tgindex

Bonga University

описание

Bonga University is one of the Public Higher Educational Institution in Ethiopia. call +251474524523 https://t.me/BongaUniversityCommunication

10 991
подписчиков
Охват к подписчикам
15,6%
ERR
Реакции к просмотрам
0,08%
34 на 27 постов
Пересылки к просмотрам
0,05%
21
Постов в день
3,6
всего 27

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 20:56እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ! የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ኤፍ ኤም 92.1 ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የባህል እና ሳይንስ ተቋም /ዩኔስኮ/ያወጣውን Expression Of Interest /EOI/ For Community Radio Partnership የፕሮግራም ይዘት ውድድር ማሸነፍ ችለናል። በመሆኑም በቀጣይ በወጣቶች ፣ በሴቶች እንዲሁም በጤና ላይ መስራት የሚያስችለንን መርሀ-ግብር የምናጠናክርበትን አቅም ይፈጥርልናል። በመሆኑም ለፕሮግራም አዘጋጅ ፣ አቅራቢ እና የሬድዮ ዝግጅት አስተባባሪ የመሳሰሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በቀጣይ የምናገኝ ይሆናል። ከዚህም ባሻገር የበለጠ ፕሮግራሞቻችን ጥራት እና ይዘት ጨምረው መጓዝ የሚያስችል አቅምም ይፈጥርልናል። ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሁሌም የተሰጠውን የመንግስት ተልዕኮ ከማሳካት ባሻገር የህብረተሰባችንን ሁለንተናዊ ችግሮችን በጥናት እና ምርምር ለመፍታት እየሰራ ያለ የመንግስት ከፍተኛ የት/ት ተቋም ነው። በድጋሚ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ! በጋራ እንችላለን!2,40%
  • 12 авг.የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ-ግብር የሁለተኛው ክፍል እና የማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄደ። ::::::::::::::ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም:::::::::::::: ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ-ግብር ከሐምሌ 4/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ተግባራት ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል። በዛሬው የመጨረሻ ቀን መርሀ-ግብር የአንዲት በጥልቅ ድህነት ውስጥ ያለች ሴት የስምንት ልጆች እናት በቦንጋ ከተማ ልዩ ስሙ በሚሽን ሰፈር አካባቢ የቤት እድሳት መርሀ-ግብር በማስጀመር ነበር። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) በመርሀ -ግብሩ ማስጀመሪያ ወቅት መልዕክት አስተላልፈዋል። ክቡር ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት አንዱ እንደነዚህ አይነት የማህበረሰብ አገልግሎት እና ሰብዓዊ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ ቤት የምናድስላት ሴት ደግሞ እጅግ በጣም ችግረኛ በመሆኗ እኛም የአቅማችንን በማድረግ ሀገራዊ ሀላፊነታችንን ለመወጣት ያስችለናል ብለዋል በዚህም ደስተኞች ነን ብለዋል። በክቡር ፕሬዝዳንቱ መሪነትም የቤት እድሳቱ የግንባታውን ሂደት በይፋ በማስጀመር ወደ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አረጋውያን ማዕከል ችግኝ ተከላ ፕሮግራም መካሄድ ችሏል። በአረጋውያን ማዕከል በተከናወነው ፕሮግራም የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አልማዝ ሀ/ወልድ የማዕከሉን የስራ እንቅስቃሴ የሚገልጽ አጭር ሪፖርት አቅርበዋል። በመጨረሻም የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ-ግብር ማጠቃለያ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ቀርቧል። በመልዕክታቸውም ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስ/ር ሰራተኞችን ለማዕከሉ ለሚያደርጉት ድጋፍ አመስግነው እንደዚህ አይነት ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ለማዕከሉ አረጋውያን ረጅምን ዕድሜ ተመኝተዋል። ክቡር ፕሬዝዳንቱ የተለያዩ የመንግስት መዋቅሮችን ያመሠገኑ ሲሆን በማጠቃለያው ለአረጋውያኑ ድጋፍ የአልባሳት ፣ የገንዘብ እና የቴምር ድጋፍ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የተላኩትን ስጦታዎች ለአረጋውያኑ በማበርከት የፕሮግራም ፍፃሜ ሆኗል። በጋራ እንችላለን!0,90%
  • 13 авг.ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለቦንጋ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወጣቶች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። :::::::::::::: ነሀሴ 07/2018 ዓ.ም:::::::::::::::: ስልጠናው በህይወት ክህሎት ፣ ውጤታማ አመራርነት እና የአደዛዥ ዕፅ ተጠቂነት የሚሉ ርዕሶች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል። መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መማ/ማስ/ምር/ቴክ/ማህ/አገ/ት ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ልዩ ረዳት መ/ር ጌትነት ገ/ሚካኤል የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ከፍተዋል። መ/ር ጌትነት በመልዕክታቸው እንደገለፁት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮው የክረምት በጎ ተግባራት ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት በዝርዝር ገልፀዋል። የዛሬውም ስልጠና በተለይ ወጣቶችን መሠረት ባደረገ መልኩ ሲያዘጋጅ በምክንያት መሆኑን አውስተዋል። ተሳታፊ ወጣቶችም ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ተገቢውን ክህሎት እንድትጨብጡ በማለት ስልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል። ስልጠናውን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መ/ራን የሆኑት ጌትነት ገዛኸኝ (ዶ/ር) እና መ/ር ፍሬው አስረስ በተለያዩ ርዕሶች ላይ እንደሚሰጡ ከወጣው መርሀ-ግብር መረዳት ይቻላል። ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል። በጋራ እንችላለን!0,67%
  • 20:56без подписи0,00%
  • 20:56без подписи0,00%
  • 20:56без подписи0,00%
  • 13 авг.без подписи0,00%
  • 13 авг.без подписи0,00%
  • 13 авг.без подписи0,00%
  • 13 авг.без подписи0,00%
  • 13 авг.без подписи0,00%
  • 13 авг.без подписи0,00%