tgindex
HISNUL MUSLIM

comment @Hisnul_Muslim99_bot

Последний пост
10 дек.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 569
−5 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 237
20 постов
Вовлечённость
49,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 10 дек.2 8113831

    ሶላት እየሰገዳችሁ ኢማናችሁ ከወረደ እና ልባችሁ የደረቀ ከመሰላችሁ ከታች የተጠቀሱት ምክንያቶች ሊሆኑ ስለ 'ሚችሉ ለማስተካከል ይሞክሩ‼️ Disclaimer: ይሄ ፅሑፍ በሶላታችሁ ትኩረት ማጣት ባዶነት እንዲሰማችሁ ተብሎ የተፃፈ ሳይሆን ክፍተታችንን ተረድተን ከወዲሁ እንድናርም ሰበብ ማድረሻ ነው! 1⃣ ሰላት ላይ ቆመን ትኩረታችን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በዱኒያ ጉዳይ ተጠምደን ካገኘነው። ኹሹእ የጎደለው ሰላት የኢማን መሸርሸርን ያመላክታል። 2⃣ ስንሰግድ መረጋጋት የሚጎድለን ከሆነ። እንደ ስፖርት ጠቅ ጠቅ አድርገን የምንጨርስ ከሆነ፤ስንቀራም የተጅዊድ ህጉን ደጋግመን እየጣስን መሆኑን እያወቅን እና ለማስተካከል ምንም ጥረት ካላደረግን ከአላህ ጋር ያለን ትስስር መላላቱን ያሳያል። 3⃣ በቀን አምስቴ እየሰገድን ሰላት በሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ ካላሳደረ ፈተና ላይ ነን። ሰላት ከአሉባልታ፣ሀሜት፣ውሸት፣ሀራምን ከመዳፈር ካላስቆመን ልባችን በከባዱ መድረቁን አመላካች ነው። 4⃣  ካለ ምንም ምክንያት ሰላት የምናዘገይ ከሆነ። አርፍዶ መስገድ ካዘወተርን፣ጀመዓ እና ጁመዓ ሰላቶች ሲያመልጡን ልባችን ካልደነገጠ ኢማናችን የጎደለው ትልቅ ግብዓት ለመኖሩ ጠቋሚ ነው። 5⃣ እንሰግዳለን ግን የኢማን ለዛ(ጥፍጥና) ከራቀን። በአላህ ያለን ተወኩል ሲቀንስ፣ነገራቶችን ወደ እርሱ ማስጠጋት ስናቆም ሰላታችን ተቀባይነቱ መውረዱን ያመላክታል። 6⃣ ሲመቸን ብቻ የምንሰግድ ከሆነ። ቀጣይነት የጎደለው አሰጋገድ ትልቅ ወንጀል ነው። ፈጅርን አሳልፎ ዙህርን አስርን ዘሎ መግሪብን መስገድ ልባችን ከአላህ ጋር መራራቁን ያሳያል። 7⃣ በኢስላሚክ ድንጋጌዎች ላይ ቸልተኛ መሆን ከጀመርን። ውዱእ በአግባቡ አለማድረግ፣ቂብላን በትክክል ተስተቃጭቶ አለመስገድ፣የልብስን እና የራሳን ንፅህና አለመጠበቅ፣ለቁርአን ክብር ማጣት፣ለሶፍ አለመሽቀዳደም ከታየብን ቀልባችን ለመጥቆሩ በቂ ማስረጃ ነው። 8⃣ ለይሉኝታ መስገድ። የአላህን ትዕዛዝ ለማሟላት መሆኑን ዘንግተን ሰዎች አዩኝ አላዩኝ ብሎ መስገድ ትልቅ ክስረት ነው። ሪያዕ ስራን ያበላሻል። ልብንም ያደርቃል። 9⃣ እየሰገድን ከወንጀል መራቅ ካቃተን። ሰላታችን እኛን ከመጥፎ ነገር መከልከል ካልቻለ እና የወንጀላችን አድማስ እየሰፋ ከመጣ ሰላታችን ተቀባይነቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ለመግባቱ ተጨባጭ ማሳያ ነው። 🔟 መስጂድ መሄድ የሚከብደን ከሆነ። ወደ መስጂድ ሄዶ መስገድ በወንዶች ላይ ግዴታነቱ የተደነገገ ሆኖ ሳለ ቤት ውስጥ አዘውትሮ መስገድ በኢማን ለመድከማችን አንዱ ማሳያ ነው። መስጂድ ከሄድንም በኋላ ውስጥ ላይ ለመቀመጥ መረጋጋት ማጣት፣ሱና ሰላቶችን ሳንሰግድ መውጣት፣ስልክ ላይ ከተጣድን፣ከደርስ ከራቅን፣ለሸይኾች ክብር ካጣን...💔። ያስታውሱ! ምንም እንኳን በሰላታችን ጣዕም ብናጣ በፍፁም መስገድ ማቆም የለብንም። የተበታታነው ልባችን በሂደት በሰላት ይሰበሰባል። ተወኩላችን ያድጋል። ኢማናችን ይፋፋል። ጭንቀታችን ይሸሻል። ባዶነታችን ይሞላል። ስብራታችን ይጠገናል። ቁስላችን ይታከማል። እንባችን ይታበሳል። ማጣት በማግኘት ይተካል። ۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡ 39:53 t.me/Hisnul_Muslim99

  • 9 июн. 2025 г.3 145168из Brave_Mindz

    አሳ አጥማጆች ወደ ባህር ሳይሄዱ ሲቀሩ መረባቸውን ይጠግናሉ። ባህሩን ለመቅዘፍ ወጀቡ አስቸጋሪ ሲሆን አስጋሪዎቹ እጃቸውን አጣጥፈው አይቀመጡም። ቀጣይ ስራቸውን የሚያቀላጥፍላቸውን ዝግጅት ያደርጋሉ። መረባቸውን ይጠግናሉ፣መንጠቆዎቻቸውን ያስተካክላሉ፣መሳሪያዎቻቸውን ይስላሉ። ልክ ወጀቡ ጋብ ሲል ወደ ስራቸው ይሰማራሉ። የስኬት ጉዞም ልክ እንደዚህ ተመሳሳይ ነው። የሕይወት ውጣ ውረድ አላፈናፍን ሲለን መለስ ብለን መውጫችንን የሚያቃልሉልንን ነገራቶች መጠገን ይኖርብናል። ወጀቡ እስኪ ሰክን ድረስ መረቡን መጠገን የሚሻ ሰው ቻናሉን ይወዳጅ😊...                t.me/Brave_Mindz

  • በሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ዘመን በተውበቱ ላይ ቋሚ ያልነበረ፣ ሁሌም እየቶበተ ተመልሶ እዚያው የሚነከር የኔ ቢጤ ነበር። ሃያ አመት በዚህ ሁኔታ ቆይቷል። እኔስ ብሆን ስንት ዓመቴ በዚህ መልኩ ስኖር?!… : አላህ ሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ላይ ራእዩን አወረደ። "እገሌ ለሚባለው ባርያዬ ንገረው። እኔ ተቆጥቼበታለሁ!" አላቸው።… ሰይዲና ሙሳ መልእክቱን አደረሱ። ሰውየውም እጅግ አዘነ። ደነገጠ። እንዲህ እያለ ወደ ሜዳ ወጣ: ‐ «ኢላሂ! እዝነትህ አልቆ ነው?! ወይስ ኃጢኣቴ ጎድቶህ?! የይቅርታ ካዝናህ ነጠፈ?! ወይስ በባሮችህ ላይ ሰሰትክ?! የቱ ወንጀል ነው ከይቅርታህ የሚገዝፈው?!… ቸርነት ቀዳሚ ጠባይህ ነው።… መናጢነት፣ ኃጢኣት የመጤው "እኔ" ተከሳች ጠባይ ነው።… ታዲያ የኔ ጠባይ ካንተ ጠባይ ሊያይል ይችላል?!… ባሮችህን ከረሕመትህ ከጋረድክ ማንን ይከጅላሉ?!… አንተ ካባረርካቸው ወደ ማን ይሸሻሉ?!… ኢላሂ! እዝነትህ ካለቀና ቅጣትህን መቅመሴ የግድ ከሆነ የባሮችህን ኃጢኣት በሙሉ እኔ ላይ አድርግ። በነፍሴ በዥቻቸዋለሁ!… » : አዛኙ አላህ እንዲህ አለ: ‐ «ሙሳ ሆይ! ሰውየው ዘንድ ሂድና እንዲህ በለው: ‐ «ኃጢኣትህ ሰማይና ምድርን ቢሞላ እንኳን እምርሃለሁ። በሙሉ ኃያልነቴ፣ በሰፊው ይቅርታዬ፣ በማይነጥፍ እዝነቴ እና በማያልቀው ምህረቴ እስካወቅከኝ ድረስ ምሬሃለሁ!» : ታሪኩን ኢማም አል‐ገዛሊይ "ሙካሺፈቱል‐ቁሉብ" ላይ አስፍረውታል። ©Wezir jj t.me/Hisnul_Muslim99

  • ድመቱ እንኳን ዘውጅ አለው። እኛ ግን አሁንም ላጤ ነን። ማሳጅ ጠላሁ😁።

  • ረመዷን 21 አራተኛው ኸሊፋ ዐሊይ ኢብን አቡ-ጧሊብ የሞቱበት ቀን ነገሩም እንዲህ ነው ዐሊይ (ረዐ) በ38 ሒጅራ ኢራቅ ነኽረወን ከተባለ ቦታ ኸዋሪጃዎች ገጥመው በርካቶቹን ገደሏቸው። ይህ ከሆነ ከሁለት ዓመት በኋላ በ40 ሒጅራ አጋሮቻቸው የተገደሉባቸው ኸዋሪጃዎች በቀል ለመመለስ በመካህ ተሰባሰቡ። ❝ጓዶቻችንን ካጣን በኋላ ምን ህይወት ይቀረናል? ለምን እነዚህን አጥፊ መሪዎች ገድለን ለወንድሞቻችን አንበቀልም?❞ አሉ። ዐንዱረሕማን ኢብን ሙልጂም የተባለው ግብፃዊ ተነስቶ ❝እኔ ለዐሊይ እበቃችኋለሁ!❞ አለ። በረክ ኢብን ዐብዱላህም ተነሳና ❝እኔ ለሙዓዊያህ!❞ አለ። ዐምር ኢብን በክር ደግሞ ❝እኔ ለዐምር ኢብን አል-ዓስ!❞ በማለት የሚገድሏቸውን ሰዎች ተከፋፈሉ። ሶስቱ ገዳዮችም ሞት ቢመጣ እንኳን ወደኋላ ላለማለት ተማማሉ። ሰይፋቸውንም መርዝ አደረጉበት። ግድያውም በተመሳሳይ ቀን በረመዳን 17ኛው ቀን ላይ እንዲሆን ወስነው ኢብን ሙልጂም ወደ ኢራቅ ኩፋ፣ በረክ ወደ ሶርያ ደማስቆ፣ ኢብን በክር ደግሞ ወደ ግብፅ ፉስጣጥ ተጓዙ። ♦️ በረመዳን 17 ሌሊት ዐሊይ (ረዐ) እንደተለመደው ሰዎችን «ሰላት! ሰላት! ተነሱ!» እያሉ ወደ መስጂድ ተጓዙ። ከመስጂዱ በር ላይ ደርሰው ወደ ውስጥ ሊገቡ ሲሉም ድንገት ከአንደኛው አቅጣጫ የተሰነዘረ ሰይፍ ሳታቸውና የበሩን መቃን መታው። ቀጥሎ ከሌላኛው አቅጣጫ የተሰነዘረው ሰይፍ ግንባራቸውን አገኛቸው። ደማቸውም በፊታቸው ላይ ፈስሶ ፂማቸውን አረሰረሰው። ዐሊይም (ረዐ) ❝ያዙት❞ አሉ። ሰዎች በተለያዩ አቅጣጫ በመበታተን ገዳዮቹን ለመያዝ ተሯሯጡ። ከጥቂት ቆይታ በኋላም ሁለት ሰዎች ተይዘው መጡ። አንደኛው በሰይፍ የመታቸው ዐብዱላህ ኢብን ሙልጂም ሲሆን ሁለተኛው ቀድሞ የሳታቸው ተባባሪው ሻቢብ ኢብን በጅራህ ነው። ዐሊይም (ረዐ) ኢብን ሙልጂምን ❝አንተ የአላህ ጠላት! የበደልኩህ ነገር አለህ?❞ አሉት። እሱም ❝እኔ የአላህን መጥፎ ፍጥረት ለመግደል ሰይፌን አርባ ቀን ስዬዋለሁ።❞ አላቸው። ዐሊይም (ረዐ) ❝አይመስለኝም! ይልቁንም አንተ ከአላህ ፍጥረቶች ሁሉ የከፋኸው ነው። በሳልከው ሰይፍም ራስህ ትገደልበታለህ።❞ አሉት። ወደ ቤት ከተወሰዱ በኋላ ሐኪሞችም ሊረዷቸው ተሰባሰቡ። አሲር ኢብን ዐምር የተባለው የታወቀ ሐኪምም ጭንቅላታቸው ውስጥ ደም እንደፈሰሰና መሞታቸው እንደማይቀር ሲረዳ ❝የምዕመናን መሪ ሆይ! ኑዛዜ ካለህ ንገራቸው። ወደ ሞት እየሄድክ ይመስለኛል።❞ አላቸው። ዐሊይም (ረዐ) ወደ ሞት እንደተቃረቡ ሲያውቁ በቅድሚያ ስለ ገዳያቸው አያያዝ ተናገሩ። ❝በዚህ በተመታሁበት ምክንያት ከሞትኩኝ ገዳዬን እንደዚሁ ምቱና ግደሉት። ነገር ግን አደራ በጀናዛው ላይ እንዳትጫወቱ። ምክንያቱም ነቢዩ በውሻ ሬሳ እንኳን ቢሆን እንዳትጫወቱ ብለዋል። እንዲሁም ምግቡንም ከጥሩ መኝታውንም የተስተካከለ አድርጉለት።❞ አሏቸው። ከዚያ በኋላ ዐሊይ (ረዐ) ለሶስት ቀናት ያህል ❝ላ ኢላሃ ኢለሏህ!❞ ከምትለው ቃል በቀር ሌላ ከአፋቸው ሳይወጣ ቆይተው በረመዳን 21 በ«63» ዓመታቸው ህይወታቸው አለፈች። ♦️ ወደ ሙዓዊያህ የተላከው አል-በረክ በተመሳሳይ ቀን ሌሊት ላይ ሙዓዊያህ ወደሚያስግድበት መስጂድ በመግባት ከጀርባው ወጋው። ነገርግን የፈለገውን ያህል ጉዳት ሳያደርስበት ሰይፉ ከእጁ ላይ ወደቀ። ከዚያም ተያዘና ተገደለ። ♦️ ወደ ዐምር የተላከው ኢብን በክር ደግሞ ዐምር ኢብን አል-ዓስ ለሰላት እስኪቆም ከጠበቀ ከኋላ በመውጋት ገደለው። ነገርግን በወቅቱ ዐምር አሞት ከቤት ቀርቶ ነበርና የገደለው ሌላ ሰው ነበር። ከዚያም እሱም ተይዞ ተገደለ። (ታሪኽ አጥ-ጠበሪይ ቅፅ 6)©ሰል ማን        @Hisnul_Muslim99

  • ዛሬ አይደል እንዴ ይሄን ጉድ You Tube ላይ የማየው። ግዴታ ስገዱ የተባሉ ነው የሚመስሉት። አልሰማሁም part😁

  • በረመዷን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች ⛔️ ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣ ⛔️ ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሰሑርን አስቀድሞ በመመገብ ሱብሕ ሳይሰግዱ መተኛት፣ ⛔️ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም (ሙሰልሰላት) ማሳለፍ፣ ⛔️ ረመዷንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣ ⛔️ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣ ⛔️ ተራዊሕ ላይ በየአራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐ እና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣ ⛔️ የተራዊሕ ኢማሞች በጣም ረጅም የቁኑት ዱዓእ ማድረግ፣ ⛔️ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ ስርአት በሌለው መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣… አለ) ⛔️ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ" እያሉ መዞር፣ (10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣ ⛔️ ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣ ⛔️ እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ ⛔️ ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያስፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣ ⛔️ ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣ ⛔️ ሴቶች ሽቶ ተቀብተው ለተራዊሕ መውጣት፣ ⛔️ በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች በየ ጎዳናውና በየካፌው አላስፈላጊ መዝረክረክ፣ ⛔️ሃሜት ማብዛት ⛔️ ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣ ⛔️ ቀኑን በካርታ፣ በዳማ እና መሰል አጉል ነገሮች ማሳለፍ፣ ⛔️ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ⛔️ የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣ ⛔️ በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርኣን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።) ⛔️ ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ ተሰብስበው እያወሩ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣ ⛔️ አንዳንድ አካባቢዎች የዒሻእ ሶላትን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣ ⛔️ አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣ ⛔️ አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማስገደድ፣ ወዘተ ⛔️ ከመግሪብ ሰላት በፊት ባለችዋ ወቅት ከዱዐ መዘናጋት ⛔️ ኣዛን እስከ 'ሚጨርስ ድረስ ሳያፈጥሩ መቆየት ⛔️ ፉጡር ላይ ተጠምዶ የመግሪብ ኣዛን ከመመለስ መዘናጋት ⛔️ የመግሪብ ቀብልያ ከመስገድ ይልቅ ለዚህም ለዚያም እያቀባበሉ ሱና ማስመለጥ ⛔️ በፉጡር ተጥዶ የመግሪብ ሰላት ቤት መስገድ ⛔️ የመግሪብ ቀብልያም ይሁን ባዕድያ ቸላ ማለት ⛔️ በኢፍጣር ሰዓት ከልክ በላይ በልቶ ራስን ማስጨነቅ ⛔️ ከመግሪብ እስከ ዒሻ ያለው ወቅት በትርኪ ምርኪ ማባከን ⛔️ የተራዊሕ ሰላት ከኢማም ጋ ሙሉ ከመስገድ መዳከም ⛔️ ሰሁርን መተው ⛔️ የሰሁር ሰዓት ዱዐ ከማድረግ መዘናጋት ⛔️ ለጥንቃቄ በሚል ስሁርን በጣም በጊዜ መብላት ⛔️ ህፃናት ጾም ከማለማመድ መዘናጋት©        t.me/Hisnul_Muslim99

  • አላህን መፍራት  ↠እውቀትን የፈለገ አላህን ይፍራ 🥀{وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ وَيُعَلِّمُكُمُ ٱللَّهُ } «አላህንም ፍሩ፡፡ አላህም ያሳውቃችኋል» ↠ሲሳይን የፈለገ አላህን ይፍራ 🥀{وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجْعَل لَّهُۥ مَخْرَجًۭا وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ} «አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል» ↠ የነገራቶችን መግራራት የሚፈልግ አላህን ይፍራ 🥀{ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجْعَل لَّهُۥ مِنْ أَمْرِهِۦ يُسْرًۭا } «አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን, ያደርግለታል» @Hisnul_Muslim99

  • እውነት ነው😁።

  • የረመዷን ደንቦች በአቡ ዳውድ በተዘገበው ሐዲስ ነብዩ ﷺ ከንጋት በፊት ለመፆም ያልወሰነ (ያልነየተ/ያላሰበ) አልፆመም ብለዋል። ለሱኹር ለመነሳት የቻልነውን ያክል መሞከር አለብን። ረሱል  ﷺ ከንጋት በፊት ጥቂት ብሉ በዚያን ጊዜ ምግብ መብላቱ በረካ አለውና ብለዋል። ብዙዎቻችን በራሳችን ደካማነት ምክንያት ይህን ትልቅ በረካ እናጣለን። ምግብ ባይኖር እንኳ አንድ ተምርና ውሃ መውሰድ ይኖርብናል። ከንጋት በፊት ያለው ጊዜ እንደ በረካ የሚታሰብበት ምክንያት የሌሊቱ አንድ ሶስተኛ በመሆኑ  አላህ ወደ ታችኛው ሰማይ የሚወርድበትና ምህረቱን የሚቸርበት ጊዜ ስለሆነ ነው። ሌላው ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ልዩ ጊዜ በመሆኑ ነው። ሱኹር ከበላን በኋላ እና ከፈጅር ሶላት በፊት የተወሰነ ትርፍ ጊዜ ሊኖረን ይገባል። አነስ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ዘይድ ቢን ሳቢት ከነብዩ ﷺ ጋር ሱኹር በላን። እናም ረሱል ለሶላት ቆሙ። በሱኹርና በአዛን መካከል ያለው ትርፍ ጊዜ ምን ያህል ነው ስል ጠየኳቸው። በሱኹርና በአዛን መካከል ያለው ትርፍ ጊዜ 50 የቁርአን አያዎችን ለመቅራት በቂ የሆነ ጊዜ ነው ሲሉ መልሰዋል ብሏል። ለማፍጠር መጣደፍ ወይም መፍጠን ይኖርብናል። ነብዩ ﷺ ሰዎች በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሆነው ይቆያሉ ለማፍጠር እስከ ተጣደፉ ድረስ ብለዋል። በተምር እና በውሃ ማፍጠር ሱና ነው። ነብዩ ﷺ አንዳችሁ በፆማችሁ ጊዜ ፆሙን በተምር ይፍታ። ምንም ካላገኘ በውሃ ያፍጥር ብለዋል። ሲዋክ (መፋቂያ) መጠቀም ሱና ነው። ነብዩ እየፆሙ ሲዋክ ይጠቀሙ ነበር። ሲዋክ በመጠቀም የአፍ፣የጥርስ እና የድድ ንፅህናን ለመጠበቅ ይጠቅመናል። በተለይ በፆም ወቅት። @Hisnul_Muslim99

  • ጠቃሚ መረጃዎች 1⃣ የፆም ንያን ጀናባ በሆንበት ጊዜ ቢሆን እንኳን መነየት የምንችል ሲሆን ከንጋት በኋላ መታጠብ እንችላለን። 2⃣ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ምሽት ላይ ያቆመላት ሴት ቀጣዩን ቀን ለመፆም መነየት ይኖርባታል። ጉሱል (ሙሉ ትጥበት) እስከ ንጋት ድረስ ማዘግየት ትችላለች። ነገር ግን ሙሉ ትጥበቷን ከፈጅር ሶላት በፊት መፈፀም ይኖርባታል። 3⃣ ፆመኛ ሰው ጥርሱን መንቀል ፣ ቁስሉን ወይም ጉዳት የደረሰበትን የአካል ክፍል ማከም፣የዓይን ጠብታ መጠቀም ይችላል። ሆኖም የዓይን ጠብታው ጣዕም በጉሮሮው ቢወርድ ፆሙ አይበላሽም። 4⃣ ፆመኛ ሰው ሲዋክ ወይም የጥርስ ብሩሽ በመጠቀም ጥርሱን ማፅዳት ይችላል። ቀኑን ሙሉ ወይም ከሶላት በፊት ጥርስን በሲዋክ መፋቁ ሱና ነው። 5⃣ ፆመኛ ሰው በሞቃት የአየር ንብረት ወይም በውሃ ጥም ቢቃጠል ይህን የሚያቀልለትን ነገር ማድረግ የሚችል ሲሆን ሰውነቱን ለማቀዝቀዝ ውሃ ወይም የአየር ማቀዝቀዣ መሳሪያ መጠቀም ይፈቀድለታል። 6⃣ በጭንቀት ወይም በሌላ ችግር ምክንያት የመተንፈስ ችግር ያጋጠመው ፆመኛ የአተነፋፈስ ስዓአቱን ለማስተካከል አፉ ውስጥ የሆነ ነገር መርጨት ወይም መሳብ ይችላል። 7⃣ አፍን መጉመጥመጥ እና አፍንጫን ወይም የደረቁ ከናፍሮችን በውሃ ማርጠብ ይፈቀዳል። ነገር ግን እየፆመ በተጋነነ መልኩ ብዙ ውሃ በጥልቀት ወደ አፍ ወይም ወደ አፍንጫ ማድረስ የተጠላ ነው። 8⃣ ፀሐይ እንደ ጠለቀች ያለምንም ማዘግየት ወዲያውኑ ማፍጠር (ፆምን መፍታት) ሱና ነው። 9⃣ በፆም ወቅት ብዙ መልካም ስራዎችን አብዝቶ መስራትና የተከለከሉ ነገሮችን ሁሉ መራቅ ሱና ነው። 🔟 ፆመኛ ሰው ዋጅብ (ግዴታ) የሆኑ ስራዎችን ሁሉ መስራት እና ከተከለከሉ ነገሮች ሁሉ መራቅ ይኖርበታል። ለምሳሌ የቀኑን አምስት አውቃት ስግደቶችን በጀመዓ መስገድ ይኖርበታል። ከተከለከሉ ነገሮች ደግሞ ለምሳሌ ሐሜት፣ውሸት መናገር፣ማታለል፣አራጣ መብላት ወ.ዘ.ተ መከልከል ይኖርበታል። ይህን በተመልከተ የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ “ውሸት መናገርና መጥፎ ስራዎችን መስራት ያልተወ ሰው አሏህ ምግብና መጠጥ መተውን አይፈልግም” ብለዋል።          @Hisnul_Muslim99

  • አልሐምዱ ሊላህ! ሸዕባን አጠናቀናል። ቅዳሜ ረመዷን 1 ነው። ምሽቱን ተራዊሕ እንጀምራለን።

  • ፆምን የሚያበላሹ ነገሮች ፆመኛ ሆነን ሳናስበው ዘንግተን(ረስተን) ብንበላ ወይም ብንጠጣ ወይም ደግሞ ተገደን እንድንበላና እንድንጠጣ ብንደረግ ፆማችን አይበላሽም። ሃያሉ አሏህ በቁዱስ ቁርአን እንዲህ ይላል፦ ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን(አትቅጣን) (በሉ)። {አል-ቁርአን 2:286} ልቡ በኢማን ረግታ ይህን እንዲያደርግ ከተገደደ ሰው በቀር {አል- ቁርአን 16:106} ልባችሁ ሆንብሎ ባሰበው እንጅ ሳታውቁ በሰራችሁት ስህተት ሃጢያት የለባችሁም። {አል-ቁርአን 33:5} ስለዚህ ሳናውቅ ረስተን ብንበላ ወይም ብንጠጣ ፆማችን አይበላሽም። እንዲሁም ፀሐይዋ በመጥለቋ ምሽቱ ጀምሯል ብለን በማሰብ ብንበላና ብንጠጣ ወይም ደግሞ ንጋቱ ገና እንዳልጀመረ አስበን ብንበላ ብንጠጣ ፆማችን አይበላሽም። በተመሳሳይ መልኩ እየፆምን እንዳለ የዘር ፈሳሻችን ሳናስበው ቢፈስ ፆማችን አይበላሽም። ፆም የሚያበላሹ ነገሮች ምንድን ናቸው? ፆም በሚከተሉት ስምንት ነገሮች ይበላሻል። 1⃣ ግብረ ስጋ ግኑኝነት ማድረግ: ፆም ግዴታ የሆነብን ሰዎች በረመዷን ቀን ላይ ግኑኝነት ከፈፀምን ይህን ቀን ማካካስና መቶበት ይኖርብናል። ያለፈንን ቀን ለማካካስ አንድ ባሪያ ነፃ ማውጣት ይጠበቅብናል። ይህን ማድረግ ካልቻልን ሁለት ወር በተከታታይ ለመፆም እንገደዳለን። ይህንንም ማድረግ ካልቻልን ስልሳ ድሆችን መመገብ ይኖርብናል። 2⃣ ሆን ብሎ የዘር ፈሳሽን ማፍሰስ 3⃣ ሆን ብሎ መብላት መጠጣት 4⃣ የምግብ መርፌ መወጋት ፆም ያበላሻል። ምክንያቱም ከመብላትና ከመጠጣት ጋር ተመሳሳይ ነውና። 5⃣ ደም መለገስ (መሰጠት): ፆመኛ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ብዙ ደም ፈሶት እንዲያገግም ደም ቢለገሰው ፆሙ ይበላሻል። 6⃣ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም 7⃣ የዋግምት(ሀጀማ) ደም መፍሰስ: ደም በራሱ ጊዜ ከአካል ከፈሰሰ ፆም አያበላሽም። ለምሳሌ የነስር ደም ወይም ደግሞ ጥርስ ከተነቀለ በኋላ የሚፈስ ደም 8⃣ጣታችንን ወደ ጉሮሯችን በማስገባት ሆን ብለን እንዲያስታውከን ብናደርግ ፆማችን ይበላሻል። ሳናስበው በድንገት ቢያስታውከን ግን ፆማችን አይበላሽም።   @Hisnul_Muslim99

  • የፆም ህግጋቶች 1⃣ ፆም ጎልማሳ በሆነ ፣ ጤናማ አዕምሮ ባለውና መፆም በሚችል ማንኛውም ሙስሊም ወንድም ሆነ ሴት ላይ ግዴታ ነው። 2⃣ አማኝ ያልሆነ ሰው አይፆምም፤ ቢፆምም ተቀባይነት የለውም። ምናልባት አሏህ ቀጥተኛውን መንገድ መርቶት ኢስላምን ቢቀበል ያለፉትን የፆም ቀናት ማካካስ አይጠበቅበትም። 3⃣ ፆም ለህፃናት ግዴታ አይደለም። ነገር ግን ይለምዱት ዘንድ እንዲፆሙ መበረታታት ይኖርባቸዋል። 4⃣ አዕምሮው የተዛባ ሰው መፆምም ሆነ ሰዎችን በመመገብ ማካካስ አይገደድም። 5⃣ ለዘለቄታው መፆም የማይችሉ ሰዎች ለምሳሌ በጣም ያረጁና ስር በሰደደ ህመም እየተሰቃዩ ምንም የማገገም ተስፋ የሌላቸው ሰዎች በመፆም ፈንታ ድሆችን መመገብ ይጠበቅባቸዋል። 6⃣ ታሞ የማገገም ተስፋ የሌለው ሰው ፆሙ አስቸጋሪ ከሆነበት ፆሙን ሊያፈርስ ይችላል። ሆኖም ግን ካገገመ በኋላ ያለፈውን ቀን ማካካስ ይኖርበታል። 7⃣ ነፍሰጡር ሴቶችና ጡት የሚያጠቡ እናቶች በረመዷን ወቅት መፆም አስቸጋሪ ከሆነባቸው ወይም ልጄ ይጎዳብኛል ብለው ከፈሩ ፆማቸውን መፍታት ይፈቀድላቸዋል። ብኋላ ላይ ግን ያለፋቸውን ቀናት ማካካስ ይኖርባቸዋል። 8⃣ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ላይ የሆኑ ሴቶች በዚህ ወቅት መፆም አይፈቀድላቸውም። ነገርግን በኋላ ላይ ያለፋቸውን ቀናት ማካካስ ይገደዳሉ። 9⃣ መንገደኛ ሰው መፆም ወይም ደግሞ አለመፆም የሚችል ሲሆን ካልፆመ በኋላ ላይ ያለፉትን ቀናት ማካካስ ይኖርበታል።           t.me/Hisnul_Muslim99

  • በመጪው ረመዷን የተሻለ የዒባዳ አፈፃፀም ለማድረግ የሚያግዝ ዕቅድ። ለአዘጋጀው አካል አላህ ምንዳውን ይደራርብለት። Share በማድረግ እናዳርሰው። t.me/Hisnul_Muslim99

  • በረመዷን ዋዜማ እየተጋባችሁ ያላችሁ ጥንዶች ተከታታይ 2 ወር ከመፆም ጀሊሉ ይጠብቃችሁ።

  • የረመዷን ሌቦችን ተጠንቀቁ! አንደኛው ሌባ፦ ቴሌቭዥን ሲሆን ለሥጋም ሆነ ለመንፈስ ከፍታ አጋዥ ካልሆኑ የረመዷን ሙሰልሰላቶች እና አዘናጊ ድራማዎችን ተጠንቀቁ። የረመዷን ውድ ጊዜያት ለውድ ነገሮች መዋል አለባቸው፡፡ ሁለተኛው ሌባ፦ በስልክ አላስፈላጊ ወሬ ማውራት ለብዙ ስህተት ያጋልጣል። ትርፍ ንግግር ወደ ሀሜትና ያልታሰቡ ወንጀሎች ይመራል። ለተሻለ ምንዳ በረመዷን በንግግር ጭምር ቁጥብ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ሶስተኛው ሌባ፦ ወጣ ገባ ማብዛት/መዞር፡፡ በረመዷን ከመስጂድ እና ከቤት የበለጠ ማረፊያ የለም፡፡ ወደ ከተማም ይሁን ወደ ገበያ ካለበቂ ምክንያት መዞር ማብዛት ዓይንንም ሆነ ጆሮን ያልሆነ ነገር ላይ ይጥላል፡፡ ፆምን ይሰርቃል፤ምንዳዉንም ያጓድላል፡፡  አራተኛው ሌባ፦ ማምሸት፡ ያለምክንያት ማምሸት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለዉም፡፡ የረመዷን ምሽቶች ምርጥና ውብ ናቸው፡፡ በቁርኣን፣ዚክር እና በተለያዩ ዒባዳዎች መዋብ አለባቸው፡፡ አምስተኛው ሌባ፦ ኩሽና:በተለይ ለሴቶች፡፡ሙሉውን ረመዷን ማዕድ ቤት የሚያሳልፉ ቁርኣንን፣ሶላትን እና ዚክርን የረሱ ብዙ ናቸው፡፡ ረመዷን የፆም ወር ነው፡፡ ትልቁን ትኩረት ለሆድ መስጠት ዓላማዉን መሳት ነው የሚሆነው፡፡ ስድስተኛው ሌባ፦ ሶሻል ሚዲያ:ዛሬ ላይ የብዙዎቻችን ችግር ሆኗል፡፡በቤትም ሆነ በመስጂድ ሳይቀር ትልቅ ትኩረት ሰጥተነው ጊዜያችንን እየጨረስንበት ነው፡፡ በዚህም ከዚክር፣ከቁርኣንና ከዱዓ እንዳንጠቀም አዘናግቶናል፡፡ ሰባተኛው ሌባ:- ትርፍ እንቅልፍ ነው። ዓመቱን ሙሉ ተኝተን ነው የከረምነው። ቢያንስ በረመዷን እንኳን በተቻለን መጠን እንቅልፋችንን ቀንሰን በዒባዳ ልንጠነክር ይገባል። በረመዷን ያልረጠበ ቀልብ፣በረመዷን ያልተገራ  አንደበት በአዘቦት ቀን የመራሱ ነገር አጠያያቂ ነው። እንቅልፋችንን በልኩ እናድርገው። መጪው ረመዷን ዱዓችን የሚሰማበት፣ስብራታችን የሚጠገንበት፣ልባችን የሚረጥብበት፣ጭንቀታችን የሚወገድበት፣አንድነታችን የሚጠናከርበት፣ሰላማችን የሚያብብበት የእዝነት ወር ያድርግልን።            t.me/Hisnul_Muslim99

  • ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ رضي الله عنه ጀናዛውን መላዒካዎች የተሸከሙት እና ዓርሽ የተንቀጠቀጠለት ሰሃባ በእስልምና ውስጥ የቆየው 7 ዓመታትን ብቻ ነበር። እኛ ስንት ዓመታትን ቆይተን ልባችን አለመርጠቡ ያማል💔።

  • #ምክር_ለወጣቶች_( Day ) السلام عليكم ورحمت الله وبركاته بسم الله الرحمان الرحيم 🌟 وذكر فاءن ذكرا تنفع المؤمنين، وما خلقت الجن والاءنس الا ليعبدون يا اختي المسلمة يا من اللتزمت كتاب الله تلاوة، وتدبرا ،وعملا ، يا من تريدين الخلود في الجنة اليك  هذه الكامات التي تخرج من قلب اختك وترد لك السعادة في الدنيا والفوز في الأخيرة አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ የአላህን መፅሀፍ በማንበብ፣ በማስተንትን፣እንዲሁም በመስራት የተቆራኘሽው እህቴ፣ በጀነት መዘውተርን የምትፈልጊዋ እህቴ  ሆይ  ላንቺ በዱንያም በአኼራም ደስታን እና እድለኝነትን ከምትመኝልሽ እህትሽ ልብ ውስጥ የሚወጡትን ንግግሮች እንኪ, ይህች ፅሁፍ የምታተኩረው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ Day ለምታከብሩ ተማሪዎች ሁሉ በተለይ ለሙስሊም እህቶች እንድታስተውሉ ለማስታወስ ነው እሺ ቢስሚላህ 1, የተፈጠርንበት አላማ አላህን በትክክል ለመገዛት እንድሆነ እና በተሰጠን ግዜ እንደምንጠየቅ ለምን ረሳን በአላህ ????????? 2, እዛ Day የሚከበርበት ቦታ የሚሰሩትን ሀራም ስራዎች ለምሳሌ ሰላትን ማዘግየት፣ ኢኽቲላጥ ፣ ዘፈኖች ....... ሌሎችም የእስልምና ትዕዛዝን የሚቃረኑ ስራዎች እንደሚሰሩ እያወቅን የምንሄድበትስ ምክንያት ምንድን ነው??? 3, ይህንን አያህ ማስተንተን ለምን አቃተን? "ياءيها الذين آمنو اتقو الله حق تقاته ولاتموتن الا وانتم مسلمون" "እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ትክክለኛ የሆነ መፍራትን ፍሩት ሙስሊም ሆናችሁ ቢሆን እንጂ እንዳትሞቱ" እህቶች በ ደንብ እናስተውል ሴት ልጅ ያለ ሀያእ ምንም አይደለችም። የሰሀቢያቶችንም ታሪክ ብናይ በሀያእ ፣ ትልቅ በሆነ ኢልም ነው  የምናቃቸው ፉጢማ(ረ.ዐ)እኮ በሀያቷ 3ግዜ ነው  ከቤቷ የወጣችው ይህም በኒካህ፣ ለሀጅ እና ስትሞት ነበር። አጂብ እኛ ግን ....... ሌላው ቀርቶ Day ለማክበር የሚሄድ ራሱ በጣም  በዝቷል መልሺ እስኪ እህቴ ይሄ ስራ አላህን ከመፍራት ነውን ??? አንተስ ብትሆን ወንድሜ ቁርአንን ሀፍዘህ ፣በህግጋቱ ሰርተህ ፣ሙስሊም ኡማውን መጥቀምን ፣ትልቁ ግብህን ለምን ረሳህ ??? ሁላችንም በጊዜያችን እንጠየቃለን ። "ስንሰራው በነበረው ስራ እንሞታለን፣ በሞትንበት ነገርም እንቀሰቀሳለን ። "ሒሳብም ምርመራም አለብን እኮ አህባቢ ለግራውንድ ማይነሷ ቤታችን ለቀብራችን ብርሃን ካሁኑ መያዝ እንጀምር። ከመቼውም ግዜ በላይ በዒልም እንጠንክር ምክንያቱም 👇 انما يخش الله من عباده العلماء ስለተባልን፣ አላህን ለመፍራት ትዕዛዝን እና ክልከላን ለማወቅ ዒልም ግዴታ ነውና በኢልም እንጠንክር አደራ ከአላህ ራህመት ተስፋ አድርገን ወደሱም ተዋድቀን እንለምነው እሱ ምህረተ ሰፊ ነውና ተውባችንን ይቀበለናል ኢንሻአላህ ሱብሀን ወጣትነት አያታለን ወላሂ ወጣትነትም ያልፋል ወጣትነታችን ሳያልፍ እንጠቀምበት። ሁሌም ሞት እንደማይረሳን እናስታውስ ወደ ተውባም እንቻኮል አላህ ያግዘን ያረብ ንግግርን ሰምተው ከሚሰሩበት ኢላሂ ያድርገን እውነትን ካረጋገጥኩ ከአላህ ነው ከተሳሳትኩም ከነፍሲያዬ እና ከሸይጧን ነው አላህ ኸይሩን ይግጠመን والله اعلم ✍ የአንሷር ልጅ

  • ان الحمد لله ؛ نحمده ونستعنه ونستغفره؛ ونعوذ باالله من شرور انفسنا ومن سيءات اعمالنا ؛ من يهد الله فلا مضل له ومن يضليل فلا هادي له ؛ واشهد ان لااله الا الله وان محمد عبده ورسله! اما بعد احيكم بتحيت الاءسلام وان اقول لكم አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ በዚህች አጠር  ያለች ፅሁፍ ከፊታችን ስለሚጠብቀን ትልቁ የረመዳን ወር  ወሳኝ ነጥቦችን እናያለን በአላህ ፍቃድ☺️ ፅሁፌም ኢኽላስ እንዲኖረው እና አንባቢዎችንም እንድትጠቅም ጌታዬን እየተማፀንኩ ፅሁፌን እጀምራለው። ቢስሚላህ قال تعلى في كتابه العظيم "ياءيها الذين ءامنو كتب عليكم الصيام كما كتب على الذين من قبلكم لعلكم تتقون" "እናንተ ያመናችሁ ሆይ ፆም ከእናንተ በፊት ለነበሩት ሕዝቦች በግዴታነት እንደ ተደነገገ ሁሉ በእናንተም ላይ ተደንግጎል ትጠነቀቁ ዘንድ" ሰሀቦች እናንተ ያመናችሁ ተብሎ የሚጀምሩ አያዎችን በትኩረት ያዳምጡ ነበር ትዕዛዝን ወይንም የተከለከሉ ነገሮችን ይዞ ስለሚመጣ አላህም በዚህ አያህ የፃም ዋነኛው አላማ ተቅዋ እንዲኖረን እንደተፈለገ ቁልጭ አድርጎ ነግሮናል☺️ ለእንግዳችን እስኪ ምን ማድረግ እንዳለብን እንመልከት 😊 1, "አላህ ባሮቹ በመራባቸው ወይም በመጠማታቸው ምንም ሀጃ የለውም መጥፎ እና ውድቅ ንግግሮችን እስካልተው ድረስ"ተብለናል ስለዚሕ ከመጥፎ ንግግሮች ራሳችንን ልንቆጥብ ይገባል 2 , "ሙስሊም ባሰፈሩት ዘገባ እያንዳንዱ የሰው ልጅ በጎ ስራ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ይባዛል።አላህ እንዲህ ብሏል"ፆም ሲቀር "እርሱ የኔ ነው እኔው እመነዳዋለው። 3, ብዙ ሰዎች ረመዳን፣ ኢድ ሲደርስ ቁሶችን ለመለወጥ ይሯሯጣሉ። አሏህ ያዘነላቸው ደግሞ የቁርአን የአዝካር የለይል ሰላት ............ የኸይር ስራ በርናሚጅ ያወጣሉ ።አላሕ ካዘነላቸው ያድርገን🤲 4, ሰሀቦች አመቱን ሙሉ ረመዳንን ከማስታወስ አይቦዝኑም ነበር። የመጀመሪያውን 6 ወር ጌታቸው እንዲያደርሳቸው ዱዐ ሲያደርጉ የቀረውን ደግሞ 6 ወር እንዲቀበላቸው ዱዐ ሲያረጉ🥹እኛስ ................ አላህ ይምራን ወላሂ😔 በአጠቃላይ ልባችንን አጥበን ሀራምን ርቀን ሀላልን አዘውትረን ልንጠብቀው ይገባል ከዛሬ ጀምረን እስቲቃማውንም እንዲሠጠን ዱዐ እያደረግን ዝግጅታችንን ከዛሬው እንጀምር አላህ ይርዳን🤲 ሁላችንንም አላህ ረመዳንን አድርሶን በትክክል ፆመን፣ ተስተካክለን ለተቀሩት ወራቶች ስንቅ ምንይዝበት ያድርገን🤲 እኔም በፃፋኩት እናንተም ባነበባችሁት ተጠቃሚዎች ያድርገን😁ወቢላሂ ተውፊቅ ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ ✍ የአንሷር ልጅ

HISNUL MUSLIM — tgindex