- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 864
- 1/48двое суток
- 990
- 1/72трое суток
- 1 067
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የጸረ ሙስና ትግሉ የሕዝብና የመንግሥት ቋሚ አጀንዳ ሆኖ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ ---------------- (ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 8 ፣ 2018 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ በኢትዮጵያ የፀረ ሙስና ትግል የሕዝብና የመንግሥት ዘላቂና ዋና አጀንዳ ሆኖ መቀጠል አለበት አሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ። የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል ማጠቃለያ መድረክ "የፀረ ሙስና ትግል ትናንት፣ ዛሬና ነገ"በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው፡፡ ም/አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ ዛሬ የምናከብረው የጸረ ሙስና ትግል ያለፈውን ለመዘከር ብቻ ሳይሆን፣ ያለንበትን ለመገምገምና ወደፊት የምንመራበትን አቅጣጫ ለመወሰን የሚያስችለን ነው። በሀገራዊ ምክክሩ ዋና ዋና መወያያ ነጥቦች መካከል ሙስና እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች በግንባር ቀደምትነት የተቀመጠ አጀንዳ መሆኑን አንስተው የፀረሙስና ትግሉ የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የመላው ህዝብ የጋራ ሀገራዊ ህልውና ጉዳይ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብለዋል። እነዚህ ሶስት መሰረቶች የፀረ-ሙስና ትግሉ የማዕዘን ድንጋዮች ሆነው አሁንም ያገለግላሉ ሲሉ አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት መንግሥት ሙስናን ለመታገል ዘመናዊ እና መዋቅራዊ የሪፎርም ስራዎችን በስፋት እየተገበረ እንደሚገኝ ጠቁመው በተለይም ሀገራዊ የጥቆማ መቀበያ ሥርዓት፣ የዜጎችን ድምፅ ያለስጋት እንዲሰማ አድርጓል ብለዋል። ዲጂታል የሀብት ማሳወቂያ እና ማስመዘገቢያ ሥርዓት ደግሞ የመንግሥት ተቋማት አመራር እና ሰራተኞች ሀብት ለህዝብ ግልጽ ማድረጉን አመልክተዋል፡፡ በመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎትና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) የተደገፉ አሰራሮች ሌብነትን በቴክኖሎጂ አቅም የሚያጋልጡ አዲስ የትግል ምዕራፎች መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡ ሙስና የገንዘብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሥነ-ምግባር፣ የሞራል፣ የአስተዳደር፣ የፍትሕ፣ የልማት፣ የሀገር እና የትውልድ ግንባታ ጉዳይ በመሆኑ ሁሌም ቋሚ የሕዝብና የመንግሥት አጀንዳ ሆኖ ሊቀጥል እንደሚገባም የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ አስገንዝበዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
መንግሥት የፈጠራቸውን መልካም ዕድሎች በመጠቀም ብልሹ አሰራሮችን መዋጋት እንደሚገባ ተገለፀ ---------------------- (ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 08 ፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ መንግሥት የፈጠራቸውን መልካም እድሎች በመጠቀም ለሀገር ልማት በጋራ መትጋትና ብልሹ አሰራሮችንም መዋጋት ይገባል ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ እውነቱ አለነ ገለጹ። የተከበሩ አቶ እውነቱ አለነ ይህን የገለፁት የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል ማጠቃለያ መድረክ "የፀረ ሙስና ትግል ትናንት ዛሬ እና ነገ በሚል መሪ ሀሳብ" በአዳማ በተካሄደ መድረክ ላይ ነው። በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ እውነቱ አለነ፤ የሙስና ትግል የመጀመሪያ ምዕራፍ መከላከልን፣ ምርመራንና ክስን በአንድ ተቋም በማድረግ ይሰራ እንደነበር አስታውሰዋል። ሆኖም እንቅስቃሴው ህዝብን የትግሉ ባለቤት ያላደረገ የሙስና መከላከል ስራን የረሳና ለትውልድ የስነ-ምግባር ግንባታ ቦታ የማይሰጥ ነበር ብለዋል። በሁለተኛው ምዕራፍ፣ ከሚሊኒየሙ መባቻ ጀምሮ ለውጡ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ የነበረው ወቅት በልማታዊ መንግሥት ስም ከፍተኛ ጣልቃገብነት የተካሄደበት እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋበት እንደነበር አንስተዋል። በዚህም ምክንያት የህዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ ሜጋ የመንግሥት ፕሮጀክቶች በሙስና እና በሌብነት ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው እንደነበር ተናግረዋል። በሶስተኛው ምዕራፍ፣ ማለትም ከሀገራዊ ለውጡ መባቻ ጀምሮ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ከሙስና ትግል አኳያ መሰረታዊ ለውጥ መደረጉን ገልጸዋል። በኮሚሽኑ ላይ ከተደረጉት ማሻሻያዎች መካከል ዋነኛው የህግ ሪፎርም መሆኑን አንስተው፤ ሙስናን በአንድ ተቋም ብቻ መታገል ስለማይቻል ሁሉም የመንግሥት ተቋማት የትግሉ ባለቤት እንዲሆኑ መደረጉን አብራርተዋል። በሶስቱም የመንግሥት አካላት መካከል ጥብቅ የመረጃ ቅብብሎሽ፣ ጠንካራ ትስስር እና ቅንጅት እንዲፈጠር የሚያስችል ለውጥ ተደርጓልም ነው ያሉት። ይህም ስርዓታዊ እና መንግሥታዊ ሙስና መሰረት እንዳይኖረውና እንዳይፈጠር ለማድረግ የሚያስችል የሚያበረታታ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የታየበት መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የዲጂታላይዜሽንን መልካም እድሎች በመጠቀም አገልግሎቶችን ከሰው ንክኪ ነፃ እና አካታች በሆነ መንገድ ማቅረብ መቻሉ፣ መሰረታዊ የእሳቤ ለውጥ ማምጣቱንና ለፀረ-ሙስና ትግሉ ጠንካራ መሰረት እየጣለ እንደሚገኝ አክለው ጠቁመዋል። በመሆኑም የተጀመሩ አዎንታዊ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል፣ በመጪው ጊዜም ያልተቋረጠና የተቀናጀ የሙስና ትግል ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል ኢዜአ መዘገቡን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
ኢትዮጵያ እና የሳውዲ አረቢያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸው ግንኙነት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ ------------------- (ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 5፣ 2018ዓ.ም፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት የሳውዲ አረቢያ ቱሪስት አስጎብኚ ቡድንን ተቀብሎ አወያይቷል። በዚህ ወቅት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ኖጎ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያ በተለያዩ ዘርፎች የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ያለቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸው፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ ያላቸው መልካም ግንኙነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። የቱሪዝም መዳረሻዎች በተሻለ ሁኔታ እየለሙ መሆናቸውንና መሰረተ ልማቶችም ተሟልተው ለጎብኝዎች ምቹ መሆናቸውን የገለጹት የተከበሩ ዲማ(ዶ/ር)፤ ዘርፉን ይበልጥ በማሳደግ የሁለቱን ሀገራት ግንኙት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል። የሳውዲ አረቢያ ቱሪስት ቡድን አባልና የሶሻል መዲያ ባለሙያ አቶ አሊ ዳውድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያ የጠበቀ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፤ ሁለቱን ሀገራት በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ግንኙት ለማሳደግ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑንም በጉብኝታቸው ማረጋገጥ እንደቻሉ ጠቁመዋል። የሳውዲ አረቢያ ቱሪስተ ቡድን አባልና የጂቡቲ አየር መንገድ ማናጀር አቶ አሊድ አሊ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራች እንደሆነ መገንዘባቸውን ገልጸው፤ ለዓብነትም የአዲስ አበባ መዝናኛ ፓርኮች እና ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎቹ በፍጥነት እየለሙ መሆናቸውን አንስተዋል። የቡድኑ አባልና የትረስት ትራቭል መስራች ሊና መሐመድ በበኩላቸው በቱሪዝም ዘርፉ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ያሏትን የቱሪስት መስህቦች እና ታሪካዊ ቅርሶች በዓለም እንዲታወቁ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል። (በ ተስፋሁን ዋልተንጉስ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
ምክር ቤቱ ማህበራዊ ትስስሮችን የማጠናከር ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ ----------------------- (ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 3፣ 2018 ዓ.ም፤ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበራዊ ትስስሮችን የማጠናከር ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ምክር ቤቱ በክረምት በጎ ስራ በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን፣ ዳዬ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች የስብዕና ግንባታና ማነቃቂያ ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናውን የሰጡት የተከበሩ ከበደ ገነቲ (ዶ/ር) ወጣቶች ሰብአዊ ሀብቶች፣ የለውጥ ዋና ተዋናዮች፣ ለዲሞክራሲ ግንባታ ወሳኝ ሞተሮች፣ ሀገር ጠባቂዎች፣ የባህል አምባሳደሮች፣ የማህበረሰብ ልማት በጎ ፈቃደኞች፣ የዘላቂ ልማት ግቦች አስፈፃሚዎች ናቸው ሲሉ ገልፀዋል። ይህም ሆኖ ወጣትነት ሀገርን የመረከብ ትልቅ ኃላፊነትን እና ጠንካራ ዝግጅትን የሚጠይቅ ነው፤ ስለሆነም በቀጣይ ረዥም ህይወትን ለመኖርና ችግሮችን ለማሸነፍ ያለውን እምቅ አቅም መጠቀም እንዳለበትም አብራርተዋል። ወጣቱ ይህን እምቅ ሀይሉን አንዳንድ አፍራሽ ሀይሎች ለተሳሳተ ዓላማ እንዳይጠቀሙበትም የመንግስትን እና የህዝብን ትክክለኛ መንገድ በአግባቡ ተረድቶ በአቋሙ ፀንቶ መቆም እንዳለበትም አሳስበዋል። ስለሆነም ወጣቶች የተሻለ ህይወትን ለመምራትና የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነትና ግዴታን ለመወጣት ጊዜያቸውን በንባብ ማሳለፍ እና በስራ እና በስራ ፈጠራ መቀየር እንዳለባቸውም ነው የተከበሩ ከበደ ገነቲ (ዶ/ር) ያስገነዘቡት። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ የተመራ የፓርላማ ቡድን የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሄደ ------------------ (ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 3፣ 2018 ዓ.ም፤ ሲዳማ ዳዬ፤ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የተመራው የፓርላማ ቡድን በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን፣ በዳዬ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሂዷል። በመርሀ-ግብሩ ላይም የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ እንደተናገሩት ዛሬ የምንተክላቸው ችግኞች ለአካባቢ ጥበቃ ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ ለውሀና አፈር ጥበቃ የሚያግዙ እና ለቀጣይ ትውልድ የምናስተላልፋቸው ውድ ሀብት ናቸው ሲሉ ገልፀዋል። የተተከሉት ችግኞች ለመድሐኒትና ለምግብነት የሚውሉ ናቸው ያሉት የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ የአረንጓዴ አሻራ ስራ በመንግስት እና ክረምትን ብቻ ጠብቆ የሚሰራ ሳይሆን እያንዳንዱ ዜጋ የተተከሉ ችግኞችን ሁልጊዜ የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን አስገንዝበዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
ምክር ቤቱ ለአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት የሚውል የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ ------------------ (ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 2፣ 2018 ዓ.ም፤ ሲዳማ ዳዬ፤ የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ዞን፣ ዳዬ ከተማ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት መርሀ-ግብር አካሄደ። በመርሀ-ግብሩ ላይ ምክር ቤቱ ለአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት የሚውል አስር ሚሊየን ብር (10,000 000) ድጋፍ አድርጓል። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የበጎ አድራጎት ስራን በመከተል ምክር ቤቱ በየአመቱ እየተገበረ እንደሚገኝ እና እስካሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ስራ መከናወኑን አስታውሰዋል። የአቅመ ደካማዎችን ቤት ማደስ እርስ በርስ የመረዳዳት ባህልን እና የእርስ በርስ ትስስርን ከማጠናከሩም ባሻገር አንድ ቤትን ማደስ የአንድን ቤተሰብ ተስፋ ማደስ ጭምር መሆኑንም አስገንዝበዋል። ምክር ቤቱ ለቤት እድሳት ያደረገውን የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ ቼክ የጽህፈት ቤቱ የዋና ጸሐፊ ተወካይና የአስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ፀሐፊ አቶ ከረዩ ባናታ ለምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ለአቶ ዘነበ ሙንጣሻ አስረክበዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
"ሰውን ማክበር፤ መተባበር እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ ነው" --- የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ------------------ (ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 2፣ 2018 ዓ.ም፤ ሲዳማ ዳዬ፤ ሰውን ማክበር ፤ መተባበር እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ ነው ሲሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ገለጹ። የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ ይህን የገለፁት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2019 በጀት አመት በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ዞን፣ ዳዬ ከተማ በተካሄደ የክረምት የበጎ ስራ መርሀ-ግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው። የዕለቱ መርሀ-ግብር የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግና በጋራ ችግኝ መትከል ነው ያሉት ም/አፈ-ጉባኤ እነዚህ ሶስቱ ተግባራት በተለያዩ ዘርፎች ቢፈፀሙም የሚያገናኛቸው አንድ ትልቅ ሀገራዊ እሴት አለ። እሱም ሰውን ማክበር፤ መተባበር እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ ነው ብለዋል። አያይዘውም ለተማሪዎች የሚደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በቀጥታ ለሀገራችን የወደፊት ዕድገት የምናደርገው መዋዕለ ንዋይ ነው። ዛሬ ቦርሳ፣ ስክሪፕቶ የምንሰጠው ተማሪ ነገ ሀገሩን የሚያገለግል ሐኪም፣ መምህር፣ መሐንዲስ፣ ጠበቃ፣ ሳይንቲስት ወይም መሪ ሊሆን ይችላል ስለዚህም ትምህርትን አስመልክቶ የሚደረግ ድጋፍ አንድን ተማሪ ብቻ ሳይሆን የአንድን ሀገር የወደፊት ተስፋ መደገፍ እንደሆነም አብራርተዋል። በመጨረሻም ም/አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሁሉም አካላት ጋር በመተባበር ማህበራዊ ፍትህን፣ የትምህርት ጥራትን፣ የዜጎች ኑሮን ማሻሻል እና ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ብለዋል። በመርሀ-ግብሩ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአቅም ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎች የ350 ደርዘን ደብተር፣ የ350 ስክሪፕቶ እንዲሁም በተናጠል የ350 ቦርሳ ድጋፍ አድርጓል። በመርሀ-ግብሩ ላይም የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚንስትር የተከበሩ ወ/ሮ መሰረት ኃይሌ፣ የምክር ቤቱ የአማካሪ ኮሚቴ አባላት፣ የሴቶች ኮከስ ም/ሰብሳቢ፣ የጽህፈት ቤቱ የዋና ጸሐፊ ተወካይና የአስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ፀሐፊ እና የጽ/ቤቱ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የሲዳማ ክልል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዘነበ ሙንጣሻ፣ የዳዬ ከተማ ከንቲባ ኢ/ር ታምራት ተሰማ እና የየዘርፉ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች በተከበሩ ም/አፈ-ጉባኤ መሪነት ዳዬ ከተማ ለተገኘው የፓርላማ ቡድን ከፍተኛ አቀባበል አድርገዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሯ ያስመዘገበችው ውጤት የኮፕ 32 አዘጋጅ ሀገር አንድትሆን እንዳስቻላት የተከበሩ ተስፋዬ በልጅጌ( ዶ/ር)ገለፁ --------------------- (ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 27፣ 2018 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ ፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሯ ያስመዘገበችው ውጤት የኮፕ 32 አዘጋጅ ሀገር አንድትሆን እንዳስቻላት ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት በርካታ ችግኞችን መተከላቸውን አስታውሰው፤ በዚህ ዓመትም ከ 8 መቶ ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል በማቀድ እየሰራች መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መሿለኪያ አካባቢ በተካሄደው የችግኝ ተከላ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው አሻራቸውን ያኖሩት የተከበሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) እለቱ ታሪካዊ እለት ነው ያሉ ሲሆን፣ በአራቱም አቅጣጫ ያሉ ኢትዮጵያውን በአንድ ጀንበር፣ ለአንድ አላማ በመሰለፍ ትልቅ ተግባር እያከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን በመተባባር፣ በአንድነት፣ በመደመር አዳዲስ ታሪክ ከመስራት ማንም ሊያግዳቸው እንደማይችል ማሳያ መሆኑን እና ኢትዮጵያ በራሷ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ የሚያሻሽል ታሪካዊ ክንዋኔ በመሆኑ አንድምታው ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ እያከናወነችው ያለው ተግባር ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም የሚተርፍ እና ምሳሌ የሚሆን ትልቅ ስራ ነው፤ የአረንጓጌ አሻራ ስራና ስትራቴጂ ለአፍሪካ እና ለመላው ዓለም ምሳሌ የሚሆን መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተከናወኑ ሰፊ ስራዎች ምርትና ምርታማነት መጨመሩን፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ትልቅ ለውጥ እየመጣ መሆኑን የአቮካዶ፣ ማንጎ፣ፓፓያ ኤክስፖርት ትልቅ ምሳሌ የሚሆን መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በአረንጓዴ አሻራ ስራ ግብርናው ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማት መሸጋገር መቻሉን፣ የመሬት ለምነት እየጨመረ መሆኑን፣ የሰው ልጆች የሚኖሩበትን የተሻለ አካባቢ ከመፍጠር ባለፈ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን እንድትችል አስተዋፅኦው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዓለም ላይ አስቸጋሪ ከሚባሉት ነገሮች አንዱ የአየር ንብረት ለውጥ ነው ያሉት የተከበሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ይህን በመከላከል ረገድ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ትልቅ አስተዋፅኦ አንዳለው ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ስራዋ ዓለም አቀፍ እውቅና በማግኘት የኮፕ 32 አዘጋጅ ሀገር በመሆን መመረጧንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ፈትሂ ማህዲ(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ 8 ሚሊዮን ችግኞችን መትከላችን ለሀገራችን፣ ለቀጠናው፣ ለአፍሪካ ብሎም ለመላው ዓለም ትልቅና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት መሆኑን ገልፀዋል። አክለውም፣ የዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ በመደማመጥ፣ ለሀገር አንድነት እና ለቀጣይ ትውልድ የሚበጅ ትሩፋት ለማምጣት በሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በሚደረግበት ወቅት መካሄዱ ልዩ ትርጉም እንዳለው ገልፀዋል። (በ-ኃይለማርያም አየለ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
"የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለዓለም ምሳሌ የሚሆን ስኬታማ ሥራ ነው" --- የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ---------------------- (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 27፣ 2018 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለዓለም ምሳሌ የሚሆን ስኬታማ ሥራ መሆኑን ገልጸዋል። ምክትል አፈ ጉባኤዋ ይህን የገለጹት፣ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ መሿለኪያ አካባቢ በተዘጋጀው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮችና አባላት በተገኙበት ወቅት ነው። እንደ ሀገር በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ዘርፎች ለውጦችን ለማምጣት የተለያዩ ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ከእነዚህ ተግባራት መካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በዛሬው ዕለት እየተካሄደ የሚገኘው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለትውልድ ተስፋን ለመትከል፣ አረንጓዴና ዘላቂ አካባቢን ለመፍጠር፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እንዲሁም የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ዓለምን እያስጨነቁና እየፈተኑ ከሚገኙ ጉዳዮች አንዱ የአየር ንብረት ለውጥ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህንን ለመቋቋም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መፍትሔ በመሆኑ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ በወሰዱት ኢኒሼቲቭ እና ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት ሰፋፊ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ እና ትላልቅ ለውጦችም እየመጡ መሆኑን የተከበሩ ምክትል አፈ ጉባኤ አንስተዋል። አክለውም የዘንድሮን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ -ግብር ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ እንደነበር ጠቁመው፣ ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ሁሉም ዜጋ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሀሳብ በመያዝ 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ተፈጥሮን በመንከባከብ የተገኘው ድል ቀላል አይደለም ያሉት ምክትል አፈ-ጉባኤዋ፣ ምርታማነትን ከመጨመር አንፃር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለዓለም ምሳሌ የሚሆን ስኬታማ ሥራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የዛሬው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የአካባቢ ጥበቃን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፍ ብሄራዊ ኃላፊነት መሆኑን በመግለፅ ሁሉም ዜጋ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል። (በ-ኃይለማርያም አየለ ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
"የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ አይነተኛ መሣሪያ ነው" — የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ — (ዜና ፓርላማ) ሰኔ 27፣ 2018 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የሀገርን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ አይነተኛ መሣሪያ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለፁ። አፈ ጉባኤው ይህን የገለፁት፣ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መሿለኪያ አካባቢ በተካሄደው የችግኝ ተከላ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው። አፈ ጉባኤው አያይዘው፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት ባለፉት ሰባት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሁሉንም በየደረጃው በማሳተፍ ስኬታማ ተግባር መከናወኑን ገልፀዋል። የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአንድ ቀን ዘመቻ ብቻ አለመሆኑን እና የእለት ተዕለት ተግባር በማድረግ ባህል እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል። መርሐ ግብሩ ከተፈጥሮ ጋር የተስማማ ኑሮ የምንፈጥርበት፣ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥም አይነተኛ መሣሪያ መሆኑን ገልፀዋል። አክለውም ባለፉት ሰባት ዓመታት የደን ሽፋናችን ከ17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ማደጉን ጠቁመው፣ ይህም ትውልድን የሚገነባና ትውልድን የሚያሻግር ትልቅ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። 48 ቢሊዮን ችግኞችን እንደ ሀገር መትከል ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅሰው፣ የዚህ ስኬት ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም፣ ወንዞች እንዲያገግሙ፣ የአካባቢ ሥነ ምህዳር እንዲጠበቅ እና ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ እንዲረጋገጥ የችግኝ ተከላው ከፍተኛ ሚና እንዳለው አያይዘው ጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሀገራዊ ምክክሩ በስኬት እየተካሄደ መሆኑን የገለፁት የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከቀደሙት መርሃ ግብሮች በተለየ ሁኔታ ሀገራዊ አንድነትንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል። መላው ኢትዮጵያዊ የራሱን አሻራ እንዲያሳርፍ እና የዚህ ታሪካዊ ክንውን አካል እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። በመርሃ ግብሩ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፣ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ መሰረት ኃይሌ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር ቴዎድሮስ ምህረት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት አመራሮች ተገኝተዋል። (በ- ኃይለማርያም አየለ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ አመራሮች እና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል ---------------------- (ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 27፣ 2018 ዓ.ም.፤ አዲስ አበባ፤ የምክር ቤቱ አባላት ፣ አመራሮች እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊና ታሪካዊ መርሐ ግብር አካል በመሆን ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ችግኞችን በመትከል ላይ ይገኛሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘንድሮውን ጨምሮ ባለፉት ዓመታት በዚህ መርሐ ግብር ላይ ጉልህ እንቅስቃሴ በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል። የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የምድራችን የጋራ ሥጋት የሆነው የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ሁሉም ኢትዮጵያ በጋራ በመንቀሳቀስ ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራውን በማሳረፍ ላይ ይገኛል። የሚተከሉ ችግኞች አብዛኛዎቹ ለምግብነት የሚውሉና አገር በቀል የፍራፍሬ፣ የቅመማ ቅመም፣ ለእንስሳት መኖነት የሚያገለግሉ እና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸው። መርሐ ግብሩ አገራዊ አንድነት በማስጠበቅ ኅብረተሰቡን በአንድ ዓላማ በማሰብ ለቀጣዩ ትውልድ ተስፋን ለማውረስ ጉልህ ሚና አለው። ይህ ታሪካዊ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ በመላው ሀገራችን አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ የሚከናወን ይሆናል ( በ በለጠ ሙሉጌታ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
"እስካሁን ውይይት የተደረገባቸው አጀንዳዎች እና ቃለ-ጉባኤዎች ለጠቅላላ ጉባኤው ይቀርባሉ" ---- ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ------------------------ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የምክክር ጉባኤ ሂደት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸውም ተሳታፊዎች በ10 እና በ50 ንዑስ ቡድኖች ተከፋፍለው ሲወያዩባቸው የነበሩ ጉዳዮችን 250 አባላት ላለው ቡድን ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናግረዋል። በእነዚህ ውይይቶች መግባባት የተደረሰባቸው አጀንዳዎች በቀጣይ 500 አባላት ላሉት ጉባኤ እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል። ይህ የ500 አባላት ስብስብም በቀረቡለት አጀንዳዎች ላይ በስፋት ተወያይቶ ሐሳቦቹን የጋራ ካደረገ በኋላ ጉዳዮቹ ለዋናው ጠቅላላ ቡድን የሚቀርቡ ይሆናል ብለዋል። በውይይቱ ሂደት በሐሳቦች ላይ ሙሉ በሙሉ መግባባት ላይ በማይደረስበት ጊዜ፣ ሁሉም ቡድኖች መርጠው ባዘጋጁዋቸው ቡድኖች አማካኝነት ተጨማሪ ውይይት እንደሚደረግባቸውም ፕሮፌሰር መስፍን አብራርተዋል። ይህንን ተግባር የሚያከናውኑ 350 የሚሆኑ ተወካዮች ዛሬ የተመረጡ ሲሆን፣ እነዚህ ተወካዮች የቀረቡት ቃለ ጉባኤዎች ትክክለኛ መሆናቸውን በማረጋገጥ ይፈራረማሉ። ተወካዮቹ የሚያጸድቋቸው እና የሚፈራረሙባቸው ሰነዶችም ከነገ ጀምሮ ለጠቅላላው ጉባኤ እንደሚቀርቡ ተገልጿል። በጉባኤው እየተከናወነ ያለው የተወካዮች ምርጫም ሆነ በውይይት አጀንዳዎቹ ላይ የሚደረገው መመካከር ያለምንም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጣልቃ ገብነት ሙሉ በሙሉ በነጻነት እየተካሄደ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ እየመከረች ነው! ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
ዜና ዕረፍት ----------------- የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አምባሳደር ስንቅነሽ እጁጉ ወልደ ማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ አምባሳደር ስንቅነሽ እጁጉ በኦሮሚያ ክልል ምዕራባዊ ሸዋ ደንዲ ወረዳ (ኢልፈታ በኬ አካባቢ) ምርጫ ክልል ሕዝብን በመወከል ከ2003ዓ.ም እስከ 2007ዓ.ም በምርጫ ተመርጠው የአራተኛው የምክር ቤት አባል በመሆን በቅንነትና በታማኝነት አገልግለዋል፡፡ አምባሳደር ስንቅነሽ እጁጉ በ1972 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉን እና በ1980 ዓ.ም ደግሞ በእንግሊዝ ኢስት አንግሊያ ዩኒቨርሲቲ በአናሊቲካል ኬሚስትሪ የሁለተኛ ዲግሪ ማስተርሳቸዉን አግኝተዋል። አምባሳደር ስንቅነሽ እጁጉ ከምክር ቤት የአባልነት የሥራ ዘመናቸው በፊት በሙያቸው የተለያዩ ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን በመምህርነት፣ በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከባሙያነት እስከ ኃላፊነት፣ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ዲኤታ እንዲሁም የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው አገልግለው በ2006 ዓ.ም በብራዚል፣ በአርጀንቲና እና በቺሊ የኢትዮጵያ የፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ልዩ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዉ ጡርታ እስከወጡበት ሃምሌ 2010 ዓ.ም ድረስ አገልግለዋል፡፡ በ2003 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ምዕራባዊ ሸዋ ደንዲ ወረዳ (ኢልፈታ በኬ አካባቢ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን ሀገርንና ሕዝብን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ አምባሳደር ስንቅነሽ እጁጉ የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት ልጆች እናት ነበሩ፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በአዲስ አበባ ገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ቤተሠቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 6፡00 ተፈጽሟል፡፡ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀድሞ አባሉ አምባሳደር ስንቅነሽ እጁጉ ህልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሠቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡
በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው የስልታዊ ቡድን ምክክር ዛሬም ቀጥሎ ውሏል --------------------- (ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 23፣ 2018 ዓ.ም፤ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው 250 አባላት ባሉት 16 ስልታዊ ቡድኖች የተደራጁ ተመካካሪዎች ምክክር ዛሬ ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ቀጥሎ ውሏል፡፡ በ250 አባላት የተደራጁ 16 ስልታዊ ቡድኖች ከጥቃቅንና ንዑስ ቡድኖች በተገኙና በተጠናቀሩ የአጀንዳ ምክረሃሳቦች ላይ ከትላንት ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም ጀምረው ተመካክረዋል፡፡ ትላንት ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም በነበረው የምክክር ውሎ ከእያንዳንዱ ሰልታዊ ቡድን በተመረጡ 25 የአጀንዳ ምክረሃሳብ አጠናካሪዎች አማካኝነነት የተጠናቀሩ ምክረሃሳቦችን ያዳመጠው 16ቱ ባለ 250 አባላት ስልታዊ ቡድን፣ በጥቃቅንና በንዑስ ቡድኖች ተነስተው በቀረበው ቃለ ጉባኤ ላይ ያልተካተቱ፣ በአግባቡ ያልተብራሩ ያላቸውን ሃሳቦች ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡ ስልታዊ ቡድኖቹ በዛሬው ውሏቸው የተሰጡ አስተያየቶች ተካተውበት በድጋሜ የተደራጀውን ቃለ ጉባኤ የጋራ በማድረግ በቀጣይ ለሚደረገው እና 500 ተመካካሪዎችን ለያዙ 8 ቡድኖች ምክክር ዝግጅት ሲያደርጉ ውለዋል፡፡ በነገው ዕለት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ እገዛ የሚያደርጉ የክልል (ከተማ መስተዳደር) እና የፌዴራል ተወካዮች ምርጫ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ እየመከረች ነው! ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
"ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች" - አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ------------------- (ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 22፣ 2018 ዓ.ም፤ ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ገልጸዋል። የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ለስራ ጉብኝት ከመጡት የአዘርባጃን ሪፐብሊክ የፓርላማ አፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በፓርላማ ዲፕሎማሲ፣ በኢንቨስትመንት፣ በትምህርት፣ በባህልና በንግድ ያላቸውን ትብብርና ግንኙነት እንደሚያጠናክሩ በተደረገው ውይይት ተገልጿል። ከአዘርባጃን በተገኘው ልምድ በቅርቡ ተግባራዊ እየሆነ ያለው መሶብ (MESOB) የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተቋማት ውስጥ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ የተገልጋዮችን እንግልት እያስቀረ መሆኑን አፈ ጉባኤው አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማዕድንና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ትልቅ የኢንቨስትመንት አቅም እንዳላት አፈ ጉባኤው ገልጸው፤ የአዘርባጃን ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅረበዋል። በሀገሪቱ የተካሄደውን ዲሞክራሲያዊ ምርጫና የሀገራዊ የምክክር ሂደትን ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተማዋን ለቱሪስቶች ምቹ እያደረገ እንደሚገኝና ከባኩ ከተማ ጋር በቅርሶች አስተዳደር፣ በቱሪዝምና ከተማ አስተዳደር ልምድ ለመውሰድ ፍላጎት መኖሩም ተገልጿል። የአዘርባጃን ሪፐብሊክ የፓርላማ አፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እና በአዘርባጃን መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ እና ሁለንተናዊ ግንኙነት የሚያጠናክሩ የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመው በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ገልጸዋል። (በ አበባው ዮሴፍ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የአዘርባጃን ፓርላማ አፈ ጉባኤን ተቀበሉ -------------------- (ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 21፣ 2018 ዓ.ም፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የአዘርባጃን ሪፐብሊክ የፓርላማ አፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ሲገቡ አቀባበል አድርገውላቸዋል ። አፈ ጉባኤዋ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል። አፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የፓርላማ ዲፕሎማሲ ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማህበራዊ የትሥሥር ገጹ ባጋራው ጽሁፍ ገልጿል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
"ከድምፅ ብልጫ ይልቅ የጋራ መግባባትን ያነገበ ሀገራዊ ምክክር ነው" --- ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ----------------------- (ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 21 ፣ 2018 ዓ.ም፤ እየተካደ ያለው ሀገራዊ ምክክር ከድምፅ ብልጫ ይልቅ የጋራ መግባባትን ያነገበ ስለመሆኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አረአያ የሀገራዊ ምክክሩን አፈጻጸም፣ አሳታፊነት እና የቀጣይ አቅጣጫዎች አስመልክተው ሰፊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም አሁን ላይ ከ4 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እየተሳተፉበት ያለው የውይይት አወቃቀር በደረጃ እያደገ የሚሄድ መሆኑን አብራርተዋል። ተሳታፊዎቹ መጀመሪያ አስር አስር አባላት ባሏቸው 400 ቡድኖች ተከፋፍለው ውይይት የጀመሩ ሲሆን፣ ሂደቱም ደረጃ በደረጃ ከ10 ወደ 50፣ ከዚያም ወደ 250 ከፍ እያለ መጥቷል። ስምንት አበይት አጀንዳዎች የተለዩ ሲሆን፣ እያንዳንዱ አጀንዳ በመጨረሻ 500 ተሳታፊዎች ወዳሉት ዋና ቡድን የሚያድግ ይሆናል። በአሁኑ ሰዓት ተሳታፊዎች በ10 እና በ50 ቡድኖች አጀንዳዎቻቸውን በስፋት ከተወያዩበት በኋላ ሀሳቦቻቸውን አጠቃለው አሁን ወደሚገኙበት የ250 ስልታዊ ቡድን ምዕራፍ ተሸጋግረዋል። በዚህ ደረጃም ተሳታፊዎች በነጻነት እና በተረጋጋ ሁኔታ ሀሳቦቻቸውን እያደራጁ ይገኛሉ። የምክክሩ ዋና አላማ በድምጽ ብልጫ ሰዎችን ማሸነፍ ወይም ማግለል ሳይሆን በመግባባት ላይ መድረስ በመሆኑ፣ ትንሽ ቁጥር ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሀሳብ በትልቅ ቁጥር እንዳይሸፈን በእኩልነት የመወያየት መድረክ ተፈጥሯል። ውይይቶቹ በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በትግርኛ፣ በሶማልኛ እና በሌሎችም እንዲሁም በምልክት ቋንቋ የቀጥታ ትርጉም አገልግሎት እየተካሄዱ ይገኛሉ። በተጨማሪም የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፓነል ኤክስፐርቶች እና ኮሚሽነሮች ሂደቱን የማስታረቅ እና የመደገፍ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው። የሰነድ እና የታሪክ ጥራት እንዳይበላሽ የተሳታፊዎች መገኘት በጥብቅ እየተከታተለ መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር መስፍን፣ የ250ው ቡድን ስራ እስከ ሰኞ ባለው ጊዜ ውስጥ ሲጠናቀቅ የተጠቃለሉት ሀሳቦች ወደ 500ው ቡድን አጠቃላይ ውይይት እና ውሳኔ እንደሚሸጋገሩ አስታውቀዋል። ይህ አካታችና ጥንቃቄ የተሞላበት ሂደት የዘመናችንን ሀገራዊ መግባባት የሚያመጣ ትልቅ ብስራት እንደሚሆን የላቀ ተስፋ ተጥሎበታል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
"ኢትዮጵያ በዓመት ለወደብ ኪራይ እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታወጣለች" ---- የተከበሩ ዶ/ር ፈትሂ ማሕዲ ---------------------- ( ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 20፣ 2018 ዓ.ም.፤ኢትዮጵያ በዓመት ለወደብ ኪራይ እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደምታወጣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ ምክትል ሰብሳቢው ይህንን የገለጹት በኢትዮጵያ የኪርጊዝ ሪፐብሊክ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አዲልቤክ ቱልቴሚሮቭን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡ የተከበሩ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት ባለመሆኗ ምክንያት በየዓመቱ ለወደብ ኪራይና ተያያዥ የሎጂስቲክስ አገልግሎቶች እስከ 2 ቢሊዮን አሜሪካን ዶላር የሚደርስ ከፍተኛ ወጪ ለማውጣት መገደዷን ገልጸዋል። ይህ ወጪ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ያስረዱት ምክትል ሰብሳቢው፣ የባሕር በር ማግኘት እና አጋር ከሆኑ ሀገራት ጋር ቀጣናዊ የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ ትስስር መፍጠር ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ህልውና እና ዘላቂ ልማት ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። በውይይቱ ወቅት ትኩረት ከተሰጣቸው አበይት ጉዳዮች መካከል የንግድና የግብርናው ዘርፍ ትብብር ግንባር ቀደሙን ስፍራ የያዘ ሲሆን፣ ሁለቱ ሀገራት ያሏቸውን እምቅ ተፈጥሮአዊ፣ የግብርና ምርቶችና የኢኮኖሚ አቅሞችን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን ማጎልበት እንደሚገባቸው የተከበሩ ፈትሂ (ዶ/ር) አመላክተዋል፡፡ በዚህም ዘርፍ የቴክኖሎጂና የልምድ ልውውጥ ማድረግ የሚቻልበት የትብብር ማዕቀፍ መዘርጋት እንዳለበት አፅንኦት ተሰጥቶበታል። በተጨማሪም በውይይቱ ወቅት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ ወንድማማችነት እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማፅናት እየተከናወኑ ባሉ አበይት ሀገራዊ ሁነቶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል። በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ መግባባትን ለመፍጠርና የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት እየተሰራ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሥራ እንቅስቃሴ በውይይቱ ተብራርቷል፡፡ እንዲሁም፣ ኢትዮጵያ ያካሄደችው የ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ አሳታፊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ እንደነበር ምክትል ሰብሳቢው ለአምባሳደሩ ገልጸውላቸዋል፡፡ አምባሳደሩ ከቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢና ከሌሎች የኮሚቴ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል። የቋሚ ኮሚቴው አባል የተከበሩ አምባሳደር ተውፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ በውሃ ኃብት የበለጸገች ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፣ የውኃ ሀብትን ጨምሮ በቀጣናዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ኢትዮጵያ ከ ኪርጊዝ መንግስት ጋር በትብብር እንደምትሰራ ነው ያብራሩት፡፡ በተመሳሳይም ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ የባህር በር ማጣቷን ለአምበሳደሩ የገለጹላቸው ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የባህር በር አንድታገኝ ሁለቱ ሀገራት በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ አምባሳደር አዲልቤክ ቱልቴሚሮቭ በበኩላቸው፣ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ለማደስና ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ያረጋገጡ ሲሆን፤ በተለይም የፓርላማ ዲፕሎማሲውን በመጠቀም በንግድ፣ በግብርና፣ በሎጂስቲክስ እና በሌሎችም ሁለገብ ዘርፎች የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። (በ-ስሜነው ሲፋረድ) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት በምክር ቤቱ ጽ/ቤት የ5 ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ -------------- (ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 18፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ከተለያዩ የዓለም ሀገራትና ከሀገር ውስጥ ተቋማት የተወሰዱ መልካም ተሞክሮዎችን ያካተተውና ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚተገበረው ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ከሠራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ላይ ተሳታፊዎች ዕቅዱ ሳይንሳዊ አካሄድን የተከተለ፣ ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ የዳሰሰና ቀድሞ ለውይይት መቅረቡ የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል። በተጨማሪም ልምድ ከሚወሰድባቸው የዓለም ሀገራት እንዲሁም ከሀገር ውስጥ የፕላንና ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ተሞክሮ መወሰዱ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይም የሠራተኞችን ማኅበራዊ ሁነት፣ የሥራ ክፍሎችን ቁርኝትና የሕዝብን ተሳትፎ የሚያጠናክሩ ነጥቦች ይበልጥ እንዲጎለብቱ አስተያየት ሰጥተዋል። የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የዋና ጸሐፊ ተወካይና የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ከረዩ ባናታ እንደገለጹት፤ ዕቅዱ በአጭርና በረጅም ጊዜ ተከፋፍሎ የሚተገበርና አዳዲስ ሁነቶችን ታሳቢ እያደረገ የሚቀጥል ነው ብለዋል። የፓርላማውን ሚዲያ የይዘት አማራጮች ማሻሻል፣ ከእያንዳንዱ የሥራ ክፍል ጋር በስታንዳርድ ዙሪያ መመካከር እና በውስጥ አቅም በርካታ ሥልጠናዎችን መስጠት ትኩረት የሚሰጣቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን አብራርተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ እና የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ምክትል ዋና ጸኀፊ (የሙያዊ ዘርፍ ተወካይ) ወ/ሮ ቁስቋም ማሞ በበኩላቸው ጽሕፈት ቤቱ የተቋቋመበትን ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ የማጠናከር ዓላማ መነሻ በማድረግ በጥናት ላይ የተመሠረቱ ውጤታማ ሥልጠናዎች ለሠራተኞች እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፈለጉሽ ወርቁ እንደገለጹት የውጭና የሀገር ውስጥ ተሞክሮዎች ከፓርላማው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚጣጣም መልኩ የተወሰዱ ናቸው ብለዋል። አክለውም ዕቅዱ ፈታኝ ሁኔታዎችን ለመቋቋምና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ጠቁመው፣ በቀጣይም የፓርላማ ራዲዮና ስቱዲዮ ለማቋቋም በስፋት እንደሚሰራ ገልጸዋል። (በ ሀብታሙ አብርሃም) ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
በምክክር ሂደቱ ተመካካሪዎች በአጀንዳዎች ላይ ሀሳባቸውን ያለ ገደብ እየገለጹ ነው ----------------- (ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 18 ፣ 2018 ዓ.ም፤ በሃገራዊ ምክክር ሂደቱ ተመካካሪዎች በአጀንዳዎች ላይ ሀሳባቸውን ያለ ገደብ እየገለጹ መሆኑን የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለፁ። ዋና ኮሚሽነሩ የምክክር ሂደቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ከ10ሩ ንዑስ ቡድኖች የመነጩ ሃሳቦች ተጠናክረው ለ50ዎቹ ቡድን አባላት እየቀረቡ መሆኑን አንስተዋል። በመዋቅሩ መሰረትም እያንዳንዳቸው 10 አባላት ያሏቸው ንዑስ ቡድኖች ሲወያዩባቸው የቆዩትን ሃሳቦች፣ አመለካከቶችና ምልከታዎች ከማመንጨት ተሻግረው ወደ ማጠናከር መሸጋገራቸውን ገልፀዋል። ተሳታፊዎች በምክክር መድረኩ ላይ ሀሳባቸውን እያወጡ እየተመካከሩ እንደሚገኝም በመግለጫቸው አንስተዋል። አርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩ፣ አካል ጉዳተኞች፣ የተገፉ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች በመከባበር አጀንዳዎቻቸውን እያነሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የሃገራዊ ምክክሩ ሂደት አበረታች መሆኑን በመግለፅ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል። በጥንቃቄ የተደራጁና የተጠናከሩ የውይይት ውጤቶችም በአሁኑ ሰዓት በየንዑስ ቡድኖቹ ሰብሳቢዎችና ጸሃፊዎች አማካኝነት 50 ተመካካሪዎች ለያዙት ቡድኖች በንቃት እየቀረቡ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። እንዲሁም ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሃይማኖት ተቋምም ሆነ ሌላ አካል በሌላው ላይ የሐሳብም ሆነ የቁጥር ብልጫ ወስዶ ጫና እንዳያሳድር ክትትል እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።