tgindex
EAS
@EthioaddissportEASанглийский

Welcome to #EAS - "The home of Football funny videos & Pictures" Enjoy ! Ethioaddis Sport(#EAS) በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ የሚቀርብ የስፖርት ፕሮግራም ሲሆን ዘወትር አርብ ምሽት ከ 3:00 - 5:00 እና እሁድ ከሰአት ከ 6፡00-7፡00 የሚደመጥ ነው።ለማንኛውም አስተያየትዎ 0983848811 ይጠቀሙ።

Последний пост
16 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
209
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 471
−7 за 5 дн.
Сутки
−4
−0,12%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
621
40 постов
Вовлечённость
17,9%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 209
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
194
1/48двое суток
222
1/72трое суток
239

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • #EAS 389 በፕሪምየርሊጉ አርሰናልን የሚፎካከር ይኖራል? የቻዊንጋ እህትማማቾች ዕለተ እሁድ ነሀሴ 10/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ ይጠብቁን። የአውሮፓ የሊግ ውድድሮች እየተጀመሩ ነው።በላሊጋው የመጀመሪያዎቹ ሁለት የመክፈቻ ጨዋታዎች ሁለት ቀይ ካርዶች የታዩበት ነበር። የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግን ጨምሮ ሌሎች ሊጎች በቀጣዮቹ ሳምንታት ይጀመራሉ። በፕሪምየርሊጉ ሻምፕዮኑ አርሰናል ዋንጫውን ደግሞ የማግኘት እድል እንዳለው በስፋት እየተደመጠ ይገኛል። ከዋንጫ አሸናፊነት የሚያቆመው ቡድን ይኖራል?ከሆነ እነማን? የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ በሞሮኮ ይከናወናል። ካሜሮን እና ማላዊ ይፋጠጣሉ የማላዊ ብሔራዊ ቡድን ጎትተው ለፍፃሜ ያበቁት ደግሞ የቻዊንጋ እህትማማቾች ናቸው። ክለቦች የአቋም  መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ 👉 ማን ዩናይትድ 2-4 ኤሲሚላን 👉 ቼልሲ 3-1 ሶሴዳድ 🔥 ሞርጋን ሮጀርስ ጎል አስቆጥሯል በነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 388 አራሆ ወደ ሊቨርፑል ምርጥ ዝውውር ወይስ ስጋት? ዕለተ እሁድ ነሀሴ 03/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ ይጠብቁን። ሊቨርፑል በዝውውር መስኮቱ ላይ እስከ አሁን ድረስ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገ አይገኝም። ታላቁ ተጨዋቻቸው ሞ ሳላህ ከለቀቀ በኋላ ቦታው በጠንካራ ተጨዋች አልተተካም። በሌሎች ቦታዎችም እንዲሁ ክፍተቶች ቢኖሩም የስካሁኑ ዝውውር ቡድኑን ከፍ ያደረጉ አይመስሉም። አሁን ደግሞ አራሆ ወደ ክለቡ በውሰት ውል መቀላቀሉ ተሰምቷል።ተጨዋቹ ወደ ሊቨርፑል መዛወሩ ጥሩ ዝውውር ወይስ ስጋት? የሊግ ውድድሮች ሊጀመሩ ጥቂት ቀናቶች ቀርተውታል።ክለቦችም የአቋም  መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ 👉 ማን ዩናይትድ 1-1 ፒ ኤስ ጂ የአዳዲስ የማን ዩናይትድ ፈራሚዎች ጅማሮ እንዴት አያችሁት? 👉 ቼልሲ 3-0 ኤሲ ሚላን ጂዮቫኒ ኩዌንዳ በቀኝ መስመር ላይ ዊሊያን እስቲቫኦን መፎካካር አይችልም? ዛሬ አርሰናል ከ ዶርትሙንድ ሲቲ ከ አትሌቲኮ ሊቨርፑል ከ ሞናኮ በነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS  387 የተረሱት መሠረት ጣዮች The Underrated Pioneers ኢትዮ-አዲስ ስፖርት የነሐሴ 1/2018 የዕለተ-አርብ የእኛና የእናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። እግር ኳስ በየዘመናቱ ቀጥሎ ሊመጣ ላለው ነገር ፈር የቀደዱ አልያም መሠረት የጣሉ ኃያሌ ባለሙያዎችን አሳይታናለች። እነዚህ ፈር ቀዳጆች በተለያየ ኃላፊነት ላይ ሆነው ማገልገል የቻሉ ሲሆን ከነዚህ መካከል አሰልጣኞችም ይገኙበታል። ሆኖም እነዚህ ታሪክ ሰሪዎች በተገቢው መጠን አድናቆትና ምስጋና ሲሰጣቸው የማንመለከትበት ጊዜ ይኖራል። የዚህ ሰለባ ከሆኑ ታላላቅ አሰልጣኞች መካከል ሁለቱን በዛሬው መሰናዶአችን እንዳስሳለን። ታላላቆቹ የአውሮፓ ሊጎች ሊመለሱ እጅጉን ተቃርበዋል። ይህንን ተከትሎ ክለቦች የመጨረሻ ደረጃ ዝግጅታቸውን በሜዳም ሆነ ከሜዳ ውጪ እያደረጉ ይገኛሉ። በሜዳ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች ከሜዳ ውጪ ደግሞ ዝውውሮች! ነገ በአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች ✅ማንችስተር ዩናይትድ ከፒ ኤስ ጂ ✅ቼልሲ ከኤሲ ሚላን ✅ኢንተር ሚላን ከጁቬንቱስ ሲጫወቱ እሑድ ደግሞ ✅አርሰናል ከዶርትሙንድ ✅ሲቲ ከአትሌቲኮ ✅ሊቨርፑል ከሞናኮ ይፋለማሉ። የዝውውር መስኮቱም ያልጠበቅናቸውን ዝውውሮች ጨምሮ አስደምሞናል። ሮድሪ ወደባርሳ የማቅናቱን ነገር እንዴት አያችሁት? በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳባችሁን አጋሩን። #EAS-የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 386 ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ! የአካል ብቃት፣ጤናማ አመጋገብ፣በቂ እረፍት .. ዕለተ እሁድ ሀምሌ 26/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። የዛሬ ቆይታችን ከተጋባዥ እንግዶች ጋር ይሆናል።ልምዳቸውን ያካፍሉናል። ስለ ጤናማ የኑሮ ልምምዶች፣አመጋገብ እና የአካል ብቃትን ጨምሮ በሌሎች ሀሳቦች ላይ ቆይታ ይኖረናል። የሊግ ውድድሮች ሊጀመሩ ጥቂት ሳምንታት ቀርተውታል።ክለቦችም የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛሉ። 👉 ቶተንሀም 2-1 ቼልሲ 👉 አርሰናል 4-1 ጂሮና 👉 ማን ዩናይትድ 2-1 አትሌቲኮ ማድሪድ 👉 ኖርጋርድ ወደ ኤቨርተን ለመዘዋወር ተስማምቷል።ይህም የጉማሬሽ ወደ አርሰናል የሚያደርገው ዝውውር ይበልጥ መቃረቡን የሚያመለክት አይሆንም? የዛሬ ጭምጭምታዎች 👉 ማን ዩናይትድ ማይልስ ልዊስ ስኬሊን ለማዘዋወር ሁኔታዎችን እያጤነ ነው። 👉 ሲቲ ፔድሮ ኔቶ ላይ አይኑን ጥሏል። በነዚህ እና በሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 385 Delap's Dramatic Drop (3D) ኢትዮ-አዲስ ስፖርት በዕለተ አርብ ሐምሌ 24/2018 የእኛና የእናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 አየር ላይ ትውላለች። በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ካሉ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች አንዱ ቼልሲ ነው። ሰማያዊዎቹ በተለያዩ ስፍራዎች ራሳቸውን እያጠናከሩ ሲገኙ የአጥቂ መስመራቸውም ከተጠናከሩ ቦታዎቻቸው መካከል ይጠቀሳል። አንጋፋው ዳኒ ዌልቤክ የቡድኑ አዲስ ፈራሚ ሲሆን ኒኮላስ ጃክሰንን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾችም በዚሁ ስፍራ የሚገኙ አማራጮች ናቸው። በዚህ ሁሉ መካከል ሊያም ዴላፕ ተረስቷል። ከአንድ አመት በፊት እንደእንግሊዝ እግር ኳስ ተስፋ ይታይ የነበረው ዴላፕ አሁን የሚገኝበት ሁኔታና የነገሮች መገላበጥ አሳዛኝ ነው። በዛሬው መሰናዶአችን በዋናነት በዚህ ዙሪያ እናደርጋለን። ✅የተጫዋቾች ዝውውር ጉዳይ የወቅቱ ትልቅ ርዕስ ነው።ሆኖም ሰሞኑን ገበያው ትንሽ ቀዝቀዝ ያለ ይመስላል። ምክንያቱ ምን ይመስላችኋል? ✅ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርና ፊፋ ተፋጥጠዋል። ምክንያቱ ደግሞ "የዓለም ዋንጫ ለገበያ የሚቀርብ ሸቀጥ አይደለም!" የሚል ነው። የUEFA ሀሳብ ትክክል አይመስላችሁም? ✅የሊግ ውድድሮች ለመጀመር ተቃርበዋል።ምን ያህል ጉጉት አድሮባችኋል? በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ሀሳባችሁን እያጋራችሁ ጠብቁን። #EAS- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 384 የዝውውር ዝምታ በሊቨርፑል ዕለተ እሁድ ሀምሌ 19/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። የአውሮፓ የ 2026/2027 የሊግ ውድድሮች ሊጀመሩ አንድ ወር ብቻ ቀርቶታል። ክለቦችም የቅድመ ውድድር ጊዜያቸውን በልምምድ፣በአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች እንዲሁም ክፍተቶቻቸውን ለመድፈን በዝውውሩ እየተሳተፉ ይገኛሉ። የእንግሊዙ ሊቨርፑል ግን እስከ አሁን ድረስ በንቃት ተሳትፎ እያደረገ አይገኝም። ምንም እንኳን የዝውውር መስኮቱ ክፍት ቢሆንም የሊጉ ጅማሮ መቃረብ ተከትሎ ክለቡ በዝውውር ላይ መቀዛቀዙ ደጋፊዎችን አሳስቧል። ሊቨርፑል ለምን ዝምታን መረጠ? 👉 ፔዤ ተጠባባቂ ተጨዋቾቹን ለሌሎች ክለቦች ማከፋፈሉን ቀጥሏል።ጎንካሎ ራሞስ ወደ ሚላን፣ ካንግ ኢን ሊ ወደ አትሌቲኮ ተቀላቅለዋል። 👉 ቪኒ፣አልቫሬዝ እና ጉማሬሽ ከ አርሰናል ጋር ስማቸው የተነሱ ተጨዋቾች ናቸው።መድፈኞቹ ማንን ማስፈረም ይችላሉ? 👉 ፓልመር፣ጇ ፔድሮ፣ሞርጋን ሮጀርስ፣ስቲቫኦ፣ፔድሮ ኔቶ እና ሌሎች።ቼልሲ ጠንካራ የአጥቂ ስብስብ ያለው ቡድን ነው ማለት እንችላለን? በነዚህ እና በሌሎች ጉዳዮችን ጨምራችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 383 የርገን ክሎፕ- አዲሱ የጀርመን አለቃ ኢትዮ-አዲስ ስፖርት በዕለተ አርብ ሐምሌ 17/2018 የእኛና የእናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 አየር ላይ ትውላለች። በዓለም ዋንጫው አሳፋሪ ቆይታ የነበራት ታላቋ የእግር ኳስ ሀገር  ጀርመን ከገባችበት የውጤት ማጣት አዘቅት ያወጣኛል ብላ ያሰበችውን ባለግርማ ሞገስ የርገን ክሎፕ ዛሬ በይፋ ቀጥራለች። በሊቨርፑልና በዶርትሙንድ በሰሩት ተአምር ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ክሎፕም ስራውን ለመቀበል ሳያንገራግሩ ለ 2030 የዓለም ዋንጫ የታለመውን ፕሮጀክት ተቀብለዋል። በዛሬው መሰናዶአችን በዋናነት በዚህ ዙሪያ እናደርጋለን። ከአለም ዋንጫው መጠናቀቅ መልስ የተጫዋቾች ዝውውር ጉዳይ ተፋፍሟል። ✅ አርሰናል ብሩኖ ጊማሬሽን ማስፈረሙ የሚቀር አይመስልም። ✅ቼልሲ ላክሮአን ከፓላስ መንትፏል። ✅ሲቲ ወጣቱ አዩብ ቡአዲ ላይ አይኑን ጥሏል። ✅የዘንድሮው ዩናይትድ ድምፁን አጥፍቶ እየሰራ ነው። ✅ሊቨርፑል እስካሁን ሳላህን አልተካም። የዝውውር ገበያውን እንዴት እያያችሁት ነው? በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ሀሳባችሁን እያጋራችሁ ጠብቁን። #EAS- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 382 ቆይታ ከ ተጋባዥ እንግዳ ጋር ዕለተ እሁድ ሀምሌ 12/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። የአለም ዋንጫ ፍፃሜ ዛሬ ምሽት ይከናወናል።አርጀንቲና እና ስፔን ለሌላ ክብር ፊትለፊት ይፋጠጣሉ። የልዊስ ዴላ ፎንቴ እንደ ቡድን የሚንቀሳቀሰው ስፔን ጠንካራ አልሸነፍ ባይነትን መገለጫው ካደረገው አርጀንቲና የሮድሪ እና ጓደኞቹ የኳስ ፍሰት ከ ፓራዴዝ እና ጓደኞቹ የሜዳ ላይ ተጋዳይነት አይን ውስጥ የሚገቡት ሜሲ እና ያማል? ከወር በላይ ቆይታ በነበረው የ 48 ሀገራት ውድድር ዛሬ ከሁለቱ አንዱ በአሸናፊነት ይሞሸራሉ።አርጀንቲና ወይስ ስፔን? እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በጋራ 10 ጎሎችን አስቆጥረው ደረጃቸውን ለይተው ወጥተዋል። ኪሊያን ሁለት ጎሎች አስቆጥሮ ከሜሲ ፊት ተቀምጧል።አሁን የምንግዜው የአለም ዋንጫው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እርሱ ነው። ዛሬ ቆይታ የምናደርገው ከእንግዳ ጋር ይሆናል። ማን አሸናፊ ይሆናል? ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 381 የአድማጮች ቀን በዓለም ዋንጫው ዙሪያ ኢትዮአዲስ ስፖርት በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 የአርብ ምሽት መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 አየር ላይ ይቆያል። ከረጅም ሳምንታት ቆይታ በኋላ EAS በዕለተ አርብ የእኛና የእናንተ መሰናዶ ተመልሷል። በአለም ዋንጫ ጅማሮ ምክንያት ሳይተላለፍ የቆየው ፕሮግራማችን ሲመለስ የዓለም ዋንጫው የፍፃሜው ጨዋታ ላይ ደርሶ ነው። እሑድ ምሽት በኒውዮርክ ሜትላይፍ ስታዲየም የአውሮፓ ሻምፒዮኗ ስፔን ከዓለም ሻምፒዮኗ አርጀንቲና ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ፍፃሜውን ያገኛል? ዛሬ ለአድማጮች አብዛኛውን ክፍለ ጊዜ የምንሰጥበት ቀን ነው። ✅የዓለም ዋንጫውን እንዴት አያችሁት? ✅ግምታችሁ ምን ያህል ስኬታማ ነበር? ✅ማን ሻምፒዮን ይሆናል? ✅የትኛው ቡድን አስገረማችሁ? ✅የትኛው ቡድን ከጠበቃችሁት በታች አቋም አሳየ? ሀሳባችሁን አጋሩን። #EAS- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 380 ጊልቤርቶ ሞራ .. አሌሀንድሮ ጋርናቾ .. ዕለተ እሁድ ሀምሌ 05/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። የአለም ዋንጫው ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሻገሩን ተከትሎ በአለም ዋንጫ የተመረጡ ጉዳዮች ላይ እና የጋርናቾ ከቼልሲ ለመልቀቅ መቃረብ የዛሬ ጉዳያችን ነው። እንደ አርጀንቲና እያንዳንዱ የጥሎማለፍ ጨዋታዎች የተፈተነ ቡድን የለም ማለት ይቻላል። አነጋጉ ላይም በስዊዘርላንድ ተፈትኖ መጨረሻ ላይ ግን አሸንፈው ወጥተዋል።አርጀንቲናዊያን ተፋልመው ማሸነፍን ለምደውበታል። ቀጣይ ከ እንግሊዝ በውድድሩ ሁሉም የሚስማማበት የፈረንሳይ ያልዋዥቀ አቋም ነው።በመንገዱ ያሉትን እየሰባበረ ግማሽ ፍፃሜ ተገኝቷል። ቀጣይ - ባለፈው የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ካሸነፈቻት ስፔን ማን ለፍፃሜ ይበቃል? በአለም ዋንጫው ያየነው ወጣቱ የሜክሲኮው ጊሊቤርቶ ሲልቫ ላይ ታላላቅ ክለቦች አይናቸውን ጥለዋል። ጋርናቾ ከቼልሲ ውጪ ብሎ ማንችስተር ዩናይትድን ለቆ ሰመያዊዎቹን በተቀላቀለ በአንድ አመቱ ክለቡን ሊለቅ ነው። ወጣቱ ባለ ተስፈኛ የእድገት ጉዞው እያሽቆለቆለ ይመስላል። 👉 ጁድ ቤልንግሀም 6ኛ የአለም ዋንጫ ጎሉን አስቆጥሯል 👉 የኢምቦሎ አሳፋሪ ዳይቭ 👉 የአልቫሬዝ ድንቅ ጎል ሀሳባችሁን ኮሜንት ሳጥን ውስጥ አካፍሉን? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 379 የአለም ዋንጫ ጉዳዮች .. ዕለተ እሁድ ሰኔ 28/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። የአለም ዋንጫው ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሻገሩን ተከትሎ በአለም ዋንጫ የተመረጡ ጉዳዮች ላይ ዛሬም ቆይታ እናደርጋለን። ወደ ሩብ ፍፃሜ ለማለፍ የሚደረጉ ጨዋታዎች ተሟሙቀው ቀጥለዋል።ሞሮኮ እና ፈረንሳይ ከ 8ቱ ሀገራት ውስጥ ሁለቱ ሆነዋል። ቀጣይ ደግሞ እርስበርስ ይፋለማሉ። ፈረንሳይ ከ ሞሮኮ አንዷ አዘጋጅ ሀገር ካናዳ ወድቃለች።ለአሰልጣኙ ጄሺ ማርሽ ግን የተሻለው ቡድናቸው እንደነበር ያምናሉ። የቡድናቸው ኮከብ ጆናታን ዴቪስ በጁቬንቱስ በየሳምንቱ አለመጫወቱ እንደጎዳው እየተደመጠ ይገኛል። ለናንተ 👉 እንደተጠበቀው ያላገኛችሁት ወይንም ከተጠበቀው በላይ ያገኛችሁት ሀገር ማነው? 👉 የኮከብ ጎል አስቆጣሪ አሸናፊስ ማን ሆኖ ያጠናቅቃል? 👉 ሞሮኮ ፈረንሳይን ማሸነፍ ትችላለች?ከሆነ ለዋንጫ ትጠበቅ? 👉 የሜክሲኮ በሜዳዋ ጠንካራ መሆን ለእንግሊዝ ፈተና ይሆናል? 👉 ያልተወራላት ድምጿን ያጠፋችው ኮሎምቢያስ? ሌሎች ትዝብታችሁን ጨምራችሁ በኮሜንት ሳጥን ውስጥ ሀሳባችሁን አካፍሉን? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 378 የአለም ዋንጫ ጉዳዮች .. ዕለተ እሁድ ሰኔ 21/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። የአለም ዋንጫው የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀው ወደ ጥሎማለፉ የተሻገሩ ሀገራት ተለይተዋል። 32 ሀገራት ተጋጣያቸውን አውቀዋል።ብዙዎቹ ታላላቅ ሀገራት ቀለል ያለ የሚመስል ተጋጣሚ ደርሷቸዋል። ኔዘርላንድ ከ ሞሮኮ ጋር የሚያደርጉት ፍጥጫ በትልቅነት የሚነሳ ነው። ብራዚል ከ ጃፓንም ሳይዘነጋ እኛም በተመረጡ የአለም ዋንጫ ጉዳዮች ላይ ቆይታ ይኖረናል የለሊቱ አበይት ጉዳዮች እንዴት ነበሩ? 👉 የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በተሰጥኦ የተሞላ ነገርግን ዋንጫ ለማንሳት ብዙ ስራ የሚፈልግ መሆኑ 👉 ሜሲ በ 3 ጨዋታ 6ኛ ጎሉ 👉 ዊሳ የኮንጎ አዳኝ .. 👉 የኦስትሪያ እና አልጄሪያ የመጨረሻ ደቂቃ ድራማዎች እናንተስ ምን ታዘባችሁ? በኮሜንት ሳጥን ሀሳባችሁን አካፍሉን? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 377 ተስፋ ሰንቀው ነገር ግን ..? ቱርክ፣ኢኳዶር እና ቱኒዚያ ዕለተ እሁድ ሰኔ 14/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። የአለም ዋንጫው ያልተጠበቁ ክስተቶችን እያሳየን ይገኛል።ትናንሾቹ ታላላቆችን እየፈተኑ። ኬፕ ቨርድ ስፔንን ሳውዲ ኡሩጓይን ኳታር ስዊዘርላንድን ኩራሳኦ ኢኳዶርን የሚጠቀሱ ናቸው። ስማቸው ከፍ ብሎ ተስፋ ሰንቀው ነገርግን አለም ዋንጫው ቅዠት የሆነባቸው ደግሞ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ ተርኪ፣ኢኳዶር እና ቱኒዚያ ይጠቀሳሉ። በነዚህ ቡድኖች ላይ ቆይታ ይኖረናል። እናንተስ አለም ዋንጫው እንዴት አገኛችሁት? 👉 ትናንት አይቮሪኮስት በሚያስቆጭ መልኩ በጀርመን ተሸንፋለች። 👉 ኩራሳኦ ኢኳዶርን ነጥብ አስጥላለች 👉 ጃፓን ቱኒዚያ ላይ 4 አስቆጥራለች 👉 ኔዘርላንድ ቀለል ተደርጋ የምትታይ ቡድን እንዳልሆነች አሳይታለች እናንተስ ምን ታዘባችሁ? በኮሜንት ሳጥን ሀሳባችሁን አካፍሉን? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 376 የኤሺያው 'ቀዩ ሰይጣን' - ደቡብ ኮሪያ ዕለተ እሁድ ሰኔ 07/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። በ 2026 የአለም ዋንጫ እስከ አሁን ከተመለከትናቸው ቡድኖች አሸናፊ ከሆኑት ውስጥ አንዷ ደቡብ ኮሪያ ነች። ደቡብ ኮሪያ ቼኪያን 2-1 በማሸነፍ አጀማመሯን ማሳመር ችላለች። ነገርግን ደቡብ ኮሪያ ጨዋታውን አሸነፈች ብቻ ተብሎ ማለፍ አግባብ አይደለም። ያስመለከተችን ውብ ጥራት ያለው እንቅስቃሴ እና አስደናቂ የቡድን ጎሎች ጭምር ነው። ኮሪያ እንደ ጃፓን ሁሉ ኳስ ላይ መሰረት ያደረገ ያማረ እግርኳሷ ብዙዎችን አፍ ያስከፈተ ነበር። የዛሬ ቆይታችን የኤሺያው 'ቀዩ ሰይጣን' ላይ ቆይታ እናደርጋለን። አለም ዋንጫው እንዴት አገኛችሁት? 👉 የሞሮኮ ወጣቶች ለብራዚል የራስ ምታት ነበሩ።ኢጎር ቲያጎ ብራዚል የማይመስል አጥቂ እያሉት ነው። 👉 ሀይቲ ብትሸነፍም ስኮትላንዶችን አስጨንቃ ነበር። 👉 አውስትራሊያ ሳትጠበቅ ተርኪን አሸንፋለች። 👉 4-1 የአሜሪካ መሻሻል ወይስ የ ፓሯጓይ መዳከም? ዛሬ 👉 ጃፓን ከ ኔዘርላንድ በነዚህ እና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ፃፉልን። #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 375 ብራይተን ያስፈረመው ናይጄሪያዊው ኔይማር! ዕለተ እሁድ ግንቦት 30/2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። ታላላቆቹ የአውሮፓ ክለቦች እይታ ውጪ በሆኑ ገበያዎች ላይ አይጠፉም ተሰጥኦ ፈልፍሎ ማደን የተካኑበት፤አግልብቶ መልሶ በመሸጥ እና ትርፋማ በመሆንም የተዋጣላቸው ናቸው። ክለባቸውም በሁለት እግሩ የቆመበት ታላቅ ሚስጢር ይኸው "የቢዝነስ ሞዴል"ነው። ጥሬ ተሰጥኦን ተቀብለው በጥቂት አመታት ውስጥ ወደ ውድ ኮከብነት ይቀይሩታል። ሳይጋፉ የገዙት ጥሬ ተሰጥኦ ትርምስ በበዛበት ጨረታ አዋደው ይሸጡታል። አሁንም እንደዛው ነው።ተረኛው "ናይጄሪያዊው ኔይማር" እየተባለ የሚገኘው ዛዶክ ዮሀና ነው። የ 18 አመቱ ባለ ተሰጥኦ የግላቸው ማድረጋቸው ተረጋግጧል። የዛሬ ቆይታችንም በዚሁ ናይጄሪያዊ ታዳጊ ላይ ቆይታ እናደርጋለን። ሀሙስ ምሽት የአለም ዋንጫው ይጀመራል።ግን ደግሞ በጉጉት ውስጥ ያለ አይመስልም። ድባቡ ቀዝቅዟል፣ግርማ መጎሶ ተነስቷል።ከወዲሁ ብዙ ነገሮች እየተደመጡ ይገኛሉ። ውድድሩ በምን አይነት ጉጉት እየጠበቃችሁት ነው? የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ 👉 ቤልጄም 5-0 ቱኒዚያ ቱኒዚያ ወደ ሀገራቸው ቀድመው ከሚመለሱ ውስጥ ተካታለች። 👉 ጀርመን፣እንግሊዝ፣ፓርቹጋል እና ብራዚል አሸንፈዋል። በነዚህ እና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ፃፉልን። #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 374 የሪያል ማድሪድ ፖለቲካ! ዕለተ አርብ ግንቦት 28 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። ከዓለም ዋንጫው ጅማሮ በፊት የእግር ኳስ አፍቃሪውን ቀልብ መስረቅ የቻለው ትልቁ ጉዳይ እሑድ የሚደረገው የሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነው። ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ የስልጣን ጊዜያቸውን ለማራዘም፣ ወጣቱ ኤነሪኬ ሪኬልሜ ደግሞ የአባቱን ህልም እውን ስለማድረግ እያለሙ ይወዳደራሉ። በሁለቱም በኩል እየተደረጉ ባሉ ቅስቀሳዎች የታላላቅ ተጫዋቾች ስም እየተጠራ ነው። ሪኬልሜ "ከተመረጥኩ ኤርሊንግ ሀላንድን ከሲቲ አስኮበልላለው" የሚል አነጋጋሪ መቀስቀሻን እየተጠቀመ ሲሆን ፔሬዝ ደግሞ ከተመረጥኩ የፊታችን ማክሰኞ የ150 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ጥያቄ ለአንድ ተጫዋች አቀርባለሁ እያሉ ነው። አመሻሹን ደግሞ ይህ ተጫዋች የባየርኑ ጥበበኛ ሚሸል ኦሊሴ ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ። ✅ የዝውውር ገበያው ቀስ በቀስ እየጋለ ነው። ኢራኦላን አሰልጣኝ ያደረገው ሊቨርፑል በርካታ ክፍተቶቹን ለመድፈን ሩጫ ላይ ነው። አርሰናል፣ሲቲ፣ዩናይትድ፣ቼልሲ፣ቶተንሐም፣ቪላ፣ ባርሳ፣ጁቬ፣ሚላን፣ኢንተር... ታላላቆቹ በሙሉ የክረምት ሩጫቸውን ተያይዘዋል። በነዚህ እና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ፃፉልን። #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 373 ኢኳዶሪያዊያኖቹ ዊሊያን ፓቾ እና ፒየር ሂንካፒ! ዕለተ እሁድ ግንቦት 23 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። የክለቦች ውድድር ቁንጮ የሆነው የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ በሀንጋሪ ቡዳፔስት በፑሽካሽ አሬና ስታድየም ተጠናቋል። ፔዤ በድጋሜ የአውሮፓ ሀያልነቱን ክብር ያስጠበቀበት ድል ተጎናፅፏል። መድፈኞቹ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፊ የሚሆኑበትን እድል ማግኘት አልቻሉም። በዚህ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ ፍፃሜ ሁለት ኢኳዶራዊያን በተቃራኒ ሆነው ተፋልመዋል። ከፓሪስ በመቀጠል አሸናፊዋ ኢኳዶር ነበረች። ዊልያን ፓቾ እና ፒየሮ ሂንካፒ በትናንቱ ጨዋታ ላይ ኢኳዶርን ባኮሩት ወርቃማ ልጆቿ ዙሪያ ቆይታ እናደርጋለን። እናንተስ የምሽቱ ጨዋታ እንዴት አያችሁት? 👉 የአርቴታ የጨዋታ አቀራረብ፣ ፣የተጨዋች ምርጫ እና ቅያሪ? 👉 የማጋሌሽ መለያ ምት ጉዳይ? 👉 ኤነሪኬ ለ 3ኛ ጊዜ የአውሮፓ ቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫ አንስቷል።ታዲያ በታሪክ ከሰፈሩት ከቁንጮ አሰልጣኞች ዝርዝር እንዲገባ አያደርገውም? በነዚህ እና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ፃፉልን። #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 372 ስንብት! ዕለተ አርብ ግንቦት 21 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። ሁሉም ታላላቅ የአውሮፓ የእግር ኳስ ሊጎች ከሞላ ጎደል ተጠናቀው ባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ ሻምፒዮንስ ሊግ ብቻ ቀርቷል። በነገው ዕለት ይህ ውድድር ፔዤ ከአርሰናል ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል። ይህንን ተከትሎም ጊዜው የዓለም ዋንጫ እና የዝውውር መስኮት ይሆናል። ሁለቱም አሁን የሚዲያ ትኩረቱን እየተረከቡት ይመስላል። የዓለም ዋንጫው ተሳታፊዎች ስብስባቸውን በሚያሳውቁበት ጊዜ በሚፈጠሩ ትኩረት ሳቢ ጉዳዮች ማነጋገሩን ሲቀጥል ዝውውር ደግሞ ሌላኛው ከፍተኛ ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ሆኗል። ክለቦች ክፍተታቸውን ለመሙላት ተጫዋች ፍለጋ ገበያ ይወጣሉ። የተሳካላቸው በጊዜ የቤት ስራቸውን መወጣት ሲጀምሩ አንዳንዶቹ ደግሞ ካልተሳኩ ድርድሮች በኋላ የራሳቸውን ውሳኔ እየወሰኑ ነው። ከእነዚህ መካከል የአምናው የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሊቨርፑል ተጠቃሽ ነው። ካለፈው አመት ጀምሮ አነጋጋሪ የነበረው የኢብራሂማ ኮናቴ ኮንትራት ጉዳይ በመጨረሻም ያለስምምነት ተጠናቋል። ኢቡም ቀያዮቹን ለመሰናበት ቀናትን ብቻ ይጠብቃል። ዛሬ የምናነሳው ጉዳይም ይህንኑ ነው። የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ነገ በቡዳፔስት ፍፃሜውን ያገኛል። 👉 ፔዤ ወይስ አርሰናል? 👉 የዓለም ዋንጫ በቀጣይ ሳምንት ይጀመራል። ምን ያህል እየጠበቃችሁት ነው? 👉 በዝውውር መስኮቱ የምትደግፉት ክለብ ምን አይነት ስራ እንዲሰራ ትፈልጋላችሁ ? በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን አድርሱን። #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 371 ዳኒ ካርቨሀል! ዕለተ እሁድ ግንቦት 16 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል። ከ 9 ወራት በላይ ሲካሄድ የቆየው የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ዛሬ አመሻሽ 12:00 ላይ በእኩል ሰአት በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል። አርሰናል ዋንጫውን የሚያነሳበት አንድ ቀሪ ወራጅ ቡድን የሚለይበት ለአውሮፓ የክለቦች ውድድር የሚሳተፉ ክለቦች የሚለዩበት ይሆናል። ከኛ ግን ዛሬ የተለያዩ አጫጭር ርዕሶች ጋር ቆይታ እናደርጋለን። 👉 የካፍ ቻምፕየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ 👉 ኸል ሲቲ ወደ ፕሪምየርሊግ መመለሱ 👉 የፕሪምየርሊግ ቡድኖች ገቢ 👉 ካርቨሀል ከ ማድሪድ ጋር መለያየቱ .. የእለቱ የፕሪምየርሊግ ጨዋታዎች ውስጥ 👉 ብራይተን ከ ማን ዩናይትድ ብሩኖ ሪከርዱን ይሰብር ይሆን? 👉 ቶተንሀም ከ ኤቨርተን ዴቪድ ሞይስ ዌስትሀም እንዲወርድ አልፈልግም ብለዋል።ቶተንሀምን በማሸነፍ የቀድሞ ክለባቸው እንዲቆይ ያደርጉ ይሆን። 👉 የውድድር አመቱ ኮከብ ተጨዋች ለብሩኖ ፈርናንዴዝ ተሰጥቷል።ምን ሀሳብ አላችሁ? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

  • #EAS 370 3 Lions 3 Big Omission! ዕለተ አርብ ግንቦት 14 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት "የኛ እና የናንተ" መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ይከታተሉ። አብዛኛዎቹ የሊግ ውድድሮች ሊጠናቀቁ አንድ ጨዋታ ብቻ የሚቀራቸው ሲሆን አሸናፊዎቹም ተለይተው ታውቀዋል። በሳምንቱ አጋማሽ አርሰናል፣አል ናስር እና ዛማሌክ የየሊጎቻቸው አሸናፊ መሆናቸው አረጋግጠዋል። በተለያየ አህጉር ላይ ያሉ እነዚህ ክለቦች የሚያመሳስላቸው የሊግ ዋንጫን ካገኙ አመታት የተቆጠሩ መሆኑ ወይንም በየሊጎቻቸው ላይ ለአመታት የበላይነት ተወስዶባቸው የነበረ በመሆኑ ዘንድሮ ቀምበሩን ሰብረው የድል ረሀባቸውን ያስታገሱበት በመሆኑ ነው። ለመሆኑ የውድድር አመቱን እንዴት አገኛችሁት?ምንስ ታዘባችሁ? ዛሬ የውድድር አመቱን መቋጫ በማስመልከት ሰፋ ያለ ጊዜ ለተከበራችሁ አድማጮቻችን እንሰጣለን። እኛ ለመግቢያ ያህል ግን በእንግሊዝ ብ/ቡድን ምርጫ ዙሪያ ጥቂት እንላለን። የአርሰናል ደጋፊዎች ደስታው እንዴት እያደረጋችሁ ነው?ይህ በጎ ስሜት ለቻምፕየንስ ሊጉ ፍፃሜ አስተዋፅኦ ይኖረው ይሆን? የ CR7 ወዳጆችስ? ሮናልዶ የመጀመሪያ የሳውዲ ዋንጫውን ሲያሳካ ምን ተሰማችሁ? ዩናይትድ ወደ ቻምፕየንስ ሊጉ መመለሱ ተጨዋቾችን ለማዘዋወር ቀላል አያደርግለትም?ለናንተ የቀዮቹ ደጋፊዎች አማካይ ላይ ቡድናችሁ ማንን ቢያስፈርም ትመርጣላችሁ? አጠቃላይ በውድድር አመቱ ዙሪያ በቀጥታ ስልክ ከናንተ ጋር ከ 3፡45 ጀምሮ ቆይታ እናደርጋለን። 👉 ማጓየር፣ሾው፣ትሬንት፣ፎደን፣ፓልመር፣ጊብስ ኋይት፣ኮልዊል፣ቶሞሪ.... በምርጫው የሉም።የማን መዘለል አስገረማችሁ? #EAS - የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት