ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
Статистикаአትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ በሀገር ውስጥ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የሚያጠነጥን ፕሮግራም ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት ከ3-4 እና ሰኞ ምሽት ከ12-1 በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሚቀርብ
- Последний пост
- 5 июл. 2025 г.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ አውስትራሊያ በረራ ሊጀምር ነው የኢትዮዽያ አየርመንገድ ወደ አውስትራሊያ መናገሻ ከተማ ሜልበርን መደበኛ የመንገደኛ በረራ አገልግሎት ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደሆነ ታወቀ አየርመንገዱ የሚከፍተው አዲስ የበረራ መስመር አፍሪካን ከአውስትራሊያ በማገናነኘት ለንግድ ቱሪዝም እና አንቬስትመንት ፍሰት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል የበረራ መስመሩ ረዘም ያለ በመሆኑ አየርመንገዱ ኤርባስ ኤ350 ወይም ቢ787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን እንደሚጠቀም ታውቋል የአየርመንጉዱ የስራ ሃላፊዎች ከሜልበርን ኤርፖርት ማኔጅመንት ጋር በመነጋገር የቅድመ ዝግጅት ስራ በማከናወን ላይ ናቸው
የሲቪል አቪየሽን ዋና ዳይሬክተር ከሃላፊነታቸው ለቀቁ የኢትዮዸያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ ከሃላፊነታቸው ለቀቁ አቶ ጌታቸው በባለስልጣኑ በሃላፊነት ባገለገሉበት ሶስት አመት ተኩል የሃገሪቱን የአቪየሽን ኢንዱስትሪ ሪፎርም ፕሮግራም በመንደፍ ሰፊ የፖሊሲ እና ሬጉላቶሪ ስራዎችን እንዳከናወኑ ባልደረቦቻቸው ይመሰክሩላቸዋል ቀደም ሲል አቶ ጌታቸው የትራንፖርት ሚኒስትር ዴኤታ በመቀጠልም በሞንትሪያል ካናዳ በሚገኘው የአለምአቀፍ የሲቪል አቪየሽን ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው አገልግለዋል አቶ ጌታቸው በዳካር ሴኔጋል የሚገኘው የአፍሪካ ሲቪል አቪየሽን ኮምሽን ተዋዳድረው የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ዳይሬክተር አድርጎ እንደቀጠራቸው ለማወቅ ተችሏል በአቶ ጌታቸው ምትክ የሲቪል አቪየሽን የአየር ትራፊክ ማኔጅመንት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዮሃንስ አበራ እንደተሾሙ ታውቋል
без подписи
የስማርት ባህርዳር ፕሮጀክት ትግበራ ሊከናወን ነው የስማርት ባህርዳር ፕሮጀክት ትግበራ ስምምነቱን የተፈራረሙት ደግሞ ኢትዮ ቴሌኮም እና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ናቸው። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው፥ ባህርዳርን በዓለም ተመራጭ የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ከተማ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል። ባህርዳር ከተማ አባቶች በዘመናዊ ፕላን የመሰረቷት በተፈጥሮ የታደለች ናት ያሉት ከንቲባው፤ ይህን ተፈጥሮ በትጉህ የልማት ስራ ከፍ ለማድረግ 22 ኪ.ሜ የኮሪደር ልማት ስራ መጀመሩን አንስተዋል። በስማርት ባህርዳር ፕሮጀክት የተጀመረውን ከተማዋን የማዘመን ስራ በቴክኖሎጂ ለማገዝም የስማርት ሴኪዩሪቲ አገልግሎት የካሜራ ተከላ መጀመሩን ገልፀዋል። ስማርት ሲቲ የአሰራር ሥርዓትን በቴክኖሎጂ በማገዝ ፅንሰ ሀሳብ ላይ ተመስርቶ በሰላምና ደህንነት ስራ፣ በትራፊክ እንቅስቃሴ፣ በትምህርት፣ በቱሪዝም እና በአገልግሎት ዘርፎች አጋዥ ቴክኖሎጂን መታጠቅ እና መጠቀም መሆኑን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አስገንዝበዋል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው፥ ኢትዮ ቴሌኮም ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሲነሳ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና በዓለም ተመራጭ ለማድረግ ስለመሆኑ አንስተዋል። (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ) - በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q - በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6 - በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf - በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8 - በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203 ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
без подписи
без подписи
ኢትዮ ቴሌኮም 5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ በባሕር ዳር ከተማ አስጀመረ ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛውን ትውልድ (5ጂ) ኔትወርክ አገልግሎት በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ባህርዳር ከተማ አስጀምሯል፡፡ በዚህ መሠረት ኩባንያው በባህር ዳር ከተማ እና አካባቢው የሚገኙ የድርጅት እና ግለሰብ ደንበኞች የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ ቴክኖሎጂ ትሩፋት ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ማድረጉ ተገልጿል፡፡ በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። 5ኛው ትውልድ የሞባይል አገልግሎት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂግጂጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር ከተሞች እና አካባቢያቸው ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል፡፡ (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ) - በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q - በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6 - በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf - በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8 - በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203 ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያውያን ስላቀረበው የአክሲዮን ሽያጭ ማወቅ ያሉብን ጉዳዮች ይህ የአክሲዮን ድርሻ ሕብረተሰቡ የኩባንያው ባለቤት እንዲሆን ታስቦ የተከፈተ ነው፡፡ የአክሲዮን ሽያጩ ሁለት ዙር ይኖረዋል፤ የመጀመሪያው ዙር ከትላንት ጀምር ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡ ስለመጀመሪያው ዙር የመደበኛ አክሲዮን ሽያጭ ማወቅ ያሉብን ጉዳዮች፦ • የአንድ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር ነው፤ • ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው 33 አክሲዮን ሲሆን፣ ጠቅላላ ዋጋው 9 ሺህ 900 ብር ነው፤ • ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው 3 ሺህ 333 አክሲዮን ሲሆን ጠቅላላ ዋጋው 999 ሺህ 900 ብር ነው፤ • ግብይቱ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው፤ • የአክሲዮን ግዢ የሚከናወነው በቴሌ ብር ሲሆን፣ ክፍያው የሚጠናቀቀው በ48 ሰዓታት ውስጥ ነው፤ • የአክሲዮን ሽያጩ የሚቆየው ከጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ነው፤ • አዳዲሶቹ የአክሲዮን ባለቤቶች የሚታወቁት ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም፤ • አክሲዮን ገዢዎች ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፤ • ከዝቅተኛው የአክሲዮን መጠን በታችም ሆነ፣ ከፍተኛው የአክሲዮን መጠን በላይ መግዛት አይቻልም፤ (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ) - በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q - በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6 - በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf - በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8 - በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203 ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
без подписи
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ አደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያውያን ክፍት የተረደረገውን የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል። ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ ያለው 100 ቢሊየን አክሲዮን ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 10 በመቶውን አክሲዮን ነው በዛሬው ዕለት ለሽያጭ ይፋ የሆነው፡፡ የእያንዳንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚሁ መሠረት አንድ ሰው ከ33 አክሲዮን ጀምሮ እስከ 9 ሺህ 900 አክሲዮን ድረስ መግዛት የሚችል ሲሆን÷ ይህም በብር ሲገለጽ ከ3 ሺህ 333 ብር እስከ 999 ሺህ 900 ብር ይደርሳል ማለት ነው፡፡ (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ) - በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q - በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6 - በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf - በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8 - በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203 ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ828 ቢሊዮን ብር በላይ ዝውውር መፈጸሙ ተገለፀ ከዘመን መለወጫ ጀምሮ በነበሩት በዓላት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከ828 ቢሊዮን ብር በላይ ዝውውር መፈጸሙ ተገለፀ። ከነሐሴ 30 እስከ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም በነበረው ጊዜ ውስጥ በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች በተከናወኑ ከ145 ሚሊዮን በላይ ግብይቶች የብር 828,549,614,770 ዝውወር ተፈፅሟል። በወቅቱ በባንኩ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከተፈፀመው ግብይት ውስጥ 84 በመቶ ያህሉ በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት የተከናወነ ሲሆን፣ ይህም በገንዘብ ከ696.5 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ) - በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q - በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6 - በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf - በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8 - በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203 ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከ2 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳሰበ አዲስ የምንዛሪ ተመን አሰራር ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በውጭ ምንዛሪ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን የገለፀው ብሔራዊ ባንኩ፤ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል። አሁንም ቢሆን ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን ገበያ መር በሆነ መንገድ መተመናቸውን እና ይህንኑ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ብሔራዊ ባንኩ በመግለጫው ጠቁሟል። እስካሁን በነበረው አሰራር ንግድ ባንኮች ከውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቁትን ኮሚሽን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር ጠቅሶ፤ ወደፊት ግን ኮሚሽኑን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁ አዝዟል። (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ) - በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q - በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6 - በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf - በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8 - በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203 ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
ሜታ- ፌስቡክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የደንበኞች ተሞክሮ የሚያሻሽል (flagship) ፕሮግራም ተግባራዊ ሊያደርግ ነው የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ከሜታ-ፌስቡክ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ የንግድ ልማት እና ስትራቴጂክ አጋርነት ዳይሬክተር ቪካስ ሜኖን እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የደንበኞችን የዲጂታል ተሞክሮ ለማሻሻል በሚረዱ ጉዳዮች ላይ ስትራቴጂያዊ ውይይት አድርገዋል ። ሜታ-ፌስቡክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የደንበኞችን ዳታ አጠቃቀም የሚያሻሻል (flagship) ፕሮግራም በኢትዮጵያ ለመጀመር መወሰኑን ያስታወቀ ሲሆን ይህም ከኩባንያው ጋር ያለውን ትብብር ወደላቀ ደረጃ እንደሚያያርስ ገልጿል። ማዕቀፉ ደንበኞች አካውንታቸው ውስጥ ሂሳብ ባይኖርም የሜታ-ፌስቡክ አገልግሎቶችን ለተወሰነ ጊዜ በነጻ በመጠቀም ግንኙነታቸውን እንዲያስቀጥሉ ከማስቻል ባሻገር እንደ ጤና፣ ትምህርት እና የስራ እድሎች የመሳሰሉ ጠቃሚ መረጃዎችን ከክፍያ ነጻ በማቅረብ በመረጃ የበለጸገ ንቁ ዜጋ ለመፍጠር ያስችላል፡፡ የዲጂታል ሊትሬሲን እና አካታችነትን ማሳደግ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን የገለፁት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ሀገራዊ የይዘት ፈጠራ እንዲጎለብት ማድረግ እና የዲጂታል ስነምህዳሩን የሚያሻሽሉ ፋይዳ ያላቸው ፕሮግራሞችን መተግበር እንዲሁም የሳይበር ደህንነት እና መረጃ አያያዝን በጋራ አስተማማኝ ስለማድረግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ የስምምነቱ ትግበራ የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትን እና አካታችነትን በመጨመር የሀገሪቱን ዲጂታል ሊትሬሲ በማሳደግ እንዲሁም ለደንበኞች የላቀ ተሞክሮ በማምጣት ለሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እድገት የላቀ ሚና ይጫወታል ተብሏል ፡፡ (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ) - በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q - በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6 - በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf - በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8 - በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203 ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
без подписи
без подписи
ዳሸን ባንክ 6.4 ቢሊየን ብር ትርፍ አስመዘገበ ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት ብር 6.4 ቢሊየን ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ፡፡ የባንኩ ባለአክሲዮኖች 31ኛ መደበኛና 26ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በሚሊንየም አዳራሽ ዛሬ የተካሄደ ሲሆን ያለፈው ዓመት የባንኩ የስራ አፈፃፀም፣ የዚህ በጀት ዓመት እቅድና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ባለፈው በጀት ዓመት በባንክ ኢንዱስትሪው አውንታዊና አሉታዊ ሁኔታዎችን የፈጠሩ አለም አቀፋዊና አገራዊ ክስተቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ አገራት የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል ያወጧቸው ጥብቅ ፖሊሲዎች፣ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት፣ እንዲሁም በቀይ ባህር አካባቢ የሚፈፀመው ጥቃት በአለም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያሳደሯቸውን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለአብነት አንስተዋል፡፡አቶ ዱላ ባለፈው በጀት አመት በኢትዮጵያ የነበረው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ በተለያዩ ቦታዎች የቀጠሉ ግጭቶችና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እጥረት በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ የበኩሉን አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አስገንዝበዋል፡፡ የበጀት ዓመቱ ሲጀምር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ጥብቅ የገንዘብ ፓሊሲ ይፋ ማድረጉንም አስታውሰዋል፡፡ እነዚህና ሌሎች የፖሊሲ ለውጦች ባንኮች በሚያቀርቡት የብድር መጠንና ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውንም አመልክተዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የባንክ ኢንዱስትሪው የገንዘብና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ውስጥ የነበረ ቢሆንም ዳሸን ባንክ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ የደንበኞቹን ፍላጎት ለሟሟላት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮ-ቴሌኮም በተሌብር በኩል እንዲሁም ሳፋሪኮም በኤምፔሳ አማካኝነት በሞባይል ባንክ አገልግሎት ዘርፍ ከፍተኛ ፉክክር እንዲፈጠር ያደረጉበት አመት መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የዳሸን ባንክ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን የ30.9 ቢሊየን ብር እድገት ማስመዝገቡንና የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 145.9 ቢሊየን ብር መድረሱን አቶ ዱላ አውስተዋል፡፡ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ለባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ያበረክተው ድርሻ 11.1 ቢሊየን ብር እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው ያለፈው ዓመት ምንም እንኳን የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ባንኩ ይህን ተቋቁሞ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡ የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ሃብት ባለፈው በጀት ዓመት የ27 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ብር 183.7 ቢሊየን መደረሱን ገልፀዋል፡፡ ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 1.44 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘት እንደቻለና ይህም ለባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡ ባንኩ በአሁኑ ወቅት ከ6.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉትም ተመልክቷል፡፡ ዳሸን ባንክ ከተለያዩ አገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት መቀጠሉን ያመለከቱት አቶ አስፋው ከኤግልላየን ሲስተምስ ቴክኖሎጂ ጋር የተፈራረመው ስትራቴጂክ ስምምነት አዳዲስ ዲጂታል አገልግሎቶችን ይበልጥ ለደንበኞቹ ለማቅረብ እንደሚያስችለው አስገንዝበዋል፡፡ ባንኩ ከብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት እና ከኔዘርላንድ የልማት ባንክ ጋር የፈጠረው አጋርነት የ40 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲያገኝ ያስቻለው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ዳሸን ባንክ በበጀት አመቱ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የ40 ሚሊየን ዶላር የንግድ ልውውጥ ዋስትና ፈንድ ማግኘቱንም አቶ አስፋው አመልክተዋል፡፡ ዳሸን ባንክ ማህበራዊና አካባቢያዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን የገለፁት አቶ አስፋው ከዚህ አኳያ ባለፈው በጀት ዓመት የአካባቢ ማህበራዊና አስተዳደር (Environment, Social and Governance) ፓሊሲ በማዘጋጀትና ቢሮ በማቋቋም መስራት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት የተለያዩ ሽልማቶችን ከተለያዩ አህጉራዊና አለምአቀፍ ተቋማት ተቀብሏል፡፡ ባንኩ በእንግሊዝ በሚታተመው ዘባንከር መፅሄት በኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ ባንክ ተብሎ የተሸለመ ሲሆን የዓለም ባንክ አካል ከሆነው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የላቀ ዓለም አቀፍ የንግድ ፋይናንስ አገልግሎት በሚሰጡ ባንኮች ዘርፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዳሸን ባንክ ለአነስተኛ ተቋማት ብድር በማቅረብ ዘርፍ ቀዳሚ ባንክ በመሆን ከ“አፍሪካ ባንክ 4.0 ጉባኤ” ሽልማት ተቀብሏል፡፡ (ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ) - በቴሌግራም :- https://bit.ly/3jHql5q - በፌስቡክ ፡- https://bit.ly/3jIjJ6 - በትዊተር ፡- https://bit.ly/37MJGzf - በዌብሳይት :- https://bit.ly/3KOpzz8 - በዩትዩብ፦https://youtube.com/@originsbusiness2203 ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑን እናመሰግናለን
የፐርፐዝ ብላክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ 10 ግለሰቦች በማታለል ሙስና ወንጀል ተከሰሱ #Ethiopia | የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ በ10 ግለሰቦች እና ሁለት ድርጅቶች ላይ ክስ መስርቷል። ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። ተከሳሾቹ 1ኛ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱ (ዶ/ር)፣2ኛ የተቋሙ ም/ስራ አስፈጻሚ ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር)፣ 3ኛ የተቋሙ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና የቦርድ አባል ወ/ሮ ኤፍራታን ነጋሽን ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ግለሰቦች እንዲሁም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ እና ኖትር ዲዛይን ሃ/የተ/የግ/ማህበር ናቸው፡፡ ተከሳሾቹ በአዲስ አበባ ከተማ መሃል ሜክሲኮ ላይ በ100 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ባለ 3 መኝታ ቤት መኖሪያ ቤት በ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ በማስተዋወቅ ሰዎች ቤት ለመግዛት ሲሄዱ "መጀመሪያ ገንዘቡን አስገቡና ውሉን ትመለከታላችሁ "በማለት ከሌሎች ግብረዓበሮቻቸው ጋር በመሆን አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀም፣ ሰዎች ገንዘቡን ካስገቡ በኋላ ደግሞ የአክሲዮን ግዢ ውል እንዲፈርሙ በማድረግ ምንም አይነት የግንባታ ቦታ ባልተረከቡበት ሁኔታ 2 ቢሊየን 234 ሚሊየን 200 ሺህ ብር በመሰብሰብ፣ ቤቱን ሰርተው ሳያስረክቡ በመቅረት እንዲሁም ግማሹን ገንዘብ ወደ ውጭ እንዲሸሽ በማድረግ፣ ኮሚሽን በመቀበልና በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ሲከናወን እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። በዚህ መልኩ ፖሊስ ሲያከናውነው የቆየው የምርመራ ማጣሪያ ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ዝርዝር ክሶችን በየደረጃቸው አቅርቦባቸዋል። ከቀረቡ ክሶች መካከል በአንደኛው ክስ ላይ ከ1ኛ-9ኛ ባሉ ተከሳሾች ላይ እንደተመላከተው፤ በኢፌዲሪ የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና (ለ) እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32 (2) ላይ የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል ክስ ይገኝበታል። እንደ አጠቃላይ በቀረበው ተደራራቢ ክስ ዝርዝር ችሎት ለቀረቡ 4 ተከሳሾች ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን ÷የተከሳሾቹ ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበውን ክስ ዝርዝር ተመልክተው ዋስትና ላይ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ዋስትና ላይ የሚደረገውን የግራ ቀኝ ክርክር ለመከታተል ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ተዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾችን ፖሊስ በአድራሻቸው አፈላልጎ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በታሪክ አዱኛ
без подписи
ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻውን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሊሸጥ ነው * * * * * ግዙፉና መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻዉን ለህዝብ መሸጥ እንደሚጀምር ተሰምቷል ። በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ የነበረዉን የቴሌኮም ዘርፍ ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ለግል ባለሃብት በይፋ መሸጥ እንደሚጀምር ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ። ምንጭ : - ካፒታል
без подписи