Bemnet Library
описание
📚ማንኛውንም አይነት መጻሕፍት እዚህ ያገኛሉ።ከ2014 ጀምሮ! እንደ እርስዎ ላሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ቁጥር 1 ምርጫዎች ነበርን! Owner፦ @Bemni_Alex
Лучшие посты
за три месяцаአንድ ወንድ ስለ ፍቅሩ ሺህ ቃላት ሊደረድር ይችላል፤ አንቺ ግን የምትመዝኚው በተግባሩ ብቻ ይሁን። እደውላለሁ ብሎ ካልደወለ፣ እመጣለሁ ብሎ ካልመጣ፣ እውነታው ያለው እዚያው ጋ ነው። ስራ በዝቶብኝ ነው ወይም ስልኬ ተበላሽቶ ነው የሚሉ ሰበቦችን አትቀበይ። አንድ ወንድ በእውነት አንቺን ከፈለገ ተራራ ገፍቶ እንኳ አንቺ ጋ ይደርሳል። ካልመጣ ምክንያት ስላለው ሳይሆን፣ ፍላጎት ስለሌለው መሆኑን ተረጂና ቦታሽን አስከብሪ። 📕 ርዕስ: አምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች ✍ ደራሲ: ጋሪ ቻፕማን 📚 @Bemnet_Library
አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ጥቅማጥቅሞችን ከመስጠቷ በፊት ለ90 ቀናት መጠበቅ አለባት። ይህ የጊዜ ገደብ ወንዱ ለአንቺ ያለው ፍላጎት ስሜታዊ ብቻ መሆኑን ወይም ደግሞ በእውነት አንቺን ለማግኘት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ለመለየት ይረዳል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ወንዱ ላንቺ የሚሰጠውን ትኩረት፣ የሚያደርገውን ጥረትና ትዕግስቱን በማየት እውነተኛ ማንነቱን መረዳት ትችያለሽ። መስፈርቱን የማያከብር ወንድ ጊዜሽን እንዲያባክን አትፍቀጂ። 📕 ርዕስ፦ እንደ ሴት ሁኚ፥ እንደ ወንድ አስቢ ✍️ ደራሲ፦ ስቲቭ ሃርቪ 📚 @Bemnet_Library
ጠላትህ በፍፁም ሊከዳህ አይችልም።የምትከዳው ምስጢርህን በሚያውቁት፤አብረውህ በሚበሉትና ከልብህ በምታምናቸው የቅርብ ሰዎችህ ነው።ዛሬ የምታምነው ጓደኛህ ነገ ጥቅሙ ሲነካ ቀዳሚው ከሃዲህ ሊሆን እንደሚችል አትጠራጠር። ስለዚህ ማንም ሰው ላይ መቶ በመቶ መደገፍ እና ሚስጥርህን ማካፈል የለብህም።የሰውን ልጅ ተለዋዋጭ ተፈጥሮ በመረዳት፣ አንድ ቀን ጀርባቸውን ሊሰጡህ እንደሚችሉ አውቀህ ሁልጊዜም ራስህን ጠብቅ። 📕 ርዕስ:- 48ቱ የሀይል ህጎች ✍️ ደራሲ:- ሮበርት ግሪን 📚 @Bemnet_Library
без подписи
- 24 июл.36,7 тыс просмотров
ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ በጣም ተወዳጅ የሆኑ 3 መጽሐፎች 📕ርዕስ:- ብርቅርቅታ ✍️ደራሲ:- ዳኒኤላ ስቲል 📚 @Bemnet_Library
ወንድ ልጅ ድክመቱን፣ ፍርሃቱንና እንባውን የሚያሳይሽ ከሆነ፣ ይህ ማለት ደካማ ነው ማለት ሳይሆን ከአንቺ በላይ የሚያምነው ሰው የለም ማለት ነው። አንድ ወንድ ለሴት ልጅ ልቡን፤ጥንካሬውንና ድክመቱን ሲከፍት ሙሉ እምነቱንና ሕይወቱን ለአንቺ አሳልፎ እየሰጠ ነው።በዚህን ጊዜ አንቺ ማድረግ ያለብሽ ሚስጥሩን እንደ ጦር መጠቀም ሳይሆን፣ እንደ ውድ ሀብት ጠብቅሽ አስፈላጊ እንደሆነ፤እንደምትተማመኚበት እና ጀግናሽ እንደሆነ እንዲሰማው ማድረግ ነው። 📕 ርዕስ: አምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች ✍ ደራሲ: ጋሪ ቻፕማን 📚 @Bemnet_Library
ወንድ ልጅ አንድን ነገር እንዲያደርግልሽ ስትጠይቂው እንደ ግዴታ ሳይሆን እንደ ፍላጎት እንዲቆጥረው አድርጊ። ወንዶች የሚወዱትን ሰው ደስተኛ ለማድረግ ትልቅ ተነሳሽነት አላቸው። ነገር ግን ነገሩ እንደ ትዕዛዝ ወይም እንደ ግዴታ ሲቀርብላቸው ይሸሻሉ። ይሄን ብታደርግልኝ በጣም ደስ ይለኛል የሚለው ቃል፣ ይሄን ማድረግ ነበረብህ ከሚለው ቃል በሺህ እጥፍ ይበልጣል። 📕 ርዕስ: አምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች ✍ ደራሲ: ጋሪ ቻፕማን 📚 @Bemnet_Library
አንድ ሰው በሰዎች ፊት ያንተን ደካማ ጎን ወይም የድሮ ስህተትህን አንስቶ የሚያላግጥብህና እየቀለድኩ ነው የሚልህ ከሆነ፣ አላማው መሳቅ ሳይሆን የሰዎችን አመለካከት በአንተ ላይ ማበላሸት ነው። እንዲህ አይነት ሰዎች አንተን በማሸማቀቅ እነሱ የበላይነት እንዲሰማቸው ይፈልጋሉ። ይህ የስነ-ልቦና ጨዋታ አንተን ዝቅ አድርጎ ራሳቸውን ከፍ ለማድረግ የሚጠቀሙበት መርዛማ ስልት ነው። 📕 ርዕስ፦ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ህጎች ✍️ ደራሲ፦ ሮበርት ግሪን 📚 @Bemnet_Library
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ራስ ወዳድ ነው፤በዚህ ምክንያት የራሱን ጥቅም ለማስከበር ሲል አንተን እንደ መሰላል ሊጠቀምብህ ይችላል።አብዛኛዎቹ ሰዎች ይህን መራራ እውነታ ካለመረዳታቸው የተነሳ ሁልጊዜ በሰዎች ጥቅመኝነት እየተሰበሩ ይኖራሉ።በዚህ ጊዜ ዓለም የምታከብረው ጠቃሚ እቃን እንጂ መልካም ሰውን አይደለም።ስለዚህ የራስህን ጥቅም ለማስከበር የዋህነትህን ልክ እንደ ሰዎቹ ተፈጥሮ ተለዋዋጭ አድርገው።ይሄ ማለት ደግ መሆን ባለብህ ጊዜ ደግ ሁን፤መጥፎ መሆን ባለብህ ጊዜም መጥፎ ሁን! 📕 ርዕስ፦ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ህጎች ✍️ ደራሲ፦ ሮበርት ግሪን 📚 @Bemnet_Library
መርዛማ ሰዎችን የምትለይባቸው 3 ምልክቶች 1,ሁልጊዜ ራሳቸውን እንደ ተበዳይ ያቀርባሉ። ጥፋት አጥፍተው እንኳ አንተን ጥፋተኛ አድርገው በመውቀስ አንተ ይቅርታ እንድትጠይቃቸው ያደርጉሃል። በነሱ ህይወት ውስጥ ሁሌም ተጠያቂው ሌላ ሰው ነው። 2,ሚስጥርህን ለሌላ ጊዜ ይጠቀሙበታል። በቅርብ ጓደኝነት ወቅት የነገርካቸውን ድክመት ወይም ሚስጥር፣ በመካከላችሁ አለመግባባት ሲፈጠር አንተን ለማጥቃት ወይም ዝቅ ለማድረግ እንደ መሳሪያ ይጠቀሙበታል። 3,የሌላውን ስም ያጠፋሉ። ካንተ ጋር ሆነው የሌላውን ሰው ስም ያለማቋረጥ የሚያጠፉና መጥፎ የሚያወሩ ከሆነ፣ ከሌላ ሰው ጋር ሲሆኑም የአንተን ስም እንደሚያጠፉ ጥራጣሬ አይኑርህ። 📚 @Bemnet_Library
