tgindex
EBS TV

https://telega.io/c/etv_newss

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
42
Всего постов
115
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 548
+9 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
79
40 постов
Вовлечённость
1,7%
к подписчикам
Постов в день
6,0
всего 115
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
107
1/48двое суток
122
1/72трое суток
132

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • 15 авг.261из tikvahethiopia

    የሕግ ባለሙያዎች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠበቆች ላይ ተጥሎ የነበረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ አገደ። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገቢዎች ቢሮ፣ የሕግ ባለሙያዎች (ጠበቆች) ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ጋር በተያያዘ ላቀረቡት አቤቱታ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዕግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አሳውቋል። ቢሮው ለዞንና ለከተማ አስተዳደር የገቢ መሥሪያ ቤቶች ባስተላለፈው ማብራሪያ ፣ በጥብቅና ስራ የተሰማሩ የሕግ ባለሙያዎች በገንዘብ ሚኒስቴር በወጣው መመሪያ ቁጥር 1104/2018 መሠረት ለተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲመዘገቡ ተሰጥቶ የነበረው ድንጋጌ ላይ የመመሪያ ክለሳ አቤቱታ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ነበር። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበውን አቤቱታ ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ፣ ጠበቆች ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲመዘገቡ የሚያዘውን መመሪያ በጠበቆች ላይ ተፈጻሚ እንዳይሆንና በዕግድ እንዲቆይ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በመሆኑም በፍርድ ቤቱ የተለያዩ መዝገቦች የታገዱ ጉዳዮች መኖራቸውን ቢሮው አረጋግጧል። ነገር ግን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባው በዕግድ መቆየቱ፣ ጠበቆችን ከሌሎች የግብር ግዴታዎች ነፃ እንደማያደርጋቸው ያሳሰበው ቢሮው ማንኛውም የሕግ ባለሙያ (ጠበቃ) የንግድ ሥራ ገቢ ግብሩን በተመለከተ በክልሉ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 301/2018 መሠረት የመክፈል ግዴታው እንደጸና ነው ብሏል። ባለሙያዎቹ እንደ ደረጃ "ለ" ግብር ከፋይነታቸው የሒሳብ መዝገብ የመያዝ ወይም በታወቀው የገቢ ማሳወቂያ ቅጽ (Form) መሠረት ግብራቸውን በወቅቱ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ነው ያለው። ይህ የፍርድ ቤት ዕግድ የሚያገለግለው ከተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ጋር ለተያያዘው ጉዳይ ብቻ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፣ የንግድ ሥራ ገቢ ግብራቸውን በሒሳብ መዝገብ የማያሳውቁ ጠበቆች እንደግብር ከፋይነታቸው ከነሐሴ 1/2018 ዓ.ም ወይም ከህዳር 1/2019 ዓም ጀምሮ በሦስተኛ ወገን ወይም በግምት የንግድ ስራ ገቢ ተወስኖ እንዲያሳውቁ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። የሂሳብ መዝገብ መያዝ የሚገባቸው ግብር ከፋዮችም ግዴታቸውን ካልተወጡ በአዋጁ የተደነገጉ አስተዳደራዊ ቅጣቶችም ተፈጻሚ እንደሚሆኑባቸው አሳውቋል። በሌላ በኩል የፌደራል ጠበቆች ማህበር የጠበቆችን የግብር አከፋፈል ሁኔታ በተመለከተ እያከናወናቸው ስላላቸው ስራዎች ለአባላቱ በሰጠው ማብራሪያ በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን እያደረገ ስለመሆኑ አንስቷል። ማህበሩ ጠበቆች ከ«ለ» ደረጃ ግብር ከፋይነት ውጪ ተደርገው የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ የሚጠየቁበትን አዲሱን አሰራር በመርህ ደረጃ ተገቢ እንዳልሆነ ያምናል ያለ ሲሆን ይህም በሕግ ማሻሻያ ሊታረም የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ከመንግስት አካላት ጋር በቀጣይነት እያነሳ ይገኛል ብሏል። በዚህ ምክንያት መመሪያው እስኪወጣ ድረስ ጠበቆች እንደ ቀድሞው አሰራር በተመጣጣኝ የገቢ መቶኛ ተቀናሽ ስሌት መሠረት ግብራቸውን እንዲከፍሉ ጊዜያዊ አሰራር እንዲፈቀድ ማህበሩ መጠቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማህበሩ ከሰጠው ማብራሪያ ላይ ተመልክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • без подписи

  • #NationalDialogue🇪🇹 የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሚዲያዎችና ለህብረተሰቡ መልዕክት አስተላልፏል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከተጀመረ አንድ ወር መሆኑን የገለጸው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ፣ ሂደቱ አሁን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ባለፈው አንድ ወር የተሳታፊዎች መከባበር፣ መደማመጥና በጋራ ጉዳዮች ላይ መወያየት አመርቂና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጿል። በምክክሩ ሂደት አለመግባባቶች መከሰታቸውም የምክክር ሂደቱ አካል መሆኑን አስረድቷል። ኮሚሽኑ ስለሚዲያ ምን አለ ? ኮሚሽኑ በተለይ የምክክሩ ሂደት ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ሲገባ የተዛቡ፣ ያልተረጋገጡና ከእውነታው የራቁ መረጃዎች በግለሰቦች፣ ቡድኖችና በአንዳንድ የሚዲያ ባለሙያዎች ሊሰራጩ እንደሚችሉ ጠቁሟል። እንደ ኮሚሽኑ ገለጻ፣ እነዚህ የተሳሳቱ መረጃዎች በምክክሩ ላይ ስጋትና ጥርጣሬ ከመፍጠር ባለፈ፣ ህዝቡን ሊያደናግሩና የምክክሩን ሂደት ሊያወሳስቡ ይችላሉ። በመሆኑም ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑ በይፋ የሚወጡ መረጃዎችን እና በምክክሩ ቦታ የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን የሚያሰራጯቸውን የተረጋገጡ መረጃዎች ብቻ እንዲከታተል አሳስቧል። ኮሚሽኑ ለሚዲያ ተቋማት፣ ለጋዜጠኞችና ለተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተለይ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። በምክክሩ ሂደት ላይ ፦ - ገና ያልተጠናቀቀ፣ - ያልተረጋገጠ - ከቦታው በይፋ ያልተገለጸ መረጃን ማሰራጨት በህዝብ ዘንድ ያልተገባ ብዥታና መደናገር ሊፈጥር ስለሚችል፣ እንዲህ ካሉ ተግባራት እንዲቆጠቡ ኮሚሽኑ አሳስቧል። በተለይም የምክክሩ ውስጣዊ ሂደቶች፣ ውይይቶች ወይም ያልተጠናቀቁ አጀንዳዎች ላይ ግምታዊ መረጃ በማቅረብ ህዝብን ማደናገር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠይቋል። ኮሚሽኑ የሙያና የሥነ-ምግባር ጥሰት የሚፈጽሙ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎችን እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል። መሰል ተግባራት ሲታዩም ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ተጠያቂነት እንዲኖር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። ይህ ክትትልና እርምጃም ወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስገንዝቧል። ለህብረተሰቡ ምን መልዕክት ተላለፈ ? ኮሚሽኑ መላው ህብረተሰብ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከመከተልና ከማጋራት በመቆጠብ፣ የምክክሩን ሂደት በተረጋገጠ መረጃ እንዲከታተል ጥሪ አቅርቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • без подписи

  • #AddisAbaba #NationalDialogue🇪🇹 (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) በአዲስ አበባ ጉዳይ ስምምነት የተደረሰው "የፌዴራል ተጠሪ ትሁን" በሚል ሆኖ፣ "የኦሮሚያም መቀመጫ እንድትሆን ሕገመንግስቱ እውቅና ይስጥ" የሚለው ግን "በልዩነት" ተይዞ መሆኑ ተገለጸ። በተለይ 250 ሰዎችን ከያዘው ቡድን ጀምሮ እያከራከረ የመጣው የአዲስ አበባ ጉዳይ፣ 500 ሰዎች በያዘው ቡድንም ካጨቃጨቀ በኋላ ትናንት ያስማማው፥ ከተማዋ "የፌዴራል ተጠሪ ትሁን" በሚለው ሁሉም ተስማምቶ፣ "የኦሮሚያ ክልልም መቀመጫ እንድትሆን ህገመንግስቱ እውቅና ይስጥ" የሚለው ሀሳብ ግን "በልዩነት" ተይዞ መሆኑን የአጀንዳው ተመካካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ጉዳይ ይበልጥ ያከራከረው በምክክሩ ሂደት መሰረት በ10 እና 50 ሰዎች የተደራጁ ንዑሳንና ጥቃቅን ቡድኖች አመንጭተው በ250 ሰዎች ለተደራጀው "ስልታዊ" ቡድን ያላቀረቡት "አዲስ አበባ የኦሮሚያ መቀመጫ እንድትሆን ሕገመንግስቱ እውቅና ይስጥ" በሚል በኦሮሚያ ተወካዮች በኩል አዲስ አጀንዳ በመቅረቡና ሌሎች ክልሎች ይህ እንዲሆን ባለመቀበላቸው ነው። ባለፉት ሳምንታት በተደረጉት ምክክሮች፣ ጉዳዩ በተመለከተ የተለያዩ ሀሳቦች እየቀረቡ ከማከራከራቸውም በላይ ተመካካሪዎች ቃለጉባዔ "አንፈርምም" ብለው ከአዳራሽ እንዲወጡ ጭምር አድርጎ ነበር። ከዚያ በኋላ በተደረጉ ምክክሮች "አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌዴራሉ መንግስት ይሁን" በሚለው ተመካካሪዎች ስምምነት እንደደረሱ፣ ይህ ሲሆን ግን "የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ከተማዋ የኦሮሚያ ክልልም መቀመጫ እንድትሆን በህገመንግስቱ እውቅና እንዲሰጥ" ቅድመ ሁኔታ ማቅረባቸው ተገልጿል። የፌዴራል ተጠሪ ትሁን በሚለው ከስምምነት ቢደረስም ከተማዋ የኦሮሚያ ክልልም መቀመጫ እንድትሆን በሕገመንግስቱ እውቅና እንዲሰጥ በሚል ከዚሁ ሀሳብ ተከትሎ ምክረ ሀሳብ መቅረቡ፣ በሌላ በኩል "ለኦሮሚያ መቀመጫነቷ እውቅና ይሰጥ ከተባለማ ከተማዋ የሌሎች ክልሎችም መቀመጫ እንድትሆን እውቅና ይሰጥ" የሚል ሀሳብ አስነስቷል። ይህ ሁሉ በ250 ሰዎች ከተዋቀረው "ስልታዊ ቡድን" የተደራጁ ምክረ ሀሳቦችን በተቀበለው በ500 ሰዎችን በያዘው "የሥራ ቡድን" ከሰሞኑ ሲያመካክር፣ ሲያከራክር፣ ሲያጨቃጭ የቆየ ጉዳይ ሲሆን፣ ሙሉ አጀንዳው ተጠናቆ ወደ ቀጣዩ የምክክር ቡድን ለማለፍ ሀሳቦቹ በቃለጉባዔ ተጠናቅረው የቡድኑ ተመካካሪዎች እንዲፈርሙ ይጠበቅበት ነበር። የአዲስ አበባ ሕጋዊ አቋም ከዚያ በፊት በነበሩት ቀናት እያከራከረ ቢቆይም ትናንት የተጠናቀረው ቃለጉባዔ ላይ ግን ስምምነት ተደርሶ ተመካካሪዎቹ መፈራረማቸውን ተናግረዋል። እንዲሁ " በአዲስ አበባ ጉዳይ ከስምምነት ተደርሷል " ተባለ እንጅ ሲያጨቃጭቅ በሰነበተው ጉዳይ በምን መልኩ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ያልተነገረ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመካካሪዎችን ማብራሪያ ጠይቋል። በ"ሥራ ቡድኑ" ስለአዲስ አበባ ጉዳይ ከስምምነት የተደረሰው በምን መልኩ ነው ? አንድ የዚሁ የፌዴራል ከተሞች ጉዳይ አጀንዳ ተመካካሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ "ሁሉም የተስማማበት አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌዴራል ይሁን" በሚል መሆኑን ተናግረዋል። ከተማዋ ራሷን በራሷ የምታስተዳድር ለፌዴራል ተጠሪ እንድትሆን በቃለጉባዔው መነበቡን፣ ተመካካሪዎች መፈራረማቸውን አስረድተዋል። ሲፈረም ግን "በልዩነት" የተያዘ ጉዳይ መኖሩንም ተናግረዋል። "አዲስ አበባ የፌዴራል መንግስት ተጠሪ ትሁን" በሚለው ከስምምነት ሲደረስ፣ ከተማዋ "የኦሮሚያ ክልልም መቀመጫ እንድትሆን በሕገመንግስቱ እውቅና ይሰጥ" የሚል ምክረ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን፣ ይህም አከራክሮ "በልዩነት" መያዙን ተመካካሪው አስረድተዋል። "የኦሮሚያም መቀመጫ እንድትሆን እውቅና ይሰጥ" በሚል የቀረበው ምክረ ሀሳብ "እንዳለ ሆኖ በልዩነት ነው የተፈረመው" ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ምክረ ሀሳብ "አሁንም እንዳለ ነው፤ አልተሰረዘም" ብለዋል። ቡድናቸው ትናንት በምን እንደተስማማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያስረዱ ሌላኛው የዚሁ አጀንዳ ተመካካሪ፣ "አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌዴራል ይሁን የሚለው ሁሉም የተስማማበት ነው" ሲሉ ተናግረዋል። "አዲስ አበባ የፌዴራል ተጠሪ ከሆነች ለኦሮሚያም መቀመጫነት በሕገመንግስቱ እውቅና ይሰጥ" በሚል ምክረ ሀሳብ ከኦሮሚያ ተወካዮች መቅረቡን ገልጸው፣ "በኦሮሚያ ተመካካሪዎች በኩል ይህ ሀሳብ ቀርቧል፤ ሌላው አካል ግን አልተቀበለውም" ብለዋል። "በልዩነት የተያዘውም ሀሳብ ይሄ ነው። ሌላው በስምምነት ነው ያለቀው" ነው ያሉት። ሀሳቦቹ ገና በቀጣዮቹ ቡድኖች እንደሚመከርባቸውም ተገልጿል። በተያያዘ፣ ኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ልዩ ተጠቃሚ እንዲሆን ቀርቦ የነበረው ምክረ ሀሳብ "ልዩ ጥቅም" የሚለው ቀርቶ "የጋራ ጥቅም" እንዲሆን ስምምነት መደረሱን ተመካካሪው ገልጸዋል። "የጋራ ጥቅም" በምን መልኩ ለሚለውና ለአፈጻጸሙ ሕግ እንዲወጣለት መመከሩ ተመልክቷል። ስለአዲስ አበባ ያለልዩነት ስምምነት የተደረሰባቸው ሌሎች ጉዳዮች ምንድን ናቸው? "አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያላትን ግንኙነት" በተመለከተ፥ "ሁለቱም አካላት ተገናኝተው የሚሻላቸውን እንዲነጋገሩና በሕግ እንዲሰፍር" በሥራ ቡድኑ ስምምነት መደረሱን እኝሁ ተሳታፊ ተናግረዋል። "የአዲስ አበባ ከተማ የፖሊስና ፍርድ ቤት ጉዳይ" በተመለከተ፣ ከተማዋ "ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚቋቋም፣ ራሱን የቻለ የራሷ ፖሊስና ፍርድ ቤት እንዲኖራት" በሚል እንደተመከረበት ነግረውናል። እንዲሁም "የአዲስ አበባ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የአካታችነት ጉዳይ"ን በተመለከተ፣ "ሁሉንም አካታች በሚያደርግ፣ ከዚህ በፊት ያልተካተተ ቅርስ ካለ ተካቶ እንዲቀጥል፤ ሁሉም ብሔረሰብ አካታች የሆነ ቅርስ በከተማዋ እንዲቀመጥ" በሚል በቡድኑ ከስምምነት መደረሱን ተናግረዋል። ሌላኛው ተሳታፊም በተጠቃለለው የሥራ ቡድን ሪፖርት፣ "አዲስ አበባ ራሱን የቻለ ፍርድ ቤትና ፖሊስ ሊኖራት ይገባል" በሚል መመከሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በ"አዲስ አበባ የሥራ ቋንቋ ጉዳይ" ደግሞ፥ የፌዴራሉ የሥራ ቋንቋ የአዲስ አበባም የሥራ ቋንቋ እንዲሆን፣ በጥናት ተመርኩዞ የውጭ ቋንቋዎች መጨመር ካለባቸው በሕግ ዝርዝር ተዘጋጅተው እንዲጨመሩ ምክረ ሀሳብ መቅረቡን ተናግረዋል። የድሬዳዋ ጉዳይስ ? የፌዴራል ከተሞች ጉዳይ በተሰኘው ዋና አጀንዳ፣ ከአዲስ አበባ ጉዳይ በተጨማሪ የድሬዳዋ ጉዳይ አንዱ ነው። ጉዳዩ ያለልዩነት ስምምነት እንደተደሰበት ተገልጿል። ስለድሬ ጉዳይ "ለኦሮሚያ ትሁን"፣ "ለሶማሌ ትሁን"፣ "ለፌዴራል መንግስቱ ተጠሪ ሆና ትቀጥል" የሚሉ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ ነበር። ይሁን እንጅ፣ 250ም ሆነ 500 ሰዎችን በያዙ ቡድኖች ተጠሪነቷ ለፌድራል መንግስት ሆኖ እንዲቀጥል አመዛኝ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ ነበር። በዚሁ አጀንዳ ትናንት ተመካካሪዎች ተስማምተው ሲፈራረሙም፣ "የፌዴራል ተጠሪ ትሁን" በሚል ስምምነት መደረሱን ተመካካሪዎች ገልጸዋል። በተመካካሪዎች የተመከረባቸው እስካሁን የተነሱት ምክረ ሀሳቦች፥ በአስማሚ ኮሚቴ የሚቀርቡ ካሉ ቀርበው በዚያ የሚታዩ፣ ገና በ4ሺው ጉባያተኞች ጠቅላላ ጉባዔ ጭምር እንዲቀርቡ ተደርገው የሚመከርባቸው ናቸው። ቲ ክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • без подписи

  • ‎" አሁን ላይ ከዋና ዋና ከተሞች ርቀው በሚገኙ አከባቢዎች ከሚደረግ የቡድን ዝርፊያ በበስተቀር የሳምንቱ ሐሙስ የነበረው ሰልፍም ቀርቷል " - አቶ ዮሐንስ ሀቢቢ ‎ ‎ላለፉት ወራት በደቡብ አፍሪካ በስፋት ሲስተዋል የነበረው " የስደተኞች ይውጡልን " እንቅስቃሴ በሀገሪቱ የምርጫ ወቅት እየተቃረበ ቢመጣም ከዚህ ቀደም ከነበረው በተቃራኒ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ‎ ‎ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ወካይ ዮሐንስ ሀቢቢ " የፀረ ስደተኞች እንቅስቃሴ እንደተፈራው አይደለም "ሲሉ ገልፀዋል። ‎ ‎አሁን ላይ ከሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ወጣ ባሉ አከባቢዎች በቡድን ከሚፈፀም ንጥቂያ እና ዘረፋ በስተቀር የ " ይወጡልን " ሰልፍ መቀዛቀዙን አስረድተዋል። ‎ ‎" የነበረው ከፍተኛ ስጋት የተነሳ ለወራት በስራ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሮብን ነበር " ያሉ ሌላ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ነጋዴ " አሁን ላይ ያለው አንፃራዊ መረጋጋት ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ዘመቻ ባልነበረባቸው የአከባቢ ምርጫ ወቅቶች ጭምር ከነበረው የተሻለ ነው " ሲሉ ገልፀዋል። ‎ ‎ይህ በእንዲህ እንዳለ ደቡብ አፍሪካ ከ80,000 በላይ ያልተመዘገቡ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እና ለማጓጓዝ ከአቪዬሽን፣ የትራንስፖርት እና የቆይታ ወጪዎች ጋር ተያይዞ 18 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ወጪ ማድረጓን በመግለፅ የካሳ ጥያቄ (ወጪ እንዲሸፍኑ) ኢትዮጵያን ጨምሮ እነ ማላዊና ናይጄሪያን መጠየቋን አሶሺየትድ ፕረስ እና አፍሪካ ዶት ኮም ዘግበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • без подписи

  • የመቐለ ዓቃቤ ሕግ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ ጠየቀ። ከዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተያይዞ የተሰጠውን የሁለቱን ተከሳሾች " ነጻ ናችሁ " የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማቅረቡን የመቐለ ከተማ ዓቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት አስታወቀ። የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ታደሰ ባይሩ የመቐለ ማዕከላይ ፍርድ ቤት በዘውዲ ሃፍቱ ግድያ ተከሰው በነበሩ ግለሰቦች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት ውሳኔ ሰጥቶ መዝገቡን ዘግቶ እንደነበር ገልጸዋል። ነገር ግን ተከሳሾቹ ለሰበር ሰሚ ችሎት ባቀረቡት ይግባኝ በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑን ኃላፊው ጠቁመዋል። ዓቃቤ ሕግም ውሳኔውን እንደማይቀበል በመግለጽ ለትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረቡን አስረድተዋል። ታደሰ እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹን በነፃ የሚያሰናብተው ውሳኔ አግባብ አይደለም በሚል እና የቀደመው ውሳኔ በዳኞች 2 ለ1 ድምፅ መሻሩን በመጥቀስ ይግባኙ ቀርቧል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ “ማስረጃ ጠፍቷል” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ግን ፍጹም ከእውነት የራቀ መሆኑን የዓቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ገልጸዋል። በተጨማሪም፣ ከዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ሁለቱ ግለሰቦች በአሁኑ ወቅት በመቐለ ከተማ መኖራቸውንም ሆነ አለመኖራቸውን እንደማያውቁ አስታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • без подписи

  • " የዘውዱ ገዳዮች በነጻ መሰናበታቸው 'ዘውዱን ለሁለተኛ ጊዜ እንደመግደል ነው' " - ዘጠኝ ማኅበራት የ32 ዓመቷ ዘውዱ ሃፍቱን በመግደል የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ያሬድ ገብረስላሴ በላይ እና አንገሶም ሃይለማርያም በነፃ መለቀቃቸውን ተከትሎ 9 የሴቶች መብት እና የፍትሕ ጉዳይ ላይ ሚሰሩ ሲቪል ማኅበራት ተቃውሞ አሰምተዋል። ዘውዱ ነሐሴ 2015 ዓ/ም በመቐለ ከተማ ከጓደኛዋ ሰምሃል ገብረዝያብሔር…

  • без подписи

  • без подписи

  • " የዘውዱ ገዳዮች በነጻ መሰናበታቸው 'ዘውዱን ለሁለተኛ ጊዜ እንደመግደል ነው' " - ዘጠኝ ማኅበራት የ32 ዓመቷ ዘውዱ ሃፍቱን በመግደል የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ያሬድ ገብረስላሴ በላይ እና አንገሶም ሃይለማርያም በነፃ መለቀቃቸውን ተከትሎ 9 የሴቶች መብት እና የፍትሕ ጉዳይ ላይ ሚሰሩ ሲቪል ማኅበራት ተቃውሞ አሰምተዋል። ዘውዱ ነሐሴ 2015 ዓ/ም በመቐለ ከተማ ከጓደኛዋ ሰምሃል ገብረዝያብሔር ጋር በመንገድ ላይ ሳለች አንድ ተሽከርካሪ አጠገባቸው ይደርሳል። ዘውዱ ተሽከርካሪው ውስጥ ካሉ ሰዎች ጾታዊ ጥቃት ይፈጸምባታል። ይህን ድርጊት ለመቃወም ብትሞክርም ሊለቋት ፈቃደኛ አልሆኑም። በኋላም በያዙት ተሽከርካሪ ገጭተው ገድለዋታል። በዚህ ጉዳይ ያሬድ ገብረስላሴ በላይ እና አንገሶም ሃይለማርያም ዘውዱ ሃፍቱ ላይ ግድያ ፈጽመዋል በሚል ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የመቐለ ማዕከላዊ ፍ/ቤት የዕድሜ ልክ እስራት ፈርዶባቸው ነበር። የትግራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን በይግባኝ መርምሮ የመጀመሪያውን የጥፋተኝነት ውሳኔ ማጽናቱ ተገልጿል። የማኅብራቱ የጋራ መግለጫ እንደሚጠቅሰው፣ ያሬድ ገብረስላሴ በላይ ሙሉብርሃን መኮንን ወለገርስ የተባለች ሌላ ወጣት ሴትን በመግደልም ተከሷል ፤ በእሱ ላይ የቀረቡትን ክሶችም ሙሉ በሙሉ አምኖ ተቀብሏል። አሁን ከዘውዱ ሀፍቱ ግድያ ጋር በተያያዘ  ሁለቱም ፍርደኞች ላይ የተላለፈው የእድሜ ልክ እስራት የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመለወጥ የሚያስችል አዲስ ማስረጃ ሳይቀርብ በነፃ መለቀቃቸው ቁጣ ቀስቅሷል። ማኅበራቱ፣ " የዘውዱ ሃፍቱ ገዳዮች በነፃ መሰናበታቸው እሷን ለሁለተኛ ጊዜ እንደመግደል ነው " ብለዋል። እንዴት ነጻ ተባሉ ? ጉዳዩ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት ሲደርስ፣ ሁለቱ ተከሳሾች ላይ ለመፍረድ ጥቅም ላይ የዋለው ዋናው ኦሪጅናል የስልክ ማስረጃ ከይግባኝ መዝገቡ ውስጥ መጥፋቱ ታወቀ። ሰበር ሰሚ ችሎቱም በዚህ ምክንያት ጉዳዩን ወደ ቀድሞው ታችኛው ፍርድ ቤት በመመለስ፣ የመጀመሪያው ማስረጃ በትክክል እንዲቀርብና ብቃት ያለው ባለሙያ ማስረጃውን እንዲያብራራ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ሆኖም ይህ ትዕዛዝ ሳይፈጸም 5 ወራት እና ቢያንስ 8 ችሎቶች ማለፋቸውን መግለጫው ያስረዳል። በዚህ ወቅት የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ትዕዛዙ እንደደረሰው ለፍርድ ቤቱ ቢያሳውቅም ትዕዛዙን ለመፈጸም የሚያስፈልገው ማስረጃ አልቀረበም ተብሏል። በኋላ በመጀመሪያው ማስረጃ ምትክ የተቃኘ ቅጂ ቀርቦ እንደነበር፤ የዐቃቤ ሕጉም ቢሮ በተመሳሳይ የራሱን ቅጂ እንዳቀረበ ተገልጿል። የፌዴራል ባለሙያ በመጠቀም ማስረጃውን እንዲያስረዳ በቀረበው ጥያቄ ምትክ በትግራይ ክልል ባለሙያ ተቀይሯል ተብሏል። ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. የፖሊስ መኮንን በጽሑፍ ማስረጃው ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል። ከ9 ቀናት በኋላም ፍርድ ቤቱ ይህንን ማብራሪያ በቂ ነው በማለት ሁለቱን ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ ወስኗል። የትግራይ ፖሊስ እና የአንደኛው ፍርደኛ አባት ላይ የተነሳው ጥያቄ ምንድነው ? የጋራ መግለጫው የማስረጃው መጥፋትና ለ5 ወራት ሳይቀርብ መቆየት ከትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ጣልቃ ገብነት ጋር በቀጥታ ያያይዛል። በወቅቱ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ያገለገሉት ኮሎኔል ገብረስላሴ በላይ (አሁንም የትግራይ ኃይል አመራር ናቸው) የመጀመሪያው ፍርደኛ ያሬድ ገብረስላሴ በላይ አባት መሆናቸውን ማኅበራቱ ጠቅሰዋል። በግንቦት 2016 ዓ.ም. የፖሊስ መርማሪዎች ፍርድ ቤት " ይፈታ " ያለውን አንድ ተጠርጣሪ ከእስር እንዳይለቀቅ ያቀረቡትን ይግባኝ በተመለከተ፣ ኮሎኔል ገብረስላሴ ይግባኙን እንደጥፋት ለመቁጠር የጉዳዩን ኃላፊ ፖሊስ መኮንን በስልክ " አስፈራርተዋል " የሚል ቅሬታ ቀርቦ ነበር። የጉዳዩ የሚመለከተው የፖሊስ ክፍልም በወቅቱ በጽሑፍ ቅሬታ ማቅረቡ ተገልጿል። ይህ ክስተት በዘውዱ ጉዳይ ላይ የሥልጣን ጣልቃ ገብነት ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ... ተቋማቱ የዘውዱ ግድያ ብቸኛዋ የዓይን ምስክር ሰምሃል ገብረዝያብሔር ለ8 ወራት ያለ ክስ በእስር መቆየቷን ጠቅሰዋል። እንዲሁም ግንቦት ወር 2017 ላይ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ጨምሮ በሰባቱ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ዳኞችና ፍርድ ቤቶች ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት ከመስጠት ተቆጥበው/ስራ አቁመውም ነበር። የጋራ መግለጫውን ያወጡት ዘጠኝ ማኅበራት ምን ጠየቁ ? - በነጻ እንዲሰናበቱ በተባለው ውሳኔ ላይ በአስቸኳይ ይግባኝ እንዲባል፤ - የመጀመሪያው የስልክ ማስረጃ (ከNISS የመጣው) እና ሰበር ሰሚ ችሎቱ የጠየቀው ብቃት ያለው የፌዴራል ባለሙያ በሙሉ እንዲቀርቡ፤ - ኮሎኔል ገብረስላሴ በጥቅም ግጭት ምክንያት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ እና በተቋማቸው የተፈጸመው የአምስት ወራት መዘግየትና በግንቦት 2016 ዓ/ም የተነሳው የጣልቃ ገብነት ክስ በነፃ አካል እንዲጣራ፤ - በግንቦት 2017 ዓ/ም በፍርድ ቤት ላይ የተፈጠረው መስተጓጎልና በዚያ ምክንያት የተፈጠረው የፍርድ አገልግሎት መቋረጥ በተመለከተ ተጠያቂነት እንዲሰፍን፤ - ሰምሃል ገብረዝያብሔርና ብርቱካን ሃፍቱ፣ እንዲሁም ፍርድ ያስተላለፉ ሁሉም ዳኞች፣ ዐቃቤ ሕጎችና መርማሪዎች የጽሑፍ እና ተፈጻሚ የሆነ የጥበቃ ዋስትና እንዲያገኙ፤ - UN Women እና የተመድ የሴቶችና ሴት ልጆች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ልዩ ሪፖርተር ስለዚህ ውሳኔ መቀልበስ ሕዝባዊ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። (መግለጫውን ያወጡ 9 ማኅበራት ዝርዝር ከላይ ተመልከቱ) ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ (CEO) አቶ መስፍን ጣሰው ለተጨማሪ አንድ ዓመት በሥራቸው ላይ እንደሚቆዩ ማረጋገጣቸውን 'አዲስ ፎርቹን' ዘገበ። የአየር መንገዱ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ሰብሳቢነት የአቶ መስፍን ጣሰውን የሥራ ዘመን ማራዘሙ ተገልጿል። አቶ መስፍን በቅርብ በሰጡት መግለጫ፣ ጡረታ መውጣት የነበረባቸው ከ3 ዓመት በፊት የነበረ ቢሆንም በመንግሥት ፍላጎት መጀመሪያ ለ2 ዓመት ከዚያ ለ1 ዓመት የስራ ውላቸው መራዘሙን ተናግረው ነበር። አሁንም ለተጨማሪ አንድ ዓመት ኃላፊነታቸው መራዘሙን 'አዲስ ፎርቹን' ከእሳቸው ማረጋገጡን ገልጿል። @tikvahethiopia

  • без подписи

  • #NationalDialogue🇪🇹 አከራካሪ በነበረው በአዲስ አበባ ጉዳይ "ስምምነት" ላይ ተደርሷል ተብሏል። በምን መልኩ እንደሆነ ግን በግልጽ አልታወቀም። የሀገራዊ ምክክር ምክትል ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ስላሴ በሰጡት መግለጫ፣ በ500 ሰዎች የተደራጁት ስምንቱ "የሥራ ቡድኖች" "አብዛኛዎቹ ተግባብተው" ቃለጉባዔ ፈርመው እያጠናቀቁ መሆኑን ተናግረዋል። ከምክክሩ ጉዳዮች አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ጉዳይ ነው። በተለይ በ250 ሰዎች በተደራጀው ስልታዊ ቡድን ከተማዋ " የኦሮሚያ መቀመጫ እንድትሆን ሕገ መንግስቱ እውቅና ይስጥ " የሚል አዲስ ሀሳብ በኦሮሚያ ተመካካሪዎች ቀርቦ፣ ሌሎቹ ክልሎች ደግሞ፣ "የፌዴራል መቀመጫ ናት። የአንድ ክልል ብቻ መቀመጫ አትሆንም " በማለታቸው ሲያከራክር ቆይቷል። ያሳለፍነው ቅዳሜ በ250 ሰዎች በተደራጀው " ስልታዊ ቡድኖች " የተመረጡ 30 ሀሳብ አጠናቃሪዎች በጉዳዩ ስምምነት ባለመድረሳቸው 500 ሰዎችን ለያዘው "የሥራ ቡድን" ሳይቀርብ 500ው ጉባያተኞች ተበትነው፣ ጉዳዩ ለሰኞ ተሻግሮ ነበር። በኋላ 30 አጠናቃሪዎች ሰኞ እለት የተጠቃለለ ሪፖርት ለ500ው ጉባያተኞች መነበቡን ተሳታፊዎች በወቅቱ ነግረውናል። አንድ የዚሁ ጉዳይ ተመካካሪ ሪፖርቱ መነበቡንና፣ በቃለጉባዔው የተካተተውና በስፋት የተነሳው የአዲስ አበባ የሕጋዊነት ጉዳይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በዋናነትም ለሦስት አካላት ተጠሪ መሆን አለባት የሚል ሀሳብ መነሳቱን፥ - " ለፌዴራል ተጠሪ መሆን አለባት" - " በኦሮሚያ አካል ሆና ለኦሮሚያ ተጠሪ መሆን አለባት" - "ተጠሪነቷ ለፌዴራል ሆኖ ራሷን በራሷ ታስተዳድር" የሚሉ ሀሳቦች መሆናቸውን ገልጸዋል። አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መንግስት መቀመጫ እንድትሆን በሕገ መንግስቱ መቀመጥ አለበት የሚለው ለ500ው ጉባያተኞች በተነበበው ሪፖርት " ብዙም ጎልቶ አልወጣም። ግን እውቅና ይሰጠው የሚለው ነው ሰፍቶ የመጣው " ሲሉም ተናግረዋል። " በብዙ ተመካካሪዎች የተባለው አዲስ አበባ የሁሉም ሀብት ፈሶባት የተገነባች የሁሉም መቀመጫ ናት። በቀጣይም ሁሉም ከተማዬ ናት ብሎ እንዲመጣ ነው መሆን ያለበት። ስለዚህ ክልሎች ዋና መቀመጫችን ነው ብለው በራሳቸው ምክር ቤት ሊያሳውጁ ይችላሉ " የሚል ምክረ ሀሳብ ገልጸዋል። ይህንና ሌሎች ጉዳዮችን የያዘው ሪፖርት ሰኞ እለት ከቀረበ በኋላም ተመካካሪዎች በሪፖርቱ ይካተቱ የሚሏቸው ሀሳቦች ካሉ እንዲያቀርቡ የሚያደርጉት የጥያቄና መልስ መርሃ ግብር እንደሚካሄድ ሰኞ እለት ገልጸውልን ነበር። ሌላኛው ተመካካሪ ትናንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሰረት የአዲስ አበባ ህጋዊ ጉዳይ ማክሰኞ እና ረቡዕም በከፍተኛ ሁኔታ አከራክሪነቱ ቀጥሎ ነበር። በአንድ በኩል፣ " አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ እንድትሆን በሕገመንግስቱ እውቅና ይሰጥ " የሚል ምክረ ሀሳብ ሲቀርብ፣ በሌላ በኩል፣ " ይህ በሕገ መንግስት ላይ አይሰፍርም። የሚሰፍር ከሆነ ግን የብሔረሰቦች ዋና መቀመጫ ናት ተብሎ አብሮ ይጻፍ " የሚሉ ሀሳቦች አከራክረዋል። ከዚያም ጉዳዩ ለዛሬ ተቀጥሮ ነበር። ዛሬ ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ኮሚሽነር ሒሩት ዛሬ በሰጡት መግለጫ 500ው የሥራ ቡድን ተመካካሪዎች በስምንቱ አጀንዳዎች አብዛኛዎቹ ስምምነት መድረሳቸውንና ቃለጉባዔ ፈርመው እያጠናቀቁ መሆኑን ከመግለጽ ውጭ በአዲስ አበባ ጉዳይ በምን ስምምነት ላይ እንደተደረሰ የተናገሩት ነገር የለም። ተመካካሪዎች ጉዳዩ ከስምምነት ተደርሶ ዛሬ ቃለጉባዔ ላይ መፈራረማቸውን ሲያነጋገሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተውሏል። ቃላቸውን የሰጡ አንድ ተመካካሪ ግን፣ " አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተጠሪ ሆና " እንድትቀጥል እና ከተማዋ " የኦሮሚያ መቀመጫ እንድትሆን ህጋዊ እውቅና ይሰጥ " የሚለው ሀሳብ በልዩነት ተይዞ በአስማሚ ቡድን እንዲታይ ከስምምነት መደረሱን ገልጸዋል። " ድሬዳዋና አዲስ አበባ በፌዴራል ተጠሪነት እንዲቀጥሉ " መባሉንም አክለዋል። " የተወሰኑት እንጅ ያልፈረሙት (የፌዴራል ተጠሪ ይሁኑ በሚለው) አብዛኞቹ በቃለጉባዔው ፈርመዋል፤ በእርግጠኝነት ነው ይህን የምናገረው " ብለዋል። በከተማዋ ጉዳይ ምክክሩን " ከዚህ በላይ መቀጠል አልተቻለም። ወደጸብ ሊገባ ሆነ፤ በዚሁ ቆመ " ሲሉ ገልጸዋል። ሌሎች ብዙዎቹ ከስምምነት የተደረሰበትን ጉዳይ በግልጽ ለመናገር ፈቃደኞች ባይሆኑም፣ " ስምምነት ላይ ተደርሷል " በሚል ዛሬ በቃለጉባዔ መፈረማቸውን ሲናገሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተውሏል። " አዲስ አበባ የፌዴራል ተጠሪ፤ ራሷን በራሷ እንድታስተዳድር " ፣ " ማንም ጣልቃ ሳይገባባት ስራዋን እንድትሰራ " በሚል ምክረ ሀሳብ ስምምነት ላይ መደረሱን ሲያወሱ አስተውለናል። በተያያዘ፣ ኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ " ልዩ ጥቅም " እንዲኖረው በሚል ቀርቦ የነበረው ሀሳብ፣ " ልዩ ጥቅም " የሚለው ቀርቶ " የጋራ ጥቅም " እንዲሆንና የጋራ ጥቅሙ በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እንዲሆን መባሉም ተመልክቷል። ይህ ሁሉ በ500 ሰዎች በተደራጀው የሥራ ቡድን ታይቶ ስምምነት የተደረሰበት እንጅ ውሳኔ ላይ ደረሰ ማለት እንዳልሆነ፣ ጉዳዩ በኮሚቴዎችና በ4 ሺሕ የምክክሩ ተሳታፊዎች በይፋ እስከሚነገር ድረስ የሚስተካከሉ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተሰምሮበታል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • без подписи

  • #NationalDialogue🇪🇹 በ500 ሰዎች የተደራጁ ስምንቱ የሥራ ቡድኖች ምክክር ተጠናቆ ምክረ ሀሳባቸው፥ ሀሳቦችን "ለሚያጣጥም፣ የሚቃረኑ ነገሮች እንዳይኖሩ ለሚጠነቀቅ" ቡድን መሸጋገሩን ኮሚሽኑ አስታወቀ። የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ስላሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በ500 ተሳታፊዎች የተቋቋሙ ቡድኖች በየቡድናቸው ሲመካከሩ ቆይተው ዛሬ "አብዛኛዎቹ ተግባብተው" በምክረ ሀሳቦች ላይ ፈርመው እያጠናቀቁ መሆን ተናግረዋል። በ250 የተደራጁ "ስልታዊ" ቡድኖች ተመካካሪዎች የመከሩባቸውን ሀሳቦች 500 ሰዎችን ለያዘው "የሥራ ቡድን" አቅርበው፣ ቡድኑ ሲመክር ሰንብቷል። በዚህም በተለይ "አዲስ አበባ ሕጋዊ አቋም" እና "የመንግስት አደረጃጀት" ጉዳዮችን የተመለከቱ ሀሳቦች ሲያከራክሩ ነበር። በተለይ የአዲስ አበባ ህጋዊ ጉዳይ በብርቱ ያጨቃጠቀ ሲሆን፣ አሁን ወደስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ስምምነቱ በቀጣዩ ሂደት የሚታዩ ጉዳችም እንዳሉ ጭምር ታሳቢ ያደረገ ነው። ኮሚሽነር ሒሩት በመግለጫቸው፣ "በዚህ ሂደት ውስጥ አለመግባባቶችና ግጭቶች አልነበሩም አይባልም፤ የመኖራቸው ምክንያት ግን ይህ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን የበለጠ አረጋግጠንበታል። ግጭቶቹ ተፈትተው ወደ አንድ የጋራ ሀሳብ ላይ ደርሰው በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች ስምንቱም ቡድኖች ስራቸውን እያጠናቀቁ ነው" ብለዋል፣ ቀጣዩን ሂደት ሲያስረዱ፦ -ስምንቱም ቡድኖች ያዘጋጇቸውና የተስማሙባቸውን ሀሳቦች ለማያጣጥም፣ -የሚቃረኑ ነገሮች እንዳይኖሩ ለሚጠነቀቅ፣ -ድግግሞሽ ያሉባቸውን ምክረ ሀሳቦች ወደ አንድ ለማምጣት ለማሰራው ቡድን ተሻግሮ ቡድኑ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ስራ እንደሚጀምር ገልጸዋል። ይህ ቡድን ኮሚሽኑ አጠቃሎ የሚያቀርባቸው ምክረ ሀሳቦች አንድ ወጥነት እንዲኖራቸው የሚሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia