tgindex

አለ ሕግ

описание

ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት Alternative legal enlightenment & Service Website: alehig.com https://linktr.ee/alehig WhatsApp👉 #+251920666595 Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

16 030
подписчиков
Охват к подписчикам
21,3%
ERR
Реакции к просмотрам
0,18%
441 на 49 постов
Пересылки к просмотрам
0,55%
1 337
Постов в день
0,6
всего 50

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 12 авг.የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት (arbitration) የምስለ-ችሎት ውድድር (FDI Moot) የዞኑ አሸናፊ በመሆን አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፉ ፍጻሜ ማለፋቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፉበት በዚህ ፈታኝ ውድድር ከናይጄሪያ፣ ከኬንያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ 14 ቡድኖችን በመበለጥ ከሰብ-ሳሃራን አፍሪካ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል። በዚህ ውድድር ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ወክለው የተሳተፉት ፦ ➡ ባምላክስራ ፋሲል (የ3ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ➡ ቃልኪዳን ሰብስቤ (የ4ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ➡ ዲቦራ ታደሰ (የ4ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) እና ➡ ናሆት ግርማ (የ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ናቸው። ለዚህ አህጉራዊ ውጤት ያበቃቸው ዋና ምክንያት ምንድን ነው ? " ለዚህ ውጤት ያበቃን ቀደም ሲል በቪስ ሙት (Vis Moot) የነበረን ልምድ ነው። ከቡድናችን አራት አባላት መካከል ሦስቱ በዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ውድድር ላይ ለአንድ አመት ተወዳድረዋል። ይህ ልምድ በጣም ጠቅሞናል። አሁን ላይ የተወዳደርንበት ጉዳይ ከአለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት ጋር የተያያዙ ውስብስብ ጥያቄዎችን ያካተተ ነበር። ከዋና ዋናዎቹ የስነ-ስርዓት ክርክሮች መካከል ከሳሹ ቀደም ሲል አቤቱታውን ለሌላ አካል አቅርቦ ስለነበር አሁን እንዳይከለከል የሚለው እና የክስ ማገጃ ትእዛዝ መሰጠት አለበት ወይ ? የሚሉት ይገኙበታል። የፍሬ-ነገር ክርክሩ በበኩሉ ፍትሃዊ እና እኩል እንክብካቤ እንዲሁም ንብረት መውረስን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን አካቷል። በውድድሩ ወቅት የገጠመን ትልቁ ፈተና ከዳኞቹ ለሚቀርቡ ዝርዝር እና ያልተጠበቁ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ነው " ብለዋል። የተወዳዳሪዎቹ መሪ የሆኑትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው የህግ ተማሪ፣ የህግ ባለሙያ ቦርጋ ደለሳ፥ ተማሪዎቹ እስካሁን ያለምንም ድጋፍ ለዚህ ድል የበቁ ቢሆንም፣ በመጪው ኦክቶበር (October) ወር በቻይና በሚካሄደው የመጨረሻ ፍጻሜ ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ የገንዘብ እና የተቋማት ድጋፍ ይፈልጋሉ ብለዋል። በተለይም ፦ - ለዓለም አቀፍ ጉዞ፣ - ለእንግዳ ማረፊያ፣ - ለቪዛ፣ - ከምዝገባ ጋር የተያያዙ ወጪዎች እና ለዝግጅት ድጋፍ የሚያስፈልግ በመሆኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት (በተለይም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን) የሕግ እና የንግዱ ማኅበረሰብ፣ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች ትብብር እንዲያደርጉላቸውና እውቅና እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል። ይህ እድል የነዚህ አራት ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን፣ ኢትዮጵያን እና የአፍሪካን የሕግ ትምህርት በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅና ለመወከል የሚሰጥ ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል። ​ተወዳዳሪዎቹን ማግኘት የምትፈልጉ፣ የቡድኑ መሪ የሆኑትን የህግ ባለሙያ ቦርጋ ደለሳን በስልክ ቁጥር +251925494142 ማግኘት ትችላላችሁ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ/ም1,41%
  • 11 авг.በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገለጸ። ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል። በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል። በሲጋራ፣ በአልኮልና በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል። Source: Ethio FM 107.8 #Ethiopianbusinessdaily0,86%
  • 5 авг.የፌዴሬሽን ም/ቤት የጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን ኢ-ሕገመንግሥታዊ ሲል ሻረ 👉 " በሌላ ሰው መሬት ላይ የተገነባ ቤት የመሬቱን ባለይዞታ ባለቤት አያደርግም። " የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል የሰጣቸውን አስገዳጅ ውሳኔዎች ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ ናቸው ሲል ሽሯቸዋል። በዚህም መሠረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት "በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሠራ ሰው የቤቱ ባለቤት ይሆናል" በማለት በመዝገብ ቁጥር 30101 እና 36638 ላይ የሰጣቸውን አስገዳጅ ውሳኔዎች የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ-መንግሥቱን የሚቃረኑ ናቸው በማለት ውድቅ አድርጎታል። የምክር ቤቱ ውሳኔ እንደሚያመላክተው፤ በመንግሥት አካል ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ የመሆን እና በመሬቱ የመጠቀም ሕገ-መንግሥታዊ መብቱ ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ነው። በዚህም መሠረት አንድ ሰው የሌላ ሕጋዊ ባለይዞታ በሆነ መሬት ላይ፥ ባለይዞታው ሳይቃወመው እንኳን ቢገነባ የመሬቱ ባለይዞታነትም ሆነ የቤቱ ሙሉ ባለሃብትነት ወደ ቤቱ ሠሪ አይተላለፍም። የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(7) "በመሬት ላይ ንብረት ያፈራ ሰው የንብረቱ ባለቤት ይሆናል" የሚለው ድንጋጌ የሚሠራው ሕጋዊ የመሬት ባለይዞታነት መብት ላለው አካል እንጂ፣ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ያለ ሕጋዊ መሠረት ንብረት ለገነባ ሰው የቤት ባለቤትነት መብት ለመስጠት እንዳልሆነ ምክር ቤቱ አብራርቷል። በመሆኑም ባለይዞታው ሳይቃወም በይዞታው ላይ ቤት የሠራ ሰው የሚኖረው ሕገ-መንግሥታዊ መብት፣ ለግንባታው ያወጣውን ወጪ ወይም ግምት ከመሬቱ ባለይዞታ የመጠየቅ መብት ብቻ መሆኑ ተጠቅሷል። ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም Via @tikvahethmagazine0,67%
  • 7 апр. 2025 г.без подписи0,62%
  • 10 авг."በችኮላና በጥድፊያ" የሚዘጋጁ ህጎች፣ በህግ አወጣጥ ስርዓቱ ላይ አለመረጋጋት እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ተመላክቷል። 👉 አንዳንድ መመሪያና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የማይገመገሙ መሆኑ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። 👉 ህጎች በወጡ በሳምንት እና በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸውም እንዳሉም ተገልጿል። (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) በኢትዮጵያ የህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎች፣ የአዋጅ መሻሮችና መጣረሶች እየታዩ መሆኑን፣ ይህንንም መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ፖሊሲም ሆነ ወጥ የህግ ማዕቀፍ በሀገሪቱ አለመኖሩን ፌደራል የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት አመለከተ። ጥናቱ "የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን፣ ዓላማውም በሀገሪቱ ያለውን የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም የአተገባበር ስርዓት ከረጅምና ከአጭር ጊዜ እቅዶች እንዲሁም ከቦትስዋና፣ ከጋናና ከደቡብ አፍሪካ ተሞክሮዎች አንጻር በመመርመር የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ ነው። ህግ የማህበረሰብንና የመንግስትን መስተጋብር የሚመራ መሳሪያ እንደመሆኑ ተለዋዋጭነት ባህሪው ቢሆንም፣ የሚወጡ ህጎች ጥራት፣ ግልጽነት፣ ወጥነት፣ ተገማችነትና ቀጣይነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ጥናቱ ያስቀምጣል። ከ2010 ዓ.ም ወዲህ የተካሄደው የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በርካታ ህጎች የመውጣታቸውን ያህል፣ በችኮላና በጥድፊያ የሚወጡ ህጎች የህግ አወጣጥ ስርዓቱ የተረጋጋ እንዳይሆን፣ በህዝብና በባለሙያዎች ያልተመከረበት እንዲሆን እንዳደረጉት ጥናቱ ጠቁሟል። ይህም ባለሀብቶች የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ውሳኔ እንዳይወስኑ፣ ዜጎችም ስለ መብትና ግዴታቸው ያላቸው ግንዛቤ አናሳ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተመላክቷል። ጥናቱ ከ2010 እስከ 2018 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ አዋጆችን ሙሉ በሙሉ መመርመሩን ገልጿል። ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት፣ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋት በስድስት ተያያዥ ተቋማዊ ምሶሶዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን የለየው ጥናቱ እነሱም የህገ መንግስት የበላይነት በተግባር መረጋገጥ፣ ውጤታማ የስልጣን ክፍፍልና ሚዛን፣ ጠንካራ የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓት፣ በሙያ የታገዘ የረቂቅ ዝግጅት ተቋም፣ ትርጉም ያለው የህዝብ ተሳትፎ፣ እና ገለልተኛ የዳኝነት ቁጥጥር ናቸው። ኢትዮጵያን በተመለከተ ግን ሀገሪቱ የህግ አወጣጥ ስርዓት መረጋጋትን የተመለከተ ፖሊሲ እንደሌላት፤ ጠቅላላ የህግ አወጣጥ ስርዓትን የሚመራ ፖሊሲም እንደሌለ፤ የሚወጡ ህጎችም በአብዛኛው በጸደቁ ፖሊሲዎች ላይ ከመመስረት ይልቅ የአስፈጻሚውን ጊዜያዊ ፍላጎት የሚያንጸባርቁ ሆነው መገኘታቸውን ለይቷል። በህግ ማዕቀፍ ረገድም ኢፌዲሪ ህገ መንግስት፣ ደንብ ቁጥር 6/2008፣ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና ሌሎች ሰነዶች ቢኖሩም፣ ከማርቀቅ እስከ አፈጻጸምና ክትትል ድረስ ያለውን ሂደት በአንድ ወጥነት የሚገዛ ማዕቀፍ አለመኖሩ ተጠቁሟል፤ ያለው አሰራርም በተበታተኑና በተበጣጠሱ መመሪያዎች ላይ የተመሰረተ ነው። በአተገባበር ደረጃም ከተለዩ ክፍተቶችም ውስጥ :- - ተደጋጋሚ የአዋጅ ማሻሻያዎች (ለምሳሌ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና የኤክሳይዝ ታክስ አዋጆች በወጡ በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸው መሆኑ) ፣ - ሰፊ የአዋጅ መሻሮች (ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 ብቻውን 18 አዋጆችንና 35 ደንቦችን መሻሩ)፣ - ተደራሽ ያልሆኑ መመሪያዎች ፣ - ተቃራኒ ይዘት ያላቸው አዋጆች መውጣት፣ - ከበላይ ህጎችና ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች መኖር (በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ ማስመሰልን በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የያዘ ድንጋጌ በመሆኑ ማክሰኞ ወጥቶ በሳምንቱ ማክሰኞ ማሻሻያ የተደረገበት ሂደት መኖሩ) - የበታች ህጎች ያለ ተገቢ ግምገማ መውጣት ( በተለይ ታክስ አካባቢ ይሄ ችግር በአደገኛ ሁኔታ መስተዋሉ) - አዋጆች በተግባር ያለመፈጸም ይገኙበታል። ከጥንካሬ አኳያም የተለያዩ ግኝቶችን ያስቀመጠው ጥናቱ ባለ ሶስት ደረጃ የምርመራና የንባብ ሂደት፣ የፍትህ ሚኒስቴር ማጣራት ሚና፣ የህግ ማዕከልና አማካሪዎች መኖር፣ እንዲሁም በቅርቡ የተቋቋመው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ማሻሻያና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ እንደ አዎንታዊ እርምጃዎች ተጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የባለሙያ እጥረት፣ የተቋማት አለመናበብ፣ የአመራር ትኩረት ማነስ እና ወጥ የህግ ይረቀቅልኝ ስርዓት አለመኖር እንደ ዋና ዋና ድክመቶች ተለይተዋል። ጥናቱ ከጋና፣ ከደቡብ አፍሪካና ከቦትስዋና ተሞክሮ በመነሳት ፦ ° ፍርድ ቤቶች ግልጽ የህገ መንግስት ተጣጣሚነት የመተርጎም ስልጣን እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ° የፓርላማ ኮሚቴ ስርዓትን ማጠናከር፣ ° ሙያዊ የረቂቅ ዝግጅት አቅምን ማጎልበት፣ ° የህዝብና የባህል እንዲሁም የሃይማኖት ተወካዮች ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ፣ ° ህግ ማውጣትን ከፖለቲካ ፍጥጫ ነጻ ማድረግ፣ ° የተጠቃለለ ፖሊሲና ሁሉን አቀፍ ህግ ማዘጋጀት፣ ° ገለልተኛ የህግ ኮሚሽን ማቋቋም፣ ° በዩኒቨርሲቲዎች የሌጂስሌቲቭ ድራፍቲንግ ስልጠናና ካሪኩለም ማዘጋጀት፣ ° የህግ አወጣጥ ሉዓላዊነትን ከውጭ ተጽእኖ መጠበቅ፣ እንዲሁም የበታች ህጎችን ከአዋጅ ጋር ተጣጥመው መውጣታቸውን የሚከታተል ስርዓት መዘርጋት የሚሉ ምክረሃሳቦችን አቅርቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia0,62%
  • 28 окт.без подписи0,57%
  • 14 авг. 2024 г.без подписи0,37%
  • 14 авг.⚜አዲሱ የጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ ቁጥር 1425/2018 ⚜New _ Customs Amendment Proclamation No. 1425/2026 ⚠This New Proclamation is Effective from 23rd July; 20260,35%
  • 24 авг. 2024 г.без подписи0,31%
  • 24 июн. 2025 г.без подписи0,30%
  • 27 дек. 2024 г.без подписи0,29%
  • 5 авг. 2024 г.без подписи0,28%