tgindex

Bemnet Library

описание

📚ማንኛውንም አይነት መጻሕፍት እዚህ ያገኛሉ።ከ2014 ጀምሮ! እንደ እርስዎ ላሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቁጥር 1 ምርጫዎች ነበርን! Owner፦ @Bemni_Alex

94 726
подписчиков
Охват к подписчикам
16,5%
ERR
Реакции к просмотрам
0,79%
6 622 на 48 постов
Пересылки к просмотрам
0,29%
2 445
Постов в день
1,9
всего 49

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 14 авг.без подписи2,70%
  • 13 авг.በሰዎች ዘንድ ለመናቅ ትልቁ መንገድ ውሳኔ የማትሰጥ፣ የምትወላውልና በየጊዜው ሃሳብህን የምትቀይር አቋመ-ቢስ መሆን ነው። ሰዎች የሚንቁትን ሰው አይፈሩትም፤ አይታዘዙትምም። ድርጊቶችህ ሁሉ ጥንካሬን፣ ደፋርነትንና ቁርጠኝነትን የሚያሳዩ መሆን አለባቸው። ሰዎች በአንተ ውሳኔ ላይ መጫወት እንደማይችሉ ሲረዱ ላንተ ያላቸው አክብሮት ይጨምራል። 📕 ርዕስ:- ልዑሉ ✍️ ደራሲ:- ኒኮሎ ማኪያቬሊ 📚 @Bemnet_Library2,23%
  • 8 авг.በዓለም ላይ ሶስት አይነት የአእምሮ ደረጃ ያላቸው ሰዎች አሉ፡ የመጀመሪያዎቹ በራሳቸው አቅም ነገሮችን መረዳት የሚችሉ ጥበበኞች ናቸው፤ ሁለተኛዎቹ ሌሎች ሲያስረዷቸው መረዳት የሚችሉ ናቸው፤ ሶስተኛዎቹ ግን በራሳቸውም የማይረዱ በሌሎችም ሲነገራቸው የማይገባቸው ከንቱዎች ናቸው። ከጎንህ የምትሰበስባቸው ሰዎች የመጀመሪያዎቹና ሁለተኛዎቹ መሆናቸውን አረጋግጥ፤ ሶስተኛዎቹን አቅራቢያህ እንኳ አታድርጋቸው። 📕ርዕስ፦ልዑሉ ✍️ደራሲ፦ኒኮሎ ማኪያቬሊ 📚 @Bemnet_Library1,44%
  • 6 авг.ወንድ ልጅ ለራሱ የሚሆን ልብስ ሲገዛ የሚያስበው ስለ ዋጋው ነው፤ ሴት ልጅ ለራሷ ልብስ ስትገዛ ግን የምታስበው ስለ ሌላ ሴት አስተያየት ነው። 📕 ርዕስ:- የወንዶችና የሴቶች ስነልቦና ✍️ ደራሲ:- ሮን ቶማስ 📚 @Bemnet_Library1,41%
  • 3 авг.አንድ ሰው አንድን ፀባይ እንዲያዳብር ከፈለጋችሁ፣ ያ ፀባይ ቀድሞውኑ እንዳለው አድርጋችሁ ንገሩት። ሰዎች ጎበዝ፣ ታማኝ፣ ወይም ታታሪ ከተባሉ፣ ያንን ስማቸውን ላለማጥፋት ሲሉ የተባሉትን ለመሆን ይጥራሉ።ስለዚህ በሰዎች ውስጥ ያለውን መልካም ማንነት ቀስቅሳችሁ ማውጣት የምትችሉት፣ በመጥፎ ስም ከመጥራት ይልቅ መልካም ስም በመስጠት ነው። ለምሳሌ አንድ ሰራተኛችሁ ስራ ላይ ደካማ ቢሆን፣ "አንተ ደካማ ነህ" ብላችሁ ከመሳደብ ይልቅ፤ "ባለፈው የሰራኸው ስራ ጥራቱ በጣም ያስደንቅ ነበር፣ አሁንም ያንን ጎበዝ ሰራተኛ እንደማገኘው እርግጠኛ ነኝ" ብትሉት፣ ያንን ጎበዝ የተባለውን ስሙን ለመጠበቅ ሲል ስራውን በንቃት መስራት ይጀምራል። 📕ርዕስ፡- ወዳጅ የማፍራት ምስጢር ✍️ደራሲ፡- ዴል ካርኔጊ 📚 @Bemnet_Library1,39%
  • 10 авг.ምንም ያህል ጠንካራ ብትሆን፣ ራስህን የምትከላከልበት መሳሪያ ቢኖርህ እንኳን በህዝቡ ዘንድ ከተጠላህ ልትድን አትችልም። ትልቁና ጠንካራው ምሽግ በሰዎች ዘንድ አለመጠላት ነው። ሰዎች አንተን ከጠሉህና ከጠላቶችህ ጋር ከተባበሩ ያሰብከው ምንም አይነት መከላከያ ከውድቀት ሊታደግህ አይችልም። ስለዚህ አቅምህን ስትገነባ የሰዎችን ጥላቻ ከማተርፍ ተጠበቅ። 📕ርዕስ፦ልዑሉ ✍️ደራሲ፦ኒኮሎ ማኬቬሊ 📚 @Bemnet_Library1,31%
  • 4 авг.ማንም ሰው ትዕዛዝ እንዲሰጠው አይፈልግም። ይህንን አድርግ ወይም ያንን አታድርግ ከሚሉ ትዕዛዞች ይልቅ "ይህንን ብናደርገው ምን ይመስልሃል?" ወይም "ይህንን ለማስተካከል ምን ማድረግ እንችላለን?" የሚሉ ጥያቄዎች የተሻለ ውጤት ያመጣሉ።ምክንያቱም ጥያቄዎች ሰዎች በውሳኔው ውስጥ ተሳታፊ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ስለሚያደርግ፣ ስራውን በገዛ ፍቃዳቸውና በደስታ እንዲሰሩት ያነሳሳቸዋል። ለምሳሌ፦ ልጃችሁ ክፍሉን እንዲያጸዳ ከፈለጋችሁ "ክፍልህን አሁኑኑ አጽዳ!" ብላችሁ ከመጮህ ይልቅ፤ "ክፍልህ ስለቆሸሸና ለመጫወት ስለማያመች ብናፀዳው ምን ይመስልሃል?" ብላችሁ ብትጠይቁት፣ እሱ ራሱ መፍትሄ እንዲያመጣና ስራውን እንደ ትዕዛዝ ሳይሆን እንደ ኃላፊነት እንዲቀበለው ያደርገዋል። 📕ርዕስ፡- ወዳጅ የማፍራት ምስጢር ✍️ደራሲ፡- ዴል ካርኔጊ 📚 @Bemnet_Library1,29%
  • 20 сент. 2025 г.без подписи1,28%
  • 8 авг.በሰዎች ዘንድ መወደድ ጥሩ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን መከበርና መፈራት የበለጠ ዋስትና ይሰጥሃል። ሰዎች የሚወዱትን ሰው እንደ ሁኔታው በቀላሉ ሊከዱት ወይም ሊረሱት ይችላሉ፤ የሚያከብሩትንና የሚያስፈራቸውን ሰው ግን ለመካድ ሁለት ጊዜ ያስባሉ። ስለዚህ በደግነትህና በየዋህነትህ ብቻ ሰዎች እንዲጫወቱብህ አትፍቀድ፤ የራሳቸው ወሰን እንዳላቸው አሳያቸው። 📕ርዕስ፦ልዑሉ ✍️ደራሲ፦ኒኮሎ ማኪያቬሊ 📚 @Bemnet_Library1,24%
  • 15 нояб. 2024 г.без подписи1,20%
  • 12 авг.የሰው ልጅ አእምሮ ሊያስበው፣ ሊያልመው እና ሊያምነው የሚችለውን ማንኛውንም ነገር በተግባር ማሳካት ይችላል፤ዋናው ነገር ያንን ነገር ለማሳካት ያለው ፅኑ ፍላጎት ነው። 📕 ርዕስ፦ አስብና ሀብታም ሁን ✍️ ደራሲ፦ ናፖሊዮን ሂል 📚 @Bemnet_Library1,19%
  • 28 июл.የሰው ልጅ በተፈጥሮው ራስ ወዳድ ነው፤በዚህ ምክንያት የራሱን ጥቅም ለማስከበር ሲል አንተን እንደ መሰላል ሊጠቀምብህ ይችላል።አብዛኛዎቹ ሰዎች ይህን መራራ እውነታ ካለመረዳታቸው የተነሳ ሁልጊዜ በሰዎች ጥቅመኝነት እየተሰበሩ ይኖራሉ።በዚህ ጊዜ ዓለም የምታከብረው ጠቃሚ እቃን እንጂ መልካም ሰውን አይደለም።ስለዚህ የራስህን ጥቅም ለማስከበር የዋህነትህን ልክ እንደ ሰዎቹ ተፈጥሮ ተለዋዋጭ አድርገው።ይሄ ማለት ደግ መሆን ባለብህ ጊዜ ደግ ሁን፤መጥፎ መሆን ባለብህ ጊዜም መጥፎ ሁን! 📕 ርዕስ፦ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ህጎች ✍️ ደራሲ፦ ሮበርት ግሪን 📚 @Bemnet_Library1,06%