አንድ ሰው አንድን ፀባይ እንዲያዳብር ከፈለጋችሁ፣ ያ ፀባይ ቀድሞውኑ እንዳለው አድርጋችሁ ንገሩት። ሰዎች ጎበዝ፣ ታማኝ፣ ወይም ታታሪ ከተባሉ፣ ያንን ስማቸውን ላለማጥፋት ሲሉ የተባሉትን ለመሆን ይጥራሉ።ስለዚህ በሰዎች ውስጥ ያለውን መልካም ማንነት ቀስቅሳችሁ ማውጣት የምትችሉት፣ በመጥፎ ስም ከመጥራት ይልቅ መልካም ስም በመስጠት ነው። ለምሳሌ አንድ ሰራተኛችሁ ስራ ላይ ደካማ ቢሆን፣ "አንተ ደካማ ነህ" ብላችሁ ከመሳደብ ይልቅ፤ "ባለፈው የሰራኸው ስራ ጥራቱ በጣም ያስደንቅ ነበር፣ አሁንም ያንን ጎበዝ ሰራተኛ እንደማገኘው እርግጠኛ ነኝ" ብትሉት፣ ያንን ጎበዝ የተባለውን ስሙን ለመጠበቅ ሲል ስራውን በንቃት መስራት ይጀምራል። 📕ርዕስ፡- ወዳጅ የማፍራት ምስጢር ✍️ደራሲ፡- ዴል ካርኔጊ 📚 @Bemnet_Library
ማንም ሰው ትዕዛዝ እንዲሰጠው አይፈልግም። ይህንን አድርግ ወይም ያንን አታድርግ ከሚሉ ትዕዛዞች ይልቅ "ይህንን ብናደርገው ምን ይመስልሃል?" ወይም "ይህንን ለማስተካከል ምን ማድረግ እንችላለን?" የሚሉ ጥያቄዎች የተሻለ ውጤት ያመጣሉ።ምክንያቱም ጥያቄዎች ሰዎች በውሳኔው ውስጥ ተሳታፊ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ስለሚያደርግ፣ ስራውን በገዛ ፍቃዳቸውና በደስታ እንዲሰሩት ያነሳሳቸዋል። ለምሳሌ፦ ልጃችሁ ክፍሉን እንዲያጸዳ ከፈለጋችሁ "ክፍልህን አሁኑኑ አጽዳ!" ብላችሁ ከመጮህ ይልቅ፤ "ክፍልህ ስለቆሸሸና ለመጫወት ስለማያመች ብናፀዳው ምን ይመስልሃል?" ብላችሁ ብትጠይቁት፣ እሱ ራሱ መፍትሄ እንዲያመጣና ስራውን እንደ ትዕዛዝ ሳይሆን እንደ ኃላፊነት እንዲቀበለው ያደርገዋል። 📕ርዕስ፡- ወዳጅ የማፍራት ምስጢር ✍️ደራሲ፡- ዴል ካርኔጊ 📚 @Bemnet_Library
ወንድ ልጅ ለራሱ የሚሆን ልብስ ሲገዛ የሚያስበው ስለ ዋጋው ነው፤ ሴት ልጅ ለራሷ ልብስ ስትገዛ ግን የምታስበው ስለ ሌላ ሴት አስተያየት ነው። 📕 ርዕስ:- የወንዶችና የሴቶች ስነልቦና ✍️ ደራሲ:- ሮን ቶማስ 📚 @Bemnet_Library
በሰዎች ዘንድ መወደድ ጥሩ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን መከበርና መፈራት የበለጠ ዋስትና ይሰጥሃል። ሰዎች የሚወዱትን ሰው እንደ ሁኔታው በቀላሉ ሊከዱት ወይም ሊረሱት ይችላሉ፤ የሚያከብሩትንና የሚያስፈራቸውን ሰው ግን ለመካድ ሁለት ጊዜ ያስባሉ። ስለዚህ በደግነትህና በየዋህነትህ ብቻ ሰዎች እንዲጫወቱብህ አትፍቀድ፤ የራሳቸው ወሰን እንዳላቸው አሳያቸው። 📕ርዕስ፦ልዑሉ ✍️ደራሲ፦ኒኮሎ ማኪያቬሊ 📚 @Bemnet_Library
በዓለም ላይ ሶስት አይነት የአእምሮ ደረጃ ያላቸው ሰዎች አሉ፡ የመጀመሪያዎቹ በራሳቸው አቅም ነገሮችን መረዳት የሚችሉ ጥበበኞች ናቸው፤ ሁለተኛዎቹ ሌሎች ሲያስረዷቸው መረዳት የሚችሉ ናቸው፤ ሶስተኛዎቹ ግን በራሳቸውም የማይረዱ በሌሎችም ሲነገራቸው የማይገባቸው ከንቱዎች ናቸው። ከጎንህ የምትሰበስባቸው ሰዎች የመጀመሪያዎቹና ሁለተኛዎቹ መሆናቸውን አረጋግጥ፤ ሶስተኛዎቹን አቅራቢያህ እንኳ አታድርጋቸው። 📕ርዕስ፦ልዑሉ ✍️ደራሲ፦ኒኮሎ ማኪያቬሊ 📚 @Bemnet_Library
