Ethio Power Academy
СтатистикаWe strive to create a learning organization!!
- Последний пост
- 17:02
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 890
- 1/48двое суток
- 1 019
- 1/72трое суток
- 1 100
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🟢 ክፍል 5 እያንዳንዱ ኪሎዋት ልዩነት ያመጣል (ኤሌክትሪክን መቆጠብ በእርግጥ ውኃን ለማዳን ይረዳል?...) . . . አብዛኛውን ጊዜ ስለ ኤሌክትሪክ ስናስብ፣ እንደምንጠቀመው ፍጆታ እንቆጥረዋለን እንጂ እሱን ለማምረት ሲባል ምን እንደሚፈጅ አስበን አናውቅም… ሃይድሮ ፓወር (Hydropower) ማዕከላዊ Source በሆነበት የኃይል ሥርዓት ውስጥ፣ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ሲባል በተርባይኖች በኩል የሚፈሰው ውኃ ለፍጆታ የምንጠቀመውን ኃይል ለማምረት የሚጠቅም ነዳጅ ነው… ስለዚህም… አላስፈላጊ የኤሌክትሪክ ፍጆታን ስንቀንስ፣ በማመንጨት ሂደት ላይ የሚፈጠረውን አላስፈላጊ ጫና እንቀንሳለን… የሃይድሮ ፓወር ኃይል ተጨማሪ የኃይል ምንጭ (Marginal source) በሚሆንበት ቦታ ደግሞ ለማመንጨት ይፈስ የነበረውን ውኃ መቆጠብ እንችላለን… ይህም የኃይል ተብቃቆትን (Energy efficiency) ገንዘብ ከመቆጠብ ያለፈ ትርጉም እንዲኖረው ያደርገዋል… የሥራ ቦታዎን ዞር ብለው ይመልከቱ… 🏪 ሌሊቱን ሙሉ ክፍት ሆኖ የሚያድር ኮምፒውተር... 🏪 ባዶ ክፍልን የሚያበሩ መብራቶች... 🏪 ያለ አንዳች አስፈላጊነት የሚሠራ ኤር ኮንዲሽነር (Air conditioner)... 🏪 አስፈላጊ ባልሆኑበት ሰዓት ጭምር ግድግዳ ላይ ተሰክተው የሚተው መሣሪያዎች... እያንዳንዱ ለየብቻው ሲታይ ኢምንት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ አላስፈላጊ ድርጊት በሺዎች በሚቆጠሩ ሠራተኞች፣ ቢሮዎች፣ ተቋማት እና የሥራ ቀናት ሲባዛ ትንሹ ነገር ግዙፍ ይሆናል… ⭐️ እኛ ምን ማድረግ እንችላለን?... 💀. የማያስፈልጉ ነገሮችን ማጥፋት ከቢሮ፣ ከስብሰባ አዳራሽ፣ ከላቦራቶሪ፣ ከወርክሾፕ ወይም ከክፍል ከመውጣታችን በፊት፦ መብራቶችን መዝጋት፣ ኮምፒውተሮችን ማጥፋት ወይም ወደ Sleep mode መቀየር፣ አላስፈላጊ መሣሪያዎችን ማጥፋት… ምክንያቱም አንዲት ቀላል ልማድ ወደ ተቋማዊ ባህል ልታድግ ትችላለች… 💀. የከፍተኛ ፍላጎት ሰዓት ጫናን (Peak Demand) መቀነስ የኤሌክትሪክ ፍላጎት ቀኑን ሙሉ እኩል አይደለም… ብዙ ደንበኞች በተመሳሳይ ጊዜ ኤሌክትሪክ ሲጠቀሙ፣ በሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጠራል… ስለሆነም የጫናውን ሰዓት መለየትና ደንበኞች በተለይም ትላልቅ ተቋማት ከፍተኛ ኤሌክትሪክ የሚወስዱ መሣሪያዎቻቸውን በአንድ ጊዜ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ በማድረግ ጫናውን መቀነስ ይቻላል… 💀. የማቀዝቀዣዎችን አጠቃቀም ማሻሻል ኤየር ኮንዲሽነር ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሊወስድ ይችላል… ይሁንና በሮችና መስኮቶችን በመጠቀም ጤናማ የአየር ዝውውር ለመፍጠር መሞከር ሁኔታውን ያሻሽለዋል… ከዚሁ ጋር የተበላሹ መሣሪያዎችን በወቅቱ መጠገን እና ተስማሚ የሙቀት መጠኖችን መጠቀም አላስፈላጊ ፍጆታን ይቀንሳል… 💀. የመሣሪያዎችን ቅልጥፍና ማሻሻል በጥሩ ሁኔታ ያልተያዙ መሣሪያዎች ኃይል ያባክናሉ… ቀልጣፋ (efficient) የሆኑ ሞተሮች፣ መብራቶች፣ ትራንስፎርመሮች፣ ፓምፖች፣ ኮምፕረሰሮች እና ሌሎች የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች ግን ፍጆታቸው አነስተኛ ነው… ስለሆነም efficient ስለሆኑ ቁሶች ደንበኞች ግንዛቤ እንዲይዙ መስራት አስፈላጊ ነው… ምክንያቱም… Energy efficiency is often the cheapest "generation" we can create. 🔔 መረሳት የሌለበት ነገር… ኃይልን መቆጠብ ሰዎች ለአንድ ሳምንት ብቻ የሚያስታውሱት የዘመቻ ተግባር መሆን የለበትም… የሁልጊዜ ልማድ እንጂ… 💡 የኃይል እይታ (Power Insight) ዛሬ የምንቆጥበው ኤሌክትሪክ፣ የነገውን ኤሌክትሪክ በሚያመነጨው ውኃ ላይ የሚፈጠረውን ጫና ይቀንሳል… 📌 የእርስዎ ሚና ለኃይል ዋስትና (Energy security) አስተዋፅኦ ለማድረግ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ መምራት አይጠበቅብዎትም… ከአቅራቢያዎ ተነስተው ልዩነት መፍጠር ይችላሉ… ከቢሮ፣ ከወርክሾፕ፣ ከክፍል፣ ከቤትዎ… አንድ ማብሪያ/ማጥፊያ (Switch)፣ አንድ ኮምፒውተር፣ አንድ አምፑል፣ አንድ ኃላፊነት የተሞላበት ውሳኔ - ልዩነት ያመጣል… በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች የሚያደርጓቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ኃላፊነት የተሞሉ ውሳኔዎች ተደምረው፣ ትልቅ ብሔራዊ አስተዋፅኦ ሊሆኑ ይችላሉ… 🫥 ትልቁ ምስል አንዲት የውኃ ጠብታ ኢምንት ትመስላለች… አንዲት የኪሎዋት ሰዓት (kWh) ኤሌክትሪክም እንዲሁ… ነገር ግን ወንዝ ማለት አብረው የሚንቀሳቀሱ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጠብታዎች ስብስብ እንጂ ሌላ አይደለም… የኤሌክትሪክ ሥርዓትም እርስ በእርሳቸው የተሳሰሩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የግለሰብ እርምጃዎች ውጤት ነው… ቀጣዩ ክፍል “ከግድብ ባሻገር” “ምን ያህል ውኃ አለን?” ብለን መጠየቅ አቁመን፣ “ምን ያህል የተለያዩ የኃይል ምንጮችን መገንባት እንችላለን?” ብለን መጠየቅ ስንጀምር ምን ይፈጠራል?... ከዝናብ እስከ ብርሃን ያለው ጉዞ ይቀጥላል... ---- We Strive to Create a Learning Organization!!
🗓️ ክፍል 4 ባትሪው እየደከመ ሲመጣ... (ዝናብ ከሚያስፈልገን በታች ቢሰጠን ምን ይፈጠራል?...) (ሰሞናዊው የኤልኒኖ ስጋት የቀሰቀሰው፣ ሳይንስን በጨዋታ ያለዘብንበት የቤታችን ወግ እንደቀጠለ ነው…) ደህና… አንድ ግድብ ግዙፍ የሆነ የኃይል መጠንን ማከማቸት ይችላል… ነገር ግን ውኃን መፍጠር አይችልም… የዝናብ መጠን ለረጅም ጊዜ ከመደበኛው በታች ሲቀንስ፣ በተፈጥሮው የግድቡን የውኃ ክምችት መልሶ መሙላት (Natural recharge) ይቀንሳል… ያኔ ሰንሰለቱ ይጀመራል፦ ዝናብ ማጠር ⬇️ ወደ ወንዞች የሚገባ ውኃ መቀነስ ⬇️ የግድብ ውኃ መጠን መውረድ ⬇️ የውኃ ግፊት (Hydraulic head) ማነስ ⬇️ ኃይል የማመንጨት አቅም መዳከም ⬇️ በኃይል ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጫና መፈጠር የአየር ንብረት መለዋወጥ (Climate variability) የኤሌክትሪክ አቅርቦት ደህንነት ጉዳይ የሚሆነው እዚህ ላይ ነው… ስሱ ሚዛን ውኃ ሲያንስ፣ የተቋማችን (EEP) አንገብጋቢ እና ስሱ ጥያቄ ይገጥመዋል፦ 💠 የነገውን የማመንጨት አቅም ሳይጎዳ የዛሬውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት እንዴት እናሟላ?... 💠 በከፍተኛ ደረጃ (Aggressively) ካመነጨን፣ የተከማቸው ውኃ በፍጥነት ሊያልቅ ይችላል… በጣም ከቆጠብን ደግሞ፣ ሥርዓቱ የዛሬን ፍላጎት ለማሟላት ይቸገራል… ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚገኘው የግድብ መጠንን፣ የወንዝ ፍሰትን፣ የፍላጎት ትንበያን፣ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ሁኔታ፣ የጥገና ፕሮግራሞችን እና አጠቃላይ የኃይል ማመንጫ ድብልቅን በጥንቃቄ በማቀናጀት ነው… ለዚህ ነው እያንዳንዱ ሜጋዋት እና እያንዳንዱ ኩቢክ ሜትር ውኃ ትልቅ ዋጋ ያለው። ❕ አሁን ምን ማድረግ እንችላለን? የአየር ንብረት ክስተትን የኤሌክትሪክ ተቋም በማቋቋም ማስቆም አይቻልም… ነገር ግን የሚፈጥረውን ተጽዕኖ መቀነስ ይቻላል… ⭐️ ስትራቴጂካዊ የውኃ አጠቃቀም፦ የግድብ የውኃ መልቀቅን እንደ ወንዝ ፍሰት ትንበያ፣ እንደ ክምችት ሁኔታ እና እንደ ሥርዓቱ ፍላጎት መሠረት በማድረግ ማመቻቸት፤ ⭐️ የኃይል ብክነትን መቀነስ፦ እያንዳንዱ አላስፈላጊ የኪሎዋት ሰዓት (kWh) ማለት፣ አላስፈላጊ የኃይል ማመንጨት ማለት ነው… በውኃ ኃይል ላይ በተመሠረተ ሥርዓት ውስጥ፣ ይህ ማለት አላስፈላጊ የውኃ ፍጆታ ማለት ነው… ለምሳሌ፦ በቢሮዎች፣ በኢንዱስትሪዎች እና በመኖሪያ ቤቶች ጥቅም ላይ የማይውሉ መብራቶችን እና ማሽኖችን ማጥፋት የውኃ ብክነትን ለመቀነስ የሚደረግ ቀጥተኛ አስተዋፅኦ ነው… ⭐️ ያለውን የኃይል ምንጭ መጠቀም፦ ሁኔታዎች ሲፈቅዱ በነፋስ፣ በፀሐይ፣ በጂኦተርማል እና በሌሎች አማራጭ የኃይል ምንጮች መገልገል፣ በውኃ ኃይል ጣቢያዎች ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል… ⭐️ ትንበያን ማጠናከር፦ የአየር ሁኔታ፣ የሃይድሮሎጂ እና የኤሌክትሪክ ፍላጎት ትንበያዎች የሥራ አፈጻጸም ውሳኔዎችን መምራት አለባቸው… ⭐️ ለከፋው መዘጋጀት፣ ለተሻለው ተስፋ ማድረግ፦ ግድቦች በአደገኛ ሁኔታ እስኪቀንሱ ከመጠበቅ ይልቅ፣ አስቀድሞ በተቀረጹ የዕቅድ አማራጮች (Scenario planning) ለዝናብ እጥረት መዘጋጀት… የእኛ ሚና ⚠️ ይህ ምላሽ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ኦፕሬተሮች ብቻ አይደለም… ✅ አላስፈላጊ መሣሪያዎችን የሚያጠፋ ሠራተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ✅ ቅልጥፍናን የሚጨምር መሐንዲስ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ✅ ጥንቃቄ የተሞላበት ውሳኔ የሚያደርግ ኦፕሬተር አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ✅ የተሻለ ትንበያ የሚጠቀም እቅድ አውጪ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ✅ ኃላፊነት የተሞላበት የኃይል አጠቃቀምን የሚያበረታታ አስተዳዳሪ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ✅ በሺዎች የሚቆጠሩ ትናንሽ ውሳኔዎች ተደምረው አንድ ትልቅ ብሔራዊ ምላሽ ይሆናሉ… የኃይል እይታ (Power Insight) ውኃ ሲያንስ፣ ኤሌክትሪክ የሁላችንም ኃላፊነት ይሆናል… ትልቁ ምስል ሙሉ ግድብ ስለ መትረፍረፍ ያስተምረናል… እየቀነሰ ያለ ግድብ ደግሞ ስለ ኃላፊነት ያስተምረናል… ተፈጥሮ ነገን እንደ ዛሬ ለማድረግ ቃል ኪዳን አልገባችልንም… የመቋቋም አቅም (Resilience) ማለት ዛሬ ያለንን ሀብት በጥበብ እየተጠቀምን፣ ነገ ለሚፈጠረው እርግጠኛ አለመሆን (Uncertainty) መዘጋጀት ነው… ምናልባት የአንድ ተቋም እውነተኛ መለኪያ፣ ሀብት ሲትረፈረፍ እንዴት እንደሚጠቀመው ማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ ሀብት ሲጎድልበት በምን ዓይነት ጥበብ ምላሽ ይሰጣል የሚለው ጭምር ነው… ቀጣዩ ክፍል “እያንዳንዱ ኪሎዋት ልዩነት ያመጣል” ውኃ የኃይል ምንጭ ከሆነ፣ ኤሌክትሪክን መቆጠብ በእውነት ውኃን መቆጠብ ያስችላል?... እንዴት?... ከዝናብ እስከ ብርሃን ያለው ጉዞ ይቀጥላል... ____ We Strive to Create a Learning Organization!!
🔔 ክፍል 3 የማይታየው ባትሪ በሀገራችን ውስጥ ያሉት ትልልቅ ባትሪዎች ከሊቲየም (Lithium) ሳይሆን ከውኃ የተሠሩ ቢሆንስ?... አንድ ትልቅ ግድብ/የውኃ ማጠራቀሚያ (Reservoir) አጠገብ እንደቆሙ ያስቡ… ከዳርቻው ሆነው ሲመለከቱት ሰፊ፣ ሰላማዊ እና የተረጋጋ የውኃ አካል ብቻ ሊመስል ይችላል… ጸጥ ያለ… ረጭ ያለ… እንቅስቃሴ አልባ… ነገር ግን ከዚያ ጸጥተኛ ገጽታ በታች አንድ አስደናቂ ነገር ተደብቋል… እሱም ክምቹ አቅም (Potential energy) ነው… ውኃው ጊዜውን እየጠበቀ ነው… ግድብ - ተፈጥሮ፣ ጊዜ እና ምህንድስና የሚገናኙበት ስፍራ ነው… ዝናቡ የዘነበው ከወራት በፊት ሊሆን ይችላል… ምናልባትም ከብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቆ በሚገኝ ቦታ… ሆኖም በምንጮችና በወንዞች በኩል ሲጓዝ መሐንዲሶች ጠልፈው አከማቹት… አሁን ደግሞ እየጠበቀ ነው - ብርሃን ለመሆን… ለዚህ ነው አንድን ግድብ የኢትዮጵያ “የማይታይ ባትሪ” አድርገን ልናስበው የምንችለው… በተፈጥሮ የተሠራ ባትሪ ስለ ባትሪ ስናስብ፣ አብዛኛውን ጊዜ ወደፊት ለመጠቀም ኃይልን የሚያከማች ነገር ወደ አእምሯችን ይመጣል… ግድብም የሚያደርገው በሚያስደንቅ ሁኔታ ተመሳሳይ የሆነ ነገር ነው… በከፍታ ላይ የተከተረ ውኃ ክምቹ አቅም (Gravitational potential energy) ይይዛል… በሃይድሮ ፓወር ተርባይን (Hydropower turbine) ውስጥ አልፎ ሲለቀቅ፣ ያ አቅም ወደ ሜካኒካዊ ኃይል (Mechanical energy)፣ ከዚያም ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል (Electrical energy) ይለወጣል… ባትሪ ሊያልቅ (Discharged) ይሆናል… ግድብም እንዲሁ ነው… የወደፊቱን የውኃ ፍሰት ከግምት ሳናስገባ ኤሌክትሪክ የምናመነጭ ከሆነ፣ ዛሬ የተከማቸውን ውኃ በጣም በፍጥነት ልንጨርሰው እንችላለን… ዝናብ በበቂ መጠን ከሌለ ግድቡ ወዲያውኑ ራሱን መተካት አይችልም… ለዚህ ነው የግድብ አሰራር ዛሬ ብዙ ኤሌክትሪክ ስለማመንጨት ብቻ የማይሆነው… ይልቁንም በዛሬው ፍላጎት (Demand) እና በነገው ዋስትና (Security) መካከል ትክክለኛውን ሚዛን ማግኘትን ይጠይቃል… ይህ በተለይ በድርቅ እና በአየር ሁኔታ መለዋወጥ ወቅት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው… ጥያቄው፦ “ምን ያህል ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንችላለን?” የሚለው አይደለም… “ነገ የማመንጨት አቅማችንን ጠብቀን፣ ዛሬ ምን ያህል ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንችላለን?” የሚለው እንጂ… ግድቡ ሲሞላ፣ እያንዳንዱ ሜጋዋት (Megawatt) ቀላል ሊመስል ይችላል… ውኃው ማብቂያ የሌለው ሊመስል ይችላል… ነገር ግን እጥረት እይታችንን ይለውጠዋል… በድንገት፣ እያንዳንዱ ኩዩቢክ ሜትር ውኃ ዋጋ ይኖረዋል… እያንዳንዱ ውኃ መልቀቅ ቁልፍ ውሳኔ ይሆናል… እያንዳንዱ አላስፈላጊ አጠቃቀም የባከነ ዕድል ይሆናል.. የሰው ልጅ ብዙ ጊዜ የሚረሳውን ነገር ተፈጥሮ ታስተምረናለች፦ አንድ ነገር ስላለን ብቻ ዛሬውኑ ሁሉንም መፍጀት አለብን ማለት አይደለም… አንዳንድ ጊዜ ጥበብ ማለት መቼ መጠቀም እንዳለብን ማወቅ ነው… አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጥበብ ማለት መቼ መጠበቅ እንዳለብን ማወቅ ነው… ለዚህ ነው ዘመናዊ የኃይል ሥርዓት አሠራር ከጊዜ ጥበቃ ወደ ጊዜ ትንበያ፣ ወደ ሞዴሊንግ (Modelling)፣ የመረጃ ትንተና፣ ሁኔታዎችን አስቀድሞ የማቀድ (Scenario planning) እና የተቀናጀ ውሳኔ አሰጣጥ ማደግ ያለበት… Plant Operator ዝም ብሎ ውኃን ብቻ የሚመለከት አይደለም… ጊዜን፣ ኃይልን፣ እርግጠኛ አለመሆንን (Uncertainties) እና ስጋትን (Risk) እያስተዳደረ ነው እንጂ… ባትሪው እየደከመ (Running down) ሲመጣ… አሁን ደግሞ ከቅድሙ በተቃራኒው ያስቡ… የዝናብ መጠን ከመደበኛው በታች ነው፣ ወደ ወንዞች የሚገባው ውኃ ቀንሷል፣ የግድቡ ውኃ መቀነስ ጀምሯል፣ የኤሌክትሪክ ፍላጎት ግን ማደጉን ቀጥሏል… ይሄኔ የሥርዓቱ ኦፕሬተር አስቸጋሪ ምርጫ ይጋፈጣል፦ ዛሬ ብዙ አምርቶ ክምችቱን በፍጥነት መቀነስ?ወይስ ውኃውን ቆጥቦ የወደፊቱን የማመንጨት ሂደት ማስጠበቅ?... ቀላል መልስ የለውም… ትክክለኛው ውሳኔ በአጠቃላይ ሥርዓቱ ላይ የተመሰረተ ነው… ለዚህ ነው የኃይል ዋስትና በመጨረሻ የሥርዓታዊ አስተሳሰብ (Systems thinking) ጉዳይ ሆኖ የሚከሰተው… ግድቡ ከግሪዱ (Grid) ተነጥሎ ሊታይ አይችልም… ግሪዱ ከፍላጎት (Demand) ተነጥሎ ሊታይ አይችልም… ፍላጎት ከኢኮኖሚው ተነጥሎ ሊታይ አይችልም… እናም አንዳቸውም ቢሆኑ ከአየር ሁኔታ እና ከውኃ መጠን ተነጥለው ሊታዩ አይችሉም… ትልቁ ምስል በግድብ ውስጥ እጅግ ጥልቅ የሆነ ውበት አለ… ስለ ጊዜ ያስተምረናል… ዝናብ በአንድ ቅጽበት ይዘንባል… ግድብ ግን ያ ቅጽበት ሌላኛውን ቅጽበት እንዲያገለግል ይፈቅዳል… የትናንት ዝናብ የዛሬን ሆስፒታል ተግባር ይወስናል… የባለፈው ወር ዝናብ የዛሬን ፋብሪካ ሊያንቀሳቅስ ይችላል… በተራራ ላይ የወረደ ውኃ በመጨረሻ በብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኝ ከተማ ውስጥ ብርሃን ሊሆን ይችላል… በዚህ መንገድ - ግድብ ያለፈውን፣ የአሁኑን እና የወደፊቱን ያገናኛል… ተፈጥሮ ዛሬ የሰጠችን የነገ ኃላፊነታችንንም ጭምር ነው… ሙሉ ግድብ የመትረፍረፍ ምልክት ብቻ አይደለም - ኃላፊነትም እንጂ… የጎደለ ግድብ ችግር ብቻ አይደለም - የጥበብ መፈተኛም እንጂ… የኃይል እይታ (Power Insight) ግድብ ከውኃ በላይ የሆነን ነገር ያከማቻል… ኃይልን፣ ጊዜን፣ ምርጫዎችን እና ኃላፊነትን… ተቋማችን ሊማረው የሚገባው ጉዳይ… በተለመደው የውኃ ፍሰት ቁጥጥር ዘይቤ ብቻ መጓዝ አሁን ላይ በቂ አይደለም… ይበልጥ የሚያስፈልጉን፦ ✅የተሻለ የሃይድሮሎጂ ትንበያ (Hydrological forecasting) ✅የአየር ሁኔታ መረጃን ያገናዘበ የማመንጨት እቅድ ግድቦችን በተሻለ ሁኔታ የመጠቀም (Reservoir optimization) ልምምድ ✅የቀጥታ ሰዓት መረጃ እና ክትትል (Real-time data and monitoring) ✅ሁኔታዎችን መሠረት ያደረገ እቅድ (Scenario-based planning) ✅በውኃ እና አየር ሁኔታ ጉዳይ ላይ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር ✅በዲጂታል (በተለይ AI) የታገዙ የውሳኔ ድጋፍ ሥርዓቶችን መከተል ✅ቴክኒካዊውንና የክላይሜት ስጋቶችን የሚረዱ የተማሩ ባለሙያዎች ማፍራት የውኃ ጥበብ ውኃ ከተፈጥሮ መልክዓ ምድር ጋር መቼም አይከራከርም… መንገዱን ፈልጎ ያልፋል፣ በአንድ ቦታ ይሰበሰባል፣ ወደ ሌላ ቦታ ይንቀሳቀሳል፣ ቅርጹን ይለውጣል፣ ይጠብቃል፣ ይፈሳል፣ ኃይል ይሰጣል፣ እናም በመጨረሻ ወደ ሰማይ ይመለሳል… ውኃ - ጥንካሬ ሁልጊዜ ጉልበት ማለት እንዳልሆነ ያስታውሰናል… አንዳንድ ጊዜ ጥንካሬ ትዕግሥት ነው፣ አንዳንድ ጊዜ ዕድገት መንቀሳቀስ ነው… አንዳንድ ጊዜ ጥበብ መቼ መፍሰስ እና መቼ መረጋጋት እንዳለብን ማወቅ ነው… እናም አንዳንድ ጊዜ መረጋጋት መስሎ የሚታየው ትክክለኛውን ቅጽበት የሚጠብቅ የተከማቸ እምቅ አቅም ነው… ቀጣዩ ክፍል - “ውኃ ብርሃን ሲሆን” ጸጥተኛው ግድብ እንዴት ሀገርን ወደሚያበራ ኤሌክትሪክ ይለወጣል?... --- We Strive to Create a Learning Organization!!
💧🏪🫥 ሰላም ለእናንተ ይሁን!! -- ሰሞኑን በስልክ፣ በኢንቦክስና በአካል በተደጋጋሚ ከቀረቡልን ጥያቄዎች ውስጥ ‘ደራሽ ምን ላይ ደረሰ?’ የሚለው ጉዳይ ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አግኝተነዋል… ☀️ እውነት ለመናገር - ✅ይህ ክትትል ተስፋ ይሰጣል! ✅ይህ ጥያቄ ያበረታል! ✅ይህ ጉትጎታ የስንፍና እንቅልፍ ይነሳል! ✅ይህ ጥያቄ ደራሽ የሁሉም ሰው ሃሳብነቱን ያጎላል! እንደምታውቁት ጉዳዩ አዲስ ተቋማዊ ስርዓት የመፍጠር ሂደት እንደመሆኑና ገንዘብ ነክ እንቅስቃሴዎችም ስላሉበት ቀጣይነቱ፣ ተዓማኒነቱና ፍትሐዊነቱ ላይ ከጅምሩ መሰራት አለበት… በዚህም ምክንያት ጊዜ ወስዶብናል… ✅ የምናስበው ደራሽ - የኮሚቴ ስራ አይደለም! ✅ የምንገነባው ደራሽ - የአንድ ወቅት ተግባር አይደለም! ✅ የምናልመው ደራሽ - ከዕድሜያችን የሚበልጥ ነው! ይህ በእንዲህ እንዳለ ደራሽ ተቋማዊ ስርዓት ሆኖ ሙሉ ለሙሉ በአሰራር እስኪደገፍ ድረስ ብቻ የሚያደራጀው ጊዜያዊ ስብስብ በእስካሁን ቆይታው፡- ⭐ EEP Social Support Service (Derash) Directive - (መመሪያ)፤ ⭐ Membership registration template - (የአባልነት መመዝገቢያ)፤ ⭐ Financial management procedure - (የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ)፤ ⭐ Derash Governance Charter – (የደራሽ ማሕበራዊ ድጋፍ አገልግሎት ውል) ⭐ Emergency Support SOP – (የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ የአሰራር ስርዓት) ⭐ Digital system design – (ወደ ዲጂታል ስርዓት ማስገቢያ ሰነድ) ⭐ Vision, Mission & Guiding principles - አዘጋጅቶ ጨርሷል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቅርቡ ለሚደረገው መስራች ጉባኤ (ለዋ/መ/ቤት፣ ሦስቱ ሴንትራሎች፣ ረጲና ኤልዲሲ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች) የሚቀርብ Preliminary Financial Analysis and Sustainability Model (የቅድመ ትግበራ የፋይናንስ ፍላጎት ትንተናና የማዝለቂያ ስልት - /የአባላት መዋጮ፣ የድጋፍ መጠን፣ ከተቋም የሚፈለግ እገዛ/… ወዘተ የያዘ) ንድፍ ሰነድ አዘጋጅቶ የስብሰባውን ቀን ይጠብቃል፡፡ 🙏 አብራችሁን ለተጓዛችሁና እንደመደበኛ ስራችሁ ሂደቱን ላገዛችሁ የስራ ኃላፊዎችና ጊዜያዊ አደራጆች እጅግ አድርገን እናመሰግናለን!! 👉 ደራሽ ቻናልን ተቀላቀሉ - https://t.me/eepderash በቅርቡ እንገናኝ!! 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🔺🔺🔺 ክፍል 2 ያልተስተዋለው ነዳጅ የሃገራችን ኤሌክትሪክ ምንጭ - የመጀመሪያው ነዳጅ ከማዕድን ማውጫ የሚቆፈር አይደለም... ከሰማይ የሚወርድ እንጂ… ✅ የኤሌክትሪክ ነዳጃችን ምንድን ነው?... ይህንን ጥያቄ ለማንኛውም ሰው ቢያነሱ፣ መልሱ ምናልባት፦ “ውኃ” የሚል ይሆናል… ይህ ግልጽ ይመስላል… ደግሞም ግድቦቻችን ውኃን ተጠቅመው ተርባይኖችን (Turbines) በማሽከርከር ኤሌክትሪክ እንደሚያመነጩ የታወቀ ነው… ነገር ግን፣ ውኃ - የኃይል ሥርዓታችን የመጀመሪያው ነዳጅ አይደለም ብልዎትስ?... Water is only the carrier… እውነተኛው ነዳጅ ወንዞች መፍሰስ ከመጀመራቸው ከብዙ ጊዜ በፊት በጸጥታ የቆየ፣ በዝምታ ያደፈጠ ነው... በደመናዎች ውስጥ!... ⛈ እያንዳንዱ ብርሃን የሚጀምረው ከዝናብ ጠብታ ነው ተርባይን መሽከርከር ከመጀመሩ በፊት... የማስተላለፊያ መስመሮች (Transmission lines) ኤሌክትሪክን በመላ ሀገሪቱ ከማድረሳቸው በፊት... በአንድ ክፍል ውስጥ አምፑል በርቶ ብርሃን ከመፈንጠቁ በፊት... [በቅድሚያ ሌላ ነገር መከሰት አለበት…] ፀሐይ ውቅያኖሶችን ታሞቃለች… ውኃው ተንኖ ወደ ከባቢ አየር (Atmosphere) ይወጣል… ደመናት ይፈጠራሉ… ነፋሳት እነዚያን ደመናዎች አህጉራትን አቋርጠው ያጓጉዟቸዋል… በኢትዮጵያ ተራራማ ቦታዎች ላይ ዝናብ ይዘንባል… ያ ዝናብ ወንዞችን ይመግባል… እነዚያ ወንዞች ማጠራቀሚያዎችን (Reservoirs) ይሞላሉ… ግድቦቹ ውኃውን በተርባይኖች ውስጥ ይለቁታል… ኤሌክትሪክ ሊመረት የሚችለው ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው… እኛ የምናበራው እያንዳንዱ መብራት ከምድር በላይ ከፍ ካለ ቦታ የጀመረ የራሱ ታሪክ አለው… ✅ ተፈጥሮ የመጀመሪያዋ መሐንዲስ ናት አንድን የሃይድሮ ፓወር ጣቢያ ስናደንቅ፣ አብዛኛውን ጊዜ የምናደንቀው የኮንክሪት ግንቦቹን፣ ተርባይኖቹን፣ ጀነሬተሮቹን፣ ትራንስፎርመሮቹን እና የማስተላለፊያ ማማዎቹን ነው… ነገር ግን የመጀመሪያዋ መሐንዲስ (ተፈጥሮ) አብዛኛውን ሥራ ቀድማ አከናውናዋለች… የሰው ልጅ ግድቦችን ከመገንባቱ ከረጅም ጊዜ በፊት ተፈጥሮ የውኃን ዑደት (Water cycle) ቀርጻለች… ፀሐይ በየቀኑ በቢሊዮን የሚቆጠር ቶን ውኃ ከውቅያኖሶች ላይ ታነሳለች… ከባቢ አየር በመላው ዓለም ያጓጉዘዋል… ተራሮች የዝናብ ውኃውን ወደ ወንዞች ይመሩታል። መሐንዲሶች የዚያን ተፈጥሯዊ ጉዞ ጥቂት ክፍል ብቻ ጠልፈው ወደ ኤሌክትሪክ ይለውጡታል… አዎን - ቴክኖሎጂ ተፈጥሮን አይተካም፤ ከተፈጥሮ ጋር አብሮ ይሠራል እንጂ… 🟢 ይህ ለተቋማችን (EEP) ለምን ያስፈለገዋል? ይህ መረዳት ለሥራችን ያለንን አመለካከት ይለውጠዋል። አንድ የሃይድሮ ፓወር ማመንጫ ጣቢያ ለብቻው ተለይቶ የቆመ ፋሲሊቲ አይደለም… እጅግ ሰፊ በሆነ ሰንሰለት ውስጥ የመጨረሻው ማያያዣ እንጂ… 👉 ዝናብ ሲቀንስ ➡️ ወደ ወንዞች የሚገባው ውኃ ይቀንሳል፤ 👉 ወደ ወንዞች የሚገባው ውኃ ሲቀንስ ➡️ በግድቦች የሚከማቸው ውኃ ያንሳል፤ 👉 በግድቦች የሚከማቸው ውኃ ሲያንሥ ➡️ ኃይል ማመንጨት ፈታኝ ይሆናል፤ ለዚህ ነው የአየር ሁኔታ ትንበያ፣ የወንዞች ተፋሰስ አስተዳደር (Watershed management)፣ የግድብ አሰራር እና የክላይሜት ሳይንስ (Climate science) ለተቋማችን ስትራቴጂካዊና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች የሚሆኑት… ለዚህ ነው የኤሌክትሪክ ኃይላችንን የመጠበቅ ስራ የሚጀምረው ውኃው ግድብ ላይ ከመድረሱ ከብዙ ጊዜ በፊት ነው የምንለው… 🌧 ዝናብን በሌላ እይታ መመልከት ብዙ ሰዎች ዝናብን ዝም ብለው እንደ አየር ሁኔታ ያዩታል… የኃይል ዘርፍ ባለሙያዎች ግን ከዚያ በላይ የሆነ ነገር ያያሉ… እያንዳንዷ የዝናብ ጠብታ የወደፊቱን ኃይል የተሸከመች አነስተኛ እሽግ ናት… ሚሊዮን የዝናብ ጠብታዎች ምንጭ ይሆናሉ፤ ምንጮች ወንዝ ይሆናሉ፤ ወንዞች ግድብ ይሆናሉ፤ ግድቦች ደግሞ ኤሌክትሪክ ይሆናሉ… እያንዳንዱ የዝናብ ወቅት የሃገራችንን ግዙፍ ተፈጥሯዊ ባትሪዎች በጸጥታ መልሶ እየሞላ (Recharging) ነው… ⚡️ የኃይል እይታ (Power Insight) ተርባይኑን የሚያሽከረክረው ውኃ ቢሆንም፣ ውኃው እንዲኖር የሚያደርገው ግን ዝናብ ነው… በሃይድሮ ፓወር የሚመነጨው እያንዳንዱ ዩኒት ኤሌክትሪክ ጉዞውን የሚጀምረው ከዝናብ ጠብታ ነው… ➡️ የእርስዎ ሚና ኤሌክትሪክ እንዳይባክን ስንጠነቀቅ፣ በግድቦቻችን ውስጥ አላስፈላጊ ውኃ እንዳይፈስም እየጠበቅን ነው… ኤሌክትሪክ መቆጠብ ወጪን ስለመቀነስ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያን እጅግ ውድ የኃይል ሀብት — ውኃን — ስለመጠበቅም ጭምር እንጂ… በሺዎች በሚቆጠሩ ሰራተኞች የሚታዩ ትናንሽ ተግባራት ተደምረው ለሀገራችን የኃይል ዋስትና (Energy security) ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ… ✅ ትልቁ ምስል አንድ የዝናብ ጠብታ በራሷ ኢምንት ልትመስል ትችላለች… ነገር ግን ስፍር ቁጥር የሌላቸው የዝናብ ጠብታዎች ሀገርን ማብራት ይችላሉ… ታላቅነት አብዛኛውን ጊዜ የሚገነባው እርስ በእርሳቸው ከተሳሰሩ ትናንሽ አስተዋፅኦዎች መሆኑን ተፈጥሮ ያስታውሰናል… በሰዎችም ዘንድ እውነታው ይሄው ነው… እያንዳንዱ ግለሰባዊ ጥረት፣ ምንም ያህል ትንሽ ቢመስል፣ ከሌሎች ጥረቶች ጋር ሲቀላቀል እጅግ ታላቅ የሆነ ነገር አካል ይሆናል… [ቀጣዩ ክፍል] “ግድቦች፦ የኢትዮጵያ የማይታዩ ባትሪዎች” በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ትልልቅ ባትሪዎች ከሊቲየም (Lithium) ሳይሆን ከውኃ የተሠሩ ቢሆኑስ?... -- We Strive to Create a Learning Organization!!
🌧 🔸💡 ከዝናብ እስከ ብርሃን የኤሌክትሪክ ሕቡዕ ጉዞ [ክፍል 1] --- መብራታችንን ማጥፋት የሚችለው ውቅያኖስ በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የተከሰተ ችግር… ከኢትዮጵያ ከ15,000 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ የሚገኝ ውቅያኖስ የሙቀት መጠን... መኖሪያ ቤቶቻችንን፣ ሆስፒታሎቻችንን፣ ኢንዱስትሪዎቻችንን እና የሥራ ቦታዎቻችንን የሚያበራውን ኤሌክትሪክ ሊነካው እንደሚችል አስበው ያውቃሉ?... በመጀመሪያ ሲሰሙት የማይቻል ይመስላል… በሌላኛው የዓለም ክፍል የሚገኝ ውቅያኖስ በኢትዮጵያ የሚገኝን የሃይድሮ ፓወር (Hydropower) ጣቢያ እንዴት ሊጎዳ ይችላል?... ነገር ግን ኤል ኒኖ (El Niño) በሳይንቲስቶች፣ በመንግሥታት እና በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የኤሌክትሪክ ተቋማት — (EEP)ን ጨምሮ — በትኩረት ከሚከታተሏቸው የአየር ሁኔታ (Climate) ሁነቶች አንዱ የሆነበት ምክንያት አለ… ነገርየውን ለመረዳት፣ በመጀመሪያ አንድን ትልቅ እውነት መረዳት አለብን፦ 🔺 ተፈጥሮ እርስ በእርሱ የተሳሰረ አንድ ሥርዓት ነው። ምንም ነገር ተነጥሎ አይኖርም። ውቅያኖሶች የአየር ሙቀትንና ግፊትን (Atmosphere) ይወስናሉ፤ አየር ንብረቱ ደግሞ የአየር ሁኔታን (Weather) ይቀርጻል፤ የአየር ሁኔታው የዝናብ መጠንን ይወስናል፤ ዝናብ ወንዞችን ይመግባል፤ ወንዞች ግድቦችን/ማጠራቀሚያዎችን (Reservoirs) ይሞላሉ፤ ግድቦች ኤሌክትሪክ ያመነጫሉ፤ ኤሌክትሪክ ደግሞ የእለት ተእለት ሕይወታችንን ያንቀሳቅሳል፤ በዚህ ሰንሰለት ውስጥ ባለው በአንዱ ክፍል ላይ የሚከሰት ለውጥ፣ በመጨረሻም እያንዳንዱን ክፍል ይነካዋል… ❓ 🧊ኤል ኒኖ (El Niño) ምንድን ነው? ኤል ኒኖ በማዕከላዊ እና በምስራቃዊ ፓሲፊክ ውቅያኖስ የላይኛው የውኃ አካል ላይ በሚከሰት ያልተለመደ የሙቀት መጨመር ምክንያት የሚፈጠር ተፈጥሯዊ የአየር ሁኔታ ለውጥ ሁነት ነው… ከኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቆ ቢጀመርም፣ ያ የሙቀት መጨመር ግን የዓለም አቀፉን የከባቢ አየር ዝውውር ይለውጠዋል… የነፋስ አቅጣጫዎችና ዘይቤዎች ሲቀየሩ፣ በብዙ የዓለም ክፍሎች ያለው የዝናብ ሥርጭትም አብሮ ይለወጣል… ✅ ሀገራት ከመጠን በላይ የሆነ ዝናብና የጎርፍ አደጋ ያጋጥማቸዋል… ✅ ሌሎች ደግሞ ከመደበኛው ያነሰ ዝናብ በማግኘት ለድርቅ ይጋለጣሉ… ኤሌክትሪኳ በዋናነት በውኃ ላይ ለተመሰረተ ለእንደኛ ዓይነት ሃገር፣ ይህ ጉዳይ እጅግ በጣም ትልቅ ትርጉም አለው… ⭐️ ተቋማችን (EEP) ለምን ሊጨነቅ ይገባል? በዋናነት በከሰል፣ በነዳጅ ወይም በተፈጥሮ ጋዝ ከሚጠቀሙ ሀገራት በተለየ፣ ኢትዮጵያ አብዛኛውን የኤሌክትሪክ ኃይል የምታመነጨው ከ Hydro power (ከውኃ ኃይል) ነው… ይህ ማለት የእኛ እጅግ ውድ የሆነው የኃይል ሀብታችን ከመሬት በታች የሚገኝ አይደለም… ከደመናት የሚወርድ እንጂ… እያንዳንዱ የዝናብ ወቅት ግድቦቻችንን የሚመግቡትን ወንዞች ያድሳል… እነዚያ ግድቦች ውኃውን አከማችተው በመያዝ፣ በተርባይኖች (Turbines) ውስጥ አልፎ ኤሌክትሪክ እንዲያመነጭ ይለቁታል… ዝናብ ለረጅም ጊዜ ሲቀንስ፣ ወንዞች የሚያመጡት የውኃ መጠን ያንሳል፤ በግድቦች ውስጥ ያለው የውኃ መጠን በሂደት ይቀንሳል፤ በዚህም ምክንያት ሊመነጭ የሚችለው የኤሌክትሪክ መጠን ሊቀንስ ይችላል… ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ዝናብ ዝም ብሎ የአየር ሁኔታ ብቻ አይደለም… ዝናብ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ሰንሰለታችን መነሻ ነው… ሁላችንንም የሚያያይዝ ሰንሰለት!! ጉዞው እጅግ በጣም ቀላል እና ግልጽ ነው፦ የሞቀ የፓሲፊክ ውቅያኖስ ⬇️ የከባቢ አየር ዝውውር መለወጥ ⬇️ በኢትዮጵያ ላይ ያለው የዝናብ መጠን መለወጥ ⬇️ ወደ ወንዞች የሚገባው ውኃ መቀነስ ⬇️ በግድቦች የሚከማቸው ውኃ መቀነስ ⬇️ የሃይድሮ ፓወር ኤሌክትሪክ ምርት መቀነስ ⬇️ በብሔራዊ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ጫና መፈጠሩ በውቅያኖስ ሙቀት ለውጥ የሚጀምረው ክስተት፣ በመጨረሻም ወደ እኛ የኃይል ሥርዓት ይደርሳል… 📌 ይህ ከ EEP በላይ ለሁላችንም ለምን ያሳስበናል? ኤሌክትሪክ ከብርሃን በላይ ነው… ሕይወትን የሚያድኑ ሆስፒታሎችን ያንቀሳቅሳል፤ ኢንዱስትሪዎች ምርታማ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ትምህርት ቤቶችን፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ የመገናኛ መረቦችን እና አስፈላጊ የሕዝብ አገልግሎቶችን ይደግፋል… የኤሌክትሪክ አቅርቦት አስተማማኝነት ሲጎዳ፣ ጉዳቱ እያንዳንዱን ዜጋ እና እያንዳንዱን የኢኮኖሚ sector ይነካል… ለዚህ ነው የአየር ንብረት ለውጥ ሁኔታን መረዳት የኃይል አቅርቦትን የመረዳት አካል የሆነው… ✅ የኃይል እይታ (Power Insight) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ጉዞ የሚጀምረው ከግድብ ወይም ከተርባይን አይደለም… የሚጀምረው ከደመና፣ ከዝናብ፣ ከወንዞች እና ከፕላኔታችን እያንዳንዱን ክፍል ከሚያያይዘው የ Climate ሥርዓት ነው… ✅ የእርስዎ ሚና እያንዳንዱ ሰራተኛ መፃኢ የኃይል ምንጫችንን በመጠበቅ ረገድ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት ይችላል… ስለ አየር ሁኔታ እና ክላይሜት በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ይጀምሩ… እነዚህ ጉዳዮች የአየር ሁኔታ ተንባዮች ብቻ የሚያነሷቸው አጀንዳዎች መሆናቸው አክትሟል… የዘመናዊ የኃይል ሥርዓቶች ቋንቋ አካል ሆነዋል… በ Climate እና በኤሌክትሪክ መካከል ያለውን ግንኙነት በተረዳን ቁጥር፣ ለሀገራችን አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥ የተሻለ ዝግጅት ይኖረናል… ✅ ትልቁ ምስል ብዙ ጊዜ ዓለምን የተለያዩና የተነጣጣሉ ቦታዎች ስብስብ አድርገን እናስባለን፤ ተፈጥሮ ግን ሌላ ታሪክ ትነግረናለች… ውቅያኖሶች፣ ከባቢ አየር፣ ተራሮች፣ ወንዞች እና የሰው ልጅ በአንድ ሕያው ሥርዓት ውስጥ ተሸምነዋል… ኤል ኒኖ በምድር በአንዱ በኩል የሚከሰት ክስተት በሌላኛው ወገን ያለውን ሕይወት ሊነካው እንደሚችል ያስታውሰናል… ይህንን እርስ በእርስ የመተሳሰር ሁኔታ መረዳት፣ በአደራ የተሰጡንን ሀብቶች በጥበብ ለማስተዳደር የመጀመሪያው እርምጃ ነው… --- በቀጣይ ክፍል፦ ውኃ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነዳጅ ካልሆነ፣ ታዲያ ምንድን ነው?... --- We Strive to Create a Learning Organization!!
🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤 ማስታወሻ ለጉግል ክሮም Browser ተጠቃሚዎች . . . "የጉግል ክሮም የደህንነት ቡድን በማሰሻው (Browser) ላይ ለተገኙ 370 የደህንነት ክፍተቶች የሶፍትዌር ማስተካከያ (Security Patches) አውጥቷል፤ ከእነዚህም ውስጥ 7ቱ እጅግ አሳሳቢ (Critical) የሚባሉ ናቸው። ይህ የደህንነት ማስተካከያ እ.ኤ.አ ሐምሌ 29 የተለቀቀ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች የክሮም ቨርዥን 151 (Version 151) ለዊንዶውስ እና ማክ (151.0.7922.71/.72) እንዲሁም ለሊነክስ (151.0.7922.71) በአፋጣኝ ማዘመን (Update) ይኖርባቸዋል" ሲል INSA አሳስቧል... የኢንተርኔት ማፈላለጊያዎ ምንድነው? Chrome ከሆነ አሁኑኑ Update ያድርጉት... Settings - About chrome - Update [Automatic] ___ "Our digital future depends not only on the systems we build, but on the security habits we practice every day."
💡 ❓ Why do leaders' actions often outweigh their words in establishing culture? 📣 Leadership is fundamentally about behavioral signaling. 💬 When a leader communicates a core value (like integrity) but then ignores or tolerates a team member behaving unethically, the silence acts as an implicit endorsement of that bad behavior. 🟢 Employees are highly perceptive; they look for the 'gap' between stated values and actual practice. 🚨 Once that gap is identified, the 'tolerated' behavior inevitably becomes the new organizational norm or 'standard' because human beings naturally look for the path of least resistance and the actual boundaries of the environment, not the theoretical ones described in a mission statement. ___ ⚡️ We Strive to Create a Learning Organization ⚡️
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
Tumut - 3
⚡️ Tumut 3: When Hydropower Becomes the Battery of the Grid ዛሬ በአውስትራሊያ የነጭ የበረዶ ተራሮች (Snowy Mountains) ጥልቅ ውስጥ ስለሚገኝ አንድ የውሃ ኃይል ማመንጫ እናወራለን... እግረመንገዱን ለሃገራችን ልንኮርጀው የሚገባውን የምህንድስና ጥበብ እናነሳለን... የስኖዊ ማውንቴንስ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ scheme አካል የሆነው የቱሙት 3 የኃይል ማመንጫ (Tumut 3 Power Station)፣ ወደ 1,800 ሜጋዋት (MW) የሚጠጋ የማመንጨት አቅም (generating capacity) አለው... የማመንጫው አስደናቂ ነገር ግን የኤሌክትሪክ ምርቱ አይደለም - የምህንድስና ጥበቡ እንጂ... ውሃን እንደተከማቸ ኃይል (stored energy) የሚጠቀምበት መንገድ እጅግ ይገርማል... ✅ ነገሩ እንዴት መሰላችሁ?... ኤሌክትሪክ በሚፈለግበት ጊዜ ውሃ ከታልቢንጎ ግድብ (Talbingo Reservoir) በኃይል ማመንጫው በኩል ወደ ጁናማ ኩሬ (Jounama Pondage) ይፈስሳል... ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ፍላጎት (lower demand) በሚኖርበት ጊዜ ግን ከስድስቱ ማመንጫ ክፍሎች (generating units) ውስጥ ሦስቱ ወደ ኋላ ተመልሰው እንደ ፓምፕ (pumping units) በመስራት ውሃውን ወደ ላይኛው ግድብ ይመልሱታል... [በቀላል አነጋገር...] ➡️ ውሃ ማከማቸት → ማመንጨት → ውሃን መልሶ መሰብሰብ (Recover) → እንደገና ማከማቸት → እንደገና ማመንጨት - ነው ነገሩ… በዚህ መንገድ ያው ውሃ ኤሌክትሪክን ከአንዱ የቀኑ ክፍለ-ጊዜ ወደ ሌላው ለማሸጋገር የሚያስችል የኃይል ማከማቻ (energy storage medium) ሆኖ ያገለግላል... ይህ - እንደ ኢትዮጵያ ባሉና ከፍተኛ የሃይድሮፓወር ግድቦችን (hydropower reservoirs) በታደሉ እንዲሁም የፀሐይ (solar) እንዲሁም የነፋስ (wind) ኃይል አቅማቸው በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በሚገኝ ሀገራት፣ ግድብ ከኤሌክትሪክ ማመንጫ የውሃ ምንጭነት ባሻገር ትልቅ ፋይዳ ያለው ነገር መሆኑን አመልካች ነው... [ነገሩን ከነባር ልማዳችን ወጣ ብለን በተለየ መንገድ ለመመልከት እንድንችል እንዲህ እንጠይቅ...] ✅ ግድቦቻችን ለብሔራዊ የኤሌክትሪክ መረብ (national grid) ስልታዊ የኃይል ማከማቻ ሀብት (strategic energy storage assets) መሆን ይችላሉ ወይ?... ✅ በቂ የፀሐይ ወይም የነፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም በሚኖርበት ጊዜ - ሃይድሮፓወሩን የማመንጨት አቅም በመቀነስ ውሃን በግድቡ ውስጥ ጠብቆ ማቆየት... እንዲሁም የታዳሽ ኃይል ምርት ሲቀንስና የኤሌክትሪክ ፍላጎት ሲጨምር ደግሞ ያንን የተከማቸ ውሃ በመልቀቅ ኤሌክትሪክ ማመንጨት... [ይቻላል ወይ?...] 🎓 ሳይንስና ተግባራዊ ተሞክሮዎች - 'አዎን... የመሬት አቀማመጥ (geography)፣ የውሃ ባህሪ (hydraulics)፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች በሚፈቅዱበት ቦታ፣ "ፓምፕድ ስቶሬጅ" (dedicated pumped storage) በመጠቀም ይህን ማድረግ ይቻላል' ይላሉ... 🔔 ነገሩ ለእኛ ሃገር ነባር የሃይድሮፓወር ስርዓት አዲስ የኢንጂነሪንግ አስተሳሰብ ነው... Hydropower generation + reservoir storage + renewable energy + grid flexibility + regional interconnection (የውሃ ኃይል ማመንጨት + የግድብ ማከማቻ + ታዳሽ ኃይል + የኤሌክትሪክ መረብ ተለዋዋጭነት/ተጣጣፊነት + ቀጠናዊ የኃይል ትስስር) ሃሳቡ እያንዳንዱን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ እንደ ተነጣጣይ ሀብት ከማየት ይልቅ፣ አጠቃላይ የግድብ ስርዓታችንን እንደ እምቅ የኃይል ማከማቻ እና የማመጣጠኛ ሀብት (balancing resource) አድርጎ መመልከትን ይጠይቃል... ከቱሙት 3 የኃይል ማመንጫ ምህንድስና የምንማረውም ይህንን ነው... አዎን... ኢትዮጵያ - የሃይድሮፓወር ሀብቶቿን ኤሌክትሪክ ከማመንጨት ባለፈ፣ የወደፊቱ የታዳሽ ኃይል መረብ (renewable grid) የሚፈልገውን ተጣጣፊነት (flexibility) ለማሟላት የኃይል ማከማቻ (energy storage) አገልግሎት ወደ መስጠት ማሸጋገር ትችላለች... የሃይድሮፓወር ዕጣ ፈንታ ኤሌክትሪክ ከማመንጨትም በላይ መሆን አለበት... ይልቁንም ኃይልን ማከማቸት፣ ማሸጋገር (shifting generation)፣ ታዳሽ ኃይሎችን ማመጣጠን (balancing renewables) እና አገልግሎቱ በሚፈለግበት ጊዜ ኤሌክትሪክ ማቅረብ ላይ ማተኮር አለበት... ያን ጊዜ - ግድብ ከግድብም በላይ ይሆናል!!... ____ 📌 (አንባቢ ሆይ - ይህንን ከቱሙት 3፣ ስኖዊ ማውንቴንስ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ስኪም፣ አውስትራሊያ የተወሰደ የምህንድስና ትምህርት በጥልቀት ለመረዳት የሚሹ ከሆነ ተጨማሪ ነጥቦችን እንዲያስሱ እናበረታታዎታለን…) ____ We strive to create a learning organization.
. . . ➡️ A true team is built on: 🟢 Trust — knowing your colleagues will support you when challenges arise. 🟢 Respect — valuing different perspectives, experiences, and skills. 🟢 Communication — speaking openly, listening actively, and addressing issues early. 🟢 Accountability — taking ownership of commitments and results. 🟢 Shared Purpose — understanding that individual success contributes to collective success.
EVERY WORKPLACE HAS DIFFERENT TYPES OF PEOPLE. WHICH ONE ARE YOU? ___ Most of us are very good at identifying the people who frustrate us at work. We know who never pulls their weight, who always complains, who takes credit for other people's work, or who only seems busy when the boss is around. ___ What we rarely do is ask ourselves where we fit into the picture. Every one of us contributes to the culture of the workplace in one way or another. Some people make work easier simply because they are around. They solve problems, support others, and raise the standard. Others make work heavier. They drain the energy of the team, create unnecessary conflict, or leave everyone else carrying their share of the load. Before pointing out the kind of colleagues you work with, take a moment to reflect on the kind of colleague you are. ❓ If your team had to describe you, what would they say? ____ @ethiopoweracademy
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи