ህልምህን ኑረው_Live your dream
Статистикаየቻናል አላማ ሰዎች ራዕያቸውንና አላማቸውን ለይተው በማወቅ ለተፈጠሩበት መልካም ስራ ማዋልን እና አስተሳሰባቸውን በመለወጥ የሚፈልጉትን ህልም እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ ፣ የአሸናፊነት ልማድ፣የአእምሯችንን ሚስጥራዊ አሰራር የምናውቅበት እና የስኬታማ ሰዎች ተሞክሮም እናቀርባለን። ዩቱዩቭ: https://www.youtube.com/@Live_Your_Dream2112 https://t.me/Attitudeplc
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Видео
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 209
- 1/48двое суток
- 239
- 1/72трое суток
- 258
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
“ሰዎች የምትናገትሩን ነገር ሊጠራጠሩ ይችላሉ፣ የምታከናውኑትን ነገር ግን ከማመን ውጪ ምርጫ የላቸውም” ይባላል! እውነተኛ ማንነት፣ ስም፣ ተቀባይነትም ሆነ ዝና የሚገነቡት ድርጊቶቻችን እንጂ የምናወራቸው ወሬዎች፣ የገባናቸው ቃል ኪዳኖች ወይም የምንሰጣቸው ማብራሪያዎች አይደሉም። ሰዎች የተናገርነውን ሊረሱት ወይም በሐሳባችን ላይ ጥርጣሬ ሊያድርባቸው ይችላል፤ ነገር ግን አንድን ነገር ጀምረን ስንጨርሰው እናን ከማመን ውጪ ምንም ምርጫ እንዳይኖራቸው ያደርጋል። · ታማኝ ነኝ እያልን፣ ግን የምንዋሽ ከሆነ፣ ሰዎች የሚያምኑት ድርጊታችንን እንጂ የምንናገረውን አይደለም። · ጎበዝ ሰራተኛ ነኝ እያልን፣ ግን ኃላፊነትን የምንሸሽ ከሆነ፣ ቃላቶቻችን ዋጋ ያጣሉ። ዘወትር ጨዋትን፣ ሥርዓትን እና ታማኝነትን የምናሳይ ከሆነ፣ ሰዎች በእኛ መተማመን ምንም ሌላ ማብራሪያ አይፈልጉም። በመሪነት ቦታ ላይም ቢሆን ሰዎች በቃላት ከምንሰጠው መመሪያ ይልቅ ዘወትር በተግባር የምናሳያቸውን ነገር ይከተላሉ። ወጥነት (ተመሳሳይ ትክክለኛ ድርጊትን ማዘውተር) ተዓማኒነትን ይፈጥራል። የአንድ ጊዜ መልካም ተግባር ሰዎች አድንቀውት ያልፋሉ፡፡ በሰዎቹ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ የሚያመጣው ግን ደጋግመን የምናደርጋቸው ነገሮች ናቸው። በዛሬዋ ቀን፡- ሰዎችን በቃላችን ለማሳመን ከመሞከር ይልቅ፣ የምናምንባቸውን እሴቶች መኖርን፣ የተናገርናቸውን ነገሮች መፈጸምንና ወጥ የሆነ ማንነትን ማሳየትን እንለማመድ፡፡ ይህንን ካደረግን በጊዜ ሂደት፣ ተግባሮቻችን ከማንኛውም ንግግራችን በላይ ጮክ ብሎ መናገር ስሚጀምር ተጽእኗችን እየሰፋ ይሄዳል። ምንጭ :ዶ/ር ኢዮብ 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን 🎯🎯🎯🎯🎯🎯 🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉ ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@Asfaww ቲክቶክ: https://tiktok.com/@asfaw_motivation ፌስቡክ: https://www.facebook.com/attitudease ቴሌግራም: https://t.me/Attitudeplc ለግል ለአስተያየትዎ: https://t.me/LYDAse1 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
መጽሐፍ ማንበብ በሰዎች ሕይወት፣ አስተሳሰብና ስኬት ላይ ታላቅ አዎንታዊ አስተዋፅኦ አለው:: የሚያነቡ ሰዎች ከማያነቡ ሰዎች የዕውቀት አድማሳቸው ሰፊና ጥልቅ ሲሆን አስተሳሰባቸውም የበሰለ ነው። መጻሕፍትን ባነበቡ ቁጥር ወደ ተለያዩ ዓለማት የመጓዝ፣የሰዎችን ሕይወት የመረዳትና ጥልቅ ጥበብን የመቅሰም ዕድል ያገኛሉ። ንባብ የቃላት እውቀታቸውንና የንግግር ክህሎታቸውን ከማሳደጉም በላይ፣ ለማንኛውም ችግር ምክንያታዊና ስልታዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ ይረዳቸዋል። እነዚህ ሰዎች በራስ መተማመናቸው ከፍተኛ ነው፤ምክንያቱም በውስጣቸው የማይነጥፍ የዕውቀት ስንቅ አላቸው። ንባብ ለእነሱ አእምሯቸውን የሚያድሱበት፣ ጭንቀትን የሚቀንሱበትና ሁልጊዜም ራሳቸውን የሚያውቁበት የብርሃን ጎዳና ነው። በአጭሩ፣የሚያነቡ ሰዎች ትላንት ከነበሩበት የተሻሉ ለመሆን በየቀኑ የሚተጉ የሕይወት መሐንዲሶች ናቸው። የማያነቡ ሰዎች በአንጻሩ ዕውቀታቸውና አመለካከታቸው በአካባቢያቸው በሚሰሙትና በሚያዩት ጥቂት ነገሮች ላይ ብቻ የተገደበ ይሆናል። ዓለም በየቀኑ በሚፈጥራቸው አዳዲስ እውነታዎችና የዕድገት ለውጦች ውስጥ በፍጥነት የመራመድ ዕድላቸው ጠባብ ነው። ንባብን ሕይወታቸው ያላደረጉ ሰዎች ለአድልዎ፣ለተሳሳቱ መረጃዎችና ለወሬ የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፤ ምክንያቱም ነገሮችን በምክንያትና በማስረጃ የማመዛዘን ልምዳቸው አልዳበረም። ይህም በሰዎች ላይ ጥገኞች እንዲሆኑና የራሳቸውን ጠንካራ አቋም እንዳይገነቡ ያደርጋቸዋል። አእምሯቸውን በአዲስ አስተሳሰብ ሳያድሱ ስለሚኖሩ፣ የሕይወት እይታቸው አሰልቺና ከተለመደው አስተሳሰብ የማይወጣ የመቀጨጭ ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። የንባብ ልምድ በብርሃንና በጨለማ መካከል እንዳለው ዓይነት የሕይወት ልዩነትን ይፈጥራል። 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን 🎯🎯🎯🎯🎯🎯 🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉ ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@Asfaww ቲክቶክ: https://tiktok.com/@asfaw_motivation ፌስቡክ: https://www.facebook.com/attitudease ቴሌግራም: https://t.me/Attitudeplc ለግል ለአስተያየትዎ: https://t.me/LYDAse1 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
The Overview effect ለዘመናት የሰው ልጅ አእምሯዊና ስነ ልቦናዊ መዋቅር በወሰኖች፣ በጥበቃዎችና በክልከላዎች ግንብ የታጠረ ነበር። ማንነታችንን የምንተርከው በካርታዎች ላይ በሰፈሩ የድንበር መስመሮች፣ በጎሳና በፖለቲካ የጎራ ክፍፍሎች፣ እንዲሁም በጠበቡ የማህበረሰብ ቡድኖቻችን ጭፍን ወገንተኝነት (tribal biases) ነው። ሁላችንም እንደየምርጫችን የተሰነጠቀ መስታወት ይዘን ያንን የያዝነውን ስባሪ ብቻ ሙሉው ሰማይ አድርገን የመቁጠር ስህተት ውስጥ እንወድቃለን። ነገር ግን ከዚህ ከከበበን የዕለት ተዕለት ውክቢያ ወጣ ብሎ በጥቁሩና ማለቂያ በሌለው የህዋ ባዶነት ውስጥ ይህንን የሰው ልጅ የስባሪ አስተሳሰብ በአንድ ቅፅበት የሚያክም፣ የአመለካከት አድማስን ሙሉ በሙሉ የሚገለብጥ አንድ አስደናቂ ስነ ልቦናዊ ክስተት አለ፤ እርሱም {ኦቨርቪው ኢፌክት} (The Overview Effect) ይባላል። ይህንን ፅንሰ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ ያፈለቀው የህዋ ፈላስፋው ፍራንክ ኋይት ሲሆን፣ ክስተቱም ጠፈርተኞች መሬትን ከህዋ ምህዋር ላይ ሆነው በሚመለከቱበት ጊዜ የሚገጥማቸውን ጥልቅና ስር-ነቀል የአእምሮና የንቃተ-ህሊና መለወጥ የሚገልፅ ነው። ይህ የፕላኔታችንን ውበት ዝም ብሎ በአድናቆት መመልከት ብቻ አይደለም፤ ከዚያ በላይ የሆነ የሰው ልጅን መኖርና ምንነት ዳግም የሚመረምር ህልውናዊ መናወጥ (existential rupture) የሚፈጥር ነዉ። መሬትን ከሩቅ፣ ከናኘው የአፅንፈ-ዓለም ፀጥታ ውስጥ ሆኖ መመልከት ሁሉንም ነገር አቅፎ የያዘን አንድ ወጥና የተሟላ ስርአት እንደማየት ነው። እዚያ ላይ የፖለቲካ ድንበሮች፣ የብሄር ክፍፍሎች ወይም ቀጠናዊ አጥሮች የሉም። የሰው ልጅ በጥቃቅን ነገሮች ተከፋፍሎ የሚኖርበት ያ አሮጌ ቅዠት በአንድ አፍታ ይበራል፤ በእርሱም ምትክ ፍፁም የሆነው ሁለንተናዊ አንድነት ጉልህ ሆኖ ይታያል። ይህ ክስተት አእምሯችንን ነገሮችን ለያይቶና ነጣጥሎ ከማየት ወደ አጠቃላይ ስርአታዊ ውህደት እንዲሸጋገር ያስገድደዋል። በምድራዊ ህይወታችን የሰው ልጅ አስተሳሰብ በአብዛኛው የሚመራው {እኛ እና እነሱ} በሚል የጎራ ክፍፍል ነው። ይህ ደግሞ በዝግመተ-ለውጥ ሂደት ውስጥ ራሳችንንና ቡድናችንን ለመጠበቅ ከአባቶቻችን የወረስነው አሮጌ አሻራ ነው። ነገር ግን ይህ ክስተት ያንን ጥንታዊ መዋቅር ሙሉ በሙሉ ያፈርሰዋል። የ{እኛ} የሚለውን ትርጉም አስፍቶ የአፅንፈ-ዓለሙን የመጨረሻ ጫፍ እንዲነካ ያደርገዋል። ይህ ታላቅ ሽግግር በሶስት ዋና ዋና አእምሯዊ ለውጦች ውስጥ ያልፋል። በመጀመሪያ፣ ከህዋ ምህዋር ላይ ሆነው ሲመለከቱ በሰዎች ታሪክ ውስጥ ለብዙ ጦርነቶችና እልቂቶች ምክንያት የሆኑት ፖለቲካዊ መስመሮች ሙሉ በሙሉ የማይታዩና የሌሉ ይሆናሉ። በምድር ላይ በደም የተፃፉት ድንበሮች ውቅያኖሶችን፣ ከባቢ አየርንና አህጉራትን ብቻ ከሚያውቅ ፕላኔት አንፃር ሲታዩ ምንኛ የሞኝነትና የከንቱነት ማሳያ መሆናቸው በግልፅ ይጋለጣል። በሁለተኛ ደረጃ፣ ተመልካቹ ሰፊና ሁለንተናዊ ወደሆነ ማንነት ይሸጋገራል። ከዚያ በኋላ ግለሰቡ ራሱን የአንድ የተወሰነ ሀገር ዜጋ ወይም የአንድ ጠባብ ርዕዮተ-ዓለም አራማጅ አድርጎ ማየት ያቆማል። ይልቁንም በጥቁሩ ህዋ ውስጥ እየተጓዘች ያለች በውስጧ ህይወትን ያቀፈች አንዲት ደካማና ውብ የጠፈር መንኮራኩር አካልና ተጓዥ አድርጎ ራሱን ይቆጥራል፤ ይህንን {መርከባዊዋ-መሬት ንቃተ ህሊና} (Spaceship Earth) እንለዋለን። በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ፣ በግለሰቡ {እኔነት} እና በውጪው ዓለም መካከል ያለው ጠንካራ አጥር መፍረስ ይጀምራል። የአፅንፈ-ዓለሙ ግዙፍነት በአእምሮ ውስጥ ጥልቅ የሆነ ትህትናንና የመገረም ስሜትን ይፈጥራል። በዚህ ጊዜ ምድራዊና ጥቃቅን የሆኑት የዕለት ተዕለት ጭንቀቶቻችን በጠቅላላው ስርአት ውስጥ ቀልጠው ይጠፋሉ፤ በእነርሱም ምትክ ለዚህች ፕላኔትና በውስጧ ላለው ህይወት ሁሉ ጥልቅ የሆነ የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት ይተካል። ይህ ስነልቦናዊ ክስተት የሰዉ ልጆች ምን ያህል መሻሻል የሚችል {progressive} የሆነ ዝግመተ-ለዉጣዊ የስነ ልቦና አጥሮች እንዳሏቸዉ በዉል ማረጋገጥ የቻለም ጭምር ነዉ።
የዝሆኑ ሰንሰለት (The Elephant Rope) 🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣 አንድ መንገደኛ በጎዳና ሲያልፍ አንድ ግዙፍ ዝሆን በአነስተኛ ገመድ ብቻ እግሩ ታስሮ ቆሞ አየ። ዝሆኑ ሰንሰለት አልታሰረም። በስተጀርባውም የሚታሰርበት የብረት አጥር የለም። ዝሆኑ በቀላሉ ገመዱን በጥሶ ማምለጥ እንደሚችል ግልጽ ነበር። ነገር ግን ለመሞከር እንኳን አይፈልግም። መንገደኛው ግራ በመጋባት የዝሆኑን አሰልጣኝ "ይህ ግዙፍ እንስሳ እንዴት በዚህች ደካማ ገመድ ብቻ ተይዞ ለመሰብሰብ አይሞክርም?" ሲል ጠየቀው። አሰልጣኙም ፈገግ ብሎ እንዲህ አለው፦ "ዝሆኖቹ በጣም ትናንሽ ልጆች እያሉ የምናስራቸው በዚህችው ገመድ ነው። በዚያ እድሜያቸው ገመዱን ለመበጠስ አቅም አልነበራቸውም። ሲያድጉና ግዙፍ ሲሆኑም በውስጣቸው 'ይህችን ገመድ መበጠስ አልችልም' የሚል እምነት አብሮአቸው ያድጋል። አሁንም ገመዱ ሊያስራቸው እንደሚችል ስለሚያምኑ መቼም ቢሆን ለማምለጥ አይሞክሩም።" 💡 የታሪኩ ዋና መልዕክት፦ ብዙዎቻችን በሕይወታችን ልክ እንደዚህ ዝሆን ነን። ድሮ በልጅነታችን ወይም ቀደም ሲል በነበረን ውድቀት ምክንያት "አልችልም" የሚል የገደብ እምነት (Limiting Belief) በውስጣችን እንፈጥራለን። ትልቁ ሰንሰለት ያለው እግራችን ላይ ሳይሆን አእምሯችን ውስጥ ነው። 📌 ጥያቄ ለእናንተ፦ እናንተስ ዛሬ እንዳታድጉ አምክኖ የያዛችሁ የአእምሮ "ገመድ" የትኛው ነው?
#የሰው_ልጅን_የሚለውጡ_ልማዶች !! 1. የአቶሚክ ልማዶች (Atomic Habits)፦ ትናንሽና ተከታታይነት ያላቸው ለውጦች በረጅም ጊዜ ውስጥ ትልቅ ውጤት ያመጣሉ። 2. በማንነት ላይ ያተኮረ ልማድ (Identity-Based Habits)፦ ልማድን ለመቀየር "ምን ማግኘት እፈልጋለሁ?" ከሚለው ይልቅ "ምን ዓይነት ሰው መሆን እፈልጋለሁ?" በሚለው ላይ ማተኮር። 3. አራቱ የባህሪ ለውጥ ህጎች (The Four Laws)፦ ማንኛውንም ልማድ ለመገንባት ግልጽ ማድረግ፣ ማራኪ ማድረግ፣ ቀላል ማድረግ እና አርኪ ማድረግ። 4. ልማድ መደራረብ (Habit Stacking)፦ አዲስ ልማድን ቀድሞ በነበረና በለመድነው ልማድ ላይ መጨመር። 5. አካባቢን ማስተካከል (Environment Design)፦ ለጥሩ ልማዶች ግልጽ የሆኑ ምልክቶችን በአካባቢያችን ማዘጋጀት 6. የሁለት ደቂቃው ህግ (The Two-Minute Rule)፦ ማንኛውንም አዲስ ልማድ ሲጀምሩ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ሊያልቅ በሚችል ቀላል ስራ መጀመር። 7. የማይመች ማድረግ (Make it Difficult)፦ መጥፎ ልማዶችን ለማቆም በመንገዳችን ላይ እንቅፋቶችን መፍጠር። አጫሽ ከሆንክ ለማጨስ በማይመች ቦታ መዋል። 8. ልማድን መከታተል (Habit Tracking)፦ የምናደርጋቸውን ስራዎች መዝግቦ መያዝ ስኬታማነታችንን እንድናውቅ ይረዳናል። 9. ወዲያውኑ የሚገኝ እርካታ (Instant Gratification)፦ አእምሯችን ለወደፊት ከሚገኝ ጥቅም ይልቅ አሁን ለሚያገኘው ደስታ ቅድሚያ ስለሚሰጥ፣ ለጥሩ ልማዶች አነስተኛ ሽልማቶችን ማዘጋጀት። 10. መሰላቸትን ማሸነፍ (Goldilocks Rule)፦ ልማዶች በጣም አስቸጋሪ ወይም በጣም ቀላል ሳይሆኑ፣ ተግዳሮት ያለባቸው ሲሆኑ ይቀጥላሉ። 📖 "Atomic Habits" ✍️ጄምስ 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን 🎯🎯🎯🎯🎯🎯 🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉ ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@Asfaww ቲክቶክ: https://tiktok.com/@asfaw_motivation ፌስቡክ: https://www.facebook.com/attitudease ቴሌግራም: https://t.me/Attitudeplc ለግል ለአስተያየትዎ: https://t.me/LYDAse1 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
🛑 #የዘገየ_ትክክለኛ_ውሳኔ... ራሱ ሌላ ስህተት ነው! (The Law of Timing) "አንድን ውሳኔ በትክክለኛው ጊዜ ካልወሰንከው፣ በኋላ ላይ መቶ በመቶ ትክክለኛ ቢሆን እንኳ ዋጋ የለውም፤ ምክንያቱም ጊዜው አልፏል።" ብዙ ሰው በሕይወቱ ስህተት ላለመሥራት በሚል ሰበብ አንድን ነገር ለማድረግ ለወራትና ለዓመታት ያስባል። "ሁሉንም ነገር አጥንቼና እርግጠኛ ሆኜ ነው የምወስነው" ይላል። እውነቱ ግን ይህንን ነው፦ "ፍጹም የሆነውን ቀን ለመጠበቅ ስትል የምታዘገየው እያንዳንዱ ትክክለኛ ውሳኔ፣ ዕድሉ ካለፈ በኋላ ምንም ዓይነት ውጤት ስለማያመጣ በራሱ ትልቅ ስህተት ነው።" ✅ ስኬት የሐሳብ ጥራት ብቻ አይደለም፤ የስሌትና የሰዓት (Timing) ጉዳይም ጭምር ነው። ልክ ከ3 ዓመት በፊት መጀመር የነበረብህን አንድ የዲጂታል ቢዝነስ ወይም ኢንቨስትመንት፣ ዛሬ ላይ ቆመህ "አሁን በሚገባ አጥንቼ ገባሁበት" ብትል እንኳ ያኔ ልታገኘው የምትችለውን ትልቅ የዕድገት ማዕበልና ጥቅም አታገኘውም። ውሳኔው ዛሬም ትክክል ሊሆን ይችላል ፤ ሰዓቱ ግን ስህተት ነው። በጦር ሜዳ ላይ ጥይት ካለቀ በኋላ የሚተኮስ እጅግ ምርጥ ኢላማ እንደማይጠቅመው ሁሉ፣ ዕድሎች ካለፉ በኋላ የሚወሰን "ትክክለኛ ውሳኔ" የቁጭት መሸፈኛ ጭምብል ብቻ ነው። ✅ ፍጽምና ወጥመድ ነው፦ ሁሉንም ነገር አውቄ እጀምራለሁ ስትል ጊዜው ይቀድምሃል። ፍጹም ዝግጁ ለመሆን አትጠብቅ ፤ ውሳኔህን ዛሬውኑ አውጅ። ✅ የፍጥነት ዋጋ ከፍ ያለ ነው፦ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ ቀስ ብሎ በትክክል ከሚራመደው ይልቅ፣ ፍርሃቱን ተቋቁሞ በፍጥነት ወስኖ ስህተቱን በመንገድ ላይ የሚያርመው ቆራጥ ሰው ቀድሞ ግቡ ላይ ይደርሳል። ✅ ጊዜ ዕድልን ይበላል፦ ዛሬ ያመነታህበትና ወደኋላ ያልከው ዕድል፣ ነገ ሌላ ሰው ቀድሞህ ወስኖበት ታሪክ ሲሠራበት ማየትህ አይቀሬ ነው። ታላላቅ የዓለማችን መሪዎችና ባለሀብቶች በሙሉ መቶ በመቶ እርግጠኛ እስኪሆኑ የጠበቁ አይደሉም፤ የጊዜን ውድነት ተረድተው "አሁንኑ" በሚል ፍጥነት የወሰኑ ጀግኖች እንጂ። አንተስ? ዛሬም ውሳኔህን በማዘግየት ላይ ነህ? 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን 🎯🎯🎯🎯🎯🎯 🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉ ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@Asfaww ቲክቶክ: https://tiktok.com/@asfaw_motivation ፌስቡክ: https://www.facebook.com/attitudease ቴሌግራም: https://t.me/Attitudeplc ለግል ለአስተያየትዎ: https://t.me/LYDAse1 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
የሁለቱ ተኩላዎች ታሪክ (The Two Wolves)። 🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣 አንድ አረጋዊ የቼሮኪ (Cherokee) ጎሳ መሪ ለልጅ ልጁ ስለ ሕይወት እያስተማረው ነው። "በውስጤ ትልቅ ውጊያ እየተካሄደ ነው" አለው ለብላቴናው። "በሁለት ተኩላዎች መካከል የሚደረግ በጣም አስፈሪ ውጊያ ነው። አንደኛው ክፉ ነው — እሱም ቁጣ፣ ቅናት፣ ሃዘን፣ ጸጸት፣ ስግብግብነት/ስስት፣ ትዕቢት፣ እራስን ማዘን፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ቅያሜ፣ የበታችነት ስሜት፣ ውሸት፣ የሀሰት ኩራት፣ የበላይነት ስሜት እና እራስ ወዳድነት (ego) ነው።" በመቀጠልም እንዲህ አለ፦ "ሌላኛው ደግሞ ጥሩ ነው — እሱም ደስታ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ተስፋ፣ መረጋጋት፣ ትህትና፣ ደግነት፣ ለሰዎች በጎ መሆን/ቸርነት፣ የሌሎችን ስሜት መረዳት (empathy)፣ ልግስና፣ እውነት፣ compassion (ርህራሄ) እና እምነት ነው። ይህ የውስጥ ውጊያ በአንተም ውስጥ እየተካሄደ ነው — በሌሎች ሰዎች ሁሉ ውስጥም ጭምር።" የልጅ ልጁም ስለ ነገሩ ለአንድ ደቂቃ ያህል ካሰበበት በኋላ አያቱን "ታዲያ የትኛው ተኩላ ነው የሚያሸንፈው?" ብሎ ጠየቀው። አረጋዊው የቼሮኪ መሪም በቀላሉ "የምትመግበው" ሲል መለሰለት። ይህ ታሪክ የንቃተ ህሊናን (awareness) ኃይል በግልጽ ያሳያል። የትኛውን ተኩላ መመገብ እንዳለብህ ከመምረጥህ በፊት፣ መጀመሪያ በውስጥህ ሁለት ተኩላዎች እንዳሉ ማወቅ (ነቅቶ ማስተዋል) ይኖርብሃል። መኖራቸውን፣ ረሃባቸውን እና በውስጥህ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ ማስተዋል አለብህ። 1️⃣ የማንነትህ ቀራፂ እራስህ ነህ፦ በሁላችንም ውስጥ ጨለማና ብርሃን አለ። የሚያሸንፈው ግን ዕድል ሳይሆን አንተ ትኩረትና ጉልበት ሰጥተህ በየቀኑ የምትመግበው ስሜት ነው። 2️⃣ "የመመገብ" ኃይል፦ በቂም እና በቁጣ ላይ ስታተኩር ክፉውን ተኩላ ታጠነክረዋለህ። በምስጋና፣ በይቅርታና በደግነት ላይ ስታተኩር ደግሞ መልካሙን ተኩላ እያሳደግከው ነው። 3️⃣ ንቃተ ህሊና (Awareness)፦ በውስጥህ ውጊያ እንዳለ መጀመሪያ ካላስተዋልክ፣ የትኛውን መመገብ እንዳለብህ መምረጥ አትችልም። ሁሌም ስሜቶችህ ከመምራትህ በፊት ቆም ብለህ አስተውላቸው። 📌 ጥያቄ ለእናንተ፦ ዛሬ በሃሳባችሁና በድርጊታችሁ እየመገባችሁት ያላችሁት የትኛውን ተኩላ ነው? 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን 🎯🎯🎯🎯🎯🎯 🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉ ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@Asfaww ቲክቶክ: https://tiktok.com/@asfaw_motivation ፌስቡክ: https://www.facebook.com/attitudease ቴሌግራም: https://t.me/Attitudeplc ለግል ለአስተያየትዎ: https://t.me/LYDAse1 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
"ውድድሩን የማሸንፈው በስታዲየም ውስጥ ብርሃን ባለበት አይደለም፤ ድሉ የሚወሰነው ከዓይን ጠባቂዎች ርቆ በለሆሳስ በሚደረግ ትጋት፣ በባዶ ጂም ውስጥ በለፋሁባቸው ሰዓታት ውስጥ ነው።" ሙሀመድ አሊ
ስራ-ፈት አትሁኑ! ለምንም ነገር እራሳችሁን ካልሰጣችሁ በሁሉም ነገር መረበሻችሁ አይቀርም። ስራፈትነት ከውጤት አልባነት በዘለለ ብክነትንም ያስከትላል። የማይረባ ሃሳብ መነሻው ከስራፈት አዕምሮ ነው። ስራ ፈቶ መቀመጥ ለማንም ከባድ አይደለም፣ ማንንም የሚፈትን አይደለም። ስራፈት መሆንን መምረጥ መብት ነው፣ ህይወት ግን ለስራፈቶች ቦታ የላትም። እንኳን ያለስራ ተቀምጦ ይቅርና ቀኑን ሙሉ እየሰሩም ህይወት ክብደቷን አትቀንስም። መጥፎ ሀሳቦች የሚቆጣጠሩን መቼ ይመስሏችኋል? በቀላሉ ለሱስና ለአሉታዊ ልማዶች የምንጋለጠው መቼ ይመስላችኋል? በእርግጥም ያለስራ የምናሳልፈው ጊዜ ብዙ ሲሆን ነው። የሰው አዕምሮ በስራና በፈጠራ ሀሳቦች ካልተወጠረ በቀላሉ ለውዳቂና ጥቃቅን ሀሳቦች መጋለጡ አይቀርም። ሁሌም እድገት በሌለው ኋላቀር ሀሳብ ስትሞሉ ልባችሁ እየደነደነ፣ ግዴለሽና ተስፋቢስ እየሆናችሁ ትመጣላችሁ። ስራ ገቢ ከማምጣቱም በላይ የህሊና እረፍትን ይሰጣል። ያለምንም ስራ ቁጭ ብሎ መዋልና እራስን በስራ መወጠር የሚሰጡት የህይወትና የሀሳብ ነፃነት እኩል አይደለም። አዎ! ስራ-ፈት አትሁኑ! አዕምሯችሁን በሚያሳድጓችሁ ሀሳብና ስራ ወጥሩ፣ ነፃነትን በሚነፍጓችሁ ብዙ ነፃና የእረፍት ጊዜያት ህይወታችሁን አትሙሉ። የተገደበ እረፍትና የተገደበ የስራ ሰዓት ያስፈልጋችኋል። ስራፈት አዕምሮ የሰይጣን መነሃሪያ ነው። ሰይጠናን እንደፈለገው ይመራዋል፣ የፈለገውን ያስደርገዋል፣ ያሰኘው ነገር ውስጥ ይከተዋል። ስራፈት ስትሆኑ ሰይሰን ብቻ ሳይሆን የሰውም መጫወቻ ትሆናላችሁ። ይብዛም ይነስም ስራ በእራሱ ክብር ነው፣ አንድ መዋያና አዕምሮን ማሳረፊያ ነገር ማግኘት በእራሱ ስኬት ነው። ምንም ቢሆን ካለመስራት መስራት ይሻላል፣ የማይረባ ሀሳብ ከማሰብ ጠቃሚና ህይወት ቀያሪ ሀሳብን ማሰብ ይሻላል። ሁን ብላችሁ እራሳችሁን ጫና ውስጥ ክተቱት፣ ስራፈት በመሆን በማያሳድጋችሁ ምቾት ውስጥ አትቀመጡ። ወጣ በሉ፣ እራሳችሁን ፈትኑት፣ አቅማችሁን መዝኑ፣ እውቀታችሁን በተግባር ግለጡት። ተቀምጦ መናን ከሰማይ መጠበቅ አያዋጣም። ምንም ቢሆን መናው እስከሚወርድበት ቦታ መጓዝ የግድ ነው። "ሳይሰሩ የሚበሉ እጆች የተረገሙ ይሁኑ" እንደሚል መፅሀፍ ቅዱስ እራሳችሁን የወጣት ተጧሪ አታድርጉ። አዎ! ጀግናዬ..! ተንቀሳቀስ፣ ዞር ዞር በል፣ ለእድገትህ መሱዓትነት ለመክፈል ተዘጋጅ። አርሶ፣ ዘረቶ፣ አርሞ፣ አጭዶ፣ ወቅቶ ሰብሉን ለገበያ የሚያቀርበውን የብርቱውን ገበሬ ታታሪነት ተመልከት። መስራት ብቻ ሳይሆን ጠንክሮ መስራት በራሱ ዲኤንኤው (DNA) ውስጥ ነው። ማንነቱን ለስራ አሳልፎ ሰጥቷልና በቀላሉ የማይሰበር ጠንካራ ልብ አለው፣ የእጆቹን ስራ ፈጣሪው እንደሚባርክለት ከልቡ ያምናል፣ ፅናቱና ታታሪነቱ እንደሚከፍለው ያውቃል። ስራ ስትፈታ እጆችህ የሰይጣን መጠቀሚያ ይሆናሉ። ለመብላት መዝረፍ ትጀምራለህ፣ ስራፈትነትህን ለመርሳት ወደ ሱስ ትገባለህ፣ በአጭር ጊዜ ገንዘብ ለማግኘት ወንጀልን ጨምሮ የተለያዩ አቋራጭ መንገዶችን ትጠቀማለህ። ስራ አትናቅ፣ ከሚያስገኝልህ ገንዘብ በላይ የሚሰጥህን የሰራተኝነት ነፃነት አስብ። ስራ እየናቁ ተንቀው የቀሩ ብዙ ሰዎች አሉ፣ ስራ እየመረጡ ምራጭ ሆነው የቀሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ዛሬ በገቢው ያነሰ ስራን ብትሰራ ሁሌም እርሱን እየሰራህ አትኖርም። የሰው ልጅ ምንም ሰርቶ ምንም ገቢ ቢያገኝ አጠቃቀሙን ካወቀበት በሂደት እራሱን ማሳደጉ አይቀርም። ጠንቃቃ ሁን፣ ስራህን አክብር፣ ልብና አዕምሮህን አስገዛለት፣ ጠንክረህ ስራ የነገው ህይወትህንም ዛሬ እራስህ ወስን። 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን 🎯🎯🎯🎯🎯🎯 🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉ ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@Asfaww ቲክቶክ: https://tiktok.com/@asfaw_motivation ፌስቡክ: https://www.facebook.com/attitudease ቴሌግራም: https://t.me/Attitudeplc ለግል ለአስተያየትዎ: https://t.me/LYDAse1 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
"የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር መቃቃር የጀመረው ራሱን ከተፈጥሮ ሁሉ የበላይ አድርጎ መመልከት ሲጀመር ነው።ለዚህም መነሻ ምክንያት የክርስትና አስተምህሮ ነው።" ብሩህ አለምነህ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሰፊ ዘመናትን የያዙት የባርያ ንግድ፣ ቅኝ ግዛት፣ የተለያዩ ዓይነት ባርነቶችና የሴቶች ጭቆናዎች ሁሉ መንስኤያቸው የሰው ልጅ መቆጣጠርንና ጥቅምን ዓላማው ባደረገ አስተሳሰብ መመራቱ ነው፡፡ አንድን ነገር “መቆጣጠር” ካሰብክ ራስህን የዚያ ነገር አካል አድርገህ ማሰብህን አቁመሃል፡፡ “መቆጣጠር” የሚለው ሀሳብ የሚመጣው ራስህን ከዚያ ነገር ለይተህ ስታየው ነው፡፡ እናም አውሮፓውያን በዚህ መንገድ ተጉዘው ራሳቸውን ከተፈጥሮ ገነጠሉ፤ ራሳቸውን ከተፈጥሮ መገንጠል ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮን ለሰው ልጅ መጠቀሚያ ብቻ የተፈጠረ አድርገው እንዲቆጥሩት አድርጓቸዋል፡፡ በዚህ አስተሳሰብ ላይ ተመስርተውም የፈጠሩት ሃይማኖት (ክርስትና)፣ የካፒታሊዝም ስልተ ምርት፣ ፍልስፍናና ሳይንስም ተፈጥሮን ይበልጥ እንደመጠቀሚያ እና ሜካኒካል በሆኑ ክስተቶች የተሞላ አድርገው እንዲያስቡት አድርጓቸዋል፡፡ ለምሳሌ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሄር ምድርን የሠራት፣ እንስሳትንና እጽዋትንም የፈጠራቸው ለሰው መጠቀሚያነት እንደሆነ ይናገራል፤ “እግዚአብሄርም አለ፡- ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር፤ የባሕር አሣዎችንና የሰማይ ወፎችን፤ እንሳሳትንና ምድርን ሁሉ፤ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ፤” (ዘፍ 1፥ 26) "አላህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ ያስገዛላችሁ፤ ግልጽና ድብቅ የሆኑትንም ጸጋዎቹን በፊታችሁ ላይ ያፈሰሰላችሁ መሆኑን አታዩምን?" (ቁርአን 31፥20) እንደዚህ አይነት መንፈሳዊ አስተምህሮ እንደ ታሪክ ምሁሩ Lynn White, Jri አመለካከት፣ "የሰውን ልጅ ራሱን ከተፈጥሮ የተገነጠለና የተለየ፤ የፍጥረታት ሁሉ ማዕከልና የሁሉም የበላይ አድርጎ እንዲመለከት በማድረግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ " በሃይማኖታዊ አስተምህሮው ከተፈጥሮ ራሱን የገነጠለው አውሮፓ “ተፈጥሮን መቆጣጠርና ማስገበር ” በሚል መርህ ወደሚመራው ካፒታሊስታዊ ስልተምርት ተሸጋገረ፡፡ ካፒታሊዝምም የገበያ ውድድርን በማፋፋምና ከፍላጎት በላይ የሚጠቀም ማህበረሰብን በመፍጠር ተፈጥሮ ላይ የመጨከኑና ከመጠን በላይ የመበዝበዙን መንገድ አጠናክሮ ገፋበት፡፡ እንደ አዲሶቹ ማርክሲስቶች አመለካከት ግን የካፒታሊዝም ጦስ የሰውን ልጅ ከተፈጥሮ በመገንጠል ብቻ አያበቃም፤ "ካፒታሊዝም የሰውን ልጅ ከተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን ከራሱ ሰውነትም ገንጥሎታል፡፡ ካፒታሊዝም የሰውን ልጅ ሃይል በገበያ ብዙ ትርፍ ሊያመጣ እንደሚችል ኢንቨስትመንት በመቁጠር ሰውነትን ወደ ሸቀጥነት ቀይሮታል፡፡" እናም ወደ ሸቀጥነት የተቀየረው ሰው ለተፈጥሮ የሚያዝንበት ህሊና አጣ፡፡ የጥንቱና የምዕራብያውያን ፍልስፍና ዋነኛ ትኩረቱ ሰው ከሚኖርበት አካባቢና ከዲበ አካላዊው (ከሰማያዊው) ዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያስስ ነበር፡፡ እውነትንና እውቀትን፤ ውበትንና የሕይወት ትርጉምን ሁሉ በዚህ ሂደት ውስጥ ለማግኘት ይሞክር ነበር፡፡ ይሄም ሂደት ከተፈጥሮ ጋር የነበረውን ጥብቅ ቁርኝት የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ የጥንቱ አውሮፓዊነት ከተፈጥሮ ጋር መቃቃር የጀመረው ግን ራሱን ከተፈጥሮ ሁሉ የበላይ አድርጎ መመልከት ሲጀመር ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ትምክህታዊ አመለካከት እንዲይዝ ካደረጉት አስተምህሮቶች ውስጥ ዋነኛው ደግሞ ክርስትና ነው፡፡ " የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።" መዝሙረ ዳዊት 115፥16 ክርስትና (እና እስልምና) እግዚአብሄር ምድርን ለሰው ልጅ መጠቀሚያ እንደፈጠረ በማስተማር የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር የነበረውን ህብረትና ጓደኝነት ቆረጡት፡፡ አውሮፓዊነትም በዚህ የክርስትና አስተምህሮ ተጠልፎ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ግንኙነት ከሁለንተናዊ ህብርነት ወደ ገዥና ተገዥ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ፣ መለኮታዊና አለማዊ ወደሆነ “ቁጥጥር እና ጥቅም”ን ታሳቢ ወዳደረገ የሁለትዮሽ ግንኙነት ተቀየረ፡፡ የኒውተን ሜካኒክስ እንዲሁም የሆብስ፣ የላሜትሪ እና የዴካርት ፍልስፍናዎች መሰረታቸው ይሄው በሰውና በተፈጥሮ መካከል ያለው የበላይነትና የበታችነት የሁለትዮሽ ግንኙነት ነው፡፡ እነሱ የሚመኩበት “የምክንያታዊነት” እና “ተፈጥሮን በመቆጣጠር የማስገበር” አካሄድ መጨረሻ ላይ የምድራችንንና አጠቃላይ የሰውን ልጅ ህልውና የከፋ አደጋ ላይ ጣለው፡፡ አውሮፓዊነት ከተፈጥሮ ጋር የነበረውን የስሜት ቁርኝት ትቶ የተጓዘበት መንገድ መጨረሻው ተፈጥሮን በማምከን የሰውን ልጅ ለከፋ አደጋ ዳረገው፡፡ ✍️ ብሩህ አለምነህ 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን 🎯🎯🎯🎯🎯🎯 🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉ ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@Asfaww ቲክቶክ: https://tiktok.com/@asfaw_motivation ፌስቡክ: https://www.facebook.com/attitudease ቴሌግራም: https://t.me/Attitudeplc ለግል ለአስተያየትዎ: https://t.me/LYDAse1 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
ድንቅ ሀሳቦችና አባባሎች 1.የሰው ዘር ጠቅላላ ፍለጎት ማቆሚያ የሌለው እና ፋታ የማይሰጥ የስልጣን ወይም የክብር ጥማት ነው።መደምደሚያውም ሞት ብቻ ነው።" ቶማስ ሆብስ 2."ሰው ነፃ ሆኖ ቢወለድም በሄደበት ቦታ ሁሉ በሰንሰለት ተጠፍንጓል።አንዳንዱ ራሱን የሌሎች አለቃ አድርጎ ያስባል።ሆኖም ከእነሱ በባሰ ባርነት ውስጥ ነው።ይህ ለውጥ እንደምን መጣ አላውቅም። ምን ጉዳይ ህጋዊነቱን ያፀድቅለታል ? እርሱን መመለስ እንደምችል አሰባለሁ።" ዣን ዣክ ሩሶ 3."ሰዎች ዲሞክራሲያዊውን መሪ ሁልጊዜም የፍላጎታቸው ወኪል አድርገው ወደ ታላቅነት ምኩራብ ተንከባክበው ያወጡታል።ይህ እንግዲህ የአምባገነንነት ዛፍ የሚያጎናቁልበት ግልፅ ስር ነው።" አፍላጦን 4.«ከሰዎች መሃል የሚበዙቱ ስለራሳቸውን ብቻ ሲያስቡ ፤ የሚመሩባቸው ፍላጐቶችም በአንድ ምልከታ በቀላሉ የሚገመቱ እና በወቅቱ ባሉበት ሁኔታ ዙርያ የሚሽከረከሩ ናቸው።" ጆን ስትዋርት ሚል 5"በህይወት ያለ ነገር ሁሉ ለአንድ ነገር ሊታዘዝ ግድ ነው! እናም ለራስህ መታዘዝ ካልቻልክ ሌላው ሰው ያዝሀል። ኃያላን ራሳቸውን ይታዘዛሉ .. ሌሎችንም ያዛሉ! እነዚያ ለራሳቸው የታዘዙት ደካማ የሆኑትን እንዲያዝዙ ግድ ይሆናል።" ፍሬድሬክ ኒቼ 6."ሰዎች በተፈጥሯቸው ነፃ፣ እኩል እና ራሳቸውን የቻሉ በመሆናቸው ማንም ከራሱ ፍቃድ ውጭ መብቱ ተነጥቆ በሌላው ፖለቲካዊ ሉዓላዊ ስልጣን ስር ሊውል አይገባውም።" ጆን ሉክ 7."አንድ ነገር መረዳት ማለት ከባህሪይ እና ከውስጣዊ ማንነቱ ጋር መተዋወቅ ነው።" ጀርም ቤንታም 8."የአገር መልካምነት (በምግባር ልዕልና መላቅ) በመንግስት ስርዓቷ የሚሳተፉ ዜጎቿ መልካምነት ድምር ውጤት ነው።" አሪስጣጢሎስ 9."መልካም አርበኛ እና እውነተኛ ፖለቲከኛ በአገሩ ያለውን እሴት እንዴት አሟጦ እንደሚጠቀም ያሰላስላል።" ኢድመንድ በርክ 10."ብዙውን ጊዜ መንግስታት የዛሬውን እውነታ ለመጋፈጥ ሲደፍሩ አይስተዋልም። ከዚህም የተነሳ ለሚመጣው ዝግጁ አይደሉም።ለዜጎቻቸው የሚያቀርቡትም የማይጨበጥ ምናባዊ ደስታን ብቻ ይመስላል።" ጀርም ቤንታም 11. "ታላላቆቹ የፖለቲካ እሰጥ አገባዎች እና ግጭቶች በሀይማኖት ፣በብሄር ፣በመብት ፣በነፃነት ስም የሚደረጉ ይመስላሉ።ሀቁ ከዚህ ይለያል።ከውብ መፈክሮች ጀርባ ድብቅ የግል ጥቅምን የማስጠበቅ እኩይ ጠባያት አሉ።" ኢድመንድ በርክ የትኛውን አባባል የበለጠ ወደዳችሁት? 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን 🎯🎯🎯🎯🎯🎯 🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉ ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@Asfaww ቲክቶክ: https://tiktok.com/@asfaw_motivation ፌስቡክ: https://www.facebook.com/attitudease ቴሌግራም: https://t.me/Attitudeplc ለግል ለአስተያየትዎ: https://t.me/LYDAse1 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
ለውጥን እንዴት እናስተናግድ ?! የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ወይንም ሌሎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሁኔታ የሚመለከተን ለውጥን እንዴት እናስተዳግድ ለሚለው ጥያቄ ዘመናትን የተሻገረ በሚሊየን ኮፒዎች ከ37 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመውን አይቤን ማን ወሰደው? (Who Moved My Cheese?) መጽሃፍ ዳሰሳ እነሆ ፡ አንብባችሁ እንድትጠቀሙበት እነሆ ብለናል፡፡ ለውጥ አይቀሬ ነው…
የምትሸሸው ችግር ከኋላህ ይከተልሃል፤ የምትጋፈጠው ግን ከፊትህ ይርቃል።
ልብህን አትክፈት! ትኩረት ሁሉ እናንተ ላይ እስኪሆን ድረስ እራሳችሁ ላይ አተኩሩ። ትኩረት ትልቁ ህይወት ቀያሪ መሳሪያችሁ እንደሆነ አስታውሱ። ትኩረት መሳብ በእራሳችን ፍቃድ የፈለግነውን ነገር በእጃችን እንደመሳብ አይደለም። ትኩረት መሳብ ማለት የሌሎችን ልብ ማሸነፍ ማለት ነው። ምንም ብታደርጉ የሰውን ልብ እስካልነካችሁና እስካልማረካችሁት ድረስ በፍፁም ትኩረትን መሳብ አትችሉም። ጠንካራ ሰራተኞች፣ ብዙዎች ከሚጓዙበት መንገድ በተለየ መንገድ የሚጓዙ ሰዎች፣ ሌሎች የሚሰሩትን ስራ በተሻለ መንገድ የሚሰሩ ሰዎች አይን ሁሉ እነርሱ ላይ ነው፤ ብዙ ነገር ይወራባቸዋል፤ የሚፈልጉትን ነገርም በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። በአንድ በመረጣችሁት ዘርፍ አሸናፊ ሁኑ ትኩረት አለመሳብ አትችሉም። ብዙ ጊዜ እናንተ እራሳችሁ የምታተኩሩበት ነገር እውነተኛ ማንነታችሁን የሚያሳይ ይሆናል። ተራ ነገር ላይ ጊዜ የምታጠፉ፣ በጊዜያዊ ነገር የምትብከነከኑ፣ አንድ ነገር ጫፍ ይዛችሁ ዘመናችሁን ሁሉ እርሱን የምታሳድዱ፣ የማይፈልጋችሁን ሰው እየተከተላችሁ ዋጋችሁን የምታሳንሱ አይነት ሰው ከሆናችሁ በእርግም ደካማና ልፍስፍስ ሰዎች ናችሁ። ነገር ግን በተቃራኒው ትኩረታችሁን ፈጣሪያችሁ ላይ፣ እራሳችሁ ላይና አላማችሁ ላይ ካደረጋችሁ ሁሌም አሸናፊና ጠንካራ ሰዎች ናችሁ። አዎ! ጀግናዬ..! ልብህን አትክፈት! ለሚረባውም ለማይረባውም፣ ለሚጠቅመውም ለማይጠቅመውም፣ እንዲሁ ለተራውና ለትርኪሚርኪው ሁሉ ልብህን አትክፈት፣ ወደ ማዕከላዊው ውስጠትህ አታስገባው። ልብህን ደንደን ውስጥህንም ሻከር አድርገው። በወጡ በገቡ ቁጥር ሴት ማሳደድ፣ ዛሬም ነገም የማይጠቅም ፖለቲካ መተንተን፣ ቅድምም አሁንም ሰዎችን ማማት፣ ሁሌም በፌዝና በጫወታ መጃጃል በህይወትህ ውስጥ ምንም አይነት ትርጉም አይሰጥህም። ህይወትህን መኖር ካለብህ ልብ የሚፈልገውን ነገር እያደረክ ኑር፣ የእውነት ተፅዕኖ መፍጠር ከፈለክ የተኛውን ማንነትህን ቀስቅሰው፣ ትኩረት መሳብ፣ የሰዎችን ልብ ማግኘት የውስጥ መሻትህ ከሆነ ድምፅህን አጥፍተህ እራስህ ላይ ስራ፣ በየቀኑ አላማህን ኑር፣ በየጊዜው እራስህን እያሻሻልክ ተጓዝ። አይኖች ሁሉ እራሳቸውን ገዝተው፣ ልባቸውን አሙቀው፣ ለእራሳቸው ተነሳሽነትን ፈጥረው፣ ምክንያት አበጅተው ሌትከቀን የሚተጉ ሰዎች ላይ እንደሆነ አስታውስ። አዎ! ልብ ያስፈልግሃል። ደንዳና ልብ፣ በሆነው ባለው የማይሸበር፣ ሰው ተደግፎ እራሱን የማያጣ፣ በሰው ተማምኖ ገደል የማይገባ፣ በስንፍና በደካማነት የማይፈረጅ፣ ውስጡ እንደ አለት የጠነከረ፣ ለምንም የማይበገር ፅናት ያለው፣ ማንንም ከመስማቱ በፊት ውስጡን የሚያዳምጥ ጠንካራ ልብ ያስፈልግሃል። ነቃ ብለህ ልብህን ጠብቅ፣ ለራስህ ለመወገን ተዘጋጅ፣ አይንና ጆሮህን ሁሉ እራስህ ላይ አድርግ። ቀጣዩ እርምጃህ ምንድነው? ወደፊት ምን ለማድረግ አስበሃል? የኋላ መስታወት እያየህ መኪናህን ወደፊት እንደማትነዳ አስታውስ። በህይወትም እንዲሁ ወደፊት ትጓዝ ዘንድ ኋላ የቀሩ ታሪኮችህን ለትምህርት ያክል በትንሹ በማስታወስ ሙሉ ትኩረትህን ግን ወደፊትህ ላይ ማድረግ ይኖርብሃል። ሁሌም ቢሆን ትልቁ ፕሮጀክትህ እራስህ እንደሆንክ አስታውስ። ማንም ጠላት የለህም፣ ወዳጆችህ በሙሉ ደግሞ ያንተን ማዳን ይፈልጋሉና እራስህን አድነህ ለእነርሱም ድረስላቸው። 📌አሁኑኑ ይ🀄ላ🀄ሉን በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን 🎯🎯🎯🎯🎯🎯 🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉ ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@Asfaww ቲክቶክ: https://tiktok.com/@asfaw_motivation ፌስቡክ: https://www.facebook.com/attitudease ቴሌግራም: https://t.me/Attitudeplc ለግል ለአስተያየትዎ: https://t.me/LYDAse1 ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ፀንቶ ይኑሩ!
«የዓለም ታሪክ ነፃነትን ለማወቅ ከሚደረግ ሒደት ውጭ ምንም አይደለም።» ፍሬድሪክ ሄግል ታላቁ ጀርመናዊ ፈላስፋ ፍሬድሪክ ሔግል "philosophy of history" በተሰኘው መፅሀፍ ላይ የዓለም ታሪክ አጋጣሚ ያከታተላቸው ኹነቶች ትርዒት ሳይሆን በተቃራኒው ምክንያታዊ እና የታሰበበት ዕቅድ ውጤት ነው ይለናል። ይህ ቅጥ አምባር በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ ቁልጭ ብሎ ይታያል። የፖለቲካ ጥናትም የተሟላ የሚሆነው ተቋማት እና ሰብዕናዎች በትልቅ ዓላማ ያነገበ የታሪክ እድገት ማዕቀፍ ውስጥ ከተከወነ ብቻ ይሆናል፡፡ ለዚህ ሒደት ወይም ቅጥ አምባር (ፓተርን) ሔግል ስያሜ አውጥቶለታል። ታላቁ ኃሳብ ወይም ፍፁማዊ እውቀት (The ldea) ሲል ይጠራዋል። ሔግል በፖለቲካ ሒደት ውስጥ ኃሳብ ላለው ትልቅ ፋይዳ አፅንኦት ስለሚሰጠው ስያሜው የተገባ ይመስላል። ቁሳዊው የሰዎች እና የተቋማት ዓለም ለሔግል ብዙም ጉዳዩ አይደለም። ይልቁን ለቁሳዊው ዓለም አቅጣጫ እና ግብ የሚሰጠው መንፈስ ወይም ኃሳብ ላይ ማተኮርን ይመርጣል። ታላቁ ኃሳብ በማህበረሰብ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ እንደ ፍትህ ፤ ነፃነት ያሉ ረቂቅ እሳቤዎችን ሁሉ ጠቅልሎ የሚይዝ ማዕቀፍ ነው። «ነፃነት ይላል ሔግል በሰዎች ተግባር ውስጥ ሳይሆን በሰዎች ግንዛቤ ውስጥ ይገኛል። ፖለቲካን ለመረዳትም ማጥናት ያለብን የሰዎችን ድርጊት አይደለም፡፡ ድርጊታቸውን እንዲፈፅሙ የሚገፋፋቸውን መንፈስ እንጅ። የሰው ዘር ታሪክ በንቃት የተተለመ የሆነ ግብ ይዞ አልተጀመረም። ማህበራዊ ደመ ነብስ ንቁ የሆነ ለህይወት እና ለንብረት ደህንነት መሻትን ያመላክታል። እናም ማህበረሰብ በሚቋቋምበት ጊዜ ይህ ዓላማ ይበልጥ ጠቅላይ ሆኗል። የዓለም ታሪክ የሚጀምረው ጠቅላይ ግብን በመረዳት ነው። የመንፈስ ኃሳብ በስውር ቅርፁ ንቁ ደመነብስ ይሆናል።» ይለናል። በታሪክ ማዕከል ውስጥ ከህቡዕ ልቦና ወደ ንቁ ልቦና ወይንም ካለመንቃት ወደ ንቃት የተደረገው ሽግግር አለ። ይህም ወደ ፍልስፍናዊ ነፃነት የሚያደርሰው ሒደት ነው። አስተያየቱን ሲቀጥልም፦ «የነፃነት ዋና ተፈጥሮ ራሱን ወደማወቅ መምጣቱ ነው። በዚህም ህልውናውን ይገነዘባል።ሰዎች ከታላቁ ኃሳብ ጋር መኖርን ማወቅ አለባቸው። ሊያመልጡት አይቻላቸውምና። ሰዎች እና ተቋማት ነፃነትን ለማወቅ ከፈለጉ በትልቁ የታሪክ ሒደት ውስጥ ትክክለኛ ቦታቸውን ለማወቅ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ ታሪክ በእርሱ አመለካከት መሠረት በነፃነት አቅጣጫ የሚደረግ ተቋማዊ የለውጥ ሒደት ነው። ሰዎች ነፃነትን እንዲጨብጡ የህልውናቸውን ምክንያት ወደማወቅ ከፍታ ማንሰራራት አለባቸው፡፡ ስለዚህ ነፃነት ከእውቀት ወይም ንቃተ ልቦና (consciousness) ተለይቶ ሊታይ አይችልም። ነፃ የሆነ ሰው ለድርጊቱ እና ለባህርዩ የክልከላ አጥር ያልተበጀለት ሰው ሳይሆን በታሪክ መስክ ላይ ትክክለኛ እና ልዩ ስፍራውን ጠንቅቆ ያወቀ ነው፡፡ ይህንን ነፃነት የሚያጐናፅፈው ታላቁ ኃሳብ ብቻ ነው።" በፖለቲካ ንፍቀ ክበብ ውስጥ ብዙ ሰዎች ፍዝ ናቸው። የመረዳትም የመሳተፍም ንቃት የላቸውም፡፡ እጣ ፈንታቸውን ያለ ተቃውሞ እና ያለ አመፃ ይቀበላሉ። እነዚህ ሰዎች ሳያውቁት በጦርነት ይፈጃሉ ፤ በረሃብ ያልቃሉ ፤ በአምባገነን ጭቆና ይቆረቁዛሉ። በእያንዳንዱ ዘመን አልፎ አልፎ ግን ብቅ የሚሉ ልዩ ሰብዕናን የታደሉ ፤ የነቁ እና አብዮተኛ ግለሰቦች አይጠፉም። የአንድ መደብ አባላት አይደሉም። ልዩ መብት የታደሉ ወይንም የተነፈጉም አይደሉም። ከየትኛውም አቅጣጫ ሊወጡ የሚችሉ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ - ይላል ሔግል የፖለቲካዊ ተግባር ሰዎች ናቸዉ። የራሳቸውን ግብ እና ፍላጐት ሰንቀው በአንድ ኃሳብ ይጓዛሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች የዲያሌክቲካዊው ሒደት ዋነኛ መሳርያ ናቸው። በግልፅ ባይታወቃቸውም የተቃርኖ (አንቲቴሲስ) ኃሳብን በመድረስ ነባሩን ስርዓት ይሞግታሉ። አብዮትን በመለኰስ ታሪክን ይፅፋሉ። ሔግል የእነዚህ ሰዎች ወዳጅ ነው። ለሰው ዘር እድገት ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ማክበር ይገባናል" ይለናል
ለውጥን እንዴት እናስተናግድ ?! የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ወይንም ሌሎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሁኔታ የሚመለከተን ለውጥን እንዴት እናስተዳግድ ለሚለው ጥያቄ ዘመናትን የተሻገረ በሚሊየን ኮፒዎች ከ37 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመውን አይቤን ማን ወሰደው? (Who Moved My Cheese?) መጽሃፍ ዳሰሳ እነሆ ፡ አንብባችሁ እንድትጠቀሙበት እነሆ ብለናል፡፡ ለውጥ አይቀሬ ነው ፥ በየቀኑ ለምናያቸው ለውጦች ምላሻችን ምን ይሆን ? አድሜ ፤ የትምህርት ስርአት ፤ የስራ ሁኔታ ፤ ኮሪደር፤ የዋጋ ንረት ፤ ተላላፊ በሽታዎች። ይህን ጽሁፍ ሲያነቡ ለውጥ ስጋት ብቻ ሳይሆን አድልም አንዳለው ይረዳሉ። የመግቢያ "አይቤን ማን ወሰደው?" በዶ/ር ስፔንሰር ጆንሰን የተጻፈው ይህ ሥራ፣ ከቀላል ታሪክነት የዘለለ ዓለም አቀፍ የለውጥ አስተዳደር መመሪያ ነው። መጽሐፉ በ1998 ዓ.ም. ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ፣ ከ28 ሚሊዮን ኮፒ በላይ በመሸጥ በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ ተነባቢ የቢዝነስና የራስ-ዕርዳታ መጻሕፍት አንዱ ሆኗል። ታሪኩ እስከ 37 በሚደርሱ ቋንቋዎች የተተረጎመ ሲሆን፣ መልዕክቱ የዘመናችንን ሽክርክሪት መንገድ (Maze)—እጅግ ውስብስብ የሆነውን የጊዜውን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የቴክኖሎጂ ዓለም—ለሚመሩ ሰዎች፣ ግለሰቦች እና ኢትዮጵያውያን መሪዎችና ባለሙያዎች መሠረታዊ የሆነ መመሪያ ነው። አይቡ (Cheese) ስኬት፣ የሥራ ዕድል፣ የሀብት ምንጭ ወይም የኅሊና ሰላም ሲሆን፤ መጽሐፉ፣ አይቡ በተደጋጋሚ ሲነሳ ሰዎች በስነ-ልቦና ደረጃ ምን ምላሽ ይሰጣሉ የሚለውን በጥልቀት ይፈትሻል። ይህ ትንታኔ፣ አራቱ ገጸ-ባህሪያት በዘመናዊ የኢትዮጵያ የሥራና የንግድ ሕይወት ውስጥ እንዴት እንደሚንጸባረቁ እና ከዓለም አቀፍ ስኬታማ ተሞክሮዎች ጋር በማገናኘት ልንማርበት እንደምንችል ይዳስሳል።
የቤትህን ቁልፍ ለማንኛውም ሰው እንደማትሰጠው ሁሉ፣ ለልብህም ጠባቂ አቁምለት። ሁሉንም ሰው የቅርብ ጓደኛ ለማድረግ መሞከር፣ ራስን ለከባድ ስብራት አሳልፎ መስጠት ነው። ሰዎችን እንደየባህሪያቸው በደረጃ አስቀምጣቸው፤ አንዳንዱ ለሰላምታ፣ አንዳንዱ ለሥራ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ ለልብ ወዳጅነት።
ይህ ሰው ድሀ፣ ለማኝ ወይም ቤት አልባ አይደለም ይልቅስ በአለም ስነ-ጽሁፍ ገዝፎ የሚታየው ሊዮ ቶልስቶይ ነው። ቶልስቶይ በሩሲያ ውስጥ ሰፊ መሬት እና ትልቅ ሀብት የነበረው ቢሆንም፤ ሀብቱን ሁሉ ለድሆች፣ ለምስኪኖች፣ ለችግረኞች እና ለቤት ፈላጊዎች በመስጠት የራሱን ህይወት ባልተጋነነ መለኩ የኖረ ሰው ነው። ታዋቂ ከምንላቸው አባባሎችሁ መኃል፦ "ስለ ሀይማኖት ብዙ አትንገረኝ፣ ነገር ግን በድርጊትህ ውስጥ ሃይማኖትህን እንዳይህ ፍቀድልኝ።" “ህመም ከተሰማህ በህይወት አለህ፤ የሌሎችን ህመም ከተሰማህ ግን በውኑ አንተ ሰው ነህ”
ማንበብ ከፈለጋችሁ እዚህ ጋር አለ
ዴል ካርኒጌ ‹‹ጠብታ ማር›› ለምሳሌ ልጅህ ሲጋራ እንዳያጨስ ብትፈልግ ስለ ሲጋራ መጥፎነት አትስበክለት፡፡ ሆኖም ሲጋራ ማጨስ የአንድ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች እንዳይሆን ወይም በሩጫ ውድድር እንዲሸነፍ የሚያደርገው መሆኑን ንገረው፡፡ የሌላውን ፍላጎት የመጠበቅ ነገር ከማንኛውም ነገር ጋር ማለትም ከሕጻናት ወይም ከጥጃ ወይም ከዝንጀሮ ጋር በምናደርገው ግንኙነት ሁሉ ሊታሰብበት የሚገባ ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰንና ልጁ አንድ ቀን አንድ ጥጃ ወደ ጋጥ ለማስገባት ሞከሩ፡፡ ሆኖም አብዛኛው ሰው የሚፈፅመውን ስህተት ፈፀሙ፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን እንጂ ጥጃው የሚፈልገውን አላደረጉም፡፡ ኤመርሰን ከኋላ ወድሮ እምቢ አለ፡፡ ይህን ከንቱ ጥረቱ ታይ የነበረችው ሠራተኛ ጥጃው ምን እንደፈለገ ገባት፡፡ ጠጋ አለችና ጣቷን በዘዴ ለጥጃው አጎረሰችው፡፡ ጥጃው ጣቷን መጥባት ሲጀምር ቀስ ብላ ወደ ጋጡ እየተራመደች ይዛው ገባች፡፡ ሠራተኛው ምንም እንኳን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ ባይኖራትም በዚያች ወቅት ከኤመርሰን የበለጠ ማስተዋል ችላ ነበር፡፡ ከተወለድክ ጀምሮ ያደረግካቸውን ለምሳሌ ለቀይ መስቀል ማኅበር 100 ብር የሰጠህበት ጊዜ ቢኖር እንኳን ሌላውን ከመውደድ የመነጨ በጎ ሥራ ለመሥራት ስለፈለግህ ነው፡፡ ከመርዳት ፍላጎትህ ይልቅ የብር ፍላጎትህ ቢያይልብህ መቶ ብሩን ባልሰጠህ ነበር፡፡ እርግጥ አስተዋጽኦው እንድታደርግ የጠየቀህ ሰው እምቢ የማትለው ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ እውነት አለ፡፡ ብሩን የሰጠኸው ምናልባት ከሰውየው አንድ የፈለግከው ነገር ስለነበረ ነው፡፡ ዴል ካርኒጌ “ጠብታ ማር” (1989) ጠብታ ማር ለወዳጅዎ ይጋብዙ፡፡