አብዛኛዎቻችሁ ስታወሩ የምታተኩሩት እናንተ ስለምትፈልጉት ነገር ብቻ ነው። ነገር ግን ሰዎችን ማሳመን የምትችሉት የእነሱን ፍላጎት ቀድማችሁ ስታውቁና የእናንተ ሃሳብ ለእነሱ የሚሰጠውን ጥቅም ስታሳዩ ነው።ይሄ ማለት የሰዎችን ልብ ለመክፈት ትልቁ መንገድ ሰውየው በጣም ስለሚወደውና ስለሚሳሳለት ነገር ማውራት ነው። ለምሳሌ ከአለቃችሁ ጋር ስለ ደሞዝ ጭማሪ ማውራት ከፈለጋችሁ፣ "እኔ ገንዘብ ያስፈልገኛል" በሚል የግል ፍላጎት ከመጀመር ይልቅ፤ ባለፈው አመት ለድርጅቱ ያመጣችሁትን ውጤትና ወደፊትም ድርጅቱን ይበልጥ እንዴት ማገዝ እንደምትችሉ አውሩ። ድርጅቱ የሚፈልገውን ነገር እንደምታውቁና ለእሱም እንደምትቆረቆር ሲረዱ፣የእናንተን ጥያቄ ለመቀበል ዝግጁ ይሆናሉ። 📕 ርዕስ፦ ወዳጅ የማፍራት ምስጢር ✍ ደራሲ፦ ዴል ካርኔጊ 📚 @Bemnet_Library
ምንም ያህል ጠንካራ ብትሆን፣ ራስህን የምትከላከልበት መሳሪያ ቢኖርህ እንኳን በህዝቡ ዘንድ ከተጠላህ ልትድን አትችልም። ትልቁና ጠንካራው ምሽግ በሰዎች ዘንድ አለመጠላት ነው። ሰዎች አንተን ከጠሉህና ከጠላቶችህ ጋር ከተባበሩ ያሰብከው ምንም አይነት መከላከያ ከውድቀት ሊታደግህ አይችልም። ስለዚህ አቅምህን ስትገነባ የሰዎችን ጥላቻ ከማተርፍ ተጠበቅ። 📕ርዕስ፦ልዑሉ ✍️ደራሲ፦ኒኮሎ ማኬቬሊ 📚 @Bemnet_Library
አሰቃቂው መጽሐፍ! ከ500 ዓመት በፊት ይሄ መጽሐፍ እንዲቃጠል እና እንዲታገድ የሃይማኖት አባቶች ፈርደውበት ነበር! መፍረድ ብቻ ሳይሆን ይሄንን መጽሐፍ ያነበበ ማንኛውም ሰው እንዲገደል ትዕዛዝ ተስጥቶ ነበር ነገር ግን በአንድ ሰው ምክንያት አፈትልኮ በመውጣቱ ብዙ ሺ ሰዎች በአንድ ጊዜ አንብበውታል።በምስጢር የተለያዩ ቦታዎችና ሃገሮች ላይ ተዳርሷል።ዛሬም ድረስ አንዳንዶች ጭካኔ የተሞላበት መጽሐፍ ነው ይሉታል።አብዛኛዎቹ ደግሞ የሰውን ልጅ ባህሪ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አስደናቂ መጽሐፍ ነው ይሉታል።ብቻ አሁን ላይ ሚሊየን ኮፒ ተሸጧል።ዋሽግተን ፖስት ላይ በየሳምንቱ ከሚነበቡ መጽሐፎች ዝርዝር ውስጥ በ1ኛ ደረጃ ተቀምጧል 📕ርዕስ፦ልዑሉ ✍️ደራሲ፦ኒኮሎ ማኬቬሊ 📚 @Bemnet_Library
የምስራች በአዳማ ለምትገኙ አሽከርካሪዎች፣ Yango በአዳማ ስራውን ጀምሯል! 💛🎉 ተጨማሪ ገቢ እንዲያግኙ Yango መጣልዎ ! አሁን መኪናዎን እና ባጃጅዎን በመጠቀም ገንዘብ ይስሩ ፣ 🚕💰 🎁 በቦነስ ብቻ በየቀኑ እስከ 1,170 ብር ያግኙ! 🔥 የYango አሽከርካሪ ይሁኑ፣ ገቢዎን ያሳደጉ! 📱Yango Pro App ን አሁኑኑ ያውርዱና ይመዝገቡ! ሊንኩን ይጫኑ ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://ya.cc/t/3nVOkmT99fvrCa
የሰው ልጅ አእምሮ ሊያስበው፣ ሊያልመው እና ሊያምነው የሚችለውን ማንኛውንም ነገር በተግባር ማሳካት ይችላል፤ዋናው ነገር ያንን ነገር ለማሳካት ያለው ፅኑ ፍላጎት ነው። 📕 ርዕስ፦ አስብና ሀብታም ሁን ✍️ ደራሲ፦ ናፖሊዮን ሂል 📚 @Bemnet_Library