Southwest Ethiopia Police Commission
Статистикаበጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል ተቀዳሚ ተግባራችን ነዉ፡፡
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 285
- 1/48двое суток
- 326
- 1/72трое суток
- 352
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መረጃ ስታቲስቲክስ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወንድወሰን ወንድሙ በላኩት ሳምንታዊ የትራፊክ አደጋ መረጃ እንዳመላከቱት በክልሉ በአንድ ሳምንት ውስጥ አራት የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋዎች መከሰታቸውን ተከትሎ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡ በሁለት ዞኖች በካፋ ዞን እና በቤንች ሸኮ ዞን አደጋዎቹ መከሰታቸውን አመልክተው በካፋ ዞን ከደረሰው ሁለት አደጋ መካከል አንድ ሰው ባለሁለት እግር ሞተር በመገልበጡ የአንድ ሰው ህይወቱ ሲያልፍ እንዲሁም በቤንች ሸኮ ዞን ከሁለት አደጋዎች አንደኛው ባለሁለት እግር ሞተር እና የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ተጋጭተው የአንድ ሰው ህይወት አልፏል ብለዋል፡፡ በክልሉ በሳምንቱ ውስጥ በደረሰው አደጋ ሶስት ሰዎች ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸው በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት እንዳጋጠማቸው ኢንስፔክተር ወንደሰን አመልክተው ሁለት ከባድ እና ሁለት ቀላል በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ የጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ ምክንያት ጉዳት መመዝገቡን እና በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የጭነት ተሸከርካሪ ከባለሁለት እግር ሞተር ጋር ተጋጭተው አንድ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል፡፡ በክልሉ የደረሱ አደጋዎች መካከል ሁቱ መገልበጥ፤ሁለቱ ደግቦ ተሸከርካሪ ከባለሁለት እግር ሞተር ጋር በመጋጨታቸው ሲሆን የአደጋዎቹም ሁለቱ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር እና ሁለቱ አደጋዎች ቀኝን ለቆ ማሽከርከር መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ ኢንስፔክተር ወንደሰን ለአሽከርካሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት አሽከርካሪዎች በየአራት ሰዓቱ በቂ እረፍት ማድረግ እንዳለባቸው እና አልኮል ጠጥተውና አደንዛዥ እፆችን ተጠቅመው ማሽከር እንደሌለባቸው ገልፀው። እንዲሁም ባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪዎች አደጋ መካከያ ሄሌሜንት ማድረግ እና ፍጥነታቸውን ቀንሰው ማሽከርከር ይገባቸዋል ብለዋል ማለታቸውን ጠቅሶ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኝኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡፡ ✍️ በኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ተጨማሪ መረጃዎችን Southwest Ethiopia Police Commission በቴሌግራም ገፃችን ይመልከቱ https://t.me/swpolice
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በምሽት ጉዞ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ። የጊምቦ ወረዳ ትራፊክ አደጋ ፍሰት ቁጥጥር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ሳጅን ሳላስብ ኢካሎ እንደገለፁት በወረዳዉ በምሽት በሚደረግ ጉዞ ሁለት አደጋዎች መድረሱን አስረድተዋል። አደጋዎቹም ከአዲስ አበባ ወደ ሚዛን ተፈሪ በመጓዝ ላይ የነበረ ኮድ 3 አ አ 48437 ኦባማ አይሱዙ በጊምቦ ወረዳ ቢጣ ጨጋ ቀበሌ በተለምዶ አጠራር 460 ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሰኔ 24, ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 5፡30 ሰዓት ገደማ በመገልበጡ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሰዋል ብለዋል። በተመሳሳይ ኮድ 3 ኢት A 43674 የሆነ ሲኖትራክ ካሶኒ መኪና ከሚዛን ወደ አዲስ አበባ መስመር በመጓዝ ላይ እያለ በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ውሽውሽ ከተማ ላይ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 8፡30 ሰዓት አካባቢ መንገድ ሲተው የሰው መኖሪያ ቤት በመግባቱ የተከሰተ አደጋ መሆኑን ጠቁመዋል። በሁለቱም አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ያለመኖሩን ገልፀዉ አሽከርካሪዎች ምሽት በሚያሽከረክሩበት ወቅት ፍጥነታቸዉን ቀንሰዉና በቂ እረፍት ማድረግ እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
без подписи
без подписи
በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፋ ተገለፀ። ከቦንጋ ሺሺንዳ ተሳፋሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ዶልፊን መንገድ ስቶ በደረሰ አደጋ ተመራቂና አስመራቂዉ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ መነሻውን ከቦንጋ ያደረገው ታርጋ ቁጥሩ 00582 ዶልፊን መኪና ሰኔ 23 ሰኔ 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5:30 ላይ ወደ ሺሺንዳ ከተማ በመጓዝ ላይ ሳለ ዋና ቦላ በተባለ ቀበሌ ሲደርስ መንገድ ስቶ በደረሰ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት ወዲያውን ማለፉ ተገልጿል። በዚሁ የትራፊክ አደጋ በሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ከባድና ቀላል አደጋ መድረሱን የዘገበው ተጎጂዎች በዲንብራ ጤና ጣቢያ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን አመላክቷል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ዶክተር ካሳ በአቶ ሀብታሙ አለሙ ህልፈተ ህይወት ተሰማቸዉን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ። ኮምሽነር ዶክተር ካሳ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ዓለሙ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸውን ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸዉ ገልፀዋል። በክልሉ በአንዳንድ አከባቢዎች ተከስቶ በነበሩ የፀጥታ ችግሮች ከክልሉ ፖሊስ ጋር በመሆን አቶ ሀብታሙ ዓለሙ በሀገር ሠላምና ፀጥታዉ ወደነበረበት እንዲመለስ በሳል አመራር ይሰጡ ነበር ብለዋል። ኮምሽነር ዶክተር ካሳ አክለዉም ዛሬ እሳቸዉን በሞት ብናጣቸዉም በሰሩት ስራና ባሰፈኑን ሰላም ሁሌም ስናስታዉሳቸዉ እንኖራለን ብለዋል። በመጨረሻም ኮምሽነር ዶክተር ካሳ ለአቶ ሀብታሙ ዓለሙ ነፍስ የዘላለም ዕረፍት እንዲሰጣቸዉና ለመላው ቤተሰቦቹ፣ለዘመድ ጓደኞቹ እና ለስራ ባልደረቦቻቸዉ ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጣቸዉ በራሳቸዉና በመላዉ የክልሉ ፖሊስ አመራሮችና አባላት ስም ከልብ መፅናናትን እንመኛለን ብለዋል።
без подписи
ፖሊስና ርምጃ ጋዜጣ በሰኔ 01/2018 ዕትሙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽር ዶክተር ካሳን በሚመለከት ተከጀታዩን ለንባብ አብቅቷል፡፡ ስትራቴጂክ መኮንኑ ቀደም ሲል በደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፖሊስ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ገና ከወጣትነት እድሜያቸዉ ጀምሮ ለሀገራቸዉ ከፍተኛ የሆነ ዋጋ የከፈሉ ናቸዉ:: እንግዳችን በተመደቡባቸዉ ቦታዎች ሁሉ በዉጤታማነት ይታወቃሉ፤ በሰራዊቱም ሆነ በሚያገለግሉት ማህበረሰብ ተቀባይነታቸዉ ከፍ ያለ ነዉ:: እንግዳችን በእድገትም ሆነ በዝዉዉር ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ የሰርግ አይነት ድግስ በመደገስ ነዉ:: ይህ ሳይበቃ በሽልማት ያልተበረከተላቸዉ የስጦታ አይነትም የለም:: ይህ በህዝብ እና በሰራዊት ዘንድ ያለ ተቀባይነት ከእለት እለት ጉልበት እየሆናቸዉ አሁን ላይ የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል:: ከላይ በአጭሩ የገለፅናቸዉ የሀገራችን ፖሊስ ስትራቴጂክ መኮንን ያሳለፉትን የህይወት ዉጣ ዉረድ አባይን በጭልፋ እንደሚባለዉ ከብዙ በጥቂቱ በአንደበታቸዉ የገለፁትን ይዘን ቀርበናል:: መልካም ንባብ፦እንግዳችን ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ ይባላሉ:: ትዉልድና እድገታቸዉ በቀድሞዉ ከፋ ክፍለ ሀገር ሸዋ ጊሚራ አዉራጃ በአሁኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንች ሸኮ ዞን ሼይ ቤንች ወረዳ ተወለዱ:: በ1965 ዓ.ም ህይወትን በግብርና ሙያ ከሚያስተዳድሩ ከአባታቸዉ ከአቶ ካሳ ባይኔዝ እና ከእናታቸዉ ወ/ሮ ይጋሴ ዘፋ የተገኙት እኝህ በፎቶ ምትመለከቷቸዉ ደርባባ መኮንን ለቤተሰቦቻቸዉ ሶስተኛ ልጅ ናቸዉ:: የተወለዱበትን ቀን፣ ወርና ዓ.ም የሚገልፅ ሰነድ አልያም የልደት ሰርተፍኬት ባያገኙም አርሶ አደር አባታቸዉ በ1965 ዓ/ም በዕም ውስጥእንደተወለዱ መግለፁን አጫዉተዉናል:: አባታቸዉ አቶ ካሳ ለልጅ ስም ሲያወጡ ለምን ዶክተር አሉ ስንል ላነሳነላቸዉ ጥያቄ ኮሚሽነሩ ሲመልሱ « ዶድ ቶር » ከሚለው የሼቤንች ቋንቋ የመጣ መሆኑን በመግለፅ ትርጉሙም « አካባቢውን የሚጠብቅልኝ » ማለት ነው። «ዶድ» ማለት መሬት ወይም ይዞታ ማለት ሲሆን «ቶር» ማለት ደግሞ ጠብቅ ማለት ነው። ከዚህ የተነሳ አርሶ አደሩ አባታቸዉ ይዞታቸዉንና ርስታቸዉን ይጠብቅልኛል ሲሉ ስማቸዉ እንደወጣ በማንሳት ወደ ትምህርቱ ዓለም ሲቀላቀሉ «ዶክተር» በሚል ፀንቶ እስከ አሁን መጠሪያቸዉ ሆኖ መዝለቁን አንስተዋል። እንደ ማንኛዉም የአርሶ አደር ልጅ በተወለዱበት ቀዬ ቦረቀዉ ያደጉት ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ እድሜያቸዉ ከፍ ሲል የገብስ ማሳቸዉ በወፎች እንዳይጠረጠር አባታቸዉ እንዲጠብቁ ያደርጉ ነበር። የበቀሎ ሰብላቸዉም ሲያሸት በዝንጀሮና በጦጣ መንጋ እንዳይበላ በማባረር በኩልም ዉጣ ዉረዱ ከባድ እንደነበር ያስታዉሳሉ:: በአካባቢያቸዉ ከነበረ የጤና ባለሙያ እጥረት አንፃር የልጅነት ህልማቸዉ ተምረዉ ሀኪም መሆን የሚል ነበር:: ነጩን ጋዎን ለብሰዉ የታመመን አክማለሁ ሲሉ የወደፊት ራዕያቸዉን ሲገልፁ የነበሩት እንግዳችን ከእለታት በአንድ ቀን ወደ ሲዝ ከተማ በሔዱበት ወቅት ከርቀት የተመለከቷቸዉ ነባር እና አዳዲስ ፖሊሶች በተለይ ደግሞ የቀድሞዉ የፖሊስ ሠራዊት አባላት ሚሊተሪያቸዉን አስተኩሰዉ የለበሱበት አግባብ፤ አረማመዳቸውና ወንጀለኛን የሚይዙበት መንገድ የእንግዳችንን ቀልብ የሳበ በመሆኑ የጤና ባለሙያ እሆናለሁ የሚለዉ ምኞት በዚህ እለት ተገታ ይላሉ:: በግልፅ ለሚጠይቃቸዉ ሁሉ ፖሊስነትን ሰልጥኜ እንደ እነኝህ ሸበላ ፖሊሶች መሆን እፈልጋለሁ ሲሉም መደመጥ ጀመሩ። ፖሊስ ያኔ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተቀባይነት እንደነበረዉ ያነሱት ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ ሁኔታዎች ተደማምረዉ ፍላጎታቸዉ ከፍ በማለቱ በሙሉ ልብ ወደ ፖሊስነት ሙያ ሊቀላቀሉ ችለዋል። በሸዋ ጊሚራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ1972 ዓ.ም ፊደልን « ሀ » ብለዉ መቁጠር የጀመሩት እንግዳችን በሰአቱ ወደ ት/ቤት ለመግባት በእጃቸዉ ጆሯቸዉን እንዲነኩ አልያም ጥርሳቸዉ እየታዬ እንደነበር በፈገግታ አስታዉሰዋል። በሸዋ ገሚራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ስምንተኛ ክፍል የተከታተሉት መኮንኑ በትምህርታቸዉ ሞካሪ ከሚባሉ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ:: ከትምህርታቸዉ ጎን ለጎን በግብርናዉ ሙያም ቢሆን ያልተሳተፉበት የስራ መስክ የለም::በግብርና ህይወት ከባዱ ስራ የሚባለዉን በሬ ጠምዶ ማረስ ማንደፋረሱንም ቢሆን በደንብ እንደገፉበት ሲናገሩ በኩራት ነዉ፤ ጥሩ አራሽም ነበርኩ ይላሉ:: አባታቸዉ አቶ ካሳ ሁለት ነገር ይወዳሉ፤ ግን ደግሞ ለልጃቸዉ ለያኔዉ ወጣት ለአሁን ስትራቴጂክ የፖሊስ መኮንን ፈተና ይዞ የመጣ ነዉ:: አባት አቶ ካሳ ልጃቸዉን ማስተማር ይፈልጋሉ፤ ግን ደግሞ መሬቶቻቸዉ ፆም እንዳያድሩ መታረስ እንዳለባቸዉ ደግሞ አቋማቸዉ የፀና ነዉ:: ይህንን ሀሳብ አስታራቂ በሆነ መንገድ መላ የዘየዱት ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ በሰአቱ የወሰዱት አማራጭ ስራቸዉን እየሰሩ ትምህርታቸዉን ጎን ለጎን መከታተል አለብኝ የሚል ነበር:: ሳይማሩ የአርሶ አደር ህይወትን መግፋት በቤተሰቦቼ ሊበቃ ይገባል ያሉም ሰዉ ናቸዉ:: አሁንም ድረስ የነበረዉን ሁኔታ በደንብ ያስታዉሳሉ:: ለመማር ከነበራቸዉ ፍላጎት የተነሳ የእርሻ መሬታቸዉ ከት/ቤቱ በቅርብ ርቀት ያለ በመሆኑ የጠዋት ክፍለ ጊዜ ሲሆኑ ቀደም ብለዉ ተነስተዉ በሬዎቻቸዉን ሳር አብልተው ለሊት12 ሰዓት የእርሻ ቦታቸዉ ላይ በመገኘት በሬ ጠምደን ማረስ የሚጀምሩት የያኔዉ ሁለገብ ሰራተኛ የአሁኑ የፖሊስ ኮሚሽነር የጠዋቱ የትምህርት ጊዜ ፈረቃ ተጠናቆ የከሰአቶቹ እንዲገቡ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደወል ሲደወል አሳልፈዉ ሶስተኛው ላይ በሬዎችን ለተረኛ ሰጥተዉ በትምህርት ቤቱ ጓሮ ሮጠዉ በመግባት ትምህርታቸዉን ይከታተሉ እንደነበር ወደ ኃላ መለስ ብለዉ አጫዉተዉናል። ከትምህርት ቤት መልስም እሚያርፉ አልነበረም:: በቤተሰብ በኩል ጥያቄ እንዳይፈጠር የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ፣ አረም በማረም፣ ለከብቶች ሳር በማጨድ እና ሌሎች ተግባራቶችን ለቤተሰቦቻቸዉ በቀናነት እያገለገሉ ያደጉ ናቸዉ። ይህ ታዛዥነታቸዉ በቤተሰብ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ጭምር ተወዳጅ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል::እንግዳችን ከስምንተኛ ወደ ዘጠነኛ ክፍል እንደተዘዋወሩ የተሻለ ትምህርት ለመማር በ1980 ዓ.ም ወደ ቦንጋ ከተማ አቀኑ። ተጨማሪውን ታሪክ ለማንበብ በፖሊስ ሊንኩን ይጫኑ https://t.me/swpolice ላይ ይከታተሉን፡፡
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи