EBC
Статистика🌐 World Wide News — Breaking stories. Global updates. Real impact. Stay informed with the latest news from every corner of the world — fast, reliable, and all in one channel.
- Последний пост
- 22:26
- Последнее чтение
- 08:18
- Постов за неделю
- 56
- Всего постов
- 816
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 359
- 1/48двое суток
- 411
- 1/72трое суток
- 443
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም በ11ኛ ክፍል ለሚጀመሩ አዳዲስ የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶች የአተገባበር ማንዋል ይፋ አድርጓል። 👉 በመተግበሪያ ማንዋሉ መሰረት አንድ ተማሪ ከአቅሙና ከፍላጎቱ ጋር የተያያዘ አንድ የሙያ ዓይነት ብቻ መርጦ የሚማር ሲሆን፣ ትምህርት ቤቶች ሁሉንም 11 ዓይነት ሙያዎች በአንድ ጊዜ እንዲተገብሩ አይገደዱም። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እና ተማሪዎችን ለሥራው ዓለም ለማዘጋጀት ያለመ አዲስ የአተገባበር ማንዋል አዘጋጅቷል። በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ማንዋል፣ በ2019 ዓ.ም በ11ኛ ክፍል ለሚጀመሩ አዳዲስ የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶች ትግበራ የሚውል ሲሆን፤ የትምህርቱን አስፈላጊነት፣ ዓላማ፣ የአመራረጥ ሂደት እና የተግባርና ኃላፊነት ክፍፍልን በዝርዝር አካቷል። ቢሮው በመመሪያው መግቢያ ላይ እንደገለጸው፣ ትምህርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ሚና ቢኖረውም፣ በተካሄደው የፍኖተ ካርታ ጥናት መሰረት የአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱ ከሥራና ተግባር ጋር ያልተሳሰረና የ21ኛው ክፍለ ዘመን ክህሎትን ያላካተተ ሆኖ ተገኝቷል። ይህ ችግር ተማሪዎችን በመሠረታዊ እውቀት ብቻ ያቆምና በሥራ ዓለም ተግባራዊ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የማያስችል ነው ይላል። ችግሩን ለመፍታትም በ2017 እና 2018 ዓ.ም በሁለተኛ ደረጃ ላይ በሚገኙ ተማሪዎች በስምንት የሙያ መስኮች ማለትም ፦ - በግብርና ፣ - መረጃ ቴክኖሎጂና ኮምፒውተር ሳይንስ ፣ - ጤና ሳይንስ፣ - ኮንስትራክሽን፣ - ማኑፋክቸሪንግ ፣ - ኮሙኒኬሽንና የማህበራዊ ሳይንስ ፣ - ቢዝነስ ሳይንስ እና ስነጥበባት ውስጥ ከሚገኙት የሥራ አይነቶች አንዱን መርጠው እንዲማሩ መደረጉን አስታውሷል። ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮም ከዕድሜ ጋር የተመጣጠነ የሥራና ተግባር ትምህርት እንደተሰጠ የአተገባበር መመሪያው ያስረዳል። አሁን ደግሞ በ2019 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚቀርቡ 11 አዳዲስ የሙያ ዓይነቶችን በትምህርት ቤቱ እና በተማሪው ምርጫ ተግባራዊ ለማድረግ የመተግበሪያ መመሪያ (Manual) መዘጋጀቱ አመልክቷል። በዚህ አዲስ የአተገባበር ሥርዓት ውስጥ የተካተቱት 11 የሙያ ዓይነቶች በስድስት ዋና ዋና የሙያ ዘርፎች (Career Clusters) የተከፋፈሉ ናቸው። ° በግንባታ ዘርፍ የሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና የቧንቧ ስራ፤ ° በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የብረታ ብረት ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ እና አልባሳት ቴክኖሎጂ ፤ ° በቢዝነስ ሳይንስ ዘርፍ የሆቴል አገልግሎት፣ የፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት እንዲሁም የምግብ ዝግጅት ተካተዋል። በተጨማሪም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሶፍትዌር ማበልጸግ፣ በግብርና ሳይንስ የሰብል አመራረት እና በጤና ሳይንስ የጤና ክብካቤ አገልግሎት የሙያ ዓይነቶች ለተማሪዎች እንዲቀርቡ ተለይተዋል። የሙያ ዓይነቶቹ የሚመረጡበት ሂደት ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን በመመሪያው ታዟል። ትምህርት ቤቶች የሙያ ዓይነቶችን ከመምረጣቸው በፊት የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ ያሉትን የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ግብዓቶች፣ እንዲሁም የተማሪዎችን ፍላጎት ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በአተገባበር በመመሪያው መሠረት አንድ ትምህርት ቤት ሁሉንም 11 የሙያ ዓይነቶች ማቅረብ አይጠበቅበትም፤ ይልቁንም እንደ አቅሙና እንደ አካባቢው ሁኔታ የተወሰኑትን መርጦ ተግባራዊ ያደርጋል። ተማሪዎችም ከቀረቡት አማራጮች መካከል የአንዱ የሙያ ዓይነት ባለቤት እንዲሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ምርጫቸውም ከፍላጎታቸውና ከችሎታቸው ጋር የተገናኘ መሆን እንዳለበት ተደንግጓል። ለመመሪያው መሳካት የተለያዩ አካላት የየራሳቸው ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። የከተማዋ ትምህርት ቢሮ የመሪ ዕቅድ የማዘጋጀትና ክትትል የማድረግ ኃላፊነት ሲኖርበት፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ደግሞ ትምህርት ቤቶች የሙያ ዓይነቶችን እንዲለዩ ድጋፍ ያደርጋሉ፤ ሙያውን የሚከታተሉ ባለሙያዎችንም ይመድባሉ። ትምህርት ቤቶች በበኩላቸው ካሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር የሙያ ዓይነቶችን የመምረጥ፣ ለተማሪዎች ግንዛቤ የመፍጠርና ትግበራውን የመምራት ቀጥተኛ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ይህ የሥራና ተግባር ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን ትምህርት ቤቶች ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከግል ባለሀብቶች ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው መተግበሪያ መመሪያው ያሳስባል። ይህም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ሥራ ፈጣሪ ዜጎች እንዲሆኑና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲደግፉ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ቢሮው ለትግበራው ምቾት ይረዳ ዘንድ ለትምህርት ቤቶችና ለተማሪዎች ምርጫ የሚሆኑ ቅጾችንም ከመመሪያው ጋር አያይዞ አቅርቧል። ሙሉ የአተገባበር ማንዋሉን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አዲስ ስርዓተ ትምህርት (ካሪኩለም) ይፋ ማደረጉን ገለጸ። በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ከአሁን በፊት ከሦስተኛ ክፍል ይጀምር የነበረው ወደ ሰባተኛ ክፍል እንዲዘገይ ተደርጓል። በተጨማሪም በቀድሞው ስርዓተ ትምህርት ያልነበረው የግብረ-ገብ ትምህርት በአዲሱ ካሪኩለም መካተቱን ቢሮው ገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የትግራይ ትምህርት ቢሮ መረጃ፣ " በክልሉ ሲተገበር የቆየው ስርዓተ ትምህርት 16 ዓመታትን ያስቆጠረ " መሆኑን ገልፆ ፤ " ስርዓት ትምህርቱ የክልሉን ራዕይ ለማሳካት ከሚደረገው ጥረት ጋር በበቂ ሁኔታ የተጣጣመ አስተዋፅኦ አላበረከተም " ብሏል። ቢሮው እንዳስታወቀው፣ የትምህርት ስርዓቱን ከዘመኑ ጋር ማጣጣም አስፈላጊ በመሆኑ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተለወጠውን ዘመናዊ ዓለም የሚመጥን ስርዓተ ትምህርት መቅረፅ ወሳኝ ነው። አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ14 የዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ባለሙያዎች መዘጋጀቱን ቢሮው ገልጿል። በስርዓተ ትምህርቱም ከአካባቢው ተሞክሮ በተጨማሪ ከእስያ የስነ-ምግባር ትምህርት፣ ከስካንዲኔቪያና ከሰሜንና ምዕራብ አውሮፓ ደግሞ እኩልነትና ተጠያቂነትን የሚመለከቱ ተሞክሮዎች መካተታቸውን አስታውቋል። ቢሮው " አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ለመቅረፅ ዩኒሴፍ 550 ሺህ ዶላር ፈቃድ ቢሰጥም፣ የፌዴራል መንግሥት በጀቱን ሙሉ በሙሉ ባለመልቀቁ እስካሁን ለስራው የዋለው 200 ሺህ ዶላር ብቻ ነው " ብሏል። የ2019 ዓ.ም. የመማርና የማስተማር ሂደት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እንደሚከናወን የትምህርት ቢሮው አስታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
በኮሬ ዞን በማሳቸው ላይ ሲሰሩ የነበሩ ሁለት አርሶ አደሮች በጥይት ተገደሉ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን፣ ጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳ ወረዳ መካከል ባለው አዋሳኝ አካባቢ፣ በማሳቸው ላይ የእርሻ ሥራ ሲያከናውኑ የነበሩ ሁለት አርሶ አደሮች በጥይት ተገደሉ። የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ አርሶ አደሮቹ በማሳቸው ላይ ሥራ ላይ እያሉ በተከፈተባቸው የጥይት ተኩስ ጥቃት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ነዋሪዎቹ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንደሰሙና በኋላም ስለ አርሶ አደሮቹ መገደል መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል። አርሶ አደሮቹ ተተኩሶባቸው ከተገደሉ በኋላ አስክሬን ለማንሳትም አስቸጋሪ ሁኔታ እንደነበር ነዋሪዎቹ አክለዋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፣ በአካባቢው ከዚህ በፊትም አርሶ አደሮች በማሳቸው ላይ ሲሰሩ ጥቃት የሚደርስባቸው ሲሆን፣ ችግሩ ላለፉት 10 ዓመታት በመቀጠሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የዞኑ ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " አርሶ አደሩ ላለፉት 10 ዓመታት መውጫና መግቢያ መንገድ ተዘግቶበት በየጊዜው በማሳው ላይ መገደል የተለመደ ቢሆን ሀገራዊ ምክክር እየተደረገ ባለበት ወቅት ጭምር ይህ ጥቃት መፈጸሙ አሳዛኝ ነው፤ ችግሩ ምን ያክል ስር የሰደደ መሆኑንም ያሳያል " ብለዋል። " ችግሩ ለረጅም ዓመታት የቀጠለና መንግሥት ዘላቂ መፍትሄ ያላበጀለት መከራ ነው " ሲሉ አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዞኑ የጸጥታና የፖለቲካ አመራሮች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ በወቅቱ አልተሳካም። በሌላ በኩል፣ የኮሬ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ባወጣው መግለጫ፣ “ፀረ ሰላም” ብሎ በገለጻቸው ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት ሁለት ንጹሃን አርሶ አደሮች መገደላቸውን አረጋግጧል። መምሪያው ከአጎራባች ዞኖች፣ ከክልሉ መንግሥትና ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በአካባቢው ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን እንደሚሰራ ገልጿል። የነዋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ጥረቶችም እንደሚጠናከሩ አስታውቋል። መምሪያው በተጨማሪም ህዝቡ በክስተቱ ሳይደናገጥ አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ :- • የተማሪዎች የምልመላ እና የምዝገባ ሂደት • በዘርፉ የሚያስፈልገውን የሰው ሃይል ለማብቃት እያከናወነ ስላላቸው ስራዎች። • ዩኒቨርሲቲው እየሰጣቸው የሚገኙ ፕሮግራሞች አይነት • የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዩኒቨርሲቲው የሽያጭ እና የሽያጭ አገልግሎት ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ካሳ ጋር ቆይታ አድርጓል። ሙሉ ቃለ መጠይቁን ያድምጡ : https://youtu.be/yPI1frQwzt0?si=EXnMCuFi_ZvxA_ky
видео или голосовое, без подписи
የሕግ ባለሙያዎች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠበቆች ላይ ተጥሎ የነበረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ አገደ። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገቢዎች ቢሮ፣ የሕግ ባለሙያዎች (ጠበቆች) ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ጋር በተያያዘ ላቀረቡት አቤቱታ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዕግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አሳውቋል። ቢሮው ለዞንና ለከተማ አስተዳደር የገቢ መሥሪያ ቤቶች ባስተላለፈው ማብራሪያ ፣ በጥብቅና ስራ የተሰማሩ የሕግ ባለሙያዎች በገንዘብ ሚኒስቴር በወጣው መመሪያ ቁጥር 1104/2018 መሠረት ለተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲመዘገቡ ተሰጥቶ የነበረው ድንጋጌ ላይ የመመሪያ ክለሳ አቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ነበር። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበውን አቤቱታ ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ፣ ጠበቆች ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲመዘገቡ የሚያዘውን መመሪያ በጠበቆች ላይ ተፈጻሚ እንዳይሆንና በዕግድ እንዲቆይ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በመሆኑም በፍርድ ቤቱ የተለያዩ መዝገቦች የታገዱ ጉዳዮች መኖራቸውን ቢሮው አረጋግጧል። ነገር ግን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባው በዕግድ መቆየቱ፣ ጠበቆችን ከሌሎች የግብር ግዴታዎች ነፃ እንደማያደርጋቸው ያሳሰበው ቢሮው ማንኛውም የሕግ ባለሙያ (ጠበቃ) የንግድ ሥራ ገቢ ግብሩን በተመለከተ በክልሉ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 301/2018 መሠረት የመክፈል ግዴታው እንደጸና ነው ብሏል። ባለሙያዎቹ እንደ ደረጃ "ለ" ግብር ከፋይነታቸው የሒሳብ መዝገብ የመያዝ ወይም በታወቀው የገቢ ማሳወቂያ ቅጽ (Form) መሠረት ግብራቸውን በወቅቱ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ነው ያለው። ይህ የፍርድ ቤት ዕግድ የሚያገለግለው ከተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ጋር ለተያያዘው ጉዳይ ብቻ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፣ የንግድ ሥራ ገቢ ግብራቸውን በሒሳብ መዝገብ የማያሳውቁ ጠበቆች እንደግብር ከፋይነታቸው ከነሐሴ 1/2018 ዓ.ም ወይም ከህዳር 1/2019 ዓም ጀምሮ በሦስተኛ ወገን ወይም በግምት የንግድ ስራ ገቢ ተወስኖ እንዲያሳውቁ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። የሂሳብ መዝገብ መያዝ የሚገባቸው ግብር ከፋዮችም ግዴታቸውን ካልተወጡ በአዋጁ የተደነገጉ አስተዳደራዊ ቅጣቶችም ተፈጻሚ እንደሚሆኑባቸው አሳውቋል። በሌላ በኩል የፌደራል ጠበቆች ማህበር የጠበቆችን የግብር አከፋፈል ሁኔታ በተመለከተ እያከናወናቸው ስላላቸው ስራዎች ለአባላቱ በሰጠው ማብራሪያ በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን እያደረገ ስለመሆኑ አንስቷል። ማህበሩ ጠበቆች ከ«ለ» ደረጃ ግብር ከፋይነት ውጪ ተደርገው የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ የሚጠየቁበትን አዲሱን አሰራር በመርህ ደረጃ ተገቢ እንዳልሆነ ያምናል ያለ ሲሆን ይህም በሕግ ማሻሻያ ሊታረም የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ከመንግስት አካላት ጋር በቀጣይነት እያነሳ ይገኛል ብሏል። በዚህ ምክንያት መመሪያው እስኪወጣ ድረስ ጠበቆች እንደ ቀድሞው አሰራር በተመጣጣኝ የገቢ መቶኛ ተቀናሽ ስሌት መሠረት ግብራቸውን እንዲከፍሉ ጊዜያዊ አሰራር እንዲፈቀድ ማህበሩ መጠቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማህበሩ ከሰጠው ማብራሪያ ላይ ተመልክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
#NationalDialogue🇪🇹 የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሚዲያዎችና ለህብረተሰቡ መልዕክት አስተላልፏል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከተጀመረ አንድ ወር መሆኑን የገለጸው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ፣ ሂደቱ አሁን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ባለፈው አንድ ወር የተሳታፊዎች መከባበር፣ መደማመጥና በጋራ ጉዳዮች ላይ መወያየት አመርቂና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጿል። በምክክሩ ሂደት አለመግባባቶች መከሰታቸውም የምክክር ሂደቱ አካል መሆኑን አስረድቷል። ኮሚሽኑ ስለሚዲያ ምን አለ ? ኮሚሽኑ በተለይ የምክክሩ ሂደት ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ሲገባ የተዛቡ፣ ያልተረጋገጡና ከእውነታው የራቁ መረጃዎች በግለሰቦች፣ ቡድኖችና በአንዳንድ የሚዲያ ባለሙያዎች ሊሰራጩ እንደሚችሉ ጠቁሟል። እንደ ኮሚሽኑ ገለጻ፣ እነዚህ የተሳሳቱ መረጃዎች በምክክሩ ላይ ስጋትና ጥርጣሬ ከመፍጠር ባለፈ፣ ህዝቡን ሊያደናግሩና የምክክሩን ሂደት ሊያወሳስቡ ይችላሉ። በመሆኑም ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑ በይፋ የሚወጡ መረጃዎችን እና በምክክሩ ቦታ የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን የሚያሰራጯቸውን የተረጋገጡ መረጃዎች ብቻ እንዲከታተል አሳስቧል። ኮሚሽኑ ለሚዲያ ተቋማት፣ ለጋዜጠኞችና ለተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተለይ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። በምክክሩ ሂደት ላይ ፦ - ገና ያልተጠናቀቀ፣ - ያልተረጋገጠ - ከቦታው በይፋ ያልተገለጸ መረጃን ማሰራጨት በህዝብ ዘንድ ያልተገባ ብዥታና መደናገር ሊፈጥር ስለሚችል፣ እንዲህ ካሉ ተግባራት እንዲቆጠቡ ኮሚሽኑ አሳስቧል። በተለይም የምክክሩ ውስጣዊ ሂደቶች፣ ውይይቶች ወይም ያልተጠናቀቁ አጀንዳዎች ላይ ግምታዊ መረጃ በማቅረብ ህዝብን ማደናገር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠይቋል። ኮሚሽኑ የሙያና የሥነ-ምግባር ጥሰት የሚፈጽሙ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎችን እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል። መሰል ተግባራት ሲታዩም ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ተጠያቂነት እንዲኖር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። ይህ ክትትልና እርምጃም ወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስገንዝቧል። ለህብረተሰቡ ምን መልዕክት ተላለፈ ? ኮሚሽኑ መላው ህብረተሰብ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከመከተልና ከማጋራት በመቆጠብ፣ የምክክሩን ሂደት በተረጋገጠ መረጃ እንዲከታተል ጥሪ አቅርቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
#AddisAbaba #NationalDialogue🇪🇹 (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) በአዲስ አበባ ጉዳይ ስምምነት የተደረሰው "የፌዴራል ተጠሪ ትሁን" በሚል ሆኖ፣ "የኦሮሚያም መቀመጫ እንድትሆን ሕገመንግስቱ እውቅና ይስጥ" የሚለው ግን "በልዩነት" ተይዞ መሆኑ ተገለጸ። በተለይ 250 ሰዎችን ከያዘው ቡድን ጀምሮ እያከራከረ የመጣው የአዲስ አበባ ጉዳይ፣ 500 ሰዎች በያዘው ቡድንም ካጨቃጨቀ በኋላ ትናንት ያስማማው፥ ከተማዋ "የፌዴራል ተጠሪ ትሁን" በሚለው ሁሉም ተስማምቶ፣ "የኦሮሚያ ክልልም መቀመጫ እንድትሆን ህገመንግስቱ እውቅና ይስጥ" የሚለው ሀሳብ ግን "በልዩነት" ተይዞ መሆኑን የአጀንዳው ተመካካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ጉዳይ ይበልጥ ያከራከረው በምክክሩ ሂደት መሰረት በ10 እና 50 ሰዎች የተደራጁ ንዑሳንና ጥቃቅን ቡድኖች አመንጭተው በ250 ሰዎች ለተደራጀው "ስልታዊ" ቡድን ያላቀረቡት "አዲስ አበባ የኦሮሚያ መቀመጫ እንድትሆን ሕገመንግስቱ እውቅና ይስጥ" በሚል በኦሮሚያ ተወካዮች በኩል አዲስ አጀንዳ በመቅረቡና ሌሎች ክልሎች ይህ እንዲሆን ባለመቀበላቸው ነው። ባለፉት ሳምንታት በተደረጉት ምክክሮች፣ ጉዳዩ በተመለከተ የተለያዩ ሀሳቦች እየቀረቡ ከማከራከራቸውም በላይ ተመካካሪዎች ቃለጉባዔ "አንፈርምም" ብለው ከአዳራሽ እንዲወጡ ጭምር አድርጎ ነበር። ከዚያ በኋላ በተደረጉ ምክክሮች "አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌዴራሉ መንግስት ይሁን" በሚለው ተመካካሪዎች ስምምነት እንደደረሱ፣ ይህ ሲሆን ግን "የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ከተማዋ የኦሮሚያ ክልልም መቀመጫ እንድትሆን በህገመንግስቱ እውቅና እንዲሰጥ" ቅድመ ሁኔታ ማቅረባቸው ተገልጿል። የፌዴራል ተጠሪ ትሁን በሚለው ከስምምነት ቢደረስም ከተማዋ የኦሮሚያ ክልልም መቀመጫ እንድትሆን በሕገመንግስቱ እውቅና እንዲሰጥ በሚል ከዚሁ ሀሳብ ተከትሎ ምክረ ሀሳብ መቅረቡ፣ በሌላ በኩል "ለኦሮሚያ መቀመጫነቷ እውቅና ይሰጥ ከተባለማ ከተማዋ የሌሎች ክልሎችም መቀመጫ እንድትሆን እውቅና ይሰጥ" የሚል ሀሳብ አስነስቷል። ይህ ሁሉ በ250 ሰዎች ከተዋቀረው "ስልታዊ ቡድን" የተደራጁ ምክረ ሀሳቦችን በተቀበለው በ500 ሰዎችን በያዘው "የሥራ ቡድን" ከሰሞኑ ሲያመካክር፣ ሲያከራክር፣ ሲያጨቃጭ የቆየ ጉዳይ ሲሆን፣ ሙሉ አጀንዳው ተጠናቆ ወደ ቀጣዩ የምክክር ቡድን ለማለፍ ሀሳቦቹ በቃለጉባዔ ተጠናቅረው የቡድኑ ተመካካሪዎች እንዲፈርሙ ይጠበቅበት ነበር። የአዲስ አበባ ሕጋዊ አቋም ከዚያ በፊት በነበሩት ቀናት እያከራከረ ቢቆይም ትናንት የተጠናቀረው ቃለጉባዔ ላይ ግን ስምምነት ተደርሶ ተመካካሪዎቹ መፈራረማቸውን ተናግረዋል። እንዲሁ " በአዲስ አበባ ጉዳይ ከስምምነት ተደርሷል " ተባለ እንጅ ሲያጨቃጭቅ በሰነበተው ጉዳይ በምን መልኩ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ያልተነገረ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመካካሪዎችን ማብራሪያ ጠይቋል። በ"ሥራ ቡድኑ" ስለአዲስ አበባ ጉዳይ ከስምምነት የተደረሰው በምን መልኩ ነው ? አንድ የዚሁ የፌዴራል ከተሞች ጉዳይ አጀንዳ ተመካካሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ "ሁሉም የተስማማበት አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌዴራል ይሁን" በሚል መሆኑን ተናግረዋል። ከተማዋ ራሷን በራሷ የምታስተዳድር ለፌዴራል ተጠሪ እንድትሆን በቃለጉባዔው መነበቡን፣ ተመካካሪዎች መፈራረማቸውን አስረድተዋል። ሲፈረም ግን "በልዩነት" የተያዘ ጉዳይ መኖሩንም ተናግረዋል። "አዲስ አበባ የፌዴራል መንግስት ተጠሪ ትሁን" በሚለው ከስምምነት ሲደረስ፣ ከተማዋ "የኦሮሚያ ክልልም መቀመጫ እንድትሆን በሕገመንግስቱ እውቅና ይሰጥ" የሚል ምክረ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን፣ ይህም አከራክሮ "በልዩነት" መያዙን ተመካካሪው አስረድተዋል። "የኦሮሚያም መቀመጫ እንድትሆን እውቅና ይሰጥ" በሚል የቀረበው ምክረ ሀሳብ "እንዳለ ሆኖ በልዩነት ነው የተፈረመው" ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ምክረ ሀሳብ "አሁንም እንዳለ ነው፤ አልተሰረዘም" ብለዋል። ቡድናቸው ትናንት በምን እንደተስማማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያስረዱ ሌላኛው የዚሁ አጀንዳ ተመካካሪ፣ "አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌዴራል ይሁን የሚለው ሁሉም የተስማማበት ነው" ሲሉ ተናግረዋል። "አዲስ አበባ የፌዴራል ተጠሪ ከሆነች ለኦሮሚያም መቀመጫነት በሕገመንግስቱ እውቅና ይሰጥ" በሚል ምክረ ሀሳብ ከኦሮሚያ ተወካዮች መቅረቡን ገልጸው፣ "በኦሮሚያ ተመካካሪዎች በኩል ይህ ሀሳብ ቀርቧል፤ ሌላው አካል ግን አልተቀበለውም" ብለዋል። "በልዩነት የተያዘውም ሀሳብ ይሄ ነው። ሌላው በስምምነት ነው ያለቀው" ነው ያሉት። ሀሳቦቹ ገና በቀጣዮቹ ቡድኖች እንደሚመከርባቸውም ተገልጿል። በተያያዘ፣ ኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ልዩ ተጠቃሚ እንዲሆን ቀርቦ የነበረው ምክረ ሀሳብ "ልዩ ጥቅም" የሚለው ቀርቶ "የጋራ ጥቅም" እንዲሆን ስምምነት መደረሱን ተመካካሪው ገልጸዋል። "የጋራ ጥቅም" በምን መልኩ ለሚለውና ለአፈጻጸሙ ሕግ እንዲወጣለት መመከሩ ተመልክቷል። ስለአዲስ አበባ ያለልዩነት ስምምነት የተደረሰባቸው ሌሎች ጉዳዮች ምንድን ናቸው? "አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያላትን ግንኙነት" በተመለከተ፥ "ሁለቱም አካላት ተገናኝተው የሚሻላቸውን እንዲነጋገሩና በሕግ እንዲሰፍር" በሥራ ቡድኑ ስምምነት መደረሱን እኝሁ ተሳታፊ ተናግረዋል። "የአዲስ አበባ ከተማ የፖሊስና ፍርድ ቤት ጉዳይ" በተመለከተ፣ ከተማዋ "ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚቋቋም፣ ራሱን የቻለ የራሷ ፖሊስና ፍርድ ቤት እንዲኖራት" በሚል እንደተመከረበት ነግረውናል። እንዲሁም "የአዲስ አበባ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የአካታችነት ጉዳይ"ን በተመለከተ፣ "ሁሉንም አካታች በሚያደርግ፣ ከዚህ በፊት ያልተካተተ ቅርስ ካለ ተካቶ እንዲቀጥል፤ ሁሉም ብሔረሰብ አካታች የሆነ ቅርስ በከተማዋ እንዲቀመጥ" በሚል በቡድኑ ከስምምነት መደረሱን ተናግረዋል። ሌላኛው ተሳታፊም በተጠቃለለው የሥራ ቡድን ሪፖርት፣ "አዲስ አበባ ራሱን የቻለ ፍርድ ቤትና ፖሊስ ሊኖራት ይገባል" በሚል መመከሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በ"አዲስ አበባ የሥራ ቋንቋ ጉዳይ" ደግሞ፥ የፌዴራሉ የሥራ ቋንቋ የአዲስ አበባም የሥራ ቋንቋ እንዲሆን፣ በጥናት ተመርኩዞ የውጭ ቋንቋዎች መጨመር ካለባቸው በሕግ ዝርዝር ተዘጋጅተው እንዲጨመሩ ምክረ ሀሳብ መቅረቡን ተናግረዋል። የድሬዳዋ ጉዳይስ ? የፌዴራል ከተሞች ጉዳይ በተሰኘው ዋና አጀንዳ፣ ከአዲስ አበባ ጉዳይ በተጨማሪ የድሬዳዋ ጉዳይ አንዱ ነው። ጉዳዩ ያለልዩነት ስምምነት እንደተደሰበት ተገልጿል። ስለድሬ ጉዳይ "ለኦሮሚያ ትሁን"፣ "ለሶማሌ ትሁን"፣ "ለፌዴራል መንግስቱ ተጠሪ ሆና ትቀጥል" የሚሉ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ ነበር። ይሁን እንጅ፣ 250ም ሆነ 500 ሰዎችን በያዙ ቡድኖች ተጠሪነቷ ለፌድራል መንግስት ሆኖ እንዲቀጥል አመዛኝ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ ነበር። በዚሁ አጀንዳ ትናንት ተመካካሪዎች ተስማምተው ሲፈራረሙም፣ "የፌዴራል ተጠሪ ትሁን" በሚል ስምምነት መደረሱን ተመካካሪዎች ገልጸዋል። በተመካካሪዎች የተመከረባቸው እስካሁን የተነሱት ምክረ ሀሳቦች፥ በአስማሚ ኮሚቴ የሚቀርቡ ካሉ ቀርበው በዚያ የሚታዩ፣ ገና በ4ሺው ጉባያተኞች ጠቅላላ ጉባዔ ጭምር እንዲቀርቡ ተደርገው የሚመከርባቸው ናቸው። ቲ ክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
" አሁን ላይ ከዋና ዋና ከተሞች ርቀው በሚገኙ አከባቢዎች ከሚደረግ የቡድን ዝርፊያ በበስተቀር የሳምንቱ ሐሙስ የነበረው ሰልፍም ቀርቷል " - አቶ ዮሐንስ ሀቢቢ ላለፉት ወራት በደቡብ አፍሪካ በስፋት ሲስተዋል የነበረው " የስደተኞች ይውጡልን " እንቅስቃሴ በሀገሪቱ የምርጫ ወቅት እየተቃረበ ቢመጣም ከዚህ ቀደም ከነበረው በተቃራኒ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ወካይ ዮሐንስ ሀቢቢ " የፀረ ስደተኞች እንቅስቃሴ እንደተፈራው አይደለም "ሲሉ ገልፀዋል። አሁን ላይ ከሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ወጣ ባሉ አከባቢዎች በቡድን ከሚፈፀም ንጥቂያ እና ዘረፋ በስተቀር የ " ይወጡልን " ሰልፍ መቀዛቀዙን አስረድተዋል። " የነበረው ከፍተኛ ስጋት የተነሳ ለወራት በስራ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሮብን ነበር " ያሉ ሌላ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ነጋዴ " አሁን ላይ ያለው አንፃራዊ መረጋጋት ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ዘመቻ ባልነበረባቸው የአከባቢ ምርጫ ወቅቶች ጭምር ከነበረው የተሻለ ነው " ሲሉ ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ደቡብ አፍሪካ ከ80,000 በላይ ያልተመዘገቡ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እና ለማጓጓዝ ከአቪዬሽን፣ የትራንስፖርት እና የቆይታ ወጪዎች ጋር ተያይዞ 18 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ወጪ ማድረጓን በመግለፅ የካሳ ጥያቄ (ወጪ እንዲሸፍኑ) ኢትዮጵያን ጨምሮ እነ ማላዊና ናይጄሪያን መጠየቋን አሶሺየትድ ፕረስ እና አፍሪካ ዶት ኮም ዘግበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
የመቐለ ዓቃቤ ሕግ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ ጠየቀ። ከዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተያይዞ የተሰጠውን የሁለቱን ተከሳሾች " ነጻ ናችሁ " የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማቅረቡን የመቐለ ከተማ ዓቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት አስታወቀ። የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ታደሰ ባይሩ የመቐለ ማዕከላይ ፍርድ ቤት በዘውዲ ሃፍቱ ግድያ ተከሰው በነበሩ ግለሰቦች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት ውሳኔ ሰጥቶ መዝገቡን ዘግቶ እንደነበር ገልጸዋል። ነገር ግን ተከሳሾቹ ለሰበር ሰሚ ችሎት ባቀረቡት ይግባኝ በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑን ኃላፊው ጠቁመዋል። ዓቃቤ ሕግም ውሳኔውን እንደማይቀበል በመግለጽ ለትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረቡን አስረድተዋል። ታደሰ እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹን በነፃ የሚያሰናብተው ውሳኔ አግባብ አይደለም በሚል እና የቀደመው ውሳኔ በዳኞች 2 ለ1 ድምፅ መሻሩን በመጥቀስ ይግባኙ ቀርቧል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ “ማስረጃ ጠፍቷል” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ግን ፍጹም ከእውነት የራቀ መሆኑን የዓቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ገልጸዋል። በተጨማሪም፣ ከዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ሁለቱ ግለሰቦች በአሁኑ ወቅት በመቐለ ከተማ መኖራቸውንም ሆነ አለመኖራቸውን እንደማያውቁ አስታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
" የዘውዱ ገዳዮች በነጻ መሰናበታቸው 'ዘውዱን ለሁለተኛ ጊዜ እንደመግደል ነው' " - ዘጠኝ ማኅበራት የ32 ዓመቷ ዘውዱ ሃፍቱን በመግደል የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ያሬድ ገብረስላሴ በላይ እና አንገሶም ሃይለማርያም በነፃ መለቀቃቸውን ተከትሎ 9 የሴቶች መብት እና የፍትሕ ጉዳይ ላይ ሚሰሩ ሲቪል ማኅበራት ተቃውሞ አሰምተዋል። ዘውዱ ነሐሴ 2015 ዓ/ም በመቐለ ከተማ ከጓደኛዋ ሰምሃል ገብረዝያብሔር…
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи