Southwest Communications
Статистикаhttps://www.facebook.com/sowestcommunication?mibextid=ZbWKwL www.southwestcomunications.gov.et
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 110
- Тип
- открытый
- Язык
- французский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 440
- 1/48двое суток
- 504
- 1/72трое суток
- 543
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ክልላዊ የአንድ ጀምበር መኖ ተከላ መርሃ-ግብር በይፋ ተጀመረ ክልላዊ የአንድ ጀምበር መኖ ተከላ መርሃ-ግብር በካፋ ዞን ጊንቦ ወረዳ ቴጲቡቲ ቀበሌ በሚገኘው የግደር ማባዣ ማዕከል በይፋ ተጀምሯል። "የተሻለ መኖ ልማት ለላቀ የእንሰሳት ምርትና ምርታማነት"በሚል መርህ ቃል በተጀመረው የክረምት መኖ ተከላ ዘመቻ መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ግብርና ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የክልሉ ግብርና ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዮሀንስ መላኩ ባደረጉት ንግግር፣ መንግስት በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ከጀመራቸው ተግባራት ውስጥ የእንሰሳት ዘርፉን ማዘመን በመሆኑ በክልሉ የእንስሳት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ ዝሪያ ያላቸው ግደረሮችን ማቅረብ እና የእንስሳት መኖ ምርትን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው ለመኖ ልማት ውጤታማነት ደግሞ አቅጣጫ በማስቀመጥ እየተሰራ እንዳለም ተናግረዋል። የቢሮው ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታመነ በቀለ በጊንቦ ወረዳ ቴጲቡቲ ቀበሌ የሚገኘው የግደር ማባዣ ማዕከል የተሻሻሉ የጊደር ዝሪያዎችን ለማባዛትና ለማሰራጨት የሚረዳ መሆኑን ጠቅሰው ማዕከሉን ስራ ለማስጀመር ከሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል መኖ አንዱ በመሆኑ በዛሬው ዕለት 1.5 ሄክታር ላይ ተከላ መከናወኑን ገልጸዋል። በዛሬው ዕለት በሚኖረው ዘመቻ 3ሺህ 500 ሄክታር መሬት የሚሸፈን ሲሆን ለ2 ሳምንታት በሚካሄደው ዘመቻ በአጠቃላይ 10ሺህ ሄክታር በተለያዩ የመኖ ዓይነቶች ይሸፈናል ብለዋል። ተከላው ሁሉንም የወተትና የቀይ ሥጋ መንደሮችን ትኩረት አድርጎ የሚከናወን መሆኑን ጠቁመው የመኖ ልማት ዘመቻው በተቀመጠው ዕቅድና አቅጣጫ መሠረት እንዲከናወን ሁሉም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የተሰማሩ ፕሮጀክትና ፕሮግራሞች እንዲሁም በእርባታ ሥራ የተሰማሩ አርቢዎች አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያበረክቱም አስገንዝበዋል፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊና የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ በበኩላቸው በቀበሌው የተጀመረው የተሞክሮ ማዕከል ለአካባቢው ማህበረሰብ የተሻለ ተሞክሮዎችን ለማግኘት እና የተለያዩ የመኖ ዝሪያዎችን በቅርበት አግኝተው ለማባዛት የሚረዳ በመሆኑ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል። በካሳሁን አሰፋ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇 📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/ 📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et 📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications 📌በትዊተር twitter.com/sweprs 📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi 📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab 📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication 📌በዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x 📌በሊንክደን https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/ 📌በትሬድስ https://www.threads.com/@southwest_communications 📌በብሉ ስካይ https://bsky.app/profile/swc79..bsky.social በደብልው ኤን ሶሻል https://wnsocial.com/page/16775
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በምርጫ ማግስት በክልሉ ጠንካራ የተቋም ግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል - አቶ ፍቅሬ አማን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በምርጫ ማግስት "ከአሸናፊነት ወደ አገልጋይነት" በሚል መርህ ሀሳብ እየተከናወነ የነበረውን ድጋፋዊ ክትትልና ግብረመልስ በቦንጋ ከተማ በመገምገም ላይ ይገኛል። የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በመድረኩ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ከምርጫ ማግስት ጀምሮ በክልሉ መጠነ-ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። አቶ ፍቅሬ ፤ ከምርጫው ማግስት ጀምሮ አመራርን፣ አባላትን፣ ደጋፊዎችንና መላው ሕዝቡን በማስተባበር በመደበኛና በንቅናቄ የሚከናወኑ አጀንዳዎችን በላቀ ውጤታማነት ለማሳካት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሠራ መቆየቱን አስረድተዋል። ለወራት ወደ ታቸኛው መዋቅር በተደረገው ድጋፋዊ ክትትል የተቋም ግንባታ ሥራዎች ያሉበት ደረጃ በዝርዝር እንደሚገመገም ነው አቶ ፍቅሬ የጠቆሙት። በዚህም በክልሉ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የሞዴል ገጠር መንደር እና የፓርቲ ቢሮ ሕንፃ ግንባታዎችን እና ተያያዥ አጀንዳዎችን በየደረጃው ያለው አመራር በመቀናጀት በተሻለ ሁኔታ እየፈጸመ እንደሚገኝ አብራርተዋል። መድረኩ ዝርዝር የተቋም ግንባታ ፣ የኢንሼቲቭ እና መደበኛ ተግባራት ያለበት ደረጃ ሪፖርት በመገምገም፣ በቀጣይ በሚከናወኑ የጋራ ግቦች ላይ አቅጣጫዎችን እንደሚቀመጥ ተገልጿል። በግምገማ መድረኩ የክልል ደጋፊ አመራሮች እና የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እየተሳተፉ ስሆን የዞኖች አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ሉዓላዊነትን ከማስከበር እስከ ልማት አጋርነት የማይናወጠው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገራዊ አደራ የዓለም ሥልጣኔ ቀደምት የነበረችው ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ገናናነቷና ታላቅነቷ ተመልሳ ማየት የሠራዊቱ ልባዊ መሻት መሆኑን በማንገብ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን እናት ሀገሩን ከማንኛውም የጥፋት ቀስት በጽናትና በጀግንነት እየጠበቀ ይገኛል። ሠራዊቱ ምንም ዓይነት ምድራዊ ፈተና ሳይበግረው የሀገራችንን ገጽታ ለመገንባትና ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ እንደ ሀገር በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ ከሕዝብ ጋር እኩል እየተሳተፈ ነው። የሞራልና የብርታት ምንጩ የሆነውን ሕዝብ በውል ያስቀደመው ይህ ሠራዊት፣ የሀገር ዕድገት ወሳኝ መሠረተ ልማቶች በጥፋት ኃይሎች እንዳይወድሙ እንደ ዓይኑ ብሌን ነቅቶ በመጠበቅ በየጊዜው በሚመዘገበው ሀገራዊ ለውጥ ላይ የበኩሉን ደማቅ አሻራ እያሳረፈ ይገኛል። ለኢትዮጵያ ዕድገትና ለሕዝቡ ነፃነት መሰናክል የሚሆኑ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በጀግንነት ተፋልሞ በማክሸፍ የልማትን መንገድ እየጠረገ የሚገኘው መከላከያ ሠራዊቱ፣ የኢትዮጵያን ስምና ክብር አስጠብቆ ለመዝለቅ መክፈል የሚጠበቅበትን ውድ ዋጋ ሁሉ ያለ አንዳች ስስት እየከፈለ ነው። እናት ሀገሩን ከአንድ ራሱና ነፍሱ አስበልጦ የሚመክተው ይህ ቆራጥ የሕዝብ ልጅ፣ ከምሥረታው አንስቶ የሀገሩን ሉዓላዊነት በደሙ አንጽቶ ዳር ድንበሯን በአጥንቱ ፍላጻ እየማገረ ታሪክ ሠርቷል። ከጅምሩ ሀገር ለመጠበቅ የተደራጀው ሕዝቡን መስሎ በመሆኑ፣ ይህ የተላበሰው ሕብረ ብሔራዊ ገጽታ እና ከየትኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ ጽኑ የሀገር ፍቅር ስሜት ጠላቶቹን ድል የሚነሳበት አስተማማኝ ትጥቁ ሆኗል። በጥንት ዘመናት በሀገሩ የመጣበትን ጠላት በአይበገሬነት ድባቅ የመታው የኢትዮጵያ ወታደር፣ ዛሬ ላይ በወታደራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ወደ ሥልጣኔ ማማ እየገሰገሰ ዘመኑን በሚገባ ዋጅቷል። ከግዳጁ ጎን ለጎንም ለትውልድ ግንባታና ለሀገር አረንጓዴ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እያረጋገጠ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል በያዘችው ብሔራዊ ዕቅድ ከሕዝቡ ጋር በተቀናጀ መልኩ ያከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የዚሁ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው። ከዚህም አልፎ "የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን መፍትሔ የማስገኘት" መርህን በመከተል በቀጠናው የሰላም ዋስትና መሆኑን ያስመሰከረው ሠራዊታችን፣ በአሁኑ ወቅት በደረሰበት የላቀ የዝግጁነት ደረጃ እና በታጠቀው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለየትኛውም ትንኮሳ ተመጣጣኝ ምላሽ ለመስጠት በተሟላ ቁመና ላይ ይገኛል። በቴክኖሎጂ፣ በሰለጠነ የሰው ኃይል እና በጠንካራ አመራር የተገነባው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የማይናወጥ የሀገር ሉዓላዊነት ዓምድ እና እውነተኛ የሕዝብ አለኝታ መሆኑን በሁለንተናዊ ስኬቶቹ በተግባር አረጋግጧል። #EBC
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መርጠው ወደ ኅብረተሰቡ እየተቀላቀሉ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች የያዙት የትጥቅ ትግል በጫካ ውስጥ ተደብቆ ንፁሃንን ከመግደል እና ከመዝረፍ የዘለለ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ግብ የሌለው መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ጦርነት እና ግጭት አውዳሚ መሆናቸውን በመገንዘብ በየዕለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መርጠው ወደ ኅብረተሰቡ እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። መንግሥት ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት ያለው ቁርጠኝነት አሁንም ያልተለወጠ መሆኑን ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ማንኛውም አካል በሰላማዊ መንገድ ሀሳቡን ይዞ ለመታገል እስከፈለገ ድረስ የመንግሥት የሰላም በር መቼም ቢሆን እንደማይዘጋ አስገንዝበዋል። የኦሮሞን ሕዝብ ትግል በዋናነት የጀመሩ እና ያደራጁ አንጋፋ ፖለቲከኞች በአሁኑ ወቅት ሀገር ቤት ገብተው በፓርላማ እና በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ላይ በሰላም እየተሳተፉ መሆናቸውን አብራርተዋል። በአንፃሩም፣ አሁን የትጥቅ ትግሉን ከሚመሩት አካላት ጀርባ ያለውን ተቃርኖ አንስተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁን ላይ በጫካ ውስጥ የሚገኙት ኃይሎች የማንን አጀንዳ እያስፈፀሙ እንደሆነ ሕዝቡና ወጣቱ ቆም ብሎ ሊጠይቅ እንደሚገባ አሳስበዋል። ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በጠመንጃ ኃይል ሊገነባ እንደማይችል ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ብልፅግና ፓርቲ በብቁ ሀሳብ እና በአሸናፊ ፖለቲካ ላይ የተመሠረተ እንጂ በዘር ላይ የተንጠለጠለ አደረጃጀት አለመሆኑን አብራርተዋል። የትኛውም የፖለቲካ ቡድን ፍላጎቱን ማሳካት የሚችለው ሕዝብን አሳምኖ በምርጫ ሲያሸንፍ ብቻ መሆኑን በአፅንዖት ተናግረዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
መነጋገራችን፣ መመካከራችንና መደማመጣችን ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የመግባባት ምዕራፍ ያሻግራል!፦ ተመካካሪዎች መነጋገራችን፣ መመካከራችንና መደማመጣችን ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የመግባባት ምዕራፍ ያሻግራታል ሲሉ የዳያስፖራ ማህበረሰብና የሲቪል ማህበረሰብ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተመካካሪዎች ጉባኤው አካታች፣ ሀሳብን በነፃነት የሚገልጹበትና ለዘላቂ ሰላም መሠረት የሚጥል መሆኑን ገልጸዋል። የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የዳያስፓራ ማህበረሰብ ወኪል ተመካካሪ አቶ ልዑልሰገድ አበበ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በምክክሩ የሀሳብ ልዩነቶች በንግግርና በመደማመጥ ወደ የጋራ መግባባት እየተቃረቡ ነው። ከጉባኤው የሚፈልቀው የጋራ ሀሳብም በአንዳንድ አካባቢዎች ለግጭት መንስኤ የሆኑ ልዩነቶችን በመፍታት ለቀጣዩ ትውልድ ሰላምን ማስረከብ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ሌላው ተመካካሪ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ወኪል ተማካካሪ ጌትነት ለማ፤ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ከትንንሽ የውይይት ቡድኖች ጀምሮ በከፍተኛ መደማመጥና በአካታች አሠራር እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ እንደዚህ ዓይነት ዕድል አግኝተው እንደማያውቁ ጠቁመው፤ ምክክሩ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ህብረት እንደሚያመጣ ተናግረዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ወኪል ተመካካሪ ደሳለኝ ክፍሉ በበኩላቸው፤ የምክክር ጉባኤው ሀሳብ በነፃነት የሚንሸራሸርበትና ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የጋራ መግባባት የሚያሻግር መሆኑን ገልጸዋል። ምክክሩ ለቀጣዩ ትውልድ ሰላማዊ፣ የተረጋጋችና የተባበረች ሀገር ማስረከብ የሚያስችሉ የጋራ ሀሳቦች የሚፈልቁበት መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል። #EBC
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የኦዲት ሥርዓቱን የበለጠ ውጤታማና ተጠያቂ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላሉ– የክልሉ ዋና ኦዲተር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የክልሉን የኦዲት ሥርዓት የበለጠ ውጤታማ፣ ግልጽና ተጠያቂ ለማድረግ የባለሙያዎች አቅም ግንባታ ሥራዎችን በቀጣይነት እንደሚያጠናክር አስታውቋል። መሥሪያ ቤቱ የመንግሥት ተቋማት የፋይናንስ ሥርዓትን ማጠናከር፣ የሀብትና ንብረት አጠቃቀም በሕግና በሥርዓት መሠረት መሆኑን ማረጋገጥ እና የሕዝብ ሀብት ለታቀደለት ዓላማ መዋሉን መከታተል እንደ ዋና ተልዕኮዎቹ መሆኑን ገልጿል። በዚህ መሠረት የኦዲተሮችን ሙያዊ ብቃት ማጎልበት፣ የኦዲት አሠራሮችን ማዘመን እና የተቋሙን የአፈጻጸም አቅም ማሻሻል ላይ ትኩረት መደረጉ ተጠቅሷል። በቅርቡ በተሻሻለው የፋይናንሻልና የህጋዊነት ኦዲት ማኑዋል ዙሪያ ለኦዲተሮች የተሰጠው የሁለት ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና የእነዚህ ጥረቶች አካል ሲሆን፣ ተሳታፊዎች ከዘመናዊ የኦዲት መስፈርቶች ጋር ተጣጥመው እንዲሰሩ እድል ፈጥሯል። በስልጠናው መዝጊያ ላይ የተገኙት የመሥሪያ ቤቱ ዋና ኦዲተር አቶ አስራት አበበ ኦዲተሮች በሙያዊ ነፃነት፣ በታማኝነትና በተጠያቂነት ስራቸውን እንዲፈጽሙ አሳስበው፣ በስልጠናው የተገኘው እውቀት በተግባር ሲውል የኦዲት ጥራት እንደሚሻሻል ገልጸዋል። የመሥሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ኦዲተር አቶ አሸናፊ ንጉሴ በበኩላቸው የ2025 የኦዲት ማኑዋል የፋይናንሻልና የህጋዊነት ኦዲትን በወጥነትና በሙያዊ ጥራት ለማከናወን የሚያግዝ ጠቃሚ መመሪያ መሆኑን ገልጸዋል። የፋይናንሻልና የህጋዊነት ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ሰይፉ አለሙ በበኩላቸው ስልጠናው በአዲሱ ማኑዋል የተካተቱ ለውጦችን በአንድ ግንዛቤ እንዲተገበሩ መሠረት እንደሚጥል እና የኦዲት ሂደቶችን ከአገራዊና ከዓለም አቀፍ መስፈርቶች ጋር በማጣጣም የኦዲት ጥራትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ገልጸዋል። በስልጠናው የተሳተፉ ኦዲተሮችም ያገኙትን ክህሎት በዕለታዊ ሥራቸው ላይ በመተግበር የፋይናንስ አስተዳደር ግልጽ፣ ተጠያቂና ውጤታማ እንዲሆን የራሳቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልጸዋል። በአጠቃላይ የኦዲት ሥርዓቱን ዘመናዊ፣ ውጤታማና ተጠያቂ በማድረግ የመንግሥት ሀብትን መጠበቅ፣ የፋይናንስ ሥርዓትን ማጠናከር፣ የልማት ፕሮግራሞችን ውጤታማነት ማሳደግ እና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የተቋሙ ቀጣይ ትኩረት እንደሚሆን ተገልጿል። በተከተል ወ/ሚካኤል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇 📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/ 📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et 📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications 📌በትዊተር twitter.com/sweprs 📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi 📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab 📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication 📌በዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x 📌በሊንክደን https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/ 📌በትሬድስ https://www.threads.com/@southwest_communications 📌በብሉ ስካይ https://bsky.app/profile/swc79..bsky.social በደብልው ኤን ሶሻል https://wnsocial.com/page/16775
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም አቀፍ የጂኦ-ፖለቲካ ትንታኔ መሠረት፣ የባሕር በር ከንግድ ማስተላለፊያነት ባለፈ የብሔራዊ ሉዓላዊነት፣ የደህንነት እና የጂኦ-ስትራቴጂካዊ የበላይነት ቁልፍ መሠረት ሆኗል። ዛሬ ላይ የዓለም ኃያላን አገራት የፖለቲካ ጡንቻ እና የተፅዕኖ አቅም የሚለካው፣ የሎጂስቲክስ ሉዓላዊነታቸውን በማስጠበቅ እና ስትራቴጂካዊ የባሕር ላይ ንግድ መስመሮችን በመቆጣጠር ረገድ ባላቸው ኃይል ነው። ወደብ የሌላት አገር የሎጂስቲክስ ነፃነቷ በከፍተኛ ደረጃ የተገደበ በመሆኑ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነቷ ሁልጊዜም ቢሆን በጎረቤቶቿ በጎ ፈቃድ ላይ የተንጠለጠለ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ ብሔራዊ ደህንነትን በቀላሉ አደጋ ላይ የሚጥል ክስተት ነው። ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ስንቃኝ፣ ሰፊ የባሕር በር ባለቤትነት ለኃያላኑ አገራት የሉዓላዊነት ክብር እና የኃይል ማሳያ ሆኖ እናገኘዋለን። ለአብነት ያህል አሜሪካን ብንወስድ፣ የዓለምን ጂኦ-ፖለቲካዊ ሥርዓት የምትዘውረው በሁለቱ ውቅያኖሶች ማለትም በአትላንቲክና በፓሲፊክ ላይ ባላት ሰፊ የባሕር ዳርቻ እና እንደ ሎስ አንጀለስ፣ ሎንግ ቢች በመሳሰሉት ግዙፍ ወደቦቿ አማካኝነት ነው። አሜሪካ ዘመናዊ የባሕር ኃይሏን (Blue-water Navy) በመጠቀም የራሷን የሎጂስቲክስ መስመር ከማስጠበቅ እና የሺፒንግ መስተጓጎልን ከመከላከል አልፋ፣ በሌሎች አገራት ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ የመጣልና የንግድ እገዳ የማድረግ ጂኦ-ፖለቲካዊ ተፅዕኖ መፍጠር ችላለች። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ቻይና የዓለም ሁለተኛዋ የኢኮኖሚ ሞተር ለመሆን የቻለችው በሻንጋይ፣ ሼንዘንና ኒንግቦ በመሳሰሉት ግዙፍ ወደቦቿ አማካኝነት አምራች ኢንዱስትሪዎቿን ከዓለም ገበያ ጋር በቀጥታ በማስተሳሰር ነው። ከዚህም ባለፈ ቻይና የውጭ ኃይሎች በሎጂስቲክስ መስመሯ ላይ ሊፈጥሩ የሚችሉትን ማነቆ ለመከላከል "የዕንቁዎች ድርድር" (String of Pearls) በተሰኘው ጥልቅ የደህንነት ስትራቴጂዋ በህንድ ውቅያኖስና በቀይ ባሕር አካባቢ ወደቦችን መገንባትና የባሕር ኃይል ሠፈሮችን ማቋቋም ችላለች። ይህ ተግባር የወደብ ባለቤትነት እና የባሕር መስመር ደህንነት ለዘመናዊ ሉዓላዊነትና ለኢኮኖሚ ማስፋፋት ያለውን ወሳኝነት በግልፅ የሚያሳይ ሕያው ዳታ ነው። ወደብ ያላቸው አገራት በጦርነትም ሆነ በሰላም ጊዜ የራሳቸውን የንግድ መርከቦች በማንቀሳቀስ፣ የገቢና ወጪ ንግዶቻቸውን ከማንኛውም ጂኦ-ፖለቲካዊ መስተጓጎል ይታደጋሉ። ይህ "የሎጂስቲክስ ሉዓላዊነት" የውጭ ኃይሎች በውስጥ የፖለቲካ ውሳኔ ላይ ጫና እንዳያሳድሩ እንደ ትልቅ የብሔራዊ ደህንነት ጋሻ ያገለግላል። የባሕር በር ማጣት ግን አገራትን ለጂኦ-ፖለቲካዊ መታገቻነት በማጋለጥ ለውጭ ፖለቲካዊ ጫና በቀላሉ እንዲንበረከኩ ያደርጋቸዋል። ይህንን ዓለም አቀፋዊ ሐቅ ይዘን ወደ አገራችን ስንመጣ፣ የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የቅንጦት ጥያቄ ሳይሆን አንገብጋቢ የህልውና ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት፣ በአፍሪካ ቀንድ እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነ ቀጠና የምትገኝና ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እያስመዘገበች ያለች አገር፣ የሎጂስቲክስ ሉዓላዊነቷ በሌሎች አገራት ወደቦች ላይ መቶ በመቶ ጥገኛ መሆኑ ታላቅ የደህንነት ስጋት ነው። በመረጃ ላይ የተመሠረቱ ትንታኔዎች እንደሚያሳዩት፣ የኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆነው የገቢና ወጪ ንግድ በአንድ የወደብ መስመር ላይ ብቻ የተንጠለጠለ መሆኑ፣ አገሪቱን ለማንኛውም የውጭ ፖለቲካዊ ጫና እና የሎጂስቲክስ መቆራረጥ እጅግ ተጋላጭ ያደርጋታል። ለወደብ ኪራይና ለትራንዚት በየዓመቱ የሚወጣው በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚፈታተን ማነቆ ነው። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሙሉ እና የማይደፈር የሚሆነው፣ አገሪቱ ከውጭ የምታስገባቸውን ቁልፍ ሸቀጦች (ነዳጅ፣ ማዳበሪያ፣ መድኃኒትና የጦር መሣሪያዎችን ጨምሮ) እንዲሁም ወደ ውጭ የምትልካቸውን የእርሻና የኢንዱስትሪ ምርቶች ያለ ምንም የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት፣ ክልከላና የፖለቲካ ጫና ማስተላለፍ ስትችል ብቻ ነው። የባሕር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ነፃነቷን ከመጠበቅ ባሻገር፣ የቀጠናውን የኃይል ሚዛን እንድታስጠብቅ፣ የባሕር ኃይሏን መልሳ በማቋቋም ብሔራዊ ደህንነቷን ከውጭ ትንኮሳ እንድትከላከል እና የዓለም አቀፍ ንግድ ተወዳዳሪነቷን እንድታሳድግ ያስችላታል። በዛሬው እጅግ ተለዋዋጭና ፉክክር በበዛበት የዓለም የጂኦ-ፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ፣ እውነተኛ ሉዓላዊነት ማለት ድንበርን በጦር መሣሪያ ከመጠበቅ ባሻገር ዘላቂ የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ነፃነትን በተግባር ማረጋገጥ ማለት ነው። አሜሪካ፣ ቻይና እና ሌሎችም በኢኮኖሚ የበለፀጉ አገራት በሰፊ የባሕር በሮቻቸው አማካኝነት የሉዓላዊነት ክብራቸውን፣ የንግድ መስመራቸውንና ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸውን እንዳስጠበቁት ሁሉ፤ ኢትዮጵያም ዘላቂ ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን፣ የደህንነት ዋስትናዋን እና ታሪካዊ የጂኦ-ፖለቲካ ክብሯን ለማስቀጠል የራሷ የሆነ የባሕር በር ባለቤት መሆኗ ታሪካዊ፣ ሞራላዊና ፖለቲካዊ ግዴታ ነው። ይህ እውን ሲሆን ብቻ የሎጂስቲክስ ሉዓላዊነቷ ይረጋገጣል። #EBC በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇 📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/ 📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et 📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications 📌በትዊተር twitter.com/sweprs 📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi 📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab 📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication 📌በዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x 📌በሊንክደን https://www.linkedin.com/company/southwest-communications/ 📌በትሬድስ https://www.threads.com/@southwest_communications 📌በብሉ ስካይ https://bsky.app/profile/swc79..bsky.social በደብልው ኤን ሶሻል https://wnsocial.com/page/16775
видео или голосовое, без подписи