- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 23
- Всего постов
- 35
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 319
- 1/48двое суток
- 3 080
- 1/72трое суток
- 3 321
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
የኤልኒኖ (El Nino) ክስተት እና የኃይል አቅርቦት .....///..... ብዙ ጊዜ የኤልኒኖ ክስተት ሲነሳ አእምሯችን ወደ ድርቅ፣ የምግብ እጥረት እና የግብርና መስተጓጎል ያደላል። ነገር ግን ኤልኒኖ ከአየር ጠባይ መዛባት ባሻገር በቀጥታ ከምንጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና ደህንነት ጋር እጅግ ጥብቅ የሆነ ትስስር አለው። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አብዛኛው የኤሌክትሪክ ኃይላቸውን ከውሃ (Hydropower) በሚያመነጩ ሀገራት ላይ የኤልኒኖ መከሰት በኃይል አቅርቦት ስርዓቱ ላይ ግዙፍ ፈተና ይደቅናል። 1. የኤልኒኖ ክስተት ምንድን ነው? ኤልኒኖ በፓሲፊክ ውቅያኖስ አካባቢ የሚከሰት የአየር ጠባይ መዛባት ሲሆን የውቅያኖሱ ወለል የሙቀት መጠን ከተለመደው በላይ ሲጨምር የሚከሰት ነው። ይህ የሙቀት መጨመር፡- · የዓለም አቀፍ የንፋስና የዝናብ ስርጭትን ያዛባል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የክረምት ዝናብ ስርጭትን በመቀነስ ለከፍተኛ ድርቅ እና የውሃ እጥረት ይዳርጋል። በሌሎች የዓለም ክፍሎችም ያልተለመደ ከባድ ጎርፍ ያስከትላል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኤልኒኖ-el-nino-ክስተት-እና-የኃይል-አቅርቦት&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም
ከማብሪያና ማጥፊያ የሚዘለው የብርሃን ጉዞ ……///…….. ብዙዎቻችን ቤታችን ስንገባ እንደምናገኘው የማብሪያና ማጥፊያ ቁልፍ ኃይልን የምናገኝበት እና ሲቋረጥም ወደነበረበት የምንመልስበት ሂደት ቀላልና አፍታ የማይወስድ ተግባር ይመስለናል። ነገር ግን ማብሪያና ማጥፊያውን በተጫንንበት ቅጽበት በቤታችን ወይም በሥራ ቦታችን የሚበራው የኤሌክትሪክ ኃይል እኛ ዘንድ ለመድረስ የሚያልፍበት መንገድ እጅግ ውስብስብ፣ አደገኛ እና በሺዎች የሚቆጠሩ የዘርፉ ባለሙያዎችን የሌሊትና ቀን የማይቋረጥ አድካሚ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ምን ያህል እንረዳለን፡፡ በሸለቆዎችና በበረሃዎች የሚጀመር የኃይል ማመንጨት ሂደት የኃይል አቅርቦት ጉዞው የሚጀምረው ከኃይል ማመንጫዎች ነው። በኢትዮጵያ አብዛኞቹ የውሃ ኃይል ማመንጫዎች የሚገኙት ከመኖሪያ በራቁ አካባቢዎች፣ ከፍተኛ ንፋስና ሙቀት ባለባቸው በረሃዎች እና ሸለቆዎች ውስጥ ነው። በእነዚህ አስቸጋሪ አየር ጠባይና መልክዐ ምድር ውስጥ የሚሰሩ መሐንዲሶችና ቴክኒሻኖች ግዙፍ የውሃ እና የንፋስ ተርባይኖችንና ጄነሬተሮችን በከፍተኛ ጥንቃቄ... ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ከማብሪያና-ማጥፊያ-የሚዘለው-የብርሃን-ጉ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የወደቀው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር የኃይል ፍሰት የማመጣጠን ሥራ ይሰራል ………///…….. በለገጣፎ - ቃሊቲ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት የወደቁ 5 የብረት ምሰሶዎችን በመጠገን ዳግም አገልግሎት መስጠት እስኪጀምሩ ድረስ የኃይል ፍሰት የማመጣጠን ሥራዎች እንደሚሰሩ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ፡፡ በዘርፉ የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ተወካይ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ዘለቀ እንደገለፁት የብረት ምሰሶዎቹ የወደቁት በከባድ አውሎ ንፋስ ምክንያት ቢሆንም ቀደም ሲል በምሰሶዎቹ አካላት ላይ ይፈፀም የነበረው ተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል ለጉዳቱ መከሰት አሉታዊ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በወደቁት የብረት ምሰሶዎች ላይ በተደረገው የቴክኒክ ፍተሻ መሰረት የተሰረቁ የምሰሶ አካላትን መልሶ ለመተካት በማሻሻያ (Modification) መልክ ይገጠሙ የነበሩት ብረቶች የምሰሶዎቹን መደበኛ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ማምጣት አለመቻላቸው መረጋገጡን ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የወደቀው-የኃይል-ማስተላለፊያ-መስመር-ተ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም
ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት የመዘርጋት አስፈላጊነት! .....///..... ውሃ ለኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ዋነኛውና ዋናው የኃይል ምንጭ ነው። በተለይም በውሃ ኃይል ማመንጫዎች የሚመረተው እያንዳንዱ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የሚጀምረው ከአንዲት የውሃ ነጠብጣብ በመጠራቀም በመሆኑ የውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር ሥርዓት በኃይል ማመንጨት ሂደት ቁልፍ ሚና አለው! ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ለኃይል ዘርፉ ያለው ወሳኝ ፋይዳ የኃይል ብክነትን መቀነስ በወቅታዊ የአየር ንብረት መለዋወጥና ያላግባብ በሚባክን የውሃ ሀብት ምክንያት የሚፈጠርን የኤሌክትሪክ ማመንጨት አቅም መቀነስ ይከላከላል። ዘላቂ የኃይል አቅርቦት ግድቦች ሙሉ የማመንጨት አቅማቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ እና ሥርዓት ባለው ሁኔታ እንዲጠቀሙ ያስችላል። ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እያንዳንዷ የምትባክን የውሃ ነጠብጣብ በኃይል ማመንጨት ሂደት ላይ የምታሳድረው ተጽዕኖ በቀጥታ በመኖሪያ ቤቶች፣ በፋብሪካዎች፣ በንግድና በማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር ውጤታማ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ጥብቅ-የውሃ-አስተዳደር-ሥርዓት-የመዘርጋ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው ……///……. በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እና ሪጅኖች ለተመደቡ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና አስተባባሪ መሐንዲሶች በሥራ ላይ ደህንነት ላይ ያተኮረ ሥልጠና መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሥራ አስኪያጅ አቶ ኮርሳ ተሬሳ እንደገለፁት ሥልጠናው መሐንዲሶቹ በተመደቡባቸው የሥራ ቦታዎች ላይ በሚኖራቸው የሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት ክትትልና ቁጥጥር ላይ ያላቸውን የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው። ሥልጠናው ባለሙያዎቹ በሥራ ላይ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ስጋቶችን በመለየት መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን ነው የገለፁት። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በሥራ-ላይ-ደህንነት-እና-ጤንነት-ዙሪያ-ሥ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም
የኃይል መቋረጥን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ዘመናዊ የአደጋ ጊዜ የብረት ምሰሶዎች 🏗 በኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን መልሶ ጥገና ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ የአደጋ ጊዜ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች (Emergency Restoration Towers) በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ተደርገዋል። ይህ ቴክኖሎጂ ምን ዓይነት ጥቅሞችን ይዞ መጥቷል? ፈጣን መልሶ ጥገና ቀደም ሲል በአደጋ ወቅት ከ18 እስከ 20 የሚደርሱ የእንጨት ምሶሶዎችን መትከል ይጠይቅ የነበረ ሲሆን አዲሶቹ ምሰሶዎች ግን በደጋፊ ገመዶች (Anchor Wire) በቀላሉ የሚገጣጠሙ በመሆናቸው የተቋረጠውን መስመር በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወደ ሥራ ለማስገባት ያስችላሉ። የኃይል ጭነት ማመጣጠን የተጨናነቁ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን አነስተኛ የኃይል ፍሰት ወደሚገኝባቸው በማዘዋወር ከአገልግሎት ውጭ የነበሩ አካባቢዎች በፍጥነት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ያደርጋል። የሠራተኞች ደህንነትና የአሰራር ዘመናዊነት የጥገና ሠራተኞችን ለጉዳት እንዳይጋለጡ በማድረግ ደህንነታቸውን አስተማማኝ ያደርጋል። በተግባር ምን ውጤት ተገኘ? በሞጆ አካባቢ በተደረገ ሥልጠናና ልምምድ ባለሙያዎቹ የምሰሶ ተከላ ጊዜን ከግማሽ ቀን በታች ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡ በተጨማሪም ከቢሾፍቱ ወደ ቆቃ እና ሁርሶ እንዲሁም ከገላን ወደ ሞጆ በሚሄዱ ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመሮች ላይ ተከሰተው እስከ 7 ቀናት ሊወስዱ ይችሉ የነበሩ የኃይል መቋረጦችን በእነዚህ ምሰሶዎች አማካኝነት ፈጣን መፍትሔ መስጠት ተችሏል። በቀጣይ ምን ታስቧል? ቴክኖሎጂውን ወደ ሁሉም ሪጅኖች ለማስፋትና የጥገና ምላሽ ጊዜን ይበልጥ ለመቀነስ የሚያስችሉ ዝግጅቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የፕሮጀክት አስተዳደርን ማዘመን ለተቋም ዘላቂ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ አለው .....///..... የተቋሙን ስትራቴጂካዊ ግቦች በስኬት ለማሳካትም ሆነ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን፣ ዘመናዊና ጠንካራ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት መሠረታዊና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ተጠቆመ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቀላጠፈ ደረጃውን የጠበቀና ውጤታማ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችለውን አራተኛ ዙር የከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ሥልጠና ለፕሮጀክት ዳይሬክተሮችና ሥራ አስኪያጆች መስጠት ጀምሯል። በዕለቱ ሥልጠናውን የሰጡት በተቋሙ የአሰላ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅና አሰልጣኝ ኢንጂነር ጌቱ ያደቴ እንደገለጹት ይህ ሥልጠና ተቋሙ በፕሮጀክት አስተዳደር ረገድ የሚያጋጥሙትን መዋቅራዊና አሰራር ነክ ፈተናዎች በዘላቂነት በመሻገር፣ ከልማዳዊ አሰራር ወደ ተመራጭና ዘመናዊ የፕሮጀክት መሪነት ሥርዓት እንዲሸጋገር አቅም ይፈጥራል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የፕሮጀክት-አስተዳደርን-ማዘመን-ለተቋም&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
видео или голосовое, без подписи