tgindex
ዓምደ ሃይማኖት

ዓምደ ሃይማኖት

Статистика

ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
50
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
33 822
−56 за 2 дн.
Сутки
−8
−0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 274
40 постов
Вовлечённость
3,8%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 50
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
по 4 постам
1/24сутки в ленте
116
1/48двое суток
132
1/72трое суток
142

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • 13 авг.13из quality botton

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.7из quality bottonудалён 13 авг.

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.19из 💠 ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈ 💠удалён 13 авг.

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 авг.17711из OrthodoxAmero

    ወንድማችን አኬ በዲላ ቆጆ ነገር ከብዙ ውክቢያዎች በላይ ይህን መሰል ጥልቅ ጥቂት ውይይት ብዙ ያስጨብጣል ዲላ ያሉ ተሐድሶዎች ከነችግሮቻቸውም ጥያቄዎች እንዳላቸው እንደዚህ አይነት መድረክ ሲፈጠር ደግሞ በሩቅ ከመፈራረጅ በላይ ትክክል ያይደሉበትን ጉዳዮችን ይበልጥ እንድናቃቸው እኛ ጋ ያሉትን ለማጽናት ከእነሱም የጠፍትን ለማምጣት እነሱም በሚመለሱላቸው መልሶች ባያምኑበት እንኳን የሚታመን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት እኛጋ እንዳለ ከቤታችን ያሉትን ለማጠንከር ቆጆ ትምህርት ነው ። በመዳን ዙርያ ያሉብንን ግልጽ ልዮነቶች ወንድማችን አኬ ቁጮ ቁጮ መልሶች በመስጠት አረስርሶናል ጥምቀት እንደሚያድን ያ ማለት ደግሞ ጥምቀት ብቻ ያድነናል ማለት እንዳልሆነ የሐዋርያት ስራን የሮሜ መልእክታትን ሌሎችን አስረጂ ጥቅሶችን በመጥቀስ አስረድቷል ከተሐድሶዎች ወገን ደግሞ ጥምቀት እንደማያስፈልግ ለመዳን ማመን ብቻ እንደሚያስፈልግ ቢጠቅሱም እምነት ብቻ ነው የሚያድነው የሚል ግን አንድም አስረጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ ሳያቀርቡ ቀርተዋል ። 1.እንደ ሀሳብ ግን ዛሬ ለምሳሌ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት የተገባው ከብዙ ጉዳዮች አለመግባባ በኋላ ነው ስለዚህ ሚወያዩበት እርዕሰ ጉዳይ ቀድሞ ተይዞ ቢመጣ ። 2. የሚገባውና የሚወጣው ሰው እየበዛ ስለሆነ የበሩ መከፈትና መዘጋት ሀሳብ እየሰረቀ ስለሆነ እንቅስቀሴዎች ቢቀንሱ ካልተቻለ ከመዝጋት ወይ በሩን መክፈት ። 3. በውይይቶቹ መሀል ያሉ መሳሳቆች ቢቀሩ ። ሌላው ግን ይበል ነው አኬን ያበርክትልን ( ዲያቆን ፍፁም ከበደ ) #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 12 авг.1711из OrthodoxAmero

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 июн.2 491142из OrthodoxAmero

