tgindex
Ethiopian Public Service University

Ethiopian Public Service University

Статистика

ፐብሊክ አገልግሎት ልህቀት በተግባር ተኮር እውቀት

Последний пост
10 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
7
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Образование
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
12 940
+11 за 3 дн.
Сутки
+3
+0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 421
22 постов
Вовлечённость
26,4%
к подписчикам
Постов в день
1,0
всего 22
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
2 327
1/48двое суток
2 666
1/72трое суток
2 876

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 10 авг.2 772189

    በኢፐሰዩ የአካዳሚክ ሰራተኞች የብቃት ምዘና መስፈርት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪሰ ዩኒቨርሲቲ (ኢፐሰዩ) የአካዳሚክ ሰራተኞች የብቃት ምዘና መስፈርት ላይ ነሀሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በአባይ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ ተሰጠ። የቀረበው የምዘና መስፈርቱም በትምህርት ሚኒስቴር የጸደቀ ሲሆን፣ በመርሀ ግብሩ ላይም የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ሰራተኞች በሙሉ ተሳትፈዋል። የምዘና መስፈርቱን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰ ፣ ዩኒቨርሲቲው ባለፈው የትምህርት ዘመን በርካታና ሰፊ የለውጥ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው፣ ከእነዚህም መካከል የነባር የትምህርት ፕሮግራሞችን መከለስና አዳዲስ ፕሮግራሞችን መቀረፅ ዋና እና በግንባር ቀደምትነት ውጤታማነቱ የተረጋገጠ ስራ መሆኑን አውስተዋል። አያይዘውም የምርምር አቅጣጫና አካሄድን ከተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት አንጻር የሚቃኝ የምርምር ፍኖተ ካርታ፣ እንዲሁም የስልጠናና ማማከር አገልግሎትን በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። በተጨማሪም የአካዳሚክ ሴኔት ሌጅስሌሽን ክለሳና የተቋማዊ ጥራት ስታንዳርድ ሰነዶች ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን እና የአዲሱን የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ አደረጃጀት ማጥራትና የሰው ኃይል ልማትን ማጠናከር፣ የሀብት ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ማደራጀት፣ እንዲሁም ሁሉንም የዩኒቨርሲቲውን አገልግሎቶች በሂደት ዲጂታላይዝ ማድረግና ማዘመን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሥራዎች መከናወናቸውናና በቀጣይነትም እየተሰራባቸው መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በዚሁ የዩኒቨርሲቲውን አዲስ አደረጃጀት ማጥናትና የሰው ኃይል ምዘና ማካሄድን አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንቱ በሰጡት ማብራርያ፣ ለዩኒቨርሲቲው በተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት የተዘጋጀው አዲስ መዋቅር አሁን ላይ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመታየት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ይህ የአደረጃጀት ጥናት እስከ ሰው ኃይል ትመና ድረስ የሚዘልቅ በመሆኑ፣ መምህራንን እና አመራሮችን በመዘን ወደ ሥራ ለማስገባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመዋል። የዚሁ የመምህራን እና አመራሮች የብቃት ምዘና የሕግ መነሻ የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 እና መመሪያ ቁጥር 1152/2011 ናቸው። የምዘናው ዋና ዓላማም የአካዳሚክ ሠራተኞችንና አመራሮችን በሳይንሳዊ መስፈርቶች መዝኖ ስምሪት መስጠት ሲሆን፣ በዚህም ጥራት ያለው ትምህርት፣ ምርምር፣ ሥልጠና፣ የማማከር አገልግሎት እና የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራዎችን ውጤታማነት ማረጋገጥ እንደሆነ ተብራርቷል። የምዘና መስፈርቱ ቴክኒካዊ ብቃት (62 በመቶ) እና ባህሪያዊ ብቃት (38 በመቶ) የተሰኙ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን፣ አጠቃላይ ምዘናውም መምህራን በሚያቀርቡት ፖርትፎሊዮ፣ ሙያዊ አስተዋጽኦ እና ባህሪያዊ ብቃቶች ላይ ተመሥርቶ የሚካሄድ ነው። መመዘኛው እንደየአካዳሚክ ደረጃቸው (ከፕሮፌሰር፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር፣ ረዳት ፕሮፌሰር እስከ ሌክቸረር) የተዘጋጀ ሲሆን በመማር-ማስተማር፣ በሥርዓተ-ትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች ክለሳና ቀረጻ፣ በሥራ አፈጻጸም ግምገማ፣ በሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎች፣ በምርምር ብቃት፣ በማህበረሰብ ጉድኝት፣ እንዲሁም ተቋማዊ አበርክቶና በኮሚቴ ተሳትፎ ዙሪያ የተዋቀሩ ዝርዝር መስፈርቶች ለታዳሚዎቹ ቀርበዋል። በተጨማሪም ባህሪያዊ ብቃቶች እንደየባህሪያቸው በየፈርጃቸው ተከፋፍለው በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፣ ምዘናው ሙሉ በሙሉ የዩኒቨርሲቲውን ዋና ዋና ተልዕኮዎች ታሳቢ ያደረገ፣ እያንዳንዱ አካዳሚክ ሠራተኛ ያለውን መረጃ አቅርቦ የሚመዘንበት እና ከአድልዎና ኢፍትሐዊነት የጸዳ መሆኑ ተብራርቷል። ምዘናው የሚካሄደው ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ባሉ ገለልተኛ አካላት በተዋቀረ ኮሚቴ አማካኝነት ሲሆን፣ በሂደቱ ላይ ሊነሱ የሚችሉ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችል የአቀራረብና የአፈታት ሥርዓትም አብሮ ቀርቧል። በመጨረሻም የቀረበው ሰነድ ለሁሉም የአካዳሚክ ሠራተኞች ተደራሽ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎችም በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰ እና በአካዳሚክ ም/ል ፕሬዚደን ዶ/ር አማኑኤል ኩሲያ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

  • 10 авг.2 6242

    видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.2 6621

    видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.2 6601

    видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.2 5291

    видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.2 5841

    видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.2 48532

    በኢፐሰዩ የአካዳሚክ ሰራተኞች የብቃት ምዘና መስፈርት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ

  • 6 авг.4 5772810

    EPSU Holds Postgraduates Programs External Curricula Validation Workshop Ethiopian Public Service University held Postgraduate Programs External Curricula Validation Workshop on August 5, 2026. University faculty, external reviewers, experts, and other key stakeholders participated in the workshop. In his opening remarks, Dr. Amanuel Kussia , Vice President for Academic Affairs, welcomed the participants and said, "Your presence here today reflects our shared commitment to advancing the quality, relevance, and impact of higher education in Ethiopia. Today's workshop marks an important milestone in our university's journey toward academic excellence. Over the past several weeks, we have witnessed the commitment of our academic staff, experts, and public sector partners in reviewing our existing postgraduate programs. This workshop builds on those collective efforts and reflects our shared commitment to ensuring that every program we offer meets the highest standards of quality, relevance, and excellence." Dr. Amanuel further explained that the workshop is not simply about validating curricula, but about shaping the future capacity of the nation's public institutions. "Let us carefully examine whether these programs respond to national priorities and emerging global trends, equip graduates with the technical and behavioral competencies required in today's workplace, integrate research, innovation, digital transformation, and practical learning, promote ethical leadership, accountability, and public service values, and maintain the balance between academic rigor and professional relevance," Dr. Amanuel noted. Finally, he thanked the curriculum development teams, college leaders, and academic staff for devoting their time and intellectual efforts to reviewing these programs. He also expressed his special appreciation to the external reviewers from sister applied science universities for their devotion, expertise, and professional judgment in reviewing the programs. During the workshop, the Colleges of Urban Development Studies, Finance and Economics, and the School of Law presented their revised curricula, developed by curriculum preparation committees, for evaluation, while the College of Leadership and Governance completed its curriculum validation through a previously scheduled program. Under this initiative, the College of Finance and Economics presented four programs (Accounting and Finance, Public Financial Management, Development Economics, and Tax Policy and Administration); the College of Urban Development Studies presented three programs (Urban Planning and Development, Urban Infrastructure Planning and Development, and Real Property Valuation); the School of Law submitted two programs (Financial Regulation and Law, and International Law); and in its previous program, the College of Leadership and Governance submitted seven master's programs for evaluation (Policy Studies, Diplomacy and International Relations, Public Management, Development Management, Public Service Leadership, Leadership and Management, and Peace and Security). External reviewers from various sister applied sciences universities and key stakeholders delivered their assessments on the revised curriculum documents distributed in advance, and it was noted that the constructive feedback received will serve as valuable input to further refine the developed postgraduate programs.

  • 6 авг.4 095

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.3 462

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.4 161

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.3 360

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.3 325

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.4 049

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.3 900

    EPSU Holds Postgraduates Programs External Curricula Validation Workshop

  • 5 авг.3 91175

    የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በለውጥ ጎዳና https://youtu.be/KlSEpo7iiSg?si=f7pqABArp8jANIWN

  • 5 авг.3 996111

    የኢፐሰዩ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር በ10 ዓመት የስልጠና እና ማማከር አገልግሎት ፍኖተ-ካርታ ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ። የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ (ኢፐሰዩ) ስልጠና ኢንስቲትዩት በ10 ዓመት የስልጠና እና ማማከር ፍኖተ ካርታው ላይ የዩኒቨርሲቲው የካውንስል አባላት፣ የባለድርሻ አካላት፣ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በህዳሴ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አማኑኤል ኩሲያ በመክፈቻው ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ፣ የሀገሪቱን ዘላቂ ልማትና እድገት ለማረጋገጥ ጠንካራና ውጤታማ ፐብሊክ ሴክተር ወሳኝ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችንና ባለሙያዎችን በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ለማብቃት፣ የፐብሊክ ሴክተሩን ችግር የሚፈቱና የሚያዘምኑ የቅድመና የድህረ ምረቃ ስፔሻላይዝድ የትምህርት ፕሮግራሞችን ቀርጾ ከማስተማር በተጨማሪ፣ የተቋማትን ክፍተት በመለየት አጫጭር እና ተከታታይነት ያላቸውን ስልጠናዎች አዘጋጅቶ በመስጠት፣ የመንግስት ሰራተኞችን በአመለካከት በእውቀት እና በክህሎት ለማጎልበት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ አስከትለውም ይህ ፍኖተ ካርታ የዩኒቨርሲቲውን የስልጠናና ማማከር አገልግሎት ከሀገራዊ የሪፎርም ማዕቀፎች እና ከሲቪል ሰርቪስ ሞደርናይዜሽን አጀንዳዎች ጋር ተጣጥሞ ችግር ፈቺ አቅጣጫዎችን እንደሚጠቁም ገልጸው፣ “ፍኖተ ካርታው የዩኒቨርሲቲውን ተወዳዳሪነትና ተቋማዊ ገጽታ በመገንባት፣ በሀገር ዓቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው ፕሮግራሞች፣ በብቁ አሰልጣኞች፣ በዘመናዊ ዲጂታል የስልጠና ሥርዓቶች፣ በምርምር ላይ በተመሰረቱ የማማከር አገልግሎቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚኖረው ጠንካራ ትብብር በሀገር ደረጃና በቀጠናው የፐብሊክ ሰርቪስ ስልጠናና ማማከር የልህቀት ማዕከል እንዲሆን መሠረት ይጥላል የሚል ጽኑ እምነት አለን፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡ በመቀጠልም የተዘጋጀው የፍኖተ ካርታ ሰነድ በዶ/ር አበራ ደምስስ አማካኝነት ለተሳታፊዎቹ በዝርዝር ቀርቧል። በሰነዱ ላይ በተገለጸው መሠረት፤ ፍኖተ ካርታው ዩኒቨርሲቲው ወደ ልዩ የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ያደረገውን ሽግግር፣ የተሰጠውን ልዩ ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶችና ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም ነባራዊውን ሀገራዊ የለውጥ አጀንዳ ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዘጠኝ መሠረታዊ አምዶችን ያካተተ መሆኑም ተመላክቷል። ገለጻውን ተከትሎም ተሳታፊዎቹ ከወከሏቸው ተቋማት ፍላጎትና ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ያላቸውን ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችን እና ምክረ-ሐሳቦችን ሰንዝረዋል። በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ዶ/ር አባይ አከማቸው፣ ዶ/ር ታረቀኝ ደአ እና ዶ/ር አበራ ደምስስ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ የፕሮግራሙ አመቻች የሆኑት ዶ/ር ታረቀኝ ደአ የቀረቡት ምክረ-ሐሳቦች ጠቃሚ ግብዓቶች መሆናቸውን ገልጸው ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት እነዚህን ምክረ-ሐሳቦች በስልጠና ማዕቀፉ ውስጥ ማካተት ተገቢና አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አብራርተዋል።

  • 5 авг.3 7881

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 авг.3 9081

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 авг.3 5731

    видео или голосовое, без подписи