የደ/መ/ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት
СтатистикаOffical . በደ/መ/ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ት/ቤት ለአባላት እና ለምእመናን መረጃና አጫጭር ትምህርታዊ መልዕክት የሚደርስበት ቻናል ነው። @DebMewiSundayschool መልዕክት ካልዎት በዚህ ያድርሱን @Holies12 ወይም @Barok_12
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 10
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 473
- 1/48двое суток
- 542
- 1/72трое суток
- 584
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtu.be/lHaLt5ZmhMI
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!! “ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም”. ምሳሌ22-6 ሠላም ለእናንተ ውድ የእግዚያብሔር ቤተሰቦች የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ት/ት ቤት ለ2019 የትምህርት ዘመን እድሜያቸው ከ6 ዓመት እስከ 16 ያሉ ህፃናት እና ታዳጊ ልጆችን ለማስተማር ዝግጅት አጠናቋል ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ነገሮች 1.ሥርዓተ ቤተክርስትያን የጠበቀ የቅርብ ጊዜ ሁለት የተማሪ አንድ የወላጅ ፎቶ 2.እድሜ የሚገልፅ ሰርተፍኬት 3.የትምህርት ደረጃ የሚገልፅ ሰርተፍኬት የምዝገባ ቀን 🗓️ከነሐሴ 13-ነሐሴ 30 ብቻ ምዝገባ ቦታ 📍ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በቤተክርስቲያኑ ትምህርት ቤት ⏰ከ10:00-1:30 አድራሻ:-አውቶብስ ተራ (መናህሪያ) ከፍ ብሎ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያኖ
መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተመደቡ። ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ የቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተመድበዋል። በመሆኑም በነገው ዕለት ነሐሴ 8/2018 ዓ/ም በሀገረ ስብከቱ አደራሽ ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ታውቋል። በዚህም የሀገረ ስብከቱ የሥራ ሐላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ በቤተ ከህነት ሥራ አስኪያጆች እንዲሁም የሀገረ ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሠራተኞች በአቀባበሉ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል። #ምንጭ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት/Addis Ababa Diocese Media Service
የደ/መ/ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት pinned a photo
ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ እመቤቱ ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተጸነሽ አይደለም በሕግ ከሐና ከኢያቄብ ተወለድሽ እንጂ። ✨ አባ ሕርያቆስ(ቅዳሴ ማርያም )✨
https://youtu.be/6KXIj1j2U1M
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!! “ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም”. ምሳሌ22-6 ሠላም ለእናንተ ውድ የእግዚያብሔር ቤተሰቦች የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ት/ት ቤት ለ2019 የትምህርት ዘመን እድሜያቸው ከ6 ዓመት እስከ 16 ያሉ ህፃናት እና ታዳጊ ልጆችን ለማስተማር ዝግጅት አጠናቋል ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ነገሮች 1.ሥርዓተ ቤተክርስትያን የጠበቀ የቅርብ ጊዜ ሁለት የተማሪ አንድ የወላጅ ፎቶ 2.እድሜ የሚገልፅ ሰርተፍኬት 3.የትምህርት ደረጃ የሚገልፅ ሰርተፍኬት የምዝገባ ቀን 🗓️ከነሐሴ 13-ነሐሴ 30 ብቻ ምዝገባ ቦታ 📍ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በቤተክርስቲያኑ ትምህርት ቤት ⏰ከ10:00-1:30 አድራሻ:-አውቶብስ ተራ (መናህሪያ) ከፍ ብሎ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያኖ
የደ/መ/ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት pinned a photo
ውድ የቤተ መጽሐፍ ተጠቃሚ በሙሉ የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት ቤተመጽሐፍት ስያሜ ለማውጣት የስም ማሰባሰቢያ ቅጽ አዘጋጅቷል።እርሶም የዚህ መንፈሳዊ ቤተመጽሐፍት የሚሆን ስያሜ ዓላማን እና መንፈሳዊ የሚገልጽ ስም እንድትጠቁሙን በትሕትና እንጋብዛለን። ⭕️ማስታወሻ ➠እባክዎ የሚሰጡት ስያሜ ትርጉም ያለው እና መንፈሳዊ ይዘት ያለው ስያሜ ይጻፉ። ➠ ይህ Link በመጫን ስያሜውን መስጠት ይችላሉ። https://docs.google.com/forms/d/1y7AN3SkWBRhHvnubZZ_RF07alMbYLwB48XRclDa1TaI/viewform ለተጨማሪ ሀሳብ እና አስተያየት +251911352899 +251922963155 +251921348052 +251919043087 ለሚሰጡን አስተያየትዎና ተሳትፎዎ እናመሰግናለን!
ልዩ መንፈሳዊ የኅብረት ጉባዔ " ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው።" መዝ ፻፴፩ ፥፩ 🗓️:- እሁድ ነሐሴ 10 /2018 ዓ.ም ⏰:- ከ 3:45 ሰዓት ጀምሮ 📍፦ በካቴድራሉ ት/ቤቱ አዳራሽ 💒አድራሻ➛አውቶብስ ተራ(መናህሪያ) ከፍ ብሎ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል(አዲሱ ሚካኤል )
መንፈሳዊ የመጽሐፍ ዳሰሳ ⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺ የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ት/ቤት የመጽሐፍ ዳሰሳ አዘጋጅቷል። አንቀጸ ብርሃን ትርጓሜ በመምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ 🗓ረቡዕ ነሐሴ6 /2018ዓ.ም ⏰ ከምሽቱ 12:00ሰዓት ጀምሮ ቦታው:- በፈለገ ዮርዳኖስ አዳራሽ 💒አድራሻ➛አውቶብስ ተራ(መናህሪያ) ከፍ ብሎ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል(አዲሱ ሚካኤል )
без подписи
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ (ጾመ ማርያም) በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን። ''ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኅበኢይበሊ'' ጾመ ፍልሰታ(ጾመ ማርያም ) ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ ተሰደደ፤ ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም 64 ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር 21 ቀን 49 ዓመተ ምሕረት ዐረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡ ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደ ጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤ እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ ክብር ይግባትና የ ማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሡ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡ የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ዐይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ6ኛው ወር ከነሐሴ 1 ቀን እስከ 14 ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ14ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ3ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደ ሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው። እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡ ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤ እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤ እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡ በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ሐዋርያት በመንፈሳዊ ቅናት ተነሳስተው « ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤዋን ዐይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ጀምረው በ16ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ 1 እስከ 15 ቀን ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡ እመቤቴ ማርያም ሆይ፦ ኀዘንን ወደሚረሱበት ትካዜን ወደማያስቡበት የተረጋጋ ፍጹም ደስታ ወዳለበት ለተጓዘው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል መልክአ ፍልሰታ የጾሙ እና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድርገን፤ትንሣኤዋንም ለማየት ያብቃን አሜን
መንፈሳዊ የመጽሐፍ ዳሰሳ ⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺⁺ የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ት/ቤት የመጽሐፍ ዳሰሳ አዘጋጅቷል። አንቀጸ ብርሃን ትርጓሜ በመምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ 🗓ረቡዕ ነሐሴ6 /2018ዓ.ም ⏰ ከምሽቱ 12:00ሰዓት ጀምሮ ቦታው:- በፈለገ ዮርዳኖስ ቤተ መጽሐፍ 💒አድራሻ➛አውቶብስ ተራ(መናህሪያ) ከፍ ብሎ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል(አዲሱ ሚካኤል )
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
без подписи
без подписи
без подписи
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት "ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል።" መዝሙር ፷፭÷፪ የጾመ ፍልሰታ የጸሎት መርሐ ግብር በየዕለቱ 👉 ውዳሴ ማርያም 👉 መዝሙረ ዳዊት (ለዕለቱ የተመረጠው) 👉 መሐረነ አብ 👉እንዚራ ስብሐት ይደርሳል። 🗓️ከነሐሴ 1 - 16 /2018ዓ.ም ⏰ምሽት 12:00 ጀምሮ 💒በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