    + የሰው ልጅ ቅድስተ ቅዱሳን + ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰውነታችን ክፍሎች ኹሉ ለይቶ ልባችንን ብቻ ለራሱ እንዲሆን ለምን መረጠው ? "ልጆች ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ " ይላል ምሳ 23-26 እንዲሁም የመጀመርያው ትእዛዝ "አምላክህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ውደድ " የሚል ነው ዘዳ 6-5 በእውነቱ ከሆነ እንደ ርኅራኄ የውሃት ምሕረትና ፍቅር ካሉ ስሜቶች አንጻር ከልብ ይልቅ ጥልቅ ነገር በሰው ዘንድ የለም ። ልብ የሰው ልጅ እጅግ ለስላሳና ቅን የኾኑ ስሜቶች ማዕከል ነው ። ኾኖም ግን እግዚአብሔር የሰው ልብ የሚፈልገው ለዚህ ብቻ አይደለም ። በልብ ውስጥ ከደግነት ከርኅራሄ ከምሕረት ወይም ከፍቅር በላይ የኾነ ሌላ ባሕርይ አለና። ይኽውም ልብ የሰው ልጅ ማንነት ምንጭ መኾኑና ዋና ባሕርያቱ ኹሉ ከእርሱ የሚመነጩ መኾኑ ነው ። ልብ የሰው ልጅ ቅድስተ ቅዱሳን ነው ። እግዚአብሔር በውስጡ ሊያድርበት ሚያበቃውም በዚህ ልዮ ባሕርዮ ምክንያት ነው ። አንድ ሰው እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ወደደ ማለት በሙሉ ማንነቱ ወደደው ማለት ነው ። ራሱንም ያለ ምንም መከልከል ለእግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው ። አባ መቃርስ ልብ አዕምሮን ሕሊናን አሳብን እንደሚያካትት ይናገራል ። በዚህም እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ልብ እንዲፈልግና በፍቅሩም እንዲማርክ ያደረገውን ወሳኝ ምክንያት ይጠቁመናል ። እግዚአብሔር ስሜት በሚጎዳበት ወይም በሚዋረድበት ጊዜ ወዲያውኑ በሚጠፍው ስሜታዊ ፍቅር - ያ ፍቅር ምንም ያህል ከፍተኛ ቢኾንም አይደሰትም ። እግዚአብሔር የሚፈልገው የልብን ፍቅር ነው ። ይህም ማለት ሰው ራሱን (ኢጎውን) እና ማንነቱን ኹሉ አሳልፎ ሰጥቷል ማለት ነው ። ይህ ፍቅር በቁስል የሚቀሰቀስ በመከራ የሚነጥር (የሚሞረድ) እና በሞት ደግሞ ይበልጥ የሚፈጸም (ፍጹም የሚኾን) ፍቅር ነው ። ዠ ( ኦርቶዶክሳዊ የጸሎት ሕይወት "በአባ ማቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት" ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ ገጽ 248-249) ዲያቆን ፍጹም ከበደ ሰኔ 6 2018 ዓ.ም #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

  • 13 июн.1 555из OrthodoxAmero

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 июн.1 2603

    ቻናል መግዛት ሚፈልግ ያናግረኝ 👇 @Fisumkeb

  • 8 июн.1 46143из birhanuadmassa

    + The New Normal ስለሚባለው ነገር + ( Maryamawit Henok Lemessa ) ታውቃላችሁ? በአማርኛ ቀጥተኛ ትርጉም ላገኝለት አልቻልኩም (አዲሱ መደበኛነት/ አዲስ ልምምድ ሴንስ አልሰጥሽ አለኝ። በተሻለ የሚገልጽ ካለ ወዲህ በሉኝ) ፤ ለማንኛውም ምንድነው የሚለውን ለመግለጽ፦ አንድ ህሊናን የሚሰቀጥጥ ዘግናኝ ግፍ በተደጋጋሚ ሲከሰት፣ የሰው ልጅ አእምሮ ያለማቋረጥ የሚመጣበትን የድንጋጤ ማዕበል መቋቋም ስለሚያቅተው፣ ራሱን ለመከላከል ሲል ሰቆቃውን እንደ መደበኛ የዕለት ዜና ወደ መቀበል ይሸጋገራል። ያልተለመደውና አሰቃቂው ግፍ ቀስ በቀስ የህይወት አካል ሲሆን፣ ትላንት ጎረቤቱ በግፍ ተገድሎና ንብረቱ ወድሞ ያደረ ሰው፣ በማግስቱ ጠዋት ምንም እንዳልተፈጠረ አሜን ብሎ የለመደውን ኑሮውን መግፋት ይጀምራል። ይህ አደገኛ የሞራል ስብራትና የህሊና መደንዘዝ ግለሰብን ብቻ ሳይሆን ስርዓትንም ስለሚቆጣጠር ሚዲያዎች፣ የሰብአዊ መብት ተቋማትና ሚዛናዊ ነን የሚሉ ጸሐፊዎች ሳይቀሩ የሚፈሰውን የንጹሃን ደም አይተው እንዳላዩ በዝምታ ማለፍን ይመርጣሉ። ከሁሉ በላይ የዚህ አእምሮን የመቆጣጠር ሂደት አስከፊው ማሳያ፣ የህብረተሰቡ የድንጋጤ መለኪያ ከሰው ልጅ ህይወት ክቡርነት ወደ ቁጥር ስሌት መውረዱ ነው። አእምሮው በግፍ የተገራ ማህበረሰብ ንፁሀን ተገደሉ ከሚለው የሰቆቃ ጥልቀት ይልቅ፣ ለመሆኑ ስንት ተገደሉ? የሚለው ስታቲስቲክስ ብቻ ሚዛን ይደፋበታል። በአጭሩ The New Normal ማለት፣ የሰውን ልጅ ህሊና ሰልቦ፣ ሞትን፣ ፍርሃትንና ግፍን አቅፎ በሰቆቃ ውስጥ ዝም ብሎ የመኖር አሳዛኝ ልምምድ ነው። ልልምድ የሚያስከትለው ጭካኔን በጸጥታ እንዲቀበል የሚያስገድድ አስፈሪ የአእምሮ እስር ቤት ነው። ... ዛሬ በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይም በኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት፣ የንጹሃን ግድያ፣ ማዋከብ እና የንብረት ውድመት ከብሔራዊ የድንገተኛ አደጋነት ስሜት ወርዶ የተለመደ የዕለት ተዕለት ዜና ሆኗል። ለምን ከመደጋገሙ የተነሳ ተለምዷል። The Normal ሆኗል። የሰው ልጅ መከራና በግፍ የፈሰሰው የንጹሃን ደም ልክ እንደ አቤል ደም ወደ ፈጣሪ እየጮኸ ባለበት በዚህ ዘመን፣ ህብረተሰባችን ግን አደገኛ የህሊና መደንዘዝ ውስጥ ገብቶ ዋነኛ የሞራልና የሃይማኖት መለኪያውን እያጣ ይገኛል። ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ መክብብ 8፥11 ላይ "በክፉ ሥራ ላይ ፈጣን ፍርድ አይሰጥምና ስለዚህ በሰው ልጆች ልብ ክፉን ነገር ለማድረግ ሞላ" እንዳለው፣ የዚህ የህዝብ ዝምታና የመላመድ አስከፊው ውጤት ወንጀለኞችን እጅግ አደፋፍሯቸዋል። ፍርድና ተጠያቂነት እንደማይመጣባቸው ሲረዱ እብሪታቸው ጣሪያ ነክቶ፣ ዛሬ ላይ አንዳንዶች በፈጸሙት ጭካኔ በአደባባይ ሲፎክሩ ይታያሉ። ቀድሞ ወንጀል ሰርቶ መደበቅ መካድ የነበረው ተረስቶ ምን ታመጣለህ? አጠፋሃለሁ፣ ጨርስሃለሁ ወደሚል ድፍረትና መለማድ ተቀይሯል። የደነዘዘው ማኅበረሰብም ሰምቶ ያልፈዋል። ሲፎክር የነበረው አካል የተናገረውን ነገ ይፈጽመዋል። የርሸና ዜናዎቸን Scroll አደርገን እናልፋቸዋልን። አእምሯችን መሞታችን ምንም አይደል ይለናል። አንገት ቢቆረጥም ዋናው ጤና ነው ፌዝ ቢመስልም እየኖርንበት ነው። ... አንድ Record የተደረገ Video ደርሶኝ እንደ ማኅበረሰብ ምን ላይ እንዳለን ግራ ያጋባል። ወጣቱ ልጅ ''አርሲ ላይ ተገደልን ትላላችሁ? ወላሂ ገና እናጠፋችዃለን። እንኳን ለመኖር ለሰላምታ ራሱ አትቀቁም ቃፊሮች ይላል... ቀጥሎም ምራቁን ይተፋል። ሌላ የደረሰኝ Video ላይ ትላንት Record የተደረገ ነው ተናጋሪዎቹ በግሩፕ ሆነው ''አይደለም በህይወት ያላችሁትን በመቃብር ያሉትን ክርስቲያኖች ሬሳ አውጥተን ነው የምናቃጥለው ይላል አንደኛው ሌላኛው በAfaan Oromoo ምንም ብትንጫጩ እናጠፋቹሃለን ይላል... ቀጣዩ ተናጋሩ አርሲ ከእኛ ጋር ቃፊር አይኖርም። ይላል። ከኖራችሁም ግብር እየከፈላችሁ ትኖራላችሁ ይላል። የሚገርመው ከተናገሪዎቹ ግማሾቹ ፊታቸው እየታየ ነው በሰላምየሚናገሩት ከፊሎቹ ስማቸው። በድፍረት እየተባለ ያለው ለመኖር ብቻ "ልዩ ግብር እና ክፍያ መክፈል አለባቸው" እስከማለት የደረሱ ጽንፈኞች መኖራቸው የህግን መዋረድ ያሳያል። ይሁን እንጂ እዚህ ላይ በግልጽ ሊሰመርበት የሚገባው ትልቅ እውነት፣ ይህንን አጸያፊ ድርጊት የሚፈጽሙት ጥቂት አክራሪዎች ዋሃቢያእንጂ፣ አብሮ በሰላምና በፍቅር የሚኖረው፣ አብሮን ማዕድ የሚካፈለው የሌላው እምነት ተከታይ ወንድማችን አለመሆኑን ነው። ትግላችን ከደም አፍሳሽ ከአሸባሪ እና ከክፋት መንፈስ ጋር እንጂ፣ አብሮን ከኖረው ህዝብ ጋር ፈጽሞ ሊሆን አይችልም። በመጨረሻም እያንዳንዱ ምእመን ቆም ብሎ ራሱን ሊጠይቀው የሚገባ አንድ ጥልቅ ጥያቄ አለ፦ አንድ ማህበረሰብ በእውነት አደጋ ላይ የሚወድቀው መቼ ነው? መጀመሪያ ግፍ ሲታይና ሲፈጠር ነው ወይስ ሰዎች ያንን ግፍ ሲላመዱት? በእውነት ግፍን መላመድ ከግፉ በላይ አጥፊ ነው። ስለዚህ ከዚህ የዝምታ እና የመደንዘዝ መንፈሳዊና ስነ ልቦናዊ እንቅልፍ በአስቸኳይ ልንነቃ ይገባል። በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው የሰው ልጅ ክብር ይጠበቅ፣ ፍትህ እንደ ወንዝ ትፍሰስ፣ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ፤ ማንም ሰው በማንነቱና በእምነቱ የተነሳ በገዛ ሀገሩ ላይ ባይተዋር አይሁን። ሁላችንም በጋራ ለፍትህና ለንጹሃን ደህንነት ድምፃችንን ከፍ አድርገን የምናሰማበት ጊዜ አሁን ነው፤ አለበለዚያ ይህ የዝምታ አዲሱ ልምምድ/The New Normal ሁላችንንም ይውጠናል። ... ከታች የተያያዘው ምስል AI ያመረተው ነው። ከጽሁፍ ባሻገር ወገኖቻችን ያሉበትን ሁኔታ በምስል ያሳይልኝ ዘንድ ያዘጋጀሁት ነው።

  • 5 июн.1 0102из OrthodoxAmero

    " ሃይማኖት የአንድ ጎሣ ብቻ አይደለም " ጥንቅቅ ያለ ጹሑፍ ነው ( ግንጊልቻ) ድብዝዝ ሲል እያነሳው ላለንበት ችግር የአተያይ ድቀት ማነበው ኦርቶዶክስን ለአንድ ለተወሰነ ማህበረሰብ ስም ሰጥቶ በዚያ ሽፍን የሚደረጉ ሰውን ከሰውነት ውጪ አውጥቶ የሚደርሱ ግፎችን ሚያሳይ ነው አንድነት ስለማጣት ፦ " መልክአ ምድራዊ ውሕደታችን ከተረጋገጠ መቶ አመታት በኋላ እንኳን ልባዊ ውሕደት (አንድነት ) እንደሌለን የሚያሳብቁ እሳቤዎችንና ድርጊቶችን በወዳጅም በጠላትም ፈት እየተጋለጠ ነው " ይለናል ። ስለታሪክ ፦ "ታሪክ አንድን ጉዳይ ከሥር መሠረቱ ጀምረን እንድናውቀው ስሚያግዘን የአንድን ክስተት እውነትነት በስሜት የይደለ አሳማኝ በኾነ ቅቡልነት ባለው መልኩ (Logically) እንድንሞግተው ፣ አልያም እንድንቀበለው ያግዘናል ። እናም ታሪክን በአግባቡ የሚያጠና ትውልድ በቂ መረጃ ያለው (well informed ) በራሱ የሚተማመን (self-confident) እና ትክክለኛውን ውሳኔ መስጠት የሚችል (decision maker) ይኽናል ። እንደዚህ አይነት መረዳት ያለው ትውልድ ባለመሆናቸውን "እርቶዶክስንና ኦርቶዶክሳዊ እሴቶችን ኹሉ ከሰሜናዊነት ጋር እያላተሙ ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ለረጅም ጊዜያት የቆየ ሴራ ነው ። ለዚህ ድምዳሜያቸው በማሳያነት ከሚያነሷቸው ነጥቦች መካከል ደግሞ ዋና ዋናዎቹ ፦ በሰሜን አቅጣጫ ስለገባ ፣ የአብያተ ክርስቲያናቱ አቀማመጥ በአብዛኛው የሰሜን ኢትዮጵያ መልክአ ምድር ("ተራራማ ቦታዎች ላይ መኾኑ አብዛኞቹ ቅዱሳንና ቅዱሳት መካናት "ሰሜናውያን መኾናቸው " የሚሉት በመጽሐፍ የተጠቀሱ ናቸው ። ለእነዚህ አይነት ፀሐፊዎችም መጽሐፍ ያለባቸው ታሪክን " ራሳቸውን ከየትኛውም አይነት የፖሎቲካና የሃይማኖት እስረኝነት ነፃ ማውጣት የቻሉ ናቸው" ብሎ ከትቧል ። አንደ ማሣርጊያ የመነሻ እርዕስ የሆነውን ገጽ 255-256 ያለውን ፦ ሃይማኖት በተፈጥሮ "የአንድ ጎሣ ብቻ " አይደለም ሊሆንም አይችለም ። እንዲውም እ.ኤ.አ 1872 (የዛሬ 150 ዓመታት በፊት ) በምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይኽንን መሰል ችግር (የጎሣ ፖለቲካ እና ጎሣዊ ሃይማኖተኛነት) ተፈጥሮ ነበር ይኽንን ለመከላከል በወቅቱ ከዐሥራ አምሥት በላይ በኾኑ ፖትርያርኮች በቁስጥንጥንያ (የዛሬዋ እስንታቡል/ቱርክ ) አንድ አስቸኳይ ስብሰባ ተደርጎ (ፖን-ኦርቶዶክስ ልዩ ጉባኤ) እስከ አሁን ለብዙ ውሳኔዎች መነሳሻ የሚኾን ውሳኔ ተላልፎ ነበር ። ይኸውም ፦ ሃይማኖትን በጎሣ መከፍፈል (Phyletism or ethnophyletism) እና ከሌላ ጎሣ የመጡትን ምእመናን ማግለል (Xenophobia "ዘመናዊው የቤተክርስቲያን ኑፍቄ " (The contemporary ecclesiastical heresy) የተባለ ሲኾን በሃይማኖት ውስጥ ኾነው በጎሣ የሚያስቡ "መፍቅሬ ጎሣ መናፍቃን ተብለዋል አስተሳሰቡም ተወግዟል ። ይኽ ውሳኔ በካቶሊክ በዓለም አብያተ ክርስቲያናትም በተመሳሳይ መልኩ ጸንቷል ( ተቀባይነት ) አግኝቷል ። ( የመጽሐፍ ስም "ግንጊልቻ" ነው ጸሐፊ "ፉፋ ኦላና ኩማ (አባ ቀልቢ) ) ዲያቆን ፍፁም ከበደ ግንቦት 28 2018 ዓ.ም #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

  • 5 июн.1 012

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 июн.1 666из OrthodoxAmero

    видео или голосовое, без подписи

  • 31 мая1 39634из OrthodoxAmero

    + መንፈሱና ሙሽራይቱም ና ይላሉ + መንፈስ ቅዱስ ምሥጢር ገላጭ በመሆኑ ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ተርጓሚነት ወንጌልን ትሰብካለች ለምሳሌ ባኮስ የተባለ የሀገራችን ጃንደረባ አምልኮተ እግዚአብሔርን ለመፈጸም ወደ ኢየሩሳሌም በሚጓዙበት ጊዜ ትንቢት ኢሳይያስን ሲያነብ ትርጉሙ ከበደው በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን እንዲተረጉምለት እንዳዘዘው ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል ። የሐዋ 8-28 ወንጌላዊ ዮሐንስ በራእዩ "መንፈሱና ሙሽራይቱም ና ይላሉ" ብሎ እንደተረጎመው መንፈስ ቅዱስ በመምህራን በሊቃውንት እያደረ ምሥጢር ያናግራል ንባብ ያስተረጉማል ። ራዕ 22-7 "መንፈሱ" ፦ የተባለው መንፈስ ቅዱስ ሲሆን "ሙሽራይቱ"፦ የተባለችው ማኅበረ ምዕመናን ናቸው ። ስለዚህ በቅድስት ቤተክርስቲያን የሚሰበከው ወንጌል የሚቀደሰው ቅዳሴ የሚቆመው ማሕሌት ሰዓታት በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቅኝት የሚቀርብ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ሲናገር ፦ " መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም ። 1ኛ ቆሮንቶስ 2-10 " (ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያረድ ቅጽ-2 ገጽ 485 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምጸ) ዲያቆን ፍፁም ከበደ ግንቦት 23 2018 ዓ.ም #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

  • 26 мая1 20153из birhanuadmassa

    የማምሻ ዕድሜ ወግ ( ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ) ከ"ትዝታ ዘአለቃ ለማ" መጽሐፍ በኋላ በቤተ ክህነት ሊቃውንት ዘንድ ተዘጋጅቶ የቀረበ እንደዚህ ያለ ሌላ መጽሐፍ እኔን አልገጠመኝም። መጽሐፉ ታሪኩና ትረካው ልዩ ጣዕም ያለው መሆኑ እንደ ተጠበቀ ሆኖ በሕይወታቸው ገጠመኝነት የሚያነሷቸው አንዳንድ ጉዳዮች ግን በግሌ ብዙ ግርምቶችን ፈጥረውብኛል፣ ትልልቅ ትምህርቶችንም ሰጥተውኛል። እውነቱን ለመናገር እያረጀሁ ይሁን ወይም በሌላ ድክመቶቼ ወይም በመጽሐፉ ድክመቶች ምክንያት አንዳንድ መጻሕፍትን በጉጉት ለማንበብ ጀምሬ መቀጠል አቅቶኝ አቆማለሁ። ይህን መጽሐፍ ረቂቁ ደርሶኝ ስመለከት ግን እንደ ዋዛ ማታ ላይ ጀምሬው ሳልጨርሰው ሌላ መጽሐፍ ለማስገባት አላስችል ብሎኝ በነጋታው ለመጨረስ ራሱ ያስገደደኝ ግሩም መጽሐፍ ነው። አዘጋጁ ዶ/ር ጸጋዘአብ የሕትመት ቅጂውን ማነስ ሲነግረኝ አዝኜ ነበር። ነገር ግን አሁን ለብራና መጻሕፍት መደብር የቅጂ መብቱን ሰጥቶ ከባለፈው በተሻለ ቁጥር ለሁለተኛ ጊዜ ታትሟል። ስለዚህ የት እናግኘው ስትሉኝ የነበራችሁ ሁሉ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አጠገብ እና አራት ኪሎ ፕላዛ ውስጥ በሚገኙት የብራና መጻሕፍት መደብር ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ።

  • 22 мая1 25343из OrthodoxAmero

    + ማናቀው ስማችን + ብዙ ጊዜ ቀርበው ሚያወሩን ሲርቁን ርዕስ አርገው ሚያወሩብን የሚብራራ ስም የሰጡን ወዳጆች አሉን የተለያየ አመለካከት ለእኛ የሚኖራቸው ሰዎች ስማችን ሲነሳ አንድ የተለየ የሚያውቀው እኛን ይገልፃል ሌላውም እንደዛ ሰው ስለኛ በብዙ ማንነት ያውቀናል ። ሰው እኮ ባሕርው ነው ወይ ሰለ እገሌ አላውቅም ላለማለት በማወቁ በሚወራው አጀዳ ተሳታፊ ለመሆን በዚህ የተለያየ ሰው የማንነት ተጠያቂ ለመሆን ከሱ አንፃር ስለሚፈተፍትለት ሰው የተሻለ ሆኖ ለመታየት በሚነግረው በሚነግራቸው ግለሰብ ፈት ። የተሻል ከሆንክ ደግሞ ይከፍል ለማታቀው ስምህ ሚሰጠው ማንነት እዛ ዋላ ከዛ ታየ በዚህ ክፋ ነው ያያ ነገር ደግሞ የተሻለ አረገው እንጂ ደግ ስለሆነ አግዞት ይህ ገጠው ሚል ጥቂት ነው ። ምክንያቱም ምስጋናውን እንወስዳለን ብዙዎች እኛን ለመሆን እንጂ የሚያወራውን እሱን ለመሆን ምሳሌ ስለማያረጉ ። ሰው በምናቡ የበታችነት እንዳይሰማው ስለ እኛ የተለያየ ምክንያት ይነድፍል ። በቅዱሱ መጽሐፍ ጌታችን አንድ ጥያቄ ይጠይቃል "ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም መልሰው፦ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም፦ ኤልያስ፥ ሌሎችም፦ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል ይላሉ አሉት"። ሉቃ 9-18 ብዙ ስለእኛ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ አብረውን የእኛ ስላልናቸው ስዎችም የሚናገሩ አሉ እንዲህ አይነት ስለሆን አንተ ደግሞ ከሱ የተለየህ ስለሆንክ ከሱ ጋ ባትሆን ሚሉ አሁን አዝነውልን ብቻ መስሎን ተቀብለን የእኛን ሰው ካገለልን ስህተት ነው ያ ሰው ስም ሰጥቶ ከሚፈርደበት ወዳጃችን በላይ የከፍ ማንነት ውስጥ ሆኖ ያለ ከሆነስ አዝኖልን ሳይሆን ቀንቶብን ቢሆንስ ? መፈተሽ አለብን ። በማቴዎስ ወንጌል ላይ ያሳለፈችው የኃጥያት ህይወት አድክሟት አሁን ደግሞ በሱ እርፍት ልታርፍ በእንባ እግሩን የምታርስ የተወደደ ሽቶ ገዝታ በንስሐ በሱ የተወደደች ነፍስ ለመባል ስለቀረበች አንዲት ምስኪን ሴት ለጌታችን አብረውት ያሉት ሲነግሩት የነበረው እንዲያርቃት ሊያቀርቧት የማይገባ በደል እንዳለባት ነበር ጌታችን ግን ወደሱ ካልተመለሱት ከእነሱ ይልቅ ወደሱ የተመለሰችውን ሴት ታላቅነት ሲገልፅ እንዲህ ነበር ያለው ፦ " እርስዋ ይህን ሽቱ በሰውነቴ ላይ አፍስሳ ለመቃብሬ አደረገች ። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል። ማቴዎስ 26 ፥12 አዲስ ስም የሚሰጠን እሱ ስለእኛ ያውራልን ። ሼር ያድርጉት ማታቁት ስም የወጣላቹ ሁሉ ። 🙏 ዲያቆን ፍፁም ከበደ ግንቦት 14 2018 ዓ.ም #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

  • 9 мая1 73572из OrthodoxAmero

    ኢየሱስ የተነበበባት ፊደላችን ተወለደች። የትኛውም ከአንደበታችን የሚወጣ ቃል ረቂቅ ነው። አይታይም አይጨበጥም። "ኢየሱስ" ብለን በቃላችን ብቻ ብንናገር ስሙ አይዳሰሰም አይታይም። ይህን ስም ማየትና መንካት ከፈለግን የግዱን ኢየሱስ ብለን በፊደል መጻፍ ያስፈልገናል። በወንጌል "እግዚአብሔር መንፈስ ነው" ተብሎ ተጽፏል።መንፈስ ማለት ረቂቅ ማለት ነው። ረቂቁ አምላክ እንዴት ገዘፈ? እንዴት ታየ? በፊደል ስለተገለጠ ነዋ። ፊደል ያልናት ድንግል ማርያምን ነው። ረቂቁ አምላክ ሰው ስለሆነባት ስለታየባት ቤዛ ሊሆነን ግዙፍ ሥጋን ስለነሳባት። እሷ ፊደል ከሆነች ልጇ ወንጌል ነው። ወንጌልን ያለ ፊደል ምን ብለህ ታነበዋለህ? እንዴትስ ታየዋለህ? ወንጌላችን የሚጻፍባት ፊደል ዛሬ ከሐና ማሕፀን ከኢያቄም አብራክ ተገኘች። ሰአሊ ለነ ቅደስት! ( ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው ) #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

  • 26 апр.1 93873из OrthodoxAmero

    " ከዚህ ውሃ ስጠኝ " መጻጉዕ አልጋ ላይ ተኝቶ ያልበደለውን አምላክ እግር ሲያወጣ በደለው ዳግም መጠማት ውስጥ ተያዘ ። የሰማርያዋ ሴት ግን ብልህና አዋቂ ሴት ስለነበረች ዳግመኛ መጠማት እንዳያገኛት ጌታዋን ተማጸነችው ። የዚህች ሴት እምነት ከፈሪሳዊው የአይሁድ አለቃ ኒቆዲሞስ የበለጠ ነበር ። ጌታችን ኒቆዲሞስ ዳግመኛ በጥምቀት ስለመወለድ በነገረው ጊዜ ኒቅዲሞስ ያንን የጥመቀት ውሃ ጌታን አለመነውም ነበር ። "ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል ? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? (ዮሐ 3-4) በማለት የጥርጥር ጥያቄ አንስቷል ። ሴቲቱ ግን ካስተዋልናት የሕይወት ውሃ ዝም ብላ አትለምነውም ይልቁንም ምክንያቷንም ጭምር በማስቀመጥ ለጌትነቱ ልመና በማቅረብ ነበር ። (ሳምራዊቷ ሴት ገጽ 210-211 ኢዮብ በቀለ ) እየተነበበች ያለች የሳምራዊቷ ሴት ታሪክ መጽሐፍ የተቀነጨበች ። #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

  • 12 апр.2 09377из OrthodoxAmero

    + ትንሣኤው የተገለጠላቸው ሴቶች + የጌታችንን ትንሣኤ በተለያየ መንገድ አራቱ ወንጌላውያን ጽፈዋል መላእክት በክርስቶስ መሞት ልባቸው ለተሰበረ ስለመነሳቱ ባለማመን ውስጥ ለነበሩ ሴቶች ክርስቶስ መነሳቱን ሲያሳምኑ ዮሐንስ ሁለት መላእክት ለመቅደላዊት ማርያም ማቴዎስ ደግሞ ለብዙ ሴቶች አንድ መላአክ ሰለመነሳቱ ሲያነግሯቸው ፅፈውልናል ( ዮሐ 20-10፥11 ማቴ 28-1፥3) ። መላእክት መጀመርያ ትንሳኤውን ሲያሳምኑ ሴቶቹ ደግሞ ቀጥለው ለሐዋርያቱ እንዲያበስሩ ሆኗል ይህም የሴቶችን ክብር ለመግለጥና የሞትን ዜና በመጀመርያ የሰማችው ሴትናትና ትንሳኤውን በማብሰር ደግሞ ቀዳሚ እንዲሆኑ በማድረግ ሲክስ ነው ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን ሲገልጥ "እጅግ ተዋርዶ የነበረውን ያንን ጾታ ሴትነትን ለክብር ለመልካም ተስፍ አበቃው የታመመውንም የሔዋንን ኹኔታ ፈወሰው " ይለናል ። ጌታችን ወደ ምድር ከሴት በመወለድ የሴትን እፍረት አስወግዶ ማክብር ብቻ ሳይሆን ከምድር ተለይቶ ሞቶ ሲነሳሞ ትንሳኤውን እንዲያበስሩ በማድረግ አክብሮታል ። ጌታችን መነሣትህ አይተው "እግሩን ያዙት " እንደተባሉት በመነሣትህም ማቴ 28-9 እርግጠኛ እንደሆኑት ሴቶች እሆን ዘንድ "በኋጥያት ሳለች የተሞትች ናት " 1ኛ ጢሞ 5-6 የተባለችውን ነብሴን በንስሐ ትንሳ ዘንድ እርዳት ከዛ እግርሕን ብቻ አይደለ ቅዱስ እራስህን በንጹሕ ህሊና ቅዱስ ቅርባንህን ለመቀበል የበቃሁ እሆናለሁ ። መልካም የትንሣኤ በዓል ! ዲያቆን ፍፁም ከበደ ሚያዚያ 4 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