tgindex
💻ᴍᴀᴍ ᴛᴇᴄʜ ᴛᴇᴄʜɴᴏʟᴏɢʏ ɪɴsᴛɪᴛᴜᴛᴇ📲

💻ᴍᴀᴍ ᴛᴇᴄʜ ᴛᴇᴄʜɴᴏʟᴏɢʏ ɪɴsᴛɪᴛᴜᴛᴇ📲

Статистика

እንኳን ወደ M A M T E C H በሰላም መጡ ። በዚህ ቻናል 🌎 ስለ ቴክኖሎጂ የተሟላ መረጃ የሚያገኙበት: 🕌 በተጨማሪም ወቅታዊ ኢስላማዊ መረጃወችና ኢስላማዊ ትምህረቶችን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ➡ ማንኛውም አስተያዬት ሲኖሮዎት 👇👇 @Mam_tech_1_bot

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
6
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
11 018
+10 за 3 дн.
Сутки
−3
−0,03%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
190
21 постов
Вовлечённость
1,7%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 22
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
116
1/48двое суток
132
1/72трое суток
143

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.50из ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ!

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.68удалён 14 авг.

    ማን ቀድሞ ይመልስ !  🚀🚀 ትክክለኛውን መልስ የመለሰ add  የሚለውን በመጫን ጠቃሚ ነገር ያገኛል ! ጥያቄ  👉 በቁርኣን ውስጥ ረጅሙ ሱራ (ምዕራፍ) ማን ይባላል?

  • 12 авг.1033из MuradTadesse

    የዚህን ወንድማችንን የተቆራረጡ ቪድዮዎች በገፄ ላይ ሲመጡ አዳምጫቸው ነበር። ታሪኩ ልብ ይሰብራል፣ በርካታ የዱንያ ሙሲባዎችን ያሳለፈ ብርቱ ሰለምቴ ወንድማችን ነው። አሁንም ላይ የሚሠራው ሊስትሮ ነው። በጣም ያሳዘነኝና ልቤን የነካው ንግግሩ፤ ሰዎች እኔን ጫማ አያስጠርጉኝም። ትልቅ ሰው ነው በሚል እርሱን ወደታች ጫማቸውም ማስጠረግ ኃፍረትና ሼም ሆኖባቸው ነው። በርግጥ አልፈርድባቸውም። «ለኔ የሚጠቅመኝ ግን ቢያስጠርጉኝ ነበር!» ሲል የበለጠ ልቤን ነካው። እኔም ቢሆን ብሆን ይህ ወንድማችን ቢያጋጥመኝ፤ ደፍሬ በዚህ ሐይባው ለማስጠረግ ይከብደኛል። ግን ደግሞ ለርሱ የሚጠቅመው ባስጠርገው ነው። አላህን በማይፈሩ የምድር ጭራቆች፣ የሰው ሸይጧኖች ዘግናኝና ለጆሮ ሰቅጣጭ ግፍ የተፈጸመበት፣ 4 ልጆቹን በተከታታይ በሞት ያጣ… ወንድማችን ነውና፤ ሚዲያ ላይ ከወጣ አይቀር፤ ላልሰማችሁ ቪድዮዎቹን እያጋራኋችሁ፤ እንደተለመደውና ለሌሎች እንደምናደርገው፤ ዛሬም ለዚህ ወንድማችን 3 ነገሮችን ተረባርበን ብናደርግ ብዬ አሰብኩ። 1) ከሊስትሮው የተሻለ ገቢ የሚያገኝበትንና ኑሮውን መምራት የሚያስችለውን መካከለኛ አዋጭ ቢዝነስ ብናስጀምረው፣ 2) ከቢዝነሱ ማቋቋሚያ የተወሰነ እንዲተርፈው አድርገን፤ ስነ ልቦናውም ስለተጎዳ፤ ዑምራ ብናስደርገውና መንገሱን አዲሶ ቢመጣ ብዬ አሰብኩ። 3) የጤና ተቋም ያላችሁ አካላት፤ አናግሩኝና በአካል ተገኝቶ የተለያዩ ምርመራዎችንና የስነ ልቦና ጥገና ትሪትመንቶችን ብታደርጉለት መልካም ነው። በዚህ ረገድ ፈቃደኛ የሆናችሁ፤ ሃሳባችሁን ልስማና ለድጋፉ በራሱ ስም የተከፈተ አካውንት አጋራችኋለሁ። የወንድማችን ስሙ ዑመር ታረቀ ነው። እስኪ ቪድዮውን አጋጥሟችሁ የሰማችሁት ካላችሁ፤ ሃሳባችሁን አካፍሉኝ። || t.me/MuradTadesse

  • 11 авг.131из mam_quote2

    https://t.me/mam_quote2

  • 10 авг.143из MuradTadesse

    ወላጆች → ባልጠፋ ት/ቤት ልጆቻችሁን ሴኩላር ባልሆኑ የሌላ እምነት ተከታዮች ብቻ በሚማሩባቸው ኃይማኖታዊ ት/ቤቶች አታስገቡ። አንዱ ልጁን ካቶሊኮች ት/ቤት አስገብቶት፤ ከኬጂ ሲመረቅ ኬክ ሲቆርስ «በስማም» አለ። من تجالس توارث! ኢስላማዊ ት/ቤቶች ደግሞ – ፕሊስ ጥራታችሁን ጨምሩ። እንኳን የኛውን ሰው የሌላውንም የምታማልሉ ሁኑ።

  • እናንተም ተሳተፉና ተበሉ! አካውንታቸው ላይ የቀረው 59 ብር ብቻ ነው! በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉት ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት ሽመልስ እና ቤተሰቦቻቸው፣ በዘመናዊ የዲጂታል ቀማኞች ወጥመድ ውስጥ ወድቀው ከ1.3 ሚሊየን ብር በላይ ተዘርፈዋል። ጉዳዩ የተጀመረው «ቤት ቁጭ ብሎ በወር ከ70 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር መሥራት ይቻላል» በሚል ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚወጣ አታላይ ማስታወቂያ ነው። የቤት እመቤት የሆነችው ባለቤታቸው ነገሩን አምና አፕሊኬሽኑን ስትሞክረው፤ ወደ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ ግሩፖች በመግባት «አሊባባ ኦንላይን ንግድ» በሚባል አደገኛ መዋቅር ውስጥ ትገባለች። አጭበርባሪዎቹ ሰዎችን ለማጥመድ የተካኑ ስለሆኑ፣ እምነት ለማግኘት ሲሉ በመጀመሪያ 800 ብር ልከው 1,500 ብር ይመልሱላቸዋል። ቤተሰቡም «ነገሩ እውነት ነው» ብሎ እንዲያምን ያደርጉታል።ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ትክክለኛው ሰቆቃ የሚጀምረው። የገንዘቡ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲመጣ፣ የራሳቸውን ቁጠባ ጨምሮ ከውጭ ሀገር ከምትኖር የባለቤታቸው እህት ጭምር 600,000 ብር ተበድረው ገቢ ያደርጋሉ። አጭበርባሪዎቹ ጨካኝነታቸውን አሳይተው «አንደኛ ደረጃ ነጋዴ ስለሆናችሁ ከፍተኛ ግብር መክፈል አለባችሁ» በማለት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስገቡ አድርገው በድምሩ 1.3 ሚሊየን ብር እንዲዘረፉ አድርገዋቸዋል። በሐሰተኛው መተግበሪያ ላይ 3 ሚሊየን ብር አትርፈዋል ተብሎ ይታይባቸውም ነበር፤ ነገር ግን ገንዘቡን ማውጣት ሳይችሉ ቀርተው አካውንታቸው ላይ የቀረው 59 ብር ብቻ ነው! ይህ ሁሉ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸም ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት በሥራ ስምሪት (ፊልድ) ላይ ነበሩ። የገንዘቡን መበላት ስትሰማ የባለቤታቸው ልብ ድንጋጤን መቋቋም አቅቶት ዛሬ ላይ በጽኑ ታማ በጸበል ቦታ መንፈሳዊ ሕክምና እየተደረገላት ይገኛል። የዕድሜ ልክ ድካማቸው በአንድ ቀን ባዕድ ኃይል መናጋቱ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ከቷቸዋል። የማለዳ ቤተሰቦች ሆይ! ዛሬ ሶሻል ሚዲያ ላይ «ቀላል ገንዘብ፣ ያለ ሥራ ብዙሀብት» የሚሉ ማስታወቂያዎች በዝተዋል። ከዚህ በፊት ብዙዎችን አጥምደዋል፤ አሁንም እየጨረሱ ነው። እባካችሁ ይህንን መሬት ላይ ያለውን እውነታ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት (በማካፈል) ሕብረተሰቡ ከዚህ መሰል የዲጂታል ቀማኞች ራሱን እንዲጠብቅ ግንዛቤ እንፍጠር። የተሰበረውን ቤተሰብ ፈጣሪ ያጽናናቸው! ማለዳ

  • ቁርአን በተጅዊድ መቅራት የምትፈልጉ ከታች ባለው ሊንክ መመዝገብ ትችላላቹ ። 👇👇👇👇 @Alif_jema_online_qirat_center ማናገር እና መመዝገብ ይችላሉ

  • ሰላም! ዛሬ ስለ computer አፃፃፍ ትንሽ እንማማር ። ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ እንዴት እንደሚፃፍ ያውቃሉ?ሲጽፉስ ምን ያህል ይፈጥናሉ? ========================= ❖መጀመሪያ Ge'ez 10 Software ያወረዱ እና install ያድርጉት ከዛም አማርኛ መፃፍ ስትፈልጉ power ge'ez status phonetic Unicode Mode (ፎ) ላይ ያድርጉት በ English መፃፍ ስትፈልጉ ደግሞ power ge'ez status English Mode (ኢ) ላይ አድርጉት ከዛም የሚከተሉትን ኣጭር መግላጫ በትክክል ይመልከቱ። ◕ሀ➭H_ሁ➭Hu_ሂ➭Hi_ሃ➭Ha_ሄ➭Hy_ህ➭He_ሆ➭Ho ◕ለ➭L_ሉ➭Lu_ሊ➭Li_ላ➭La_ሌ➭Ly_ል➭Le_ሎ➭Lo ❖ሐ➭Shift+h_ሑ➭Shift+hu_ሒ➭Shift+hi_ሓ➭Shift+ha_ሔ➭Shift+hy_ሕ➭Shift+he_ሖ➭Shift+ho መ➭M_ሙ➭Mu_ሚ➭Mi_ማ➭Ma_ሜ➭My_ም➭Me_ሞ➭Mo ❖ሠ➭Shift+s_ሡ➭Shift+su_ሢ➭Shift+si_ሣ➭Shift+sa_ሤ ➭Shift+sy_ሥ➭Shift+se_ሦ➭Shift+so ◕ረ➭R_ሩ➭Ru_ሪ➭Ri_ራ➭Ra_ሬ➭Ry_ር➭Re_ሮ➭Ro ◕ሰ➭S_ሱ➭Su_ሲ➭Si_ሳ➭Sa_ሴ➭Sy_ስ➭Se_ሶ➭So ❖ሸ➭Shift+s_ሹ➭Shift+su_ሺ➭Shift+si_ሻ➭Shift+sa_ሼ ➭Shift+sy_ሽ➭Shift+se ሾ➭Shift+so ◕ቀ፡➭Q ቁ፡➭Qu ቂ፡➭Qi ቃ፡➭Qa ቄ፡➭Qy ቅ፡➭Qe ቆ፡➭Qo ◕በ፡➭B ቡ፡➭Bu ቢ፡➭Bi ባ፡➭Ba ቤ፡➭By ብ፡➭Be ቦ፡➭Bo ◕ተ፡➭T ቱ፡➭Tu ቲ፡➭Ti ታ፡➭Ta ቴ፡➭Ty ት፡➭Te ቶ፡➭To ◕ ቸ፡➭C ቹ፡➭Cu ቺ፡➭Ci ቻ፡➭Ca ቼ፡➭Cy ች፡➭Ce ቾ፡➭Co ◕ነ፡➭N ኑ፡➭Nu ኒ፡➭Ni ና፡➭Na ኔ፡➭Ny ን፡➭Ne ኖ፡➭No ❏ኘ፡➭Shift +n ኙ፡➭Shift +nu ኚ➭Shift+ni ኛ፡➭Shift +na ኜ፡➭Shift +ny ኝ፡➭Shift + ne ኞ፡➭Shift +no ◕ከ፡➭Ka ኩ፡➭Ku ኪ፡➭Ki ካ፡➭Ka ኬ፡➭Ky ክ፡➭Ke ኮ፡➭Ko ❖ ኸ ☛capslock + Shift + h ኹ ☛capslock + Shift + hu ኺ ☛capslock + Shift + hi ኻ ☛Capslock + Shift + ha ኼ ☛Capslock + Shift + hy ኽ ☛Capslock + Shift + he ኾ ☛Capslock + Shift + ho ❏ኀ፡➭ Capslock + H ኁ፡➭ Capslock + HU ኂ፡➭Capslock + HI ኃ፡➭Capslock + HA ኄ፡➭Capslock + HY ኅ፡➭Capslock + HE ኆ፡➭Capslock + HO ❏አ፡➭Capslock X ኡ፡➭Xu ኢ፡➭Xi ኣ፡➭Xa ኤ፡➭Xy እ፡➭Xe ኦ፡➭XoDe ❖ዐ፡➭Shift +x ዑ፡➭Shift +xu ዒ➭Shift +xi ዓ፡➭Shift +xa ዔ➭Shift +xy ዕ፡➭Shift +xe ዖ➭Shift +xo ✪ወ፡➭W ዉ፡➭Wu ዊ፡➭Wi ዋ፡➭Wa ዌ፡➭Wy ው፡➭We ዎ፡➭wo ✪ዘ፡➭Z ዙ፡➭Zu ዚ፡➭Zi ዛ፡➭Za ዜ፡➭Zy ዝ፡➭Ze ዞ፡➭Zo ❏ዠ፡➭Shift + Z ዡ፡➭Shift + Zu ዢ፡➭Shift + Zi ዣ፡➭Shift +Zaዤ፡➭Shift + Zy ዥ፡➭Shift +Ze ዦ፡➭Shift + Zo ✪ፈ፡➭F ፉ➭Fu ፊ፡➭Fi ፋ፡➭Fa ፌ፡➭Fy ፍ፡➭Fe ፎ፡➭Fo ✪ ፐ፡➭P ፑ፡➭Pu ፒ፡➭Pi ፓ፡➭Pa ፔ፡➭Py ፕ፡➭Pe ፖ፡➭Po ✪ገ፡➭G ጉ፡➭Gu ጊ፡➭Gi ጋ፡➭Ga ጌ፡➭Gy ግ፡➭Ge ጎ፡➭Go ✪ደ፡➭D ዱ፡➭Du ዲ፡➭Di ዳ፡➭Da ዴ፡➭Dy ድ፡➭ዶ፡Do ❏ጠ፡➭Shift + t ጡ፡➭Shift + tu ጢ፡➭Shift + ti ጣ፡➭Shift+ta ጤ፡➭Shift + ty ጥ፡➭Shift + te ጦ፡➭Shift + to ❏ጨ፡➭Shift +c ጩ፡➭Shift +cu ጪ፡➭Shift +ci ጫ፡➭Shift+caጬ፡➭Shift +cy ጭ፡➭Shift +ce ጮ: ➭Shift +co ❏ጸ፡➭Capslock + t ጹ፡➭Capslock + tu ጺ፡➭Capslock + ti ጻ፡➭Capslock + ta ጼ፡➭Capslock + ty ጽ፡➭Capslock + t ጾ፡➭Capslock + to ❖ ፀ➭☞Capslock+Shift+t ፁ➭☞Capslock+Shift+tu ፂ➭☞Capslock + Shift + ti ፃ➭☞Capslock + Shift + t ፄ➭☞Capslock + Shift + ty ፅ➭☞Capslock + Shift + te ፆ➭☞Capslock + Shift + to ✪ጀ፡➭J ጁ፡➭Gu ጂ፡➭Ji ጃ፡➭Ga ጄ፡➭Gy ጅ፡➭Ge ጆ፡➭Jo ✪ቨ፡➭V ቩ፡➭Vu ቪ፡➭Vi ቫ፡➭Va ቬ፡➭Vy ቭ፡➭Ve ቮ፡➭Vo ቋ➭Capslock+qwa ቧ➭Capslock+bwa ቷ➭Capslock+twa ኟ➭Capslock +Shift+nwa ቿ➭Capslock+cwa ሟ➭Capslock+mwa ቷ➭Capslock+twa ጓ➭Capslock gwa ፏ➭Capslock+fwa ሯ➭Capslock +rwa ዷ➭Capslock+dwa ቯ➭Capslock+vwa ኋ➭Capslock+hwa ዟ➭Capslock+zwa ዧ➭Capslock+Shif+zwa ኗ➭Capslock+nwa ሏ➭Capslock+lwa ኳ➭Capslock+kwa ሷ➭Capslock+swa ጇ➭Capslock+jwa ጧ➭Capslock+twa ======================================

  • ስማርት ስልኮቻችን ሀይል እንዴት መሙላት አለብን…? በርካታ ተግባራትን የሚያከናውኑበት ስማርት ስልክዎ ባትሪ በፍጥነት እያለቀ ተችገረዋል? የተለያዩ ስልቶችን ተጠቅመው የስልክዎን ባትሪ ቢያንስ ሙሉ ቀን እንዲያስጠቅምዎትስ ጥረት አድርገዋል? በቴክኖሎጂው መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች የስልካችን ባትሪ በፍጥነት እያለቀ የምንቸገረው በሶስት ምክንያቶች መሆኑን ይገልፃሉ። የመጀመሪያው በስማርት ስልኮቻችን የጫንናቸው መተግበሪያዎች መብዛት እና እያወቅንም ይሁን ሳናውቅ ተከፍተው ባትሪ መብላታቸው ነው። የስማርት ስልካችን ላይ ሙጭጭ ብለን አልላቀቅ ማለትም ሌላኛው የባትሪ እድሜን የሚያሳጥር ልማድ ነው። ሶስተኛው እና ዋነኛው የባትሪ ህይወትን የሚያሳጥረው ተብሎ በባለሙያዎች የተጠቀሰው ደግሞ የሀይል አሞላላችን (ቻርጅ አደራረጋችን መሆኑ ተገልጿል። ብዙዎቻችን የስማርት ስልካችን ባትሪ ሙሉ በሙሉ ሲያልቅ ቻርጅ ማድረግ እንዳለብን እናምናለን። በአንዳንዶቻችን ዘንድ ደግሞ ቻርጅ እንደሰካን ሞባይላችንን መጠቀም የባትሪውን አገልግሎት ያራዝማል የሚል አመለካከት አለ። ይሁን እንጂ የሞባይል ባትሪ እንደ ሰው ልጅ ሁሉ “መጨናነቅን” አይወድም ነው የሚለው ባትሪ ዩኒቨርሲቲ የተሰኘ ኩባንያ። ስልካችንን ቻርጅ እያደረግን መጠቀም የባትሪውን እድሜ ያሳጥራልም ይላል። ስለ ስማርት ስልክዎ ባትሪ ከመጨነቅ የሚገላግሉ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችም ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች አስቀምጧል። የስልክዎ ባትሪ ሙሉ ቻርጅ ከተደረገ በኋላ ሞባይሉን ከቻርጀሩ ይንቀሉት፡ ኩባንያው እንደሚለው የስማርት ስልካችን ባትሪ ከአቅሙ በላይ ቻርጅ ሲደረግ የረጅም ጊዜ አገልግሎቱ እየወረደ ይመጣል። ስልካችን 100 ፐርሰንት ቻርጅ ከሆነ በኋላ እንደተሰካ መተው ለከፍተኛ መጨናነቅ በመዳረግ የባትሪውን ሀይል የመያዝ አቅም ይቀንሰዋል። (እስከ 100 ፐርሰንት ቻርግ ማድረግም ለመጀመሪያ ጊዜ ካልሆነ አስፈላጊ አይደለም፡ ከአድካሚ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኋላ ጡንቻዎችን ማፍታታት እንደሚገባ ሁሉ ስልካችንም ሙሉ በሙሉ በሀይል ከተሞላ በኋላ ከቻርጀሩ መንቀል ይገባል። ባትሪውን ከሙቀት ይጠብቁት የስማርት ስልክ ባትሪዎች በቀላሉ በሙቀት ይግላሉ። ለዚህም ነው አፕል ራሱ የአይፎን ስልኮችን ቻርጅ ስታደርጉ መሸፈኛ (ኬዞቹን ብታወጡት በማለት የሚመክረው። ስለሆነም ስልካችን ቻርጅ ስናደርግ መሞቁን ካስተዋልን ሽፋኑን ማውጣት ይኖርብናል። የባትሪያችን ጤና ለመጠበቅ ስማርት ስልካችን ቻርጅ የምናደርግበት አካባቢ የፀሀይ ሙቀት የሌለበት ቢሆንም ጥሩ ነው። 100 ፐርሰንት ላይ እስከሚደርስ መጠበቅ የለብንም፡ እንደ ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ገለፃ ከሆነ ከፍተኛ ቮልቴጅ ባትሪውን ስለሚያጨናንቀው ባትሪን መቶ በመቶ ሀይል መሙላት አያስፈልግም። ስማርት ስልካችን ቀኑን ሙሉ ቻርጅ ማድረግም በባትሪው እድሜ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብሏል። ቻርጅ ለማድረግ የባትሪውን ማለቅ አይጠብቁ። ስልካችን ቻርጅ ለማድረግ ባትሪው ተሟጦ እስኪያልቅ መጠበቅ የለብንም። ባገኘነው አጋጣሚ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን ሀይል ይዞ የመቆየት አቅም ያሳድገዋል። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ስልቶች የስማርት ስልካችን ባትሪ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል እና ቀኑን ሙሉ ከስጋት ነፃ እንድንሆን ይረዳናል ። ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት እባኮት ሼር ማድረግ እንዳይረሱ። እንኳን ወደ M A M T E C H በሰላም መጡ ። በዚህ ቻናል 🌎 ስለ ቴክኖሎጂ የተሟላ መረጃ የሚያገኙበት: 🕌 በተጨማሪም ወቅታዊ ኢስላማዊ መረጃወችና ኢስላማዊ ትምህረቶችን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ➡ ማንኛውም አስተያዬት ሲኖሮዎት 👇👇 @Mam_tech_1_bot

  • 10 ነፃ ሶፍትዌር ማውረጃ ድረ-ገፆች 1) www.FileHippo.com 2) www.Ninite.com 3) www.Cnet.com 4) www.Softpedia.com 5) www.MajorGeeks.com 6) www.FilePuma.com 7) www.DownloadCrew.com 8) www.FileHorse.com 9) www.SnapFiles.com 10) www.DonationCoder.com https://t.me/mamtech1

  • የተዘጉ ስልኮች መክፈት ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ የተዘጉ ስልኮችን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው? Network ሰጪ ድርጅቶች በመላው አለም ላይ ይገኛሉ። በሀገራችንም ethio telecom ይገኛል። በሌሎች ሀገራት ደግሞ ከ አንድ በላይ network አቅራቢ ድርጅቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት በመንግስት ስር ሳይሆን በግል ተቋማት ስር ስለሆኑ ነው።ለዚህም ጎሮቤታችን Kenya ጥሩ ማሳያ ናት። ከአንድ በላይ የመኖሩ ጥቅም ህዝቡ የተሻለ አማራጭ ያገኛል ድርጅቶቹም የተሻለ ነገር ለማቅረብ ፉክክር ዉስጥ ይገባሉ። አንድ አንድ network ሰጪ ድርጅቶች ደግሞ አለም አቀፍ እውቅና አላቸው። ለምሳሌ T-mobile, verizon, orange, vodafone..... እነዚህ ድርጅቶች ከሚፎካክሩቸው መንገዶች አንዱ ደንበኞችን ለመሳብ ሲሉ የስልክ ቀፎዎችን በቅናሽ ዋጋ ያቀርባሉ። ይህን የሚያደርጉት ደንበኞቻቸው የአየር ሰአት በገዛቸዉ ቁጥር ተጠቃሚ ስለሚሆኑ ነው። ነገር ግን በዚህ መንገድ የተገዙ የስልክ ቀፎዎች ከተገዙበት የnetwork ሰጪ ተቋማት ውጪ ያሉ sim cardoችን አይቀበሉም ይህም ምክንያቱ በ security code ስለሚቆለፉ ነው። እንደዚህ አይነት ስልኮች ሀገር ስለቀየሩ ሳይሆን እንቢ የሚሉት ከተገዙበት የ network ሰጪ ድርጅት ዉጪ ባሉ network ሰጪ ድርጅቶች sim card ስለማይሰሩ ነው። የተዘጉ ስልኮች የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ። Sim not valid, wrong sim,unknown sim, phone restricted, contact service provider..... ከ network ሰጪ ድርጅቶች የተገዛ ስልክ ለመክፈት ሁለት መንገድ አለ። 1. Computer , flasher box, እና flasher file በመጠቀም መክፈት ይቻላል። ይህ ዘዴ አሁን ላይ ethio telecome የሚዘጋቸውን ስልኮችንም ይመለከታል ነገር ግን በዚህ Method ለመክፈት Computer, flasher box እና flasher file ያስፈልገናል። ስለ Computer ማብራራት አያስፈገኝም ነገር ግን በዚህ Method ትንሽ አሸጋሪ የሚሆነው Universal flasher box ማግኘት ነው ይሄ box የተለያዩ ጥቅሞች ሲኖሩት ከዚህም ውስጥ በስልኩ ሞዴል የራሱን flasher file ከ Google ላይ በማወረድ ከስልኮቻችን ጋር በማገናኘት የትኛውንም ስልክ ማስተካከል እንችላለን ከ hardware ውጪ ምንም አይነት ችግሮችን እንድናስተካክል ያስችለናል። ይህ universal flasher Box orginale ስልኮችን IMEI create በማድረግ አሁን ላይ ላለው ethio telecome ለሚዘጋቸው ስልኮች ፍቱን መድሃኒት ሲሆን የ flasher box ዋጋ በ Ethiopia 4326birr አከባቢ ሲሆን የተወሰኑ ሞባይል ቤቶች በ addis abeba እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። ለምሳሌ ለመጠቆም ያህል መርካቶ ይርጋ ሃይሌ building ላይ በኛ በኩልም ይህን flasher box ማግኘት ይችላሉ። 2. ለ ድርጅቱ መጠነኛ ክፍያ በመፈጸም ማስከፈት ሲሆን:- ለምሳሌ iphone በ icloud የተዘጉ ስልኮችን መጥቀስ ይቻላል እንደዚህ አይነት ስልኮች የ e-commerce እንዲሁም credit card ይጠይቃሉ። ይሄ አገልግሎት ደግሞ እኛ ሀገር ስለሌለ ያለው አማራጭ ውጭ ሀገር በምናቀው ሰው ማስከፈት ነው። ይህ ማለት ድህረ ገፁ ላይ ግብተን የስልኩን ሞዴል ስናስገባ ክፍያ ይጠይቀናል ክፍያውም የሚከናወነው በ ማስተር ካርድ ስለሆነ ክፍያውን ውጪ ሃገር ማስተር ካርድ ባለው ሰው ከባላንሱ ላይ እንዲፈፅምልን በማድረግ ክፍያው ከተፈጸመላቸው ድርጅቱ ኮዱን በሚያስገባው Email አድሬስ ስለሚልክልን ወድያውኑ መክፈት ይቻላል። በ icloud የተዘጉ ስልኮች በማስተር ካርድ በ አሁን ጊዜ የሚያስከፈለው 104$ ዶላር ነው ለዚህም ነው በአዲስ አበባ በተለያዩ የ ሞባይል ቤቶች በተለይ መርካቶ ላይ ከ200$ ዶላር በላይ የሚጠይቁት ጥቅማቸውን በማሰብ ማለት ነው። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለባችሁ ውጪ ሃገር ላይ የ ማስተር ካርድ ቪዛ ኮዱን አስገብቶ ክፍያውን ሊፈፅምላችሁ እና በ Email የሚላክለትን Code ሊልክላችሁ የሚችል ወዳጅ ከሌላችሁ ምንም አይነት አማራጭ የላችሁም ከ200$ ዶላር በላይ ከፍለን ከማስከፈት ውጪ ስልኩን መጠቀም አንችልም። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ይሄ መንገድ ስላካችንን በመጀመሪያ ሩት ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለ ሩት ከዚህ በፊት Post ላይ ማብራሪያ ስለሰጠን ከዛ ላይ ገብተው ያንብቡ። ሩት የሆነ ቀፎ ካለን እንደሚከተለው በማድረግ imei መቀየር እንችላለን ። ይህን ዘዴ ለመጠቀም ሁለት ፕሮግራሞች እንጠቀማለን የመጀመሪያው:- 1.Mobileuncle MTK IMEI Write Tool የሚለውን ሶፍትዌር ኮምፒውተራችን ላይ ዳውንሎድ እናደርጋለን ከዛ በዚፕ ያለውን ፕሮግራም ስንከፍት የሚያመጣልን ዊንዶው ላይ Y ብልን ፅፈን enter እንጫናለን ከዛ የሞባይላችንን imei እንፅፍና create IMEI .BAK ብለን አዲስ የተፈጠረውን imei.bak ፋይል ወደ ሜሞሪ ካርድ እንልከዋለን። ሜሞሪ ካርዱን ቀፎ ውስጥ ካስገባን በኋላ... 2.ይህን አፕሊኬሽን ቀፏችን ላይ እንጭናለን mobileuncle_MTK_toolv2.9.9.apk 3.ከዛ የጫነውን አፕሊኬሽን ስንከፍት ሩት ኣክሰስ ጥያቄ ሲጠይቅ grant ብለን ፍቃድ እንሰጠዋለን። ከዛ IMEI backup and restore የሚለውን ከፍተን ,restore IMEI.bak. ስንል ቅድም ሜሞሪ ላይ ያስቀመጥነውን ፋይል ወደ ቀፏችን ይፅፍልናል። ሲጨርስ ቀፏችንን Restart አድርገን መደወያው ላይ *#06# አስገብተን በትክክል መፃፉን እናረጋግጣለን። ነገር ግን ሚሞሪ የማይወስዱ ስልኮች እና የተወሰኑ ሞባይሎች ለምሳሌ iphone...etc በmobile Uncle tools ImEI backup restore የሚለው not supported ካላችሁ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርንው በ method one የሚከፈቱ ስለሆኑ የግድ Flasher box መግዛት ይጠበቅባችኋል። 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ▬▬▬▬▬📌Share https://t.me/mamtech1

  • видео или голосовое, без подписи

  • 💻ᴍᴀᴍ ᴛᴇᴄʜ ᴛᴇᴄʜɴᴏʟᴏɢʏ ɪɴsᴛɪᴛᴜᴛᴇ📲 pinned «አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ የማም ቴክ ቤተሰቦች ትንሽ ጠፋ ብለናል ኢንሻ አላህ በቅርቡ ለእናንተ ይጠቅማል ያልነውን አዳድስ የቴክ መረጃዎችን እና ትምህርቶችን ይዘን እንመጣለን በትግስት ጠብቁን ። እንኳን ወደ M A M T E C H በሰላም መጡ ። በዚህ ቻናል 🌎 ስለ ቴክኖሎጂ የተሟላ መረጃ የሚያገኙበት: 🕌 በተጨማሪም ወቅታዊ ኢስላማዊ መረጃወችና ኢስላማዊ ትምህረቶችን የሚያገኙበት…»

  • አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ የማም ቴክ ቤተሰቦች ትንሽ ጠፋ ብለናል ኢንሻ አላህ በቅርቡ ለእናንተ ይጠቅማል ያልነውን አዳድስ የቴክ መረጃዎችን እና ትምህርቶችን ይዘን እንመጣለን በትግስት ጠብቁን ። እንኳን ወደ M A M T E C H በሰላም መጡ ። በዚህ ቻናል 🌎 ስለ ቴክኖሎጂ የተሟላ መረጃ የሚያገኙበት: 🕌 በተጨማሪም ወቅታዊ ኢስላማዊ መረጃወችና ኢስላማዊ ትምህረቶችን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ➡ ማንኛውም አስተያዬት ሲኖሮዎት 👇👇 @Mam_tech_1_bot https://t.me/mamtech1

  • Channel photo updated

  • ​ማሜ ቋንቋ እና ኮምፒውተር ማሰልጠኛ ተቋም Mame Language & Computer Training Center ​🎓 ብቁ ያድርጉ! እውቀትዎን ያሳድጉ! ​ ​የምንሰጣቸው አገልግሎቶች / Our Services: ​የቋንቋ ትምህርቶች (Languages): ​Afaan Oromoo ​Arabic (ዓረብኛ) ​English (እንግሊዝኛ) ​የኮምፒውተር ስልጠና (Computer Training): ​ልዩ የኮምፒውተር ስልጠና ከብቁ ሙያ ማረጋገጫ (Certificate) ጋር ​💡 ለምን እኛን ይመረጣሉ? ​እጅግ ተመጣጣኝ ዋጋ ​ብቃት ያላቸው አሰልጣኞች ​⚠️ ማሳሰቢያ፡ ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ! ​📍 አድራሻ፡ 44 ማዞሪያ 📞 ስልክ፡ 0951637195 | 0920266107 @mamtech1

  • 🌍 ኢንተርኔት እንዴት እንደሚሰራ እና ለምን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ በበለጠ ዝርዝር እና በሰፊው እናብራራለን። ⏺💡 ኢንተርኔት እንዴት ይሠራል? ኢንተርኔት የሚሰራበት መንገድ በጣም የተወሳሰበ ቢሆንም፣ በዋናነት መረጃን በትናንሽ ክፍሎች (ፓኬቶች/Packets) በመከፋፈል እና በተለያዩ መንገዶች በመላክ ላይ የተመሰረተ ነው። ✅ 1. የመረጃ ዝውውር ፕሮቶኮሎች (Protocols) ኢንተርኔት እንዲሰራ መሰረታዊ የሆኑ "ቋንቋዎች" ወይም የህጎች ስብስቦች አሉ። ✅ TCP/IP (Transmission Control Protocol/Internet Protocol):    ✅ IP (የኢንተርኔት ፕሮቶኮል): ይህ እያንዳንዱን መሳሪያ (ኮምፒውተር፣ ስልክ፣ ወዘተ) በኢንተርኔት ላይ የሚለይ አድራሻ (IP Address) እንዲኖረው ያደርጋል። ልክ የፖስታ አድራሻ እንደሚያስፈልግ ሁሉ፣ IP አድራሻ መረጃው በትክክለኛው ቦታ መድረሱን ያረጋግጣል።    ✅ TCP (የዝውውር ቁጥጥር ፕሮቶኮል): ይህ ደግሞ መረጃው በትክክለኛ ቅደም ተከተል እና ያለምንም ስህተት ወደ መድረሻው መድረሱን ያረጋግጣል። አንድ ትልቅ መልዕክት ወደ ትናንሽ "ፓኬቶች" የሚቆራርሰው እና በመድረሻው ላይ መልሶ የሚጠረዝፈው TCP ነው። ✅ HTTP/HTTPS (Hypertext Transfer Protocol): ድረ-ገጾችን እና ሌሎችንም መረጃዎች ከአገልጋዩ ወደ እኛ የድር አሳሽ (Web Browser) ለማስተላለፍ የሚያገለግል ፕሮቶኮል ነው። HTTPS ደህንነቱ የተጠበቀ (Encrypted) የመረጃ ልውውጥን ያቀርባል። ✅ 2. የኔትወርክ መሠረተ ልማት (Infrastructure): መረጃው የሚተላለፍባቸው አካላዊ መንገዶች ናቸው። ✅ የኦፕቲካል ፋይበር ኬብሎች (Fiber Optic Cables): እነዚህ በብርሃን ፍጥነት መረጃን የሚያስተላልፉ ቀጭን የመስታወት ገመዶች ናቸው። አብዛኛው የዓለም ኢንተርኔት ግንኙነት የሚካሄደው በባህር ስር በተዘረጉ ግዙፍ የኦፕቲካል ፋይበር ኬብሎች ነው። ✅ ራውተሮች (Routers): እነዚህ መሳሪያዎች እንደ የትራፊክ ፖሊስ ሆነው ያገለግላሉ። እያንዳንዱን የመረጃ ፓኬት (Packet) ተቀብለው መድረሻውን አይተው በጣም ፈጣን እና ቀልጣፋ በሆነው መንገድ እንዲጓዝ ይመራሉ። ኢንተርኔት የሚሰራው በሺዎች የሚቆጠሩ ራውተሮች እርስ በርሳቸው በመተባበር ነው። ✅3. የዶሜን ስም ስርዓት (DNS - Domain Name System) ⏺ ሰዎች ድረ-ገጾችን የሚያገኙት በቀላሉ በሚታወሱ ስሞች (ለምሳሌ: google.com) ነው። ሆኖም ኮምፒውተሮች የሚግባቡት በቁጥር በተጻፉት IP አድራሻዎች ነው። ⏺ DNS ልክ እንደ ስልክ ደብተር ይሰራል። እኛ የጎራውን ስም ስንጽፍ፣ DNS አገልጋይ የዚያን ስም ትክክለኛ የIP አድራሻ አግኝቶ ለኮምፒውተራችን ይሰጣል። ከዚያ በኋላ ኮምፒውተሩ በትክክለኛው አገልጋይ (IP Address) ጋር ይገናኛል። ✅ 🌐 ኢንተርኔትን ለምን እንጠቀማለን? ⏺ ኢንተርኔት ትልልቅ ለውጦችን አመጥቷል። ✅ 1. ዓለም አቀፍ ትስስር እና ግሎባላይዜሽን: ኢንተርኔት ድንበሮችን በማጥፋት ግሎባላይዜሽንን አፋጥኗል። ⏺ ዓለም አቀፍ ንግድ: ትናንሽ ኩባንያዎች እንኳን ምርቶቻቸውን በዓለም ዙሪያ መሸጥ ይችላሉ። ⏺ ባህልና ትምህርት: የተለያዩ ባህሎችን፣ ቋንቋዎችን እና እውቀቶችን ከማንኛውም የዓለም ክፍል በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ⏺ የፖለቲካ ተሳትፎ: ሰዎች በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በቀላሉ መረጃ ያገኛሉ፣ ይወያያሉ እና ይሳተፋሉ። ✅ 2. ትምህርት እና ዕውቀት ማግኘት: ኢንተርኔት የመማር ሂደቱን ዲሞክራሲያዊ አድርጓል። ⏺ ክፍት የትምህርት ሀብቶች (OER): ነፃ መጽሐፍት፣ የጥናት ጽሑፎች እና የምርምር ሪፖርቶች በቀላሉ ይገኛሉ። ⏺ MOOCs (Massive Open Online Courses): ከዓለማችን ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ነፃ ወይም ርካሽ ኮርሶችን መውሰድ ይቻላል። ⏺ የምርምር ትብብር: ሳይንቲስቶች እና ተመራማሪዎች አካላዊ ርቀት ሳይገድባቸው በአንድ ፕሮጀክት ላይ አብረው መስራት ይችላሉ። ✅ 3. ፈጠራ እና የኢኮኖሚ ዕድገት ⏺ የጅምር ሥራዎች (Startups): አዳዲስ የንግድ ሞዴሎች እና ፈጠራዎች በኢንተርኔት ላይ ተመስርተው በቀላሉ ሊፈጠሩ እና ሊስፋፉ ይችላሉ። (ለምሳሌ: አፕሊኬሽኖች፣ ሶፍትዌር አገልግሎቶች) ⏺ የርቀት ሥራ (Remote Work): የሰራተኛ ቅልጥፍናን ይጨምራል፣ እና ኩባንያዎች የትኛውንም የአለም ክፍል ባለሙያ መቅጠር ይችላሉ። ⚠️ ፈተናዎች እና ሥጋቶች ከእነዚህ ጥቅሞች ባሻገር ኢንተርኔት የራሱ የሆኑ ፈተናዎች አሉት: ⏺ ሳይበር ደህንነት (Cybersecurity): የኢንፎርሜሽን ስርቆት፣ የማልዌር ጥቃቶች እና የሳይበር ወንጀል ስጋቶች አሉ። ⏺ የግላዊነት ጉዳዮች (Privacy): ትልልቅ ኩባንያዎች ስለ ተጠቃሚዎች የሚያከማቹት የመረጃ መጠን አሳሳቢ ሆኗል። ⏺ የሐሰት መረጃ (Misinformation): የትኛውም ሰው በቀላሉ መረጃ ማሰራጨት በመቻሉ፣ ሐሰተኛ ወሬዎች እና የተሳሳተ መረጃ በፍጥነት ይሰራጫል። ✅ በአጭሩ፣ ኢንተርኔት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ያለው ፋይዳ እጅግ ሰፊ እና ከግንኙነት በላይ ነው። የዕውቀት፣ የንግድ እና የባህል ልውውጥ መሰረት ነው። https://t.me/mamtech1

  • ✅ DHCP Server (Dynamic Host Configuration Protocol) ምንነት፣ አሰራር እና ጥቅም በዝርዝር ማብራሪያ። ✅ በአጭሩ DHCP ማለት የኔትወርክ "አስተናጋጅ" ማለት ነው። አንድ እንግዳ (ኮምፒውተር ወይም ስልክ) ወደ አንድ ድግስ (Network) ሲመጣ የመቀመጫ ቁጥር (IP Address) የሚሰጥ አካል ነው። ✅ 1. DHCP ምንድን ነው? (What is DHCP?) DHCP ማለት Dynamic Host Configuration Protocol ነው። ⏺ አንድ ኮምፒውተር፣ ስልክ ወይም ታብሌት ከአንድ ኔትወርክ (ለምሳሌ ከቤትህ WiFi) ጋር ሲገናኝ፤ በኔትወርኩ ውስጥ መታወቅ እንዲችል IP Address (መታወቂያ ቁጥር) ያስፈልገዋል። ⏺ ይህንን ቁጥር ሰው በእጁ እያንዳንዱ መሳሪያ ላይ መፃፍ ሳይጠበቅበት፣ DHCP ሰርቨሩ በራሱ (Automatically) ለሁሉም መሳሪያዎች ያከፋፍላል። ✅ 2. DHCP ምን ይሰጣል? (DHCP Assigns): ለአንድ መሳሪያ የሚከተሉትን 4 ወሳኝ ነገሮች ይሰጣል፡ ⏺ IP Address: የመሳሪያው ብቸኛ መለያ ቁጥር (ለምሳሌ፡ 192.168.1.10)። ⏺ Subnet Mask: ኔትወርኩ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ የሚለይበት ኮድ (ለምሳሌ፡ 255.255.255.0)። ⏺ Default Gateway: መሳሪያው ወደ ኢንተርኔት ለመውጣት የሚጠቀምበት በር ወይም የራውተር አድራሻ። ⏺ DNS Server: የዌብሳይት ስሞችን (ምሳሌ https://www.google.com/search?q=google.com) ወደ ቁጥር የሚቀይርልን አገልጋይ። ✅ 3. እንዴት ይሰራል? (How DHCP Works - DORA) DHCP አድራሻ ለመስጠት የሚከተለውን DORA የሚባል ባለ 4 ደረጃ ሂደት ይጠቀማል፡ ⏺ D - Discover (መፈለግ): ኮምፒውተርህ ኔትወርኩ ላይ ሲገባ "እዚህ አካባቢ IP አድራሻ የሚሰጥ አለ?" ብሎ ለሁሉም ይጮሃል (Broadcast ያደርጋል)። ⏺ O - Offer (ማቅረብ): DHCP ሰርቨሩ ጥያቄውን ይሰማና፣ "አዎ አለሁ! ይሄው ይሄን IP አድራሻ (ምሳሌ 192.168.1.10) ውሰድ" ብሎ ያቀርብለታል። ⏺ R - Request (መጠየቅ): ኮምፒውተርህ የቀረበለትን አድራሻ ያይና፣ "እሺ ይሄን አድራሻ ወድጄዋለሁ፣ ልጠቀምበት?" ብሎ መልሶ ይጠይቃል። ⏺ A - Acknowledge (ማጽደቅ): DHCP ሰርቨሩ "እሺ ፈቅጄልሃለሁ፣ አድራሻው ያንተ ነው" ብሎ ያጸድቅለታል። ከዚህ በኋላ ኮምፒውተሩ ኢንተርኔት መጠቀም ይችላል። ✅ 4. ጥቅሙ ምንድን ነው? (Why DHCP Matters) ⏺ አውቶማቲክ ነው (Automatic IP Assignment): እያንዳንዱን ስልክ እና ላፕቶፕ ላይ ቁጥር እየሞሉ ጊዜ ማጥፋት የለም። ⏺ ግጭትን ያስወግዳል (Avoids IP Conflicts): ሁለት መሳሪያዎች ተመሳሳይ ቁጥር (IP) እንዳይኖራቸው ይከላከላል። ሰው በእጁ ቢሞላ ግን የመሳሳት እድል አለው። ⏺ ቀላል አስተዳደር (Easy Network Management): በተለይ ለትላልቅ ቢሮዎች ኔትወርክን መቆጣጠር ቀላል ያደርገዋል። ⏺ ለተለያዩ ቦታዎች ይሆናል: ከቤት ኔትወርክ ጀምሮ እስከ ትላልቅ የዳታ ማዕከላት (Data Centers) ድረስ ያገለግላል። ✅ በአጠቃላይ DHCP ማለት እኛ ሳናውቀው ከበስተጀርባ ሆነሮ ስልኮቻችን እና ኮምፒውተሮቻችን ያለምንም ችግር ከኢንተርኔት ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ነው።

  • 28 июл.30251из mam_quote2

    ደረጃ 1፦ አስተሳሰብህን ለውጥ የለውጥ መጀመሪያው አስተሳሰብን መለወጥ ነው፡፡ የትኛውን አስተሳሰብ ነው ምለውጠው ካልክየተቀጣሪነት አስተሳሰብህን መጀመሪያ ቀይር፡፡ እመነኝ ተቀጥሮ ሃብታም የሆነ ሰው የለም፡፡ ደመወዝ ማደንዘዣ ዕጽ መሆኑን ተገንዘብ ፡፡ደመወዝ እንዳትድንም እንዳትሞትም በማድረግ ፈሪ እንድትሆን ያደርግሃል፡፡ ቢዝነስ ለመጀመር ብከስርስ ብለህ ትፈራለህ፤ያለ ደመወዝ ህይወት ባዶ ይመስልሃል፤አይዞህ አትፍራ ይህ የሁሉም ተቀጣሪ ሰው ስጋት ነው፡፡በተቀጣሪ እና በስራ ፈጣሪ መካከል ያለው ትልቁ ልዩነት አስተሳሰብ ነው። ተቀጣሪዎች ትኩረት የሚያደርጉት በደመወዝ ጭማሪ፤በስራ ዋስትና እና ቀጣሪያቸው በሚሰጣቸው ጥቅማጥቅም ላይ ሲሆን፣ ስራ ፈጣሪዎች ግን ትኩረታቸውን የሚያደርጉት ችግሮችን በመለየት መፍታት፣ እሴት መፍጠር እና ለውጤቱ ኃላፊነት መውሰድ ላይ ነው። ተግዳሮቶችን እንደ ዕድል ማየት ጀምር፤ ደመወዝህ አይበቃህም ፡፡ስለዚህ ሲቸግርህ ዝም አትበል ተንቀሳቀስ ፤አንብብ ምን ማድረግ እንዳለብህ ጭንቅላትህን አሰራው ፡፡ ደረጃ 2፦ ዋጋ ያለው ተፈላጊ ክህሎት አዳብር (ማስተር አድርግ) ማንኛውም ስኬታማ ንግድ የሚጀምረው ከአንድ ክህሎት ወይም ሙያዊ ብቃት ነው። እንደ ግራፊክስ ዲዛይን፣ ዲጂታል ማርኬቲንግ፣ ሽያጭ (sales)፣ ድረ-ገጽ ማልማት (web development)፣ ኮፒራይቲንግ (copywriting) ወይም ማማከር (consulting) በመሰሉ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ ክህሎቶች ላይ ትኩረት አድርግ። ክህሎትህ እያደገ በሄደ ቁጥር ደንበኞችን መሳብና ገቢ ማመንጨት ይበልጥ ቀላል ይሆንልሃል። ስለዚህ ስራህንም ሳትለቅ ጎን ለጎን ሌላ ተጨማሪ ገቢ ማግኛ የሚሆን ስኪል በነጻ ከዩቲዩብ መማር ጀምር፡፡ልብ በል ይሄን ስታደርግ አንደኛ ገቢህን ታሳድጋለህ ሁለተኛ ደግሞ እንዴት የራስን ቢዝነስ መጀመር እንደሚቻል በደምብ ትማራለህ፡፡ስለዚህ ጎን ለጎን የምትሰራው ስራ ደመወዝህን ተክቶ አንተን ሚያኖር እነደሆነ ስትረዳ ከተቀጣሪነት ወጥተህ ሙሉ በሙሉ ከራስህ ስራ ላይ ትኩረትህን ታደርጋለህ፡፡ አሁንም ልብ በል ደመወዝህን ለቢዝነስህ እግር መትከያ አድርገው፡፡ የምትጀምረው ቢዝነስ አገልግሎት መስጠት ስለሆነ ምንም መነሻ ገንዘብ አያስፈልግህም፡፡ ደረጃ 3፦ የግል ብራንድህን (Personal Brand) ገንባ ሰዎች የሚሸምቱት ከሚያምኑት ሰው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሙያዊ ገጾችን ክፈት፣ ከተማርካቸው ስኪሎች ጠቃሚ ይዘቶችን አጋራ፣ ስራዎችህን አሳይ፣ እንዲሁም ሙያዊ ብቃትህን አስመስክር። ጠንካራ የግል ብራንድ ማዘጋጀት ለማስታወቂያ ከፍተኛ ገንዘብ ሳታወጣ ዕድሎችን እንድታገኝ ይረዳሃል፡፡ ደረጃ 4፦ የፍሪላንስ (Freelance) ወይም የጎንዮሽ ስራዎችን ጀምርአሁን ካለህበት ስራ ከመልቀቅህ በፊት፣ ባዳበርከው ክህሎት በትርፍ ጊዜህ ገቢ ማግኘት ጀምር። ከትናንሽ ደንበኞች ጋር ስራ፣ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቅ፣ እና ከደንበኞች ጋር እንዴት መገናኘት እንደምትችል ተማር። ይህ ደረጃ የፋይናንስ ስጋትን በመቀነስ ልምድ እንድታገኝ ይረዳሃል። ደረጃ 5፦ ሽያጭ እና ማርኬቲንግ ተማር የሽያጭና ማርኬቲንግ ስኪል የገንዘብ መፈልፈያ ማሽኖች ናቸው፡፡ሁሉም ድርጅት በሚበባል ደረጃ ደምበኛ ሚያመጣለትና ማርኬቲንግ የሚሰራት ሰው በጣም ይፈልጋል፡፡ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች ደንበኛ ማግኘት ስለማይችሉ ብቻ ይከስማሉ። አገልግሎቶችህን እንዴት እንደምትሸጥ፣ የእሴትህን ጠቃሚነት እንዴት እንደምታስረዳ፣ በዋጋ ላይ እንዴት እንደምትደራደር እና ስራህን በኢንተርኔት እንዴት እንደምታስተዋውቅ ተማር። ሽያጭ እና ማርኬቲንግ ክህሎትን ወደ ገቢ የሚቀይሩ መሳሪያዎች ናቸው። እነዚህን ስኪሎች ስታዳብር የንግድ ድርጅቶችን በአሪፍ ክፍያ ታግዛቸዋለህ፡፡ ግቢህም እያደገ ይሄዳል፡፡ ደረጃ 6፦ የተለያዩ የገቢ ምንጮችን ፍጠር በአንድ ደንበኛ ወይም በአንድ ስራ ላይ ብቻ ከመደገፍ ይልቅ የገቢ ምንጮችህን አውጣጣ (diversify አድርግ)። የተለያዩ አገልግሎቶችን አቅርብ፣ ዲጂታል ምርቶችን ፍጠር፣ ስልጠናዎችን ስጥ፣ ወይም ተደጋጋሚ የገቢ መስመሮችን (recurring revenue) ገንባ። ብዙ የገቢ ምንጮች መኖር የንግድህን መረጋጋት ይጨምራሉ። ደረጃ 7፦ አሰራሮችን (Systems) ዘርጋ ሁሉንም ነገር በራሳቸው ለመስራት የሚሞክሩ ስራ ፈጣሪዎች ውለው አድረው በስራቸው ይሰላቻሉ። ለኮሙኒኬሽን፣ ለፕሮጀክት አስተዳደር፣ ለደንበኞች አገልግሎት እና ለፋይናንስ የሚሆኑ የአሰራርስርዓቶችን (systems) ዘርጋ። ጥሩ አሰራሮችን መዘርጋት ንግዱ በብቃትና በተሳለጠ ሁኔታ እንዲያድግ ያስችላል። ደረጃ 8፦ ገንዘብ ቆጥብ፣ ትርፍህንም መልሰህ ኢንቨስት አድርግ የምታገኘውን ገቢ በሙሉ ከመጠቀም ተቆጠብ። ከትርፍህ የተወሰነውን ክፍል ለመስሪያ መሳሪያዎች፣ ለትምህርት፣ ለማርኬቲንግ እና ለንግድህ እድገት መልሰህ ፈሰስ (reinvest) አድርገው። ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች ትርፍን ለቢዝነሳቸው ማስፋፊያ እንጅ ለሌላ ወጭ መሸፈኛ አያደርጉትም፡፡ ደረጃ 9፦ ከሰራተኝነት በወደ ንግድ ባለቤትነት ተሻገር የደንበኞችህ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ፣ ተደጋጋሚ ስራዎችን ለሌሎች ውክልና በመስጠት (outsource በማድረግ) አንተ እንደ ስትራቴጂ መንደፍ፣ ሽያጭን ማቀላጠፍ እና ንግድ ማስፋፋት ላይ ባሉ ከፍተኛ ዋጋ ባላቸው ተግባራት ላይ ትኩረት አድርግ። ግቡ የራስህን ስራ መፍጠር ብቻ ሳይሆን፣ የትልቅ ደርጅት ባለቤት መሆን ነው። ደረጃ 1ዐ፦ ማሳደግና ማስፋፋት (Scale and Expand) ንግድህ ትርፋማ ከሆነ በኋላ፣ በአጋርነት፣ ሰራተኞችን በመቅጠር፣ አገልግሎቶችን በማስፋፋት፣ ወደ አዲስ ገበያ በመግባት ወይም ምርቶችን በመፍጠር ንግድህን የምታሳድግበትን ዕድል ፈልግ። እድገት የሚመጣው ብዙ ሰዎችን በማገልገል እና የላቀ እሴት በማቅረብ ነው።) ሲጠቃለል፡ ተቀጣሪ ጊዜን በገንዘብ ይለውጣል ፤ስራ ፈጣሪ ደግሞ ከግል ጊዜው ባለፈ እሴት እና ገቢ የሚያመነጩ ስርዓቶችን (systems) ይዘረጋል።

💻ᴍᴀᴍ ᴛᴇᴄʜ ᴛᴇᴄʜɴᴏʟᴏɢʏ ɪɴsᴛɪᴛᴜᴛᴇ📲 — tgindex