ሆይ... አንድ ሰው ቁርኣንን ባጠናቀቀ ቁጥር የነሱን አይነት አጅር ታገኛላችሁ! ታዲያ ለምን ለዚህ አመት ትርፋማ ፕሮጀክትህ አታደርገውም? በናንተ ምክንያት ሰዎች ቁርኣንን እንዲሞሉ ለምን አትተጉም? አሁንም እያመነታህ ነው? ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- " ወደ መልካም ስራ የመራ ሰው የሰራው ሰው ምንዳ ይኖረዋል።" ግሩፕ ካላችሁ አላህ ፈቅዶ ሽልማታችሁን እጥፍ ድርብ ለማድረግ ይህንን መልእክት ላኩላቸው። እና አስታውስ፣ ኃጢአት ልትሠራ በምትሆንበት ጊዜ፣ እነዚህ ሦስት ጥቅሶች፡- ➊. አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን? ➋. የጌታውንም ቦታ ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት። ➌. አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል። እነዚህን ቃላት ከወደዷቸው ሳታካፍላቸው አትውጣ። በጎን ሥራ የሚመራ ሰው የሰራው ሰው ምንዳ ይኖረዋል። ስለ አንተ ስለምጨነቅ፣ ይህን መልእክት ልኬልሃለሁ። ለምትወዳቸው ሰዎች ከእርሱ ጋር አትስማ። አላህ ጀዛህን ይክፈልህ።@Adnan567mh

  • 🌹🌹🌹መ ልካም ጁመአ ይኡንላችው ❤️❤️❤️

  • ኢማሙ ሻፊዒይ እንዲህ ይሉ ነበር ፦ ተጓዝ … ከምትለየው ነገር ምትክን ታገኛለህ ፣ ልፋ ጣር … የህይወት ጥፍጥና ያለው በጥረት ፣ በልፋት ውስጥ ነው የውሀ አንድ ቦታ ላይ መቆየት ያበላሸዋል ፤ ውሃው የሚፈስ (የሚንቀሳቀስ) ከሆነ ግን ጥሩ ይሆናል ፤ ያ ካልሆነ ግን ዉሃው ይቆሽሻል ፣ አንበሳ ከሚኖርበት ቦታ ከ(ጫካ) ለማደን ካልወጣ የሚበላውን ነገር አያገኝም ፤ ቀስትም ከደጋኑ ካልተለየ አይወነጨፍም ( ግቡን አይመታም ) ፣ ፀሀይ ሁሌም አንድ ቦታ ላይ ብቻ የምትቆይ ቢሆን ኖሮ … የሰው ልጅ ባጠቃላይ ፀሀይን በሰለቸ ነበር ። ተጓዝ ( ተሰደድ ) ጤናማ ትሆናለህ ✌🏿! #اسحاق_عبدالكافي ☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን✔ JOIN 👇 @Adnan567mh 🌐💚💛❤️

  • 6 нояб. 2024 г.10,3 тыс10742

    ትልቁ ስጦታ… ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “አላህ ገንዘብን ለሚወደውም ለሚጠላውም ይሰጣል። ኢማንን ግን ለሚወደው እንጂ ለሌላ አይሰጥም። አላህ ባሪያውን በወደደው ግዜ ኢማንን ይለግሰዋል።” ☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን✔ JOIN 👇 @Adnan567mh 🌐💚💛❤️

  • የመካ እና የመዲና ሱራዎች ጥቂት ስለ ቁርኣን (ክፍል - 1) ~ ቁርኣን ነብያችን ﷺ መካ እያሉ በሚወርድ ጊዜ የሙስሊሞች ቁጥር አናሳ ነበር። አጋሪዎች ብዙሃን ነበሩ። መዲና ውስጥ በነበሩ ጊዜ ደግሞ የሙስሊሙ ኃይል ተጠናክሯል። መካና መዲና የነበሩት ተቃራኒ ኃይሎች በብዛት ከእምነትም፣ ከንቃተ ህሊናም አንፃር ልዩነት አላቸው። በነዚህና መሰል ልዩነቶች የተነሳ በሁለቱ ዘመኖች የወረዱ ሱራዎች ትኩረትና ይዘት ልዩነት ይታይበታል። ይሄ የተወሰነ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይፈልጋል። ከወረዱበት ዘመን አንፃር ሲታይ ከ114 የቁርኣን ምእራፎች ውስጥ 20ዎቹ መደኒያ ናቸው፣ በዘመነ መዲና የወረዱ። 12ቱ ኺላፍ አለባቸው። ቀሪዎቹ መኪያ ናቸው። ስለዚህ ከቁጥር አንፃር አብዛኞቹ የቁርኣን ምእራፎች መካ የወረዱ ናቸው ማለት ነው። በነገራችን ላይ የመካ እና የመዲና ሱራዎች የሚታወቁባቸው መለያዎች አሉ። 1 - የመካ ሱራዎች፦ ሀ - "ከልላ" (كلا) የሚለው ቃል ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። ለ - ሰጅደተ ቲላዋ ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው። ሐ - በመሀላ የሚጀምሩ ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው። መ - በሑሩፉ ተሀጂ (ሑሩፉል ሙቀጠዐ) የሚጀምሩ ሱራዎችም ከበቀረህ እና ኣሊ ዒምራን ውጭ መኪያ ናቸው። በቀረህ እና ኣሊ ዒምራን መደኒያህ ናቸው። ሱረቱ ረዕድ ኺላፍ አለባት። ሠ - በውስጣቸው "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መኪያ ናቸው። ረ - በ "አልሐምዱ" የሚጀምሩ ሱራዎች መኪያ ናቸው። እነሱም አምስት ሱራዎች ናቸው። ሰ - ከሱረቱል በቀረህ ውጭ "ቀሶሱል አንቢያእ" የያዙ ሱራዎች መኪያ ናቸው። 2 - የመዲና ሱራዎች፦ ሀ - በውስጣቸው "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መደኒያ ናቸው። ለ - ስለ ሙናፊቆች የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው። አልዐንከቡት ስትቀር። እሷ ግን መኪያ ነች። ይሁን እንጂ በውስጧ ስለ ሙናፊቆች የሚያወሳው ክፍል መደኒይ ነው። ሐ - ሑዱድ እር ፈራኢድ የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው። ምንጭ፦ ዲራሰህ ፊ ዑሉሚል ቁርኣኒል ከሪም፣ ፈህድ አሩሚይ ☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን✔ JOIN 👇 @Adnan567mh 🌐💚💛❤️

  • በጣም ትልቅ ፀጋ ዉስጥ ነን! """"""""""""""""""""""""""" ታዋቂው ዳዒ ዐምር ኻሊድ እንዲህ ይላል - በአንድ ወቅት ከሆኑ ወጣቶች ጋር ተቀማምጠን ሳለን እንደዋዛ የአላህን (ሱ.ወ.) ፀጋዎች መቁጠር ጀመርን፡፡ የትኛው ፀጋ እንደሚበልጥም አወጋን፡፡ ~ ከኛ መካከል አንዱ ‹ጤና ነው› ሲል ተናገረ፡፡ ~ ሌላኛው ‹ልጆች ናቸው› አለ፡፡ ሌላው ‹ማየትና መስማት መቻል ነው› አለ፡፡ ~ ‹ትልቁ ፀጋ እናቴ ናት› ያለም አለ፡፡ ~ እንዲሁ ‹ሀብት የሠጠኝ ጌታ በርግጥም ትልቁን ፀጋ ሠጠኝ› ያለም ነበር፡፡ ~ ‹እስልምና ነው› ያለም አለ፡፡ ~ ከመካከላችን አንድ የአሥራ ስምንት ዓመት ወጣት ግን አላህ (ሱ.ወ.) ከሠጠን ፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ ‹ጌታችን ጌታችን መሆኑ ነው፡፡› አለ፡፡ ትርጉሙ ምን ማለት ይሆን? ይህ ታዳጊ ወጣት በዚህች ዓለም ላይ ትልቁ ፀጋ ጉዳያችን ይዞ ያለው አላህ (ሱ.ወ.) መሆኑ ነው ማለቱ ነው፡፡ እሱ ነው ዋስትናችን፡፡ ልባችንን፣ እጃችንን፣ ግንባራችንን… ሁሉ ነገራችን ይዞ ወደ መልካም ነገርና ወደ ስኬት የሚመራን አላህ ነው፡፡ ትልቁ የአላህ ፀጋ አላህ አላህ መሆኑ፣ አላህም ጌታችን መሆኑ ነው፡፡ ጥራትና ልዕልና የተገባው ይሁን፡፡ በአላህ ጌትነት ወደድን፣ መልዕክተኛው ነቢያችን መሆናቸውን ወደድን፣ እስልምናን በሃይማኖት በኩል ወደድን፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) ለሚወደውም ለማይወደውም ሀብት ይሠጣል፡፡ አላህ ላመነበትም ለካደዉም ገንዘብ ይሠጣል፡፡ ጤና፣ ቤትና ንብረት ይሠጣል፡፡ እስልምናን ግን የሚሠጠው እርሱ ለወደደው ሰው ብቻ ነው፡፡ ወደ መንገዱ የሚመራው ራሱ የመረጠውን ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ሙስሊም መሆን መመረጥ ነው፡፡ ሙስሊም መሆን መብለጥ ነው፡፡ ሙስሊም መሆን መወደድ ነው፡፡ ባይወደን ኖሮ መቼ ይሠጠን ነበር፡፡ አላህ ወዶን እስልምናን ሠጠቶናልና ክብር ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ይሁን፡፡ አላህ እኔ፣ አንተና አንቺ ግን ሳንለምነው፣ ሳንማፀነው ፣ ሳንወተውተው ሙስሊም አደረገን። ለኢብራሂም (ዐ.ሰ.) አባት ፣ ለኑሕ (ዐ.ሰ.) ልጅ፣ ለሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) አጎት ያልሰጠውን ፀጋ ሠጠን፡፡ አላህ እስልምናን ሠጠን፡፡ አምላካችን ንፁህ የተፈጥሮ ሃይማኖትን ለገሰን፡፡ እንደ እስልምና ምን ገር የሆነ ሃይማኖት አለ፡፡ ለመረዳትም ሆነ ለትግበራ አይከብድም፡፡ ይህ በርግጥም ትልቅ ችሮታ ነው። አላህ የትላልቅ ችሮታዎች ባለቤት ነው። እርሱ ችሮታውን ለሚሻው ሰው ብቻ ይሠጣል። ነገርግን ብዙዎች አላህ የሠጣቸውን ፀጋ አያስተውሉም ፤ አያስተነትኑም ፤ አስተንትነውም አያመሰግኑምም፡፡ የእስልምና ፀጋ ከየትኛውም ፀጋ ሁሉ የላቀ ነው፡፡ ቢመዘን ቢለካ የትኛውም ፀጋ አይደርስበትም። ምስጋና ወደቀናው መንገድ ለመራን ጌታ ይሁን። እሱ ባይመራን ኖሮ  ባልተመራን ነበር። "እስልምናን ለሰጠን አላህ ምስጋና ይገባው" በሉ። ☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን✔ JOIN 👇 @Adnan567mh 🌐💚💛❤️

  • 🍂 ⇛ የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል… ~ ከመካከላችሁ አፀያፊ ተግባር ሲተገበር ያስተዋለ ሰው በእጁ ያስወግደው። ካልቻለ በምላሳ። ካልቻለ በቀልቡ ይጥላ። [ሙስሊም] @Adnan567mh

  • 🔶"ዱዓዕ ሁሉም ነገር ያስተካክላል  አንተ ብቻ ዱዓ ስታደርግ የቂን ይኑርህ በቅርቡ የዱዓህን ፍሬ ታያለህ ኢንሻአላህ ☝️....!! ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው ከጭንቀትም አዳነው....!🥰☝️♥️ 🔶"ماذا قال يونس عليه السلام في بطن الحوت...؟!! 💙💙 🔶"وَذَا النُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَاضِبًا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقْدِرَ عَلَيْهِ فَنَادَىٰ فِي الظُّلُمَاتِ أَن لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ (ዓሳም ዋጠው)፡፡ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ፡፡ 🔶"فَاسْتَجَبْنَا لَهُ وَنَجَّيْنَاهُ مِنَ الْغَمِّ ۚ وَكَذَٰلِكَ نُنجِي الْمُؤْمِنِينَ 🔶"ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጭንቅም አዳነው፡፡ እንደዚሁም ምእመናንን እናድናለን፡፡ 🔶"وَزَكَرِيَّا إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ رَبِّ لَا تَذَرْنِي فَرْدًا وَأَنتَ خَيْرُ الْوَارِثِينَ 🔶"ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ ሲል» ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ 🔶"فَاسْتَجَبْنَا لَهُ وَوَهَبْنَا لَهُ يَحْيَىٰ وَأَصْلَحْنَا لَهُ زَوْجَهُ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا يُسَارِعُونَ فِي الْخَيْرَاتِ وَيَدْعُونَنَا رَغَبًا وَرَهَبًا ۖ وَكَانُوا لَنَا خَاشِعِينَ 🔶"ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ለእርሱም የሕያን ሰጠነው፡፡ ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት፡፡ እነርሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ኾነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡          {አል-ዓንብያዕ 87-90 }🤲      ለኛም  ጥሪያችንን ተቀበን ያረብ...!🤲 @Adnan567mh

  • ራሴን ታዘብኩት ከሁለት ቀን በፊት የረመዷን የመጀመሪያውን ጁሙዐ ለመታደም ወደመስጂድ አቀናው። ያው ረመዷንም ስለሆነ ሰው ይበዛልና መስጂድ ውስጥ ቦታ ማግኘት ማይታሰብ ስለሆነ ብዙ ሰው ውጪ እያነጠፈ ይቀመጣል። እኔን ጨምሮ ግን ሁላችንም ጥላ ቦታ ፍለጋ አይናችንን ብናማትርም ስለሌለ ፀሀይ ላይ ተቀመጥን። የተወሰነ ሰው ደሞ ሰላቱ እስኪጀመር ወደጥግ ሄዶ ከፀሀይ ተጠለለ። ይሄኔ ነው የቂያማ እለቷ ፀሀይ ትዝ ያለችኝ። ዘንግቻት ነበር እንዳሁኑ ብዙ ሺ ኪሎ ሜትር ርቃን ሳይሆን አንድ ስንዝር ያህል ቀርባን የምታቃጥለን ግዜ መኖሩን መዘንጋቴ አስገረመኝ። ብዙ ሰውም ይህን የዘነጋ ይመስለኛል። በዚያ ቀን በነጯ ምድር ላይ የሰው ዘር በሙሉ እንዲቆም ሆኖ በፀሀይ ቃጠሎ ሲነድ ሰባት ሰዎች ግን ከአላህ አርሽ ስር እንደሚጠለሉ ተነግሯል። የዱንያ ፀሀይ እንዲ ያማረረን እኛ በአርሽ ጥላ ስር ከሚጠለሉት ለመሆን መጣር ታድያ የኛ ፋንታ ነው። እስኪ ለማስታወስ ያህል እነዚህ 7 አይነት ሰዎች እነማን እንደሆኑ እንመልከት👇 🔹አቡ ሁረይራ(ረ.ዐ)እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ)እንዲህ ብለዋል። ሰባት ሰዎች አላህ ከርሱ ውጪ ሌላ ጥላ በማይኖርበት ቀን ከአርሽ ጥላ ስር ያስጠልላቸዋል።እነርሱም: 1 ፍትሀዊ መሪ፣ 2 በጌታው አምልኮ ተኮትኩቶ ያደገ እና በዚያ መንገድ ወጣትነቱን ያሳለፈ 3 አላህን እያመለከ ያደረ(አላህን ብቻውን ሆኖ ያወሳ)፣ 4 ልቦናው መስጂድ ላይ የተንጠለጠለ(ከመስጂድ ጋር የተሳሰረ)፣ 5 ለአላህ ሲሉ የተዋደዱ በርሱ የተገናኙና በርሱም የተለያዩ ሁለት ሰዎች፣ 6 ክብርና ውበት ያላት እንስት(ለወሲብ)ጋብዛው አላህን እፈራለሁ ያላት(ግለሰብ)፣ 7 የቀኝ እጁ ምትመፀውተው የግራ እጁ የማታይ ያክል ምፅዋትን የደበቀ (ግለሰብ)ናቸው። (ቡኻሪና ሙስሊም) ☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ ተማሪ ነኝ። Telegram የምጠቀመው «✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለማድረስ ብዮ ነው። ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አላህ ይ ቀበለን✔ JOIN 👇 @Adnan567mh 🌐💚💛❤️

  • ረመዷን - 4 *** ረመዷን ቀላል ወር አይደለም ። ዱዓ የሚሰማበት፣ ተውባ ተቀባይነት የሚያገኝበት፣ መልካም ሥራ የሚወደድበት ወር ነው። ደጋጎች ይህን ወር እንደ ትልቅ አጋጣሚ ይጠብቁታል። ወሩ የዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ነዉና ለረመዷን ብቻ የሚያስቀምጡት ዱዓ አላቸው። በመንፈስ ተዘጋጅተው፤ ዉስጥ ዉጪያቸዉን አጽድተው ይጠባበቁታል። ከወሣኝ ዱዓኦች መካከል የረመዷን ዉስጥ ዱዓ አንዱ ነው። ሱሑር ላይ ፆም ስትይዙ፣  ማታ ስታፈጥሩ፣ በአዛንና ኢቃማ መካከል፣ ሱብሒ ከመድረሱ በፊት ያለዉን ጊዜ፣ በሱጁድ ዉስጥ፣ ከያንዳንዱ የግዴታ ሶላት በኋላ ዱዓ በማብዛት ተጠቀሙበት። ማን ያውቃል የልባችሁ መሻት ምላሽ የሚያገኘው በዚህ ወር ዉስጥ ሊሆን ይችላል ። @Adnan567mh

  • 🍂🍁🍂የረመዷን ሌቦች🍁🍂🍁 👉 ክፍል አንድ ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን ወሰላቱ ወሰላም ወአላ አሽረፊል አምቢያኢ ወል ሙርሰሊን ነብይና ሙሃመዲን ወአላ አሊሂ ወሰህቢሂ አጅመኢን አማ በዕድ አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ የተከበራችሁ ውድ እህት ወንድሞች የአላህ ራህመት ሆኖ ይህ የተከበረው ረመዷን ወር ላይ አላህ አድርሶናል ከሚፆሙትም አድርጎናል ይህ ማለት በጣም ትልቅ ኒዕማ ነው አላህን(ሱብሃነ ወተዓላ)ልናመሰግነው ይገባል። እናም ይሄንን ትልቅ እድል ልንጠቀምበትና በአግባቡ በመጠቀም ለኼራችን ስንቅ ልንይዝበት ይገባናል። አላህ ያላቀው የሆነ ትልቅ ወር ነው አላህ ያላቀውን ይህን ወር ደግሞ እኛም በተግባር መልካም ስራ በመስራት ልናከብረው ይገባል። እንጂ መጥፎ ስራ በመስራት አላህን ከማመፅ ልንቆጠብ ይገባል። ሃቂቃ ይህ ወር ለአማኝ ባሮቹ ብዙ የጀነት ሰበቦች የደገሰበት የሆነ ትልቅ ወር ነው። ስለዚህ አንድ ሙስሊም የሆነ አካል አኼራ የሚያሳስበው ነገ ጀነትን የሚናፍቅ የሆነ ሰው የሄንን ትልቅ አድል ሊጠቀመው ይገባል።   አላህ (ሱብሃነ ወተዓነላ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል "አያመን መእዱዳት" በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ናቸው አለ። "በናንተም ላይ ፆም ተደነገገ ከናንተ በስተፊት በነበሩት ሰዎች ላይ እንደተደነገገው" ዋናው የተደነገገበትም ምክንየት ተቅዋና ታገኙና "አላህን ልትፈሩ ዘንድ ነው" አለን ይህ የተከበረው ወር ደግሞ ቀናቶቹ በጣት የሚቆጠሩ የሚታወቁ ቀናቶች ናቸው ምክንያቱም ወሩ ከሰላሳ አይበልጥምና ከነዚህ ወር ቀናቶችም አስረኛው ቀን ላይ እንገኛለን ስለዚህ አንድ ሰው አንድ ቀን አሳልፎ ወደሌላ ቀን በተሸጋገረ ቁጥር ይህ የረህመት ወር ረመዷን እያመለጠው ነው ማለት ነው ስለዚህ ራስን በማጠንከር ወደ ኋላ ሚያደርጉንን ነገር ትተን በኢባዳ ልንጠነክር ይገባል ቀን በቀን ራሳችንን ልንፈትሽና ያለብንን ጉድለት ልንጠግን ይገባል ማለት ነው። እንደሚታወቀው ይህ ረመዷን የመልካም ስራ የቁርዓን ወር ነው የሶላት የኢባዳ ወር ነው የዚክር ወር ነው ስለዚህ አቅማችን በቻለ ልክ በኢባዳ ልንጠነክር ይገባል። በአልባሌ ነገሮች ይሄንን ውድ ትልቅ ወር ልናጠፋው አይገባም። ግዚያችንን በመልካም ነገር ልንጠቀመው ይገባል እያንዳንዱ አቅለኛ የሆነ ሰው እያንዳንዷን ሰከንድ እያንዳንዷን ደቂቃ በአልባሌ በሆነ ነገር እንዲያልፍ መፈቀድ የለብንም ይቺ ደቂቃ ይቺ ሰከንድ ናት ረመዷን ማለት የረመዷን ሰላሳ ቀን ማለት አሁን እያሳለፍናቸው ያሉት እያንዳንዷ ደቂቃና ሰከንድ ናቸው። ስለዚህ እያንዳንዷን ሰአት እያንዳንዷን ቀን እያንዳንዷን ሰከንድ በመልካም ስራ ልናሳልፈው ይገባል ማለት ነው። ወንጀል ሊበቃን ይገባል ወደ አላህ ትክክለኛ ተውበት ልናደርግ ይገባል እውነተኛ ተመላሾች ልንሆን ይገባል አስራ አንድ ወራቶች ላይ ብዙ ወንጀል አሳልፈናል ብዙ ወንጀል ሊኖርብን ይችላል አላህ (ሱብሃነ ወተዓላ) ደግሞ የዛን ወንጀላችንነ ማበሻ ረመዷንን አመጣልን እናም ይሄን የሰጠንን እድል እንጠቀምበት። ወላሂ ይሄ ትልቅ ኒዕማ ነው ስንት ሰዎች አሉ የተከለከሉ ትናንተ እንደኛው የነበሩ ረመዷንን በጉጉት የሚጠብቁ የነበሩ ሰዎችን ዛሬ አፈር በላያቸው ላይ ተጭኖባቸው ቀብር ውስጥ ገብተዋል። እንደኛው ሲጓጉ የነበሩ ሰዎች ረመዷን አንድ ቀን ሲቀረው ወደ አኼራ የሄደ ሰው አለ። ወይም ደግሞ በሌላ ምክንያት ወደ አኼራ ባይሄድም እንኳ መፆም ያልቻሉ አሉ አልጋ ቁራኛ ሆነው የተቀመጡ መፆም የእፈለጉ ያልቻሉ ብዙዎች አሉ እኛን ከነሱ አላደረገንም ሳንሞት በጤናችን ወዶን እዚህ የራህመት ወር ውስጥ አስገባን። ሃቂቃ ትልቅ እድል ሰጦናል ይሄን እድል ልንጠቀምበት ይገባል። ሁላችንም ልንጠቀምበት ይገባል ቁርዓን በመቅራት ሶላት በማብዛት ዚክር በማለት ተራዊህም በመስገድ ሰደቃ በማብዛት ለእናት አባቶቻችን ለወንድም እህቶቻችን ባጠቃላይ መልካም በመስራት ዝምድናንም በመቀጠል መልካም ስነ ምግባር በማሳየት ባጠቃላይ አላህ በደነገጋቸው ኢባዳዎች በኢኽላስ ልንጠነክር ይገባል። (አላህ የበለጠ ያውቃል) መልዕክቱን ሼር በማድረግ በዚህ ውድ ወር ከኢባዳ የተዘናጉትን ወንድም እህቶቻችንን እናንቃቸው። (በውስጥ መስመር ከአስር ላላነሰ ሰው በመላክ አብሮነታችሁን ግለፁልን።) ባረከላሁ ፊኩም በዱዓችሁ አትርሱኝ https://t.me/Adnan567mh