- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 11
- Всего постов
- 68
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 30
- 1/48двое суток
- 34
- 1/72трое суток
- 37
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾችታወቁ። መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት ስም ዝርዝር የወጣ ሲሆን በዋናነት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ገነት አስማማው ይገኙበታል፡፡ ሙሉ ዝርዝራቸው ተከታዩ ነው፡- 1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው 2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም 3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው 4. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ 5. ዶ/ር መሠረት ቀለመወርቅ 6. ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው 7. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ 8. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው 9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው 10. ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ 11. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ 12. አቶ አለልኝ ምህረት 13. አቶ መንበር አለሙ 14. አቶ ማይክ መላክ 15. አቶ አሳምነው ታደሠ 16. አቶ ደሳለኝ እጅጉ 17. አቶ እሱባለው በለጠ 18. አቶ እስክንድር ሽፈራው 19. አቶ መሰለ ቸሩ 20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ 21. አቶ ጫኔ ዘየደ 22. ወ/ት ሃሊማ አህመድ 23. ወ/ት ህይወት አለማየሁ 24. አቶ ሲሳይ መልካሙ 25. አቶ ታደሰ ወዳይነው 26. አቶ በላይ ሲሳይ 27. አቶ ያሬድ ግርማ 28. አቶ ማረው ስለሺ 29. አቶ ሠለሞን ተፈሪ 30. አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ ደብዳቤው እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከመንግስት ጋር በጀመረው ውይይት በመጨረሻ ፈርሙ የተባሉት ተከታዮቹን ጉዳዮች ያካትታል፡- “በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ውሰዱ፤ በአማራ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለሞቱ ሰዎች፣ ለቆሰሉ ሰዎች (በየመዝገብ ቁጥሩ ይለያያል) ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ለወደመው በበሊዮን የሚገመት ንብረት ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ሀገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እና እሳቤ ካልተመራች ማለታችሁን ወንጀል ነው በሉ፤ ያለ አግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው ስለማለታቸው እና ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ” በቅድመ ሁኔታ እንደቀረበላቸው ይህንን ተከትሎ ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ “እኛ ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ በህግም፣ በሞራልም፣ በታሪክም ተቀባይነት የለውም ብለን አንፈርምም” ብለዋል፡፡ አክለውም፤ “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችም ህጋዊ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ የ60 ሚሊዮን ህዝብን መልካም እሴት ወንጀል ነው ብለን አውቀን አንሰጥም ወንጀልም አይደለም፤ በህገመንግስት እና በዓለምአቀፍ ህጎች ነፃ ሆኖ የመኖር መብታችንን ፈቅደን አንተውም፤ በህግ የተከለከለውን ራስን መከላከል እና ራሳችንን ወንጀለኛ አናደርግም” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን መመልከት ተችሏል፡፡ አዲስ ማለዳ
видео или голосовое, без подписи
በአንገር ጉትን ከተማ የአማራ ተወላጆች ላይ የተከፈተው መንግስት መር ጭፍጨፋ ተባብሶ ቀጥሏል። የአቢይ አህመድ አገዛዝ በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል የደቀነበትን ከፍተኛ ውጥረት አቅጣጫ ለማስቀየርና በተለይም በአማራ ክልል ውስጥ እየደረሰበት ያለውን ተደጋጋሚ ወታደራዊ ሽንፈት ለመሸፋፈን በሚል፡ በምስራቅ ወለጋ ዞን በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ ይፋዊ ሕዝባዊ እልቂት አውጆ እያስፈፀመ መሆኑ ታወቀ። አገዛዙ የመከላከያ ሠራዊትን፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይልን፣ የገዳ ኮማንዶን፣ አድማ ብተናንና ሚኒሻዎችን እንዲሁም በነዚሁ ወታደሮች ከለላና ሽፋን የተቋቋሙና ሽፋን የሚሰጣቸው የቄሮ ቡድኖችን በማሰማራት፡ ከነሐሴ 04/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በከፈተው መንግስት መር ጭፍጨፋ ነፍሰጡር እናቶችንና የሕክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ ከ30 በላይ ንፁኋን ወገኖች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል። በክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ በገዳ ኮማንዶና በሚኒሻ ኃይል ከለላ እየተሰጣቸው በክላሽንኮፍ ጀምሮ ሜጫና ሌሎች ስለታማ መሣሪያዎችን የታጠቁት የቄሮ ቡድን አባላት ቤት ለቤት እየዞሩ ጥቃት እያደረሱ ሲሆን፡ ከተገደሉት መካከል ነፍሰጡር ሴቶች፣ እመጫት እናቶች፣ ሕፃናትና ሁለት የሕክምና ባለሙያዎች እንደሚገኙበት መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የአይን እማኞች አረጋግጠዋል። ከተገደሉ ንፁኋኖች በተጨማሪ የአማራ ተወላጆች ቤት እየተመረጠ " የፋኖ ቤት" በሚል በእሳት ጋይቶ እንዲወድም ተደርጓል።
видео или голосовое, без подписи
የዘንድሮውን የግብር ዘመን ተከትሎ በተጣለባቸው ከፍተኛ የግብር ግምት ምክንያት ሥራቸውን ለማቆምና የንግድ ፈቃዳቸውን ለመመለስ እየተገደዱ መሆናቸውን በርካታ ነጋዴዎች ገልጸዋል። እንደ ነጋዴዎቹ ገለጻ፣ ለአሁኑ የግብር ዘመን የተጣለባቸው የግብር ግምት ቀደም ሲል ይከፍሉት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር እስከ ሶስት እጥፍ ያህል ጭማሪ አሳይቷል። በአሁኑ ወቅት ባለው የገበያ መቀዝቀዝ፣ የኑሮ ውድነትና የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም መዳከም ምክንያት ንግዳቸው የተቀዘቀዘ መሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ የተጠየቁት መጠን ከሚያገኙት ገቢ ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን በመሆኑ የተደቀነባቸውን ከፍተኛ የግብር ጫና መሸከም አለመቻላቸውን ያስረዳሉ። በዚህም ምክንያት የንግድ ፈቃዳቸውን ለመመለስ ማመልከታቸውን፣ ሱቆቻቸውን ዘግተው ከንግድ ዓለም ለመውጣት መገደዳቸውንና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ዳግም ግምገማ እንዲያደርጉላቸው አቤቱታ በማስገባት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ይህ ሁኔታ በአስቸኳይ መፍትሔ ካልተበጀለት የበርካታ ዜጎችን የሥራ እድል አደጋ ላይ ከመጣሉ ባሻገር፣ በገበያው ላይ ተጨማሪ የዋጋ ንረትና የዕቃዎች እጥረት ሊፈጥር እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
видео или голосовое, без подписи
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የተፈፀመ‼️ ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት ግልሰቦች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል። ድርጊቱ የተፈጸመው አገና በተባለችው ልዩ ቦታ ሲሆን ወንጀሉን የፈጸሙት የመንግስት ኃይሎች ከአካባቢው የአበሽጌ አገና ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተጠቅሷል።የተያዙትም ከተያዙ በኋላ እንዲረሸኑ መደረጉን የአካባቢው ምንጮች ይገልፃሉ። Via:- መሰረት ሚዲያ
видео или голосовое, без подписи
#NationalDialogue🇪🇹 በ10 እና 50 ሰዎች በተደራጁ ቡድኖች ደረጃ ያልተነሳ "አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ እንድትሆን በሕገ መንግስቱ ሕጋዊ እውቅና ይሰጥ" የሚል አዲስ አጀንዳ በ250 "ስልታዊ" ቡድን በመቅረቡ በዚህ ሀሳብ አንፈርምም ብለው ትናንት መድረክ ረግጠው የወጡ ተመካካሪዎች እንደነበሩ ተሳታፊዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ዛሬ ከከሰዓት በኋላ ግን መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል። አንድ የፌዴራል ከተሞች ጉዳይ ተሳታፊ በሰጡን ቃል መጀመሪያ፣ "አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለማን ትሁን? 'ባለቤቷስ ማነው? በሚለው ባለቤቷም፤ ተጠሪነቷም ለኦሮሚያ ይሁን'" እና "የብሔር ብሔረሰቦች የሁላችንም ከተማ ናት። ተጠሪነቷ ለፌዴራል መንግስቱ ይሁን" የሚሉ አከራካሪ ሀሳቦች እንደነበሩ አስታውሰዋል። "በኋላ የመጀመሪያውን ሀሳብ ያራምዱ የነበሩ የኦሮሚያ ፖለቲከኞች ሀሳባቸውን አንስተው አዲስ አበባ የፌዴራሉ መንግስት መቀመጫ መሆኗን አንከለክልም" ብለው፣ "'ግን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ ትሁን የሚለው ህጋዊ እውቅና ይሰጠው" በሚል የአቋም ለውጥ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በአንፃሩ ሌሎች ተመካካሪዎች ደግሞ፣ "የፌዴራልና የሁላችንም ከተማ ካልናት በኋላ ለአንድ ማህበረሰብ ልዩ መቀመጫነት መስጠት ተገቢ አይደለም" የሚል መከራከሪያ ማቅረባቸውን ገልዋል። "በመጨረሻም 500 ቡድኖች ድረስ ሁለቱ ሀሳቦች መጥተዋል" ብለዋል። "አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ትሁን" የሚለው አጀንዳ "ለ15 ቀናት ስንወያይ አልነበረም። 250 ቡድን ላይ ስንደርስ አዲስ የመጣ ሀሳብ ነው" ያሉት ተሳታፊው፣ ከታች ጀምሮ ያልመጣ ሀሳብ ለምን ከላይ መጣ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ እንደነበር አስረድተዋል። ሌላኛው ተሳታፊ፣ የኦሮሚያ ክልል ተሳታፊዎች "አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል አካል መሆን አለባት" ሲሉ፣ የሌላ ክልሎች፣ "አዲስ አበባ የፌዴራል አካል ነው መሆን ያለባት" የሚል ሀሳቦቹ ማከራከራቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ሀሳብን ለማቀራረብ በተደረገ ውይይት ከኦሮሚያ ክልል የምክክሩ ተሳታፊዎች "እሺ የፌዴራል አካል ትሁን" በሚል ተስማምተው፣ ከተማዋ የፌዴራል አካል ስትሆን ግን "ኦሮሚያ 50 ሲደመር አንድ መሰጠት አለበት"፣ "የፌዴራል ሕገመንግስት አዲስ አበባን እንደ ኦሮሚያ ከተማ አድርጎ እውቅና እንዲሰጠን እንፈልጋለን" የሚሉ ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጣቸውን ተናግረዋል። "50 ሲደመር አንድ" ማለት ውክልና መሆኑን ገልጸው፣ "ውክልና ማለት ደግሞ ሙሉ በሙሉ የኦሮሚያ ማለት ነው። ስለዚህ አይሆንም ለአንዱ አካል ብቻ መብትን የሚሰጥ ነው" የሚል ሀሳብ በሌላ በኩል እንደቀረበበትም ተናግረዋል። ሌላኛው የዚሁ አጀንዳ ተሳታፊ የሁለቱን ተሳታፊ ሀሳቦች ተጋርተዋል። ተመካካሪዎች ለምን መድረክ ረግጠው ወጡ ? ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጻ ከሰጡት ተሳታፊዎች አንዱ፣ "ትናንት መድረክ ጥለን ወጥተናል። ጥለን የወጣንበት ምክንያት ከትናንት በፊት የተስማማንበት ነገር ትናንት ሲነበብ ብዥታ ፈጥሮ ነው። ኦሮሚያን ወክለው የሚመካከሩት ሰዎች ፈረሙ የሌላው ግን አልፈርምም ብሎ ነው የወጣው" ብለዋል። ብዥታ የፈጠሩት "50 ሲደመር አንድ" እና "የፌዴራል ሕገመንግስት አዲስ አበባን እንደ ኦሮሚያ ከተማ አድርጎ እውቅና" እንዲሰጥ የሚሉት ግልጽ ማብራሪያ ስሌላቸው መሆኑን አስረድተዋል። ይህም ሰሞኑን እንደገና ወደኋላ ተመልሰው እንዲወያዩ እንዳስገደዳቸው ገልጸዋል። ሌላኛው ተሳታፊ፣ "አዲስ አበባ የኦሮሚያ መቀመጫ መሆኗን መቀበል አለባችሁ የሚል አይነት ግፊት ሲመጣ ይህንን አንቀበልም የሚሉ ትናንት መድረክ ረግጠው ወጥተው ነበር" ብለዋል። ሌላኛው ተሳታፊም ይህንኑ ሀሳብ ነግረውናል። ስልታዊ ቡድን ላይ ቀረበ በተባለው አዲስ አጀንዳ፣ ለኮሚሽኑ ቅሬታ ያስገቡ ፓርቲዎች እንዳሉም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል። ተመካካሪዎቹ ዛሬ ምን ላይ ደረሱ ? ዛሬ ከሰዓት በፊት በነበረው ውይይት ወደ መግባባት መገባቱን ተሳታፊዎች ገልጸዋል። አንዱ ተሳታፊ፣ ብዥታ የፈጠሩ ጉዳዮች ከተብራሩ በኋላ አዲስ አበባ የፌዴራል አካል እንድትሆን፣ የኦሮሚያ ተመካካሪዎች ያቀረቡት ሀሳብም "በልዩነት ተይዞ" በ250 ቡድን መስማማታቸውን ነግረውናል። ሌላ ተካታፊ፣ አዲስ አበባ የፌዴራል መንግስቱ ተጠሪ ትሁን የሚለው በብዙሃኑ ከስምምነት እንደተደረሰ ገልጸዋል። ሕገ መንግስቱ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ እንድትሆን እውቅና ከሰጠ "ኦሮሚያ ለወደፊት የአዲስ አበባ ባለቤትነትን እንዳይጠይቅ" በግልጽ መደንገግ እንዳለበት ሀሳብ መቅረቡንም በሻይና ቡና ሰዓት በተመካካሪዎች ዘንድ ሲወሳ አስተውለናል። ኮሚሽኑ ዛሬ ከሰዓት እንዳስታወቀው፣ በስልታዊ ቡድኖች ተደራጀተው የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች 500 አባላት ላሉት የሥራ ቡድን ቀርበዋል። የቡድኖቹ ሀሳቦች "በአጀንዳ ተቀራራቢነት፣ ተመጋጋቢነት እና ልዩነት በተመካካሪዎች እንዲታይ እድል ሰጥቷል" ብሏል። ተመካካሪዎች ከስልታዊ ቡድኖች ሀሳቦችን እንዲያቀናጁ 30 አባላት ያሉበትን ሀሳብ አቀናጆችን መምረጣቸውንና በቀጣዮቹ ቀናት የስልታዊ ቡድኖች ሀሳቦች በተመረጡ አቀናጆች ተዋህደው እንደሚቀርቡ አስታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
• እንኳን ለጾመ ማርያም (ፍልሰታ) አደረሰን አደረሳችሁ ‼ "…ጾመ ማርያም አጭር ናት። ግን ሲበዛ ጣፋጭም ናት። እጅግም ተናፋቂም ናት። የልጅነት ትዝታችን፣ የመጫዋት፣ የመቦረቅ የሥጋ ፍላጎታችንን ገና በጠዋቱ መግታት፣ መለጎም የተማርንበት፣ ጾም ጸሎትን፣ እስከ 9 ሰዓት ያለ ምግብ ያለ ውኃ መዋልን የጀመርንበት፣ ተጋፍተን፣ ተሻምተን የምን ሥጋወ ደሙ የተቀብለንበት፣ ከቁርባን በኋላ ከቤት ሳይጡ፣ ሳይራገጡ፣ ሳይሯሯጡ፣ ሰከን ብሎ፣ ለሥጋወ ደሙ ክብር ሲባል ከቤት ሳይወጡ፣ በዝናብ በጭቃው ሳይሯሯጡ፣ አደብ ገዝቶ ፈታኙን የልጅነት የቡረቃ ጊዜ በትዕግስት፣ በአርምሞከቤት በተነጠፈ ፍራሽ ላይ ቁጭ ብሎ፣ ማሳለፍን መማር የምንጀምርባት ናት ጾመ ማርያም። "…ጾመ ማርያም በልጅነታችን ጽናትን፣ ለፈተናዎች ያለመበገርንም በተግባር የምንማርባት ጾም ናት። ዶፍ ዝናብ ቢወርድ፣ በረዶ ቢጥል፣ ጎርፍ ቢጎርፍ ሥርዓተ ቅዳሴው እስኪያልቅ ድረስ ንቅንቅ ባለማለት ጸንቶ መቆምን የተማርንበት ናት ጾመ ማርያም። "…ነሐሴ የኢትዮጵያ 12 ኛው ወር ነው። ሰኔ ላይ የሚዘጋው ትምህርት ቤት የሁለት ወር እረፍቱን ጨርሶ ለአዲስ ዓመት ዝግጅት የሚያደርግበት ወር ነው። በአዲሱ ዓመት በወርሀ መስከረም ትምሕርት ቤት ሲከፈት በጾመ ማርያም ሁለቷን ሱባኤ ሲጸልዩ፣ ሲጾሙ፣ ሲያስቀድሱ፣ ሲቆርቡ የከረሙ ሕጻናት መንፈስ ቅዱስን እንደ ሸማ ተጎናጽፈው፣ የእውቀት ብርሃንን ለብሰው፣ በደስታ ነው ትምሕርታቸውን የሚጀምሩት። በትምሕርታቸውም ስኬታማ፣ ውጤታማ ነው የሚሆኑት። ወላጆች በተለይ ልጆቻችሁ ከፍ ሲሉ ከእነሱ ጋር ሊቀር የሚችል አንዱ የልጅነት ትዝታ ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ነው እና ሕጻናቱን ቤተ ክርስቲያን ውሰዷቸው። "…በዚህ በወርሀ ነሐሴ በጾመ ማርያም ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔር የእመቤታችንን ምስጋና ውዳሴና ቅዳሴ ለመስማት፣ ለማንበብም ያበቃን። በቸርነቱም ብዛት ከጣዕሙ ብዛት የተነሳ አጥንትን የሚያለመልም የመላእክትን ምስጋና የሕይወትን ቃል ያሰማን፡፡ ከእመቤታችን ከወላዲተ አምላክ ከድንግል ማርያም በረከት ረድኤት ያሳትፈን፡፡ መዋእለ ጾሙን በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈጽመን። የእመቤታችንን ፍቅሯን በልባችን፣ ጣዕሟን በአንደበታችን ይሳልልን ያሳድርብን አሜን፡፡ "…እንደምን አደራችሁ?
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи