TIKVAH TIGRAY
СтатистикаTikvahtigray ይህ የቲክቫህ ትግራይ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 8
- Всего постов
- 153
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 90
- 1/48двое суток
- 103
- 1/72трое суток
- 111
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
#Fake : በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የአማራ ክልል ፖሊስ " ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ የላከው ነው " ተብሎ የተሰራጨው የትግራይ ተወላጆች ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ የሚያዝ ደብዳቤ ሐሰተኛ መሆኑ ተገልጿል። ደብዳቤው ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም የተጻፈ ቢሆንም፣ ተቋሙ የቀድሞ ስያሜውን " የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን " ወደ አማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከቀየረ ወራት ተቆጥሯል። በተጨማሪም፣ ደብዳቤው ላይ ፈርመዋል የተባሉት መንገሻ አውራሪስ ከተቋሙ ከለቀቁ ዓመታት መቆጠራቸው ተመላክቷል። በመሆኑም ደብዳቤው ከእውነት የራቀና ሀሰተኛ ነው። #AMC @tikvahtigray
без подписи
" እኔና ልጆቼ ጭንቀትና ሐዘን ጸንቶብናል። እባካችሁ እውነቱን ንገሩንና እርማችንን እናውጣ " - ወ/ሮ ገነት እዝራ የካሜራ ባለሙያ ፊልሞን ከተሰወረ አንድ ዓመት ቢያልፈውም ፤ እስካሁን የት እንዳለ አልታወቀም። በመቐለ ከተማ በድንገት የተሰወረው ወጣቱ የካሜራ ባለሙያ ፊልሞን (ፊላሪ) ከጠፋ ከአንድ ዓመት በላይ ተቆጥረዋል። ፊልሞን ነሐሴ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ገደማ በመቐለ ከተማ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ በባጃጅ እየተጓዘ ሳለ በድንገት መሰወሩን ቤተሰቦቹ ይገልጻሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የት እንዳለና ምን እንደደረሰበት የሚያሳይ የተረጋገጠ መረጃ እስካሁን አልተገኘም። ቤተሰቡ እንደሚለውም በጉዳዩ ላይ አዲስ የምርመራ ውጤት አልተገኘም። ፊልሞን የሁለት ሕፃናት አባት ሲሆን፣ ባለቤቱ ወ/ሮ ገነት እዝራ ባለቤቷ ከጠፋበት ዕለት ጀምሮ ለጥየቃ ወደ ፖሊስ በተደጋጋሚ እንደምትሄድ ተናግራለች። " እስከ አሁን የሞባይሉ ቁጥሩ ይሰራል። ይሁን እንጂ ይኑር አይኑር የታወቀ ነገር የለም " ስትል ወ/ሮ ገነት ገልጻለች። ቤተሰቡ ከፖሊስና ከሌሎች የጸጥታ አካላት የተሻለ ምርመራና ግልጽ መረጃ እንደሚጠብቅ ገልጿል ። ወ/ሮ ገነት በተለይም የክልልና የፌደራል የጸጥታ አካላት ጉዳዩን በበቂ ሁኔታ መመርመራቸውን አለመረዳቷን ተናግራለች። " እኔና ልጆቼ ጭንቀትና ሐዘን ጸንቶብናል። እባካችሁ እውነቱን ንገሩንና እርማችንን እናውጣ " ስትል ተማጽናለች። ቤተሰቡ እንደሚለው ፣ ወደ ፖሊስ በየጊዜው ቢመላለስም " አዲስ ነገር የለም " ከሚል መረጃ የዘለለ ተጨማሪ የተጨበጠ መረጃ አልተሰጠውም። ከተሰወረ አንድ ዓመት ቢሞላም፣ " የካሜራ ባለሙያው ፊልሞን (ፊላሪ) የት ደረሰ?" የሚለው ጥያቄ አሁንም መልስ አላገኘም። @tikvahtigray
በራያ አላማጣ ወረዳ "የትግራይ ኃይሎችን ዒላማ ያደረገ" የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ምንጮች ተናገሩ! በትግራይ ክልል ራያ አላማጣ ወረዳ "መረዋ" የተባለ ቀበሌ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለሥልጣን እና የትግራይ ኃይሎች ምንጮች ተናገሩ። "ትምህርት ቤት" ላይ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት "ሦስት የትግራይ ኃይሎች አባላት ሲገደሉ፤ ሰባቱ መጎዳታቸውን" ምንጮቹ ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት ምንጮች እንደሚስረዱት፣ የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ትናንት ሰኞ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም. ጠዋት 2፡30 ገደማ ነው። ከአላማጣ ከተማ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በዚህ ስፍራ ሦስት ጊዜ ጥቃት እንደደረሰ ተገልጿል።በጥቃቱ ዒላማ የተደረገው "አርሚ 26" የተባለው የትግራይ ኃይሎች አባላት እንደሆኑ ቢቢሲ ትግርኛ ከወታደራዊ አዛዦች እና ከደቡብ ትግራይ ዞን ጽሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ አመልክቷል። የፌደራል መንግሥት ተፈጽሟል ስለተባለው የድሮን ጥቃት አስካሁን በይፋ አስተያየት አልሰጠም። ቢቢሲ ስለ ጥቃቱ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ኮሎኔል ቢረሳው ሽፈራው ያቀረበው ጥያቄ ወዲያው ምላሽ አላገኘም። ሁለት ጊዜ ጥቃት የተፈጸመው በመረዋ ቀበሌ በሚገኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የትግራይ ኃይሎች አባል፣ "ጥቃቱ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ነው የተፈጸመው።ክረምት በመሆኑ፣ ትምህርትም ስለሌለ የአርሚ 26 [አባላት] በዚያ ተጠልለው ነበር" ሲሉ "ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ ኃይሎች አባላት" መሆናቸውን አስረድተዋል። በዚህ ጥቃት ሦስት የትግራይ ኃይሎች አባላት ወዲያውኑ እንደተገደሉ እና ሰባቱ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሲቪል እንዲሁም ወታደራዊ ምንጮች ተናግረዋል።ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውም አክለዋል። ሦስተኛው ጥቃት የደረሰው ወንዝ የሚገኝበት አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል።በትግራይ ክልል የራያ አላማጣ ወረዳ አስተዳዳሪ ዳንኤል ታምራት በበኩላቸው ጥቃቱ "ሲቪሊያን ሰዎች" ላይ ማነጣጠሩን እና ትምህርት ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱን በማንሳት ከስሰዋል።"ድሮኗ ጉዳት ያደረሰችው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው። ጥቃት ያደረሰችው አንደኛ በትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደግሞ ነዋሪዎች ውሃ በሚቀዱበት ስፍራ ላይ ነው። በርካቶች ቆስለዋል፤ አንድ ደግሞ ወዲያውኑ ሞቷል" ብለዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ብዛት አራት መሆኑንም ተናግረዋል።እንደ ፌደራል መንግሥት ሁሉ፣ የክልሉን ሥልጣን የተቆጣጠረው በዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው አስተዳደርም ስለ ጥቃቱ በይፋ አስተያየት አልሰጠም።ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው አንድ የትግራይ ኃይሎች ምንጭ ግን ጥቃቶቹ የተፈጸሙት "ከባሕር ዳር እና ቢሾፍቱ ከተሞች በተነሱ ድሮኖች ነው" የሚል ክስ አቅርበዋል።"አንዲት ድሮን ጠዋት ከባሕር ዳር ተነስታ እንደሄደች አውቀናል፤ ሳትዞር በቀጥታ ነው የደበደበችው" ብለዋል። ቢቢሲ እነዚህ ክሶች በገለልተኝነት አላረጋገጠም። Via_BBC @tikvahtigray
የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ለተጨማሪ ዉጊያ እየተዘጋጁ ነው ተባለ‼️ የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጣቂዎች ለተጨማሪ ዉጊያ የሚያደርጉት ዝግጅት መቀጠሉን የተለያዩ ወገኖች አስታወቁ። የአዉሮጳ የሰላም ተቋም መገናኛ ዘዴዎችንና ሌሎች ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የመቀሌና የአዲስ አበባ ግንኙነት ይበልጥ እየተበላሸ ነዉ። ሁለቱ ወገኖች የሚያደርጉት የጦር ኃይል ንቅናቄም ሌላ ጦርነት ሊጫር ይችላል የሚለዉን ሥጋት አንሮታል። ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸዉን ሰላማዊ፣ ሁሉን አካታችና ገንቢ በሆነ ዉይይት እንዲፈቱ ተቋሙ ጠይቋል። የአይን ምሥክሮች በበኩላቸዉ የትግራይ ኃይል የሚባለዉ የታጣቂዎች ስብስብ በርካታ ተዋጊዎችን ወደ ምዕራብ ትግራይ እያዘመተ ነዉ። የትግራይ ተዋጊዎች ትግራይ ክልልን ከአፋርና ከአማራ ክልሎች ጋር በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢም ምሽግ እየቆፈሩ መሆኑንም የዓይን ምሥክሮች አስታዉቀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ባንፃሩ አማራና አፋር ክልሎች ከፍተኛ የወታደራዊ ንቅናቄ እያደረገ መሆኑንም የዓይን ምሥክሮች ተናግረዋል። @tikvahtigray
ጦርነት ከተጀመረ የኤርትራ መንግስት አይኖርም፤ ይቀየራል - ባጫ ደበሌ‼️ አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ ጦርነት ከተቀሰቀሰ የኤርትራ መንግስት ፋፃሜ ይሆናል ሲሉ አስጠነቀቁ። ባጫ በቀጠናው መንግስት ይቀየራል ጂኦግራፊ ይቀየራል ሲሉ የጦርነቱን ውጤት ተንብየዋል። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተወሰነ ድንበር የለም ያሉት ባጫ፣ እሱም ራሱ ችግር ይፈጥራል ነው ያሉት። በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ጦርነት ከተጀመረ ግንባር እና ደጀን አይኖርም ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ባጫ ይህን አስተያየት የሰጡት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ውጥረት በተነገሰበት ወቅት መሆኑ አነጋጋሪ ሁኗል። የቀድሞው የጦር አመራር የአሁኑ ዲፕሎማት ይህን ሁሉ ዛቻ መሰል አስተያየት ከሰጡ በኋላ ግን አያስፈልግም ብለዋል። @tikvahtigray
без подписи
без подписи
без подписи
የመሳሪያ ዲፖ ተያዘ‼️ በሱዳን የሚንቀሳቀሰው የህወሓት አርሚ 70 በሸረሪና ግንባር አከማችቶት የነበረው የመሳሪያ ዲፖ ተያዘ‼️ ከሸረሪና ካምፕ ወጣ ብሎ 'ግዴማ' በተባለች ቦታ መጋዘን ውስጥ እንዲሁም ከመሬት በታች በኮንክሪት በተሰራ ግዙፍ ምሽግ ተጠራቅሞ የነበረ ተተኳሽ፣ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣ ሮኬት፣ የአጭር እና መካከለኛ ርቀት ሚሳይሎች፣ RPG-7፣ የሳተላይት ስልኮች፣ የሬዲዮ መገናኛ፣ የቅኝት ድሮኖች፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና ለጊዜው ምንነታቸውን ለመለየት ያልተቻሉ የጦር መሳሪያዎች ገቢ መደረጋቸውን ምንጮቹ አረጋግጠዋል። እንደ ወታደራዊ ምንጮቹ ገለፃ ከሆነ፤ በትናንትናው እለት ብቻ ከሸረሪና እና ግዴማ ካምፕ 31 ከባድ ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ከአርሚ 70 የተማረኩ የተለያዩ ትጥቆችን ወደ ሁመራ እና ዳንሻ ከተማ ተጓጉዘዋል። ለዚህ ዲፖ መገኘት የተማረኩ የአርሚ 70 ታጣቂዎች አስተዋጽኦ አድርገዋል። @tikvahtigray
የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ለተጨማሪ ዉጊያ እየተዘጋጁ መሆናቸዉ ተነገረ! የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጣቂዎች ለተጨማሪ ዉጊያ የሚያደርጉት ዝግጅት መቀጠሉን የተለያዩ ወገኖች አስታወቁ።የአዉሮጳ የሰላም ተቋም መገናኛ ዘዴዎችንና ሌሎች ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የመቀሌና የአዲስ አበባ ግንኙነት ይበልጥ እየተበላሸ ነዉ።ሁለቱ ወገኖች የሚያደርጉት የጦር ኃይል ንቅናቄም ሌላ ጦርነት ሊጫር ይችላል የሚለዉን ሥጋት አንሮታል።ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸዉን ሰላማዊ፣ ሁሉን አካታችና ገንቢ በሆነ ዉይይት እንዲፈቱ ተቋሙ ጠይቋል። የአይን ምሥክሮች በበኩላቸዉ የትግራይ ኃይል የሚባለዉ የታጣቂዎች ስብስብ በርካታ ተዋጊዎችን ወደ ምዕራብ ትግራይ እያዘመተ ነዉ።እንደሚሉት የትግራይ ተዋጊዎች ትግራይ ክልልን ከአፋርና ከአማራ ክልሎች ጋር በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢም ምሽግ እየቆፈሩ መሆኑንም የዓይን ምሥክሮች አስታዉቀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ባንፃሩ አማራና አፋር ክልሎች ከፍተኛ የወታደራዊ ንቅናቄ እያደረገ መሆኑን የዓይን ምሥክሮች ተናግረዋል። ከአፋር ክልል በደረሰን መረጃ መሠረት በክልሉ የዞን አራት ተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ተጨማሪ ወታደሮች ሠፍረዋል።ነዋሪዎቹ በሥም በዘረዘሯቸዉ ወረዳና ቀበሌዎች ወታደሮችን ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀሱና ተጨማሪ ኃይል ማስሩ እስከ ትናንት ማታ ድረስ ቀጥሎ ነበር። (ፎቶ: Archive) Via DW @tikvahtigray
በዘውዱ ሀፍቱ ግድያ እድሜ ልክ ተፈርዶባቸው የነበሩ ግለሰቦች ከእስር መፈታታቸውን 'ይኾኖ' ማህበር አስታወቀ በትግራይ ክልል ወጣት ዘውዱ ሀፍቱን በመግደል ወንጀል በእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት ያሬድ ገብረሥላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያም ከእስር መፈታታቸውን በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅት 'ይኾኖ' (Yikhono) አስታወቀ። እንደ ማህበሩ ገለፃ፣ ሁለቱ ግለሰቦች በፈጸሙት ዘግናኝ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው የጽኑ እስራት ውሳኔ ከተላለፈባቸው ገና አንድ ወር ያህል እንኳ ሳይሞላው ነው ከእስር ነፃ የወጡት። ዕድሜዋ 32 የነበረችው ዘውዱ ሀፍቱ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በታቀደ ጥቃት በህዝብ ፊት በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ እና በመኪና በመጨፈለቋ ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል። ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ በቆየባቸው ሁለት ዓመታት ውስጥ፦ በዳኞች ላይ ይደርስ የነበረ ዛቻ እና በችሎት ውስጥ የተፈጠሩ ረብሻዎች ሂደቱን ሲያስተጓጉሉት መቆየታቸው ተገልጿል። ፍርድ ቤቱ ጥፋተኝነታቸውን በማረጋገጥ ያለ ምንም ይቅርታ (ይግባኝ) የዕድሜ ልክ እስራት ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ከእስር ተፈተዋል የተባሉት ተከሳሾች ያሬድ ገብረሥላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያም ሲሆኑ፣ ያሬድ በወቅቱ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የ22ኛ ሰራዊት አዛዥ ሆነው የሚያገለግሉት የኮሚሽነር ገብረሥላሴ በላይ ልጅ እንደሆነ ተገልጿል። የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ቤተሰቦች እንደሚያስረዱት፣ በምርመራው እና በፍትህ ሂደቱ ወቅት የባለስልጣናት ተፅዕኖ እና ጣልቃ ገብነት እንደነበር ጠቁመዋል። የግለሰቦቹ ከእስር መፈታት በክልሉ የፍትህ ስርዓት እና በሕግ የበላይነት ላይ ትልቅ ጥያቄ ማስነሳቱን የጠቆመው 'ይቅኖ' ማህበር፣ ውሳኔው የሴቶችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ገልጿል። በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ #JusticeForZewdu በሚሉ ሃሽታጎች ለወጣት ዘውዱ ሀፍቱ ፍትህ እንዲረጋገጥ፣ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ጣልቃ በሚገቡ ባለስልጣናት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ጥሪዎች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ። Via Asfaw Gedamu ጉርሻ @tikvahtigray
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи