Aroma Official
Статистикаእኛ "አሮማዎች" ነን። ይህ የንጉሡ ወንድና ሴት ልጆች ወርቃማው ዘመን ነው ። በዚህ ፔጅ ላይ ስለ ታላቁ የእግዚአብሔር መንግሥት ጥበብና ስልጣን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ትውልዱን እንሰብካለን ። "መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን ወ አሜን።
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 351
- 1/48двое суток
- 402
- 1/72трое суток
- 433
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
⭐️ እሁድ ከጠዋቱ 3፡00 - 7፡00 ⭐️ የአምልኮ የጸሎት እና የቃል ጊዜ በአሮማ ቤተክርስቲያን 📍 አድራሻችን ከመገናኛ ወደ ቦሌ (ገርጂ) በሚወስደው መንገድ፣ ወደ 24 እንደታጠፉ ከአንበሳ ድልድይ 200 ሜትር ገባ ብሎ፤ ኤል ኤ (L.A) ሆቴል ፊት ለፊት እንገኛለን Location(https://maps.app.goo.gl/E2LpJ4com1FAQymX6?g_st=atm) የቤተክርስቲያኗ ቋሚ ፕሮግራሞች ➡️እሁድ ከጠዋት 3፡00-7፡00 ➡️ሐሙስ ማታ 11፡00- 2፡00 | Facebook | YouTube | TikTok |
በአገልጋይ ካስየ በእግዚአብሔር የተመረጠው አገልጋይ ትንቢተ ኢሳይያስ 42:1-8 > ⁸ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።" 1. የአገልጋዩ መጠራትና ድጋፍ ይህ አገልጋይ መደገፊያው ያደረገው ራሱን እግዚአብሔርን ነው። አገልጋዩ በታላቅ መለኮታዊ ጥሪ የተጠራና የተደገፈ ነው። ክርስቲያናዊ ሕይወት ያለ መንፈስ ቅዱስ አይሞከርም። አንድ ክርስቲያን ለጽድቅ እንዲቆም የእግዚአብሔር ቅድስናና ሕልውና በእርሱ ላይ ሊሆን ይገባል። ይህ አገልጋይ አገልግሎቱን የሚጀምረው እግዚአብሔርን ከማስተዋወቅ ነው፦ ከሰማይ የወረድሁት የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ እንጂ የራሴን ፈቃድ ለማድረግ አይደለምና።» (የዮሐንስ ወንጌል 6:38) 2. የአገልጋዩ ባሕርይና ማንነት (የእውነተኛ አገልጋይ ልብ) ይህ አገልጋይ ገራምና እውነተኛ የአገልጋይነት ልብ ያለው ነው። የተቀጠቀጠውን ሸምበቆ አይሰብርም፥ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል።» (ኢሳይያስ 42:3 / ማቴዎስ 12:20) ይህ ቃል ስለ ባሕርዩ፣ ገራምና የዋህነቱ ይነግረናል። ✓ርኅሩኅ እረኛ፦ ይህ አገልጋይ የቆሰሉትንና የተሰበሩትን የሚጠግን፣ በእግዚአብሔር የተመረጠ እረኛ ነው። ሁላችንንም እኩል የሚያገለግል፣ የማያዳላና በሰውነታችን እንደዚሁ የሚወደልን ነው። ✓ኃይል አለው ነገር ግን አይጠቀምበትም፦ ያንን ያህል ሩህሩህ ነው! ኢየሱስ የተሰበረውን ቶሎ አይጥለውም፤ የደበዘዘውን አይነቅለውም፤ ይልቁንም በትዕግሥት የሚጠብቅና የሚያለመልም ነው! በእርሱ ላይ የተደገፈ ሕይወት ብርሃንን ይካፈላል። 3. የአገልጋዩ ተልእኮ (የእግዚአብሔርን ቅድስና ወደ ምድር ማምጣት) ዓለማችን በግፍ፣ በበደልና በክፉ ሥራ የተሞላች ናት። አማኝ ተስፋ ከቆረጠ ዓለም ምን ትሆናለች? ስለዚህ በእውነት መቆምና ደካሞችን ማገዝ ከእኛ ይጠበቃል። እግዚአብሔር የክርስቶስን ብርሃን ለእኛ ያካፈለው ለሌሎች እንድናበራው ነው። ዓይኖቻችን ሲከፈቱ በዓለም ላይ ያለውን ሁኔታ ማየት እንችላለን። ነቢዩ ማየት ያልቻለውን፣ አገልጋዩ ግን አይቷል—እርሱም እስረኞችን ነፃ ለማውጣት ነው! > «የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።» (ኢሳይያስ 42:7) ቤተክርስቲያን ነፃነትን ታውጃለች፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ መጥቶ ነፃ አውጥቶናል። ክርስቶስ ነፃ አውጥቶናልና ሰይጣን በእኛ ላይ የሚያቀርበው ምንም ዕዳ የለብንም! ስለዚህ ሰው ነፃ የሚወጣው ወደዚህ ታማኝ አገልጋይ ሲመጣ ነው። ክርስቶስ ነፃ አውጪ ነው፤ ከተሰርንበት ፈትቶ ወደ እግዚአብሔር ያሰገባናል። 4. ተልእኮውን በድል የፈጸመ አገልጋይ ይህ አገልጋይ ተልእኮውን በድል አጠናቋል። ኢየሱስ ሁላችንን የሚያድን የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው። ሲታይ የተናቀ ቢመስልም፣ በእግዚአብሔር ፊት ግን ፍርድን የሚያወጣ አዳኝ ነው። > «አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።» (ማቴዎስ 12:18_21) መልእክቱ ዓይኖቻችንን እንድንከፍት ነው! ይህ አገልጋይ ሲጨርስ ክብርን ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰጥቷል፦ «እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።» (ኢሳይያስ 42:8) ✨ለእኛ የተላለፈው መልእክት፦ የእግዚአብሔር ጽድቅና ቅድስና አይቀየርም። የዳንበትን የእግዚአብሔር እውነት ይዘን በዚህ በጨለማው ዓለም ላይ በብርሃንና በቅድስና መገለጥ አለብን። በቅድስና ከዓለም ልንለይ ይገባል። ለራሳችን የምናቀርባቸው 3 ጥያቄዎች፦ ✓ በዚህ በታመነው አገልጋይ ላይ ሙሉ በሙሉ እታመናለሁን? ✓ ይህንን አገልጋይ እየመሰልኩት ነውን? ✓በእርሱ ታላቅ ተልእኮ ውስጥ እየተሳተፍኩ ነውን? ወደዚህ አስተማሪ አገልጋይ ዓይኖቻችንን ማነሳት አለብን! በመንፈስ ቅዱስ መደገፍ፣ በዚህ ተልእኮ ውስጥ መሳተፍና ክብርን ሁሉ ለአብ መስጠት ከአማኝ ይጠበቃል። ተባረክልን ካስየ🙏🙏🙏
ለመሆኑ እኛ አማኞች የኢየሱስን ጌትነት ለምን እንናገራለን? 1. ጌታ ኢየሱስ ጌታ ስለሆነ (ራእይ 19:11-16) ይህ ስም አስቀድሞ የነበረና ያለ ነው። እኛ «ኢየሱስ ጌታ ነው» ስንል እግዚአብሔርን እያከበርንና እየተስማማን ነው፤ ልባችን የጌትነቱ ስፍራ ነውና። 2. የሰው ልጆች የመዳን መንገድ ሁሉ ከዚህ የተከበረ ስም ጋር ስለተኮራኘ (ሮሜ 10:9) የኢየሱስ ትንሣኤ የተረጋገጠ ነው፤ ትንሣኤው ክርስትናችንን እውነት ያደርገዋል። የምንሰብከው ሞቱን ብቻ ሳይሆን ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱንም ጭምር ነው። የልባችን መዝገብ ትንሣኤውን አረጋግጧል፤ አንደበታችንም በልባችን ያለውን ይመሰክራል። ጌትነቱ የመዳናችንን ምስጢር ወደ ሰማይ አቅርቧል። ያመነ ደግሞ የሚጠመቃት አንዲት ጥምቀት አለች—እርሷም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ስትሆን፥ አጥማቂው ደግሞ ራሱ ጌታ ኢየሱስ ነው። ዮሐንስ «ከእኔ በኋላ የሚመጣው በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል» እንዳለው። የእግዚአብሔር ምስጢር ተገልጧል—እርሱም ልጁ ነው። መጻሕፍት ሁሉ የሚናገሩለት አንድ እውነት የኢየሱስ ብቸኛ አዳኝነት ነው። 3. ለእግዚአብሔር ክብር (ፊልጵስዩስ 2:9-11) የማንኛውም ስም የማይተካከለው ስም ነው! ሰዎች ከማንኛውም ነገር ለማምለጥ ብለው ከኢየሱስ ውጭ ያለ መንገድ ሊያድናቸው ወይም ሊያመልጡበት አይችሉም። እኛን ያስከተለን የእርሱ የቆሰለ ጀርባ ነው። ሰማይ የሚቀበለው ማንኛውም አምልኮ በኢየሱስ ስም ከሆነ ብቻ ነው። የዘመናት ባለቤት የሆነው ብቸኛው ጌታ ኢየሱስ ነው። «ኢየሱስ ጌታ ነው» ስንል አብን እያከበርን ነው። በራእይ ላይ እንደተጻፈው—የታረደውና ያሸነፈው አንድ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው። 4. አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር የሆነበት እንዲሁም ከሞት ያመለጥንበት ስለሆነ በእግዚአብሔር መንፈስ ሆኖ «ኢየሱስ የተረገመ ነው» የሚል ማንም የለም። በየዘመናቱ ኢየሱስን ታግሎ ያሸነፈ የለም የዳንበት ያመለጥንብት ስም_ኢየሱስ ✨በጊዜውም ቢሆን ወይም ያለጊዜው—ኢየሱስ ጌታ ነው! ተባረክልን መጋቢ🥰🥰🥰
ኢየሱስ ጌታ ነው!!!🔥🔥🔥 ፊልጵስዩስ 2:6-11 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፤ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፤ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፤ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። > ስለዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ከዛሬ ሁለት ሺህ ዓመታት በ ጀምሮ በቤተክርስቲያን በኩል «ኢየሱስ ጌታ ነው» ተብሎ ሲታወጅና ለዚህም የሚያስፈልገው መስዋዕትነት ሲከፈልበት የኖረው ይህ ድምፅ፣ አሁን ያለንበት ዘመን ላይ ደርሷል። ይህ አዋጅ ለአማኝ ብርታት ነው። ለማያምኑ ደግሞ ፍርሃትንና መንቀጥቀጥን ያመጣል። ቃል ብቻ ሳይሆን የፍጥረት ዓለም መክፈቻ መለኮታዊ አዋጅ ነው፤ ለእግዚአብሔር ክብር የተዘጋጀ አዋጅ ነው! በክርስቲያናዊ ድንበር ለሚመጡት ሁሉ ይህ ስም እንደ መፈክርና እንደ ጽኑ መለኮታዊ አዋጅ ይቀጥላል። እኛ ይህንን አዋጅ የምንናገረው ተረድተን ነው። ኢየሱስ ለአንዳንዶች ፍልስፍና፣ የሃይማኖት መዝሙር፣ ነቢይ ወይም ከመላእክት አንዱ ሊሆን ይችላል። ለእኛ ለአማኞች ግን ኢየሱስ ትላንት፣ ዛሬ እስከ ዘላለምም ጌታ ነው! (የዮሐንስ ወንጌል 1:1) ዛሬ ጨለማ ስለማያሸንፈው፣ በመጀመሪያ ስለነበረው አካላዊ ቃል፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለነበረውና እግዚአብሔር ስለሆነው ቃል እንናገራለን። «በመጀመሪያ ቃል ነበረ» ስንል፤ በኦሪት ዘፍጥረት 1:1 ከተጻፈው የፍጥረት መጀመሪያ በፊት የነበረውን መጀመሪያ ማለት ነው። ታሪካዊ የጊዜ ዳራ የማይሰራለት የዘላለም አምላክ፤ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላ እንደ እርሱ ያለ አምሳያ የሌለው ማለት ነው። ግሪኮች «ሎጎስ» (Logos) የሚሉት ይህ አካላዊ ቃል—ፊተኛውና ኋለኛዉ፣ መጀመሪያን የሚያስጀምር አልፋ፣ ፍጻሜውን የሚዘጋ ኦሜጋ ነው። የኢየሱስን ዘላላማዊ አምላክነት የሚጠራጠሩ ብዙዎች ናቸው። ነገር ግን ኢየሱስ በመጀመሪያው የነበረው ቃል፣ በመጀመሪያው የነበረው ታላቅ ብርሃን ነው። መሰረታችን የተመሰረተው እዚህ ላይ ነው! በክብር ያረገው የወረደው እርሱ ብቻ ነው፤ እርሱ አስቀድሞም ሲኖር የነበረው የተከበረው ኢየሱስ ነው። ✨አንዳንዶች "ራሱን ጌታ ነኝ አላለንም፤ ሰዎች የፈጠሩት ነገር ነው" ይላሉ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፦ * ዮሐንስ 8:53 — ለአንዳንዶች ሃይማኖተኞች ኢየሱስ ዝቅ ያለ ቢመስላቸውም፥ ነገር ግን ኢየሱስ ማንም የማይደርስበት ተቀናቃኝ የሌለው ጌታ ነው። * ዮሐንስ 20:30 — መጽሐፍ የተጻፈው ለዚህ ነው። ምንድን ነው ጊዜአችንን የወሰደብን? ስብከታችን፣ መዝሙራችንና ጨዋታችን ስለ ኢየሱስ ብቻ ነው ሊሆን የሚገባው፤ የክብር ተስፋ የሆነው ኢየሱስ ሊመጣ ነውና! ሕይወት ይህ ነው። * ዮሐንስ 13:14 — "መምህርና ጌታ ነኝ" ብሏል። ኢየሱስ የሚቀነስ ጌትነት የለውም፤ ጌትነት የኢየሱስ ማንነት ነው። (ተጨማሪ የምስክርነት ክፍሎች፦ ማቴ. 16:16፣ ዮሐ. 20:28፣ ፊል. 2:5፣ ቆላ. 2:9፣ ቲቶ 2:13፣ መዝ. 47፣ ዕብ. 1:11) ከጌታ ከኢየሱስ ውጭ በአካል ወደ ሰማይ የወጣ የለም። የዘላለም አምላክ የለየለት ጌታ ኢየሱስ ነው። በፊልጵስዩስ ላይ የተጻፈው ቃል ሁሉ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ የሚናገር ቃል ነው።
⭐️ እሁድ ከጠዋቱ 3፡00 - 7፡00 ⭐️ የአምልኮ የጸሎት እና የቃል ጊዜ በአሮማ ቤተክርስቲያን 📍 አድራሻችን ከመገናኛ ወደ ቦሌ (ገርጂ) በሚወስደው መንገድ፣ ወደ 24 እንደታጠፉ ከአንበሳ ድልድይ 200 ሜትር ገባ ብሎ፤ ኤል ኤ (L.A) ሆቴል ፊት ለፊት እንገኛለን Location(https://maps.app.goo.gl/E2LpJ4com1FAQymX6?g_st=atm) የቤተክርስቲያኗ ቋሚ ፕሮግራሞች ➡️እሁድ ከጠዋት 3፡00-7፡00 ➡️ሐሙስ ማታ 11፡00- 2፡00 | Facebook | YouTube | TikTok |
የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፤ ችኵል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።" — ምሳሌ 21:5 ✓ችኩልነት ማለት እግዚአብሔርን አለመጠበቅና በራስ አእምሮ መቸኮል ነው። ✓ ትጋት የሚጀመረው በመጀመሪያ በአእምሮ በማሰብና በማቀድ ነው። ✓ተፅዕኖ ፈጣሪነት፦ ክርስትና የሥራ ትምህርት ጠልነት ወይም ስንፍና አይደለም፤ በማንኛውም ስፍራ በጽድቅ ተፅዕኖ መፍጠር አለብን። ✓ትውልድን የሚያሻግር፣ የሚያሳርፍ፣ ድኅነትን የሚያሸንፍ የባርነትን ቀንበር የሚሰብር የትጉሃን ሀሳብ ነው። ሁሉም የነገር ውጤት የሚጀምረው ከሀሳብ ነው። ዳዊት በመዝሙሩ፦ *"አምላክ ሆይ፤ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደምን የተከበሩ ናቸው! ቁጥራቸውም እንደምን ታላቅ ነው!"* ይላል የእግዚአብሔር አሳብ በውስጣችን ሲወርድ ሕይወታችንን ይለውጣል። አእምሮን በጥበብ መሙላት፦ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ጥበብንና አእምሮን ሁሉ አበዛልን (ኤፌሶን 1:8)። ✓መንፈሳዊነት የሚጀምረው ቃሉን በትክክል በመረዳት ነው። ✓እግዚአብሔር ቤት ያለው ዕውቀት ቁጭ ብሎ መማር ያስፈልጋል፤ በተጨማሪም በመንፈሳዊው ዓለም ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ ዕውቀታችንን መጨመር ይገባናል። እንደ ክርስቲያን መቅበዝበዝን ከሕይወታችን ማስወገድ አለብን። ✓ኢየሱስ ሙሉ ዕረፍት ነው፦ በእርሱ ካላረፍን የማንም ወይም የትኛውም ምድራዊ ነገር ረሃባችንንና ጥማታችንን ሊያረካ አይችልም። ይሁዳ ከኢየሱስ ጋር እየኖረና እያደረ፣ ሌላ የሚያሻግረው ነገር በመፈለጉና በመቅበዝበዙ ምክንያት ወጣ። ✓እውነተኛው ስኬት (Jesus is the Last Success)፦ ዋናውን ኢየሱስን ይዘናል። ከፍጥረት ሁሉ ይልቅ እንደ እግዚአብሔር አሳብ ብቻ እንዲያስብ የተፈቀደለት ፍጡር ሰው ብቻ ነው! በኢየሱስ በኩል በጎ ነገርን ብቻ የምናስብበት አዲስ ልብና አእምሮ ተሰጥቶናል። 🎯 🎯 🎯 🎯 እግዚአብሔር የሚያየው የውስጥ ልባችንንና ሀሳባችንን ነው። በችኩልነት ሳንቅበዘበዝ፣ በትጉህ ሀሳብና በቃሉ ዕውቀት እየታደስን፣ እውነተኛ ዕረፍታችን በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በመደገፍ ልባችንን ለጽድቅ ማዘጋጀት አለብን!
በአገልጋይ ያሬዶ "የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል። የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል። እግዚአብሔር ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ ይወድዳል። ትዕቢተኛ ዓይንና ደፋር ልብ የኀጥኣንም እርሻ ኃጢአት ነው። የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፤ ችኵል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።" — ምሳሌ 21:1-5 ሰው በራሱ አእምሮና ዕውቀት መንገዱ ሁሉ ትክክለኛና የቀናች ልትመስለው ትችላለች፤ እግዚአብሔር ግን የሰውን ልብ (የውስጥ መሻቱን) ይመዝናል። ✓በመጽሐፍ ቅዱስ ልብ ምንድነው? ልብ የአእምሮ፣ የዕውቀት፣ የፍላጎትና የእስትንፋሳችን/የነፍሳችን ማዕከል ነው። ሰዎች የሰሙትንና የሚያውቁትን ይናገራሉ፤ እግዚአብሔር ግን ከንግግር በስተጀርባ ያለውን የተሰወረውን የውስጥ መሻት ያያል። ✓ዛሬ የተቸገርንበት ነገር፦ የውስጣችን መሻትና የውጫዊ ማንነታችን/ንግግራችን እየተለያየና እየተጋጨ መምጣቱ ነው። በእኛ ዘንድ የእግዚአብሔር ጥያቄ *"በውስጣችሁ ያለው መሻት ምንድነው?"* የሚል ነው። እግዚአብሔር ሰሎሞንን "ምን እንድሰጥህ ትወድዳለህ? "ባለው ጊዜ፣ ሰሎሞን የጠየቀው የውስጥ መሻቱ ለህዝቡ የሚፈርድበትንና የሚያስተዳድርበትን ጥበብና አስተዋይ ልብ ነበረ (1ኛ ነገሥት 3:9)። ✓ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅ፦ እግዚአብሔር ውጫዊ ከሆነው ከመሥዋዕትና ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይልቅ፣ የውስጥ ጽድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ ይወድዳል (ምሳሌ 21:3፣ 1ኛ ሳሙኤል 15:22)።
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
⭐️ የእሁድ ፕሮግራም በአሮማ ⭐️ 📸ሐምሌ-19 ቀን የፎቶ ትዉስታ📸
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
✓ ሰውነታችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና የንጉሡ መኖሪያ ነው። ፈቃዱን ለልባችን ሲነግረንና ልባችን ፈቃዱን ማስተናገድ ሲጀምር የመንግሥቱን መልክ መምሰል እንጀምራለን። 💵 . የገንዘብ ፍቅር ሰይጣን ፍጡር ስለሆነ ከፈጣሪ ከእግዚአብሔር ጋር አይወዳደርም። ሰይጣን በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ አንዳች ተጽዕኖ ማምጣት አይችልም። ነገር ግን ሰዎች ባለማወቅ ለተለያዩ ነገሮች አምላካዊ ስፍራ ሰጥተዋል። ✓ገንዘብ አምላክ ሲሆን፦ ሳናውቅ አምላክ ካደረግናቸው ነገሮች አንዱ ገንዘብ ነው። ገንዘብ መጠቀሚያ እንጂ እኛ የምንገዛለት ሊሆን አይገባም። ✓የገንዘብ ፍቅርና ዓለምን መውደድ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነው (1ኛ ዮሐንስ 2:15)። ሐሳባችንንና አእምሯችንን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ገንዘብ ብቻ ከሆነ፣ እሱ አምላካችን ሆኗል ማለት ነው። ✓ሚዛናዊነት፦ ገንዘብ እውነት ነው በጣም ያስፈልጋል! ነገር ግን መውደድና ማምለክ የለብንም። ገንዘብን መጠቀሚያ ብቻ ማድረግ አለብን። 🕊️ . የጭንቀት ጉዳት፦ ጭንቀት የአስተሳሰብ አቅማችንን ይቀንሰዋል፤ ባጣነውና በጎደለን ነገር ላይ ብቻ እንድናተኩር ያደርገናል። ጌታ ኢየሱስ *"አትጨነቁ"* ሲል አታስቡ ማለቱ ሳይሆን፣ በጭንቀት አእምሯችሁን አታቃትሉ ማለቱ ነው። የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፣ አያጭዱምም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። አንተ ደግሞ ጤና ከተሰጠህ ሠርተህ እንድትበላ ተፈጥረሃል፤ ነገር ግን ሕይወትህን በጭንቀት ማጥፋት የለብህም። "የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።" *ሮሜ 14:17* 🎯 ማጠቃለያ በዳግም ልደት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ብንገባም፣ መንግሥቷን በሕይወታችን የምንወርሰውና የምንለማመደው በመንፈሳዊ ዕድገት ነው። ቤተክርስቲያን ምእመናንን *Kingdom Minded* (በመንግሥቱ አስተሳሰብ የሚመሩ) አድርጋ ማሰልጠን አለባት። ✓የእግዚአብሔር መንግሥት እየሠራች መሆኑን የምናውቀው በልባችን በመንፈስ ቅዱስ ደስታና ሰላም፣ እንዲሁም በሕይወታችን የክርስቶስ ጽድቅ ሲገለጥ ነው።ነገሩ ከልብ ጋር የተያያዘ ስለሆነ የልብ ለውጥ ያስፈልጋል። ስለ እግዚአብሔር መንግሥት መናገር፣ መረዳትና በሕይወት መኖር አለብን! ይህንን የሚያደርግ ለዋጭ ቃል ወደ እኛ መጥቷል!🙌🙌🙌 ያነበበ ይጠቀማል 🙏 ተባረክልን መጋቢ🥰🥰🥰
ማቴዎስ 6:24-33 እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤" — ማቴዎስ 6:33 የዚህ ምንባብ አጠቃላይ አውድ ስለ እውነተኛ አምልኮ፣ ስለ ሕይወት ቅደም ተከተል እና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የሚናገር ነው። ጌታችን ኢየሱስ ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም" ብሎ ሲጀምር፣ ስለ አገዛዝና ስለ ሁለት ታላላቅ መንግሥታት እየነገረን ነው። 👑 1. መንግሥት "መንግሥት" የሚለው ቃል አገዛዝን፣ አስተዳደርን እና መቆጣጠርን የሚያመለክት ነው። ✓በዕብራይስጥ፦ (Malkhut) ✓በግሪክ፦ ባሲሊያ (Basileia) ✓በእንግሊዝኛ፦ Kingdom እግዚአብሔር አምላክ ንጉሥና ጌታ ስለሆነ፣ የሚገባውና ያለው የተዘጋጀ ዙፋን አለው። ✓መጥምቁ ዮሐንስ ስለ መንግሥቱ አብሥሯል (ማቴዎስ 3:1-2)። °ጌታችን ኢየሱስ የመጣበትን ዋና ምክንያት ሲናገር፦ " ለሌሎቹ ከተሞች ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል፤ ስለዚህ ተልኬአለሁና"* ብሏል (ሉቃስ 4:43)። በደቀ መዛሙርቱም መካከል ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በምሳሌዎች አሰፍቶ አስተምሯል (ማቴዎስ 13)። "ቀን ከቀጠሩለትም በኋላ ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያ ቤቱ መጡ፤ እርሱም ከጧት እስከ ማታ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በመመስከር አሳቡን ገለጠላቸው፤ እነርሱንም ለማሳመን ከሙሴ ሕግና ከነቢያት መጻሕፍት እየጠቀሰም ስለ ኢየሱስ አስረዳቸው።" — የሐዋርያት ሥራ 28:23 ⚔️ 2. የመንግሥት ለውጥ እና የደኅንነት ምሥጢር ወገኖቼ! ውጊያው የመንግሥትና የመንግሥት ነው—የጨለማው መንግሥት ወይም የብርሃኑ መንግሥት! ✓የመንግሥት ለውጥ፦ ሰው በጌታ በኢየሱስ ሲያምን የመንግሥት ለውጥ ያደርጋል። ከጨለማው ሥልጣን አውጥቶ ወደ ፍቅር ልጁ መንግሥት አፈላለሰን (ቆላስይስ 1:13)። ✓ዳግም ልደት፦ የምንወለደው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ነው (ዮሐንስ 3:3)። የምንወለደውም ከማይጠፋ ዘር በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ነው (1ኛ ጴጥሮስ 1:23)። ያላመኑትንም የምንጠራው ወደዚሁ መንግሥት ነው። ✓ የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠው የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስና በእርሱ በኩል እኛን ወደ መንግሥቱ ለመመለስ ነው (1ኛ ዮሐንስ 3:8)። ✓ የእግዚአብሔር መንግሥት ሠራዊት ያላት፣ ንጉሥ ያላት፣ የህይወት ስርዓት ያላት፣ ግዛት፣ ሕገ-መንግሥትና የተሟላ አቅርቦት ያላት ታላቅ መንግሥት ናት! 🔑 የእግዚአብሔር መንግሥት ማደሪያዋ የእግዚአብሔር መንግሥት የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪና መርማሪ በሆነው በእግዚአብሔር ዘንድ ያለች ናት። ነገር ግን እግዚአብሔር ለተጠሩትና ለወደዱት የመንግሥቱን ምሥጢር በመንፈሱ በኩል ገልጦላቸዋል! እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማያት አጸና፥ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።" — መዝሙር 103:19 የመንግሥቱ ዙፋን፦ የእግዚአብሔር መንግሥት የሚዳሰስ ቁስ አይደለችም። *የእግዚአብሔር መንግሥት በውስጣችሁ/በመካከላችሁ ናት"* ተብሎ እንደተጻፈ (ሉቃስ 17:21)፣ ዙፋኗ በአማኙ ልብ ውስጥ ነው።
⭐️ እሁድ ከጠዋቱ 3፡00 - 7፡00 ⭐️ የአምልኮ የጸሎት እና የቃል ጊዜ በአሮማ ቤተክርስቲያን 📍 አድራሻችን ከመገናኛ ወደ ቦሌ (ገርጂ) በሚወስደው መንገድ፣ ወደ 24 እንደታጠፉ ከአንበሳ ድልድይ 200 ሜትር ገባ ብሎ፤ ኤል ኤ (L.A) ሆቴል ፊት ለፊት እንገኛለን Location(https://maps.app.goo.gl/E2LpJ4com1FAQymX6?g_st=atm) የቤተክርስቲያኗ ቋሚ ፕሮግራሞች ➡️እሁድ ከጠዋት 3፡00-7፡00 ➡️ሐሙስ ማታ 11፡00- 2፡00 | Facebook | YouTube | TikTok |