ኡስታዝ አክመል ኑራቶ ሙሳ (Ustaz Akmel Nurato Mosa) قناة أستاذ أكمل بن نوراتو بن موسى
Статистикаይህ በኡስታዝ አክመል ኑራቶ ሙሳ የሚሰጡ ደርሶች፣ ሙሃደራዎች እንዲሁም ጠቃሚ መልዕክቶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው። የቴሌግራም ቻናሉን ሊንክ በመንካት ቤተሰብ ይሁኑ t.me/DaruNurChannel 🌐قناة تهتم بنشر دروس ومحاضرات وفوائد الأخ أكمل نوراتو موسى سدده الله ጥያቄና አስተያየት ካልዎት በዚህ ማስፈንጠርያ ይላኩ @malekitmeqebya333
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 153
- 1/48двое суток
- 175
- 1/72трое суток
- 189
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
የማለዳ መልእክት (43) ~ ለዒልም እንቅፋት ከሚሆኑ ሰበቦች ውስጥ አንዱ ቀሪ ማብዛት ነው። ተደጋጋሚ ቀሪ፦ * የዒልምን ጣእም ያሳጣል። * ባለፈን ትምህርት እንዳንቆጭ ይልቁንም መቅረትን እንድንላመድ /'ኖርማል' አድርገን እንድንወስድ/ ያደርጋል። * ከነ ጭራሹ ከዒልም ሰፈር የመራቅን በር ይከፍታል። ስለዚህ ስንፍናችን ጋር ጊዜያዊ እንኳን ቢሆን ወዳጅነት ከመመስረት እንጠንቀቅ። ልማድ ይሆናል። በጊዜ ድክመታችንን እናስተካክል። ዒልምን በመከታተል ላይ ቆራጥ እንሁን። ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ፈፅሞ ከዒልም ማእዶች ያለን ተሳትፎ አይቆራረጥ። ዛሬ ቆራጥ ከሆንን የየቀኑ የተጠራቀመች ዒልም በዓመቱ መጨረሻ ትልቅ ክምችት ይወጣታል። ጠብታ ተጠራቅሞ ብዙ ያቁራል። ጠብታ ውሃ ድንጋይ ይበሳል። ፅናት ኖሮን ጥረታችን ዓመታትን ከተሻገረ በርግጠኝነት በአላህ ፈቃድ ጉልህ ለውጥ ይኖረናል። በዚህ አብዛኛው ሰው - አስተማሪውን ጨምሮ - በስሜት፣ በቡድንተኝነት፣ በአስመሳይነት፣ በእልህ፣ በቢድዐ፣ በሞራል ዝቅጠት፣ ... በተለከፈበት ዘመን ከአላህ ጋር እንደ ዒልም ያለ ዋስትና የለም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 26 /1448)
https://youtu.be/KiOZWO5r-SU?si=Pc5H6zGmwiflqrIT
የዛሬው ኹጥባ ርዕስ ኢንሻ አላህ الثقة بالله وحسن التوكل عليه በአላህ መተማመን እና በእርሱ ላይ መልካም መመካት መመካትን በተመለከተ ይሆናል
ግጥም
አንድ ቀን ይመጣል ወደ እናትህ አልጋ ትመለከታለህ እሷን ግን አታገኛትም እንዲሁም አንድ ቀን የአባትህን ድምፅ ትፈልገዋለህ ነገር ግን አትሰማውም ስለዚህ ዛሬ ጭንቅላታቸውን ሳሙ ነገ የመቃብራቸውን አፈር ከመሳም በፊት በሕይወት ሳሉ ይቅርታቸውንና ደስታቸውን ፈልጉ የወላጆች መልካም ማድረግያ በር ለዘላለም ሳይዘጋባችሁ በፊት እባካችሁ ወላጆቻችሁን አስደስቷቸው አባትና እናቱ በሕይወት ያሉለት ሰው ታላቅ ሀብት እንዳለው ይወቅ ምክንያቱም እነርሱ ከጀነት በሮች ሁለቱ ናቸው ነቢዩ ﷺ ስለ እናት እንዲህ ብለዋል ከእግሯ አትለይ ጀነት በዚያ አለ እንዲሁም እንዲህ ብለዋል አባት ከጀነት በሮች መካከል መካከለኛው (ታላቁ) በር ነው የአላህ ውዴታ በወላጆች ውዴታ ውስጥ ነው የአላህም ቁጣ በወላጆች ቁጣ ውስጥ ነው
"ስለ ትዕግሥት ሺህ ኹጥባዎችን ኹጥባ በደርግልህ ነገር ግን ትዕግሥትን የሚያስተምሩ ሁኔታዎችን አልፈህ ካላወቅህ ትዕግሥት ምን እንደሆነ ሊገባህ አይችልም
ጥቆማ ትናንት የፈተና ውጤት ከተነገረ በኋላ የቁርኣን ፈተና ያላለፉ በርካታ ልጆች እና ወላጆች ቅስማቸው ተሰብሮና ተክዘው ተመልክቻለሁ። ለዚህ መፍትሔ ይሆን ዘንድ እኔ የማውቀውን መድረሳ ላመላክታችሁ ኦርቢት በሚገኘው ኹለፋኡ አር-ራሺዲን መድረሳ ገንደ ተስፋ ኡስታዝ ጠይብ ጋ መስቀለኛ ኢቅረእ መስጂድ ኡስታዝ አብዱረዛቅ ነምበር ዋን ኢቅረእ መስጂድ ጎራ በሉ ምዝገባ ካልጨረሱ ልጆቻችሁ በጥሩ ሁኔታ እዚያ ይያዙላችኋል ኢንሻ አላህ።
ለሂፍዝ ከተፈተኑ 61 ሴት ተማሪዎች መካከል ፈተና ያለፉ ተማሪዎች ስም ዝርዝር
ለሂፍዝ ከተፈተኑ 76 ወንድ ተማሪዎች መካከል ፈተና ያለፉ ተማሪዎች ስም ዝርዝር
"ሰሞኑን ለተከታታይ ቀናት የነዘር እና የሂፍዝ ፈተና መኖሩ የሚታወስ ነው። በመሆኑም ኢንሻአላህ ለሂፍዝ ያለፉ ተማሪዎች (የወንዶችም የሴቶችም) ስም ዝርዝር ከዐስር በኋላ ይለቀቃል።
አምስት መቶ ደረሰ 📢 አስደሳችና ወቅታዊ መረጃ ከመርከዝ አስ-ሱና (አሸዋ ቢላል መስጂድ - ድሬደዋ) አልሀምዱሊላህ! በአሁኑ ሰዓት የመርከዛችን የቁርኣንና የኪታብ ተማሪዎች ቁጥር 500 የደረሰ ሲሆን በ14 ኡስታዞች አማካኝነት የእውቀት ብርሃን እየተቀሰመ ይገኛል። ይህንን ትልቅ የምስራች ስናበስር ትናንትን ወደኋላ መለስ ብለን ማስታወሱ ተገቢ ነው። ከዚህ ቀደም በተለይ በአሸዋና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ልጆቻችን የቁርኣን እይታ (ነዘር) እና የሂፍዝ ትምህርት ለማግኘት፣ ስለ ዲናቸው መሰረታዊ እውቀትን ለመጨበጥ ምን ያህል ይንከራተቱና ይቸገሩ እንደነበር የቅርብ ትዝታችን ነው። ዛሬ ግን አላህ በችሮታው ይህንን የዒልም ማዕከል ሰጠን። ነገር ግን ይህንን ያህል ቁጥር ያለው ተማሪ ይዞ እያንዳንዱን በየደረጃውና እንደ አቅሙ እውቀት እንዲጨብጥ ማድረግ ምን ያህል አድካሚና ከባድ እንደሆነ የመርከዙ የቦርድ አባላትና በቅርብ ያሉ ወንድሞች ምስክሮች ናቸው በተለይም ደግሞ ለመርከዙ ቋሚ የገቢ ምንጭ አለመኖሩና ስራው ሰፊ መሆኑ አቅማችንን በእጅጉ እየተፈታተነው ይገኛል። መርከዛችን ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርስ አሁን ያለንበት ደረጃ ብቻውን በቂ አይደለም። ይህ የሁላችንም ቤት ነው፤ ሁላችንም ልንጠብቀው ልንቆረቁርለትና ልናግዘው የሚገባ የጋራ ሀብታችን ነው። ይህ ማዕከል እዚህ እንዲደርስ የድሬደዋ ማህበረሰብ ያደረገው አስተዋፅኦ ታሪካዊ ነው በተለይም ንቁ የሆነው ወጣቱ ክፍል የደርዘን ተራ የሲጋራ ተራ የሰልባጅ ተራ የታይዋን ነጋዴዎችና መላው የድሬደዋ ህዝብ ላደረጋችሁት መልካም ድጋፍ ምስጋናችን ከልብ ነው። በመጨረሻም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ሲሉ ቀንና ማታ ምንም ነገራቸው ሳይሳሱ በውድ ወድማችን አብዱሰላም ሰብሳብነት ለሚለፉት ውድ የቦርድ አባላት እንዲሁም በዙሪያቸው ሆናችሁ ለምትደግፉ በሙሉ አላህ በጤናችሁ በዕድሜያችሁና በገንዘባችሁ ላይ በረከቱን ያፍስስባችሁ በቀጣይም ይህንን የዒልም ፋኖስ ይበልጥ ለማንደድ ጠንካራና የማይቋረጥ ድጋፋችሁ እንደማይለየን ሙሉ እምነት አለን። ጀዛኩሙላሁ ኸይረን!
የዛሬው ጁምዓ ኹጥባ ርዕስ خطبة الجمعة علاج المخاوف والأحزان የልብ ፍርሃትና ሐዘን መፍቴዎቹ
وقد قيل قديما نصف السلامة في التغاضي عن الناس ونصف الأدب في عدم التدخل فيما لا يعنيك ونصف الحكمة في الصمت የሰላም ግማሹ ሰውን ከመከታተል መቆጠብ ነው የአደብ ግማሹ በማያገባህ አለመግባት ሲሆን የጥበብ ግማሹ ዝምታ ነው
ማሳሰቢያ ለወላጆች መርከዝ አስ-ሱና (አሸዋ ቢላል መስጂድ) መርከዛችን በየዓመቱ አዳዲስ ተማሪዎችን በነዘርና በሂፍዝ (በሁለቱም ጾታዎች) ተቀብሎ እንደሚያስተምር ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት የምዝገባ ማስታወቂያ ሳይወጣና ትክክለኛው ጊዜ ሳይደርስ ልጆቻቸውን ለማስመዝገብ በአካልና በስልክ የሚወተውቱ ወላጆች በብዛት እየጠየቁ ይገኛሉ (ዛሬ ብቻ ከ5 በላይ ጥያቄዎችን አስተናግጃለሁ) ስለሆነም ይህ የሰኔ ወር አልቆ በሐምሌ ወር ውስጥ በማስታወቂያ እስከሚነገር ድረስ ወላጆች በትዕግሥት እንድትጠባበቁ ባረከሏሁ ፊኩም። ልጆቻችሁ የመግቢያ ፈተናውን አልፈው መስፈርቱን ካሟሉ በመርከዙ እንደ አቅሙ የሚስተናገዱ ይሆናል ኢንሻ አላህ።
«የጀማዓ ሰላት ስያመልጠን የማይሰማን የልብ ሞት» قال حاتم الأصم رحمه الله تعالى مصيبة الدين أعظم من مصيبة الدنيا ولقد ماتت لي بنت فعزاني أكثر من عشرة آلاف، وفاتتني صلاة الجماعة فلم يعزني أحد مفتاح التأهب لدار القرار: ( 30 ) 📜 ትርጉም፦ ታላቁ ዓሊም ሐቲም አል-አሰም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ በዲን (በመንፈሳዊ ሕይወት) ላይ የሚደርስ መከራ በዱንያ (በምድራዊ ሕይወት) ላይ ከሚደርስ መከራ እጅግ የላቀና የከበደ ነው ይኸውላችሁ አንዲት ሴት ልጄ በሞተች ጊዜ ከዐስር ሺህ በላይ ሰዎች መጥተው አጽናኑኝ ነገር ግን አንዲት የጀማዓ ሰላት አምልጦኝ በነበረበት ወቅት አንድም ሰው መጥቶ ያጽናናኝ ወይም ሐዘን የገለጸልኝ አልነበረም።" ልብ የሚነካ ማጠቃለያ ይህ ንግግር በጀማዓ ሰላት ላይ ሊኖረን የሚገባውን ንቃትና ጥንቃቄ በብርቱ ያስታውሰናል የቅርብ ሰው በሞት ሲለይ በምድራዊ ሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ስብራት ሆኖ ይታየናል፤ ሰዎችም በዙሪያችን ከበው ያጽናኑናል ነገር ግን ከዚያ በላይ ትልቅ ዋጋና ምንዳ ያላት የጀማዓ ሰላት ስታመልጠን በነፍሳችን ላይ ምን ያህል ታላቅ መከራና ኪሳራ እየደረሰባት እንደሆነ ልብ አንለውም።
ማሰብያን የሚቆጣጠር ቲላዋ
https://youtu.be/eBtghQQwTnw?si=ir1fSSJwwv0FKyxN
قَالَ يَحْيَى بْنُ مُعَاذٍ دَوَاءُ القَلْبِ خَمْسَةُ أشْيَاءَ قِرَاءَةُ القُرْآنِ بِالتَّفَكُّرِ وَخَلَاءُ البَطْنِ وَقِيَامُ اللَّيْلِ وَالتَّضَرُّعُ عِندَ السَّحَرِ، وَمُجَالَسَةُ الصَّالِحِينَ حلية الأولياء وطبقات الأصفياء" للحافظ أبي نعيم الأصبهاني (في ترجمة يحيى بن معاذ الرازي).
መርከዝ አስ-ሱና (አሸዋ ቢላል መስጂድ) ለነዘርና ለሂፍዝ የተቀበላቸውን ተማሪዎች የትምህርት ዘመን ማጠናቀቂያን አስመልክቶ ለመጨረሻው ፈተና ብቁ ለማድረግ ከሁለት ወር በላይ በተከታታይ ሲሰጥ ከነበረው ፈተና የተቀነጨበ። ሰኔ እሁድ 7/2018 ድሬደዋ